ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 537
Suscriptores
+24824 horas
+5847 días
+97230 días
Archivo de publicaciones
ሰበር የድል ዜና
መጋቢት 19/2018 ዓ/ም
በአንኮበር ወረዳ ደረፎ መገንጠያ ላይ አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር አራተኛ ሻለቃ ቃኘዎች በዛሬው እለት ታሪክ ሰርተዋል።
መነሻውን ከአንኮበር አድርጎ እንቅስቃሴውን ወደ ደረፎ መገንጠያ ያደረገው ያረጋ ከበደ ስልጣን ጠባቂ 30ኛ ሻለቃ አድማ ብተናና ሚሊሻ በአንድ መኪና ተጭኖ ሲንቀሳቀስ የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦር 4ኛ ሻለቃ ነበልባሎቹ ቃኘዎች ቀድመው ገዢ ቦታ በመያዝ ጥላት ደረፎ መገንጠያ ላይ ሲደርስ በመኪና ላይ እዳለ ድገተኛ መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በጥላት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል።
ከሞተው የጥላት ሃይል መካከል ከአንኮበር ወረዳ ደረፎ ቀበሌ ልዩ ቦታው አጋምበረት ከሚባል አካባቢ ሚኒሻ የነበረች ላምሮት ጥላሁን የተባለች የብልፅግና ገረድና ሌሎች ዘጠኝ የጥላት ሃይል በተሰራው ኦፕሬሽን ላይመለሱ የተሸኙ ሲሆን ብዛት ያለው ቁስለኛ ጭኖ ወደ አንኮበር ወረዳ ፈርጥጦ ተመልሷል።
ነበልባሎቹ በፈፀሙት መብረቃዊ ጥቃት የተናደደው ጡት ቆራጭ ሀይል ያለ የሌለ ሃይሉን ይዞ ወደ ቦታው በሁለት አቅጣጫ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ከወሻውሽኝ የመጣው መከላከያ ሃይል ወደ ደበሌ ሲያመራ ሁለተኛው ከአንኮበር የመጣው አድማ ብተና ደረፎ መገንጠያ መግባት አቅቶት ውርደቱን እደተከናነበ ተመልሷል።
በሌላ ዜና ከአንኮበር ወረዳ እና አልዩ አምባ ከተማ ያለው የአገዛዙ ሰራዊት በተከታታይ ቀናት እየፈረሰ እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦርን እየተቀላቀለ ይገኛል።
አፋብን የሰጠውን የምህረት አዋጅ በዛሬው እለት ተቀብለው አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦርን የተቀላቀሉ አድማ ብተናውች፦
1,ቢተው ደሴ ከ29ኛ ሻለቃ ከሻበል ሁለት ሲሆን ሁለት እግር ክላሽ ከዘጠና ጥይት ጋር
2, ም/አ/ አለቃ ልጃለም ደሳለኝ ከ29ኛ ሻለቃ ከሻበል ሁለት ከአልዩ አምባ አንድ እግር ክላሽ ከዘጠና ጥይት ጋር ህዝባችንን ለሚያሰቃይ ስርአትና ለወደቀ አገዛዝ አንተባበርም በማለት ከአልዩ አምባ ከተማ በመክዳት አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ጦርን በሰላም ተቀላቅለዋል።
፦መረጃውን ያደረሠን የእቴጌ ጣይቱ ክ/ጦር ህ/ግንኙነት ክፍል
፦ድል ለአማራ ህዝብ
፦ክብር ለተሰው ሰምዓታት
፦አፋብን ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ መሐመድ ቢሆነኝ ኮር ሚዲያና ኮሚኒኬሽን
+3
ልማደኛው ደጃዝማች ፬ኛ ኮር
በ4 አቅጣጫ የመጣውን ጠላት እያበራየው ነው።ወታደራዊ ተሽከርካሪ፣አመራር እና ቁጥሩ የበዛ የጦር መሳሪያ ከነ ተተኳሹ በጠዋቱ መብረቃዊ ጥቃት ሲማረክ የጋለው መሬት መቀበሪያው የሆነው ስፍር ቁጥር የለውም።
አፋብን በላይ ዕዝ ደጃዝማች ፬ኛ ኮር 🔱🔱🔱
ህልውናችን በአርበኝነታችን!!
ዮለንስ ንጉሱ ሙጨ
መጋቢት 19/2018 ዓ.ም
የአድማ ብተና አባሉ ዋርድያውን ገድሎ ፋኖን ሲቀላቀል ፋኖን ከድቶ ለአገዛዙ ሲያገለግል በነበረ ባንዳ ላይ እርምጃ ተወሰደ‼️
አማራ ላይ የሚደርሰውን የዘር ፍጅት የተረዳ የአድማ ብተና አባሉ መላክ ዳኛቸው ህዝብን ሲዘርፍና ሲያሰቃይ የነበረን ጠላት ዋርድያ በወጣበት በመግደል እና አንዱን በማቁሰል ኮሪያ ክላሽ ከነ ሙሉ ትጥቁ በመያዝ በትላንትናው ዕለት ከባሶሊበን ወረዳ ኮርክ ከተማ ከሚገኘው የጠላት ካምፕ በመውጣት ተአምረኛው 34 ክ/ጦርን ተቀላቅሏል።
በሌላ በኩል በባንዳ ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ የሚገኘው 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦር በትላንትናው ዕለት ምሽት 2:05 ላይ በደጀን ወረዳ የላኛት ላገኔ ቀበሌ የጓደኛውን ትጥቅ በመያዝ ወደጠላት ተቀላቅሎ የነበረ ባንዳው ሞስዬ መኩሪያው ላይ እርምጃ ወስዷል።
ባንዳው ሞስዬ መኩሪያዊ የየላኛት ላገኔ ጊዜያዊ አስተዳደር ሆኖ ሲሰራ ከቆየ በኋላ የጠላትን እኩይ ሴራ በመሸከም ለፋኖ የሚያገለግሉ ስዎችን ግንኙነት አላቸው በማለት ሲያስገድል ከቆየ በኋላ ወደ ጠላት ተቀላቅሎ ለስለላ በገባበት ገብተው ጀግኖቹ የ34ኛ ክ/ጦር አባላት እስከወዳኛው ሸኝተውታል።
በተጨማሪም የአገዛዙን መፈራረስ የተረዳው የመከላከያ ሰራዊት አባሉ ደርባባው አየነው የትኖራ ከሚገኘው የጠላት ካምፕ ቃኝና መሀንድስ በመውጣት 34ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል ።
ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ34ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል!
19/ዐ7/2018 ዓ.ም
+1
Honorable President Kikwete,
The Amhara Fano National Movement has the honor of extending its sincere congratulations on your recent appointment by the African Union Commission.
በጎንደር ከተማ ዘር ተኮር ግፍና በደሉ ተጠናክሮ ቀጥሏል!!
ሊቀ ትጉሃን ስሙር መክበብ ይባላል።በተለያዩ አብያተ ቤተ ክርስቲያናት መንፈሳዊ አገልግሎት በማገልገል እንዲሁም ቤተ ክርስቲያናት በማሰራትና በማህበራዊ በጎ ጉዳዮች ሁሉ ግንባር ቀደም ተሳታፊና አስተባባሪ በመሆኑ በጎንደር ከተማና አካባቢው ወረዳዎች ከፍተኛ አንቱታን ያተረፈ አገልጋይና ሊቅ ነው።
የአማራ ህዝብ በደልና መከራ አንገሽግሾት የአማራ ፋኖን በመቀላቀል የጎንደሬ በጋሻው ክ/ጦርን በአመራርነት በህልውና ትግላችን ተጠቃሽ የጎላ ተግባር በስራት ላይ ይገኛል።
የሊቀ ትጉሃን ስሙር መክበብ ከፋኖ ጎን መቆም ያስበረገገው የኦህዴድ / ብልፅግና ፍርስራሽ አገዛዝ የአርበኛ ሊቀ ትጉሃን ስሙር መክበብ ቤተሰቦችን በጎንደር ከተማ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ አግቶ ዘር ተኮር ግፍና በደል እየፈፀመ ይገኛል።
1ኛ...ጥሩ አስማማው (የትዳር አጋር)
2ኛ... ቤዛዊት ስሙር (ልጅ)
3ኛ ...ስለቴ ስሙር (ልጅ) የተባሉ የአርበኛ ሊቀ ትጉሃን ስሙር መክበብ ባለቤትና ነብስ ያላወቁ ህፃናትን በመናገሻዋ ከተማ ጎንደር እምብርት አግቶ ዘር ተኮር ግፍና በደል እየፈፀ ይገኛል።
እንደ አብነት የጥቂት አርበኛ ቤተሰብ ላይ የተፈፀመውን የእገታ ወንጀል እናሳውቅ እንጅ ድርጊቱ በሁሉም አርበኛ ቤተሰብ ላይ ያነጣጠረ ዘር ተኮር ጅምላ እገታና ሸብር በመፈፀም ንፁሃን ወገኖቻችን ከመበደልና ተሻጋሪ የወንጀል በቀል ከመትከልና ፋኖን በጭካኔ ከማነሳሳት የዘለለ የሚያሳካው አንዳችም ግብ የሌለው ሲሆን መሰል ወንጀሎችን በፈፀሙና ባስፈፀሙ እንዲሁም በቸልታ ጉዳዩን በተመለከቱ ላይ ከተለመደው በላይ ኮምጨጭ ያለ አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት እንደምንገደድ እናስጠነቅቃለን።
ህልውናችን በአርበኝነታችን!!
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
በምስራቅ አማራ (ወሎ) የሚንቀሳቀሰው የምኒልክ ዕዝ አዲስ ወታደራዊ መዋቅር ይፋ አደረገ
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ስር የሚገኘውና በወሎ ቤተ-አማራ ቀጠና የሚንቀሳቀሰው ምኒልክ ዕዝ፣ ትግሉን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና ድርጅታዊ አቅሙን ለማጎልበት አዲስ ወታደራዊ አሰላለፍ ይፋ አድርጓል።
ዕዙ ላለፉት ሶስት ዓመታት ከ26 በላይ ክፍለ ጦሮችን በማስተባበር በርካታ ወታደራዊ ጀብዱዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። እነ አርበኛ ሞላ ደስየ፣ መሀመድ ቢሆነኝ፣ አሸናፊ አለሙ፣ ሲልአምላክ ደጉ፣ አደም አሊ እና ይታገሱ አራጋውን የመሰሉ ጀግኖች የተሰዉለትን የሕዝብ የመኖርና ያለመኖር ትግል በላቀ ወታደራዊ ጥበብ እየመራ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት ዕዙ ራሱን በ6 ኮሮች፣ በ22 ክፍለ ጦሮች እና በአንድ ልዩ ዘመቻ በድጋሚ በማዋቀር ዝግጁነቱን አረጋግጧል።
የዕዙ አዲስ የወታደራዊ መዋቅር ዝርዝር
የምኒልክ ዕዝ የኮር እና የክፍለ ጦር ስያሜዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
| የኮር ስያሜ | በስሩ የሚገኙ ክፍለ ጦሮች |
|---|---|
| 101ኛ ኮር | 11ኛ፣ 15ኛ እና 35ኛ ክፍለ ጦር |
| 102ኛ ኮር | 12ኛ፣ 49ኛ እና 65ኛ ክፍለ ጦር |
| 303ኛ ኮር | 14ኛ፣ 16ኛ፣ 19ኛ፣ 21ኛ እና 81ኛ ክፍለ ጦር |
| 104ኛ ኮር | 23ኛ፣ 24ኛ እና 25ኛ ክፍለ ጦር |
| 105ኛ ኮር | 29ኛ፣ 33ኛ፣ 45ኛ፣ 47ኛ እና 71ኛ ክፍለ ጦር |
| 106ኛ ኮር | 22ኛ፣ 31ኛ እና 34ኛ ክፍለ ጦር |
ተጨማሪ መዋቅር፦
* የዕዙ ልዩ ዘመቻ ክፍለ ጦር
በኦሮሞ ታጣቂዎች በግፍ የተጨፈጨፉት የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች በጅምላ በስካባተር ተቀበሩ‼️
" ሰባቱ ወዲያው ተገደሉ። አንዱን የሞተ መስሏቸው ጥለውት ሄዱ። አልሞተም ግን እግሩ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። ስድስቱ በሰፊ ጉድጓድ በአንድ ቦታ ተቀብረዋል " - የፋብሪካው ሠራተኞች
➡️ " አንድ የከባድ መኪና ሹፌር እና ረዳትም ተገድለው ተገኝተዋል። የሰዎች መታገት የተለመደ ሆኗል። የጸጥታ አካላት አሉ ግን እያዩ እንዳላዩ ነው የሚሆኑት " - ነዋሪ
በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችን እና ሌሎችን ጨምሮ በሁለት ቀናት ብቻ ዘጠኝ ሰዎች ሲገደሉ፣ ሌሎች መጎዳታቸውን የፋብሪካው ሠራተኞች እና ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ጉዳዩን ያጣራ አንድ የአካባቢው ነዋሪ በሰጠን ማብራሪያ፣ የፋብሪካው ሠራተኞች በታጣቂዎች የተገደሉት መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም መሆኑን ገልጾ። " አንድ የፋብሪካውን አመራር ለማጥቃት ሂደው ነው ሰባቱን አጃቢዎቹን የገደሏቸው " ብሏል።
ጥቃት አድራሾቹ፣ " መሬታችን ተወስዷል " የሚል ጥያቄ እንዳላቸውም ገልጿል። ጥቃቱ የደረሰው " ጮሬ " በሚባለው የፋብሪካው ካምፕ መሆኑን ያስረዳው ነዋሪው፣ " ሟቾቹ የስኳር ፋብሪካው የጥበቃ ሠራተኞች ናቸው። ታጣቂዎቹ ድንገት መጥተው ተኩስ ፈጽመውባቸው ወዲያው ነው ጫካ የሚገቡት " ሲልም ተናግሯል።
በተያያዘ፣ " ሰባቱ ሰዎች ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፊት መተሐራ እና ወለንጭቲ መካከል የከባድ መኪና ሹፌር እና ረዳትም ተገድለው ተገኝተዋል። በአካባቢው የሰዎች መታገት የተለመደ ሆኗል። የጸጥታ አካላት አሉ ግን እያዩ እንዳላዩ ነው የሚሆኑት " ሲልም ገልጿል።
ሌላኛው ነዋሪ፣ ከ2010 ጀምሮ በየዓመቱ እስከ ዘጠኝ ሰው " የሚገደልበት " ሁኔታ መኖሩን አስረድተው፣ " ህዝቡ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እያገኘ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።
የሰሞኑን ጎድያ በተመከለተም፣ " በአንድ መኪና ላይ ነው ሰባቱንም የመንግስት ተቀጣሪዎች፤ የስንት ልጆች አባቶችን በአንድ ቀን ገድለውብናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ሰሞኑን የተገደሉት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች " ትልልቅ ሰዎች ናቸው " ሲሉ ያስረዱ አንድ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ የፋብሪካው ሠራተኛ ደግሞ፣ ጥቃቱን " አሳዛኝ " ሲሉ ጠርተውታል።
ሰባቱ ሠራተኞች የተገደሉት አንድ የፋብሪካውን አመራር አጅበው በነበረበት ወቅት መሆኑን ተናግረዋል።
የታጣቁት አካላት የፋብሪካው ሠራተኞች ላይ ተኩስ የከፈቱባቸው " ገና ከፒካፕ መኪና ላይ ሳይወርዱ " መሆኑን፣ በዚህም ሌሎቹ ሲገደሉ አብረው የነበሩት አመራሩ " የውሃ ቦይ ውስጥ ገብተው፣ እየተሳቡ " የተኩሱን ቦታ በመራቅ በህይወት መትረፋቸውን አስረድተዋል።
እኚሁ የፋብሪካው ሠራተኛ፣ ይህ ጥቃት ተፈጽሟል ብሎ ለመናገር እንኳ ከፍተኛ ስጋት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ሌላኛው የፋብሪካው ሠራተኛ በበኩላቸው፣ ግድያው የተፈጸመበት " ጮሬ " በተሰኘው ቦታ አጠገብ መሆኑን ገልጸዋል።
በአጠቃላይ ከሟቾቹ ጋር ዘጠኝ ሰዎች ነበሩ ብለው፣ " ሰባቱ ወዲያው ተገደሉ። አንዱ የሞተ መስሏቸው ጥለውት ሄዱ። አልሞተም ግን እግሩ ከጥቅም ውጭ ሆኗል። አንዱ ደግሞ ተርፏል " ብለዋል። " ስድስቱ በሰፊ ጉድጓድ በአንድ ቦታ ከክብር በታች በሆነ መንገድ በመንግስት ስካባተር አስቆፍረው በዚያው ገደል በጅምላ ተቀብረዋል " ነው ያሉት።
አዲስ የመጡት የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ ለሟች ቤተሰቦች " በየቤታቸው ሂደው ለእያንዳንዳቸው 150 ሺሕ ብር ሰጥተዋል። 'የተማረ ልጅ ካላቸው በቋሚነት ሥራ እንቀጥራን፣ ካልተማሩ በመደብ 6 የአባታቶቻቸውን ቦታ ይይዛሉ' ሲሉም ቃል ገብተዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ ያለውን ድባብ ሲያስረዱ ደግሞ፣ ለጊዜው "መከላከያ ገብቷል" ብለዋል።
የአካባቢው ነዋሪ ግን፣ " በአካባቢው የጸጥታ ችግር ተንሰራፍቷል። በሰላም ወጥቶ መግባት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል " ሲሉም የሁነቱን አሳሳቢነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ከአንድ ወር በፊት ሁለት ልጆች ታግተው 2 ሚሊዮን ብር ተጠይቆባቸው ነበር። 2 ሚሊዮን ብር ተሰብስቦ አንድ ልጅ ወስዶ ሰጣቸው። በኋላም ለቀቋቸው። ከፍተኛ ድብደባ እና ራሳቸውን እስኪስቱ ድረስ የረሃብ ስቃይ አድርሰውባቸው መንገድ ላይ ነው የጣሏቸው " ሲሉም አስታውሰዋል።
" ገንዘቡን ያደረሰው ልጅ ግን ተገድሏል" በማለት አዝነዋል። ከመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መካከል አንዱ በበኩላቸው፣ ታጣቂዎቹ "ከአዳማ መተሐራ መንገድ በኃይለኛው እያገቱ ነው፤ ተሳፋሪም መውሰድ ጀምረዋል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የስኳር ፋብሪካውንም ሆነ ሌሎች የአካባቢውን ኃላፊዎች ለማግኘት ለቀናት ያደረገው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን፣ ጥረቱ ይቀጥላል።
#መረጃዎችን #ሸር በማድረግ የሚዲያችንን የድል ራዕይ ያስቀጥሉ!
መጋቢት 18/2018 ዓ.ም
ተኩላውን ከማባረር ይልቅ በጎችን እንሰብስብ
እንድንመራ የተሰጠን ድርጅት ነው ! ግዙፍ የታጠቀ ኃይል ያለበት ተቋም። በእንባ የራሰ ጉንጭ በልቅሶ የደበዘዘ አይን ተስፋ የጣለበት የትውልዱ መዳኛ የህዝብ መሰባሰቢያ አዳራሽ ነው። ትኩረታችን ከአላማችን ጋር ይሁን መንገዳችንም ነፃነት ወደሚነፍስበት ተራራ እናድርግ።
የአማራ ህዝብ እልቂት ! የዘር ፍጅትና መንግስታዊ ጭፍጨፋ መቼም የትም ቢሆን የምንዘነጋው አይሁን ።ጠላቶቻችን አምርረው የሚዋጉን የተለየ ሀጢያት በደል ኑሮብን አይደለም ይልቁንም ምድር ላይ እንዳንኖር ዘራችንም እንዳይገኝ መጠሪያችን እንዲጠፋ አማራዎችም እንዳንባል ስለሚፈልጉ እንጅ።
ስንፍና ከላያችን ላይ ይራገፍ ድንቁርናም ከአዕምሯችን ይላቀቅ ።
የጠላቶቻችንን አንደበት የሚሰማ ጀሮ ይዳፈን ወገኑን የሚገድል ባንዳ አንገቱ ይቀላ እኛ የምድር ታጋዮች ሚሊዮኖችን ለማሰለፍ እንትጋ እንድከም የጀግናውን ህዝብ ልጆች አሰልጥነን አስታጥቀን ለአማራነቱ የሚፋለም ለክብሩ የሚዋደቅ አርበኛ እናፍራ። ተኩላዎችን ከማባረር ይልቅ በጎችን እንሰብስብ ያኔ ተመሳስለው ከጉያችን የተወሸቁት ሁሉ በበረሀው አውሎ ንፋስ ይጠረጋሉ አሊያም ትቢያ ይለብሳሉ።
እኛ ጠላቶቻችን ላይ እናተኩሩ መንገዳቸውንም አላማቸውንም እናሳጥር አላማችንም ያ ይሁን ሽንፈታቸውም በመቃብራቸው ላይ ይጻፍ ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
ማጥራትና ማብቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል!!
✅ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲሰጥ የነበረው የኮር የግምገማ ስልጠና ተጠናቀቀ✔️
ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲሰጥ የነበረው የኮር የግምገማ ስልጠና በውጤት ተጠናቀቀ። ይህ ስልጠና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) መመስረትን ተከትሎ የትግሉን አቅጣጫ፣ አደረጃጀትና አመራር በአዲስ መልክ ለማደራጀት ተካሂዶ ውጤታማ እንቅስቃሴ እየተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።
እንደሚታወቀው ሰሜኑ የጎንደር ክፍል በርካታ ተጋድሎዎችን በማድረግ ለበርካታ አመታት በትግል የሚታወቀው ይህ ቀጠና ሰራዊቱንና ህዝቡን በማስተባበርና አደራጅቶ በመምራት በኩል የሚያስፈልገውን ጥልቅ ግምገማ በማድረግ በርካታ የፖለቲካና ወታደራዊ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ በኩሩ ተገልጿል። በፍጥነት እያከናወነ ያለው የፋኖ አደረጃጀትና የትግል መስመር እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በመውረድ ሰራዊት በማንቃት በማጥራትና በማሰልጠን ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲሰጥ የነበረው ጠንካራ የግምገማዊ ስልጠና በዛሬው ዕለት በርካታ ውሳኔዎችን በማሳረፍ መልሶ የማደራጀት ስራውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።በመጨረሻም ከዚህ በፊት መጠሪያውን ራስ አሞራው ውብነህ ሶስተኛ ኮር ይባል የነበረው የበላይ ዕዝ የኮር አደረጃጀት ከዛሬ ጀምሮ 208ኛ ኮር ተብሎ ተሰይሟል ሲል የኮሩ መረጃ ያመላክታል።በዚህ የቀጠለው የሰራዊት ግንባታ እና ነፃ የወጡ ቀበሌዎችን የማስተዳደርና የማደራጀት የኮሩ ዋና ተግባራት ደጀን የሆነውን ህዝባችን በተጓተተ የትግል አካሄድ የነበረውን ድክመትም ህዝባችንን ይቅርታ በመጠየቅ በብርሃን ፍጥነት ህዝባችንን ማሻገር አለብን ሲል የኮሩ ግምገማ ያመላክታል ተብሏል። በግምገማው የማጠቃለያ ምዕራፍ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከፍተኛ አመራሮችና የበላይ ጠባቂ አባት አርበኞችም ስብሰባውን በማስጀመርና በመዝጋት ሃሳባቸውን ገልፀዋል ተብሏል።በሌላ በኩል የአፋብን ምክትል ሊቀመንበር ለወታደራዊ ጉዳይ አርበኛ ሃብቴ ወልዴም በማጠቃለያ ግምገማው ተገኝተው የማጠቃለያ ንግግር ሰተዋል።በዚህ ማብራሪያቸውም አማራን እንኳን ትጥቁን ቀበቶውን እናስፈታዋለን ያለውን የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ የጠላት ሰራዊት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት የምንሰጥበት ወቅት በመሆኑ እርስ በራሳችሁ ሳትገፋፉ በመደጋገፍ በየመክሊታችሁ በቅንነት ከጠላት ላይ እርብርብ እንድታደርጉ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።በጨረሻም የአማራን ህዝብ መምራትና ማስተባበር የታደለ መሪ ነው ሲሉ አክለዋል ለዚህም ዋናኛ ምክንያቱ ደግሞ ጠዋት ቤተ-ክርስቲያን ላይ ወይም መስጊድ ላይ ቁመህ ከስአት ጦርነት ግባ ስትለው ወደ ኋላ ሳይል ለጦርነት የሚቀርብን ህዝብ ነው እየመራን ያለነው ሲሉ የህዝቡን ተሳቶፎና ተባባሪነት ገልፀዋል።በዚህ የግምገማ የማጠቃለያ ምዕራፍም አርበኛ ሰፈር መለሰ እና አርበኛ እሸቴ ባየም በመገኘት ለትግሉ ይጠቅማል ያሉትን መልዕክት አስቀምጠዋል።በዚህ የግምገማ ስልጠና ኮሩን ደከመኝ ሰለችኝ ሳይሉ ሲያስተባብሩ ለነበሩ የዕዙ ግብረ-ሃይል አባላትና አመራሮችም ማለትም
✔️አርበኛ አስምሮ ፍቃዴ የበላይ ዕዝ ከፍተኛ አመራር የግብረ-ሃይሉ ሰብሳቢ
✔️አርበኛ ሻጋ ጌታቸው የበላይ ዕዝ ም/ወ/አዛዥ-አባል
✔️አርበኛ አስፋው ሰርፀ የበላይ ዕዝ ዕ/ዝ/ መምሪያ ኃላፊ-አባል
✔️ አርበኛ ዶ/ር እያቸው ብርሃኑ የበላይ ዕዝ ም/ጤና መምሪያ ኃላፊ -አባል
✔️ እና ሌሎችም ላስተባበሩና ተግባሩን በቀጥታ ለመሩ የቀጠናው የዕዝ አመራሮች ምስጋና በማቅረብ ለዚህ ግምገማና ስልጠና ተፈፃሚነት የተግባር ቁርጠኝነት ይረዳ ዘንድ የኮሩን የመልሶ ማደራጀት መዋቅር የቁርጥ ቀን ልጆቹን በጥልቀት በመገምገም እንደሚከተለው ሰይሟል።
1. ዋና አዛዥ................አርበኛ ወርቁ ሙሉ
1.1. ወ/ቃል አቀባይ.....አርበኛ ሳሙኤል አበራ
1.2. ጽ/ቤት ኃላፊ....አርበኛ አብረሃም ኢያሱ
1.3.ህግና ስነምግባር ክፍል......አርበኛ ጌታቸው ጌጡ
1.4. ወታደራዊ መረጃና ደህንነት..........#####
2. ምክትል ወ/አዛዥ..................አርበኛ ማሩ አዴ
2.1. ዘመቻ መምሪያ ....... አርበኛ ፶አለቃ አስራት ጌታቸው
2.2 ም/ዘመቻ መምሪያ.........አርበኛ የሽበር አስማማው
2.3. ልዩ ኦፕሬሽን ......አርበኛ መቶ አለቃ ባምላኩ ጌታቸው
2.4 መገናኛ ....... አርበኛ ኮማንዶ ስመኘው ይስማው
2.5 ወታደራዊ ስልጠና ...... አርበኛ አለቃ አለሙ ሙሌ
2.6 ም/ወ/ስልጠና.............አርበኛ ሃብታሙ ምህረቴ
2.7 ቃኝና መሀንዲስ ............አርበኛ ጤናው አየነው
3. የፖለቲካ ኃላፊነት...........አርበኛ ፃዲቅ ዋለልኝ
3.1 ም/ፖለቲካ ኃላፊነት .........አርበኛ ማርሸት አሰፋ
3.2 ም/አደረጃጀት መምሪያ.............አርበኛ ንጉሴ አገኘሁ
3.3 ህዝብ ግንኙነት........አርበኛ ዘመነ ተሾመ
3.4 ህዝብ አስተዳደር ..........አርበኛ ፍቅሩ የማታው
3.5 ም/ህዝብ አስተዳደር..........አርበኛ የሽበር አጥናፉ
3.6 ቀጠናዊ ትስስር ...............አርበኛ ጥሩየ ቀናው
3.7 ትም/ትና ስልጠና.......አርበኛ እሸቱ ዘነበ
3.8 ም/ትም/ትና ስልጠና........ቄስ ገ/ስላሴ ነሲቡ
3.9 ወጣቶችና ሴቶች ........አርበኝት ኮማንደር አታላ አለሙ
4. ወ/አስተዳደር ኃላፊ ........አርበኛ ይርጋ ክቡሬ
4.1. ም/ወ/አስተዳደር ........አርበኛ ሰፊው ሙላት
4.2. የሰው ሀይል...........አርበኛ እማምነው መርቆ
4.3. ፋይናንስና ግዥ .........አርበኛ ማርሸት ንጋት
4.4 ም/ፋይናንስና ግዥ............አርበኛ ጌጡ መልካሙ
4.5 ሀብትና ንብረት አፈላላጊ .......አርበኛ በውቀት አላቸው
5. ሎጂስቲክ ኃላፊ ...........አርበኛ በሬ አወቀ
5.1. ም/ሎጀስቲክ ...........አርበኛ ብርሀን ወርቄ
5.2. ኦርዲናንስ ............አርበኛ ማርየ በለጠ
5.3. ህክምና ክፍል ሀላፊ .......አርበኛ ዶ/ር ቢልልኝ መሳፍንት
6. ኦዲት ክፍል ሰብሳቢ .......አርበኛ ሻንበል ጣመ ዋለልኝ
በመጨረሻም ለአመራሩ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የቀጠና የስራ ስምሪት በስራ አመራሮቹ በኩል የተሠጠ መሆኑን ተገልጿል።
ከበላይ ዕዝ 208ኛ ኮር የህዝብ ግንኙነት መምሪያ!!!
የብልፅግና መከላከያ ሠራዊት እና የሚኒሻ አባላት እርስ በእርስ ተዋጉ!
የራያ ቆቦ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ቆቦ ከተማ በአገዛዙ ወታደሮች መካከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእርስ ግጭት የአንድ ሚኒሻ አባል ሕይወት ሲያልፍ የሟቹ ሚኒሻ አባል የትዳር አጋርን ጨምሮ ሌሎች የሚኒሻ አባላት መቁሰላቸውን የመረብ ሚዲያ የምስራቅ አማራ ቀጠና ዘጋቢው ለማረጋገጥ ችሏል።
ግጭቱ የተቀሰቀሰው በመከላከያ ሰራዊት እና በሚኒሻ አባላት መካከል ሲሆን፡ መከላከያ ሠራዊቱ "ግልገል ፋኖ" ብሎ በሚጠራቸው የሚኒሻ አባላት ላይ ጥብቅ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ታውቋል።
በግጭቱ ምክኒያት "ወገናችን የመከራ መአት እየወረደበት ለጥቂት ገንዘብ ስንል ከአገዛዙ ቆመንም የምንገደል ከሆነ ወንድሞቻችን እንዳደረጉ ያርጉን" ያሉ የሚኒሻ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው ጠፍተው ፋኖ ወዳለበት ቀጠና መሄዳቸው ነው የተነገረው።
መጋቢት አስራ ስምንት (18) ቀን ሺህ ስምንት መቶ ሰባ (1870) ዓመተምህረት‼️
#ዝክረ_ታሪክ
ከአንድ መቶ አርባ ስምንት (148) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ታሪክን የኋሊት!!
ከዛሬ አንድ መቶ አርባ ስምንት (148) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት አጼ ዮሐንስ አራተኛ እና የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በወሎ ቦሩ ሜዳ ላይ ተገናኝተው ንጉሥ ምኒልክ የንጉሥ ነገሥቱን የበላይነት መቀበላቸውን አጼ ዮሐንስ ደግሞ የምኒልክን በሸዋ ላይ ንጉሥነታቸውን በመተማመን ስምምነት የተፈራረሙበት እና ንጉሥ ነገሥት አጼ ዮሐንስ ለንጉሥ ምኒልክም ዘውድ የጫኑላቸው ዕለት ነበር።
ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ ከሞቱ በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሥ ነገሥት ለመሆን ብዙ ኃይል እያደራጁ ይጠባበቁ የነበሩት የትግራዩ ደጃዝማች ካሳ ምርጫ እና የሸዋው ምኒልክ ኃይለ መለኮት ነበሩ፡፡ በወቅቱ የተሻለ የኃይል የበላይነት የነበራቸው ደጃዝማች ካሳ ምርጫ ጥር አስራ ሦስት (13) ቀን ሺህ ሰምንት መቶ ስልሳ አራት (1864) ዓመተምህረት በእለተ እሁድ #በአክሱም_ጽዮን ቤተክርስቲያን #በጳጳሱ_አቡነ_አትናቴዎስ እጅ ተቀብተዉ ‹‹ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ግርማዊ ዮሐንስ ራብዓዊ ስዩመ እግዚአብሔር ንጉሥ ጽዮን ንጉሥ ነገሥት ዘኢትዮጵያ›› ተብለው ነገሱ።
የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ ግን የአጼ ዮሐንስ አራተኛን ንጉሥ ነገሥትነት ለመቀበል አመነቱ፡፡ ራሳቸውንም ‹‹ንጉሥ ነገሥት›› ብለው ሰይመው ነበርና፡፡
አጼ ዮሐንስ አራተኛም ንጉሥ ነገሥትነታቸው በንጉሥ ምኒልክ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ብዙ አይነት ጥረቶችን ሰላማዊ ማሳሰቢያ እና የኃይል እርምጃ ማስጠንቀቂያ አደረጉ፡፡ በመጨረሻም መጋቢት አስራ ስምንት (18 ) ቀን ሺህ ስምንት መቶ ሰባ (1870) ዓመተምህረት ሁለቱ መሪዎች ንጉሥ ምኒልክ (ንጉሥ ሸዋ) የንጉሥ ነገሥት አጼ ዮሐንስ አራተኛን ደግሞ የበላይነት ማለትም ንጉሥ ነገሥትነት የተቀበሉበትን እና አጼ ዮሐንስ አራተኛም ደግሞ የምኒልክን የሸዋ ንጉሥነት የተቀበሉበትን ወይም ያፀኑበትን ስምምነት ሸዋ ውስጥ ልቼ በተባለ ቦታ ላይ ተስማምተው የተፈራረሙት ዕለት ነበር፡፡
በስምምነቱ መሰረት ንጉሥ ምኒልክ «ንጉሥ ነገሥት» የሚለውን ማዕረግ መጠቀም እንዲያቆሙ ተስማሙ፡፡ ንጉሥ ነገሥት አጼ ዮሐንስ አራተኛም «አባቶችዎ ባቀኑት አገር ንጉሥና ጌታ ነዎት፡፡ ስምምነታችንን እስካከበሩ ድረስ ስልጣንዎን አከብራለሁ፡፡ መንግሥትዎን ያጠቃ እኔን እንዳጠቃ ጦርነት ያወጀብዎንም በእኔም ላይ እንዳወጀ እቆጥረዋለሁ» በማለት ንጉሥ ምኒልክ ከአባቶቻቸው የወረሱትን የሸዋ ንጉሥነት አጸደቁላቸው፡፡ ንጉሥ ምኒልክም በሺህ ሰምንት መቶ ሰባ አራት (1874) ዓመተምህረት ለኢጣሊያ መንግሥት በፃፉት ደብዳቤ «ከአባቴ ከአጼ ዮሐንስ አራተኛ ጋር ታረቅሁኝ፡፡ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነናል» ብለዋል፡፡
የልቼ ስምምነት በአጼ ዮሐንስ አራተኛና በንጉሥ ምኒልክ (ሽዋ) መካከል ከአስር (10) ዓመታት በላይ የዘለቀ ቤተሰባዊ ዝምድናና አንጸራዊ የሆነ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር ያደረገ ውል ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ስምምነቱ ንጉሥ ምኒልክ ጎበዝ ዲፕሎማት መሆናቸውን ያሳዩበትና የወደፊት የንጉሥ ነገሥትነት ጉዟቸውን በብልሃት ያሳመሩበት እንደነበርም ብዙ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።
#የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️
#ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️
ምንጭ፦ ልዑል ዓምደጽዮን ሠርፀድንግል
18/ዐ7/2018 ዓ.ም
👉የትግራይ አዲስ አስተዳደር በአዲስ አበባ እየተቋቋመ ነው።
👉አዲስ አበባ የከተሙት የህወሓት ተቃዋሚ ጀነራሎች እና ፖለቲከኞች የትግራይን ጊዜያዊ አስተዳደር ለመረከብ እየተዘጋጁ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራ ነው።
👉በእነ ጀነራል ጻድቃን የሚመራው ሰብስብ ወደ ትግራይ ሰብሮ ለመግባት አፋር የመሸገውን ሓራ መሬት ወይም የትግራይ ሰላም ኃይል ወታደራዊ ክንፍ በሎጅስቲክ ፌደራሉ እያጠናከረ ይገኛል,ይኸ የሚሆነው ጀኔራል ታደሰ ወረደን የስልጣን ጊዜው እያበቃ ስለሆነ እሱ የሚባለውን ካልፈፀመ ለመተካት ነው።
🌈አዲስ አበባ የተደራጀው ኃይል ፖለቲካዊና ወታደራዊ ክንፉን በማጠናከር ወደ ትግራይ መግባት እና አሁን ያለውን ስርአት ወያኔን ማስወገድ, ካልሆነ ተገዳዳሪ ሀይል መፍጠር ችግሩ ከትግራይ እንዳይወጣ ማድረግ ነው።
👉 ይኸን ሀይል የሚመሩት ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ፣ ብርጋዴር ጀነራል ገብረእግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ)፣ ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት (ጆቤ)፣ ኢንጅነር አሰፋ አብርሃ እና ጀነራል ተክላይ አሸብር (ወዲ አሸብር) ናቸው ።
🌈ኹለት ሳምንት የሥልጣን ዕድሜ የቀራቸው ጀነራል ታደሰ ወረደን አስተዳደር ለመረከብ ተዘጋጅቷል የተባለው ኃይል ከወዲሁ ምክር ቤት እያቋቋመ ነው ።
🌈የጀነራል ታደሰ ወረደ የስልጣን ጊዜ የሁለት ሳምንታት እድሜ የቀረው መሆኑን ተከትሎ፤ ትግራይን ለመረከብ እየተቋቋመ ነው በተባለው ምክር ቤት ብዙ የትግራይ ፓርቲዎችን ያቀፈ ሲሆን በጀነራል ጻድቃን የሚመራው “የትግራይ የለውጥ ፈላጊዎች እንቅስቃሴ” አባል የሆኑት፣ የጌታቸው ረዳ ስምረት፣ ባይቶና፣ ዓረና ትግራይ፣ ትንሳኤ 70 እንደርታ እና ቃንጪ ሓቂ የተባሉ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው።
🌈በአፋር የሚንቀሳቀሰው ሓራ መሬት ወይም የትግራይ ሰላም ኃይል በመባል የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፣ ወታደራዊ ክንፍን ከመቸውም ጊዜ በላይ ማጠናከርና ወደ ትግራይ እንድገባ ይደረጋል
🌈አዲስ አበባ የተደራጀው ስብስብ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመቆጣጠር ጥረት ከፌደራል መንግስቱ ሲሆን፣ ለዚህም መንግሥታዊ ምክር ቤት እያቋቋመ ነው።
🌈ምክር ቤቱ የጀነራል ታደሰ የሥልጣን ጊዜ ከማብቃቱ በፊት፣ በቅርቡ በአዲስ አበባ ይፋ እንደሚያደረግ ሊደረግ ይችላል።
🌈ይኸ ሁሉ የሚሆነው እነ ታደሰ ወረደን አውርዶ, ገብረፅዮንን ሀይል የሚገዳደርና የሚዋጋ ሀይል መፍጠር, ከዚያ የፋኖን ትስስር ከትግራይ ሀይል ያለውን ማቋረጥ ሲሆን ይኸን ለማድረግ የሀራ መሬት ታጋዮችን ማጠናከርና ተኩስ እንድጀምሩ ማድረግ ነው, አፋር ላይ ትኩረት ይጠይቃል ።
በርካታ የአገዛዙ ኃይል ወደ ደቡብ ወሎ ምዕራባዊ አካባቢዎች ገብቶ በንፁኃን እና በንብረታቸው ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን አጠናሮ ቀጥሏል‼️
ከደሴ በስተምዕራብ ከሚገኙት ወረዳዎች መካከል በአምስቱ ማለትም በመካነሰላም ዙሪያ ገጠር ወረዳ፣ በመሐል ሳይንት ወረዳ፣ በወረኢሉ ወረዳ፣ በአማራ ሳይንት ወረዳ እና ወግዲ ወረዳ ውስጥ የሚገኘው የአገዛዙ እግረኛ ሰራዊት ተጨማሪ ኃይል እንድላክለት ተደርጎና የሜካናይዝድ ምድብተኞች ድጋፍ ተሰጥቶት ለተከታታይ ቀናት የንፁኃንን መንደሮች በመደብደብ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል::
አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ሰራዊት ሜካናይዝድ ምድብተኞች እና እግረኞች በተኩስ ካደረሱት ጉዳት በተጨማሪ የበርካታ ንፁሃን አርሶ አደሮችን ትጥቅ ገፈዋል::
የንፁሃን ቤት እና ሱቅ ጭምር ተዘርፏል:: በዛሬው ዕለት መጋቢት 18/2018 ዓ.ም ደግሞ በአማራ ሳይንት ግንባር ወደ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም አቅጣጫ የጠላት ኃይል ሜካናይዝድ ምድብተኞች መድፍ እየተኮሱ ነው:: አቶ ደምለዉ ምንያህል የሚባል የአማራ ሳይንት ወረዳ 016 ቀበሌ ነዋሪ ተድባበ ማርያም ቀጠና ውስጥ ዛሬ ከጧቱ 3:00 ሰአት ላይ በጠላት ካባድ መሳሪያ ተመቶ ተሰውቷል።
የአፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 105ኛ ኮር ሰራዊትን ክንድ መቋቋም ያቃተው የጠላት ኃይል የጦር ሜዳ ሽንፈቱን ለማካካስ ንፁሓን ላይ ጉዳት ማድረስን ባህሉ ስላደረገው ሰሞኑንም ይህንኑ የግፍ ግፍ በመፈፀም ላይ ይገኛል::
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
©አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
መጋቢት 18/2018 ዓ.ም
18/ዐ7/2018 ዓ.ም
