ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 413
Suscriptores
+2224 horas
+437 días
+1 38430 días
Archivo de publicaciones
መረጃ ባህር ዳር‼️
በባህር ዳር ከተማ ከማለዳው ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ ወጣት እየታፈሰ ነው የከተማዋ ወጣቶች ብርቱ ጥንቃቂ እንዲያደርጉ ከስፍራው ለአማራ ድምፅ አድርሰውናል ስራ የሌለውና ፖል ቤት የተገኘው በሙሉ እንዲታፈስ ትዕዛዝ ወርዷል
አደራ ልጄ
ገንዘብ ውርሴን አምጪ አትበይኝ አደራ
መኪና ቪላ ፎቅ አትበይኝ አደራ
ባቡር አውሮፕላን አትበይኝ አደራ
እናትሽ ድሀ ነኝ
ሀገር ተቀበይኝ ሰንደቅ እንዳበራ
ደስ አሰኝኝ ልጄ እኔም ባንቺ ልኩራ።
ለትውልዱ ይተላለፋል ዳዊት ነኝ ከትግል ሚዳ
በአራቱም ማዕዘን እውነተኛውን አውደ ውጊያ ከግንባር ሁነን እየሰራን እንገኛለን ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
የአደረጃጀት ዜና
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ስር የሚገኙ ክፍለ ጦሮችን ወታደራዊ መመሪያው በሚጠይቀው መስፈርት መሰረት በአዲስ መልኩ የማደራጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል::
በዚህም መሰረት በምዕራብ ወሎ ግንባር ለጋምቦ እና ከላላ ወረዳ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ 2 ክፍለ ጦሮች ማለትም ሸዋንግዛው ካሳ ክፍለ ጦር እና ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ወደ አንድ እንድመጡ በማድረግ ሰራዊታቸው ተበውዞ በ3 ሻለቃዎች የተዋቀረ አዲስ ውህድ ክፍለ ጦር የተመሰረተ ሲሆን ስያሜውም የስመጥሩው ጀግና ማስታወሻ እንዲሆን በሚል ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ተብሎ እንዲጠራ ሰራዊቱ በሙሉ ድምፅ ወስኗል::
ክፍለ ጦሩ የተዋቀረባቸው ሻለቃዎች ስያሜም በትግሉ ሂደት የተለየ የጦር ሜዳ ጀብዱ ፈፅመው በተሰው ጓዶች ስም እንዲሆን የተደረገ ሲሆን በዚህም መሰረት 1ኛ ሻለቃ ሸዋንግዛው ሻለቃ ሲባል ለሻለቃ 2 ደግሞ እንድሪስ ተሾመ ሻለቃ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል:: በብስቁልሉ ኦፕሬሽን ጠላትን አንቀጥቅጦና በርካቶችን ደምስሶ በስተመጨረሻ ጥይት ሲያልቅበት ትጥቄ ጠላት እጅ አይገባም ብሎ ብሬኑን ድንጋይ ላይ ከስክሶ በክብር እና በጀግንነት በተሰዋው በአርበኛ አህመድ አቀስታ ስም ደግሞ 3ተኛው ሻለቃ ተሰይሟል::
በሪፎርሙ መሰረት ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው አርበኞች ክፍለ ጦሩን በእውቀት እና በእውነት እንዲመሩ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል::
1ኛ. አርበኛ አለልኝ ተሰማ - ዋና አዛዥ
2ኛ. አርበኛ ጀማል ብሬን - ምክትል አዛዥ
3ኛ. አርበኛ ዳዊት ፍሰሀ - የወታደራዊ አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ
4ኛ. አርበኛ አህመድ ሁሴን - ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
4.1 አርበኛ አቢ ሙሉ - ምክትል ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
5ኛ. አርበኛ እንድሪስ አቢ - ሎጅስቲክስ
6ኛ. አርበኛ ይመር ሁሴን - የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ
7ኛ. አርበኛ ጀማል ክብረት - ፋይናንስ
7.1. አርበኛ ኡመር አሊ - ምክትል ፋይናንስ
8ኛ. አርበኛ ክብረት አባው- የወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ ኃላፊ
8.1. አርበኛ አህመድ ሙስጠፋ - የወታደራዊ ስልጠና ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
9ኛ. አርበኛ ሙሀመድ ደረሰ - ኦርዲናንስ
9.1. አርበኛ አቡዬ በቀለ - ምክትል ኦርዲናንስ
10ኛ. አርበኛ አብዱ ሙሀመድ - የሰው ኃይል ዘርፍ ኃላፊ
11ኛ. አርበኛ ጌታዬ እረሽድ - የህክምና ዘርፍ ኃላፊ
11.1. አርበኛ አሰን አቡዬ - የህክምና ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
12ኛ. አርበኛ አሊ ሙሀመድ - ሀብት አሰባሳቢ
12.1. አርበኛ ክራር - የሀብት አሰባሳብ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ
እነዚህ አርበኞች የክፍለ ጦሩ አመራሮች ሆነው በአብላጫ ድምፅ ስለተመረጡ እነሱም በበኩላቸው ትግሉን በአግባቡ ለመምራት በአማራ ህዝብ እና በፈጣሪ ስም ቃል ገብተዋል::
ከአደረጃጀት ሪፎርሙ በተጨማሪ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ ለክፍለ ጦር እና ሻለቃ አመራሮች የወታደራዊ አመራር ስልጠና መስጠቱ ታውቋል::
ለክፍለ ጦሩ ሰራዊት አባላትም ወታደራዊ እና የፓለቲካ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በዋናነት በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እንድወስዱም ተደርጓል::
የክፍለ ጦሩን ሰራዊት የግዳጅ አፈፃፀም ብቃት ይበልጥ ለማሻሻል እና የማድረግ አቅሙን ለማዳበር ሲባል በቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባይ ክፍለ ጦር አመራር ሻለቃ ክንዱ ሰውነት አማካኝነት ለተከታታይ 15 ቀናት ወታደራዊ ስልትን የተመለከተ የተግባር እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለሰራዊት አባላት እንደተሰጠም ነው ለማረጋገጥ የቻልነው::
ሰራዊቱ በፓለቲካ እና በውትድርናው ዘርፍ የተሻለ ግንዛቤ ኖሮት ግዳጁን በብቃት እንድወጣ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ሰራዊቱ የሚተዳደርበትን ወታደራዊ መመሪያ ለሁሉም በማሳወቅ በመመሪያው መሰረት ለመታገል ፍቃደኛ የማይሆኑት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ የማስተካከል ስራ ሊሰራ እንደሚገባ የዕዙ ዋና ሰብሳቢ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ለኮሩ አመራሮች አስታውሶ ከእንግዲህ ተጠያቂነት ያለው አሰራር ተግባራዊ እንደሚሆን መናገሩም ታውቋል::
ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ በበኩሉ ስለ መሪነት እና ሌሎች ወታደራዊ ጉዳዮች ለክፍለ ጦር እና ሻለቃ አመራሮች ስልጠና ሲሰጥ ባስተላለፈው መልዕክት እጃችሁ ላይ ያለው የሰው ህይወት ነውና በእውቀት እና ጥበብ ይህን ትግል ልትመሩ ይገባል ሲል አሳስቧል:: ኮሎኔሉ ወታደራዊ ስነ-ምግባርን በተመለከተም ለአመራሮቹ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ሰርቷል:: በመጨረሻም አመራሮቹ መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠና ቀጣይነት ባለው መልኩ ቢሰጠን ሲሉ ይበልጥ የመማር እና የማወቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም
ወምበርማ ብርጌድ
"""የሁለት ቀኑ የወምበርማ ብርጌድ ተጋድሎ """
( ወምበርማ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት መመሪያ ጥቅምት 27/2018 ዓ.ም )
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
አፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 5ኛ ክ/ጦር ወምበርማ ብርጌድ ሽንዲ ከተማ የመሸገዉን የአገዛዙ አገልጋዮች ከፈራረሰዉ ሥርዓት ከአለቆቻቸዉ ተልዕኮ ተቀብለዉ ወደ ወገዳድ ሲንቀሳቀሱ ነበልባሎቹ የወምበርማ ብርጌድ ቆጥላን ላይ ረጅም ሰዓት በማድፈጥ ከሁለት ሰዓት እስከ ስምንት ሰዓት ከጠላት ጋር ሀይለኛ ተጋድሉ አድርገዋል ።
በአዉደ ዉጊያም ፦
ከአስራ አምስት በላይ የአገዛዙ ሀይል ወደላይኛዉ እንደተሸኙ እንዲሁም ፦
አራት ፓትሮል ቁስለኛ ከወገዳድ ጭኖ ወደ ማርቁማ እንደወሰዳቸዉ እና ወደ ሲኖ መኪና ገልብጦ ሽንፈቱን ለመደበቅ ቡሬ ሆስፒታል እንደወሠዳቸዉ የዉስጥ ምንጮቻችን ገልፀዉልናል ።
በደረሰባቸዉ ከባድ ምት ተደናግጠዉ ወገዳድ መሽጎ ጠላት ቢያድርም አይበገሬዎቹ የወምበርማ ብርጌድ ሽንዲ ከተማ ሰርገዉ በመግባት ሀይለኛ ተጋድሎ ፈፅመዋል ። በአዉደ ዉጊያዉም በቁጥር ያልታወቀ የአገዛዙ አገልጋዮች ወደላይኛዉ ሲሸኙ ፣ ቁስለኛዉን እንደተለመደዉ ወደ ጤና ጣቢያ አስገብቷል ።
አንድ አማራ!!!!!
እስከ ምጽአት አማራ!!!!
አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ አስተሳስብ ፣ አዲስ ትዉልድ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 27 ቀን 2018 ዓ.ም (# አሻራ ሚዲያ)
™~~~~~~~~~~||
ምስራቅ ኢትዮጵያ!
አብይ አህመድ ድሬድዋ የኦሮሞ ነበረች/ነች ካለ በኋላ የኦሮሞ አክቲቪስቶች እና አመራሮች በተደጋጋሚ እያስተጋቡት ያለ በኦሮሚኛ የተዘጋጀ ቅንብር ፁሁፍ ሲተረጎም:-
"It's been 30 years since Hararghe lost Harar. It's been 30 years since Ethiopia lost Assab. Ethiopia will reclaim port and Hararghe to reclaim Harar."
ከላይኛው ቲተር አረበኛ ፊደልም የተጻፈ አለው።
+2
..............የአደረጃጀት ዜና !! ...........
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር የ77ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በአርበኛ ስሜነህ ሙላቱ ፣ በአርበኛ ግሩም ምሳሌ እና በሀምሳ አለቃ ታደሰ ልንገር አስተባባሪነት ተጠናቋል ።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
ጡት ቆራጩ አገዛዝ የህዝብ ማመላለሻ ሹፌሮችን ተኩሶ አቆሰለ፣ደበደበ‼️
ዘራፊዉና ጡት ቆራጩ የጁላ ስብስብ ሙሉ አቸፈር ላይ ከዱርቤቴ_ቁንዝላ መንገዱን ዘግቷል።
ለምን ብለዉ የጠየቁ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን አስሯል ሹፌሮችን ተኩሶ አቁስሏል፣ደብድቧል።
በጭንቀት የራደዉ ልበ ፍሱ የጁላ ሰራዊትና የናት ጡት ነካሾች ካድሪ፣አድማ ብተና፣አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻ ባለሀብቶችን እየጠቆሙ እያሳሰሩ ይገኛሉ አሽከርካሪዎችን በተመሳሳይ እያሰቃዩ ይገኛሉ።
ያም ሆነ ይህ ሊበን ላይ ዉጥረቱ ነግሷል። እኛም በንስር እይታ እየተከታተልን እንገኛለን ከቆንጆዎቹ የሚያልፍ አንዳች ነገር የለም ::
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
በሰሜን አማራ ቀጠና አንዳቤት ከተማ አከባቢ በተደረገ ውጊያ ከ25 በላይ የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ!
በአንዳቤት ከተማ ዙሪያ ሜላት ቀበሌ ልዩ ስማቸው ወልድሀና፣ መርጅ እና ጠንቆጥ ገብርኤል በተባሉ አከባቢዎች በተደረገ ውጊያ የውባንተ ልጆች ድል እንደ ሸማ ሲቀዳጁ፡ በአንፃሩ ደግሞ የፀረ አማራው አገዛዝ ተላላኪው ኃይል ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ማስተናገዱን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።
በጠላት ላይ ብርቱ ጥቃት የፈፀሙት በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሜጄር ጄኔራል ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክ/ጦር ስር የሚገኙት የአንዳቤት ብርጌድ ጀግኖች ሲሆኑ፡ ውጊያው ዛሬ ጥቅምት 26/2018 ጧት ጀምሮ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ዘልቆ ውሏል ተብሏል።
በውጊያው 10 የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ ከ15 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን ነው መረብ ሚዲያ ከኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ የቻለው።
ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ኃይል፡ የዘፈቀደ ከባድ መሣሪያ ድብደባ በመፈፀም በአብያተ ክርስቲያናትና በአርሶ አደሮች ሰብል ላይ ውድመት ማድረሱ ተነግሯል።
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ክፍለጦር አመራሮች የአቅመ ደካሞችን ሰብል ሰብስበዋል ።
በቀን 26/02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት አንስቶ፤ የክ/ጦሩ አመራሮች ከአውደውጊያ ጎን ለጎን የማህበረሰቡን ሰብል በመሰብሰብ አጋርነታቸውን አሳይተዋል ።
የክፍለጦሩ የስታፋ አመራሮች እና የሰራዊቱ አባላት በሸዋ በረኀት ወረዳ ፥ ሀገረማሪያም ከሰም ወረዳ እና ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የአቅመ ደካሞችን ሰብል በመሰብሰብ የህዝብ ልጅ መሆናቸውን አስመስክረዋል ። እንዲሁም ወቅቱ የሰብል ስብሰባ እንደመሆኑ መጠን በየአከባቢው ያሉ ፋኖዎች የአቅመ ደካማዎችን ሰብል በጋራ በመተባበር እንዲሰበስቡ ጥሪ አስተላልፈዋል ።
ከአውደውጊያ ጎን ለጎን የአቅመ ደካሞችን ሰብል በመሰብሰባችን ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የከሰም ክፍለጦር ማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ይታገሱ አሰፋ ተናግረዋል ።
ወቅቱ ሰብል የሚሰበሰብበት ጊዜ በመሆኑ የማህበረሰቡን ሰብል በየተዋረዱ እየሰበሰብን እንገኛለን ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ህግ አገልግልት ክፍል ኮማንደር ነጋሽ አሰፋ ገልፀዋል ።
የህወሓት ቡድን በዛሬው ዕለት የአፋር ክልል ወሰንን ተሻግሮ በመግባት ስድስት መንደሮችን “በጉልበት ተቆጣጥሯል” ሲል የክልሉ መንግስት ወነጀለ። የአፋር ክልል መንግስት ምሽቱን ባወጣው መግለጫ የህወሓት ቡድን ከድርጊቱ “በአስቸኳይ ካልተቆጠበ”፤ ራሱን “ከውጫዊ ጥቃት” የመከላከል ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አስጠንቅቋል።
የአፋር ክልል መንግስት ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው፤ ዛሬ ምሽት አምስት ሰዓት ገደማ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አማካኝነት ባወጣው አጭር መግለጫ ነው። ክልሉ በዚሁ መግለጫው “ጠብ ጫሪ” እና “ከጥፋቱ የማይማረው” ሲል የጠራው የህወሓት ቡድን፤ ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 26፤ 2018 ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ በአፋር አርብቶ አደሮች ላይ “የካባድ መሳሪያ” ተኩስ መክፈቱን አስታውቋል።
ተኩስ የተከፈተባቸው አካባቢዎች በአፋር ክልል፣ ዞን ሁለት፣ መጋሌ ወረዳ፣ ቶንሳ ቀበሌ የሚገኙ አካባቢዎች መሆናቸውንም ክልሉ ገልጿል። የህወሓት ቡድን የአፋር ክልል ወሰንን ተሻግሮ ጥቃት ፈጽሞባቸዋል የተባሉት አካባቢዎች፤ ዋራዓ እና ሚልኪ የሚል መጠሪያ ያላቸው ናቸው።
“የህወሓት ጣብ-ጫሪ ቡድን በቶንሳ ቀበሌ ላይ ተኩስ በሚከፈትበት ወቅት ሰላም ወዳድ የአፋር ሽማግሌዎች እንዲመለሱ ቢማጸኗቸውም፤ ጉጅሌው ግን አሻፈረኝ በማለት ግጭቱን አስከትሏል” ሲል የአፋር ክልል በዚሁ መግለጫው ላይ ወንጅሏል። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከትላንት በስቲያ ባደረጉት ንግግር፤ “በከሃዲነት” እና “በወንጀለኛነት” የፈረጁትን የህወሓት ቡድን “ጉጅሌ” የሚል ስያሜ መስጠታቸው የሚታወስ ነው። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራም ቻናላችን ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
#የስብሰባ_መረጃ_ባህርዳር ‼️
አገዛዙ አርብ ማለትም በቀን 28/02/2018 ዓ.ም በባህርዳር ሙሉ ትምህርት ቤቶችን ዘግቶ መምህራን እና ሰራተኞች ላይ የተለመደ ለሀጩን ሊያዝረከርክ ዝግጅቱን ጨርሶ ተፈፃሚ እንዲደረግ ለትምህርት ቤት አመራሮች ትዛዝ የሰጠ ሲሆን በሱፐርቫይዘሮች አማካኝነት የተላለፈው መልዕክት ከታች ተያይዟል
👇👇👇👇👇👇👇
ለሁሉም የግልና የመንግስት ት/ቤት መምህራን ከኬጅ_8ኛ ክፍል ሠራተኞች በ28/2/2018 ዓ,ም በመምሪያ ደረጃ ስብሰባ /መድረክ / ስላለ/ ሁሉም በሚዘጋጀው መድረክ እንድትገኙ ከወዲሁ እያሳወቅን በዕለቱ ትምህርት የለም ዝግ ነው ::ጥሪ መጠራቱን ፊርማ ተዘጋጅቶ እንዲፈርሙ ይደረግ በማይገኙት ላይ ሃላፊነቱን ት/ቤቱ ይወስዳል የስብሰባ ቦታ ስዓት ወደፊት ይገለፃል !!
ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል በማለት የንስር አማራ ምንጮች መረጃው አናብስቱ ይጠቀምበት ዘንድ አስተላልፈዋል ።
26/ዐ2/2018 ዓ.ም
"እናቴን አምጡ" የሕፃኑ ታምራት አውግቸው ተማፅኖ።
EOTCMK TV ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም
እናትና አባት ከተጋቡ ወደ አስር ዓመት ገደማ እንዳስቆጠሩ የቅርቦቻቸው ይናገራሉ።
ኑሯቸው በምሥራቅ አርሲ ዞን በጉና ወረዳ ኖኖ ጃዌ ቀበሌ ነውና እንደ ሀገር እና አካበቢ ማኅበረሰብ ሁሉ የዕለት ጉርስ የዓመት ቀለብ የሚያገኙት ደረቁን መሬት አለስልሰው ፣ ከብቶች አርብተው ባገኙት ጥሪት ነው። የሕጻን ታምራት አውጋቸው ወላጆች።
የዚህ ብላቴና ቤተሰቦች በክርስትና ሕይወታቸውም ቢሆን ቤተክርስቲያንን ሳይሱሙና የፈጠራቸውን ሳይማልዱ ውለው አያድሩም። እንደ ቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መጾም ፣ መጸለይና ማስቀደስ ግዴታ መሆኑን በተግባር መፈፀማቸውንም መረጃውን ከነገሩን ከቅርቦቻቸው ሰምተናል።
የታምራት ቤተሰቦች በቀያቸው በነበሩበት ወቅት በትዳር አንድ ወንድና አንድ ሴት ልጅ አፍርተዋል ።
አበው እንደሚሉት የቀንም ጎዶሎ አለና በምሥራቅ አርሲ ዞን በጉና ወረዳ ኖኖ ጃዌ ቀበሌ በሚገኘው የመኖሪያ ቀያቸው ሐሙስ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ ሀገር ሰላም ቀየው አማን ብለው በተኙበት ሰዓትን ቆጥሮ ለመግደል የሚፋጠን እግርና እጅ ከለሊቱ 6:00 ላይ ወደ ኦርቶዶክሳዉያኑ ቤት አመራ።
ሞት በራቸውን ያንኳኳው የታምራት አውግቸው ቤተሰቦችና ጎረቤቶቻቸው በድቅድቅ ሌሊት እየተገፈተሩ ከቤታቸው በማስወጣት ከደጃፋቸው በሚገኘው ሜዳ ላይ ደርድረው አንበረከኳቸው።
በወቅቱ ብላቴናው ከእናቱ ጀርባ ላይ እንደነበር ያዩ ምስክሮች ነግረውናል።
ታዲያ የታምራት እናት እና አስራ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች በዘነበባቸው ተኩስ ሕይወታቸውን ማትረፍ ሳይችሉ እስከ ወዲያኛው ላይመለሱ አሸለቡ።
በሰዓቱ ሕፃን ታምራት ከመሬት ወድቃ የእናትነት ትንፋሿ ሲርቀው እናቱ ከወደቀችበት እንድትነሳ ይማፀናት ጀመር።
ይህንን የሰሙ እነዛ የታጠቁ ኃይሎች ልጅነቱ ሳያሳሳቸው ወገኖቹ የቀመሱትን ጥይት እነሆ ሲሉ ተኮሱበት።
ሕፃን ታምራት አውግቸውም በደረሰበት ጉዳት መቋቋም አቅቶት ከእናትና ከብዙ ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን አጠገብ ወደቀ።
በሰዓቱ የሚደርስላቸው ባለመኖሩ የብላቴናው እግር ላይ ያሉት የደም ስሮች ተፈጥሯዊ የደም መዘዋወራቸውን ለማከናወን ተሳናቸው።
አይነጋ የለምና በአስክሬን መሀል ራሳቸውን ከአገኙት መካከል አንዲት የ8 ዓመት ታዳጊ የሰው ያለህ እያለች ትጣራ ጀመር።
አካባቢ ከማታ ይልቅ በጥቂቱም ቀን የተሻለ ነውና ሕፃናቱን ወደ ሕክምና፣ ቤተሰቦቻቸውን ደግሞ አፈር ለማቅመስ በአካባቢው ወደ ሚገኘው አጥቢያ አመሩ።
በሕፃናቱ ላይ በደረሰው ከባድ ጉዳት አዳማ ለሕክምና ቢመጡም የታዳጊ ታምራት ጉዳት እጅጉን በማየሉ ወላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ሊመጣ ችሏል።
ሕፃን ታምራት ከእግሩ ባሻገር ሌሎች የሰውነቱ አካላት ላይ ጉዳት ስለደረሰበት የሕክምና እርዳታ ሊደረግለት ችሏል።
ይሁን እንጂ የደረሰበት ጉዳት ከባድ በመሆኑ በሆስፒታሉ የሕክምና ባለ ሙያዎች ትእዛዝ መሰረት ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:00 አንድ እግሩ ሊቆረጥ ችሏል።
ይህ ብላቴና ከእግሩ መቆረጥ በተጨማሪ በቤተሰቡ ናፍቆት እየተሰቃየ ይገኛል ሲሉ አስታማሚዎቹ ይናገራሉ።
የሕመም ስቃዩን የአልቻለው ይህ ታዳጊ በአሁኑ ወቅትም "እናቴን አምጡ እያለ" ክፉኛ እንደሚያለቅስና ከፍተኛ ስነ ልቡናዊ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
የሕፃን ታምራት ቤተሰቦች እና ሌሎች ኦርቶዶክሳውያን ቤተክርስቲያንን ብለው በአካባቢው ባለመራቃቸው ይህ አይነት አሰቃቂ ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚሉት አስታማሚዎቹ ከጥቃቱ የተረፉትን ሕፃናት ልጆችን የመንከባከብ እና የማሳደግ ኃላፊነት የሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ነው ይላሉ።
በተለይም ለብላቴናው ሰው ሰራሽ እግር ፣ ወደ ጤናው ሲመለስ ትምህርትና መሰል እገዛዎችን ከቤተክርስቲያንና ከምእመናን እንጠብቃለን ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በተመሳሳይ የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው የ8 ዓመቷ ታዳጊ የእነ ታምራት የቅርብ ጎረቤት ስትሆን በአሁኑ ወቅት በአዳማ ሕክምና እየተከታተለች ትገኛለች።
በአርሲ ሀገረ ስብከት በርካታ ኦርቶዶክሳዉያን በጭንቅ ውስጥ የሚገኙ በመሆናቸው ላሉት ልንደርስላቸው ለተጎዱት ድጋፍ ልናደርግላቸው ይገባል መልእክታቸው ነው።
የታምራት አባት ከዚያች ምሽት በኋላ የት እንደሚገኙ ማወቅ እንደማይቻል እና እህቱ ደግሞ ቤተሰብ ጋር መሆኗን ሰምተናል።
©ማኅበረ ቅዱሳን
#የጠላት_እንቅስቃሴ_መረጃ‼️
ፓዊ ያለው ጡት ቆራጩ የአገዛዙ ኃይል ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ወደ እንጅባራ .ኮሶበር መስመር ተንቀሳቅሶ መገንጠያ ደርሷል የወገን ኃይል አስፈላጊውን ክትትልና ጥንቃቄ ያድርግ ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል‼️
26/ዐ2/2018 ዓ.ም
+7
..............የአደረጃጀት ዜና !! ...........
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር የ99ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ።
በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።
ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ።
የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ፣ በአርበኛ ስሜነህ ሙላቱ አስተባባሪነት ተጠናቋል ።
አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!
የአርሲው ጭፍጨፋ
🛑እነዚህ አርሲ የተጨፈጨፉ አማሮች ምናቸው ነው ኦሮሞ የሚመስለው?
🛑 አርሲ ውስጥ የኦሮሞ ክርስቲያን ከየት መጣ?
🛑 የተካሄደው የኦርቶዶክስ ጭፍጨፋ ሳይሆን የአማሮች ጭፍጨፋ ነው!!
"ኢትዮጲያ አትፈርስም" የሚለው ተምኔታዊ አስተሳሰብ የፈሪዎች እና የሰነፎች ፓለቲካ ነው።
ብልፅግና ፓርቲ እና አስተሳሰቡ ኢትዮጲያ ከተሰራችበት ስሪት አንፃር ስናየው በፍፁም ሃገር አፍራሺ ነው።
በመሰረታዊነት ኢትዮጲያ ለዘመናት የእርስ በእርስ ግጭት በነበረባት ጊዜ እንኳ የማዕከላዊ መንግስቱ ደካማ አልነበረም!!
ሰዎች ኢትዮጲያ አትፈርስም ስንት ነገር ተሻግረን እዚህ የደረስን ሃገር ነን የሚል አጉል ጨዋታ ሲጫወቱ እንሰማለን።
እውነታው ግን ኢትዮጲያ በአብይ አህመድ ዘረኛ እና ጠቅላይ አገዛዝ ወደ ብተና ጫፍ እየሄደች መሆኑ ነው።
በብልፅግና አስተሳሰብ እና ርዕዮተ ዓለም ሃገር ማለት በድህነት፣በእርስ በእርስ ጦርነት፣በስደት እና በዘረኝነት የብሔር እና ብሔረሰብ ህዝቦች ላይ የሚደረሰው ሰው ሰራሺ እና መዋቅራዊ ግፍ ስኬት መሆኑን አይተናል።
ስለዚህ ብልፅግናን እንደ ህዝብ መዋጋት የማንችል እና በጋራ ቆመን የሃገሪቱን ህልውና ማስጠበቅ ካልተቻለ እመኑኝ ኢትዮጲያ እንደ ሃገር የመፍረስ አደጋ ተጋርጦባታል።
ብልፅግና ስለ ሰላም የሚሰብከው በሰፋቸው መሪዎች እና ልሂቃን ስም እንጅ በመላው ኢትዮጲያ ውስጥ፣በጎረቤት ሃገራት እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር አገዛዙ ቅጥረኛ እና ደንታቢስ የአላዋቂዎች ስብስብ መሆኑ የተረጋገጠ ነው።
"ኢትዮጲያ አትፈርስም " የሚለው ተምኔታዊ ሃሳብ የፈሪዎች እና የሰነፎች ፓለቲካ ነው።
በሰላም እጦት፣በኢኮኖሚ ድቀት እና በራስ ጠልነት የተጠቃው ህዝብ በመጨረሻም አዳኙ ማን ይሆን ትላላችሁ??
ስለሆነም ሃገር ወደለየለት ፍራስራሺነት ከመግባቷ በፊት ኢትዮጲያውያን ከአማራ ፋኖ እና አገዛዙ ላይ ነፍጥ ካነሱ ሁሉ እንዲትቆሙ አደራ እላለሁ።
ሃገሩን ከባዕዳን በሚገኘው ብድር እና መሳሪያ ወገኑን የሚጨፍጭፍ መንግስት እንደት ህዝባዊ ቅቡልነት ኖሮት ሃገረ -መንግስቱን ሊያስቀጥል ይችላል??
የህዝብን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ያነሱ ሁሉ ባዳ እና ባንዳ በሚል አድስ ትርክት በየሰፈሩ የሚጮኸው የብልፅግና ዕጅ አስታጣቢ በየት ሞራሉ ነው የአማራ ፋኖን ሰራዊት የሚከሰው??
አብይ አህመድ እኮ የኢትዮጲያን ብሔራዊ ጥቅም እና ሉአላዊ ግዛት አሳልፎ የሰጠ ባንዳ ነው።
ታዲያ በምን ሞራሉ እና ፋኖን እና ትግሉን ሊያሸንፍ የሚችለው??
ቅጥረኝነትን እና ተገዥነት ከአሜሪካ እስከ ግብፅ እና አረብ ኤምሬት ሃገሩን ለባዕዳን ሲሰልል የነበረ ሰላቶ እንደት የህዝብ ልጆቹን እውነተኛ ትግል መቀልበስ ይችላል።
ስለሆነም ትግላችን እየፈረሰች ባለችው ሃገር ፍርስራሺ ላይ ህልውናችንን ለማትረፍ ጭምር ነው።
"ሃገሬ በሰማይ ነው" ከሚሉት ወገን አይደለንም!!
አባቶቻችን እና ቀደምቶቻችን ሃገር ሲሰራ እና ሲገነባ እንደት እንደነበር አስተምውን አልፈዋል።
እኛ ልጆቹ ደግሞ በዘረኛ እና ጠቅላይ አገዛዝ ሃገር የብተናዋ ጫፍ ላይ ስለደረሰች ደም ገብረን፣አጥንት ከስክሰን ወደ ቀደመ ክብሯ ለመመለስ የጀመርነው የአማራ ህዝብ እና የልጆቹ ትግል ያሸንፋል እንላለን።
ዓላማችን ብሔራዊ ንቃት ያለው ማህበረሰብ በመገንባት የህዝብንና እና የሃገርን ህልውና መታደግ ከሚችሉት ጋር በመቆም ሃገረ መንግስቱን ማስቀጠል ነው።
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
ዝንታለም አማራ
ወይራው አማራ
ጥቅምት 26-02-2018
