ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 285
Suscriptores
+3924 horas
+3057 días
+69830 días
Archivo de publicaciones
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ በመፈፀምና በምዕራብ ወሎ ግንባር አደገኛ የተባለውን የ11ኛ ዕዝ ምሽግ በመስበር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::
የምዕራብ ወሎዋ መካነሰላም ከተማ ውስጥ መቀመጫውን አድርጎ ግራ ቀኝ ያሉ ወረዳወችን በመውረር ንፁሀንን ሲገድል እና ንብረት ሲያወድም የምናውቀው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት 4 ምሽጎች ሌሊቱን ተሰብረዋል። በመካነሰላም ግንባር ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ሌሊቱን በፋሽስቱ አብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂዎች ላይ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ጥቃት ሰንዝሮ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል::
በቅርቡ ከተለያዩ ዕዞች ተቃርሞ 11ኛ ዕዝ በሚል ስያሜ የተደራጀው የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት በወገን ኃይል ላይ በሞርተር የታገዘ ተኩስ ቢከፍትም ሞት አይፈሬዎቹ የአማራ ልጆች በፈፀሙት የጦር ሜዳ ጀብዱ ጠላት ሱባ ሜዳ፣ ክሬቸር፣ ሶዬ እና አሜጃ የተባሉ ቦታወች ላይ ያዘጋጃቸውን ምሽጎች ለቆ እንድፈረጥጥ የተደረገ ሲሆን የተደመሰሱ የጠላት ኃይል አባላት ስለመኖራቸውም ነው ከስፍራው የደረሰን መረጃ የሚያመላክተው::
የብልፅግና መከላከያ የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር እግረኛ ሰራዊት በሜካናይዝድ ምድብተኞች ታግዞ የተሰለፈ ቢሆንም የውጊያ የበላይነት በ29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ተወስዶበት በርካታ አባላቱን የተነጠቀ ሲሆን ቁስለኛም እንደታቀፈ ተረጋግጧል:: በተለምዶ ሶዬ ተብላ በምትጠራው አካባቢ እና ቆርኬ ሚካኤል አጠገብ የጠላት አስከሬን መንገድ ላይ ወድቆ እንደነበር የአይን እማኞች ገልፀዋል::
አንድ ጋንታ የሚሆን የጠላት ኃይል መመታቱንም ነው ለማረጋገጥ የቻልነው:: በተለይ በሶዬ በኩል ለማለፍ በማሰብ የተኩስ ጫና ለመፍጠር የሞከሩ የጠላት ኃይል አባላት ከተወሰኑት ውጭ በፋኖ ጥይት እንደተመቱ የሚያሳይ መረጃ ደርሶናል:: የ29ኛ ክፍለ ጦር ፋኖወች የጠላትን ምሽግ በመስበር ወደ ከተማይቱ የገቡ ሲሆን ጠላት በበኩሉ ካምፑን ጭምር ለቆ ወደ ከተማይቱ ፈርጥጧል::
የ29ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ ስንደው ገዜ እና ምክትሉ አርበኛ ሆነለት ገዜ እንድሁም የክፍለ ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ መብሬ ጫብሲ በጋራ በመሆን በመሩት ኦፕሬሽን የጠላት አከርካሪ ክፉኛ ተሰብሯል ሲል የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለዕዙ በላከው የአውደ ውጊያ ሪፓርት ገልጿል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም
ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 22ኛ ክፍለጦር ከ11ኛ ክፍለጦር ጋር ጥምረት በመፍጠር በጠላት ከፍተኛ ሰባዊ እና ቁሳዊ ክሳራ ማድረስ ችሏል ።
********
መጋቢት 26/2018ዓ.ም
በትናንትናው ዕለት በቀን 25/07/2018ዓ.ም መነሻውን መራዊ መሸንቲና ጨንታ ያደረገው ወራ*ሪው የብልፅግና ሰራዊት በሌሊት ተንቀሳቅሶ አነጋግ አስራ ሁለት (12:00 )ሰዓት ሜጫ ኤፌሳ ሀሙሲት ና አማሪት እንዲሁም ባህርዳር ዙሪያ ድልሽት ኔቶርክ አጥፍቶ በመግባት የክፍለ ጦር፣የኮርና የድርጅት አመራሮች ለማፈን ሙከራ ያዱረገ ቢሆንም አመራሩ ከበባውን በሚገርም ወኔና ጀግንነት ያለምንም መስዋዕትነት ሰብሮ ከወጣ በሗላ ሊከብ የመጣን የጠላት ሀይል ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ11ኛ ክፍለ ጦር እና የ22ኛ ክፍለ ጦር ተርቮ ሻለቆችን በማቀናጀት ለማፈን እየተግተለተለ የመጣን የብልፅግና ሰራዊት መልሶ ቀለበት ውስጥ በማስገባት ጠላትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት ተችሏል ።
ከተለያየ አቅጣጫ የመጣውን አረመኒ ሰራዊት ከድልሽት እና ኤፌሳ መሀል የምትገኝ አቨርጨቅ ጫፍ ላይ
ከቀኑ 11:00ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00ሰዓት በተደረገ አውደ ውጊያ ከጠላት ጋር በጀግንነት በመዋደቅ ጠላትን አፈር በማስጋጥ
1. አንድ ብሬን ሁለት አስቃጥላ ጥይት እንደያዘ
2.አንድ ስናይፐር
3. 11 ክላሽ ኮፍ
4. 01አይኮም ሬዲዮ
5.ከ20 በለይ ሙት፣ ብዛት ያለው ቁስለኛና በእጅ የተያዙ ምርኮኞችን ጨምሮ መማረክ ሲቻል ጠላትም የተደረገበትን ከበባና የተፈፀመበትን መብረቃዊ ጥቃት መቋቋም አቅቶት በመንፈራገጥ ላይ እያለ ተጨማሪ ሀይል ከመራዊና ከመሸንቲ በሁለት አቅጣጫ በማስመጣት የተረፈ ሰራዊቱንና ቁስለኛውን በመያዝ አስከሬኑን ሳያነሳ እያዝረከረከ የሽንፈት ካባውን ተከናንቦ ወደ መጣበት ተመልሷል።
ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ! አዲስ ተስፋ!አዲስ አስተሳሰብ!
ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት!

እነ ሞት አይፈሬ ከወሎ ቤተ አማራ ሰማይ ስር✊
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ዘመቻ መሪ፣ የ1ኛ ሻለቃ አመራሮች እና የተወሰኑ አባላት እንድሁም የክፍለ ጦሩ ቃኝ የሆኑ ጥቂት ፋኖወች ናቸው የሚል ማብራሪያ ነው የደረሰኝ::
ከዚህ ቀደም ኢንጅነር ደሳለኝ አሰፋ ክፍለ ጦር ይባል የነበረው አደረጃጀት የስያሜ ለውጥ ተደርጎለት 29ኛ ክፍለ ጦር ተብሏል የሚል መረጃም ነው ደርሶኛል::: 29ኛ ተብሎ ሊሰየም የቻለው ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የቀጠናው ፋኖወች መካነሰላም ከተማን ከጠላት ነፃ ማውጣትና ለረጅም ጊዜ ማስተዳደር ችለው ስለነበር ያን ታሪካዊ የድል ቀን ለማስታወስ ነው ተብሏል::
ጀንበር መለስ ሲል ይመጣሉ ማታ፣
አፈ ሾጤ ጥይት አቅመው በካርታ፤
የተባለላቸው ሞት አይፈሬዎቹ የመካነሰላም አናብስት አዳራቸውን የጠላትን አከርካሪ ሰብረዋል:: ከክፍለ ጦሩ ሻለቃዎች እና ቃኝ የተውጣጣ የተወሰነ ኃይል ብቻ ወደ ከተማ አቅንቶ ትናንት ለዛሬ ሌሊት የፈፀመው ጀብዱ ስለመኖሩም ማረጋገጫ ደርሶኛል:: በአርበኛ ስንዴው ገዜ መሪነት ታሪክ ተሰርቶ አድሯል::
እርጥቡን ደረቁን ትበላለች ላም!!
የጎበዞች ሀገር መካነሰላም!!
ሲባል እየሰማን አድገን ነበር ትርጉሙ አሁን በደንብ ገብቶናል::
ጀግናማ ይወለድ እንጂ ህእ!!
ድል ለአማራ ልጅ::
እናሸንፋለን!!
አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ጀግኖቻችን በድል ተንበሻብሸው አምሽተዋል።
ቀን 26/7/2018ዓ/ም
ብልፅግና ሀገር ሰላም እያለ የምርጫ ካርድ በግዳጅ ህዝቡን ለማስወጣት በስልጣን ጠባቂው ታጅብ ሲንቀሳቀስ አይበገረወቹ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል።
በቀን 25/7/2018ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው እዝ አርበኛ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር አይበገሬዎቹ ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ ክ/ጦር አዲት ግራር ሻለቃና ነበልባሎቹ በረራ ክፍለ ጦር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መንዝና ግሼ አውራጃ መንዝ ጌራ ወረዳ ጓሳ ላይ የብልፅግናው ሆድ አደር ሰራዊት መሽጎ በነበረበት አማራ ጠል ሰራዊት ላይ በወሰዱት የማጥቃት ኦብሬሽን አናብስቶቹ ታላቅ ድልን ተቀዳጅተዋል።
አይበገሬወቹ የአርበኛ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር አናብስቶች ከሁለቱም ክ/ጦር የተውጣጡ ሻለቆች በመሆን አስገራሚ ማጥቃት በጠላት ላይ አድርገው የጠላትን ሁለት ጠንካራ ምሽጎች ተደምስሰዋል።
አውደውጊያው ከተጀመረበት ጊዜና ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት የአናብስቶቹ ክንድ እንደ እሳት እረመጥ የፈጀው የጠላት ሀይል በአራት መኪና ሙትና ቁስለኛውን ወደ መሀል ሜዳ ከተማ አስገብቷል።
የጠላት ቁስለኞች ሀኪም ቤት ቢገቡም አራት አድማ ብተናና ሁለት ሚሊሻ በህክምና ላይ እዳሉ መሞታቸውን የውስጥ መረጃዎቻችን አድርሰውናል።
አጠቃላይ 26 የስርዓቱ አሽከሮች ሲደመሰሱ ከ15 በላይ የሚሆኑ የአማራ ህዝብ ወረርሽኞች ደግሞ ከባድና ቀላል ቁስለኛ ሆነው በመሀል ሜዳ ሆስፒታል እየማቀቁ ይገኛሉ።
በአጠቃላይ በነበረው አውደ ውጊያ ጠላት ከፍተኛ የሰው ሃይልና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል።እንዲሁም ከፍተኛ የአድማ ብተናና የሚሊሻ አመራሮች ስማቸው ለጊዜው በውል ያልታወቀ ወደ ገሀነብ መሸኘታቸው ታውቋል።
አናብስቶቹም ግዳጃቸውን በሚገባ በማሳካት አጠቃላይ በወገን የድል የበላይነት በጠላት የተለመደ ሽንፈት ተጠናቋል።
በሌላ ዜና አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ግዙፉ አስቴ ጎማ ተራራ ክፍለ ጦር የውሸት ፕሮፓጋንዳ ይዞ የመጣውን የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ወራሪ ሃይል ግብዓተ መሬቱ እየተፈፀመለት ይገኛል።
ብልፅግና በውሸት ማጭበርበሬያ ምርጫ አካሂዳለሁ በማለት በርካታ የሽኔ ታጣቂና የአማራ ሆድ አደር ባንዳዎችን ከየቦታው ሰብስቦ ከስልጣን አስጠባቂው ሰራዊት ጋር በጥምረት ካሰማራ ዛሬ 7ተኛ ቀኑን እያስቆጠር ይገኛል።
በቀን 25/7/2018 ዓ/ም ከኦሮሚያ ልዩ ዞን ከሸኔ የተሰባሰበና የ102ተኛ ልዩ ዘመቻ አየር ወለድ ኮማንዶ እደለመደው በሴራር ጉር ቀበሌ ንፁሃንን በግፍ እየረሸኑ ጅብ ለማስበላት ሲንቀሳቀስ በጀግኖቹ አይበገር ሻለቃ ከፍተኛ ጉዳት አስተናግዶ ተዋርዶ ተመልሷል።
ከግሼ እራቤል ወደ አንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ግሾጌና ሸበቶ ቀበሌ ሲንቀሳቀስ የነበረው ወራሪ ሃይል ከጦርመሳያ ከተማ ወደ አስቴ ጎማ ተራራ ወጫቃ ምሽግ ከ40 በላይ የብልፅግና ሰራዊት ጭኖ ሲጎዝ የነበረው አንድ አይሱዙ FSR መኪና ከከተማው መውጫ ላይ ምሽት 12:25 አካባቢ ደፈጣ በመጣል ሙሉ በሙሉ ከነሰራዊቱ በክደ ነበልባሎቹ አያሌው መክት ሻለቃ ቃኘዎች በጨበጣና በአርቢጅ ላይመለሱ እስከወዳኛው ግብአተ መሬታቸው ተፈፅሟል።
የፋኖንን ብትር መቋቋም ያቃተው አማራ ጠል የብልፅግና ሰራዊት ሃገር ሰላም ብሎ ከስራ ወደ ቤቱ በሚሄደው ንፁሃን የ26 አመት ወጣት አሳምነው ደስታ የተባለ የቀን ሰራተኛ በአሰቃቂ ግፍ ሁኔታ እረሽነውታል።
መረጃውን የክፍለ ጦር ህዝብ ግንነቶች አድርሰውናል።
፦ክብር ለትግሉ ሰማዕታት !!
፦ድል ለአማራ ህዝብ!!
፦ድል ለአፋብን!!
፦አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን
ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ በመፈፀምና በምዕራብ ወሎ ግንባር አደገኛ የተባለውን የ11ኛ ዕዝ ምሽግ በመስበር ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::
የምዕራብ ወሎዋ መካነሰላም ከተማ ውስጥ መቀመጫውን አድርጎ ግራ ቀኝ ያሉ ወረዳወችን በመውረር ንፁሀንን ሲገድል እና ንብረት ሲያወድም የምናውቀው የፋሽስቱ አብይ አህመድ ሰራዊት 4 ምሽጎች ሌሊቱን ተሰብረዋል። በመካነሰላም ግንባር ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ሌሊቱን በፋሽስቱ አብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂዎች ላይ የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር 29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ጥቃት ሰንዝሮ አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል::
በቅርቡ ከተለያዩ ዕዞች ተቃርሞ 11ኛ ዕዝ በሚል ስያሜ የተደራጀው የፋሽስቱ አብይ መከላከያ ሰራዊት በወገን ኃይል ላይ በሞርተር የታገዘ ተኩስ ቢከፍትም ሞት አይፈሬዎቹ የአማራ ልጆች በፈፀሙት የጦር ሜዳ ጀብዱ ጠላት ሱባ ሜዳ፣ ክሬቸር፣ ሶዬ እና አሜጃ የተባሉ ቦታወች ላይ ያዘጋጃቸውን ምሽጎች ለቆ እንድፈረጥጥ የተደረገ ሲሆን የተደመሰሱ የጠላት ኃይል አባላት ስለመኖራቸውም ነው ከስፍራው የደረሰን መረጃ የሚያመላክተው::
የብልፅግና መከላከያ የ11ኛ ዕዝ 203ኛ ኮር 87ኛ ክፍለ ጦር እግረኛ ሰራዊት በሜካናይዝድ ምድብተኞች ታግዞ የተሰለፈ ቢሆንም የውጊያ የበላይነት በ29ኛ ክፍለ ጦር ሰራዊት ተወስዶበት በርካታ አባላቱን የተነጠቀ ሲሆን ቁስለኛም እንደታቀፈ ተረጋግጧል:: በተለምዶ ሶዬ ተብላ በምትጠራው አካባቢ እና ቆርኬ ሚካኤል አጠገብ የጠላት አስከሬን መንገድ ላይ ወድቆ እንደነበር የአይን እማኞች ገልፀዋል::
አንድ ጋንታ የሚሆን የጠላት ኃይል መመታቱንም ነው ለማረጋገጥ የቻልነው:: በተለይ በሶዬ በኩል ለማለፍ በማሰብ የተኩስ ጫና ለመፍጠር የሞከሩ የጠላት ኃይል አባላት ከተወሰኑት ውጭ በፋኖ ጥይት እንደተመቱ የሚያሳይ መረጃ ደርሶናል:: የ29ኛ ክፍለ ጦር ፋኖወች የጠላትን ምሽግ በመስበር ወደ ከተማይቱ የገቡ ሲሆን ጠላት በበኩሉ ካምፑን ጭምር ለቆ ወደ ከተማይቱ ፈርጥጧል::
የ29ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ አርበኛ ስንደው ገዜ እና ምክትሉ አርበኛ ሆነለት ገዜ እንድሁም የክፍለ ጦሩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ መብሬ ጫብሲ በጋራ በመሆን በመሩት ኦፕሬሽን የጠላት አከርካሪ ክፉኛ ተሰብሯል ሲል የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለዕዙ በላከው የአውደ ውጊያ ሪፓርት ገልጿል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም
በቆሪ ሜዳ ቀበሌ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ፤
በኤፍራታና ግድም ወረዳ ቆሪ ሜዳ ከተማ በአንድ የከተማዋ ነዋሪ ጀግና አርበኛ ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥቃትና የጅምላ ጭፍጨፋ የሚያሳይ ሌላው ጥቁር ጠባሳ ሆኖ በትናንትናው ዕለት አልፏል!!
በትላንትናው ዕለት ከሌሊቱ በግምት 6:00 ገደማ በባንዳነት ወደር የማይገኝለት በኤፍራታግድም ወረዳ ምክትል አስተዳድሪ የወረዳው ሰላምና ደህንነት ሀላፊ ወንድሙ ካሳ የካራቆሪ ሊቀመንበር ባንዳው አዲስ በረድ ሆነው የአብይ አህመድን ወንበር አስጠባቂ የመከላከያ ኃይሎች እና ባንዳ ሚሊሻ በተፈጸመ ከፍተኛ ከበባ፣ በቦምብና በከባድ መሣሪያ የታገዘ ጥቃት አቶ ደጀን ፀጋየ እና በ እንግድነት የመጡ ሁለት ዘመዶቹን በግፍ እንዲገደሉ አስደርገዋል።
በነበረው የተኩስ ልውውጥም አቶ ደጀን በመኗሪያ ቤቱ ግቢ ወጥ ያሉ ወታደራዊ ቦታወችን እየቀያየረ ይጠላትን ሀይል እንደቆሎ ሲያረግፈው አድሮ ሲነጋጋ ሊሸነፍላቸው ስላልቻለ ከ15 በላይ f1 የ እጅ ቦንብ ከ20 በላይ ኢነርጋ ቦንብ ዲሽቃ እና rpj በመጠቀም እና ቤቱን ከጥቅም ውጭ በማድረግ የአማራን ህዝብ የዘር ማጥፋት ውንጀል ፍጽመውበት አድረዋል።
ይህ ጥቃት ወታደራዊ አስፈላጊነት የሌለውና በንጹሐን ላይ ብቻ ያነጣጠረ ሲሆን አቶ ደጀን ፀጋየ ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ረፋዱ አራት ሰዓት ድረስ ለረጅም ሰዓታት በጽናት ሲከላከል መቆየቱና በዚህ አስከፊ ፍልሚያ ውስጥ አራት የአረመኔውን ሰራዊት ገድሎሎ እና የመከላከያውን ሻለቃ መሪ ጨምሮ በርካታዎችን አቁስለው በመጨረሻም አብረውት ለእንግድነት ከመጡ ዘመዶቹ ጋር የክብር መስዋዕትነትን ተቀብለዋል።
"ይህም ቆሪ ሜዳ የተፈጸመው ይህ ድርጊት በገለልተኛ አካላት ሲመረመር ዓለም አቀፍ የዘር ማጥፋት (Genocide) መስፈርቶችን ሊያሟላ የሚችልበት ዕድል ሰፊ መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ። የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ህዝብ ላይ፣ በታቀደና በታለመ መልኩ የሚፈጸም ጥቃት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩት መሰል ድርጊቶች ይህንኑ እውነታ የሚያጠናክሩ ሆነዋል።
ይህ ጥቃት አንድን ግለሰብ ሳይሆን የአንድን ማህበረሰብ ህልውና ለመቅጠፍ የታለመ ግልጽ መልዕክት ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። ተጎጂዎችም አቶ ደጀን ፀጋየ እና መላው ቤተሰባቹ በከባድ መሣሪያ የታገዘ ከበባ ውስጥ የቆየና ለ4 ሰዓታት የዘለቀ ጥቃት ሲሆን አብይ አህመድ የዘር ማጥፋት ወንጀል ስጋት እና የንጹሐን እልቂት አሁንም ቀጥሎበት ይገኛል።
የአማራ ፋኖ የግንባር ወቅታዊ ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችን ይወዳጁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

አፋብን_ቴዎድሮስ_ዕዝ_105ኛኮር 44ኛክፍለ_ጦር_ሰከላ_ወረዳ_ላይ_ድል_አስመዝግቧል
ጠላት በቀን የሚያደርገዉ ሙከራ ፍፁም አልሳካ ማለቱን ተከትሎ በሌሊት ተደጋጋሚ ሙከራ እያደረገ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ትናንት በሌሊት ከብር አዳማ ጥምር ጦር የሚለዉን የጋፈፋ ሰራዊት በመያዝ ወደ ሰካላ ወረዳ የፋኖ ቀጠና በማምራት ከባባ ለማድረግ አስቦ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም የ105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ነበልባሎች የተካኑበትን ደፈጣ በመጠቀም ጠላትን ሲለበልቡት አድረዋል።
ከበባና ወከባ ለመፍጠር አስቦ የተንቀሳቀሰው አራዊት ቡድን ፦
11 ሬሳ ጥሎ
15 በላይ ቁስለኛ አንጠልጥሎ በእሳት አየተለበለበ ወደ መጣበት ብር አዳማ ፈርጥጦ ሊገባ ተገዷል።
ጠላት ምንም አይነት የወታደራዊ የበላይነት ማግኘት አለመቻሉን ተከትሎ ሁለት ንፁሃን ገበሬዎችን ከቤታቸው በሌሊት አስወጥቶ ቁስለኛ በማሸከም አፋኖ ወስዷቸዋል።
የብር አዳማ ጤና ጣቢያ በዚህ ሰሃት ለመከላከያ ህክምና ብቻ እያገለገለ ለማህበረተሰቡ ፍፁም ዝግ ሁኖ በአካባቢው ሁሉ ምንም አይነት ህዝብ እንዳያልፍ ተከልክሏል ሲሉ የከተማው ነዋሪ መረጃውን አጋርቶናል።
ከሰሞኑ በተመሳሳይ ሁኔታ በሶስት አቅጣጫ በመንቀሳቀስ ወደ ሰከላ ለመግባት ሲሞክር ቲሊሊ ከተማ አቅራቢያ በ44ኛ ክፍለ ጦር ተገርፎ ከ30 በላይ ሬሳ በመጣል ደርዘን በላይ ጥቁር ክላሽ እንደተማረከ ይታወቃል።
በድል ታጅቦ የቆየዉ ክፍለ ጦር ራሱን እንደንስር አድሶ የጠላትን ቅስም እየሰበረ ይቀጥላል።
#ላንጨርስ_አልጀመርንም
©አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 44ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት!
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ም/አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ እና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በጋራ ድል ተቀናጁ‼️
የምኒልክ ዕዝ 104ኛ ኮር 25ኛ ክፍለጦር 1ኛ ሬጅመንትና ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘራያቆብ አንደኛ ኮር ቡርኬ ደምሴ ክፍለ ጦር በግሸ ራቤል ግንባር ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሙሀመድ ቢሆነኝ ኮር አስቴጉማ ክፍለ ጦር በመኮይ ግንባር የ104ኛ ኮር 25ኛ ክፍለ ጦር ቃኝና የቀጠናው አባት አርበኞች በበተሆ ግንባር በጋራ በሰሩት የተጠና እና ጥላትን ስቦ በማስገባት ሙትና ቀለስለኛ አድርገው ወደመጣበት መልሰውታል።
አስቴ ጎማ ክፍለ ጦር አንድ የስርዓቱን ጨፍጫፊ ይዞ ሲጓዝ የነበረ ኦራል በRPG ከነጫነው ሰራዊት እንድወድም አድርገዋል።የአማራን ህዝብ ለማጥፋት አቅዶ እየሰራ ያለው የብልፅግና ስርዓት የደረሰበትን ሽንፈት የተለመደ የበቀል ርምጃውን ህዝብ ላይ አሳርፏል። በአልብኮ ወረዳ 08 ቀበሌ ተደጋጋሚ መድፍና ሞርተር በመወርወር አራት ንፁሀን ሲቆስሉ አምስት የአርሶ አደሮች ቤት ከነንብረታቸው ወድሟል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
25/ዐ7/2018 ዓ.ም
የድል ዜና
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ በአራት አቅጣጫዎች የመጣውን የጠላትን ኃይል በመምታት ድልን ተቀዳጀ!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ትናንት ታሪካዊ አንድነቱን ባበሰረ ማግስት፣ በዛሬው ዕለት በከፈተው መጠነ ሰፊ ማጥቃት በወንበር አስጠባቂው የአብይ አህመድ ሰራዊት መከላከያ፣በአድማ ብተና እና በሚሊሻ ኃይሎች ላይ በከፈተው አውደ ውጊያ ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል። ከሁለቱ ግዙፍ ኮሮች በተውጣጡ ሻለቆች የጠላትን ሀይል እንደገብስ ሲወቁት አምሽተዋል። መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦር ከመሐል ሜዳ ተነስቶ ወደ ባሽ ይገሰግስ የነበረውን የአገዛዙን አራዊት ሰራዊት መንገድ በመዝጋትና የገነባውን ምሽግ በመሰባበር በወሰዱት መጠነ ሰፊ ማጥቃት ወደ መጣበት እንዲፈረጥጥ አድርጓል።
በግሸ ወዠድ ጦር መሳያ ግንባር የመሐመድ ቢሆነኝ ኮር የአስቴጉማ ተራራ ክፍለ ጦር ከግሸ ወደ ወዠድ የሚወስደውን ዋና መስመር ይዞ የነበረውን የጠላት ኃይል ድባቅ መትቶታል። በዚህ ውጊያ አንድ ሙሉ የጠላት FSR Isuzu ሙሉን የጠላት ሀይል ለወሬ ነጋሪ ባልተረፈ ሁኔታ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል። እንዲሁም ከአጣዬ መሐል ሜዳ መስመር የዓፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር ስር የሚገኙት የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር እና የዓፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለ ጦር በአንድነት በመሆን፣ ከአጣዬ ወደ መሐል ሜዳ በሚወስደው መንገድ ጓሳ ላይ መሽጎ የነበረውን ወራሪ ኃይል አመድ አድርገውታል።
በዚህም አራቱ ክፍለ ጦሮች በወሰደው ብርቱ እርምጃ በጠላት ላይ ከፍተኛ የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ኪሳራ ደርሶበታል።በዛሬው አውደ ውጊያ የብአዴንና የብልጽግና ወንበር ጠባቂ ኃይሎች በርካታ የጦር መሣሪያዎችና ትጥቆች በፋኖ እጅ ተማርከዋል።ትላንት በአንድነት ቆምን ዛሬ ደግሞ በተግባር ድልን ማብሰራችን ለእኛ የአማራ የነፃነት ማማ የጠላት የውድቀት መጨረሻው መሆኑን አሳይተናል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው።
መጋቢት 25/07/2018 ዓ.ም

የአፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዕቆብ ፩ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው።
መጋቢት 25/07/2018 ዓ.ም