ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más4 411
Suscriptores
-724 horas
+137 días
+1 18630 días
Archivo de publicaciones
ዓለም ላይ ተቀርጾ በደም የተጻፈው!
በዓለም ላይ አይገኝ እንዲህ የቆረጠ፣
ከድሎት ከምቾት ህዝቡን የመረጠ ።
ቡሬ ዳሞት አዝኖ ዐማራ ተክዞ፣
ጃቢ ቋሪት አልፎ ፈርስቤትን ይዞ።
ደምበጫ ሲነካ ጅጋና ስከላ፣
ዐማራ በጎጃም መቼ ቃሉን በላ።
ደብረማርቆስና ደብረወርቅ ቢገቡም፣
ዐማራን ለማጥፋት ክተት ቢታወጅም።
ሞጣ ቀራኒዮ ባህርዳር ዱርቤቴ፣
ብለው ቢዘምቱበት ዐማራ ጠላቴ።
መሸንቲ መራዊ ዳንግላ አንጅባራ፣
አማኑኤል ሉማሜ እያልን ብንጣራ ።
ቀድሞ የተረዳው የወገኑን ጉዳት፣
ኢላማ መሆኑን አይቶ ዐማራነት።
በአካባቢው ሊያጥሩት ጎጃም ነህ ቢሉትም፣
ልክ ነው አላቸው ቀየውን አይክድም።
እንደ እናት መቀነት አባይ ቢከበኝም፣
እንደሌላው ሁሉ በአድራሻ ብጠራም፣
ዐማራ ወገኔን መቸም አልረሳውም ።
ለዐማራ ለመኖር ለዐማራ ለመሞት ፣
ዓለም ላይ ተገኘ ዓርማው በንቅሳት።
ብዎለድ ማንኩሳ ብወለድም ጎጃም፣
ቡሬ ዳሞት ባድግ መንደሬን ባልረሳም
ዐማራነት ገብቶኝ በኖርሁበት ዘመን፣
ውድ ህይዎቴን ልሰጥ ለዐማራ ስዎስን፣
የጽናት ምልክት መታሰቢያ እንዲሆን።
ቆዳይ ይተለተል ይመመኝ ስሰራ፣
ብቃት እንዲሆነኝ ለመስጠት አደራ
መጻፊያ ሰሌዳው ለትውልድ አሻራ
ደሟ ቀለሙ ነው ዋናው ቃል ዐማራ።
ጠላትም ወዳጅም እርሙን እንዲያወጣ
ዐማራን በሙሉ እጅጉን ያስቆጣ ።
በዓለም ላይ ተቀርጾ በደም የተጻፈው፣
ታርኳም እውነቷም ዐማራ የሚል ነው።
መታሰቢያነቱ ለፋኒት በዓለም
ሁሌም የሰውነት እእምሮ ፈጽሞ የሌላቸው የአገዛዙ ተጠቃሚዎች ህይውታቸውን ለህዝባቸው መስዋእት ያደረጉትን እያደረጉ ያሉትንም ሆነ ንጹሃንን በአረመኔ አገዳድል የሚገድሉት ሁሌም ሁለት ዓላማዎች ይዘው ነው። አንድ በ አገዳደሉ ጭካኔ ሌላው እንዲፈራና መታገሉ እንዲያቆም ሁለት ደግሞ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ እንደሚጮህ ሁሉ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት ቀድመው ተደራጅተው ነው። በዐማራ ላይ በዚህ መልኩ የሚሰሩት ግፍ ግን እንደሚያጠፋቸው ብቻ ሳይሆን ዐማራ ሌላ አማራጭ እንደሌለው የበለጠ እንዲረዳ እያደረገው ነው። አዎ የዐማራን ደም ያፈሰሰ ሁሉ የሚገባውን ቅጣት የሚያገኝበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
ድል ለዐማራ ህዝብ
ገጣሚ ጋሽ አዲስ
መውጫችን ማሸነፍ ብቻ ነው።💚💛❤
#
+1
''ምንም ቢሆን ከሃገር አትበልጥም'' ፋኒት በአለም ዋሴ❗️
ፋኒት #በአለም_ዋሴ ፣ ብላቴናዋ እንስት የአባቷን የደጃዝማች #በላይ_ዘለቀን ቃል ከመሰዋቷ በፊት ነግራን ነዉ ያለፈችዉ።
ማንም በሌለበት ብቻዉ ሞት እያንጃበበት ባየ ጊዜ እኔ ''ብሞትም ትግሌን ግን አደራ'' እንዳለዉ ሰማዕቱ ሳሙኤል አወቀ። ቆራጦች ከማለፋቸዉ በፊት የማይረሳ ታሪክ ጥለዉ ያልፋሉ።
የብላቴናዋን ትግል አደራ❗️
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለ ጦር እጅግ ግዙፉ የቀጠናችን አሃድ ነዉ፡፡ ይህ ክፍለ ጦር የጠላት የስበት ሀይልና ቋት ያለበትን ቤዝ ሸፍኖ ይገኛል፡፡ ባህርዳር አፍንጫ ስር የተቀመጠ የወገን ሀይል በመሆኑ ጠላት ይህን ሀይል ለመናድ ከዉስጥም ሆነ ከዉጭ ያላደረገዉ ጥረት አልነበረም፡፡ አልተሳካም፤ አይሳካምም፡፡ አሁንም የተለየ ችግር የለም፡፡ አይኖርምም!
፤
ለበርካታ ወራት ከተጠና ስትራቴጂካዊ እቅድ በኋላ ወደ ትግበራ በመግባት የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የተሻለ የአወቃቀር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል። በመዋቅር ስራ ውስጥ ደግሞ የስር ነቀል (transformation)፣ የማሻሻያ (transaction/ reform) እና የሽግግር(transition) ለውጦች ይደረጋሉ። የቴዎድሮስ ዕዝ አመራርና ሰራዊቱ በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ይገኛሉ። እንባን ከሚያስወርድ ግምገማ እስከ እስር፣ ከሀላፊነት መታገድ እስከ መረሸን የሚያደርስ ውሳኔ በአጥፊ አካላት ላይ ድርጅቱ በመወሰን የእርምትና ማስተካከያ ሲሰራ ቆይቷል። እየተሰራም ይቀጥላል፡፡ የቀጠናው ትግል በሀሳብ የበላይነትና አቻ ስሜት (peer Leadership) የሚያምን ጉምቱ ሰው ከፊት ሁኖ የሚመራው ተቋም ነው። ለዉጥ ሲኖር ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች፤ የዉጊያ አዉዶችና የስራ ስምሪቶች ባሉበት የመቆም (stack and freeze) ተግዳሮት ይገጥማቸዋል፡፡
፤
ለዚህም ይመስላል አንዳንዶቹ ከቅንነት ግን ደግሞ አሰራርን ካለማዎቅ፤ አብዛኞቹ ከመሰሪነትና ስዉር ፍላጎት (Double Standard) የለዉጥ ሂደት ጉዞን እንቅፋት ለመሆን ይጥራሉ፡፡ አመራርን በርብርብ መስደብ፤ ምደባን አስቀድሞ በሚዲያ ገፅ አዉጥቶ መበተን፤ በአፍ የትግሉ አካል መስሎ በተግባር ግን የጠላት አጀንዳ አካል (part of enemy’s propaganda and tactical manipulation) መሆን ተገቢ አይደለም፡፡ የተቋም ሰዎች Manipulative tactics can make the victim feel confused, disappointed in themselves, and inadequate እንዲሉ!
፤
በትግሉ ውስጥ ሊኖረን የሚገባንን ሚናና አስተዋፅኦ ሳንረዳ፣ በሰራዊት አሃድ አንድነትና ጓዳዊ ዝምድና ላይ ሊከሰት የሚችልን የቢሆናል ትንታኔን ሳያስተውሉ፣ ትችትና ገፅታ ገደላን በማዳበል የሚደረግ የስድደብ ድምር ውጤት፣ የመርገምት ዕዳና ጣት ቅስራው ውርጅብኝ ሁሉ መዳረሻ ግቡ ወደ ቀጠናዉና ዕዙ መሪዎቻችን የአቅም ውስንነትና ተጠየቅነት የሚሄድ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል። ዝርዝር ኪስ ይቀዳል እንዲል የአራዳ ልጅ ብዙ ማለት ቢቻልም ይበቃል! ግን ግን አሁን የደረስንበት ቦታ ያለፍንበትን መንገድ ሁሉ አያስረዳም፡፡
፤
እረፍት አልባ ሌሊቶች፤ እረፍት አልባ ቀናቶች ለተቋማዊ መጠናከርና ለትግሉ የድል ግስጋሴ ያለመታከትና ድካም እየተሰሩ ነው። ትግሉን በተሸከመው ህዝባችንና አብዮቱን በሚመሩት ፊታውራሪዎቻችን ሙሉ እምነት ሊኖረን ይገባል። እኛ ግን የህዝባችንን የማሸነፍ አቅም ለአፍታ ተጠራጥረን አናውቅም!
አርበኛ ማንችሎት እሱባለው
ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም.
በሰብዓዊነት ላይ የሸፈተውን አገዛዝ መታገል የሰው ልጅ ሁሉ ግዴታ ነው!!
የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ዛሬ ካለበት ደረጃ ይደርስ ዘንድ በርካታ መስዋዕትነት ተከፍሎበታል። አገዛዙ አረመኔነትን፣ አውሬነትን እና ዓለም አቀፍ አሸባሪነትን ተላብሶ ባካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። የሟቾችን አስከሬን በእሳት አቃጥሏል፣ አካላቸውን ቆራርጧል። የሐይማኖት ተቋማትን ምሽግ በማድረግ አራክሷል።
በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ ላይ የሽብር ተግባራትን መፈፀም አንደኛው የጦርነት ስልት አድርጎት ቆይቷል።
ጥቅምት 02 ቀን 2018 ዓ.ም ምዕራብ ጎጃም ማንኩሳ አካባቢ ከጠላት ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ቀላል ጉዳት ደርሶባት የአገዛዙ ሰራዊት እጅ የወደቀችው የ19 ዓመቷ ፋኒት በዓለም ዋሴ ላይም ተመሳሳይ ድርጊት ተፈፅሞባታል። ፋኒት በዓለምን ከነ ህይወቷ በእጁ የያዘው ሰራዊት ከበላይ ኃላፊወቹ በተሰጠው መመሪያ መሰረት የፋኖዋን ሁለት ጡቶች በመቁረጥ አስፋልት ላይ ከመጣሉም ባሻገር "አማራ" የሚል ንቅሳት ያለበትን የቆዳዋን አካል በመግፈፍ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ አሳይቷል።
አገዛዙ ለመደበኛ ሰራዊቱ ከሚሰጠው የጥፋት ተልዕኮ ባሻገር መሰል የሽብር ድርጊቶችን የሚፈፅም ኃይል በየ አሃዶቹ በመመደብ በሽብር ተግባር ህዝቡን ሊያሸንፍ በመጣር ላይ ይገኛል።
የአፋብኃ ሰራዊት እና አመራር ይህንን የአገዛዙን ዋነኛ ባህሪ አስቀድሞ በመረዳት የአገዛዙን ሰራዊት በመተናነቅ የመጨረሻው ህቅታ ላይ እንዳደረሰው ሁሉ የአብይን ቡድን ሙሉ በማስወገድ የአማራን ህዝብ ማህበራዊ እረፍት ማምጣት ልዩ ተልዕኮው አድርጎ የሚሰራ ይሆናል።
ፋኒት በዓለም ዋሴ ላይ የተፈፀመው አውሬያዊ ተግባር በመላው የአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት እንደመሆኑ ይህንን እና መሰል ስምሪት የሚሰጠውን አረመኔ አገዛዝ ከነ መዋቅሩ ነቃቅለን ለመጣል ለምናደርገው የፍትህ ተጋድሎ መላው ኢትዮጵያዊ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናችን እንዲቆም እንጠይቃለን።
በሰብዓዊነት ላይ የሸፈተውን አገዛዝ መታገል የሰው ልጅ ሁሉ ግዴታ መሆን ይገባዋል።
ሕልውናችን በተባበረ በክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ለሕዝብ ታምኖ መታገል የበለጠ ክብርና ሞገስ እንዳለው በተግባር ማስረዳት ይጠበቅብናል!
<< ..ፖለቲካ ቁማር ሳይሆን ጥበብ ነው፡፡ ጥበብ መሆኑን ዘንግተው በፖለቲካው ለሚቆምሩ ድኩማን ፣ እውነትን ሁሌ ስለምንይዝ እንበልጣለን እንጅ አናንስም። እንሸንፋለን እንጅ ፣ አንሸነፍም፡፡ ለሴራ ፖለቲካ እጅ አንሰጥም፡፡ ከመሽኮርመም ፖለቲካ ወጥተን ለአማራ ህዝብ ህይወታችንን ጭምር ለመስጠት ዝግጁ ነን! >> ይህ ወንድማችን ዮሐንስ ቧያለው ከ5 አመት በፊት ከአማራ ባለሀብቶች ጋር በነበረው ውይይት የተናገረው ንግግር ነው።
ጆን በስርአቱ ውስጥ ሆነው ''ህዝባችንን አንረሳም!'' ሲሉ ፥ በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ በድፍረት በመሞገት ብሎም በሰላ ትችታቸው ከምናውቃቸው በጣት ከሚቆጠሩ አመራርና ፖለቲከኞች መካከል በመጀመሪያው ረድፍ የሚቀመጥ ነው።
''ሠውን ይበልጥ የምታውቀው ስትቀርበው ነው'' እንደሚባለው ፣ በመጥፎ የታሪክ አጋጣሚ ''አዋሽ አርባ'' በተሰኘው ምድራዊ ሲኦል አብረን ባሳለፍናቸው የመከራ ጊዜያት ውስጥ ፣ ጆን በሚዲያ ከምናውቀውም በላይ ቆራጥ ፣ ቆፍጣና ፣ ከሰው ጋር ተግባቢ ፣ የተረጋጋ ስብእና ያለው ፣ አስተዋይ ፣ ሁለንተናዊ የመረዳት አቅሙና ፖለቲካዊ እውቀቱ የሚያስደምም ፣ ከምንም በላይ ደግሞ ላመነበት ነገር ሞትንም ቢሆን ፊትለፊት የሚጋፈጥ ፅኑ ሰው መሆኑን ፣ አብረነው የነበርነው ሁሉ የምንመሰክረው ሀቅ ነው።
ጆን የዛሬ አሳሪዎቹን ሁሉ የፖለቲካ ሀሁ ያስተማረ ፣ ትልቅ አቅም ፣ ስምና ስልጣን የነበረው ሰው ነው። እንደማንኛውም የስርአቱ ካድሬ የፖለቲካ ቁማር መጫወቻ ካርድ ሆኖ እያገለገለ ፣ የሚያየውና የሚሰማውን ግፍ ባላየ እያለፈ ፣ አድርባይና ተላላኪ ሆኖ ፣ የአገዛዙን ፖለቲካዊ ድራማ እያዳመቀ ቢቀጥል ኖሮ ፣ በግሉ ምንም የማይጓደልበት ፣ የጠየቀው የሚደረግለት ፣ ያዘዘው የሚፈፀምለት ሰው ሆኖ መኖር ይችል ነበር።
ነገርግን የሱ ስብእና ፈፅሞ ይሄን አይፈቅድም። በዚህ አውድ የማይገለፁ በርካታ ውጣውረዶችንም አልፏል ፣ አሳሪዎቹን ጉሮሮ ለጉሮሮ ተናንቆ ተንበርካኪ አለመሆኑንና ከህዝቡ ጥያቄና ትግል ጎን ተሰልፎ ለሚመጣበት ፣ ሞትንም ቢሆን በፀጋ ለመቀበል ቁርጠኛ መሆኑን በመንገር ተስፋቸውን አስቆርጧቸዋል።
የበቀል በትራቸውን በይፋ ማሳረፍ በጀመሩ ማግስት በተደጋጋሚ ህክምና እየከለከሉ ፣ ከህክምና እያቋረጡ ፣ ወደአዋሽ አርባ ኮንሰንትሬሽን ካምፕ በመውሰድ ለወራት እንዲሰቃይ ፣ እንዲጎሳቆል ፣ ህመሙ ተባብሶ ህይወቱ አደጋ ላይ እንዲወድቅ ፣ ....በማድረግ የሰው ልጅ ይፈፅመዋል የማይባል የግፍ ዶፍ ቢያዘንቡበትም ፣ እርሱ ግን አካሉ ቢጎሳቆል ህመሙ ቢያሰቃየውም እንኳ ፣ ከአለት የጠነከረ ሞራሉን ሊሰብሩት አልቻሉም ፣ ከአቋሙ አንድ ኢንች እንኳ ዝንፍ ሊልላቸው አልፈቀደም።
መንፈሰ ጠንካራው ጆን ፣ ልቦለዳዊ የወንጀል ታርጋ ተለጥፎበት ፣ ከህመሙ ጋር እየታገለና ተደጋጋሚ ቀዶ ህክምና እየተደረገለት ከሌሎች እልፍ ወንድም እህቶቻችን ጋር በቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስሮ ስለህዝቡ መሪር መስዋዕትነትን እየተቀበለ ይገኛል!
ታዲያ! ይህ ''ህዝቤ እየተሰቃየና ክብሩ ተገፎ ባለበት ፣ ግላዊ ድሎትና ምቾት ምኔም አይደለም!'' ብሎ ስለህዝቡ መከራን እየተቀበለ ያለ ወንድማችንን በሁለንተናዊ መልኩ አጋርነታችንን ልናሳየው ይገባል!
ለአሳሪዎቹ ፦ ለግፍ ሰሪዎች ከመታመን ይልቅ ለሕዝብ ታምኖ መታገል ፣ የበለጠ ክብርና ሞገስ እንዳለው በተግባር ማስረዳት ይጠበቅብናል!
በአገዛዙ እስር ቤቶች በግፍ ታስረው ፣ ስለህዝባቸው መሪር መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ ወንድም እህቶቻችንን ለአፍታም ልንዘነጋቸው አይገባም!
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ፩ኛ ክፍለ ጦር እጅግ ግዙፉ የቀጠናችን አሃድ ነዉ፡፡ ይህ ክፍለ ጦር የጠላት የስበት ሀይልና ቋት ያለበትን ቤዝ ሸፍኖ ይገኛል፡፡ ባህርዳር አፍንጫ ስር የተቀመጠ የወገን ሀይል በመሆኑ ጠላት ይህን ሀይል ለመናድ ከዉስጥም ሆነ ከዉጭ ያላደረገዉ ጥረት አልነበረም፡፡ አልተሳካም፤ አይሳካምም፡፡ አሁንም የተለየ ችግር የለም፡፡ አይኖርምም!
፤
ለበርካታ ወራት ከተጠና ስትራቴጂካዊ እቅድ በኋላ ወደ ትግበራ በመግባት የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የተሻለ የአወቃቀር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል። በመዋቅር ስራ ውስጥ ደግሞ የስር ነቀል (transformation)፣ የማሻሻያ (transaction/ reform) እና የሽግግር(transition) ለውጦች ይደረጋሉ። የቴዎድሮስ ዕዝ አመራርና ሰራዊቱ በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ይገኛሉ። እንባን ከሚያስወርድ ግምገማ እስከ እስር፣ ከሀላፊነት መታገድ እስከ መረሸን የሚያደርስ ውሳኔ በአጥፊ አካላት ላይ ድርጅቱ በመወሰን የእርምትና ማስተካከያ ሲሰራ ቆይቷል። እየተሰራም ይቀጥላል፡፡ የቀጠናው ትግል በሀሳብ የበላይነትና አቻ ስሜት (peer Leadership) የሚያምን ጉምቱ ሰው ከፊት ሁኖ የሚመራው ተቋም ነው። ለዉጥ ሲኖር ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች፤ የዉጊያ አዉዶችና የስራ ስምሪቶች ባሉበት የመቆም (stack and freeze) ተግዳሮት ይገጥማቸዋል፡፡
፤
ለዚህም ይመስላል አንዳንዶቹ ከቅንነት ግን ደግሞ አሰራርን ካለማዎቅ፤ አብዛኞቹ ከመሰሪነትና ስዉር ፍላጎት (Double Standard) የለዉጥ ሂደት ጉዞን እንቅፋት ለመሆን ይጥራሉ፡፡ አመራርን በርብርብ መስደብ፤ ምደባን አስቀድሞ በሚዲያ ገፅ አዉጥቶ መበተን፤ በአፍ የትግሉ አካል መስሎ በተግባር ግን የጠላት አጀንዳ አካል (part of enemy’s propaganda and tactical manipulation) መሆን ተገቢ አይደለም፡፡ የተቋም ሰዎች Manipulative tactics can make the victim feel confused, disappointed in themselves, and inadequate እንዲሉ!
፤
በትግሉ ውስጥ ሊኖረን የሚገባንን ሚናና አስተዋፅኦ ሳንረዳ፣ በሰራዊት አሃድ አንድነትና ጓዳዊ ዝምድና ላይ ሊከሰት የሚችልን የቢሆናል ትንታኔን ሳያስተውሉ፣ ትችትና ገፅታ ገደላን በማዳበል የሚደረግ የስድደብ ድምር ውጤት፣ የመርገምት ዕዳና ጣት ቅስራው ውርጅብኝ ሁሉ መዳረሻ ግቡ ወደ ቀጠናዉና ዕዙ መሪዎቻችን የአቅም ውስንነትና ተጠየቅነት የሚሄድ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል። ዝርዝር ኪስ ይቀዳል እንዲል የአራዳ ልጅ ብዙ ማለት ቢቻልም ይበቃል! ግን ግን አሁን የደረስንበት ቦታ ያለፍንበትን መንገድ ሁሉ አያስረዳም፡፡
፤
እረፍት አልባ ሌሊቶች፤ እረፍት አልባ ቀናቶች ለተቋማዊ መጠናከርና ለትግሉ የድል ግስጋሴ ያለመታከትና ድካም እየተሰሩ ነው። ትግሉን በተሸከመው ህዝባችንና አብዮቱን በሚመሩት ፊታውራሪዎቻችን ሙሉ እምነት ሊኖረን ይገባል። እኛ ግን የህዝባችንን የማሸነፍ አቅም ለአፍታ ተጠራጥረን አናውቅም!
አርበኛ ማንችሎት እሱባለው
ዛሬ አዲስ ቅዳም ላይ‼️
በዛሬዉ የጥቅምት 6/2018 ዓ/ም የአዲስ ቅዳም ከተማ ልዩ ኦፕሬሽን ከተደመሰሱት አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻዎች ለቅምሻ ያህል እንሆ‼️
1ኛ ነጋ ፈንታሁን አመሻ ቀበሌ ሚሊሻ
2ኛ የቆየ እንዳለዉ አመሻ ቀበሌ
3ኛ ባንቲገኝ አመሻ ቀበሌ
4ኛ ደረጀ ጉላ ቀበሌ
5ኛ ሰጤ የኔዉ ወርቁ ጉላ ቀበሌ
6ኛ ዋለ አበበ አዱርዣ ቀበሌ
7ኛ ማሩ ደግነህ ጉላ ቀበሌ
8ኛ ደሳለዉ ሙሉነህ ኳሪ ጎኸና ቀበሌ
9ኛ የኔዉ
10ኛ ተሻለ ምልክት አምሳል ስጋዲ ሚካኤል |ቻግኒ|
ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ ባልሰማሽ‼️
ቻዉ ሚሊሻ😀😀😀😀😀
ይበልጣል የዉነቱ ጀግናዉ
በራያ ግንባር በመቶዎች የሚቆጠር የፋሽስቱ አገዛዝ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል:: በዚህም ቆቦ ሆስፒታልና ቆቦ ጤና ጣቢያ የህዝብ አገልግሎት ዝግ ሆኖ ውሏል!
አፋብኃ ምኒልክ ዕዝ በበርካታ ቀጠናዎች ከፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ጋር ከባድ ትንቅንቅ እያደረገ የተለመደውን ድል እያስመዘገበ ነው::
የምኒልክ ዕዝ አምስቱም ኮሮች እና የዕዙ ልዩ ዘመቻ እንዲሁም በመደራጀት ላይ ያሉ አሃዶች ከፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ጋር ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ እያደረጉ አመርቂ ድል እያስመዘገቡ ይገኛሉ::
በዘመቻ አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) በርካታ ሰራዊቱና አመራሩ የተመታበት ጠላት ለክፉ ቀን ብሎ ያስቀመጠውን ብዛት ያለው ሰራዊቱን የኦሮሚያ ብልፅግና ልዩ ሃይልን ጨምሮ በማስገባት የተወሰደበትን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት ለመቀልበስ ማጥቃት እያደረገ ቢሆንም በምኒልክ ዕዝ አናብስቶች ባግባቡ ተመክቶ በርካታ ሰራዊቱም እየተመታበት ብሎም እየኮበለለበት ይገኛል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም ዛሬ ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም ማለዳ ጀምሮ ከስድስት በላይ ግንባሮች ላይ ከባድ ትንቅንቅ በማድረግ አመርቂ ድሎች ተመዝግበዋል::
ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን!
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ጥቅምት 6/2018 አ.ም
የብልጽግና ቡድን እርስ በእርሱ እየተካሰሰ ነው፦
==============
ሲነገር አልሰማ በማለት ብልጽግናን አምኖ የተጠጋው የሚሊሻ ቡድን አዲስ ቅዳም ላይ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሷል።
👉የብልጽግናው ቡድን እጁን ለፋኖ በሰላም እንዳይሰጥና ህይወቱን እንዳያተርፍ መከበቡን እንኳ ለሚሊሻው አልነገሩትም።
👉ብልጽግና መንደርም ሆቴል ውስጥ የውስኪ አንገት ጨብጦ የአዞ እንባ እያለቀሰ ነው😭😭😭።
👉 በተለያዬ ቦታ ያላችሁ የሚሊሻ አባላት ከአዲስቅዳሙ ትምህርት ወስዳችሁ፤ ብልጽግናን ያመነ ጉም የዘገነ ነውና ነገሩ በሰላም እጅህን ለፋኖ በመስጠት ቤተሰብህን ምራ፣ልጆችህን አሳድግ። እምቢ ካልህ.........
©የቻለ አድማሱ
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራምና ፊስቡክ ቻናላችን እና ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9
ሰበር ዜና‼️
የአማራ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የኃለማርያም ማሞ ክ/ጦር በሀገረ-ማርያም ከሰም ወረዳ፡ ኮርማሽ ንዑስ ቀበሌ በልዩ ኦፕሪሽን ድል ተቀዳጀ !
በቀን 06/01/2018 ዓ.ም፡ ከሌሊት 11:00 ሰዓት አንስቶ እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ የአፋብኃ የኃለማርያም ማሞ ልጆች ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር ከባድ ትንቅንቅ አድርጓል ። በክፍለጦሩ ከአራቱ ሺህ አለቃ እንዲሁም የክ/ጦሩ ቃኝና መሃንዲስ በተውጣጣ ሀይል ጠላት ላይ ከበባ በያዝ ከባድ ኪሳራ ማድረሳቸውን ከሰም ሚዲያ ከስፍራው ለማረጋገጥ ችሏል ።
በሀገረ-ማርያም ከሰም ወረዳ፡ ኮርማሽ ቀበሌ ከሌሊቱ 11:00 ጀምሮ ሰዓት እስከ 1:00 ሰዓት፤ውጊያ የኃለማርያም ማሞ ልጆች በደረጉት የጨበጣ ውጊያ ከፍተኛ የሆነ ጀብድን ሰርተዋል ። የአገዛዙን ሰራዊት ሚሊሻ፣ የኦሮሚያ ልዩ ብሎም የመከላከያ ሰራዊት በጥምር-ጦር ቢገጥምም፤ የፋኖን ምት መቋቋም ሲቅተው የኮርማሽን ንዑስ ቀበሌ ጥሎ 'እግሬ አውጪኝ' ብሎ ፈርጥጧል ። ከሌሊቱ 6:00 እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት በተደረገ አውደ-ውጊያ አፋብኃ የኃለማርያም ማሞ ክ/ጦር በጠላት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል ። በዚህም 3 ሙት እና ቁጥሩ በውል የማያታወቅ ቁስለኛን ከስፍራው በአፕቡላንስ ወደ ጤና ጣቢያ ሲያመላልስ መዋሉ ምንጮች ለጣቢያችን ጠቁመዋል ።
የአማራን አዲሱን ትውልድ (የአማራውን ወርቃማ ትውልድ) የሚመጥን ሚዲያ ጎልደን አማራ ይሰኛል።
ይቀላቀሉን አንበሳዬ
👇👇👇👇👇👇
@GoldenAmhara
@GoldenAmhara
@GoldenAmhara
ጎልደን አማራ
ይህ የአማራው ወርቃማ ትውልድ ነው።
This is Golden Generation of Amhara
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
የአማራን አዲሱን ትውልድ (የአማራውን ወርቃማ ትውልድ) የሚመጥን ሚዲያ ጎልደን አማራ ይሰኛል።
ይቀላቀሉን አንበሳዬ
👇👇👇👇👇👇
@GoldenAmhara
@GoldenAmhara
@GoldenAmhara
ጎልደን አማራ
ይህ የአማራው ወርቃማ ትውልድ ነው።
This is Golden Generation of Amhara
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
#2ኛው_አመራር_ተገድሏል‼️
ጠላቶቻችንን እየመራ አመጦ ህዝባችንን የሚያስጨፈጭፍ፣ መሰል ድርጊቶችን ያስፈፀም እንዲሁም እህታችንን ጡቶቿን ያስቆረጠና አማራነትን ከቆዳዋ ያስገፈፈው #የብዓዴን_ጀንንበር እየጠለቀች ነው። በዛሬው የአነማይ ወረዳ ከፍተኛ የብአዴን ሹመኛ መገደሉ ይታወሳል። አሁን ደግሞ #ሌላኛው ሆድ አደር አዲስ ቅዳም ቀጠና #ተገድሏል ሲሉ አናብስቶች ለንስር አማራ ገልፀዋል።
ዝርዝር መረጃ ይዘን የምንመለስ ይሆናል‼️
#ደም_በደም_ይጠራል‼️
06/ዐ2/2018 ዓ.ም
ደጋ ዳሞት ወረዳ ላይ ያለው አሁናዊ ሁኔታ
ከወረዳው ዋና ከተማ ከሆነችው ፈረስ ቤት ጠላት ጠቅልሎ ከወጣ ሳምንት ሊሞላው ነው። በከተማው ውስጥ ምንም አይነት የፀጥታ ኃይል የለም። ጠላት ያለው ከሁለት ቦታ ማለትም በስተምስራቅ አቅጣጫ ሻንጊ ደረቄ ዱቤ ተራራ ከሚባል የገጠር ቀበሌ እና በስተደቡብ አቅጣጫ ዝቋላ አረፋ መገንጠያ ከሚባሉ የገጠር ቀበሌዎች ካድሬዎችን ጨምሮ በሁለት ሥራዎች ላይ ሰፍሮ ይገኛል።
ለምንድነው ከተማውን ለቆ የወጣ ብለን ለማጣራት ሞክረን ነበረ። ነዋሪዎቹ የሚያውቁት ነገር እንደሌለና በከተማው የሚናፈሰው ግን መከላከያው ቀድሞ ራሱን ለመከላከል በሁለት ቦታ መስፈርን እንደመረጠ እና
የቡሬ ዳሞት ፋኖዎች ምርቃት ላይ አርበኛ ዘመነ ካሴ ባስተላለፈው መልዕክት "በቅርቡ ወታደራዊ ዘመቻ እናውጃለን" ብሎ በተናገረ ማግስቱ የአብይ አህመድ ሠራዊት ጓዙንና ምግብ የሚሰራበትን ብረድስት፣ እንጨትና ሌሎች ቁሳቁሶችን ማጓጓዝ እንደጀመረ፣ ካድሬዎችና ሚሊሻም አብረው ጓዛቸው ሸክፈው እንደወጡ ለማወቅ ችለናል ።
የደጋ ዳሞት ብርጌድ አሁን ወርቃማ እድል ያገኘ ይመስለኛል። ጠላት በሁለት ቦታ ኃይሉን ቀናንሶለታል!! ወታደራዊ ዕቅድና ስትራቴጂ ነድፎ ቢያንስ አንድ ቦታ ላይ የሰፈረውን ማስቀረት ይችላል። በተለይ ሻንጊ ደረቄ ላይ የሰፈረው ለፋኖ ምቹ ስለሆነ ማድረግ ያለበት ቢያስብበት እላለሁ!!
ፍኖተ-አማራ ሚዲያ ወቅታዊና ትኩስ የፋኖ እንቅስቃሴን መረጃን ከግንባር ሁነን በአራቱም ማዕዘን እየሰራን እንገኛለን።
ለሁሉም አማራ ተደራሽ እንሆን ዘንድ እየሰራን እንገኛለን የበኩሉዎን አስተዎፆ የቴሌግራምና ፊስቡክ ቻናላችን እና ጆይን ሸር አድርጉ አድራሻችን👇👇👇👇 ‼️
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk
https://www.facebook.com/share/p/17FBBgD9xG
