es
Feedback
ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
3 678
Suscriptores
+2624 horas
+3797 días
+1 10930 días
Archivo de publicaciones
የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች በብልፅግናው አገዛዝ ባደባባይ እየተዘረፉ መሆኑን ነዋሪዎች በማስረጃ እያጋለጡ ቀጥለዋል:: ጀምበር የጠለቀችበትና ተስፋ የቆረጠው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ የህዝብ ሃብት መዝረፉን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የሰሜን ወሎ ዞን ወልድያና ቆቦ ከተማ ካድሬዎችም የከተሞቹን የህዝብ ሃብት ባደባባይ እየዘረፉ መሆኑን ነዋሪዎች በማስረጃ እያጋለጡ ይገኛሉ:: ከዚህ ጋር ተያይዞም ባለፈው ጊዜ ቆቦ ከተማ ሁለገብ አዳራሽን ሸጠው የተከፋፈሉ ሆድ አደርና አገር አፍራሽ የዞንና የወረዳ ካድሬዎች እንዲሁም የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አመራሮች በማስረጃ የተጋለጡ መሆኑ ይታወሳል:: ጉዳዩም በፍርድ ቤት ተይዞ የህዝብ ሃብት የሆነው ቆቦ ሁለገብ አዳራሽ ተመላሽ እንዲሆን ተወስኖ እንደነበር ከፍርድ ቤት ያገኘነው ማስረጃ ይናገራል:: ስለሆነም አሁንም ዘረፋው ተጠናክሮ ቀጥሎ ከዚህ በታች በማስረጃ የተዘረዘሩት የወልድያ ከተማ እና የቆቦ ከተማ መሬቶች ለጦርነት አላማ ሊውሉ ጥርና የካቲት/2018 ዓ.ም በወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ለሽያጭ መቅረባቸውን የከተሞቹ ህዝብ ባደረሰን ማስረጃ አረጋግጠናል::  ወልድያ ከተማ በክልሉ ከፍተኛ የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች የሚዘረፉበት ከተማ ሲሆን ባለፉት ሶስት አመታት ድሃ የቀበሌ ነዋሪዎችን በማፈናቀል የአገዛዙ ሹማምንቶች እንደተከፋፈሉትና ዛሬም ተጠናክረው እንደቀጠሉበት ከህዝብ የደረሰን ማስረጃ ያሳያል:: ቆቦ ሁለገብ አዳራሽ ባለፈው ጊዜ ሰማኒያ ሚሊየን ብር እና ከዛ በላይ ተሽጦ ገንዘብ ሲካፈሉ ተጣልተው በፍርድ ቤት ትዛዝ ገንዘቡ ለገዥ ተመላሽ ከሆነ በኋላ እንደገና ለጨረታ የቀረበ ሲሆን እነዚህና ሌሎች ለጊዜው በስም ያልተጠቀሱ የህዝብ ሃብት የሆኑ መሬቶች የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ ላለው የብልፅግና አገዛዝ ለጦርነቱ አላማ ለማዋል እየተዘረፉ በህገወጥ ጨረታ ለገበያ መቅረባቸውን ነዋሪዎች በማስረጃ አስደግፈው አድርሰውናል:: በመጨረሻም ለመላው ህዝባችን ምኒልክ ዕዝ ከሚያዚያ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ያፀደቀውን መመሪያውን መሰረት በማድረግ የህዝብ ሃብት ጊዜውን ጠብቆ ለህዝብ መሆኑና መመለሱ አይቀርምና ተስፋ የቆረጠው አገዛዝ ካድሬዎች የጦር መሪዎች ስግብግብ ነጋዴዎችና ህገወጥ ደላላዎች ተቀናጅተው ከሚሰሩት የመሬት ወረራና ዘረፋ ባለመሳተፍ ሃብታችሁን እንድትጠብቁ ብሎም ከህልውና ትግሉ ጎንም እንድትቆሙ ስንል ዛሬም እንደ ትላንቱ መልክታችንን እናስተላልፋለን! *ማስታወሻ፦ ምኒልክ ዕዝ በሁሉም የወሎ ቤተ-አማራ አካባቢዎች በአገዛዙ እየተዘረፉ ያሉ የህዝብ ሃብቶችን የሚከታተልና ማስረጃ የሚይዝ ህቡዕ (ስውር) አደረጃጀት እንዳለው ለህዝብ ማሳወቃችን የሚታወስ ነው::  መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምኒልክ ዕዝ የካቲት 5/2018 ዓ.ም

➧➧➧ በእሳት ተፈትኖ እንደወርቅ ነጥሮ የወጣው አዲሱ ትውልድ ይሄ ነው!! በዛሬው ዕለት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ያስመረቃቸው ተወርዋሪ ኮማንዶዎች!!👇👇
+2
➧➧➧ በእሳት ተፈትኖ እንደወርቅ ነጥሮ የወጣው አዲሱ ትውልድ ይሄ ነው!! በዛሬው ዕለት በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ያስመረቃቸው ተወርዋሪ ኮማንዶዎች!!👇👇

የአማራ ዲያስፖራ ሆይ ለምን ከትግራይ ሕዝብ አትማርም? በገዛ ለቅሶአችንና በሀዘናችን ድራማ እስከመቼ ይሰራሉ?! የጠላትን ርካሽ ፕሮፓጋንዳ መቀልበስና ማዛባት፣ አለብን! ሥርዓቱ ሰሞኑን በአንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በጎንደር ቀጠና የደረሰበትን ምትና ስብራት ለመጠገን በወገን ላይ ስም የማጥፋትና የማጠልሸት የሚዲያ ዘመቻ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው። ይህ በሐሰት ላይ የተመሠረተ የስም ማጥለሸት ዘመቻ የተለመደና ያደረ ቢሆንም ሰሞኑን ግን በተለየ ሁኔታ እራሱ በድሮንና በሞርታር ያቃጠላቸውን እና ያፈረሳቸውን መሠረተ ልማቶች በመለጠፈ የፋኖስን የአማራን ሕዝብ ታጋዮች ገፅታ ለማበላሸት እየተጠቀመበት ነው። የኔ አስተያየት ምንድን ነው? በተለይም በውጭ ሀገር የምንኖር የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ይመለከተናል ያገባናል የምንል ሁሉ ፦ ሶስት ከተማ ተያዘ፣ አራት ጠላት ተማረከ፣ እንዲህና መሠል ደጅ ላይ ባለው ታጋይ ሊሠሩ የሚችሉ እዉነታዎችን በማስተጋባት ብቻ ከመጠመድና  ከጊዜያዊ ሆያሆየ ወጥተን እንስራ። በዘላቂነትና ወጥነት ባለው መልኩ አለም አቀፍ የሳይበር፣ የሰልፍና የዲፕሎማሲ ዘመቻ በማድረግ እነኝህ የወደሙ ተቋማትንና ጥቃት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ምስልና ድምፅ በማስተጋባት በማቀናበር የጠላት ኦህዴድን ዘመቻ ለመቀልበስ አለም አቀፍ ጫና በመፍጠር ማዕቀብ እንዲጣልበት እና ቅቡልነት እንዲያጣ ማድረግ ይኖርብናል። ይህ ዘመቻ በተጠና መንግድ መረጃን ከአንድ ቋት ወስዶ በማዘጋጀትና በመበተን ጠላትን እረፍት ከመንሳት ባለፈ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ ለአማራ ህዝብ ህልውና ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው ያደርጋል። ይህን ማድረግ የማንችል ከሆነ ግን የተደራጀ የፕሮፓጋንዳ ቡድን ያለው ሥርዓት እራሱ የፈፀመውን በደልና ግፍ የኛን ስም ጥላሸት ለመቀባት ይጠቀምበታል። በጎረቤት ጥሩ ነገርን መማር ስለማይከፋ እስኪ ከትግራይ ወገኖቻችን በመማር በአለም አቀፍሚዲያዎች፣ በዲፕሎማሲ ኮሚኒቲ ውስጥ፣ በሳይበር ላይ እና አለም አቀፍ ሰልፍ በመውጣት ዘመቻ እናድርግ? ማስታወሻ፦እስከአሁን ያሉ መልካም ነገሮች የሉም እያልኩ ሳይሆን የበለጠ መሥራት ይጠበቅብናል ለማለት ነው።

ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ ከ16 በላይ የድሮን ጥቃት በደብረታቦር እና አካባቢው መፈፀሙ የአደባባይ ሀቅ ነው። የንፁሃን ወገኖቻችን ዋጋ እጥፍ ድርብ ርምጃ እየወሰድን ነው።ተጠናክሮ ይቀጥላል። ዮሐንስ ን
+1
ንፁሃንን ኢላማ ያደረገ ከ16 በላይ የድሮን ጥቃት በደብረታቦር እና አካባቢው መፈፀሙ የአደባባይ ሀቅ ነው። የንፁሃን ወገኖቻችን ዋጋ እጥፍ ድርብ ርምጃ እየወሰድን ነው።ተጠናክሮ ይቀጥላል። ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከ6 ወር በላይ ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች አስመረቀ ============== በዛሬው ዕለት በቀን 05/06/2018 ዓ.ም በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ
+2
አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከ6 ወር በላይ ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች አስመረቀ ============== በዛሬው ዕለት በቀን 05/06/2018 ዓ.ም በአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከ6 ወር በላይ ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች የኮርና የክ/ጦር አመራሮች በተገኙበት በደማቅ አስመረቀ። የጠላትን ኃይል በመደምሰስ ከነፍስ ወከፍ እስከ መካናይዝድ መሳሪያዎች፣ከመሰረታዊ ወታደር እስከ ኮረኔል ማዕረግ ያላቸውን የጠላትን ሀይል በመደምሰስና በመማረክ የሚታወቀው ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 99ኛ ክ/ጦር ከ6 ወር በላይ ሲያሰለጥናቸው የነበሩና የውጊያ ማርሽ ቀያሪ የሆኑ ኮማንዶዎችን ከአማራ ፋኖ አንድነት መመስረት ማግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የሀገር ሽማግሎች፣የሀይማኖት አባቶችና የጦር አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በደማቅ አስመርቋል። የዛሬ ተመራቂዎቹ እንደወርቅ ቀልጠውና ተፈትነው በወጡ የኮማንዶ አሰልጠኞች ሰልጥነው አስቸጋሪውን የኮማንዶ ስልጠና እና ወታደራዊ ጥበብ በማለፍ ለዛሬዋ የምረቃ ዕለት የደረሱ ሲሆን ቀጣይ የሚጠብቃቸውን ማንኛውንም ግዳጅ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በገቡት ቃል ኪዳን መሰረት አረጋግጠዋል። 👉ሙሉ ዝርዝር የቪዲዮ መረጃውን በመረጃ ቲቪ የሚተላለፍ ይሆናል!! አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት የካቲት 5/2018ዓ.ም

ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ወደ ጦርነት ሊገባ መሆኑን የተገነዘበው ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል‼️ ከዚህ ጋር ተያይዞም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 49ኛ ክፍለ ጦር የሆኑ አምስት
+1
ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ከየ አቅጣጫው ወደ ጦርነት ሊገባ መሆኑን የተገነዘበው ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ይገኛል‼️ ከዚህ ጋር ተያይዞም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ 49ኛ ክፍለ ጦር የሆኑ አምስት አባላት ከኦህዴድ ብልፅግና ጋር ሆነን ወገናችንን አንወጋም በማለት ምስራቅ አማራ ኮር 1 አሳምነው ክፍለ ጦርን ተቀላቅለዋል:: ክፍለ ጦሩም አቀባበል አድርጎላቸዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ትግላችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 05/ዐ6/2018 ዓ.ም

በእነማይ ወረዳ ደብረፅሞና ቀበሌ ኖሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ!! 64ኛ ክ/ጦር የካቲት 05/2018 ዓ.ም የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክፍለ ጦር አመራሮች እና የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት አመራሮች የካቲት 04/2018 ዓ.ም በእነማይ ወረዳ ደብረፅሞና ቀበሌ ማህበርሰብ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በእነማይ ወረዳ ደብረፅሞና ቀበሌ የውይይት መድርክ ከሆላ ደጀኑ ሰራዊታችን አደረጃጀት፣ በፋይናስ አሰባሰብ፣ በፍትህ አሰጣጥ፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና መሰረተ ልማት፣ በቀበሌ አስተዳደር ፀጥታ ጉዳዩች እንዲሁም የቀበሌ ጊ/መንግስት አመራሮችን በመገምገም ተተኪ አመራር የማብቃት እና ህዝብ ያመነባቸው መሪዎችን ወደ ፊት የማምጣት ስራዎችን ላይ በሰፊው ውይይት ተካሂዶል። የአማራ አንድነት መሪዎችን መምረጡ እና ወደ አንድ መምጣት ህዝባችን ከተደቀነበት የህልውና አዳጋ በአጭር ግዜ ነፃ ለማውጣት ድርጅቱ በእየ ዘርፍ እየሰራ መሆኑን የክፍለ ጦር አመራሮች በስብሰባ መድርኩ ለተገኙት የማህበርሰብ አስረድተዋል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!! የካቲት 05/2018 ዓ.ም የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ከውጭ ቱሪስቶች ጋር ውይይት አደረገ!!! ፡ እየገነባነዉ ያለዉ ስርዓት ሰዉ ሰዉ ሚሸት ነዉ። ትግላችን አቃፊም አለማቀፋዊም ነዉ ስንል በምክናያት ነዉ።የእኛ ትግል ማንንም በብሔሩ በቀለሙ ፈርጆ አይጠላም ነጥሎ አይወድም።ሁሉንም ያለምንም ቅደመ ሁኔታ "ሰዉ" በመሆኑ ብቻ አክብሮ ይይዛል አብሮ ይወዳል።የትግላችን አፈ-ሙዝ የተነጣጠረዉ ባሪያ አድርገዉ እንኳን ሊገዙን በማይሹ በአብይ አህመድ እና በስርዓቱ አጎብዳጆች ላይ ነዉ። ዉሸትን እና ብልጭልጭ ግንባታዎችን(ኮሪደር ልማትን) ለሃገር ግንባታ፣ለገፅታ እና ለዲፕሎማሲ እንደ ግብዓት የሚጠቀመዉ ብልፅግና በዚህ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊን እንዲዋረዱ አድርጎናል። አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር የ22ኛ ክፍለጦር አመራሮች አርበኛ ሀብታሙ አለኸኝ የክፍለጦሩ ም/ስብሳቢ ፣ አርበኛ ገደፉው አይዘንጋው የክፍለጦሩ ም/ጦር አዛዥና ሌሎችም በተገኙበት ጭስ አልባው ነዳጅ እየተባለ በሚጠራው የቱሪስት መስህብ ቦታ ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ጭስ አባይ ከተማ ላይ ከውጭ አገር ቱሪስቶች ጋር በመገኘት፤መንግስት ነኝ የሚለው አካል ፋኖ ዘራፊና አላማ የለለው ሽፍታ ነው እያለ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እንደሚሰራው ሳይሆን ፋኖ ትልቅ አላማና ራዕይ ያለው፣ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና መረጋጋትና ለአጠቃላይ ጅኦፖለቲካዊ ጉዳዮች የበኩሉን እየተወጣ ያለ የነፃነት ታጋይ(ተፋላሚ ኃይል ) መሆኑን በማስረዳት ለማንኛውም የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጋ ቱሪስት ልዩ ጥበቃ የሚደረግለትና የቱሪስት ቦታዎችን በነፃነት ጎብኝቶ በሰላም ወደ መጣበት የሚመለስ መሆኑን በመነጋገር ውይይታቸውን አጠናቀዋል። የውጭ ሀገር ቱሪስቶችም በተደረገላቸው አቀባበልና እንክብካቤ ተደስተው የተደረገላችውን እንክብካቤ ቦታውን ለመጎብኘት ለሚመጡ ቱሪስቶችና ለአለም አቀፍ ዲፕሎማቶች እንደሚያጋሩ ገልፀዋል። የካቲት 5 2018 ዓ.ም! ክፋት ለማንም! በጎነት ለሁሉም! አዲስ ትውልድ!አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

​የአማራ ፋኖ በምስራቅ አፍሪካ ካሉ የሽምቅ ተዋጊዎች መካከል በብቃቱና በተጋድሎው ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። ይህ ትውልድ ለነፃነቱ የሚከፍለው መስዋዕትነት፣ የጥንት አባቶቻችንን የታሪክ ባለቤትነት
​የአማራ ፋኖ በምስራቅ አፍሪካ ካሉ የሽምቅ ተዋጊዎች መካከል በብቃቱና በተጋድሎው ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው። ይህ ትውልድ ለነፃነቱ የሚከፍለው መስዋዕትነት፣ የጥንት አባቶቻችንን የታሪክ ባለቤትነት ዳግም የሚያጸናና በክብር የሚመዘግብ የመጨረሻው የታሪክ አደራ ተሸካሚ ትውልድ መሆኑ ነው ​ይህ ትውልድ በትከሻው ላይ ከባድ አገራዊና ህዝባዊ አደራ ተጭኖበታል። ሆኖም ይህ ትውልድ ከጥፋት የሚድነውና ድሉን የሚያረጋግጠው ዛሬን በትጋትና በጽናት መጋፈጥ ሲችል ብቻ ነው። ሆኖም ተራራና ገደሉን፣ ሸንተረርና ወንዙን ሳይበግረን በጠንካራ ስራና በስትራቴጂ ማሸነፍ ስንችል ​ስትራቴጂያዊ ስፋት፡ ያሉበትን ቀጠናዎችና የቁጥጥር ክልሎችን በማስፋት የጠላትን እንቅስቃሴ መገደብ ስንችል ብቻ ነው። ​ አንድነታችን የአባቶቻችንን የጀግንነት ታሪክ በመስክ ላይ በተግባር መድገም ስንችል በአጠቃላይ የአሁኑ ትግል ተራ መከላከል ብቻ ሳይሆን፣ የቀጠናውን ፖለቲካዊና ወታደራዊ ካርታ የሚቀይር የነፃነት ጉዞ መሆን ሲችል ነው ለዚህም ካለንበት ቦታ ወጥተን ቁጥጥራችንን ማስፋትና በጠንካራ ተጋድሎ ማሸነፍ ብቸኛው አማራጭ ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል መሪ" አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ" 💪💪💪💪💪💪💪💪💪

አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ አፋብን ጎንደር /ጠ/ግዛት ዕዝ # ከጨጨሆ ሀሙሲት # ከበለሳ እብናት ደብረታቦር ድረስ እየፈፀማችሁ ያላችሁት ጀብዱ ትውልድ ሁሉ እየዘከረው የሚቀጥል አኩሪ ተጋድሎ ነው። ዓብ
አፋብን በላይ ዘለቀ ዕዝ አፋብን ጎንደር /ጠ/ግዛት ዕዝ # ከጨጨሆ ሀሙሲት # ከበለሳ እብናት ደብረታቦር ድረስ እየፈፀማችሁ ያላችሁት ጀብዱ ትውልድ ሁሉ እየዘከረው የሚቀጥል አኩሪ ተጋድሎ ነው። ዓብይ አህመድ ጦርነት የመተንኮስ እንጅ ጦርነትን በድል የመቋጨት ታሪክና ቁመና የለውም።ሊኖረውም አይችልም። በጎንደር የዓብይ ተላላኪ ካድሬ ሽሽት ላይ ነው።ቤተሰብ በማሸሽና ንብረት ዘርፎ እየተሰወረ ነው። እየሰጣችሁ ትረፉ !! የዓብይ አህመድን ሴራ አክሽፉ!! ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ

ሰበር!! ሁለተኛ ቀኑን በያዘዉ የ102ኛ ኮር የ22ኛ ክ/ጦር ትንቅንቅ ከባ/ዳር በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘዉ #ሰቀለት ላይ ተርቦች ፖራ-ሚሊታሪ አፈራርሰዉ ከጠላት የተለያዩ ምርኮዎች ተማርከዋል እስ
ሰበር!! ሁለተኛ ቀኑን በያዘዉ የ102ኛ ኮር የ22ኛ ክ/ጦር ትንቅንቅ ከባ/ዳር በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘዉ #ሰቀለት ላይ ተርቦች ፖራ-ሚሊታሪ አፈራርሰዉ ከጠላት የተለያዩ ምርኮዎች ተማርከዋል እስረኞች ተፈተዋል።የምርኮ ዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን!!

34ኛ ክ/ጦር በሉማሜ ከተማ የብልፅግና አመራሩን ሲገዲል ጃማ ከተማ ላይ ታሪክ ሲሰራ ውሏል ! የካቲት 5/2018 የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34 ክ/ጦር በትናንትናው ዕለት ሉማሜ ከተማ ላይ
34ኛ ክ/ጦር በሉማሜ ከተማ የብልፅግና አመራሩን ሲገዲል ጃማ ከተማ ላይ ታሪክ ሲሰራ ውሏል ! የካቲት 5/2018 የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር 34 ክ/ጦር በትናንትናው ዕለት ሉማሜ ከተማ ላይ የገቡት አዳኝ ቡድኖቹ ብልፅግና አለኝ በሚለው ወሳኝ አመራር የአዋባል ወረዳ ምክትል ስልጠና እና ክህሎት ሀላፊ አቶ አድሱ አለምነህ እስከወዳኛው ተሸኝቷል ። በሌላ በኩል ከቀኑ 6:00 ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ በጠላት ካምፕ ላይ በመግባት አመርቂ ድልን የተጎናፀፉት የ34ኛ ክ/ጦር አናብስት ፋኖዎች በጃማ ከተማ ላይ የመሸገውን የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል ። በዚህ ቀኑን ሙሉ የፈጀ ዉጊያ 2 ፖትሮል ሙሉ አስከሬን ሲያመላልስ እንደነበረ የአይን እማኞች የተናገሩ ሲሆን ከ15 በላይ የጠላት ሀይል ከባድ ቁስለኞች ሆነው ሆስፒታል ይገኛሉ ። በጃማ ከተማ ላይ ድል የቀናቸው የ34ኛ ክ/ጦር ፋኖዎች ምሽት ወደ ሉማሜ ከተማ በመግባት ጠላትን መግቢያ አሳጥተውት አድረዋል አዲስ ትውልድ ! አዲስ አስተሳሰብ ! አድስ ተስፋ ! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር

<< በህልውና ትግሉ አንድ እጁን ያጣ ቢሆንም፡ ስለ አማራ ሕዝብ ሲል ዛሬም በጦር ግምባር እየተዋደቀ የሚገኘው የጉናው የጦር ጠበብት )) ..................................................... ይሄንን የአማራይቱ ልጅ የጉና እንቁ ጀግና ተዋወቁት!👇 የልጅ አዋቂው አርበኛ ታድሎ አዳምጤ ይባላል። የዘረ ውባንተ ፍሬ ነው። በአማራ ሕዝብ ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከትዱር ቤቴ ካለ ድፍን አራት ዓመታትን አስቆጥሯል። በሰሜኑ ጦርነት ከጋሳኝ እስከ ጋሸና በርካታ ምሽጎችን የደረመሰ ተወርዋሪ ጀግና ነው። አልሞ ተኳሽ ባለ ስናይፐሩ የት አለ ከተባለ እሱ ይምጣ ይባላል። የስናይፐሩ ጠበብት የኢንፎርቲው ጌታ ነው። የአይኖቹ እይታቸዉ እንደ ንስር ነዉ ወኔው እና ጀግንነቱ እንደ አንበሳ ነው። ምላጭ የሚስብባቸዉ ጣቶቹ ለጠላት የተፈቀዱ ነዉ የሚመስሉት ፣ አይኖቹ እንደ አጉሊ መነፀር አቅርበዉ እና አርቀዉ እንዲያሳዩ ለሱ ብቻ ተፈቅደዋል። አርበኛ ታድሎ አዳምጤ የገደለውን ጠላት ለማወቅ በካዝናው ስንት የስናይፐር ጥይት ይዞ ነበር ብሎ መጠዬቅ ብቻ በቂ ነው። ጦሩን በወኔ በማነቃቃት በጉና ሰማይ ስር ለሚገኘው የጦር አበጋዝ ሁሉ የወኔ ስንቅ ነው። የቅንጦት ኑሮ ያላሸነፈዉ ጀግንነት ፣ በሀብትና በፀጋ ያልተበረዘ እና ያልደበዘዘ ወኔ ዛሬም በዱር በገደሉ እየተዋደቀ ይገኛል። የረገፉ ወርቅ እጆች ከትግሉ አላሸሹትም ዛሬም በጦር ሜዳ ከጠላት ጋር እየተዋደቀ ይገኛል። አርበኛ ታድሎ አዳምጤ!! በአሁኑ ሰአት በአፋብኃ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር አንድ ጉና ክፍለጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ ውስጥ ቁልፍ እና ወሳኝ ከሆኑ አርበኞች አንዱ አርበኛ ታድሎ አዳምጤ ነዉ። በትግሉ ሜዳ አሁን ድረስ እየተዋደቀ ያለ አርበኛ ጭምር ነዉ። ከብሬን እስከ ስናይፐር ፣ እንዲሁም ዲሽቃ አበጥሮ የሚተኩስ እና የክላሹ መሃንዲሱ ዛሬም በአንድ እጁ ጠላትን አበጥሮ የሚመታ ባለንስር አይኑ ለመጣ ለሄደዉ ጠላት ሁሉ የዕግር ዕሳት ሆኖ ቀጥሏል። በዕርግጥ ብዙዋቹ እንደ ታድሎ አዳምጤ አካላዊ ጉዳት ያስተናገዱ ቢኖሩም እሱ ግን አካላዊ ጉዳቱ ከትግሉ አላሸሸውም። በአንድ እጁ ተኩሶ ጠላትን የሚመታ እና የሚያስጨንቀው አርበኛ ታድሎ አዳምጤ ብቻ እና ብቻ ነው።. በነገራችን ላይ በአርበኛ ታድሎ አዳምጤ የትዉልድ ቀዬ እስቴ መካነየሱስ የተወለደዉ እና የአርበኝነት ምልክት የነበረዉ አርበኛ ሙላቴ በአንድ እጁ በመታገል እና ተኩሶ በመምታት ወደር የማይገኝለት ጀግና ነበር። ስአርበኛ ሙላቴ የዚህ ትግል ችቦ ለኳሽ አርበኛ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ እሱን የሚመስል ባለ አንድ እጅ ጉራማይሌ ተኳሽ ተክቶ ሂዷል። አርበኛ ታድሎ አዳምጤ መተኩስ ብቻ ሳይሆን የሰራዊቱ የወኔ ስንቅ ፣ የሞራል ምልዕክት እና የፅናት ተምሳሌት ጭምር ነዉ። ውድ ታላቁ የአማራ ህዝብ ሆይ ይህ አርበኛ ከእነ ፀዳሉ ደሴ ፣ ቆራጡ አንዳርጌ ጋር አብሮ የተገለ ታጋይ ነዉ። ታዲያ ሁለቱ ባንዳዎች ህዝብን ዘርፈዉ የዘረፉትን ተቀምጠዉ ለመብላት ዕጅ ሲሰጡ አርበኛ ታድሎ አዳምጤ ግን በአንድ እጁ እየተዋጋ ቀጥሏል። ፅናትን ከአርበኛ ታድሎ ያልተማሩ ሌቦች ዛሬ ላይ የአማራ ህዝብ መሳቂያ እና መሳለቂያ ሲሆኑ ባለአንድ እጁ ተኳሽ ግን እኔ ዕጅ ከምሰጥ ብሞት ይሻለኛል በማለት ከጠላት ጋር ተናንቆ ይገኛል። የውብአንተ ልጅ ፣ የገብርየ ልጅ ፣ የቴወድሮስ ትንፋሽ መሆን በዚህ ልክ ነው። ጎንደሬነት የሚለካዉ በእነዚህ ጀግና አርበኞች እንጂ በባንዳዎች አይደለም። በአንድ እጁ ከሚታገለዉ አርበኛ በላይ የሚከበርም ሆነ የሚወደድ አርበኛ የለም። ሊኖርም አይችልም። አማራነት መገፋት መሆኑን የሚገልፅ አርበኝነት ከዚህ በላይ የለም። በአንድ እጅ መታገል አማራ ምን አይነት የጭቆና ቀንበር ላይ እንዳለ የሚያሳይ ግልፅ ነገር የለም። "ጠላት ሲመጣ ገዳይ ወንበዴ፣ ከፊት ይቀድማል ታድሎ አዳምጤ" የተባለለትን ጀግና!✊ ጀግናው ድል ለአንተ እና ለጓዶችህ!🙏

በአውደ ውጊያ የተሸነፈው አገዛዝ በንፁሃን ላይ የድሮን ቦንቦችን በማዝነብ የጦር ወንጀል በመፈፀም ላይ ይገኛል። በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የበላይ ዘለቀ እዝ እና የጎንደር ጠቅላይ ግዛት እዝ በፈፀሙት ልዩ ተጋድሎ ከደቡብ እና ማእከላዊ ጎንደር በርካታ ወረዳወች የተጠራረገው የአገዛዙ ሰራዊት መሬት ይዞ መዋጋት ሲሳነው እና ከፍተኛ መፍረክረክ ሲደስርስበት ታይቷል። ይሁን እንጅ ይህ የሽብር አገዛዝ ሆን ተብሎ በታቀደ ሁኔታ ህዝብን በመጨፍጨፍ በሽብር መንገድ ወታደራዊ ሽንፈቱን ለመቀልበስ አስቦ ብዙ ንፁህን ላይ በተለይም የደብረ-ታቦር ከተማ ህዝብ እና የህዝብ ተቋማት ላይ ተከታታይ የድሮን ድብደባወችን አድርጓል። ትላንት የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ዒላማ የተደረገ የወገን ኃይል በሌለበት በቀቢፀ ተስፋነት ባደረጋቸው የድሮን ጥቃት እና ጅምላ ጨራሽ መሳሪያወችን በመጠቀም ሲቪሊያንን ጨፍጭፏል። በዚህም ደብረ-ታቦር ከተማ ላይ ብቻ ከግማሽ ቀን ባነሰ ጊዜ ውስጥ 16 ጊዜ በላይስትራቴጅክ ድሮኖችን በመጠቀም የአረመኔነት ባህሪውን አሳይቷል። በዚህ ጥቃት:- 1.የፈርጣ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ 2.የገብርየ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ 3.የዞን ጤና መምሪያ 4.የዞን ሲቪል ሰርቪስ እና ፋይናንስ ቢሮ 5.የቴዎድሮስ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ ማህበራዊ ተቋማትን እና ሌሎች የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ተቋማት አውድሟል። በመደበኛ እንቅስቃሴ ላይ እና በየቤታቸው የነበሩ የከተማ ነዋሪወችንም በድሮን ጨፍጭፏል። ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትን ጨምሮ አገዛዙ በንፁሃን ላይ የሚፈፅመው ጥቃት የሚያሳስባቸው ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ተቢዉን ሁሉ እንዲያደርጉ እናሳስባለን። አገዛዙ መሰል የጥፋት ተግባራትን ማቆም የሚችለው ከስልጣኑ ሲወገድ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚያደርገውን ፀረ-አገዛዝ ተጋድሎ አጠናክሮ ይቀጥላል።