ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 194
Suscriptores
+4524 horas
+967 días
+45930 días
Archivo de publicaciones
+7
24ኛ ክ/ጦር ከደባይ ጠላት ግን ወረዳ ብቁ ወጣቶች ጋር !!
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ደባይ ጠላት ወረዳ ጀረምስ ቀጠና የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
=======================================
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።
በምስራቅ ጎጃም ደባይ ጠላት ግን ወረዳ ጀረምስ ቀጠና እንዲሁ ህዝባዊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ወጣቶች ተሳታፊ ሁኗል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
⏭የድሮን ቅኝት⚠️
ዛሬ ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በሸዋ ቀጠናዎች፣ በመሀል አምባ፣በጭምብሬ ፣በመንዝ ቀጠና፣ በተጉለት ቀጠና፣በከሰም ቀጠና፣በኮረማሽ እና በሸረር ቀጠናዎች የድሮን ቅኝት እየተደረገ ይገኛል።
✅ከዕዙ መረጃና ደህንነት መምሪያ⚠️
ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የብልፅግና አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ!!
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆንርኝ ኮር የአስቴጎማ ተራራ ክፍለጦር በየዕለቱ የጠላትን አከርካሪ እየሰበረ፣ ህዝብን በጨረባ ምርጫ ሰበብ የሚያሰቃየውን የብልፅግና ቡድን ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ አሸናፊነቱን በድል እያስመሰከረ ይገኛል።
ማያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ፣በዚሁ የአገዛዙ መንገድ መሪና የህዝብን ስቃይ ለማራዘም ተልዕኮ ፈፃሚ ሀይል ላይ በተጠና ኦፕሬሽን መብረቃዊ ጥቃት ተፈፅሟል።
በመኮይ ዜሮ አምስት (05) ቀበሌ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት፣ፋኖን በማስወጋትና አስገዳጅ በሆነ መንገድ ህዝቡን የሚያሰቃዩትን የወረዳውን የብልፅግና አመራሮችና ካቢኒዎችን ጭና ስትጓዝ የነበረች መኪና ላይ ከፍተኛ ጥቃት ደርሷል። በዚህም መሠረት
ደምስ አበራን ጨምሮ ስምንት (8) የብልፅግና አመራሮች ላይ ከባድ እርምጃ ተወስዷል። ጥቃቱ የደረሰባቸው አመራሮች በሶስት አምቡላንሶች ተጭነው ለህክምና ወደ ደሴ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተረጋግጧል።
ክፍለጦሩ የህዝባችንን መከራና ሲቃይ በሚያራዝሙ ባንዳዎች ላይ ይህና መሰል እርምጃዎች ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያረጋግጧል።
የመረጃ ምንጭ- የመሃመድ ቢሆነኝ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ወሳኝ የደፈጣ ጥቃት ተፈጸመ፤ የብልፅግና አመራሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ!!
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ አሳምነው ዕዝ መሀመድ ቢሆንርኝ ኮር የአስቴጎማ ተራራ ክፍለጦር በየዕለቱ የጠላትን አከርካሪ እየሰበረ፣ ህዝብን በጨረባ ምርጫ ሰበብ የሚያሰቃየውን የብልፅግና ቡድን ጉሮሮ ለጉሮሮ በመናነቅ ላይ ይገኛል።
ማዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ፣ የክፍለጦሩ ብቁ የጦር አመራሮች ባቀዱት የተጠና ኦፕሬሽን፣ የአርበኛ አያሌው መክት እና የአርበኛ ሸጌ መርድ ሻለቆች በጋራ በመቀናጀት በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈጽመዋል።
በመኮይ ዜሮ አምስት (05) ቀበሌ በተፈጸመው በዚህ ደፈጣ ጥቃት፣ የወረዳውን የብልፅግና አመራሮችና ካቢኒዎችን ጭና ስትጓዝ የነበረች መኪና ላይ ከፍተኛ ጥቃት ደርሷል። በዚህም መሠረት
የጠላት ጉዳት ደምስ አበራን ጨምሮ ስምንት (8) የብልፅግና አመራሮች ላይ ከባድ እርምጃ ተወስዷል። በዚህም ተሽከርካሪዋ በመገለባበጥ ለሁለት በመከፈሏ ሙሉ በሙሉ ከአገልግሎት ውጭ ሆናለች። ጥቃቱ የደረሰባቸው አመራሮች በሶስት አምቡላንሶች ታጭቀው ወደ ደሴ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተረጋግጧል።
ይህ ድል የአስቴጎማ ተራራ ክፍለጦር በጠላት ላይ እየወሰደ ካለው ተከታታይ እርምጃ አንዱ ሲሆን፣ ትግሉ አላማውን እስኪያሳካ ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ዕዙ ያረጋግጣል።
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ፩ኛ ኮር፣ በቁጥጥራቸው ስር ባሉ ነፃ ቀጠናዎች የህዝባዊ ምክክር መድረኮችን በስኬት አጠናቀዋል።
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በተካሄዱት በእነዚህ መድረኮች፣ የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ለማሸጋገር የሚያስችል ወጥ የሆነ አሰራርን በተመለከተ ከማህበረሰቡ እና ከአመራሮች ጋር በጋራ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ የውይይት መድረኮች ህዝቡ በነቂስ በተገኘበት በታላቅ ድምቀት ምክክሩ ተካሂዷል። ተሳታፊዎች የህልውና ትግሉን አስመልክቶ ሃሳባቸውን በነፃነት የገለጹ ሲሆን፣ የአፋብን የአንድነት አሰራር የአሸናፊነት ጉዞው የመጀመሪያ ምዕራፍ መሆኑን በአጽንኦት አረጋግጠዋል።
በዚህም በግሼ ክላስተር (የላይኛው እና የታችኛው መንዝ ቀጠና) በወሎ ቤተ_አምሐራ ምኒልክ ዕዝ እና በሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ጥምረት በተዘጋጁ መድረኮች፣ በግሼራቤል ወረዳ ደል እና በኮረብቲት ቀበሌ የአርሶ አደሮች የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል። በመድረኩም ማህበረሰቡ ከፋኖ ጎን ቆመን ስረዓቱን እናፈርሳለን እንጂ ገዳያችንን አንመርጥም ብለዋል። በዕለቱ አርሶ አደሩ በአካባቢው የህልውና ትግል ሂደት ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርጓል።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ከአንድነት በኋላ እያሳየ ያለው ወጥ የሆነ አሰራር፣ ለህልውና ትግሉ ድል አድራጊነት ወሳኝ መሆኑ በመድረኮቹ በስፋት ተነስቷል። ማህበረሰቡ በነፃነት ባንጸባረቀው ሃሳብ መሰረት፣ የህዝብ እና የፋኖ አንድነት የድል ጉዞው የጀርባ አጥንት መሆኑን አረጋግጠዋል።
"ክብር ለትግሉ ሰማዕታት!"
"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!"
የአፋብን የሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሚያዚያ 23/08/2018 ዓ.ም
+2
👉 በቀን 21/08/2018 ዓ/ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ➊ⓞ❷ኛ ኮር
❷❷ኛ ክ/ጦር
የተፈፀ ጀብድ !
ልክ በሆነ ስሌት ፍፁም በሆነ ወንድማማችነት መከባበበር መደማመጥ ቅንነት የተሞላበት ያለምን ኮሽታ በወጣቶቹ የጦር መሀንዲሶች :-
1. ም/ወአዛዥ➝ ገደፋው አይዘንጋው
2. ዘመቻ መምሪያ➝ ባየልኝ ወንዱ
በትላንትናው ዕለት ቀጠናውን የሚመጥን ህዝባችን የሚያነቃቃ የጠላት ቅስም የተሰበረበት ድል እንካችሁ ብለውናል ::
👉 እኛም ከመቀመጫችን ብድግ ብለን እጅ ነስተናል 🤝
እኒህ አብሪ ኮከቦች አክለው እንደተናገሩት ይህ ጅምር ነው ነገ ባህር ዳርንና አካባቢውን እንደአጠቃላይ ምንም ዓይነት የጠላት ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ አፈራርሰን ትልቅ ድል እናበስራችኃለን ብለውናል ::
+3
201ኛ ኮር ከሰዴ ወረዳ ብቁ ወጣቶች ጋር
በተደራጀ የፖለቲካ ስራ የአማራ ህዝብ ብሔራዊ ንቃት ይዳብራል፤ ህልውናውም ይረጋገጣል!
በሚል መሪ ቃል በምስ/ጎጃም ሰዴ ወረዳ የሰዴ ከተማ የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
=======================================
ከአፋብን በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት 201ኛ ኮር በተቆጣጠራቸው ነፃ ቀጠናዎች የወጣቶች የውይይት መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት ተካሒደዋል። የህልውና ትግሉን በተደራጀ መንገድ ጫፍ ለማድረስ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለመወያየት የሚያስችል ሰነድ በመድረኩ ቀርቧል።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
ሚያዚያ 23 የቅዱስ ጊዮርጊስን የዕረፍት በዓል በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም በድምቀት ተከብሯል።
~~~~
64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት ነው። ሐገሩ ፍልስጤም አሁን እስራኤል ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ አሁን (ሉድ) ይባላል።
ሊቀ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታትን ያስጨነቀ፣ ቤሩታዊቷን ከዘንዶ አፍ ያዳነ፣ የመበለቷን ቤት ምሰሶ ያለመለመ፣ ሰባት ዓመት በፅኑ ተጋድሎ የተጋደለ በኋላ በ27 ዓመቱ በ304 ዓ.ም ሚያዚያ 23 ቀን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ነፍሱን የሰጠ ፅኑ ሰማዕት ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን እያልን ዲማ ጊዮወረጊስ የመላከ ብረሃን አድማሱ ጀንበሬ፤ የሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ፤ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ የፍቅር እስከ መቃብር ድርሰት መነሻ፤ እሳቸውም የቤተክነት ትምህርት የተማሩበት የቅዱሳን እና የጀግኖች አርበኞች መፍለቂያ ቦታ ታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ነው።
በክብር በአሉ ከተለያዩ ቦታ የተገኙ የሐይማኖት አባቶች፣ ካህናት፣ ምዕመናን እና በአካባቢው የሚገኙ የከተማዋ ኖሪዎች እንዲሁም ከአገዛዙ ጋር እየተደረገ ባለው የህልውና ትግል ሶስት ዓመት ሙሉ ዲማ ከተማን ያላስደፈሩ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች የ64ኛ ክ/ጦር አመራር እና አባላት በተገኙበት በዲማ ከተማ በደማቅ ሁኔታ አክብረውታል።
ክብር በአሉ አገዛዙ አስርጎ በአስገባቸው ሐይሎች እንዳይደናቀፍ በጀግኖች የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ የመንፈስ ልጆች 64ኛ ክ/ጦር አመራር እና አባላት ከፍተኛ ጥበቃ በማድርግ በዲማ ጊዮርጊስ በተገኘው ምዕመናኑ ጋር በሰላም ተከብሮ በሰላም ተጠናቋል።
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ከታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ሰማይ ስር
ሚያዚያ 23 የቅዱስ ጊዮርጊስን የዕረፍት በዓል በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም በድምቀት ተከብሯል።
~~~~
64ኛ በላይ ዘለቀ ክ/ጦር ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት ነው። ሐገሩ ፍልስጤም አሁን እስራኤል ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ አሁን (ሉድ) ይባላል።
ሊቀ ሰማእት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባ ነገሥታትን ያስጨነቀ፣ ቤሩታዊቷን ከዘንዶ አፍ ያዳነ፣ የመበለቷን ቤት ምሰሶ ያለመለመ፣ ሰባት ዓመት በፅኑ ተጋድሎ የተጋደለ በኋላ በ27 ዓመቱ በ304 ዓ.ም ሚያዚያ 23 ቀን ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ነፍሱን የሰጠ ፅኑ ሰማዕት ነው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን እያልን ዲማ ጊዮወረጊስ የመላከ ብረሃን አድማሱ ጀንበሬ፤ የሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ፤ የክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ የፍቅር እስከ መቃብር ድርሰት መነሻ፤ እሳቸውም የቤተክነት ትምህርት የተማሩበት የቅዱሳን እና የጀግኖች አርበኞች መፍለቂያ ቦታ ታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ነው።
በክብር በአሉ ከተለያዩ ቦታ የተገኙ የሐይማኖት አባቶች፣ ካህናት፣ ምዕመናን እና በአካባቢው የሚገኙ የከተማዋ ኖሪዎች እንዲሁም ከአገዛዙ ጋር እየተደረገ ባለው የህልውና ትግል ሶስት ዓመት ሙሉ ዲማ ከተማን ያላስደፈሩ የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ ልጆች የ64ኛ ክ/ጦር አመራር እና አባላት በተገኙበት በዲማ ከተማ በደማቅ ሁኔታ አክብረውታል።
ክብር በአሉ አገዛዙ አስርጎ በአስገባቸው ሐይሎች እንዳይደናቀፍ በጀግኖች የደጅ አዝማች በላይ ዘለቀ የመንፈስ ልጆች 64ኛ ክ/ጦር አመራር እና አባላት ከፍተኛ ጥበቃ በማድርግ በዲማ ጊዮርጊስ በተገኘው ምዕመናኑ ጋር በሰላም ተከብሮ በሰላም ተጠናቋል።
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ከታላቁ ዲማ ጊዮርጊስ ሰማይ ስር
33ኛ ክፍለ ጦር ከአገዛዙ ነፃ ባደረጋቸው አካባቢዎች ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ምክክር አደረገ
༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺༻༺
[ሚያዝያ 23/2018 ዓ.ም፣ ዐፋብን ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት]
በምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሰው 102ኛ ኮር 33ኛ ክፍለ ጦር "#ከወሬ_ወደ_ተግባር፣ #ከምክክር_ወደ_ግምባር" በሚል መሪ ቃል በቋሪት እና በጎንጂ ቆለላ ወረዳዎች ከአገዛዙ ነፃ ባደረጋቸው አካባቢዎች ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ማርሽ ቀያሪ ምክክር አደረገ።
"ወጣትነት ጉልበት ብቻ ሳይሆን የነፃነት መንፈስም ነው" ያሉት በእንዘግድም ቀጠና ምክክር የተገኙት የ3³ኛ ክፍለ ጦር የፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊ አርበኛ አማረ በላቸው፣ ሀገር ስትወረር እና ሕዝብ ሲታረድ "ነገ እሄዳለሁ" እንደማይባል አስገንዝበዋል።
በፋኖ ጊዜያዊ አስተዳደር የጎንጂ ቆለላ ወረዳ አስተዳዳሪ አርበኛ አረጋ አበረ በበኩላቸው ነፃነት በደምና በአጥንት እንጂ በልመና የምትመጣ አይደለችም በማለት ወጣቱ ሀገር ለመረከብ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ብለዋል።
ወጣቶችም በነገ ታሪክ ራሳቸውን ለማግኘት ከዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ጋር እንደሚሠለፉ ጽኑ ፍላጎታቸውን አንፀባርቀዋል።
በተያያዘም ወታደራዊ ሥልጠና በአስቸኳይ እንዲመቻችላቸው እና በዐውደ-ውጊያዎች እንዲሳተፉ ወጣቶች ጠይቀዋል።
የ33ኛ ክፍለ ጦር ጊዜያዊ መንግሥት በኹሉም አካባቢዎች ከወጣቶች ጋር ባደረገው ምክክር የዚህ ዓመት የብልጽግና ምርጫ "በአጥንትና በደም ላይ የታሰበ ድርድር" ተብሎ በወጣቶች ተገልጿል።
በመጨረሻም "አንድ ክንድ ፥ አንድ ልብ" የቋሪት እና የጎንጂ ቆለላ ወረዳ ወጣቶች በየቀጠናው ወጣት ማኅበራትን አቋቁመው ምክክሩን ቋጭተዋል።
✔ አንድ ክንድ ፥ አንድ ልብ‼
ጀነራል ተፈራ ማሞ ለዓለም አቀፉ የተቃውሞ ሰልፍ ድጋፋቸውን ገለጹ፤ “አገዛዙ በሕዝባችን ስም እየተበደረ የዘር ማጥፋት እንዳይፈጽም የዲፕሎማሲ ጫናው ይበርታ” ሲሉ አሳሰቡ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ጀነራል ተፈራ ማሞ በዛሬው ዕለት በስዊድን ስቶክሆልም ለተጀመረውና በሌሎች የዓለም ከተሞች ለሚቀጥለው ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሙሉ ድጋፋቸውን ገለጹ።
ጀነራሉ በሰጡት መግለጫ፣ የውጭው ዲያስፖራ አገዛዙ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን የዘር ማጥፋት ወንጀልና በምርጫ ስም የሚደረገውን የይስሙላ ሩጫ ለማስቆም በቆራጥነት እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል።
ጀነራል ተፈራ ማሞ ባስተላለፉት መልእክት፣ አሁን ያለው የአብይ አህመድ አገዛዝ ዲያስፖራው በሀገሩ ቋሚ ንብረት ማፍራት ቀርቶ፣ ሲሞት እንኳን ሰውነቱ በክብር እንዳያርፍ የከለከለ ጨካኝ ሥርዓት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በውጭ የሚኖረው ወገናችን ይህንን ግፍ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማሳወቅ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ጫና ማሳደር እንደሚገባው አሳስበዋል።
በተለይም አገዛዙ በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም የሚበደረው ብድርና የሚያገኘው እርዳታ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሚያ እየሆነ መሆኑን ጀነራሉ ጠቁመዋል።
በመሆኑም ዲያስፖራው አገዛዙ ምንም ዓይነት ዓለም አቀፍ ብድርም ሆነ እርዳታ እንዳያገኝ በትጋት ሊሠራ እንደሚገባ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
ይህ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍም የአገዛዙን እውነተኛ ገጽታ ለማጋለጥና የገንዘብ ምንጮቹን ለማድረቅ ወሳኝ መድረክ መሆኑን ጀነራሉ አረጋግጠዋል።
ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ዘመቻ ተጠራ!
የአብይ አህመድ አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጦርነት በመቃወም እና ሊያካሂድ ያቀደውን ምርጫ ቅቡልነት ለማሳጣት ያለመ ታላቅ ዓለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ዘመቻ መጥራቱን የደረሰን መረጃ አመለከተ።
“በዘር ማጥፋት መካከል ምርጫ የለም!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ይህ ንቅናቄ፣ የአገዛዙን አፋኝ እርምጃዎች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በይፋ ለማጋለጥ ያለመ ነው።
የተቃውሞው አስተባባሪዎች ባወጡት መግለጫ፣ አገዛዙ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት እያካሄደ ባለበት ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ሊካሄድ እንደማይችል አስታውቀዋል። “ባሩድ ባለበት ድምፅ መስጠት አይታሰብም!” (No ballots while bullets fly!) የሚለው መርህም የዚህ ንቅናቄ ዋነኛ ድምፅ ሆኗል።
ሰልፈኞቹ አገዛዙ ከዚህ በኋላ የሕዝብ ውክልና እንደሌለው፣ ቅቡልነት እንዳጣ እና የውሸት ትርክቱ ማብቃት እንዳለበት በጽኑ እያሳሰቡ ይገኛሉ።
ይህ መጠነ-ሰፊ የሰልፍ ዘመቻ በዛሬው ዕለት በስዊድን መዲና ስቶክሆልም የሚጀመር ሲሆን፣ በመጪው የግንቦት (May) ወር ውስጥ በተለያዩ የዓለም ከተሞች ቀጣይነት ይኖረዋል።
ሰልፉ የሚካሄድባቸው ከተሞችና ቀናቶች እንደሚከተለው ተመልክተዋል፦
• ስቶክሆልም፣ ስዊድን፦ ግንቦት 1 (May 1)
• ሲያትል፣ አሜሪካ፦ ግንቦት 9 (May 9)
• ብራስልስ፣ ቤልጂየም፦ ግንቦት 11 (May 11)
• ዋሽንግተን ዲሲ፣ አሜሪካ፦ ግንቦት 14 (May 14)
• ኦታዋ፣ ካናዳ እና ፓሪስ፣ ፈረንሳይ፦ ግንቦት 16 (May 16)
• ማኒቶባ (ካናዳ)፣ ሜልቦርን (አውስትራሊያ) እና ጣሊያን፦ ግንቦት 17 (May 17)
• ኦስሎ፣ ኖርዌይ፦ ግንቦት 22 (May 22)
• ሎንዶን፣ ዩናይትድ ኪንግደም፦ ግንቦት 23 (May 23)
ይህ ንቅናቄ “ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ፍትሕ እንጂ የይስሙላ ምርጫ አይደለም” የሚል ጠንካራ መልእክት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚያስተላልፍ ነው።
ሰልፈኞቹ የሚሰጡት ድምፅ ለአምባገነናዊ ሥርዓት ቅቡልነትን እንደማይሰጥና በአማራ ሕዝብ ላይ የታወጀው ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም ግፊት እንደሚያደርጉም ታውቋል።
