es
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
3 613
Suscriptores
+1324 horas
+4187 días
+1 05630 días
Archivo de publicaciones
የአብይ አህመድ አገዛዝ ወንበር ጠባቂ ቡድን በመቄት ወረዳ ከፍላቂት ገረገራ ከተማ  በቅርብ ርቀት አግሪት ዙሪያ በሚገባ ተመታ...‼️ በአማራ ፋኖ ብራሔዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ 303ኛ ግዙፉ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር  81ኛ (ራስ-አንችም እና ውባንተ አባተ) ክፍለ ጦር ፣ የ106ኛ ኮር  22ኛ ክፍለ ጦር ቃኝ እንዲሁም በጋይንትና ዙሪያው ከሚቀሳቀሰው ራስ-ጋይንት ልዩ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር በተውጣጡ አሃዶች የአብይ አህመድ አገዛዝ ወንበር ጠባቂ ቡድን መጋቢት 02/2018 ዓ/ም ከጧቱ 12:00 እስከ ቀን 10:30 ሰዓት በፈጄ ውጊያ በመቄት ወረዳ ከፍላቂት ገረገራ ከተማ  በቅርብ ርቀት አግሪት ዙሪያ በሚገባ ተመታ...!! ራሱን የአገዛዙ ታማኝ ዘብ አድርጎ የሚቆጥረውና ጥምር ጦር ብሎ የሚጠራው ወንበዴ ቡድን ፍላቂትና ገረገራ ከተማ ከሚገኘው ዋሻው ወጥቶ በደመነፍስ የተቀሳቀሰው የጠላት ኃይል በርካታ ኃይሉ የተደመሰሰ ሲሆን የመቄት ወረዳ ሰላምና ደህንነት ኃላፊ ዋናው ባንዳ መካሺ ይመርን ጨምሮ ለመቁጠር የሚታክት ወንበዴ ኃይል ቆስሏል፣ በርካታው ተበትኗል።   ይኸ ግፈኛ ቡድን የክንደ ነበልባሎችን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው በንፁሃን ላይ የግፍ በትሩን በማሳረፍ አንድ መምህርን ጨምሮ በአምስት ሰዎች ላይ ነፃ እርምጃ በመወሰድ የአማራ ሕዝብ አጥፊ መሆኑን በአደባባይ ምስክርነቱን አረጋግጧል። ይኽ ብቻም ሳይሆን የአገሪት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ጤፍን ለመዘርፍ የሞከረ ሲሆን ተዝረክርኮ እግሬን አውጭ ብሎ አምልጧል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሷል! ትግላችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ     መጋቢት:-02/2018 ዓ.ም

አፋብን ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ፤ 303ኛ ኮር ከጎንደር ጠ/ግ/ዕ 206ኛ ኮር ተወርዋሪ ክ/ጦ ጋር ጥምረት በመፍጠር በርካታ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት በመደምሰስ ድል አስመዘገቡ:: መጋቢት 02/2018
አፋብን ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ፤ 303ኛ ኮር ከጎንደር ጠ/ግ/ዕ 206ኛ ኮር ተወርዋሪ ክ/ጦ ጋር ጥምረት በመፍጠር በርካታ የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት በመደምሰስ ድል አስመዘገቡ:: መጋቢት 02/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እስከ አመሻሽ 11:ዐዐ ሰዓት በዘለቀው እልክ አስጨራሽ ውጊያ በፋኖ ድል አድራጊነት ሲደመደም፤ የጥላት ጥምር ሰራዊት  ተደምስሷል። በ106ኛ ኮር(የቀድሞው የደጋው መብረቅ ኮር)  22ኛ ክፍለ ጦር  ብቻ  በመቄት  ወረዳ አግሪት ላይ   የጥላት ብልፅግና ሰራዊት ከ35 በላይ የተደመሰሰ ሲሆን ሀያ አምስት (25) በላይ ከባድ ቁስለኛ ሆነዋል። ቀሪዎቹን 19ኙን የጥላት የተደመሰሱ አስከሬኑን ሳያነሳ  ጥላት ፈርጥጧል። በ22ኛ ክፍለ ጦር ግምባር ብቻ የጥላት ሰራዊትና መሳሪያ በገፍ ተማርኳል።               ✅11 ክላሽኮ               ✅ እስከ 1000 የሚደርስ የክላሽ ተተኳሽ               ✅ ከ500 በላይ የብሬን ተተኳሽ                         ✅ 15 ቦምብ እና 7 ትጥቅ ተማርኳል። የአማራን ህዝብ ከመጨፍጨፍ ባሻገር አዝመራውን ለጦርነት ዝግጅት እየዘረፈው መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ እለትም የማህበራትን ንብረት ለመሰብሰብ የመጣ ጠላት ላይ 106ኛ ኮር 22ኛ ክ/ጦር ሠብረቃዊ ጥቃት ፈፅሟል። የአማራን ህዝብ ለመጨፍጨፍ ስጋና ስጋት ተቀልቦ የመጣው የብርሀኑ ጁላ ሰራዊት የአሞራ ሲሳይ እየሆነ በአማራ ምድር በየቀኑ እየተደመሰሰ ይገኛል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር መጋቢት 2/2018 ዓ.ም

74ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድራቸው እናርጅ እናውጋ ወረዳ ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል ‼️ ሶማ ሻለቃ የአራራ እና ጎሮ ገደል ነዋሪወች ጋር የኮር፣ የክፍለ ጦር እና የጊዜያዊ መንግስት አመራሮች
+6
74ኛ ክ/ጦር በሚያስተዳድራቸው እናርጅ እናውጋ ወረዳ ህዝባዊ ውይይቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል ‼️ ሶማ ሻለቃ የአራራ እና ጎሮ ገደል ነዋሪወች ጋር የኮር፣ የክፍለ ጦር እና የጊዜያዊ መንግስት አመራሮች በተገኙበት ጥልቅ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሂደዋል። ➻➻➻➻➻➻➻◊◊➻➻➻➻➻➻➻ መጋቢት 02/2018 ዓ.ም በውይይቱ መድረኩ፦ ➽በፋኖ እና በህዝቡ መካከል ያሉ መስተጋብሮችን በተመለከተ ➽የድርጅቱ አሁናዊ ቁመና በተመለከተ ➽የመልካም አስተዳደርን በተመለከተ ህዝባችን ከተደቀነበት የህልውና ችግር ለመውጣት እና አገዛዙ በህዝባችን ላይ እያካሄደ ያለውን ዘር ተኮር ጭፍጨፋ ግንዛቤ በመስጠት የአማራን ህዝብ የትጥቅ ትግል በአጭር ለመቋጨት በመረጃ በሎጅስቲክ በሁሉም መንገዶች ከጎናችን እንደሚሆኑ በመግባባት የኮር እና የክፍለ ጦሩ አመራር እና የወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች ለተነሱ ጥያቄወች በቂ ማብራሪያ እና ግንዛቤ በመፍጠር የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥተዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ብልጽግና ብርክ ብርክ ብሎታል፤ ዛሬም ሁለት የሠራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን ይዘው ፋኖን ተቀላቀሉ ༻༺༻༺༻༺༻༺ [ዐፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ] መጋቢት 02/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የገዥው የብልጽግና የጦር መዋቅር በየዕለቱ መናዱን ቀጥሏል። በደጋ ዳሞት ወረዳ ወይን ውሃ መሸጎ ከነበረው የዐቢይ ሠራዊት መካከል ሁለት የቃኝና መሐንዲስ አባላት ወደ ፋኖን ተቀላቅለዋል። ከ6ኛ እዝ፣ 602ኛ ኮር፣ 25ኛ ክፍለ ጦር ቃኝና ማሐንዲስ ሻለቃ ✔ አብዲ ክንዱ እና ማርቆስ ተስፋየ የተባሉ ንቁ ወታደሮች ሁለት ጥቁር ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከ440 (እያንዳንዳቸው 220) ጥይቶች ጋር በመያዝ ወደ ዐፋብን 102ኛ ኮር፣ 33ኛ ክፍለ ጦር ገብተዋል። የወታደሮች እርምጃ በገዥው ሠራዊት ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የሞራል መውደቅና የመበታተን አዝማሚያ በግልጽ ያሳያል። በተለይም በቴክኒክና በስለላ (ቃኝና ማሐንዲስ) ዘርፍ የተሰማሩ አባላት ትጥቃቸውን ይዘው መውጣታቸው፣ በሠራዊቱ ውስጥ ያለው "አላገለግልም" ባይነት ወደ ተግባር እየተቀየረ መሆኑን ያመለክታል።

ሻለቃ ሙላት ከአሁን በፊት በሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጋዚ ኮማንዶ ክፈለ ጦር ወጋገን ሻለቃ ከአባል እስከ አመራ ድረስ ያገለገለ አቅም፣ ልምድ እና ዕወቀት የተላበሰ በሁርሶ መሰረታዊ ውትድርና ማሰል
+3
ሻለቃ ሙላት ከአሁን በፊት በሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጋዚ ኮማንዶ ክፈለ ጦር ወጋገን ሻለቃ ከአባል እስከ አመራ ድረስ ያገለገለ አቅም፣ ልምድ እና ዕወቀት የተላበሰ በሁርሶ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ እና የመኮንኖች ማሰልጠኛ ማዕከል ላይ በአስተማሪነት ያገለገለ ወታደራዊ ጥበብን የቀሰመ በወታደራዊ ሳይንስና አመራር በጦር ትምህረት ቤት የመጀመርያ ድግሪውን በሰው ሃብት አስተዳደር ሀለተኛ ድግሪውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቀብሏል። ሻለቃ ሙላት እና መሰሎቹ ለአፋብን የትግል ጉዞ ትልቅ ድርሻ አላቸው ውትድርና በውቀት በአቅም በልምድ ሲመራ ውጤታማ ይሆናል!

አፋብን🙌 በስቦ መምታት ስቦ ማስከዳት እጅግ በጣም ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው።የአገዛዙ ሰራዊት በቡድን በመሆን ወደ ፋኖ እየተቀላቀለ ነው‼️ ፍኖተ አማራ ከግባር መረጃዎች እያደረስች ትገኛለች ይወዳጁን 👇

ፈረሰ ፈረሰ ፈረሰ... ጎንደር ዙሪያ መገጭ ግድብ ዙሪያ የነበሩ በርካታ አድማ በትኖች አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ በጌምድር ክፍለ ጦር ፋሲለደስ ብርጌድን ተቀላቅለዋል። መጋቢት 02/2018 ዓ
ፈረሰ ፈረሰ ፈረሰ... ጎንደር ዙሪያ መገጭ ግድብ ዙሪያ የነበሩ በርካታ አድማ በትኖች አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ በጌምድር ክፍለ ጦር ፋሲለደስ ብርጌድን  ተቀላቅለዋል። መጋቢት 02/2018 ዓ.ም

ሰበር ሰሜን አቸፈር ! በወረዳው የሚገኘው ሚሊሻ በሙሉ በመከላከያ ትጥቅ ተቀምቶ ተጠረነፈበት ። ምክንያት አመኔታ አጠነባችኋል በማለት ። የፋኖ መልዕክት ደግም ኑ ወደ ኑሯችሁ ተመለሱ ነው ። Girum Misalie ግሩም ምሳሌ

የአገዛዙ ሠራዊት በይፋ እየፈረሰ ነው  ‼️ መጋቢት 02/2018 ዓ.ም በዛሬው ዕለት አገዛዙን የከዱ ሁለት የአድማ ብተና አባላት ይሄን ስረዓት በቃኝ በማለት አፋብን  ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደፂዎን ኮር ራንቦ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል። ከሸዋሮቢት ከተማ በመነሳት ወደ ፋኖ ነፃ ቀጠና በሰላም የገቡ ሲሆን በፋኖ አባላትም አቀባበል ተደርጎላቸዋል።አገዛዙ ግልገል ፋኖ በማለት በአይነ ቁራኛ የሚከታተላቸው የአድማ ብተና አባላት ፋኖን ለመቀላቀል ይሄ ትክክለኛው ጊዜ ነው በማለት ፋኖን እየተቀላቀሉ ነው።አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በጥምር ጦሩ ውስጥ እርስ በርስ መጠራጠሩ እየከረረ ሲሆን የአድማ ብተና እና ሚሊሻ አባላትም ምርጫቸውን ፋኖ በማድረግ እየተቀላቀሉ ነው። የአገዛዙ ሠራዊት በፋኖ ሀይል አንድ መሆን እና እየደረሰበት ባለው በትር ከፍተኛ ሽብር እና ድንጋጤ ውስጥ ገብቷል።ይህ አገዛዝ ያበቃለት መሆኑን የተረዱ የሠራዊቱ አባላት አጋጣሚውን ያገኙ ሁሉ እየተሰወሩ ወደ ፋኖ እየገቡ ነው።ፋኖን የተቀላቀሉ ጥምር ጦሩ አባላትም ፋኖን ለመቀላቀል ግዜው አሁን ነው በማለት ለቀሪ ጓዶቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኮማንዶው ይችላል በማለት ጀምሩ💪💪💪 4ኛ ደጃዝማች ኮር በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አደረገ አፋብን 4ኛ ደጃዝማች ኮር ከምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ጋብላ ቀበሌ ህዝብ ጋር ትናን
ኮማንዶው ይችላል በማለት ጀምሩ💪💪💪 4ኛ ደጃዝማች ኮር በተቆጣጠራቸው ቀጠናዎች ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አደረገ አፋብን 4ኛ ደጃዝማች ኮር ከምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ጋብላ ቀበሌ ህዝብ ጋር ትናንት የካቲት 30/2018 ዓ.ም  ሰፊ ውይይት አደረገ:: ስብሰባውን በአስተባባሪነት የመራው የአፋብን ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ ህላፊ አርበኛ ሳሙኤል ባለእድል ሲሆን በውይይቱ የፋኖ አላማና ራዕይ ,የፋኖ አሁናዊ ቁምና እንዲሁም የፋኖ የወደፊት አቅጣጫ በአጀንዳነት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው:: ስብስባውን የታደሙት የጋብላ ቀበሌ ማህበረሰቦች የፋኖን አሁናዊ ቁመና እና የህዝብ አስትዳደር ስነ አርዓት በመገንዘብ የተስማቸውን ደስታ ገልጸዋል:: በመጨረሻም ህዝቡ እራሱን በራሱ በነጻነት እንዲያስተዳድር ከራሱ ማህበረሰብ ዘጠኝ አባላትን የያዘ  የሀገር ሽማግሌዎች ኮሚቴ በማቋቁም ስብሰባው ተጠናቋል:: #መረጃውን ያደረሰን የኮሩ ህዝብ ግንኙንት ሀላፊ አርበኛ ባንዴራው ግርማይ በተባበረ ክንዳችን የህዝባችን ህልውና እናስጠብቃለን! ድል ለአማራ ፋኖ! ክብር ለሰማዕታት! መጋቢት 02 /2018 ዓ.ም

‎ይሄ የጎንደር ልጅ፤ የአማራ ደም ያለው..! ‎ይሄ የጎጃም ልጅ፤ የአማራ ደም ያለው..! ‎ይሄ የወሎ ልጅ፤ የአማራ ደም ያለው..! ‎ይሄ የሸዋ ልጅ፤ የአማራ ደም ያለው..! ‎ክፉ አመል፤ ክፉ አመ
‎ይሄ የጎንደር ልጅ፤ የአማራ ደም ያለው..! ‎ይሄ የጎጃም ልጅ፤ የአማራ ደም ያለው..! ‎ይሄ የወሎ ልጅ፤ የአማራ ደም ያለው..! ‎ይሄ የሸዋ ልጅ፤ የአማራ ደም ያለው..! ‎ክፉ አመል፤ ክፉ አመል፤ ክፉ አመል አለበት፣ ‎ነፃነትን እንጅ፤ የማይወድ ጭቆናን፤ የማይወድ ባርነት። ‎አማራነት ይለምልም🇨🇬

ስርዓቱን እየናድነዉ ነዉ!! ‎ ‎ በሰሜን አቸፈር ወረዳ ለስርዓቱ በሚሊሻነት ሲያገለግል የነበረዉ ሚሊሻ ፋኖን ተቀላቀለ። ‎ #ምስጋነዉ_አሰረስ_ሁለት_እገርክላሽ በመያዝ በዛሬዉ ዕለት የአፋብን ምዕራ
+1
ስርዓቱን እየናድነዉ ነዉ!! ‎ ‎ በሰሜን አቸፈር ወረዳ ለስርዓቱ በሚሊሻነት ሲያገለግል የነበረዉ ሚሊሻ ፋኖን ተቀላቀለ። ‎ #ምስጋነዉ_አሰረስ_ሁለት_እገርክላሽ በመያዝ በዛሬዉ ዕለት የአፋብን ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴወድሮስ ዕዝ 105ኮር 55ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ሻለቃ ተቀላቅሏል።

አፋብን ያወጣውን የምህረት አዋጅ በመቀበል ስድስት የደላንታ ወረዳ የሚሊሻ አባላት ሰባት ክላሽ በመያዝ ፋኖን ተቀላቀሉ! ጥልቅ ተሃድሶ እና መልሶ ማደራጀት ካደረገ ማግስት በርካታ አመርቂ ስራዎችን እየሰራ የሚገኘው ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል። በዚህም ድርጅታችን አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ባወረደው የምህረት አዋጅ መሰረት የአገዛዙ የፀጥታ መዋቅር እያፈረሰ ይገኛል። በዚህም ከዚህ በላይ "ከአገዛዙ ጎን ተሰልፈን ሕዝባችንን አናሸማቅቅም ፤ ለሕዝባችንም ተጨማሪ እዳ አንሆንም!" ያሉ የደላንታ ወረዳ የሚኒሻ አባላት 106ኛ ኮርን ተቀላቅለዋል። አገዛዙ አቅም የሌለው እና በጭፍን ሕዝብን የሚጨፈጭፍ የአማራ ሕዝብን አምርሮ የሚጠላ እንዲሁም የሚጠላትን ሀገር የሚያስተዳድር ፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ አገዛዝ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል። በቁጥር ስድስት (6) አባላት 106ኛ ኮርን የተቀላቀሉ ሲሆን ሰባት (7) የነፍስ-ወከፍ መሳሪያ የያዙ ናቸው። ነፍሰ በላውን ፀረ አማራ አገዛዝ በቃን በማለት 106ኛ ኮርን የተቀላቀሉት የቀድሞ የሚኒሻ አባላት የተደረገላቸውን መልካም አቀባበልና ምህረት በማስመልከት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ለአገዛዙ እድሜያቸው እና ማንነታቸውን እየገቡሩ ላሉ የአገዛዙ ሀይሎች የምህረት አዋጁን እንዲቀበሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። "አገዛዙ በቀቢፀ ተስፋ የሚዘወር ለጊዜያዊ መጠቀሚያ አድርጎ የሚወረውራችሁ መሆኑን አውቃችሁ በምንም ጥቅማጥቅም ሳትታለሉ አማራነታችሁን አስቀድሙ" ሲሉ ፀፀት የተሞላበት መልዕክት ጭምር አስተላልፈዋል። በመጨረሻም አፋብን ም/አ/ቀ ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር ለአገዛዙ የፀጥታ አባላት ከወትሮውም ጊዜ በላይ እንደ አማራ የምንሰባሰብበት እና የምንተባበርበት ሰዓት ላይ ስንሆን አንድ ሆነን የምንታገልበት ወቅት አሁን ጭምር ስለሆነ ከወገናችሁና ከመጠሪያችሁ ፋኖነት ጎን እንድትሰለፉ መልዕክት ጭምር እናስተላልፋለን። በደጋማው ቀጠና የሚንቀሳቀሰው የጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ አካል የሆኘው 106ኛ ኮር የድርጅት መርህን በጠበቀ መልኩ እና የአማራነትን እሴት፣ ወግ እና ባህል ባከበረ መልኩ ፍፁም ወንድማዊ ምህረት እና ይቅርታ የምናደርግ መሆኑን በሰፊው የአማራ ሕዝብ ስም እንገልፃለን። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር መጋቢት 2/2018 ዓ.ም

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ጊዜዊ መንግስት ለወረዳ አስተዳደሮች ስልጠና ሰጠ ። መጋቢት 02/2018ዓም ጊዜያዊ መንግስቱ በቀን 30/6/2018ዓ ም ጀምሮ የቋሪት ፣የጎንጅ ቆለላ ፣የይልማና ዴ
+1
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ጊዜዊ መንግስት ለወረዳ አስተዳደሮች ስልጠና ሰጠ ። መጋቢት 02/2018ዓም ጊዜያዊ መንግስቱ በቀን 30/6/2018ዓ ም  ጀምሮ የቋሪት ፣የጎንጅ ቆለላ ፣የይልማና ዴንሳ ፣የሜጫ ወረዳ መንግስታዊ አስተዳደሮች እና  ህግና ስነስርዓቶች ፣እንዲሁም ፋይናንስ መምሪያወች ፣ በተገኙበት ለተከታታይ ሁለት ቀናት ስልጠናውን መስጠት ተችሏል ። በስልጠናውም ➡️አጭር  የአመራር ሥልጠና ➡️የፍትህ አሰጣጥ ሂደትን ➡️የፋይናንስ አሠራር ሂደትን ➡️የህዝብ አስተዳደር ሂደትን እና የመሳሰሉትን ስልጠና ሰጥቷል ። ብቁ የህዝብ አገልጋይ እና ሀገር ተረካቢ አመራር መፍጠርን ዓላማው ያደረገው ይህ ስልጠና በኮሩ ጊዜያዊ መንስት ሀላፊ አርበኛ ይፍረድ ውዴ እና የጊዜዊ መንግስቱ አመራሮች ተሰጠቷል ። ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

በምርጫ አስፈጻሚነት የትኛዉም የአማራ ክልል ላይ የሚሳተፍ አካል እርምጃ ይዎሰድበታል አለቅ 4። አገዛዙ በአማራ ክልል አስመራጭ በማጣቱ የዩኒቨርሲትይ መምህራንን እባካችሁ የሚል በት/ም ሚኒሲቴ በኩል
+5
በምርጫ አስፈጻሚነት የትኛዉም የአማራ ክልል ላይ የሚሳተፍ አካል እርምጃ ይዎሰድበታል  አለቅ 4። አገዛዙ በአማራ ክልል አስመራጭ በማጣቱ የዩኒቨርሲትይ መምህራንን እባካችሁ የሚል በት/ም ሚኒሲቴ በኩል እየተማጸ ነ ነዉ ።  በጠቅላላ ደግሞ አማራ ክልል ቢቻ ነዉ፣ ይህ የሚያሳየው ምንያህል አማራ ክልል ላይ በራሱ መረጃ እንኳ ከግዛቱ ውጭ እንደሆን ያመነበት ነው።

ጀግናው እንዳለ እንየው የማበረታቻ እና የጀግነት ዕውቅና ሽልማት ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ተበረከተለት!! =========================== በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ ከንቲባ እና ሰላምና
+3
ጀግናው እንዳለ እንየው የማበረታቻ እና የጀግነት ዕውቅና ሽልማት ከአርበኛ ዘመነ ካሴ ተበረከተለት!! =========================== በምዕራብ ጎጃም ዞን የጅጋ ከተማ ከንቲባ እና ሰላምና ደህንነት አመራር በመሆን ለአገዛዙ በሆዳቸው በመገዛት የአማራን ህዝብ ሲያስጨፈጭፉ፣ሴቶችን ሲደፍሩ፣ባለሀብቱን ሲዘርፉ፣ ወጣቶችን ከተለያዬ ቦታ በማፈን ወደ መከላከያ ማሰልጠኛ በግዳጅ ሲልኩ የነበሩ አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ ፋኖን የተቀላቀለው #ጀግና እንዳለ እንየው የጀግና አቀባበልና የሽልማት ፕሮግራም ተደረገለት።          የአፋብን ሊቀመንበርና የቴዎድሮስ ዕዝ ሰብሳቢ ከአርበኛ ዘመነ ካሴ  የጀግና ዕውቅና ሰርተፊኬት እና 50,000(ሃምሳ ሽህ) ብር፣ ከቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 50,000(ሃምሳ ሽህ) ብር፣ ከቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ሁለት እግር ክላሽ የማበረታቻ ሽልማት የ109ኛ ኮር እና የ77ኛ ክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት ተበርክቶለታል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ መጋቢት 01/2018 ዓ.ም