ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 389
Suscriptores
-324 horas
+2587 días
+1 43630 días
Archivo de publicaciones
ከአፍብኋ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር-11ኛ ክፍለ-ጦር የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ:-
****
1. ባህር-ዳር እና አካባቢው ላይ ጠላት ብዛት ያላቸው የስለላ ሃይሎችን የላከ መሆኑ የውስጥ መረጃ ደርሶናል። በመሆኑም ከቀን 16/03/2018 ዓም ጀምሮ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ የሚንቀሳቀስ የትኛውም የታጠቀ ሃይል (በአማረ መንጌ ወይንም በላይ ዘለቀ) የተረጋገጠ ህጋዊ ጊዜያዊ መታወቂያ የመያዝ ግዴታ አለበት።
2. ጠላት የመሣሪያ ኮንትሮባንድ የሚሠሩ ነጋዴዎችን አሰማርቶ መሣሪያ ግዠ (ሽከፍ) ላይ መሆኑን ደርሰንበታል።በባህር ዳር እና አካባቢው ላይ የመሣሪያ ሽያጭ ፈፅሞ የተከለከለ ነው።ከዛሬ ጀምሮም (ከቀን 16/03/2018 ዓም ጀምሮ) ቀጠናው ላይ በንግድ መልክ ሲሸጥ ሲለውጥ የተገኘ አካል በተጨባጭ ከተገኘ ንብረቱ በክ/ጦሩ ውርስ ይሆናል። መሣሪያውንም ክ/ጦሩ ለአባሉ ትጥቅ ያውላል።
3. ለጠላት ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች የአርሶ አደር መሣሪያ የሚያስወርዱ፤ በፍኖ ስም የሚነግዱ የጠላት ሃይሎች ተሠማርተዋል።በባህርዳር እና አካባቢው ላይ የምትገኙ ማህበረሰባችንም መሣሪያችሁን በጥንቃቄ እንድትይዙ ።ከዛሬ ጀምሮ ትጥቁን ለየትኛውም አካል በሰላም አሳልፎ ከሰጠ ፤ተገቢውን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል።(በፍኖ ስም እየደወለ የሚያስወርድ አካል ካለም፤ ፍኖ አለመሆኑን ለማሣሰብ እንወዳለን)
4. ህገ-ወጥ የለቅሶ ላይ ተኩስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
5. ባህርዳር እና አካባቢው ላይ ኑሯቹህን እና ጎጇቹህን ቀልሳችሁ የምትኖሩ የመንግስት የሚኒሻ አካላት በአስቸኳይ እስከ ታህሳስ 1/04/2018 ዓም ወደቀደመ ኑሯቹህ ትመለሡ ዘንድ እናሳስባለን።ከመንግስት የምታመጡት መሣሪያ የግላችሁ መሆኑን እና አካባቢውን በሚያስተዳድረው ፍኖ የማትጠየቁ መሆኑን እንገልፃለን።
6. የአርበኛ ዘመነ ካሴን ጥሪ አክብራችሁ አሁንም ከመንግስት ተቋም አድማ ብተና፣ፓሊስ እና መከላከያ ወጣችሁ ለምትመጡ ከነሙሉ ትጥቃችሁ የትራንስፓርት ጨምረን ወደየመጣችሁበት አካባቢ የምንልካችሁ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
.................. .............
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፍ!!
ክፍት ለማንም በጎነት ለሁሉም!!
አፍብኋ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር፣11-ኛ ክ/ጦር
በአዲስ አበባ ከተማ፣ በኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች፣ ከፍላጎታቸው ውጪ "የሚሊሻ ስልጠና" እንዲወስዱ በኃይል እየተገደዱ መሆኑን ገልጸው፣ "የሚመለከተው አካል ድምጻችንን ይስማን" ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ቅሬታ አቅራቢዎች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት፣ የአካባቢው አስተዳደር አካላት "ከእያንዳንዱ ብሎክ (Block) 12 ሰዎች መሰልጠን አለባቸው" የሚል ኮታ በማስቀመጥ፣ የነዋሪዎችን ፍላጎት ሳይጠይቁ ስማቸውን ለስልጠና አስመዝግበዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ አብዛኛዎቹ በግልም ሆነ በመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ "እኛ ስራ አጥ አይደለንም፣ ከተማ ውስጥ ሰርተን ነው የምንገባው" ብለዋል። ይህ ሆኖ ሳለ፣ በስራ ሰዓታቸው ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድር መልኩ ለሚሰጠው ስልጠና እንዲመዘገቡ መገደዳቸውን ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ ስልጠናውን ለመውሰድ እንደማይችሉና በስራ ገበታቸው ላይ እንደሚያውክባቸው ሲገልጹ፣ ከአስተዳደሩ አካላት "አለመሰልጠን አይቻልም፣ 'አንችልም' ካላችሁ ለምትሰሩበት መስሪያ ቤት ደብዳቤ እንጽፋለን" የሚል ምላሽና ማስፈራሪያ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።
ይህም በነዋሪዎቹ ዘንድ ከፍተኛ መደናገርና ስጋት ፈጥሯል። "የትኛው መስሪያ ቤት ነው የአካባቢ አስተዳደር በጻፈው ደብዳቤ ተመርኩዞ፣ እኔ በግድ እንድሰለጥን የስራ ጊዜ የሚሰጠኝ?" ሲሉ አንድ ቅሬታ አቅራቢ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢውን ጸጥታ ለማስጠበቅ በሚል፣ በተለያዩ ጊዜያት በማህበረሰብ ተሳትፎ ላይ የተመሰረቱ የጸጥታ አደረጃጀቶች ሲፈጠሩ መቆየታቸው ይታወቃል። ይሁን እንጂ፣ በኮዬ ፈጬ ነዋሪዎች የቀረበው ይህ ቅሬታ፣ የእነዚህ አደረጃጀቶች አፈጻጸም በነዋሪዎች "ፈቃደኝነት" ላይ ምን ያህል የተመሰረተ ነው? የሚለውን ጥያቄ ያነሳል።
ነዋሪዎቹ፣ ይህ ከሥራ ገበታቸው ሊያፈናቅላቸው የሚችል የግዴታ ስልጠና እንዲቆምላቸውና የሚመለከተው ከፍተኛ የአስተዳደር አካል ጉዳዩን አይቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በአጽንኦት ጠይቀዋል።
~ በደብረ ኤልያስ ከተማ የበርካታ ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲፈርስ ሀገር አፍራሹ የብልጽግና ስብስብ ወስኗል።
በስሁት የፖለቲካ ትርክት ሰክሮ አማራን ከነሁለንተናው ለማጥፋት ደፋ ቀና ለሚለው የኦሕዴድ መር ሥርዓት የሚያጎበድደው የአማራ ካድሬ ለምስር ወጥና ለርካሽ ስልጣን ሲል የገዛ ሕቡን ለጨፍጫፊዎቹ በማመቻቸትና የእኩያንን ዓላማ ተፈጻሚ በማድረግ በአማራ ሕዝብ ታሪክ የማይረሳው ግፍና መከራን እያደረሰ ይገኛል።
ከነዚህም መካከል "በመልካም አንገት ላይ እንቅርት እንዲሉ" ሁለንተናዊ ልዕልናና ኃያልነትን አስተባብራ በኖረችና ባለችዋ በደብረ ኤልያስ ከተማ የተወሸቀው ጸረ ሕዝቡ የብልጽግና ስብስብ ይገኝበታል።
ከተማውን ከወረረበት ዕለት ጀምሮ በንጹሐን ላይ የመከራ ቀንበር ሲያወርድ የከረመው ገዳይ ስብስብ ዛሬ ደግሞ ሌላ ጆሮን ጭው የሚያደርግ የጥፋት ዜናን ለደብረ ኤልያስ ከተማ ነዋሪዎች አሰምቷል።
ይህም በፋል(FAL) የመንገድ ተቋራጭ በሚሰራው ሀገር አቋራጭ መንገድ ምክንያት ቤታቸው ከሙዛ ጀምሮ እሰከ አበሸብ በግምት በ3KM ርዝመት ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ያለምንም የካሳ ክፍያ ቤታቸውን እንዲነሱ ነው ዛቻ አዘል ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው።
በወቅቱ (ከ3 ዓመት በፊት) ለባለ ቤቶቹ የካሳ ክፍያ ጸድቆላቸው በሚፈጸምበት ወቅት በፈነዳው የፋኖ አብዮት ሥራው በመቋረጡ ምክንያት የካሳ ክፍያ የቀረ ሲሆን ዛሬ ግን እንዳዲስ ውሳኔዎች ተገልብጠው ያለምንም ካሳ አፍርሰው እንዲነሱ ተነግሯቸዋል።
ቅሬታ ያቀረቡ የከተማው ነዋሪዎችም "አርፋችሁ ተቀመጡ ምንም አይነት ቅሬታም ሆነ ጥያቄ ማቅረብ አይቻልም፤ እንኳን ቤታችሁ ይቅርና እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤ የማታርፉ ከሆነ እናንተንም እናፈርሳችኋለን..." በማለት ነዋሪዎችን አንገታቸውን አስደፍተው መልሰዋቸዋል።
የብልጽግናው ሌባ ስብስብ ይህንን የክህደት ተግባር የፈጸመውም የተለመደ የዘረፋ ተግባሩን ለመፈጸም ነው።
ነገሩ እንዲህ ነው! የበረኸኛው ቀስተ ደመና ሻለቃ ወረዳውን ሙሉ በመሉ ከተቆጣጠረበት ከሐምሌ 27/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ1 ዓመት ከ6 ወር ያክል ራሳቸውን የወረዳው አመራር አድርገው በመሰየም ደብረ ማርቆስ ከተማ የተወሸቁ ሆዳም ባንዳዎች ያለምንም መምሪያ በአየር ላይ እየተወራረደ ከ9000,000 (ዘጠኝ ሚሊዮን) ብር በላይ ተበልቶ በመገኘቱ ሁሉም የብልጽግና ካድሬዎች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ገብተው ሰንብተዋል።
ይህንንም የተበላ ገንዘብ ለማካካስ የካሳ ክፍያውን ወደ ራሳቸው በማዞር ካሳ ጸድቆላቸው ነገር ግን የመንገድ ተቋራጩ ስራ በማቆሙ ምክንያት ክፍያ ያልተፈጸመላቸው የቤት ባለይዞታዎች ያለምንም የካሳ ክፍያ ቤታቸውን አፍርሰው እንዲነሱ ዛቻ የተሞላበት መምሪያ አውርደዋል።
ይህ ስብስብ አስቀድሞም የደብረ ኤልያስንና ማቻክል ወረዳዎችን ለማገናኘት ጌደብ ወንዝ ሊሰራ ከታቀደው የድልድይ ማሰሪያ ገንዘብ በመቀበል ይህንን የተዘረፈ ገንዘብ ለመሙላት አስቦ እንደነበርም መረጃዎች ደርሰውናል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለሕዝባችን!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
#እውነት_እያደረች_ትጠራለች #ተደብቃ_አትቀርም‼️
አገዛዙ ወደ ፋኖ አስርጎ ያስገባውን ግለሰብ በተለየዬ መንገድ ፖለቲካ ሊሰራበት ሞክሯል
1ኛ. ፅንፈኛው (በእነሱ አጠራር) የሰላም አማራጭን እየተቀበለ እንደሆነ
2ኛ. የሰላም አማራጭ ተጠቅመው ወደ አገዛዙ ገቡ የተባሉትን ግለሰቦች በፋኖ ማልያ አሰቃቂ ተግባር እንዲፈፅሙ አድርጎ በመቅረፅ ህዝባችንና አለም አቀፉ ማህበረሰብ #የአማራ_ፋኖን ከሌሎች አሸባሪዎች ተርታ እንዲያስቀምጡትና ከህዝብ ለመነጠል ነበረ ግን እኛ የሰባዊነት ውኃ ልክ ከሆነው የአማራ ህዝብ አብራክ የወጣናንና የአፄ ምኒልክ እና #እትጌ_ጣይቱ_ብጡል ልጆች ነንና ይህ ተግባር የምንታገለውና የምንፀየፈው ተግባር ነው‼️
ተግባሩም የአገዛዙ እንደሆን ትናት የተለቀቁ screenshots መረጃዎች ምስክሮች የሚሆኑ ሲሆን የድራማው ደራሲና ተዋናይ በውይይት ጊዜ የነበረውን ሁነት በዚሁ ፎቶ ማዬት ይቻላል።
ፎቶው ከAI የፀዳ እንደሆነ ደግሞ የAI ምርመራን 100% ያለፈ መሆኑንም አብረን አየይዘናል!!
#እውነት እያደረች ትጠራለች ተደብቃ አትቀርም‼️
በጦር ሜዳ ያጣውን ድል በሚዲያው ሞክሮ ነበረ አልተሳካም!!
16/ዐ3/2018 ዓ.ም
ይህችም ትመዝገብ
የአብይ አህመድ አገዛዝ ለአማራ ህዝብ ያለው ጥላቻ ነጩም ጥቁሩም የሚያውቀው ሃቅ ነው ሆኖም ግን በአራቱም አቅጣጫ ወደ አዲስ አበባ የሚገባን የአማራ ተወላጆች ላይ በተለይም ላምበረት መናሃሪያ ላይ ወሮበላ ኃይሎች አስቀምጦ ይህ ፋኖ ነው በማለት እያሰቃየን ነው። አማራ ማለት ለኢትዮጵያ የታሪክ መሰረት፣ የቋንቋ ድልድይ፣ የነፃነት ጠበቃ፣ የሃይማኖትና የባህል ማዕከል ነው። የብዙኃን መግባቢያ የሆነ ቋንቋን በማፍራት፣ የሀገር ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ እና የኢትዮጵያን ታላላቅ ቅርስ በመጠበቅ ለዚህች ውድ አገር የማይናቅ ውለታ የፈፀመ ሕዝብ ነው።
ሁኖም አብይ አህመድና የአዳናች አበቤ ጡት ቆራጩ ኃይል ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላች በተለይም አዲስ አበባ አካባቢ እጅግ አረመኔያዊ አካሔድ ነው በማለት መረጃዎችን በውስጥ አድርሰውናል እነዚህን ዘመን የወለዳቸውን ጭራቅ የሆነ አስተሳስብ ያላቸውን የኦሮምማው አገዛዝ ስራት በገባበት ገብተን የአማራን ነፃነት የምናወጅበት ቀን ቅርብ ከመሆኑም በላይ የግፍ ሰሪዎች ስራን በአደባባይ የምናዋርዳቸው መሆኑ አይቀሪ ነው።
በመጨረሻም አዲስ አበባ ላምበረትና አውቶብስ ተራ ላይ የአብይ አህመድን ስራት ደጋፊዎች በአማራ ህዝብ ላይ የሚያደርሱትን እንግልትና ስቃይ እጅጉን ብዙህ ነው ከቅርብ ቀን ወዲህ በአራቱም ማዕዘን የሚገቡ የአማራ ተወላጆችን መናሀሪያ ላይ በመቀመጥ ህዝባችን እያሰቃዩት ይገኛሉ ስለዚህም እነዚህን አረመኒያዊ ሰወ በላ አውሪዎች በፎቶና በቭድዮ ተከታትለን መረጃዎችን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የምናጋልጥ መሆኑን እንገልፃለን።
በአራቱም ማዕዘን የፋኖን አውደ ውጊያዎች እየተከታተለ 24 ስዓት እየሰራን እንገኛለን ከታች ባለው ቴሌግራም ሊንክ ጆይን በማድርግ ይወዳጁን።
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
+3
‼️‼️ ‼️##ሰበር_ሰበር_ተቋሙ_እየፈረሰ_ነው
ስቦ ማስከዳት በሰፊው እየሰራን
ህዳር 16/2018ዓ.ም
201ኛኮር 54ኛ ሻለቃ የተቀላቀሉ
ከውጊያው ጎን ለጎን ከምንም በላይ ውጤታማ ሆኖ ስላገኘነው በሰፊው እየሰራንበት ነው
1-ዘመድ ባወቀ..ምስራቅ እዝ 304ኮር 99ክ/ጦር ሁለት ክላሽ በመያዝ
2-አሸናፊ አባይነህ.. ከ602ኛ ኮር 25ክ/ጦር
3-ቸርነት ደስታ....ከ602ኛኮር 25ኛክ/ጦር
ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ የቴወድሮስ እዝ 201ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ህዳር 16/2018 ዓ.ም
በእነማይ ወረዳ የሆላ ደጀኑ ህዝባችን ጋር ውይይት ተካሄዶል።
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
የአፋብኃ ቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር 64ኛ ክ/ጦር የእነማይ ወረዳ ጊ/መንግስት በእነማይ ወረዳ ቅድስጌ፣እነቆራ፣ሰቀላ ቀበሌዎች ከሚገኙ የሆላ ደጀኑ ህዝባችን ጋር ህዳር 16/2018 ዓ.ም ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል።
በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል የእነማይ ወረዳ የሆላ ደጀኑ ህዝባችን ከተጠረነፈው የፋኖ አባላት ጎን በመሆን በመረጃ በሎጀሲት እንዲሁም የአገዛዙን አረመኔዊ ሰራዊትን አብሮ በመፋለም ግንባር ቀደም ሆኖ ቆይቶል።
ቴዎድሮስ ዕዝ በሁሉም የጎጃም ግዛት በቅርብ ቀን ዘመኑን ያወጄ አደረጃጀት በመዘርጋቱ የተነሳ ደጀኑ ህዝባችን በአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ከእግረኛ ተጠርናፊ ሰራዊት ጎን ለጎን በየአካባቢው
➣የቀበሌ እሮንድ ጥበቃ
➣የቀበሌ ፅጥታ
➣ የቀበሌዎቹ መሰረተ ልማት
➣የህዝብ አገልግሎቶች በማስከበር እንዲሁም ለመደበኛ ሰራዊታችን የጀርባ አጥንት በመሆን ይህንን ወራሪ ሀይል ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ በተሰጣቸው አደረጃጀት እንዲያግዙ በክፍለ ጦሩ እና በወረዳው ጊ/መንግስት ግንዛቤ ተሰጥቷል።
➛ላናሸንፍ የጀመርነው ትግል የለም!
➛ ትላት ከነበርን አደረጃጀት ዛሬ ላይ እያደራጀን ያለነው ሰራዊት እጅጉን ይለያል!
አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
የቴወድሮስ ዕዝ 201ኛ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ማረጉ ተማረ ክፍለጦር ከ20 በላይ የአገዛዙ ሰራዊት በመደምሰስና ከ35 በላይ በማቁሰል ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር ስር የሚገኘው ማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ባደረገው አውደ ዉጊያ ከ20 በላይ የአገዛዙ ጦር ሲደመሰስ የጠላት ኃይል 35 ቁስለኛውን ይዞ ወደመጣበት እግሬ አውጭኝ ብሎ ፈርጥጧል።
የብርሃኑ ጁላ 12ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት፣የ65ኛ ክፍለ ጦር ሁለት ሬጅመንት ኃይልና የ65ኛ ክፍለ ጦር ሜካናይዝድ በጥምረት አንድ ዙ-23 እና አራት ዲሽቃ በመያዝ መነሻውን ከላስታ ወረዳ ብልባላ ከተማ በማድረግ ሌሊቱን በመጓዝ የማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃኝን፣ሦስተኛ ሻለቃንና የኮሩን ዘመቻ መምሪያ ኃላፊን አርበኛ ፋኖ ታዘበው ሻምበልንና ስልጠና መምሪያ ኃላፊውን አርበኛ ፋኖ አምሳ አለቃ መልካሙ ገበየሁን አፍናለሁ በሚል ቀቢፀ ተስፋ ወደ 01 ቀበሌ ይምርሃነ ክርስቶስ በመጓዝ ላይ እንዳለ ክፍለ ጦሩ ቀድሞ በደረሰው መረጃ መሠረት ዛዚያ ስላሴ፣ዳቢያና አሞራ ደብር ደፈጣ በመያዝ ህዳር 16/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:30 ሰዓት እስከ አመሻሽ 12:00 ሰዓት ለሙሉ ቀን በተደረገ ትንቅንቅ ከ20 በላይ የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ35 በላይ ቆስሏል።
በዚህ አውደ ዉጊያ ጠላት የማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃኝን፣3ኛ ሻለቃንና ከላይ የተጠቀሱ የኮር አመራሮችን ለማፈን አቅዶ የመጣ ቢሆንም ጠላት ባላሰበውና ባልጠበቀው ራሱ ታፍኖ የማረጉ ተማረ ክፍለ ጦር ቃኝንና ሁሉንም ሻለቃዎች በማሳተፍ ጠላት በወገን ክንድ ሲቀጠቀጥ ውሎ ወደመጣበት ፈርጥጧል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የላስታ ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ቢሆነኝ ቢያበይን መረጃውን አድርሷል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ህዳር 16/2018 ዓ.ም
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የቀስተ ደመና ሻለቃ ደጎልማ በሚባል ቦታ ላይ በወራሪው የብልጽግና ሠራዊት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
ሀለንተናዊ ጥፋትን በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ የሚገኘው ወራሪው የብልጽግና ሠራዊት የአርሶ አደሩን መኸር ለማውደምና ለመዝረፍ በመጣበት ደጎልማ ቀበሌ ላይ ጀግኖቹ የቀስተ ደመና ሻለቃ ፋኖዎች በአመሻሹ ሲለበልቡት አምሽተዋል።
ጀግኖቹ ጠላትን በጥይት አረር እየገረፉት ባለበት ሰዓት ለመቁረጥ የገባውን ጠላት በመልሶ መቁረጥ ድባቅ በመምታት በአመሻሹ ሙትና ቁስለኛውን አስታቅፈውታል።
ድል ለአማራ ፋኖ!
ክብር ለሕዝባችን!
ፋኖ ዘመን ባሳዝነው
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ኮሩ በ33ኛ ክ/ጦር እስካሁን የተሠሩ ሥራዎችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎች አስተላለፈ
════════════❁✿❁════════════
(ኅዳር 16/2018 ዓ.ም፣ 33ኛ ክ/ጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ)
የዐፋብኀ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ 102ኛ ኮር በ33ኛ ክ/ጦር እስካሁን የተሠሩ ሥራዎችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎች አስተላለፈ።
33ኛ ክ/ጦር በተቋቋመ በአጭር ቀናት ውስጥ ያከናወናቸው ተግባራት ቀጣይ ለሚገኙ አንፀባራቂ ስኬቶች ማሳያ መኾኑ ተገምግሟል።
በግምገማው የ33ኛ ክ/ጦር እና የ102ኛ ኮር አመራሮች እንደተናገሩት ከአፈ-ሙዝ ትግል ጎን ለጎን የሚከናወኑ አስተዳደራዊ ጅማሮዎች አበረታች መኾናቸውን በማመላከት፤ ትግላችን ሥርዓቱን በማክሰም ሕዝቡን በዘላቂነት በሚያስከብር መልኩ ሓላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።
የጊዜያዊ መንግሥት መዋቅሩን እና መመሪያውን ግልጽ፣ ለአሠራር ምቹ እና ሁሉን አቀፍ እንዲሆን ማድረግ እንደሚያስፈልግ በተሳታፊዎች ተጠይቋል።
የጦር መሣሪያ አያያዝ እና አጠቃቀም ጉዳይ ለድርጅቱ ተጨማሪ ኩራትና ስኬት በሚያመጣ መንገድ በወታደራዊ ሥነ-ምግባር እንዲመራ ጠንከር አስተያየት ተሰጥቶበታል።
በግምገማው ለተነሱ ጥያቄዎችም በሚመለከታቸው የድርጅቱ አመራሮች ተገቢ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በመጨረሻም ላጋጠሙ ችግሮች መፍትሔ በማመላከት የቀጣይ ድርጅታዊ አቅጣጫዎች ተላልፈው የዕለቱ ግምገማ ተጠናቅቋል።
የዐፋብኀ ምዕራብ ዐማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ም/ሓላፊ አርበኛ እስቲበል ዓለሙ፣ የ102ኛ ኮር ፖለቲካ ዘርፍ ሓላፊ አርበኛ ማንችሎት ጥላሁን፣ የ102ኛ ኮር ዘመቻ መምሪያ ሓላፊ ፻ አለቃ ይንገስ ብርሃኔ እና የ102ኛ ኮር አደረጃጀት ዘርፍ ሓላፊ አርበኛ ዮሐንስ አያሌው ግምገማውን መርተዋል።
😭😭 የሀዘን መግለጫ❗❗
በ77ኛ ክፍለ ጦር ስር የምትገኘዋ #ዓባይ_ሻለቃ በአጉት ለተረሸኑት ንጹሃኖች የሃዘን መግለጫ አውጣለች...
(አፋብኃ ቲዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክፍለ ጦር #ዓባይ_ሻለቃ)
በሰከላ ወረዳ በአጉት ከተማ በ አረመኔው ስርዓት በግፍ ለተረሸኑት ለቤተሰቦቻቸው እና እንዲሁም የዐማራ ጊዳይ ይመለከተኛል ብለው እየተዋደቁ ላሉት ለ3ኛ ክፍለ ጦር የፋኖ አባላቶች መፅናናትን እመኛለሁ ስትል ገልፃለች።
በክልላችን እየተፈፀመ ያለው ግፍ በዓለም ውስጥ ታይቶ ተደርጎ የማይታዋቅ ዘግናኝ ግድያዎች እና ሰቆቃዋች ለወራሪው ስርዓት ሰራዊት የሽንፈት ምልክታቸው ነው ስትልም ሻለቃዋ አመላክታለች።
ይህ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሌሊት እና ቀን የሚደነፋው #የፋስቱሽ አብይ አህመድ ወራሪ ቡድን #በዐማራ ክልል ውስጥ ከ4 ዓመት እስከ 65 ዓመት ሴቶችን #በመድፈር እና እንዲሁም በክልልሉ የታሪክ ጠባሳ ለማሳደር #ጡት ፣ #ብልት እና #ምላስ በመቁረጥ በክልላችን ላይ ከባድ ጭፍጨፋ እያካሄደ ይገኛል።
ይህ በምስሉ የምትመለከቱት የተፈጠረው በአጉት ከተማ ላይ ንጹሃንን ታርጌት ያደረገ ጭፍጨፋ በመመልከት የክልሉ ህዝብም ሊያጠፋው የመጣውን የጥፋት ሰራዊት ከፋኖ ጋር በመቆም ሊመክት እና ራሱን ሊከላከል ይገባዋል ስትል በ77ኛ ክፍለ ጦር ስር የምትገኘው ዓባይ ሻለቃ መልዕክቷን አስተላልፋለች።
ሕዳር 16/3/2018 ዓ.ም
#ዓባይ_ሻለቃ
#ድል_ለህዝባችን_ነፃነት
➧ፋኖ አይቸው ጌታሰው
+1
የምኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦር በሳልመኔ ከተማ በመግባት አስደናቂ ኦፕሬሽን ሰራ
==========
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦር በአልብኮ ወረዳ መቀመጫ ሳልመኔ ከተማ በመግባት በብልጽግና የጸጥታ አካላት ላይ ርምጃ ወስዷል::
በዚህም ድንቅ ኦፕሬሽን የአልብኮ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አመራር የሆኑት አልይ አሰን የሚኒሻ ጽ/ቤት አመራር ካሳው እና ሌሎች አጃግሬዎቻቸው ላይ በተወሰደ ርምጃ ከባድ ቁስለኛ ሁነው ሆስፒታል ገብተዋል::
መረጃውን ያደረሰን የልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አርበኛ ሱልጣን የሱፍ ነው
በተባበረ ክንዳችን ህልውናችንን እናረጋግጣለን!!!
ሰበር መረጃ ‼️
አንድ ኮሎኔል ዙ-23 ጨምሮ ከ60 በላይ አድማብተና እና መከላከያ በመያዝ ጠፍተዋል!! የከዱ ኃይሎች አስተማማኝ ሁኔታ ላይ ሲሆኑ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን!!
በአሁኑ ሰዓት የጠፍውን ኃይል ጀነራል ብርሃኑ በቀለን ጨምሮ ለመፈለግ ማርቆስ ያለው ኃይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከተማውን ለቆ አሰሳ እየወጣ ነው።
ደብረ ኤልያስ ያለው የጠላት ኃይል አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጧል!!
ሰበር ዜና
የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክፍለጦር ጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ሰነዘረ።
ጀነራል ተፈራ ማሞ ብርጌድ በከተማ ኦፕሬሽን በተደጋጋሚ በመስራት አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች ያለቺው ባለፈው ሳምንት ናደው ሻለቃ የተሳካ የደፈጣ ስራ በአሮጌ ምንጃር መፈፀሟ ዘግበን ነበር።
ትላንት ህዳር 16, 2018 ዓ.ም ማታ በ2:00 ሰዓት በአረርቲ ከተማ በአሮጌው ከብት ተራ ካሉ መጠጥ ቤት በሚገኙበት የአገዛዙ ዙፋን አስጠባቂ ሚኒሻና ኮማንዶ መከላከያ በየአረቄ ቤቱ ተወሽቀው እንደገቡ መረጃ የደረሳቸው መብረቁ ሻለቃ በብርሃን ፍጥነት ከቦታው በመድረስ በወረፋ ሱሳቸውን ሲያጣጥሙ የነበሩትን የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ኮማንዶ እና ገረዶቹ ሚኒሻዎች ቅንድብ ቅንድባቸው በማለት ስያጋድሟቸው አምሽተው በሰላም ወደ ቀጠናቸው ተመልሷል።
በዚህ የተደናገጠው የአገዛዙ ሰራዊት በአካባቢው ከሚገኙ መጠጥ ቤት ሰራተኛ አንቺ ነሽ ያስገደልሽን በማለት እንደረሸኗት አረጋግጠናል።
አረርቲ ሆስፒታል በርካታ ቁስለኛና ሙት እንደታየ በመረጃ ምንጮቻችን አማካኝነት ማረጋገጥ ችለናል።
መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር ነበልባል ክ/ጦር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።
" ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"
አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል።
ህዳር 15/03/2018 ዓ.ም
