es
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
3 279
Suscriptores
+3924 horas
+3057 días
+69830 días
Archivo de publicaciones
ነፃ በወጡ ቀጠናወች በቢቡኝ ወረዳ ወይንውሀ ከተማ ላይ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሄደ ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም በ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው በቅርቡ ነፃ
+8
ነፃ በወጡ ቀጠናወች በቢቡኝ ወረዳ ወይንውሀ ከተማ ላይ ህዝባዊ ውይይቶች ተካሄደ ➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺➺ ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም በ201ኛ ኮር 54ኛ ክፍለ ጦር በሚያስተዳድራቸው በቅርቡ ነፃ በወጡ ቀጠናወች የኮሩ አመራሮች እና የ54ኛ ክፍለ ጦር የወረዳው ጊዜያዊ መንግስት አመራሮች ህዝባዊ ውይይቶች በማካሄድ የህዝቡን አለኝታነት በሞራል የመገንባት ስራ ተሰርቷል። የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

የአብይ አህመድ ዘራፊ እና ጨፍጫፊ ሰራዊት በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ ውድመት ፈፅሟል። 64ኛ ክ/ጦር ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም የአብይ አህመድ ጨፍጫፊ እና አውዳሚ ሰራዊት በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ ለ16 ወራት መሽጎ የነበረበትን ካንፕ መጋቢት 28/2018 ዓ.ም በ64ኛ ክ/ጦር ወታደራዊ እንቅስቃሴ ስጋት በመግባት ካንፑን በመልቀቅ ብቸና ከተማ የገባ ሲሆን በዚህ ቅፅበት የፋኖ ኃይሎች ጠላት ይጠቀምበት የነበረውን ካንፕ በማሰስ በወይራ ቀበሌ በርካታ ውድመቶች የአገዛዙ ሰራዊት መፈፀሙን በማስረጃ ይዘው ወጥተዋል። የአማራን ህዝብ ከምድር ገፅ አጠፋለሁ ብሎ ጦርነት የከፈተው አማራ ጠሉ የብልጽግና ቅጥረኛ ሰራዊት በወይራ ቀበሌ ለ16 ወራት በቆየበት ወቅት በርካታ ውድመቶችን እና ጥፋቶችን መፈፀሙን በማስረጃ አርጋግጠዋል። አገዛዙ በወይራ ቀበሌ የእርሻ ሰብል መሬቶችን ምሽግ እና የጃምላ መቀበሪያ አድርጓል። በወይራ ቀበሌ የሚገኝ የህብረተሰብ ክፍል በአገዛዙ ኃይሎች ከፍተኛ ስቃይ እና መከራ ተዳረጓል። በቀበሌ የሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ የሚገኙ መገልገያ ማቴሪያሎች ወንበሮችን፣ ጠረቤዛዎችን እና መፃፍትን ጨምሮ ሙሉ የት/ት መገልገያ እቃዎች ተዘረፈዋል ወድመዋል። ትውልዱ ትምህርት ይቀስምበት የነበረው የት/ት ተቋማት በሙሉ ወድመዋል። በወይራ ቀበሌ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍል መኗሪያ ቤታቸው የሚጠቀሙባቸው ቁሳቁሶች በሙሉ ወድመዋል ተዘርፈዋል። ህፃናት፣ እናቶችን፣ በአገዛዙ ሰራዊት ተገደው ተደፍረዋል። ወጣቶች፣ አዛውንቶች፣ የቀበሌ ኖሪዎች በአገዛዙ ሰራዊት በግፍ ተደብድበው ተገድለዋል። በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ የት/ት ተቋማትን ካንፕ አድርጎ ይገኝ የነበረው የአገዛዙ ሰራዊት በርካታ ንብርቶችን ማውደሙን እና በቀበሌው ይኖሩ የነበሩ የማህበረሰብ ክፍል በአገዛዙ ዘራፊ ኃይሎች ሀብት ንብረታቸውን ማዘዝ እንደማይችሉ፣ አገዛዙ ሀብት ንብረታቸውን በየቀኑ እንደሚዘረፍቸው እንደሚታሰሩ እንዲሁም የት/ት ተቋማት መውደማቸውን በቦታው ለተገኘ የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት የሚዲያ ክፍል ኃላፊ በአካል አስረድተዋል። ይህ ከታች የምትመለከቱት ቪዲዩ በእነማይ ወረዳ ወይራ ቀበሌ አነገዛዙ ካንፕ አድርጎ የሚጠቀምበት ት/ቤት እና የአርሶ አደሮች የቤት ዕቃ ሲሆን በአምባ ገነኑ አብይ አህመድ አገዛዙ ሰራዊት የት/ት ተቋሙ ውስጥ የሚገኙ መገልገያ ቁሳቁሶች በሙሉ መውደማቸውን በቪዲዩው ዳሰሳ እውነቱን ህዝባችን እና የትግሉ ደጋፊ እውቅና እንዲኖርው እናቀረባለን። ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም የህልውና ትግሉ ችቦ የተለኮሰበት ሶስተኛ አመት መታሰቢያ! ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም የምስራቅ አማራ ፋኖ አብሪ ኮከብ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና መስዋዕትነትን የተቀበለበት ዕለት ነው! አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ "ሕልው" ለማድረግ ዉድ ህይወቱን የሰዋበት ይህንን ቅዱስ የህልዉና ትግል "ሀ" ብሎ ያስጀመረበትና ችቦ የለኮሰበት ቀን ነው:: ገና በለጋ እድሜው የቀድሞዉን የሃገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል ትግል የጀመረው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከእግረኛ እስከ ሻምበልነት ማዕረግ ድረስ እንዲሁም የቀድሞው አግዓዚ ኮማንዶ አባል በመሆን ከሃገር ዉስጥ እስከ ዉጭ አገር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ድረስ ወጣትነቱን ለሃገሩ ገብሯል:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ባጋጠመው ከባድ ቁስል ምክንያት በጡረታ ያገለለ ሲሆን ከ 2010 ዓ.ም ህዝባዊ እምቢተኝነት ቡሃላ ወጣቶችን በስፖርት በአካል ብቃትና በስነ ልቦና የማንቃት ስራ እየሰራ በኋላም ከነ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ጋር የራያ ፋኖን በመመስረትና በመቀላቀል ፀረ ወያኔ ትግሉን ተቀላቅሎ ሁሉንም ተጋድሎዎች በመሪነትና በአሰልጣኝነት በድል ተወጥቷል:: የቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ ስልጠና መምሪያን እየመራ በመካነሰላም በደሴ በሃይቅ በወልድያ በቆቦና በራያ አላማጣ በርካታ ታጋዮችን ያሰለጠነና ያፈራ ሲሆን የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል በሰራዊትና በመሪነት ላይ ያሉ በርካታ ጀግኖችን አፍርቷል:: በርካታ ጀግኖችን እያሰለጠነና እያስታጠቀ መሆኑን ያየው አገዛዙም በጥላቻ አይን ያየው ጀመረ:: የሰሜኑን ጦርነት እነ አብይ አህመድና በድኑ ብአዴን በፕሪቶሪያው የድራማ ስምምነት ከቋጩት በኋላ የአማራ ፋኖን ህግ ማስከበር በሚል ሽፋን ትጥቅ ለማስፈታት በፌደራልና በክልል ደረጃ መከላከያ በማዝመት ዘመቻ በጀመሩበት ጊዜ ግጭቶች መጀመራቸው ይታወቃል:: በዚህም በተለያዩ ጊዜያት የምስራቅ አማራ ፋኖ ሰራዊትና አመራሮችን ቀዳሚ ኢላማ ያደረገ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጠለ:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከነዚህ የፖለቲካ ጥያቄ ካነገቡ ግጭቶች ጋር ተያይዞ የብርሃኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ይመለከት በነበረው ፀረ-ህዝብ ተግባርና ነዉር እጅግ ይበሳጭና ያዝን ስለነበር በአንድ ከአብይ አህመድ ጀኔራሎች ጋር ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ በተደረገ ስብሰባ የህዝብ ናችሁ ወይስ የብልፅግና? በሚል ይጠይቃቸዋል:: ያ ከራሱ ህዝብ አልፎ ሰላም ማስከበር ጎረቤት አገር ሄዶ ረሽኑን ለህዝብ ሰጥቶ ቅጠል በልቶ የሚያድር ሰራዊት የት ገባ? ሲል በመጠየቅ እስከ ሰላም ማስከበር በደረሰ ተልዕኮው የነበረዉን ህዝባዊነት በመጥቀስ የግፈኞች ዙፋን ጠባቂ መሆናቸዉንና ነውራቸዉን ነገራቸው:: አይቀሬዉን ጦርነት የተገነዘቡትና የተረዱት የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ከወሎ ምስራቅ አማራ ፋኖ ከሸዋ ከጎጃምና ከጎንደር ፋኖዎች ጋር በመሆን ጎንደር ሱዳን ጠረፍ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን በመመስረት አርበኛ ሰፈር መለሰን ዋና አዛዥ እና ዋርካው ምሬ ወዳጆን ምክትል አዛዥ አድርጎ በመምረጥ እንቅስቃሴ ጀመረ:: ምስራቅ አማራ ፋኖ አጠቃላይ የትግል ጉዞዉን የሚዘክር ታላቅ የተሃድሶ ዝግጅት የምክር ቤቱ ዋና አዛዥ አርበኛ ሰፈር መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመከላከያ፣ የልዩ ሃይል፣ የብልፅግና አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም መላ ሰራዊቱና ህዝብ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አከበረ:: በዝግጅቱም ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራ ህዝብ በክልሉና በተለይ ከክልሉ ዉጭ እየደረሰበት ያለዉን ግፍና ጭፍጨፋ በማንሳትና በማስታወስ የአማራ ህዝብ የህልዉና አደጋ ተጋርጦበታል "ትግል ይቀጥላል" የሚል መልዕክት ለታዳሚው ለሰራዊቱና በዉስጥም በዉጭም ላለው መላው የአማራ ህዝብ በህዝብ ግንኙነቱ አርበኛ አበበ ፈንታው በኩል መልዕክት አስተላለፈ:: ይህንን ተከትሎም ከተሃድሶ ቡሃላ ትጥቅ ያስረክቡናል ይበተናሉ ስንል እንዴት "ትግል ይቀጥላል" ይላሉ በሚል የአገዛዙ ሹማምንት ከፍተኛ ንዴትና ብስጭት ብሎም ድንጋጤ ዉስጥ ገቡ:: ይህንን ተከትሎም አገዛዙ የምስራቅ አማራ ፋኖ ቁስለኞችን ሳይቀር ሰራዊቱን ባገኘበት ምቹ አጋጣሚ ሁሉ መረሸን ጀመረ:: የለየለት ግጭትም ተጀመረ:: ጥቃት የማይወደው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙም ሰራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆምና ለሚመጣው ሁሉ ነገር ተመጣጣኝ አፀፋ እንዲሰጥ ድርጅቱና መሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ያወረደዉን መመሪያ በመቀበል በአንድ ወቅት ምስራቅ አማራ ፋኖ ካምፕ ድረስ ከነ አጃቢዎቹ በፓትሮል የመጣን ኮሎኔል ከመኪናው ወርዶ እስኪፈረጥጥ ድረስ ቆፍጠን ያለ እርምጃዉን ጀመረ:: ምስራቅ አማራ ፋኖም ሰራዊቱን በምዕራብ በኩል ከራያ ቆቦ ጮቢ በር እስከ በላጎ እንዲሁም ወልድያ ዙሪያ ሳንቃና መቻሬ እንዲሁም ሙጃ ድረስ ገዥ መሬቶች ላይ በማስፈር ለአይቀሬው ፍልሚያ ተዘጋጀ:: በበርካታ አካባቢዎች ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ የነበረዉን ከፍተኛ ዉጥረትና የአማራ ልዩ ሃይል በበድኑ ብአዴን እና በነ አብይ አህመድ ሴራ መፍረሱን ተከትሎ ሚያዚያ 1/2015 አ.ም ረፋድ ላይ ቆቦ ከተማ በተጀመረ ከባድ ዉጊያ የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ጅማሮ ችቦ ለኩሶ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ መስዋዕትነት ተቀበለ:: የህልዉና ተጋድሎዉም ሸዋ በነበሩ የምስራቅ አማራ ፋኖ አሃዶችና የሸዋ ፋኖ አናብስቶች ተቀጣጥሎ ዛሬ በመላው አማራ የደረሰበት ደረጃ ደረሰ:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና ቀይ መስመር ያለፈዉን በምድርም ይሁን በሰማይ ዘመኑ ያፈራዉን ጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀዉን ጨፍጫፊና ግፈኛ ፋሽስታዊ ስርዓት እስከ መጨረሻው ህቅታ ተናንቆ በጀግንነት ተሰዉቶ ችቦ ለኩሶና አስጀምሮ ይህንን የአማራ ህዝብ ቅዱስ የህልዉና ትግል ለዛሬ ካበቁ ጀግኖች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ አልፏል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! የተሰዋህለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን! ክብር ለትግሉ ሰማዕታት! አፋብን በወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም

#UPDATE የድል መረጃ !! ከሰሞኑ በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ በ4 ( አራት ) ቦታዎች ባደረገው የከበባ ድምሰሳ ውጊያ በአረመኔው አገዛዝ ሰራዊት ላይ ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል ። የ አዴት እና ጎንጅ ቆለላ 102ኛ ኮር ሁለት ከተማዎች ላይ ጠላትን በመደምሰስ  ወታደራዊ  እና ፖለቲካዊ ድል ተቀዳጄ። 1ኛ ሰሜን ጎጃም ዞን አዴት ከተማ የነበረ አንድ ሻለቃ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።   ጠላት ከ አንድ አመት በላይ ማዘዣ ጣቢያ በማድረግ ሲጠቀምበት የነበረው የአዴት ፖሊስ ጣቢያን በመቆጣጠር እና ጠላትን በመደምሰስ በርካታ የቡድን፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እና ተተኳሽ መማረክ ተችሏል። 159 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ 14,800 የብሬን ተተኳሽ 14,984 የክላሽ ተተኳሽ ጠቅላላ ድምር = 27,784 61 የእጅ ቦንብ 221 የክላሽ ካዘና 05ኩንታል ከስክስ እና ሚሊታሪ 24 የደረት ትጥቅ 12 የወገብ ትጥቅ  መማረክ ሲቻል። 97 ሚሊሻ 37 አድማ ብተና 22 መከላከያ በድምሩ  156 ጠላትን በመደምሰስ 07 ለጠላት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ተሽገርካሪዎችን በድጋሜ አገልግሎት እንዳይሰጡ  ማድረግ ተችሏል። በዚሁ  አዴት ከተማ አገዛዙ በግፍ ለዘመናት ፋኖን ትደግፋላችሁ በማለት ሲያሰቃያቸው የነበሩ 206  የግፍ  እስረኞችን  ማስለቀቅ ተችሏል። 2ኛ :-ሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ከተማ መሽጎ የነበረውን ጠላት መደምሰስ ተችሏል።  ነበልባሎቹ 102ኛ ኮር በተመሳሳይ ስዓት ጎንጅ ቆለላ ወረዳ በመግባት 89 ሚኒሻ 24መከላከያ በድምሩ 103 የጠላት ሀይል በመደምሰስ :- 58 የነፍስ ወከፍ መሳሪያ  እና 3480 ተቷኳሽ በመማረክ ታሪክ ሰርተዋል። በአጠቃላይ 102ኛ ኮር አዴት እና ጎንጅ ቆለላ በተደረገ ውጊያ     217 የነፍስ ወከፍ መሳራያ 31264 ተተኳሽ በመማረክ  ታሪክን በእጁ ፅፏል። [[[ የደጋ ዳሞት ]]] ➡️በ27/07/2018 ዓ ም በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር በደጋ ዳሞት በተሰራ ኦፕሬሽን  የተገኙ ድሎች:- 1. የተደሰሰ የጠላት የሰው ሃይል=150      በአመራር ደረጃ  መቶ አለቃ  =01                               ሻለቃ      = 01 2. በህይወት የተማረከ የጠላት ሀይል =43                በአመራር  ሌተናል ኮሮኔል  =01                      መቶ አለቃ     =    01 3.  ከጠላት የተማረኩ መሳርያዎች             ሀ, ክላሽ =180            ለ,ብሬን =09           ሐ,ስናፐር=03           መ,ሽጉጥ 02          ሠ,የብሬን አፈሙዝ =03          ረ,የድሽቃ አፈሙዝ 01          ሰ,የድሽቃ ካዝና /የጥይት መያዣ 03 4.የድሽቃ ተተኳሽ =54 ሳጥን 5. የብሬን ተተኳሽ =94 አሰቃጥላ 6.የክላሽ  ተተኳሽ =15 ሳጥን  7. f1 ቦንብ       =72 ፍሬ 8. ጭስ ቦብ     = 16ፍሬ 9. መኪና         = 03 ➡️እሬሽን 1. ብስኩት  300 ካርቶን 2. ስኳር   25 ኩታል 3. ነዳጅ  02 ቤርሚል [[[[ የሰዴ ]]]]] በዚህ አውደ ውጊያም :- 1ኛ  መሳሪያና ተተኳሽ ብሬን ~5 ክላሽ ~ l00 ቆመህ ጠብቀኝ ~ 17 የተበላሸ መሳሪያ ~ 7 የመገናኛ ሬድዮ ~ ዐ1 የወገብ ትጥቅ ~ 16 የክላሻ ካዘና ~140 ብስቶር የእጅ ቦንብ ~ 50 የብሬን ተተዃሽ - 20000 የክለሽ ተተኳሽ ~ 15000   መማረክ ተችሏል። 2ኛ ተሽከርካሪ Long bas የአመራር መኪና  ~ 3 ፓትሮል ዳብል ጋቢና~ 4 አንሞላስ ~  1 ሞተር ስይክል - 15 አፍ አስ አር-ዐ1 በድምሩ =   ለጠላት አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ 09መኪና 15 ሞተር ሳይክል  መማረክ ተችሏል። 3ኛ  ሎጅስቲክ ጠላት ለሰራዊቱ ምግብና ሊጠቀምበት የነበረ 60 ኩንታል ጤፍ 10 ኩንታል ስኳር ዐ1 ኮንቲነር  ዘይት  መማረክ  ተችሏል። 4ኛ በእጅ የተያዘ ምርኮኛ መከላከያ ~ o7  ከመካከላቸው  አንድ መቶ አለቃ  ማዕረግ ያለው ፍራ ኮማንዶ - 3 ፖሊስ ~ 5 ሚሊሽ ~ 10 ካድሬ ~4 በድምሩ  29 የጠላት ሀይል በነፍስ የተማረኩ ሲሆን ተገቢውን እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛል። 5ኛ የተደመሰሰ ጠላት 90  መከላከያ 22  ፍራ ኮማንዶ 55  ሚሊሻ ድምር 167  የጠላት ሀይልን በመደምሰስ ታሪክ መስራት ተችሏል። [[[[[በአጠቃላይ ]]]]]] አውደ ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎች :- 1/ አዴት 2/ ደጋ ዳሞት 3/ ሰዴ 4/ ጎንጂ ቆለላ የተገኙ ድሎች :- 1/ ፖለቲካዊ ድል 1.1/ ሰዴ ወረዳን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል 1.2/ ደጋ ዳሞት ወረዳን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል 3/ የአገዛዙን ፖለቲካዊ ዕቅድ ተዛብቷል 4/ የጠላት ፖለቲካዊ አመራሮች ከባድ የስነ ልቦና ስብራት ደርሶበት ወደ ደብረማርቆስ ፣ ፍኖተ ሰላም እና ባህርዳር ኮብልለዋል። 2/ ወታደራዊ ድል የተማረከ መሳሪያ :- 1/ ክላሽንኮቭ = 486 2/ ብሬን = 14 3/ ስናይፐር = 3 4/ የቃታ መሳሪያ = 66 ተተኳሽ :- 1/ የብሬን = 76,800 2/ የክላሽ = 40,484 3/ የዱሽቃ = 3240 ተማርኳል ። ድል ለጀግናው አማራ ድል ለጀግናው ፋኖ !!

የአፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒሊክ ዕዝ አሃዶች  በደላንታ ወረዳ ተጋድሎ በማድረግ ድል አስመዘገቡ:: መጋቢት 30/2018 ዓ.ም የምኒልክ ዕዝ 106ኛ ኮር 31ኛ ክፍለ ጦር ከ104 ኮር የ24ኛ ክፍለ ጦር ሬጅመንቶች ከ101ኛ ኮር የ35ኛ ክፍለ ጦር ሬጅመንቶች በጥምረት ከጧቱ 4:00 ጀምሮ እስከ ቀን 11:00 በደላንታ ወረዳ በፀሀይ መውጫ ተራራዎች ላይ በዘለቀ አውደ ውጊያ ከመቶ በላይ የፋሽስቱ ሰራዊት እርምጃ ተወስዶበታል:: በዚህ አውደ ዉጊያ የፋሽስቱ ወበር አስጠባቂ ሰራዊት ከ50 በላይ ሲደመሰሱ፣ከ70 በላይ ቀላልና ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል። የጠላት ከባድ ቁስለኞች በመኪና እየተጋዙ ወደ ደላንታ ወረዳ ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በመከላከያ ካምፕ ውስጥ በርካታ ቁስለኞች የሲቃ ድምፅን እያሰሙ ይገኛሉ። የፀሀይመውጫ ተራራ በብርሀኑ ጁላ ሰራዊት ደም የጨቀዬ ሲሆን ለአንድ ዱርዬ ስልጣን ሲባል ይሄ ሁሉ ከንቱ ዋጋ መክፈል ተገቢ አይደለም የሚለውን ምክራችንን ግን ለነገ ሟቾች ልንነፍጋቸው አልወደድንም! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም

ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም የህልውና ትግሉ ችቦ የተለኮሰበት ሶስተኛ አመት መታሰቢያ! ሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም የምስራቅ አማራ ፋኖ አብሪ ኮከብ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና መስዋዕትነትን የተቀበለበት ዕለት ነው! አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ የህልዉና አደጋ ለመቀልበስና የአማራን ህዝብ እንደ ህዝብ "ሕልው" ለማድረግ ዉድ ህይወቱን የሰዋበት ይህንን ቅዱስ የህልዉና ትግል "ሀ" ብሎ ያስጀመረበትና ችቦ የለኮሰበት ቀን ነው:: ገና በለጋ እድሜው የቀድሞዉን የሃገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል ትግል የጀመረው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከእግረኛ እስከ ሻምበልነት ማዕረግ ድረስ እንዲሁም የቀድሞው አግዓዚ ኮማንዶ አባል በመሆን ከሃገር ዉስጥ እስከ ዉጭ አገር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ድረስ ወጣትነቱን ለሃገሩ ገብሯል:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ባጋጠመው ከባድ ቁስል ምክንያት በጡረታ ያገለለ ሲሆን ከ 2010 ዓ.ም ህዝባዊ እምቢተኝነት ቡሃላ ወጣቶችን በስፖርት በአካል ብቃትና በስነ ልቦና የማንቃት ስራ እየሰራ በኋላም ከነ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ጋር የራያ ፋኖን በመመስረትና በመቀላቀል ፀረ ወያኔ ትግሉን ተቀላቅሎ ሁሉንም ተጋድሎዎች በመሪነትና በአሰልጣኝነት በድል ተወጥቷል:: የቀድሞው ምስራቅ አማራ ፋኖ ስልጠና መምሪያን እየመራ በመካነሰላም በደሴ በሃይቅ በወልድያ በቆቦና በራያ አላማጣ በርካታ ታጋዮችን ያሰለጠነና ያፈራ ሲሆን የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል በሰራዊትና በመሪነት ላይ ያሉ በርካታ ጀግኖችን አፍርቷል:: በርካታ ጀግኖችን እያሰለጠነና እያስታጠቀ መሆኑን ያየው አገዛዙም በጥላቻ አይን ያየው ጀመረ::  የሰሜኑን ጦርነት እነ አብይ አህመድና በድኑ ብአዴን በፕሪቶሪያው የድራማ ስምምነት ከቋጩት በኋላ የአማራ ፋኖን ህግ ማስከበር በሚል ሽፋን ትጥቅ ለማስፈታት በፌደራልና በክልል ደረጃ መከላከያ በማዝመት ዘመቻ በጀመሩበት ጊዜ ግጭቶች መጀመራቸው ይታወቃል:: በዚህም በተለያዩ ጊዜያት የምስራቅ አማራ ፋኖ ሰራዊትና አመራሮችን ቀዳሚ ኢላማ ያደረገ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጠለ:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ከነዚህ የፖለቲካ ጥያቄ ካነገቡ ግጭቶች ጋር ተያይዞ የብርሃኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ይመለከት በነበረው ፀረ-ህዝብ ተግባርና ነዉር እጅግ ይበሳጭና ያዝን ስለነበር በአንድ ከአብይ አህመድ ጀኔራሎች ጋር ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ በተደረገ ስብሰባ የህዝብ ናችሁ ወይስ የብልፅግና? በሚል ይጠይቃቸዋል:: ያ ከራሱ ህዝብ አልፎ ሰላም ማስከበር ጎረቤት አገር ሄዶ ረሽኑን ለህዝብ ሰጥቶ ቅጠል በልቶ የሚያድር ሰራዊት የት ገባ? ሲል በመጠየቅ እስከ ሰላም ማስከበር በደረሰ ተልዕኮው የነበረዉን ህዝባዊነት በመጥቀስ የግፈኞች ዙፋን ጠባቂ መሆናቸዉንና ነውራቸዉን ነገራቸው:: አይቀሬዉን ጦርነት የተገነዘቡትና የተረዱት የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች ከወሎ ምስራቅ አማራ ፋኖ ከሸዋ ከጎጃምና ከጎንደር ፋኖዎች ጋር በመሆን ጎንደር ሱዳን ጠረፍ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን በመመስረት አርበኛ ሰፈር መለሰን ዋና አዛዥ እና ዋርካው ምሬ ወዳጆን ምክትል አዛዥ አድርጎ በመምረጥ እንቅስቃሴ ጀመረ:: ምስራቅ አማራ ፋኖ አጠቃላይ የትግል ጉዞዉን የሚዘክር ታላቅ የተሃድሶ ዝግጅት የምክር ቤቱ ዋና አዛዥ አርበኛ ሰፈር መለሰ እንዲሁም ከፍተኛ የመከላከያ፣ የልዩ ሃይል፣ የብልፅግና አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዲሁም መላ ሰራዊቱና ህዝብ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አከበረ:: በዝግጅቱም ምስራቅ አማራ ፋኖ የአማራ ህዝብ በክልሉና በተለይ ከክልሉ ዉጭ እየደረሰበት ያለዉን ግፍና ጭፍጨፋ በማንሳትና በማስታወስ የአማራ ህዝብ የህልዉና አደጋ ተጋርጦበታል "ትግል ይቀጥላል" የሚል መልዕክት ለታዳሚው ለሰራዊቱና በዉስጥም በዉጭም ላለው መላው የአማራ ህዝብ በህዝብ ግንኙነቱ አርበኛ አበበ ፈንታው በኩል መልዕክት አስተላለፈ:: ይህንን ተከትሎም ከተሃድሶ ቡሃላ ትጥቅ ያስረክቡናል ይበተናሉ ስንል እንዴት "ትግል ይቀጥላል" ይላሉ በሚል የአገዛዙ ሹማምንት ከፍተኛ ንዴትና ብስጭት ብሎም ድንጋጤ ዉስጥ ገቡ:: ይህንን ተከትሎም አገዛዙ የምስራቅ አማራ ፋኖ ቁስለኞችን ሳይቀር ሰራዊቱን ባገኘበት ምቹ አጋጣሚ ሁሉ መረሸን ጀመረ:: የለየለት ግጭትም ተጀመረ:: ጥቃት የማይወደው አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙም ሰራዊቱን በተጠንቀቅ እንዲቆምና ለሚመጣው ሁሉ ነገር ተመጣጣኝ አፀፋ እንዲሰጥ ድርጅቱና መሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ያወረደዉን መመሪያ በመቀበል በአንድ ወቅት ምስራቅ አማራ ፋኖ ካምፕ ድረስ ከነ አጃቢዎቹ በፓትሮል የመጣን ኮሎኔል ከመኪናው ወርዶ እስኪፈረጥጥ ድረስ ቆፍጠን ያለ እርምጃዉን ጀመረ::  ምስራቅ አማራ ፋኖም ሰራዊቱን በምዕራብ በኩል ከራያ ቆቦ ጮቢ በር እስከ በላጎ እንዲሁም ወልድያ ዙሪያ ሳንቃና መቻሬ እንዲሁም ሙጃ ድረስ ገዥ መሬቶች ላይ በማስፈር ለአይቀሬው ፍልሚያ ተዘጋጀ:: በበርካታ አካባቢዎች ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ የነበረዉን ከፍተኛ ዉጥረትና የአማራ ልዩ ሃይል በበድኑ ብአዴን እና በነ አብይ አህመድ ሴራ መፍረሱን ተከትሎ ሚያዚያ 1/2015 አ.ም ረፋድ ላይ ቆቦ ከተማ በተጀመረ ከባድ ዉጊያ የአሁኑን የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ጅማሮ ችቦ ለኩሶ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ መስዋዕትነት ተቀበለ:: የህልዉና ተጋድሎዉም ሸዋ በነበሩ የምስራቅ አማራ ፋኖ አሃዶችና የሸዋ ፋኖ አናብስቶች ተቀጣጥሎ ዛሬ በመላው አማራ የደረሰበት ደረጃ ደረሰ:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ስለ አማራ ህዝብ ህልዉና ቀይ መስመር ያለፈዉን በምድርም ይሁን በሰማይ ዘመኑ ያፈራዉን ጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው የታጠቀዉን ጨፍጫፊና ግፈኛ ፋሽስታዊ ስርዓት እስከ መጨረሻው ህቅታ ተናንቆ በጀግንነት ተሰዉቶ ችቦ ለኩሶና አስጀምሮ ይህንን የአማራ ህዝብ ቅዱስ የህልዉና ትግል ለዛሬ ካበቁ ጀግኖች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ አልፏል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! የተሰዋህለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን! ክብር ለትግሉ ሰማዕታት! አፋብን በወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ሚያዚያ 1/2018 ዓ.ም

13አባላት10 ፓራ ኮማንዶ 3 ፓሊስ 74ኛ ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል ስቦ ማስከዳት በከፍተኛ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጥሏል የፓራ ኮማንዶ አባላት እና ፓሊሶች በዛሬው እለትፋኖን ተቀላቅለዋል። >>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>> ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም 1ኛ.ችዴ ባይሌ........ፓሊስ 2ኛ.ኤፍሬም ዳኘ.......ፓሊስ 3ኛ.ምትኩ ብርለን ........ፓሊስ 4ኛ.ታደሰ ሁነኛው....ፓራ ኮማንዶ 5ኛ.ባሴ ባይችሌ......ፓራ ኮማንዶ 6ኛ.እባበይ ደመቀ....ፓራ ኮማንዶ 7ኛ.ዝግጁ አማን....ፓራ ኮማምዶ 8ኛ.ደመቀ ሙልጌታ...ፓራ ኮማንዶ 9ኛ.ያለው አዳሙ ....ፓራ ኮማንዶ 10ኛ.ወርቅነህ አበበ...ፓራ ኮማንዶ 11ኛ.ጋሻው አለኸኝ....ፓራ ኮማንዶ 12ኛ.ደግዋለ ደምስ....ፓራ ኮማንዶ 13ኛ.ደመቀ...........ፓራ ኮማንዶ ጭቆና በቃን ሴራውን ተረድተናል ቀሪ ጊዜያችን ህዝባችን ማገልገል አለብን በማለት በሰሞኑ በተሰሩ ድሎች በቂ ማሳያ ናቸው በማለት በዛሬው እለት 201ኛ ኮር 74ኛ ክ/ጦር የተቀላቀሉ ሲሆን በአመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት

ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ/ም ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ በፋኖና በአገዛዙ መካከል ከባድ ውጥረት ነግሷል። ሁኔታዎች ያስፈሩ ነበር። በተለይም ልዩ ኃይሉ ይፈርሳል ከመባሉ ጋር ተያይዞ በየቦታው ሲወጡ የነበሩ መረጃዎች ውጥረቱን ወደለየለት ጦስ እንደሚወስዱት ግልፅ አመላካች ነበሩ። በዚህ ሁኔታ፡ በራያ ቆቦ ከተማ ውስጥ በዲሽቃና በብሬን ታጅቦ በወታደራዊ ፓትሮል የሚንቀሳቀስ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ "ፋኖ መጥፋት አለበት" እያለ ሲያወራ፡ ይቺ ወሬ ከአርበኛ ፊት አውራሪ ዳንኤል አለሙ ጆሮ ደረሰች። ከፍተኛ አዛዡ በዚህ አላበቃም፡ ብዛት ባለው ወታደርና በዲሽቃ ታጅቦ ፋኖ በሰፈረበት ካምፕ በተደጋጋሚ በተሽከርካሪ ይዞራል። አዛዡ ንቀት በተሞላበት መንገድ ዙሪያ ገባውን እነገላመጠ ነበር የሚንቀሳቀሰው። በዚህ መኃል ድንገት አንድ ሰው መንገድ ዘግቶ ቆሞ። የወታደራዊ አዛዡ አጃቢዎች ማን መንገዱን ዘግቶ እንደ ቆሞ ያውቃሉ። ለመናገር ግን ድፍረቱ አልነበራቸውም። በዚህ ሰዓት ከተሽከርካሪዋ ከኋላ ወንበር ተቀምጦ የነበረው ወታደራዊ አዛዥ "ማን ነው የደፈረኝ" በሚል ለመሳደብና ለመማታት የተሽከርካሪውን በር መስታዎቱን ዝቅ ሲያደርግ ያየውን ማመን አቃተው። በድንጋጤ ተሞልቶ መርበትበት ጀመረ። ሰውየው ዳንኤል ነው። በከተማዋ የአገዛዙ ካድሬዎችና ምንጣፍ ጎታች ወታደራዊ አዛዦች እንደፈለጉ እንዳይፈነጩ እግር ተወርች አስሮ ያስቀመጣቸው። ያ ግዙፍ፣ ከርዳዳ ጀግና። በዚህ መኃል..አርበኛ ዳንኤል አንድ ሁለት እርምጃዎችን ተራመደና በተከፈተው የተሽከርካሪዋ በር መስታዎት በኩል እጁን አሳልፎ በመስደድ የወታደራዊ አዛዡን ግራቀኝ ኮሌታ አንቆ ያዘው። "አንተ ሽንታም፡ ማን አባህ ስለሆንክ ነው በካምፓችን የምትዞረው? እንዴት ብትደፍረን ነው?" አለና በነዛ ፈርጣማ እጆቹ የወታደራዊ አዛዡን ኮሌታ ጨምድዶ እንደያዘ ምራቁን ተፋበት። ሁኔታው ወደ ባሰ ግጭት እንዳያመራ በሚል ሌሎች የፋኖ አርበኞች ገስግሰው አርበኛ ዳንኤልን ይገለግሉት ጀመር። አዛዡን እንዲለቅ ለመኑት። አርበኛ ዳንኤል ግን አሻፈረኝ ብሎ አዛዡን በመስኮቱ ጎትቶ ለማውጣት ግብግብ ጀመረ። ይህን ጊዜ፡ የዳኒ ልብ በማን እንደማይጨክን የሚያውቁ ሌሎች ጓዶቹ መጥተው "ዳኒዋ ...በአሳምነው አፅም ይሁንብህ፡ እረፍ" በሚል ለመኑት። የአሳምነው ስም ሲነሳ አንጀቱ አልቻለም። "ለዛሬው ምሬሃለው፡ ድጋሚ በዚህ ስትዞር ባገኝህ ግን ያኔ አንተን አያርገኝ" ብሎ ዝቶ ድጋሚ ምራቁን ተፍቶበት ለቀቀው። ያ ምድር ጠቦት ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የነበረው ወታደራዊ አዛዥ፡ አርበኛ ዳንኤል ኮሌታውን አንቆ ካስደነገጠው ሰዓት ጀምሮ ቆቦ አላድርም በሚል መኪናውን አስነስቶ ወደ ወልድያ ከነፈ። ከዛች ቀን ጀምሮ ውጥረቱ ወደ ለየለት ጦርነት እስከሚያመራ ድረስ ቆቦን እረግጦ አያውቅም። በመጨረሻም ሻምበል ዳንኤል አለሙ ሚያዝያ 01/2015 ዓ/ም ፡ፋድ ላይ በቆቦ ከተማ በተደረገ ተጋድሎ፡ ከበባ ውስጥ የነበሩ ጓዶቹን ከበባውን በመስበር ካወጣ በኋላ፡ በቀጠለው ትንቅንቅ የአሁኑን ትግል ችቦ ለኩሶ ክቡር መስዋዕትነትን ተቀበለ። አጥብቆ ስለሚሳሳለት የአማራ ሕዝብ ሲል፡ ስለመበደሉ ዘውትር ስለሚንገበገብለት የአማራ ሕዝብ ሲል ሕያው ነፍሱን አሳልፎ የሰጠው፡ የሚያዝያ 01/2015 ዓ/ም ክቡር ሰማዕቱ አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ(ፊት አውራሪ) እሩህሩህ ነው። ደግ፡ ተጫዋች፡ ግን ደግሞ በጥላቶቹ ላይ መራርና ጎምዛዛ። ገና በለጋ እድሜው የቀድሞውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በመቀላቀል ትግል የጀመረው አርበኛ ዳንኤል አለሙ፡ ከእግረኛ እስከ ሻምበልነት ማዕረግ ድረስ እንዲሁም የቀድሞው አግዓዚ ኮማንዶ አባል በመሆን ከሃገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር ሰላም ማስከበር ተልዕኮ በመሄድ ወጣትነቱን ለሃገሩ ገብሯል:: አርበኛ ሻምበል ዳንኤል አለሙ ባጋጠመው ከባድ ቁስል ምክንያት ከመከላከያ ሠራዊት በጡረታ ያገለለ ሲሆን፡ ከ2010 ዓ/ም በኋላ ዳግም ከተጀመሩ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ንቅናቄዎች ጀምሮ ወጣቶችን የማሰልጠንና የማንቃት ስራ እየሰራ በኋላም ከነ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ጋር ሆኖ ፋኖን በመመስረት፡ የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ ውድ ሕይወቱን እስከገበረበት ቀን ድረስ በታላቅ ቆራጥነት ታግሎ ያታገለ፡ ያሰለጠነና ያደራጀ የዘመናችን ፈርጥ እንቁ ጀግና ነው። ያ ግዙፉና የአገዛዙ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮችን ጨምሮ ምራቅ ሲያስውጥና ሲያስጎመዥ እንዲሁም ሲያስፈራና ሲያርበተብት የነበረው ምስራቅ ፋኖ ከሥር መሠረቱ ጀምሮ የዳንኤል እጆች አሻራ ያረፈበት ነው።ምን አልባት በዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ አዲስ የሰለጠነ ፋኖ ካልሆነ በስተቀር ሌላው ነባሩ አርበኛ በዳንኤል አለሙ የሰለጠነ ነው ። በአማራ ፋኖ ትግል ታሪክ ውስጥ ወታደራዊ መዋቅሩን ጠብቆ በመገንባትና ዘመናዊ መሣሪያ በመታጠቅ የመጀመሪያው የሆነው ያ ግዙፍና እጅግ አስፈሪው <የምስራቅ አማራ ፋኖ> ዛሬ ምኒልክ ዕዝን ወልዷል። ዛሬ ተጠሪነቱ ለዕዙ ወታደራዊ ስልጠና መምሪያ የሆነ በአርበኛ ኮማንዶ ዳንኤል አለሙ ስም የተሰየመ ግዙፍ የኮማንዶ ማሰልጠኛ ማዕከል ተከፍቶ፡ እልፍ አዕላፍ ጀግና ኮማንዶዎችን እያፈራ ነው። ዛሬ በኮማንዶ ዳንኤል አለሙ ስም እየፎከሩ የምሽግ ጓዳን የሚበረግዱ፡ የጠላት ደረትን በሳንጃ የሚሰነጥቁ ጀግኖች እልፍ አዕላፍ ናቸው። "አማራ በየሰከንዶች ልዩነት ተደራጅቶ፡ ሰልጥኖ መታጠቅ አለበት፡ ያለበለዚያ የመጣበት የመከራ ማዕበል ይዞት ይጠፋል" የሚለውን የአርበኛ ዳንኤል አለሙን ንግግር የተቀበሉ አርበኛ ኮማንዶ ጌታቸው ሲሳይን ጨምሮ እነ አርበኛ ኮማንዶ ዮሴፍ አስማረና ሌሎች ጀግና አሰልጣኞች በዳንኤል ስም ምሽግ ሰንጣቂ ኮማንዶዎችን እያፈሩ ነው። የኮማንዶ ዳንኤል አለሙ ስም ዛሬ ላይ፡ ጀግኖች ውጊያ ሊጀምሩ ገና ጣታቸውን ከጥይት ቃታቸው ላይ ጣል ሲያደርጉ "የዳንኤልና የአሳምነው አፅም ይርዳን" ብለው መንፈሳቸውን የሚያበረቱ፡ ምሽግ ላይ "የዳኒ ወንድም" እያሉ ጠላትን የሚያርበደብዱ ጀግኖች ተፈጥረዋል። ዛሬ የኮማንዶ ዳንኤል አለሙ ስም "ዳንኤልን ብያለሁ አልነካህም አትንካኝ"..."ዳንኤልን ብያለሁ አልከዳህም"..."ዳንኤልን ብያለሁ እመልስልሀለው አበድረኝ"..."ዳንኤልን ብያለሁ ጠላቴን ሳልደመስስ አልመለስም"..."ዳንኤልን ብያለሁ ደርቤ ሳልማርክ ከዚች ምሽግ አልነቃነቅም" እየተባለ ይማልበታል። ይፎከርበታል።መላው የፋኖ ሰራዊት ይመካበታል። እና አሁን ዳንኤል አለሙ ሞቷል ማለት ይቻላል? ሞትስ ምንድነው? ሰው ሞቷል የሚባለውስ ምን አይነት ሞት ሲሞት ነው? እንዴትስ ያለ አሟሟት?

በሰሜን ሜጫ ወረዳ ሦስት የጤና ባለሙያዎች መገደላቸውን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ! በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ መጋቢት 24/2018 ዓ/ም ሦስት የጤና ባለሙያዎች ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት መገደላቸው ተሰምቷል። ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ በአቢዮት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ በነርስነትና በባለሙያነት የሚያገለግሉ ሲሆን፡ ሦስተኛው ባለሙያ ደግሞ በግል የጤና ተቋም ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ፡ በጤና ባለሙያዎቹ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በጥብቅ አውግዘዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፡ የጤና ባለሙያዎች በማንኛውም ሁኔታ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ በማሳሰብ በተፈፀመው ግድያ ላይ በአስቸኳይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

"እኔ ለህዝብ ነፃነት የወጣሁ ታጋይ እንጂ ለግል ጥቅምና ለቤተሰብ ክብር የቆምኩ ተራ ግለሰብ አይደለሁም"። 👉ከአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ወታደራዊ አዛዥ ፋኖ ታዘበው ስዬ የተላለፈ መልዕክት እኔ የጥንቶቹ ጀግኖች አባቶቼ ኩሩ ወራሽ፣ የታላቁ የበላይ ዘለቀ የትግል መንፈስ ልጅ ነኝ። አባታችን በላይ ዘለቀ "ልጄ ከሀገሬ አትበልጥም፤ ከፈለጋችሁ ቀቅላችሁ ብሏት!" ብሎ ለጠላት የሰጠው ምላሽ ዛሬም በደሜ ውስጥ ይፈላል። አገዛዙ በአውደ ውጊያ የተማረከበትን ኮሎኔል ለማስለቀቅ ሲቪል ቤተሰቦቼን በማገት ሊደራደረኝ መሞከሩ የውርደት ውርደትና የሞራል ክስረት መግለጫ ነው። ለዚህ የሽፍታ ተግባር የምሰጠው ምላሽ ግልጽና የማይታጠፍ ነው። የእኔ ቤተሰቦች ከሚሊዮኑ የአማራ ሕዝብና ከሀገሬ አይበልጡም። እኔ ለሕዝብ ነፃነት የወጣሁ ታጋይ እንጂ ለግል ጥቅምና ለቤተሰብ ክብር የቆምኩ ተራ ግለሰብ አይደለሁም። ቤተሰቦቼን በማገት ትግሉን ማስቆም ይቻላል ብሎ ማሰብ የታሪክ ድንቁርና ነው። እኔ በግለሰብ ደረጃ የምወሰን ወይም በስሜት የምነዳ ታጣቂ አይደለሁም። የ109ኛ ኮር አዛዥ እንደመሆኔ መጠን፣ ትግላችንን የሚመራውና የሚወስነው የራሱ የሆነ የጠነከረ ወታደራዊ መዋቅርና መመሪያ ነው። ትግላችንን የሚመራውና የሚወስነው የጋራ ድርጅታዊ መርኃችን እንጂ የቤተሰብ ስሜት አይደለም። በእኔ ቤተሰቦች ላይ የሚደረግ ጫና የድርጅቴንና የትግሉን መርህ ቅንጣት ታህል አይቀይረውም። በተደጋጋሚ እንደታየው ድርጅታችን፤ የሕግና የሞራል የበላይነት በማክበር ምርኮኛን በሰብአዊነት መያዝ መለያው ነው። በአንጻሩ ግን በአውድ ውጊያ የተማረከን ወታደር ለማስለቀቅ በቤት ውስጥ ያሉ ሲቪል እናቶችንና ሕፃናትን ማገት ዓለም አቀፍ የጦር ሕግን መጣስና ፍጹም የሽብር ተግባር ነው። ይህም አገዛዙ ከመንግሥትነት ወርዶ ወደ ሽፍታነት መለወጡን ለዓለም ያሳበቀ ክስተት ነው። መልዕክቴ አጭር ናት፤ ቤተሰቦቼን ብታስሩ ወይም ብትገድሉ ትግሉን ወደኋላ አታስቀሩትም። እኛ ከሞት ጋር ተስማምተን፣ ከቤተሰብ ተለይተን የወጣነው ለሚሊዮኖች ትንሳኤ ነው። ሽንፈት እና ሽፍታነታችሁን ለታሪክ አስመዝግቡ! ሆኖም፤ የአገዛዙን ነውረኛና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በአንድ ድምፅ ከማውገዝ ይልቅ፣ ያልሆነ ታርጋ ለመለጠፍና ያልታሰበ ሴራ ለመተብተብ መሽቀዳደም የታሪክ አሳፋሪ ክስተት ነው። የንጹሐን ቤተሰቦቼ መታገት በራሱ ግልጽ የሆነ የሽብር ተግባር ሆኖ ሳለ፣ ለዚህ ግልጽ በደል ሽፋን ለመስጠት የሚደረግ የቃላት ጨዋታና የ"ሴራ" ድሪቶ፣ የኅሊና መታወር እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም። እውነትን በሴራ ትረካ ለመቅበር መሞከር በበደለኛው ግፍ ላይ ሌላ ግፍ መጨመር ነው። ይህ አይነቱ አድርባይነትና የሞራል ዝቅጠት፣ ከጠላት ጥይት ይልቅ የትግሉንና የሕዝቡን ልብ የሚያደማ ሕመም ነው። ነገሩ ሳይገባቸውም ይሁን እያወቁ በንጹሐን ዕንባ ላይ የፖለቲካ ቁማር የሚጫወቱ ወገኖች፣ የታሪክና የትውልድ ፍርድ ከደጃፋቸው መሆኑን ሊረዱ ይገባል! ድል ለጭቁኑ ሕዝብ! አዲስ ትዉልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ !      ፋኖ ታዘበው ስዬ የ109ኛ ኮር ወታደራዊ አዛዥ             ሚያዚያ 01/2018

የአፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ሰሜን ምዕራብ ዞን (ክላስተር) ስር የተደራጀው የህዝብ አስተዳደር መዋቅር የሚከተለውን ይመስላል።    ወረዳ አንድ 1, ጌጤ ተሰራ                ዋና ስተዳዳሪ 2, አስራት ካሳው              ም/አስተዳዳሪ 3, አበባው  ወርቁ               ፓለቲካ 4, እሸት ደሳለኝ                 ፅ/ቤት 5, አይቶ ሐጎስ                  ሰላም እና ደህንነት 6, መ/ር ጌትነት ደሳለኝ     ህ/ግንኙነት 7, ነጋ ውብነህ               ማህበራዊ ጉዳዬች 8, ሸጋው ይግዛው           አደረጃጀት 9, መኮነን ጫቅሉ           ሀብት አፈላላጊ 10, ተንሳይ ብርሐኑ         ም/ሀብት 11,ፍቅሬ ፅጌ                 ፀጥታ 12, አንዳርጌ ይትባረክ    ፍትህ 13, የሽነህ ፀጋየ            መረጃ 14, ነጋ ብርሐኔ              ም/ ፖለቲካ 15,,አስታጠቅ ደስታ      ግምጃ ቤት        ወረዳ ሁለት 1, ሻንበል ጎበዜ              ዋና አስተዳዳሪ 2, አየነው ደሌ                 ም/አስተዳዳሪ 3, ገብረ ህይወት አዳነ       ፖለቲካ 4, ቴዎድሮስ አለማየሁ        ፅ/ቤት 5, አማኑኤል አጥናፉ         ሰላም እና  ደህንነት 6, ከተማው  ምትኩ          ህ/ግኑኝነት 7, ኤርሚያስ ወርቄ            ማህበራዊ ጉዳዮች 8, ንጉስ በላይ                  አደረጃጀት   9, ወንደሠን  ከዘራይ         ሀብት አፈላላጊ 10, ጌታው                       ም/ሀብት አፈላላጊ 11, አባይነህ ጌታነህ          ፀጥታ 12, ምስጌ ተገኘ                ፍትህ 13, ነጋሽ ይዘዘው              መረጃ 14, ደረጃው ጉሎ              ም/ፖለቲካ 15, ካሣው ከበደ               ግምጃ ቤት         ወረዳ ሶስት 1, ዘነበ ገላ                 ዋና አስተዳዳሪ 2, እሸቱ ሞላ               ም/አስተዳዳሪ 3, እርታው ታገለ          ፖለቲካ 4, አሜሪካው አለባ       ፅ/ ቤት 5, አበረ ይስማው         ሰላም እና ደህንነት 6, ማለደ አይቶ            ህ/ግንኙነት 7, ደረጀ ደሳለኝ            ማህበራዊ ጉዳዮች 8, ስልጣኑ አማረ          አደረጃጀት 9, እንዳለው አለባቸው    ሀብት አፈላላጊ 10, አደላዳይ  ይርጋ       ም/ሀብት አፈላላጊ 11, አስቻለኝ ቆያቸው      ፀጥታ 12, አስታጥቄ ጫቅሉ     ፍትህ 13, ውዱ ጫቅሌ            መረጃ 14, ጠይቅ ሲሳይ            ም/ፖለቲካ 15, ነጋ                          ግምጃ ቤት ከዚህ ቀደም ደጃዝማች 4ኛ ኮር ቀጠና የነበረው የህዝብ አስተዳደር አፋብን ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ሰሜን ምዕራብ ዞን (ክላስተር) በሚል ተተክቶ ተደራጅቷል።       ህልውናችን በአርበኝነታችን!!                  ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ