es
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
2 944
Suscriptores
-1024 horas
+77 días
+37930 días
Archivo de publicaciones
የአገዛዙ ፓራ ኮማንዶ ሚሊሻ የነበሩት ወደ ቀድሞ ቤታቸው አማራ ህዝብ እየተመለሱ ነው!!! ግንቦት 13 /2018 ዓ.ም አፋፋብን 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል በአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎ
+2
የአገዛዙ ፓራ ኮማንዶ ሚሊሻ የነበሩት ወደ ቀድሞ ቤታቸው አማራ ህዝብ እየተመለሱ ነው!!! ግንቦት 13 /2018 ዓ.ም አፋፋብን 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል በአፋብን ምዕ/አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 24ኛ ክ/ጦር ከሚያስተዳድራቸው ወረዳዎች አንዷ ከሆነችው ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ቁይ ከተማ መሽጎ ከሚገኘው የአረመኔው አገዛዙ ሰራዊት ጋሻ ጃግሬ በመሆን ሲያገለግል የነበረው  በደም አማራ የሆነ በግብር የገዳዩ አብይ አህመድ ሎሌ የነበረው #ፓራ_ኮማንዶ_ደሴ_አዳም  የተባለ   እስከ አሁን ከገዳይ ጎን ቆሜ  የህዝባችንን መከራ ና ስቃይ ማራዘሜ ቆጭቶኛል ከእንግዲህ ግን  የአማራን ህዝብ ከሚጨፈጭፍ ሰረዓት ጋራ ቀመቆም  የራሳችንን  ህዝብ አልጨፈጭፍም የበደልኩትን ህዝብም ይቅርታ በመጠየቅ በቀጣይ በፋኖ አደረጃጀት ሆኜ ለመካስ ዝግጁ ነኝ በማለት በታላቅ አማራዊ ወኔ የደባይ ጮቄ ሻለቃን በክብር ተቀላቅለዋል!!! ወጣቱ ፋኖን ሲቀላቀል  አንዱን ሚሊሻ ከመሬት በመቀላቀል በመግደል ሁለት የአገዛዙ ሚሊሻዎችን ገረዶችን በማቁሰል ደባይ ጮቄ ሻለቃን በክብር ተቀላቅሏል። ደባይ ጮቄ መቶአለቃ አዳነ ሻለቃ  ጠላትን ስቦ በማስከዳትም ይሆን በመምታት እና የጠላትን ኃይል በማፈራረስ በኩል በርካታ ስራዎችን እየሰራች ሲሆን በዛሬው ዕለትም በጀግንነት ለተቀላቀለው  አባልም  የክብር አቀባበል አድርጋለች!!! አዲስ ትውልድ አዲስ ተስፋ አዲስ አስተሳሰብ !!! ድል ለአማራ ፋኖ!!!!!! አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር  24ኛ ክ/ጦር ሚዲያ ክፍል ‎

በአመራር ጥበብ እና ወታደራዊ ሳይንስ ዙርያ ሲካሄዱ የቆዩ ስልጠናዎች በስኬት ተጠናቀቁ። ========================= አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ስራ አስፈጻሚ ፣ በስሩ ካሉ የክፍለ ጦር ስራ አስፈጻሚ አመራሮች እና የብርጌድ አመራሮች ጋር በአመራርነት ጥበብና ወታደራዊ ሳይንስ ዙርያ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል። ስልጠናውን የሰጡት ኮረኔል ሙላቴ ሲሳይ የአመራርነት ጥበብ (The Art of Leadership) ማለት ሰዎችን በአንድ የጋራ ራዕይ ዙሪያ በማሰባሰብ፣ በፈቃደኝነትና በታማኝነት እንዲከተሉ የማድረግ እና የማይቻሉ የሚመስሉ ግቦችን በተግባር የመለወጥ የማሳመን፣ የመቀስቀስና የስነ-ልቦና የበላይነት ክህሎት ነው ብለዋል። የአመራርነት  "ሳይንስ" ብቻ ሳይሆን "ጥበብ" የተባለበት ዋና ምክንያት በጽንሰ-ሃሳብ ወይም በደብተር ላይ ባሉ ህጎች ብቻ የማይገዛ  ነው ያሉት ኮረኔል ሙላቴ  ከተለዋዋጭ የሰው ባህሪ ፣ ስሜት እና ሁኔታዎች ጋር አብሮ የሚቀያየር በመሆኑ ነው። ሳይንስ "ምን መደረግ አለበት?" የሚለውን ሲያጠና፣ ጥበብ ግን "እንዴት መደረግ አለበት? ሰዎችንስ እንዴት ማስከተል ይቻላል?" የሚለውን በተግባር ይፈታል ሲሉም አክለዋለል ። ስለሆነም በየደረጃው ያለው  አመራርም የአመራርን ጥበብ ከወታደራዊ ሳይንስ ጋር አጣምሮ የአማራ ህዝብ ከተደቀነበት የህልውና አደጋ  በአንድነት ፣ በወንድማማችነትና  በእውቀት መምራት ጊዜ እማይሰጠው መሆኑን  ያስረዱት ኮረኔሉ ወታደራዊ መረጃዎች ፣ የውጊያ መመሪያ እና ዘመኑን የዋጀ የአሰራዊት አደረጃጀት እንዴት መፍጠር እንደሚቻል ለተከታታይ ቀናት በሰጡት  የስልጠና  አስምረውበታል። ስልጠናውም ለታችኞቹ አደረጃጀቶች  ቀጣይታይነት ያለው ቢሆንም በደረጃው የተሰጠው ስልጠና  በትልቅ ወንድማማችነትና ፍቅር የተሞላ መከባበር ስጦታዎችን በመለዋወጥ በክብር ተፈጽሟል። ድል ለአማራ ህዝብ !!! ድል ለአማራ ፋኖ !!! አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ 206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ቃል አቀባይ ክፍል!!!

ሰበር ዜና! በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ  የ102ኛ ኮር በአገዛዙ ምርጫ አስፈፃሚዎች እንድሁም በፖሊስ መኮነኖችና የፀጥታ አካላት ላይ እርምጃ ወሰደ። የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክፍለጦር 1ኛና 2ኛ ሻለቃ ቃኝ በጋራ በመሆን ግንቦት 12/ 2018ዓ/ም የተኩለሽ ከተማን ህዝብ በግዳጅና በድብደባ የምርጫ ካርድ በመስጠት ላይ የነበረውን ራሱን ጥምር ጦር በማትለት የሚጠራውን ህዝብን የማይወክል የአገዛዙ ሚሊሻና ፖሊስ እንድሁም የስርዓቱ አገልጋይ  የመከላከያ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፀመ። የ12ኛ ክፍለጦር 1ኛና 2ኛ ሻለቃ ቃኝ የምረጫ ካርድና አመራር አጅቦ ከተኩለሽ ከተማ ወደ ቆቦ ከተማ በመጓዝ ላይ በነበረው የአገዛዙ ቅልብ ወታደር በተለምዶ አጠራር ዝሀ ውሀ ድልድይ በመባል በሚታወቀው አካባቢ በወሰዱት የደፈጣ ጥቃት በራያ ቆቦ ወረዳ ተኩለሽ ከተማ የፖሊስ አዛዥ የነበረ መሰለ አባዩን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፀጥታ አካላት ተደመሰሱ። የጥቃቱ ምክኒያት በሰሞኑ በአማራ አርሶ አደርና የከተማ ነዋሪ  በየ መንገዱና ቤት ለቤት በመዞር የምርጫ ካርድ እንዲያወጡ ሲያስገዲድ የነበረ የጥምር ጦሩ አካል ላይ የ102ኛ ኮር የ12ኛ ክፍለጦር 1ኛና 2ኛ ሻለቃ ቃኝ ከህይወት መሳዋትነት በተጨማሪ ከባድና ቀላል ቁስለኛ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሶበታል። ተራማጅ ያልሆነውና ቆሞ ቀሩ የብልፅግና አገዛዝ  ከሐምሌ 28/2015ዓ/ም ጀምሮ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ  በሐይል የአማራ ፋኖን በ14 ቀናት ውስጥ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ሰበብ በአማራ ህዝብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለውን ግፍ  የፈፀመ ቢሆንም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ህዝቡን ከጥቃት በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት ለተከታታይ 3 ዓመት በክልሉ ከ90% በላይ አካባቢዎችን በአሸናፊነት ተቆጣጥሮ ይገኛል ። የአማራን ህዝብ በሀይል ለማንበርከክና ትጥቅ ለማስፈታት በተሳሳተ መንገድ የመጣው የብልፅግና አገዛዝ  ከትናንቱ ስህተት ሳይማር ያለ ህዝብ ፍላጎት አለም አድርጎት የማያቀውን  በጉልበት ጦርነትና የጨረባ ምርጫን በተመሳሳይ ሰዓት ለማካሔድ እየቋመጠ ቢሆንም የአማራ ልጅ ፋኖ የማይናወጥ አቋም በመውሰድ በክልሉ ምንም አይነት የአምባገነኖችና ጨፍጫፊዎች ምርጫ እንዳይካሔድ እርምጃ በመውሰድ ላይ ነው። ከማንም ጋር ሰላም መፍጠር የማይፈልገወ አገዛዙ በመላው ሀገሪቱ የጦርነት አዙሪት በመለኮስ በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣በቤንሻንጉልና በአፋር ክልል እንድሁም ከጎረቤት ኤርትራና ሱዳን ጋር የጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ያልተረጋጋች ሀገር ለትውልድ በመፍጠር ዜጎች በኑሮ ውድነት፣ በረሐብና ቸነፈር በስራ አጥነትና ጉስቁልና በከፍተኛ ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸዋል ። በመጨረሻም በሁለት ሳምንታት ውስጥ ትጥቅ አስፈታለሁ ብሎ ወደ አማራ ክልል የገባው የአብይ አህመድ የግል ወታደር ላይ ጀግናው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በየ አውደ ውጊያው የጥላትን እንቅስቃሴ በማንበርከክና የሀይል የበላይነት በመውሰድ ከነፍስ ወከፍ መሳሪያ እስከ ዙ-23ና ሞርተር 120 ድረስ በመማረክና በመታጠቅ አለምን ጉድ አሰኝቷል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ የ102ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ግንቦት 13/2018 ዓ.ም

የበረራው ንጉስ ጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር በሬማ ከተማ በፈፀመው ልዩ ሰርጂካል ኦፕሬሽን ሰባት የሚሊሻ አባላትን በመማረክ ቀሪዎች ላይ እርምጃ ሲዎስድ፣ የአፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር አሃዶች በአገዛዙ ታማኝ አገልጋይ ሚሊሾች ላይ ያነጣጠረ የተሳካ ጥቃት ፈፀሙ። ግንቦት 13/2018 ዓ.ም የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአሳምነው ዕዝ አሃዶች በሁሉም የሸዋ ቀጠናዎች በአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ላይ የተጠናከረ ዘመቻ እያካሔዱ ሲሆን በሸዋ መርሀቤቴ አውራጃ በሬማ ከተማ በርካታ የአገዛዙ ጥምር ጦር ላይ በአፄ አምደ ፅዮን ኮር በጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር አማካኝነት ከለሊቱ 7:00 ላይ በተፈፀመ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን ሰባት (7) የሚሊሻ አባላት ከከተማዋ አደባባይ ሲማረኩ በውል የማይታወቁ ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን ኮሩ በምስል አስደግፎ በላከው የአውደ ግንባር መረጃ ገልጿል። ጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር በሰራው ልዩ የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን የተደናገጠው አገዛዝ ከሚዳና አካባቢው የተወጣጡ ዘጠኝ (9) የሚሊሻ አባላት ዛሬ ረፋዱን ጨምሮ ወደ ሰራዊታችን ተቀላቅለዋል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ የአፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር የ7ለ70 ክፍለ ጦር የደመላሽ ሻለቃ ቃኚዎች ዛሬም እንደትላንቱ የጦር ወንጀለኛው ወንበር አስጠባቂ ሚሊሾች ላይ እየወሰዱ ያሉትን እርምጃ አጠናክረው መቀጠላቸውን ኮሩ አስታወቀ። በኤፍራታና ግድም ወረዳ በፈረድዉሀ ቀበሌ በመግባት የአገዛዙ ታማኝ አገልጋይ በሆነው የሚሊሻ ጠርናፊ አቶ ነጋሽ መኮንን ጨምሮ ሌሎች ሆድ አደር ሚሊሾች ላይ የማያዳግም እርምጃ ሲወስዱ ቀሪው የጠላት ኃይል መሳሪያውን በምርኮ አስረክቦ እግሬ አውጪኝ በማለት ወደ አጣዬ ከተማ መፈርጠጡን ኮሩ በመረጃው ገልጿል። በተመሳሳይ የድል ዜና የኮሩ አካል የሆኑት አናብስቶቹ የናደው ክፍለጦር የፋኖ ሰራዊት በፈፀሙት ጥቃት የብልፅግናው ታማኝ አገልጋይ፣ የህዳር አህያ ሆኖ ሲጫን በነበረ እራሱን የሰላም አስከባሪ ብሎ የሚጠራው የህዝባችን ፀረ-ሰላም አባል ላይ የማያዳግም ርምጃ በመውሰድ ግለሰቡ ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀምበት የነበረውን የጦር መሳሪያ ገቢ ማድረጉን የኮሩ የግንባር ዘጋቢ ገልጿል። በመርሓቤቴ ወረዳ ፌጥራ ከተማ ከጠዋቱ 01:30 ላይ የአፄ ዘርያዕቆብ ፩ኛ ኮር ናደው ክፍለ ጦር የፋኖ ሰራዊት በፈፀሙት የከተማ ውስጥ ኦፕሬሽን የተደናገጠው አገዛዝ እንደተለመደው የፈሪ በትሩን ወደ ሲቪሊያን በማዞር ከፍተኛ ድብደባ የፈፀመ ሲሆን በፋኖ ቤተሰቦች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስሩን አጠናክሮ መቀጠሉን ዕዙ በረጃው አረጋግጧል። ''ክብር ለትግሉ ሰማዕታት'' ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

የግንቦት 12ቱ የጀግንነት ታሪክ፤ አርበኛ ዘመነ ካሴ እና አጃቢዎቹ በጠላት ላይ የፈጸሙት ታላቅ የጦር ሜዳ ጀብዱ። ​የራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ ታላቅ ወንድም አርበኛ ገደፋው ካሴ፣ በግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ማለዳ በጠላት ኃይል ላይ የተፈጸመውን ታሪካዊና አስደናቂ ተጋድሎ ለጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደስላሴ በሰጠው ቃለ-መጠይቅ አብራርቷል። በወቅቱ በነበረው ውጊያ፣ አርበኛ ዘመነ ካሴና ጥቂት የትግል ጓዶቹ ጠላትን በድፍረትና በወታደራዊ ብልሃት በመቋቋም፣ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት ድረስ የዘለቀውን የኃይል ሚዛን ያልጠበቀ ጦርነት በአሸናፊነት ማጠናቀቃቸውን ገልጿል። አርበኛ ገደፋው እንደሚለው፣ ዘመነ ካሴ በጦር ሜዳው የነበረው ሚና ከወንድምነት አልፎ እንደ የትግል ጓድ፣ የቡድን አሰላለፍ መሪና የጠላትን እንቅስቃሴ በአርቆ አስተዋይነት የሚገመግም ወታደራዊ መሪ መሆኑን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳ ስምሪት እየሰጠ ልጆቹን ለድል እንዳበቃ ተናግሯል። ​የጦርነቱ ሂደት በእጅጉ አሳሳቢ የነበረ ቢሆንም፣ የእናታቸው ጣልቃ ገብነትና በተለይም የንብ ቀፎዎቹን ማናወጣቸው የጠላትን ኃይል በማወክ ወሳኝ ሚና መጫወቱን አርበኛው በግልጽ አስታውሷል። አርበኛ ገደፋው፣ ንብረቱ ካሴ ከኋላ በመክፈት የጀመረው ተኩስ የጠላትን ኃይል በማደናገሩ ፋኖዎች ለመንቀሳቀስ ዕድል እንዳገኙ፣ በተለይም ኮማንዶ በሪሁን እና ሌሎች ጓዶቻቸው በከፈሉት መስዋዕትነት የተቆረጠውን የብሬን ተኳሽ ኮማንዶ ሰለሞንን ከአደገኛ የጠላት ከበባ ማውጣታቸው የውጊያውን ድል አፋጥኖታል። አርበኛው አክሎም፣ በወቅቱ ፋኖዎች የነበራቸው ጥይት እጅግ ውስን (እሱ ራሱ 69 ጥይት ብቻ የያዘ) መሆኑን፣ ነገር ግን ከጠላት እየተቀበሉና እየቀሙ በመታገል እስከ 4 ሰዓት መቆየታቸውንና ጠላት የሽንፈቱን መራር ጽዋ ጠጥቶና ሬሳውን ሰብስቦ መፈርጠጡን በኩራት ገልጿል። አርበኛ ገደፋው ንብረቱ ካሴና ንቦች የፈጸሙት ድርጊት የጦርነቱን 70 በመቶ ድል እንደረዱት በማረጋገጥ፣ ዘመነ ካሴ የነበረው የመሪነት ብቃት፣ እጅግ አደገኛ በነበረው የጨበጣ ፍልሚያ ውስጥ የነበረው የላቀ ፍርሃት አልባነትና ለአላማው ያለው ጥልቅ ቁርጠኝነት ለአማራ ሕዝብ የሚታወስ የታሪክ ምዕራፍ እንደሆነ አስታውሷል። ​

+3
በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በ208ኛ ኮር ቀጠና የተሰነዘረው የድሮን ጥቃት ሙከራ ሙሉ በሙሉ ከሸፈ። ​የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የጎንደር ጠቅላይ ግዛት 208ኛ ኮር አመራሮች እንዳስታወቁት፣ አገዛዙ ዛሬ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከዳባት ወደ አጅሬ በሚወስደው መንገድ ላይ "13" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የድሮን ጥቃት ሙከራ አድርጓል። አገዛዙ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬና በውድ ዶላር ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (UAE) ካስመጣቸው የጦር መሣሪያዎች መካከል አንዱን በመጠቀም የኮሩን አመራሮችና አባላት ታርጌት በማድረግ ጥቃቱን ቢሰነዝርም፣ የጠላት እቅድ ሙሉ በሙሉ መክሸፉ ተረጋግጧል። ለአማራ ሕዝብ ደህንነት ምንም ዓይነት ደንታ የሌለው ይህ አረመኔ ሥርዓት፣ ንጹኃን ገበሬዎች በሚኖሩበት አካባቢ የድሮን ጥቃት ለመፈጸም የሞከረው ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጥላቻ በግልጽ የሚያሳይ ነው። ለማጥቃት ከተሰማሩት ሁለት ድሮኖች መካከል አንደኛው ጥቃት ቢሰነዝርም በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ የቀረ ሲሆን፣ ሁለተኛው ድሮን ግን ሳይሳካለት ቀርቶ የከሸፈ መሆኑ ታውቋል። አገዛዙ ይህንን የመሰለ አርቲፊሻል ውጊያ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚጠቀምበት በመሆኑ፣ መላው የፋኖ አባላትና የጎንደር ህዝብ በጠላት ሴራ ሳይደናገጡ የነጻነት ተጋድሎውን በጽናት እንዲቀጥሉ የ208ኛ ኮር አመራሮች ጠንካራ የማሳሰቢያ መልዕክታቸውን በፍነተ አማራ ሚዲያ መልክታቸውን አስተላልፈዋል። ​

206ኛ ኮር በተለያዩ አውደ ውጊያዎችን በማድረግ ድል መቀናጀቱን ቀጥሏል። ግምቦት 12/2018 ዓ.ም :================================== በ206ኛ ኮር ቀጠና በርካታ ሰራዊት በማ
+2
206ኛ ኮር በተለያዩ አውደ ውጊያዎችን በማድረግ ድል መቀናጀቱን ቀጥሏል። ግምቦት 12/2018 ዓ.ም :================================== በ206ኛ ኮር ቀጠና በርካታ ሰራዊት በማስከተል በመድፍ የታገዘ ውጊያ የከፈተውን ጠላት የተናነቀው 206ኛ ኮር በትናትናው እለት በጎዛምን ቀዝቀዝ እና በስናን ደብረ ዘይት አካባቢዎች እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት በመፋለም ድሎችን አስመዝግቧል። በዛሬው እለት የ206ኛ ኮር 14ኛ ክ/ጦር የቀስተ ደመና ሻለቃ በማርዘነብ የመሸገውን ጠላት አነጋጉ ላይ 11:30 ከበባ ውስጥ በማስገባት የጠላትን ቅስም ሰብራዋለች። ጠላትን በተኛበት በምሽጉ አውደ ውጊያ በመክፈት ከ50 በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ መቶ አለቃ ተሾመና መቶ አለቃ ከተወገዱት መካከል ይገኙበታል። 9 ክላሽ 4 መገናኛ ራዲዮ ፣ወታደራዊ ቦርሳና የወገብ ትጥቆች ከጠላት ተማርኳል። የክላሽ ጥይትና የብሬን ሸንሸል ከነ ጥይቱ እንዲሁ ገቢ ሁኗል። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር ዛሬም በድል ደምቆ ውሏል። ቀን 12/9/2018 ዓ/ም ትናት ግንቦት 11/2018 ዓ/ም የነበረው ውጊያ የማታማታ 1:00 ሰአት አካባቢ የክፍለጦሩ ቃኝዎችና የሻለቃ 1 አባላት ደረፎ ከተማው ላይ በጨበጣ ውጊያ ጠላት ሙትና ቁስለኛው ታቅፎ አምሽቷል። ዛሬ ግንቦት 12/2018ዓ/ም መነሻውን ከደብረብረሀን ያደረገው መከላከያ፥ አድማ ብተና ፥ፓሊስና ሚሊሻ ወደ አንኮበር እየመጣ ባለበት ሰአት የሻለቃ 2 ቃኝዎች አንኮበር ወረዳ ቁንዲ ከተማው ላይ በመጠበቅ አንድ ፓትሮል የጠላት ሀይል ላይ በተሰራ ደፈጣ መኪናው ተመቶ  ከጥቅም ወጭ ሲሆን  ሙትና ቁስለኛውን ተዝረክርኳል። በቁራማሪያም የሠፈረውን የጠላት ሀይል በሻለቃ 2ና አባት አርበኛው በጋራ ከበባ አድርገው ሲመቱት በአንኮበር በኩል ደግሞ የሻለቃ 2 አባላትና እንዲሁም የሀራባ ክላስተር አባት አርበኛ መርዳዝማች አብዬ ብርጌድ ኤፍሬም ሻለቃና ደረጀ ሻለቃ ከሻለቃ ሁለት ጋር በጋራ በመሆን አንኮበር ወረዳ ጠምቄ በተባለ ቦታ ላይ የተቀመጠውን አድማ ብተናን ደምስሰውታል ። በአጠቃላይ በጠላት ላይ የደረሰው ጉዳት 👉11 አድማ ብተና የተደመሰሰ 👉ሸበል የተባለ አንድ ፖሊሲ የተደመሰሰ 👉ሃሳብ ምንዳ የተባለ ፖሊሲ የተደመሰሰ 👉ብዛት ያለው የአገዛዙ ሰራዊት ቁስለኛ እንደሆነ ታውቋል። ክብር ለትግሉ ሰምአታት "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት

#የድል_ዜና‼️ የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ በጠላት ላይ ድልን ተቀዳጀ! ================================= ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ገና በጠዋቱ አይነኬ መስሎ መላው አማራን ሲጨፈጭፍ የነበረውን የሽብርተኛውን የብልጽግና ወራሪ ሠራዊት በመድፈርና መንጋጋውን በማራገፍ የአማራን የትጥቅ ትግል ምዕራፍ ጅማሮ በይፋ ያበሰረው የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ከጠላት ጋር ሁለንተናዊ ተጋድሎ በማድረግ በርካታ አንጸባራቂ ድሎችን ሲያስመዘግብ ቆይቷል፤ እያስመዘገበም ይገኛል። በዛሬው ዕለትም በረኸኞቹ ማርዘነብ ከተማ ላይ ወደ ተወሸቀው የጠላት ስብስብ በሌሊት በመግባትና መብረቃዊ ጥቃት በመፈጸም በጠላት ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል። ውጊያው ከሌሊቱ 11:30 የተጀመረ ሲሆን በወገን በኩል ከፍተኛ የሆነ የውጊያ ጥበብና ወታደራዊ አሰላለፍ ብልጫ የታየበት ሲሆን ወታደራዊ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ የወራሪው ሰራዊት የተደመሰሰበት፤ መሳሪያዎች፣ ተተኳሾችና ወታደራዊ ቁሳቁሶች የተማረኩበት ውጊያ ነበር። በውጊያው የተገኙ ድሎች፦ ~ 08 የነፍስ ወከፍ ክላሾች ~ 04 መገናኛ ሬድዮ ከነቻርጀሩና ሪሰርቭ ባትሪው ~ መቶ አለቃ ተሾመ የተባለው የሻለቃዋ መሪ ~ መቶ አለቃ ሽመልስ የተባለ አመራርና ሌሎችም 02 አዋጊዎች ~ በርካታ ቁጥር ያለው ካዝና፣ የእጅ ቦምቦች፣ ወታደራዊ ሻንጣዎች፣ የክላሽና የብሬን ተተኳሾች ~ የብሬን ሸንሸል ~ ከ50+ የጠላት ኃይል ተደምስሷል ~ በርካታ ቁጥር ያለው ቆስሏል ~ በተጨማሪም መኮ እንዳላማውና በላቸው ወርቅነህ የተባሉ ሁለት ባንዳ የብልጽግና አመራሮች ተማርከዋል። ~ በአሁኑ ሰዓትም ጠላት በከፍተኛ ሽብር ውስጥ ይገኛል። ድል ለአማራ ፋኖ! ቀስተ ደመና ሻለቃ

🚨 "አዎ እኔ የቀጥቃጭ ልጅ ነኝ!" አፋብን ምኒሊክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር አርበኛ ሐጂ ኑረዲን አበበ ሐሰን የተሰጠ መግለጫ የብልፅግና ሥርዓት የመጨረሻው የተስፋ መቁረጥ ካርድ የጄኔራል ዘውዱ ሰጣርጌ ነውረኛ ንግግር በራሱ ካቢኔ ላይ ቁጣንና ውርደትን ቀሰቀሰ በብሔርና በሃይማኖት እየገቡ ግጭት ለመፍጠርና ሕዝብን ለማተራመስ ሌት ተቀን ሲያሴሩ የኖሩት የብርሃኑ ጁላ ተላላኪዎችና የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጄኔራሎች በመጨረሻው የተስፋ መቁረጥ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን የሚያሳይ አሳፋሪ ክስተት በሰሞኑን መድረክ ላይ ተስተውሏል። ሰሞኑን በምዕራብ ወሎ በወግድ ወረዳ በመካነ ሰላም (በመሀል ደሳና) እና በጃማ ወረዳዎች በፋኖ ክንድ የደረሰባቸውን ከፍተኛ የሰው ኃይልና የንብረት ኪሳራ እንዲሁም የደረሰባቸውን የሞራልና የስነ-ልቦና ስብራት ተከትሎ የሥርዓቱ መጋቢዎች መሸነፋቸውን በይፋ አረጋግጠዋል። ከእነዚህም መካከል ውድቀቱን መቀበል ያቃተው ነውረኛው ጄኔራል ዘውዱ ሰጣርጌ ከአንድ የሀገር መከላከያ ጄኔራል የማይጠበቅ ፍጹም አፀያፊ አስነዋሪና ግጭት ቀስቃሽ ቃላትን በመናገር ሕዝባዊ ቁጣን ቀስቅሷል። 📌 ነገሩ እንዲህ ነው ጄኔራል ዘውዱ ሰጣርጌ በመካነ ሰላም ወረዳ የራሱን የብልፅግና ካቢኔ ሰብስቦ ባደረገው ንግግር የአማራን ሕዝብና የፋኖን መሪዎች ለማንቋሸሽና ለማሳነስ ሆን ብሎ ያዘጋጀውን የጥላቻ ካርድ መዟል። በንግግሩም፦ "በላይነህ ሰጣርጌ የሚባል የብረት ቀጥቃጭ ልጅ እና አብነው የሚባል በጫካ የኖረ አሁን ዓይኑ ጠፍቶ የማያይ ሽፍታ... የሚንቀሳቀሱት በአህያ ነው" የሚል እጅግ የወረደና ሰብአዊነት የጎደለው አገላለጽ ተጠቅሟል። ይሁን እንጂ ይህ ሆን ተብሎ ለራሳቸው የፖለቲካ ትርፍ የተመዘዘው የመጨረሻው የጥላቻ ካርድ በስብሰባው ላይ የተገኙትን የራሳቸውን የወረዳ ካቢኔ አባላት ጭምር ያስቆጣ ያሳፈረና ያሳቀቀ በመሆኑ ጄኔራሉና አጃቢዎቹ በራሳቸው መድረክ ተዋርደውና አፍረው ተመልሰዋል። 🛠️ የብረት ቀጥቃጭነት (ጥበብ) የነቢያት እንጂ የውርደት ሙያ አይደለም! ይህ ነውረኛ ጄኔራል አሳንሶና አዋርዶ የተናገረው "የብረት ቀጥቃጭነት" (የእደ-ጥበብ) ሙያ እሱ እንዳለው የሚያሳፍር ሳይሆን ፍጹም የሚያኮራ ታላቅ ጥበብ ነው። ይህ ታላቅ የፈጠራ ጥበብ የጥበበኛው ንጉሥ ሰሎሞን እና የክቡር ነብየላህ ዳውድ (ዳዊት) የሚያኮራ የእደ-ጥበብ ሥራ ነው። የሀገርን የጀርባ አጥንት የገነቡና ስልጣኔን የፈጠሩ የጠቢባንና የባለሙያዎች የክብር ማህደር ነው። ሕዝባችን ሊኮራበትና ሊያከብረው የሚገባ እንጂ፣ ተስፋ በቆረጡ ጄኔራሎች አንደበት የሚናቅ አይደለም! በመጨረሻም እኔም የዚህ ታላቅና ክቡር ጥበብ ባለቤት የሆንኩ "የቀጥቃጭ ልጅ ነኝ!" በዚህ ማንነቴና የጥበብ ምንጬ ዘላለማዊ ኩራት ይሰማኛል እንጂ ቅንጣት ታህል አላፍርበትም። ይህ የጄኔራል ዘውዱ ሰጣርጌ የወረደ ንግግር የብልፅግና ሥርዓት ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ተስፋ መቁረጡንና ማክተሚያው መቃረቡን በግልጽ ያረጋገጥንበት ማሳያ ነው። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የለውጥ ኃይሎች ይህንን የተስፋ የቆረጠ የሥርዓቱን የመጨረሻ ሴራ ተረድታችሁ ትግላችሁን እንድታፋጥኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። የብልፅግና የጥላቻ ትረካ በሕዝባችን አንድነት ይከሽፋል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ይረጋገጣል! 🦅 አፋብን ምኒሊክ ዕዝ ከፍተኛ አመራር 💂‍♂️አርበኛ ሐጂ ኑረዲን አበበ ሐሰን ---

#ሰበር_ዜና ‼️ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዓቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር  በልዩ  ተወርዋሪ ቡድን  የተሳካ  ኦፕሬሽን ፈፀመ።           ግንቦት 12/2018 ዓ.ም በናደው ክፍለ ጦር አናብስቶች የከተማ ውስጥ የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰራ። የአገዛዙ አገልጋይ በመሆን መንገድ በመምራት፣ መረጃ በመስጠት ፣የወገን ሀይል ላይ ከጠላት ጎን ተሰልፈው ሲወጉና ሲያስወጉ በነበሩ  ሚሊሾች ላይ ትናንት ምሽት 2:00 ሰአት  በመርሓቤቴ አለም ከተማ 01 ቀበሌ በተለምዶ ስሙ አጠራር ማቁር እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰርቷል።   የአማራን ወጣት በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ ማታ ማታ የተለመደውን የዘረፉ ግብራቸውን ለማድረስ ሮንድ እየዞሩ በነበረበት ሰአት በልዩ የከተማ ኦፕሬሽን ስራ የተካኑት የናድው ክፍለ ጦር የልዩ ኦፕሬሽን ቡድኑ በከተማ ውጊያ የሚሊሻ  አባሎችን ላይመለሱ በመሸኘት ግዳጃቸውን በተሳካ ሁኔታ ተወጥተዋል። የአገዛዙ ሰራዊት በውር ድንብር አሁንም ሰላማዊ ወጣቶችን እያዋከበና ሰብአዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ምንጮቻችን የገለፁልን ቢሆንም ከፍርሃት በመነጨ ስሜት ከተማዋን በተኩስ ሲንጣት ማደሩን አረጋግጠናል። ጀግኖቹ ያለ ምንም ጉዳት ወደ ጦር ሰፈራቸው በመመለስ ለቀጣይ ግዳጅ ዝግታቸው እና በፀረ -አማራ ሀይል ላይ ሁሉ እርምጃቸው እንደሚቀጥል በኩራት ገልፀዋል።   በተሰራው ኦፕሬሽን የተገኜ ድል ▸  2  ሚሊሻ የተደመሰሰ ▸  1 ክላሽ እንኮቭ የተማረከ ▸ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሚሊሻ አባላት የቆሰሉ መኖራቸውን የክ/ጦሩ ሪፖርተር አረጋግጧል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በትላንትናው ዕለት በሸዋ ደራ ቀጠና የአርሶ አደሩን ቤትና ንብረት ያቃጠለው አንባገነን አማራ ጠሉ ብልፅግና በተመሳሳይ የጥፋት እጁ በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አከለል ቀበሌ ቃቂቻ ቦካን ጫካ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በማኅበረሰቡ ተሳትፎ ከ1989ዓ.ም ጀምሮ  ለረጅም ዓመት ተከብሮ የነበረውን ጥቅጥቅ የደን ልማት በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ትላንት ግንቦት 11/2018ዓ.ም ከጠዋቱ  1:15 ሰዓት ላይ በእሳት መቃጠሉን ነዋሪዎች በምሬት ገልፀዋል። የእሳት ቃጠሎውን ያዩ በቀጠናው በአንድ ላይ ተዋደው ተዋልደው የሚኖሩ የአማራና የኦሮሞ ማኅበረሰብ የአካባቢው ነዋሪዎች ድንገተኛ ቃጠሎ የተነሳ መስሏቸው እሳቱን ለማጥፋት በቦታው ላይ በፍጥነት የደረሱ ቢሆንም በስፍራው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት  እንዳባረሯቸው እና እየተቃጠለ ያለው ጥብቅ ደንም በወረዳው አስተዳደር ይሁንታ እንደሆነና "እናንተ አያገባችሁም!" በማለት እንደተባረሩ በከፍተኛ ምሬትና በሀዘን ውስጥ ሆነው መረጃውን ለቀጠናው የኮር ዘጋቢያችን አድርሰዋል።            "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት"   "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!" የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምረያ

#ሰበር_ዜና ‼️ የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ ዘርያዓቆብ ፩ ኮር ናደው ክፍለ ጦር  በልዩ  ተወርዋሪ ቡድን  የተሳካ  ኦፕሬሽን ፈፀመ።           ግንቦት 12/2018 ዓ.ም በናደው ክፍለ ጦር አናብስቶች የከተማ ውስጥ የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰራ። የአገዛዙ አገልጋይ በመሆን መንገድ በመምራት፣ መረጃ በመስጠት ፣የወገን ሀይል ላይ ከጠላት ጎን ተሰልፈው ሲወጉና ሲያስወጉ በነበሩ  ሚሊሾች ላይ ትናንት ምሽት 2:00 ሰአት  በመርሓቤቴ አለም ከተማ 01 ቀበሌ በተለምዶ ስሙ አጠራር ማቁር እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተሳካ ኦፕሬሽን ተሰርቷል።   የአማራን ወጣት በነፃነት እንዳይንቀሳቀስ ማታ ማታ የተለመደውን የዘረፉ ግብራቸውን ለማድረስ ሮንድ እየዞሩ በነበረበት ሰአት በልዩ የከተማ ኦፕሬሽን ስራ የተካኑት የናድው ክፍለ ጦር የልዩ ኦፕሬሽን ቡድኑ በከተማ ውጊያ የሚሊሻ  አባሎችን ላይመለሱ በመሸኘት ግዳጃቸውን በተሳካ ሁኔታ ተወጥተዋል። የአገዛዙ ሰራዊት በውር ድንብር አሁንም ሰላማዊ ወጣቶችን እያዋከበና ሰብአዊ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ምንጮቻችን የገለፁልን ቢሆንም ከፍርሃት በመነጨ ስሜት ከተማዋን በተኩስ ሲንጣት ማደሩን አረጋግጠናል። ጀግኖቹ ያለ ምንም ጉዳት ወደ ጦር ሰፈራቸው በመመለስ ለቀጣይ ግዳጅ ዝግታቸው እና በፀረ -አማራ ሀይል ላይ ሁሉ እርምጃቸው እንደሚቀጥል በኩራት ገልፀዋል።   በተሰራው ኦፕሬሽን የተገኜ ድል ▸  2  ሚሊሻ የተደመሰሰ ▸  1 ክላሽ እንኮቭ የተማረከ ▸ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሚሊሻ አባላት የቆሰሉ መኖራቸውን የክ/ጦሩ ሪፖርተር አረጋግጧል። ይሕ በእንዲሕ እንዳለ በትላንትናው ዕለት በሸዋ ደራ ቀጠና የአርሶ አደሩን ቤትና ንብረት ያቃጠለው አንባገነን አማራ ጠሉ ብልፅግና በተመሳሳይ የጥፋት እጁ በሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አከለል ቀበሌ ቃቂቻ ቦካን ጫካ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በማኅበረሰቡ ተሳትፎ ከ1989ዓ.ም ጀምሮ  ለረጅም ዓመት ተከብሮ የነበረውን ጥቅጥቅ የደን ልማት በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ትላንት ግንቦት 11/2018ዓ.ም ከጠዋቱ  1:15 ሰዓት ላይ በእሳት መቃጠሉን ነዋሪዎች በምሬት ገልፀዋል። የእሳት ቃጠሎውን ያዩ በቀጠናው በአንድ ላይ ተዋደው ተዋልደው የሚኖሩ የአማራና የኦሮሞ ማኅበረሰብ የአካባቢው ነዋሪዎች ድንገተኛ ቃጠሎ የተነሳ መስሏቸው እሳቱን ለማጥፋት በቦታው ላይ በፍጥነት የደረሱ ቢሆንም በስፍራው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ሀይልና የሚሊሻ አባላት  እንዳባረሯቸው እና እየተቃጠለ ያለው ጥብቅ ደንም በወረዳው አስተዳደር ይሁንታ እንደሆነና "እናንተ አያገባችሁም!" በማለት እንደተባረሩ በከፍተኛ ምሬትና በሀዘን ውስጥ ሆነው መረጃውን ለቀጠናው የኮር ዘጋቢያችን አድርሰዋል።            "ክብር ለትግሉ ሰማዕታት"   "ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን !!" የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምረያ