es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 379
Suscriptores
-924 horas
+2477 días
+1 42930 días
Archivo de publicaciones
መርከብ ተራራ ላይ የተዘራዉ ዘር፣ ግሩም ፍሬ አፍርቶ ይሄዉ ሲሰፈር። 👇🏿 ኤፍሬም አጥናፉ ስም ብቻ አይደለም ! ድንገት ባልዋለበት እና ምንም በማይገናኝ የጠላት ሴራ እራሱን ማጎሪያ ቤት ያገኘው 10 አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ብዙ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶቹን በጠላት እጅ ወድቆ አሳልፏል ። ኤፍሬም ከብዙ ስቃይ እና መከራ በኋላ ከ ጠላት ካቴና እጇቹ እንደተፈቱ ቦታ ሳይመርጥ ለአማራነት የሚሰለጥን ወጣት ፍለጋ ትዳር ይዞ ከሚኖርበት  ከባህር ዳር ከተማ በቅርብ እርቀት ወደ ምትገኘዋ ወደ እነ ዘሪሁን እና አንሙት ያዛቸው የትውልድ ቀየ  አዴት ከተማ ጊዜ ሳያባክን የአማራነት ጀግንነቱን ብቻ በመያዝ ስልጠና የአስጀምረ የትግላችን አብሪ ኮከብ እና ችቦ ለኮሽ አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ነው ። አዴት ከተማ በድፍረት ጀመረ፣ አሰለጠነ  ፊት አውራሪውን አርበኛ ' ዘመነ ካሴን ' በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ በገዳዮቹ መሐል በድፍረት የክብር እንግዳ አድርጎ ጋበዘ አርበኛውም  ጠላት ብልፅግና በቁም ቅዠት ውስጥ በነበረበት ወቅት ድብታ ውስጥ ለገባው በዓለም ውስጥ ለሚኖር የአማራ ወጣት መልዕክቱን እንዲህ በማለት በአዴት ከተማ የእግር ኳስ ስታዲዮም  ውስጥ አስተላለፈ " ኤፍሬም ከእስር ቤት እንደወጣ እናንተን ለማሰልጠን ሲወስን አንድ ቀን ከቤቱ አላደረም ፣ ስንሰለጥን ፣ስንደራጅ እና ስንታጠቅ መከባበር እንጀምራለን    " እነዚህ እና መሰል መልዕክቶች የኤፍሬም አጥናፉ ድፍረት ጀግንነት እና የአርበኛ ዘመነ ካሴ የልብ ወዳጅነትን በአደባባይ የመሰከሩ እውነታዎች ናቸው ። የአርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክቶች ጠላት እና የጠላት ሚዲያ እያወገዙት በድፍን ጎጃም የፋኖ ስልጠና ሲጀምር ግን የስራ አስፈፃሚ እና መሰል ውሳኔዎቹን አልንበረም ነበር ። የአማራነት መንፈስ በቁርጠኛው ኤፍሬም አጥናፉ እና በመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ነገን አዋቂነት የአማራ መሬቶች የሚያስተናግዱት የፋኖ ስልጠና ብቻን ሆነ ። ኤፍሬም የተቋምን ፅንሰ ሐሳብ ተቋም በማድረግ በሁሉም አካባቢዎች የተቆማችን የአማራ ህዝባዊ ኃይል የማህበረሰብ ማንቃት ቀጥሎ ያለውን መርሐ ግብር ማለትም የወታደራዊ ስልጠና ምዕራፍ መሬት ላይ በብዙ ቦታዎች ተግባራዊ ምላሽ የሰጠ የአማራ ወንድ ነው ። በዚህም ታሪኩ ኤፍሬም አጥናፉ ግለሰብ ብቻ አልነበረም ። ኤፍሬም አጥናፉ በስልጠና ያስጀመረውን መዋቅራዊ አደረጃጀት ከመሪው አርበኛ ዘመነ ካሴ እና ሌሎች በየደረጃው ካሉ አመራሮች ጋር በሰሜኑ ጦርነት ወቅት መርጦ ለማርያም ከምፕ ውስጥ ከእኔ ጋር በአካል ለ ሶስተኛ ጊዜ ተገናኘን ። በካምፕ ውስጥ ድንቅ ቆይታ ከጓዶቹ ጋር በመሆን አሳለፍን ። ሁሉም ሰራዊት ወደ አቃስታ ጉዞ እንዳያደርግ የአብይ አህመድ ሴራ ተሳካ ። እኔ እና መሰሎቻችን የአቃስታ ጉዟችን ሲይስተጓጎል የነ ኤፍሬም አጥናፉ ጉዞ ተሳካ ። ያኔ የመለያያ ፕሮግራማችን ላይ አርበኛ ዘመነ ካሴ እና ኤፍሬም አጥናፉ እኛ ወደ ትውልድ ቦታችን በመመለሳችን በማዘን ሲሸኙን በአይናችን የተላቀስንበትን ቅፅበት ከቦታው የነበረ ሰው በፍፁም አይረሳውም ። መሪዎች ወደ አቃስታ እኛ ወደ ትውልድ ቦታችን አንድ አላማ በተለያየ ግንባር መጓዛችን ግን ግድ ሆነ ። በቅፅበት ግን ሁሌም አዴት ላይ ከነበረው የፋኖ ምርቃት ላይ አርበኛው ከአስተላለፋቸው መልዕክቶች መካከል " ሕውኃትን እናሸንፋዋለን ቃሌን ያዙ ከዛ በኋላ ግን የአማራ መከራ  አያበቃም " የሚለው  እና በእነ 10 አለቃ አበራ አየለ ሀገር አቸፈር ዱርቤቴ ከተማ ስታዲየም ላይ የክብር እንግዳ ሁኖ በነበረበት ወቅት የተናገረው " 17 ሴት እህቶችህን አሳግተህ እና አስደፍረህ 50 ሁነህ የጀበና ቡና ላይ ተጎልተህ ምን ታደርጋለህ ? የጉንጭህን ጫት ትፋው ! ውጣ ሰልጥን ! ሴት ልጆች ያልሰለጠ ወንድ ልጅን በ Boyfriend ነት አትያዙ " የሚለው ድምፅ  ግን በውስጣችን ለነገ የተባለ የትግል ተስፋ መኖሩን ያሳብቁብን ነበረ ። በቃላችን ፅኑ አድርገውናልም ። ለዚህም ኤፍሬም ግለሰብ አለመሆኑን አስረድቶናል ። የአርበኛ ዘመነ ካሴ ፣ የኤፍሬም አጥናፉ እና የሌሎች ጓዷች  ጉዞ ከመርጦ ለማሪያም ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ሆነ ። ህውሐትም በጦርነት ተሸነፈ ። በዚህ ታሪካዊ የአማራን ህዝብ ከወረራ የመከላከል ሂደት ኤፍሬም አጥናፉ መርከብ ተራራ ላይ ከተሰው ባለታሪኮቻችን መሐል አንዱ ነው ። ከዚህ ጊዜ በሗላ አፅመ እርስቱ አዲስ ቅዳም ገብርኤል ቤተክርስቲያን አፈር ከቀመሰ በኋላ  ኤፍሬም አጥናፉ በስሙ የህዕቡ አደረጃጀት ጉልበት ሁኖ ከሁለት አመት በፊት የአማራ ፋኖ በጎጃም ካሉት ግዙፍ ክፍለ ጦሮች ውስጥ በጎጃም አገው ምድር ውስጥ ያ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ ሁኖ እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ጠላትም የመሰከረላቸው ጀብዶዎች ማስመዝገቡን ቀጠለ ። ለክፍለ ጦሩም ምሳሌ ሆነ ። የኮሶበርን የሰማ ጥሩነህ ፖለቲካ ገደል ከተተ ። የአብይን አዲስ ክልል ምስረታ በአናቱ ተከለ ። አፍርሰነዋል ብለው ሲገመግሙ አዲስ ቅዳም ከተማ ገብቶ ማርኳቸው ወጣ ። የነ ግዛቸውን ሙሉቀንን ቆሻሻ እና ቀሽም ፖለቲካ በአጃክስ አስለቀቀ ። ዛሬም የአ.ፋ.ብ.ኃ አካል በመሆን ድርጅታዊ እዝ እና ሰንሰለቱን ጠብቆ የነፃነት ሐዲዱ ላይ ይገኛል ። ድርጅታዊ መስመር ጥበቃችንንም ከእርሱ የተማሩ ሁሉ ከትላንት በመማር ፣ ዛሬን በመኖር እና ነገን ተስፋ አድርጎ ለመሻገር እንደ ድሮው ሁሉ የ 10 አለቃ ኤፍሬም እጥናፉ ልጆች እና የመንፈስ ተጋሪዎቹ ይጠበቅሉ ። አዲስ ትውልድ ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣ አዲስ ተስፋ ! Girum Misalie ግሩም ምሳሌ

"አማራነት"መልኳ እና ግብሯ ምን ይመስላል ካልከኝ መልሱ "ጋሸን"(ጀነራል ተፈራ ማሞን) ይሆናል። "ጋሸዋ" ይህ ትውልድ አንተን በታሪክ ሳይሆን በአይነ ስጋ በማየቱ እኔም የዚህ ትውልድ አካል በመሆኔ
+1
"አማራነት"መልኳ እና ግብሯ ምን ይመስላል ካልከኝ መልሱ "ጋሸን"(ጀነራል ተፈራ ማሞን) ይሆናል። "ጋሸዋ" ይህ ትውልድ አንተን በታሪክ ሳይሆን በአይነ ስጋ በማየቱ እኔም የዚህ ትውልድ አካል በመሆኔ በእጅጉ ኩራት ይሰማናል። እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥህ!

ከራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የተላለፈ የትግል ጥሪ ‼️                                     ⛔️ጤና ይስጥልኝ!!! ሰውም ኢትዮጵያዊም ያልሆነውን ጭራቅ ከህዝባችንና ከሀገራችን አናት ላይ አንስተን ማንነታችንን አክብረን እና አስከብረን  የምንኖርበትን ስርአት ለመገንባት በጋራ እንነሳ!!!!   የአማራ ህዘብ በተፈፀመበት እና አሁንም እየተፈፀመበት ባለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምክንያት እራሱን ለማዳን እያደረገ ባለው ተጋድሎ አኩሪ ድሎችን ተጎናፅፏል። ሊያጠፉት እስከ አፍንጫቸው ታጥቀው የመጡትን ጠላቶቹን በታላቅ ወኔ እና ጀግንነት እየተፋለመ በያሉበት እየደመሰሰ፣ እራሱን እያደራጀ፣ ከጠላት የማረከውን እየታጠቀ ህልውናውን ለማስከበርና የወዲፊቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር በመተባበር በጋራ ለመወሰን ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል። እኛ አማራዎች በእያንዳንዱ ቀን ከምናደርገው የጦር ሜዳ ፍልሚያ ጎን ለጎን እራሳችንን የማሰልጠን፣የማስታጠቅ እና የማደራጀት ስራችንን ያለአንዳች መዘናጋት አጠናክረን እንቀጥላለን። አደረጃጀቶቻችንም የተናበበና የተቀነባበረ አመራር ለመስጠት በሚያስችለን መልኩ ለማሰባሰብ የምናደርገውን ጥረት በጥሩ መንገድ በትጋት እየሰራን ነው። ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ሀይሎች ጋር የምናደርገውን የትግል አጋርነት እና ቅርርብ መልክ ለማስያዝ የአማራ ፋኖ በከፍተኛ ትጋት እየሰራ ነው።    አማራ እራሱን እየተከላከለ በትጥቅ እና በአደረጃጀት ሀይሉን እያጠናከረ ከሌሎች ኢትዮጵያን ሀይሎች ጋር ትግሉን አስተባብሮ በድል ለመቋጨት የሚያደርገው ትንቅንቅ እንደተጠበቀ ሆኖ በከተሞች የሚኖረው ህዝብ ግን የአረመኔው የአብይ አገዛዝ ዋና ገፈት ቀማሽ ሆኖ እያለ በእጁ ብዙ ሊጠቀምበት የሚችል የትግል ግብአት እና ሀይል ቢኖረውም እስካሁን በተደረገው ትግል ላይ የትጥቅ ትግሉን በመጠኑ ከመደገፍ ባለፈ በተገቢው ሁኔታ የትግሉን ጊዜ እና መስዕዋትነት ለማሳጠር በተቀናጀ መንገድ አልተነቃነቀም።   በዛሬዋ የአብይ አህመድ አረመኔያዊ አገዛዝ ኢትዮጵያ በከተሞች ለሚኖረው ህዝብ በሰላም ወጥቶ መግባት ብርቅ ነው። ያለ ጉቦ ጉዳይ ማስፈፀም የማይታሰብ  ሆኗል። ልጆቹን ለሚገድልበት ገንዘብ ለማሰባሰብ ህዝባችንን አጥንቱን እየጋጠው ነው። በኑሮ ውድነት ሰቅዞ እያሰቃየው ነው። ከትግል መነሻችን ጀምሮ በተደጋጋሚ እንደገለፅነው የአማራ ህዝብ ህልውና የሚጠበቀውና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተጫነውን አገዛዝ ከነግሳንግሱ መቅበር የሚቻለው ሁሉንም የትግል ስልቶች በተገቢው ቦታ እና ጊዜ በተጠና እና በታቀደ መንገድ አቀናጅቶ እና አዋህዶ በመምራት እንደሆነ ላፍታም መዘንጋት የለበትም።    የኢትዮጵያ ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ አረመኔው አብይ አህመድ በትጥቅ የሚፋለሙትን ጀግኖች ለማጥፋት ሴራ የሚጎነጉንበት፣ስንቅና ትጥቅ የሚያገኝበት፣የወንበዴ እና የዘር አጥፊ መደበቂያ ዋሻ መሆኑ በአፋጣኝ ማክተም አለበት። በመሆኑም በከተሞች የሚኖረው ህዝባችን ነባራዊ ሁኔታው በሚፈቅደው የትግል አይነት ሁሉ እምቢተኝነትን በማፋፋም አረመኔውን ስርአት ለመንቀል በቆራጥነት እንዲነሳ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ የከተማ ትግላችንን በልዩ ሁኔታ የሚከታተል እና የሚያስተባብር የስራ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ተገቢውን አመራር እንደሚሰጥ እናሳውቃለን። ድል ለአማራ ህዝብ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ ትውልድ አዲስ አስሳሰብ አዲስ ተስፋ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ህዳር 6_2018 አም አርበኛ ዘመነ ካሴ

የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ፋኖዎች በጠላት ላይ ጥቃት ፈጸሙ! የተለመደ የወረራ ተግባሩን ለመፈጸም ከደብረ ኤልያስ ተነስቶ ወደ ቸርተከልና ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነ
+1
የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ፋኖዎች በጠላት ላይ ጥቃት ፈጸሙ! የተለመደ የወረራ ተግባሩን ለመፈጸም ከደብረ ኤልያስ ተነስቶ ወደ ቸርተከልና ከደብረ ማርቆስ ከተማ ተነስቶ በየቦ በኩል ወደ ሊባኖስ ቀበሌ ለመግባት በመድፍ የታገዘ ሙከራ ቢያደርግም ከደብረ ማርቆስ ከተማ የወጣው በጀግኖቹ የ14ኛ ክፍለ ጦር የበረኸኛው ጅበላ ሙተራ ሻለቃ ፋኖዎች ከፍተኛ ምት ደርሶበት ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ወደ መጣበት ተመልሷል። በጀግኖቹ ሜዳ ገብቶ የጀግኖቹን በተር መቋቋም ያቃተው ወራሪ ሠራዊት የፈሪ ዱላው በሆነው መድፍና ሞርተር የንጹሐንን ሕይወት ሲቀጥፍ ውሏል። በተያያዘ ዜና ቸርተከል ታዳጊ ከተማን የወረረው ወራሪ የብልጽግና ሠራዊት በአሁኑ በባንዶች እየተመራ የነዋሪዎችን ቤት እየበረበረና እየዘረፈ ይገኛል። እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ በዚህ አስነዋሪ ተግባሩ የተማረረው ሕብረተሰብም ቤቱን ጥሎ እየተሰደደ እንደሚገኝ ማወቅ ተችሏል። በዚህም መሠረት አንድ ዜማ በቃል የተባለችን የልጆችን እናት በአሰቃቂ ሁኔታ ጨፍጭፏል። ጥቅምት 04/2018 ዓ/ም ድል ለአማራ ፋኖ ፋኖ ዘመን ባሳዝነው የ206ኛ ኮር 14ኛ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ

#ከአርበኛ_ዘመነ_ካሴ_የተላለፈ_መልዕክት‼️ አርበኛ ዘመነ ካሴ የአፋብኃ ሴንተራል ኮማንድ አባልና የቴዎድሮስ ዕዝ ሰብሳቢ ህዳር 6/2018 ዓ.ም ያስተላለፈው መልዕክት‼️ 06/ዐ3/2018 ዓ.ም

የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ሲሆን ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎ 4 የስርዐቱ ወታደር 4 ጥቁር ክላሽና ሙሉ ትጥቅ በመያዝ    ምስራቅ አማራ ኮር አንድ የባለሽርጡ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል። የሚዋጋበት አጀንዳ የሌለው የብልፅግና ሰራዊት አሁንም በሰሜን በኩል አዲስ ጦርነት ጀምሮ ሊያዋጋን ስለሆነና መምሪያም እየወረደ ስለሆነ ነው ኮብልለን ፋኖን የተቀላቀልነው ይላሉ አንድ ስናይፐርና አምስት ክላሽ ይዘው ምኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ኮር አንድ የባለሽርጡ ክፍለጦርን የተቀላቀሉት  የሰራዊቱ አባላቶች:: በዚህም 4 ጥቁር ክላሽ  ከሙሉ ትጥቁና ተተኳሹ ጋር  እንዲሁም  የወገብና የደረት ትጥቅ ከተተኳሽና የእጅ ቦምቦች በመያዝ ወደ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦርን  ተቀላቅለዋል:: በሌላ የተጋድሎ መረጃ ምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር  እና ምስራቅ  አማራ ኮር 2 ታጠቅ ክፍለጦር  መርሳ አቅርቢያ ወረራሎ በሚባል ቦታ በተያዘ   የደፈጣ ጥቃትና በወሰዱት እርምጃ አንድ ጓድ የጠላት ሰራዊት  ቀረጥ በሚቀርጡበት ቦታ ላይ በተያዘ ዴንገተኛ ጥቃት ሙትና  ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ፋኖ ደምሌ መኮነን የምስራቅ አማራ ኮር 1 የባለሽርጡ ክፍለጦር ቃል አቀባይ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ህዳር 6/2018 ዓ.ም

ታዳጊዋ_ከተማ_ፋኖ_ተቆጣጠራት‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ሸዋንግዛው ካሳ (1ኛ) ሻለቃ ሻፊ ታዳጊ ከተማን ተቆጣጠረ:: በምዕራብ ወሎ ግንባር ከላላ እና ለጋምቦ ወረዳዎች ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር አካል የሆነው ሸዋንግዛው ካሳ (1ኛ) ሻለቃ ሰራዊት በተለያዩ አቅጫጫዎች ከበባ በማድረግ ከላላ ከተማ አቅራቢያ የምትገኘውን ሻፊ ታዳጊ ከተማን  ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረ ሲሆን ከከተማይቱ ነዋሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት እና ምክክር ማድረጉም ታውቋል:: ከዘረኛው እና ተረኛው እንዲሁም ጄኖሳይደሩ ስርዓት ጎን የቆሙ የፀጥታ አካላት ወደ ቀልባቸው ተመልሰው የአማራ ህዝብን ስለመካስ ማሰብ እንዳለባቸውና ሳይውሉ ሳያድሩ ስርዓቱን ከድተው ወደ ፋኖ እንድቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት በበርካታ ቀጠናዎች ውስጥ የሲቪል አስተዳደር መዋቅር እየተሰራ የወረዳው ነዋሪዎች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ወርቃማ ዕድል መመቻቸቱን የክፍለ ጦሩ አዛዥ አርበኛ አለልኝ የገለፀ ሲሆን ፋኖ የግለሰቦችን የዕለት ግጭት ከመፍታት እና በጥቃቅን የሰፈር ጉዳዮች ከመጠመድ ይልቅ ጠላትን እየመታ ወደ ፊት መገስገስ አለበት የሚል አቋም ተይዞ የሰፈር እና የቀበሌ ጉዳዮችን ለሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለሲቪል አስተዳደር መዋቅሩ አመራሮች መተው እንደሚገባ ስምምነት ላይ መደረሱንም ነው ለማረጋገጥ የቻልነው:: በከላላ ግምባር የሳጅን አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ሰራዊት ከሻፊ ታዳጊ ከተማ በተጨማሪ ባከት እና ቅዳሜ ገበያ የተባሉ ታዳጊ ከተሞችን ከጠላት ነፃ ማውጣቱ የተገለፀ ሲሆን ከተሞቹ ዛሬም የፋኖ ጦር ሰፈሮች መሆናቸውን ክፍለ ጦሩ አስታውቋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! ©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ 06/ዐ3/2018 ዓ.ም

ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር የአማራ ህዝብ በነብዩ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ አማራ አንድ ሁኑ ከዛሬ 500 ዓመት በፊት እንደነበረው አማራ ተከቧል ብሎ እንደተናገረ አርኣያና አምሳሉን በመከተል በጥቂት ቁርጠኛ ልጆች የተመሠረተ የአማራን ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ቀድመው በተረዱ የቁርጥ ቀን ልጆች በሻለቃ ደረጃ ተመስርቶ ከሻለቃ ወደ ብርጌድ፣ከብርጌድ ወደ ክፍለ ጦር አሁን ላይ ሰባት ክፍለ ጦሮችንና ሁለት ብርጌዶችን እየመራ በስምንት ወረዳዎች ነፃ ቀጠናዎችን ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ግዙፍ ኮር ነው። ይህ ግዙፍ ኮር በምኒልክ ዕዝ ስር የሚገኝ ሲሆን የአማራ አንድነትን የሚፈልግ ለአንድነት እየሰራ የሚገኝ ከሰፈርተኝነት አስተሳሰብ አልፎ በአማራ የተለያዩ አደረጃጀቶች ወደ አንድ እንዲመጡ ያላሰለሰ ጥረት ያደረገ፣እያደረገ የሚገኝ እነ ኮሎኔል ፈንታው ሙሃቤንና እነ መኩየን ከእነ አለቃ ምሬ ወዳጆ ጋር አንድ ለማድረግ እየጣረ የነበረ የጄኔራል አሳምነው ፅጌ ልጆች ስብስብ የያዘ ግዙፍ ኮር ነው። ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ማንም ሳያግዘውና ድጋፍ ሳያገኝ ገጀራ፣ጩቤና ዱላ ይዞ ከመከላከያ ጋር ተፋጦ ገጥሞ ብዙ መሳሪያዎችን ማርኮ የታጠቀ በሙጃ ማርያም፣በቡያ፣በሹምሽሃ አየር ማረፊያ ብዙ ተጋድሎዎችን ፈፅሞ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ የደረሰ ግዙፍ ኮር ነው። ግዙፉ ኮራችን በአመለ ሸጋው አርበኛ ኮማንዶ ሃምሳ አለቃ ወንድሙ ማሩ የሚመራ ሲሆን አርበኛው የአማራ አንድነት እንዲመጣ ታከተኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀን ከሌሊት የሚሰራ በምስራቅ በሶማሊያ ሰላም አስከባሪነት እንዲሁም በሰሜን የታገለ አርበኛ አሁንም ለአማራ ህዝብ አንድ ህይወቱን አስይዞ ለአማራ ህዝብ ታከተኝ ሳይል ልጅነቱን በትግል እየጨረሰ ያለ የአማራ አንገቱ አንድ ነው በማለት ለአማራ አንድነት እየሰራ የሚገኝ እጅግ የምንሳሳለት ቁርጠኛ ታጋያችን ነው። በመሆኑም አንዳንድ በበሬ ወለደ የሚያምኑ የእኛን ታጋዮቻችን አንዱን ከፍ አንዱን ዝቅ ለማድረግ የሄዱበትን ርቀት ስናይ፣ሲለፋደዱ እያየናቸው በመሆኑ ይህም የብልፅግና የሳይበር ሰራዊት ጠብደል ተከፋይ ግሪሳዎች መሆናቸውን ተረድተናል፤ዛሬም አይናችን ከኳሷ ላይ እንደተተከለች መሆኗ አርበኛው በአንዳንድ ወለፈንዲ ወሬኞች ቦታ የሌለው ደንታ የማይሰጠው እንደ አለት የጠነከረ ለወደፊትም ለአማራ አንድነት ሁሉንም ሳይሰስት የሚሰጥና የሚሰራ ነው። በመጨረሻም የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ ህልውናው እስካልተረጋገጠ ድረስ ትግሉን ዳር ሳያደርስ የማይተኛ እስከ ቀራኒዮ የሚደርስ ታጋያችን ለቀቅ ታደርጉልን ዘንድ የቄሳርን ለቄሳር በሚለው ብሒል ወንድማዊ ምክሬን እለግሳለሁ። "አርበኛው ኮማንድ ፍቅሩ ሙሉዬ የአማራ ፋኖ የከላስታ አውራጃ አሳምነው ኮር ምክታል አዛዥ።

🚨በጠላት አፍንጫ ስር የምትገኘዋ አባይ ሻለቃ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ስብሰባ ተካሄደ... አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦ አባይ ሻለቃ (ሕዳር 6/2018 ዓ.ም) ክን
+4
🚨በጠላት አፍንጫ ስር የምትገኘዋ አባይ ሻለቃ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ስብሰባ ተካሄደ... አፋብኃ ምዕ/ አ/ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦ አባይ ሻለቃ (ሕዳር 6/2018 ዓ.ም) ክንደ ብርቱዋ በ77ኛ ክፍለ ጦር ስር የምትገኘዋ አባይ ሻለቃ ውስብስብ የሆኑ ለአመታት አልፈታ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የሻለቃ አመራሩ አባላቶችን ሰብስበዋል። በስብሰባውም ሻለቃዋን ለመበተን እና እርስ በእርስ ለማጋጨት የተሞከሩ ክንውኖችን በጋራ በመቃወም፣ ለአማራ ህዝብ ለመኖር እንቅፋት የሆነውን አረመኔውን ስርዓት ከህዝቡ ትክሻ ለማላቀቅ የምንጊዜውም ተግባራችን ነው ሲሉም አመራሩ መክረዋል። የስብሰባው ተሳታፊ የሆኑት አንዳንድ አባላቶች ሻለቃዋ ላይ ተፈጥሮ የነበረውን ውስብስብ ችግር በጥልቀት በመረዳት አንድ የመሆን እና ጠላት በጋራ ሁነን ማጥፋት አለብን ሲሉም አባለቶች አስተያታቸውን አቅርበዋል። አንጋፋዋ እና ከብር ሸለቆ በ6 ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኝዋ ታምር ሰሪዋ አባይ ሻለቃ ውስብስብ ችግሮችን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ከትክሻዋ በማውረድ፣ ማነኛውንም ግዳጅ ለመፈጸም ዝግጁ ነን ሲሉ አመራሮቹ መልዕክ አስተላልፈው ስብሰባውን ቋጭተዋል። ➤ዘገባው የጋዜጠኛ አይቸው ጌታሰው ነው🙏🙏 #ድል_ለዐማራ_ህዝብ

የእንግሊዝ መንግስት ወደ #ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ዜጎቹ በሰጠው የጉዞ መመሪያ በአረንጓዴ ቀለም የተገለፁ አካባቢዎች ብቻ እንዲጓዙ መክሯል። በቢጫ ቀለም የተገለፁ አካባቢዎች ደግሞ ከስጋት ያልወጡ ቦታዎች
የእንግሊዝ መንግስት ወደ #ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ዜጎቹ በሰጠው የጉዞ መመሪያ በአረንጓዴ ቀለም የተገለፁ አካባቢዎች ብቻ እንዲጓዙ መክሯል። በቢጫ ቀለም የተገለፁ አካባቢዎች ደግሞ ከስጋት ያልወጡ ቦታዎች ሲሆኑ ... በቀይ የተገለፁ አካባቢዎች ላይ ደግሞ በፍፁም እንዳይጓዙ አሳስቧል !! በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከጦርነት በተጨማሪ የህዝብ አመፆች ሊኖሩ እንደሚችል የተፈራ ሲሆን የተለያዩ #ኤምባሲዎች ለዜጎቻቸው ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ነው !! አማራ ፣ ኦሮሚያ ፣ ትግራይ ፣ ሶማሊያ ክልሎች በአመዛኙ ሰላምና አለመረጋጋት ያለባቸው አካባቢዎች ሆነው ተቀምጠዋል። የሆነው ሆኖ ሀገሪቱ በዚህ አረንቋ ውስጥ ሆና ነው #ብልፅጌ ወደብ አስመልሳለሁ የምትለው 🤔 !!

‎የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን የመማሪያ ቁሳቁሶችን በበረኸት ወረዳ እየዘረፈ መሆኑ ተገለጸ። ‎======================= ‎ ‎የአብይ አህመድ ግትልትል ሰራዊት በሰሜን ሸዋ በረኸት ወረዳ የትምህርት ቤት ቁሳቁሶችን በመዝረፍ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ተጽዕኖ እያደረሰ ነው:: ‎ ‎ይህ ፋሽስት የብልፅግና አገዛዝ የአዉደ ዉጊያ ሽንፈቱን መቀበል ሲያቅተዉ  ንፁሀንን ከመጨፍጨፍ ባለፈ የትምህርት ቤት ቁሳቁስ በመዝረፍ እና የህዝብ መገልገያ መሰረተ ልማቶችን በማውደም ማህበረሰቡ ለከፋ ችግር እንዲጋለጥ እያደረገ ነዉ። ‎ ‎ቡድኑ የተለመደውን የክፋት ተግባር በሰሜን ሸዋ በረኸት ወረዳ ምንታምር ቀበሌ የሚገኝ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ዉሳቁስ በመዝረፍ የተለመደ እኩይ ተግባሩን ፈጽሟል:: ‎ ‎ይህ የአብይ አህመድ ደም መጣጭ የጥፋት ቡድን በበረኸት ወረዳ ምንታምር ቀበሌ የሚገኝ  የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሆነ 12 ላፕቶፕ እና ኮምፒዉተሮችን በመዝረፍ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲስተጓጎል አድርጓል:: ‎ ‎በዚህ የአብይ አህመድ ሰራዊት ዘረፋ የተቆጡ የበረኸት ወረዳ ኗሪዎች ጥያቄያቸውን ለሚመለከተው የትምህርት ቤቱ ሱፐርቫይዘር አቤቱታቸዉን ያቀረቡ ሲሆን የትምህርት ቤቱ ሱፐርቫይዘር የህዝብን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ንብረቶቹ እንዲመለሱ ለሚመለከተው አካል ቢያቀርብም ወዳውኑ ወደ እስር ቤት በመወርወር ለህዝብ ጥያቄ ያላቸውን ንቄት በገሀድ አሳይተዋል:: ‎ ‎የትምህርት ቤቱን ሱፐርቫይዘር ወደ እስር ቤት በመወርወር እርካታ ያላገኘው የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን የህዝብ አገልግሎት ሰጭ የውሃ መስመር በመቁረጥ ህዝቡ ለከፋ የውሃ ችግር እንዲጋለጥ አድርጓል::       መረጃውን ያደረሰን የአፋብኃ  ደቡብ አማራ ቀጣና አሳምነው ዕዝ ከሰም ኮር  ቡልጋ ክፍለጦ ሪፖርተር ቦጋለ ምንዳ ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"      አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ  የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል ህዳር 06/03//2018 ዓ.ም ‎ ‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነዉ እዝ ከሰም ኮር ቡልጋ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት

..............የአደረጃጀት ዜና !! ........... በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር የ66ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የ
+3
..............የአደረጃጀት ዜና !! ........... በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ( አፋብኃ ) የቴዎድሮስ ዕዝ የ105ኛ ኮር የ66ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ። ክፍለጦሩ በአምስት ውህድ ሻለቃ የተዋቀረ ሲሆን ለቀጣይ የህልውና ትግል ዝግጁ መሆናቸውን የክፍለጦሩ ፣ የሻለቃ አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ። የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ስራው በፋኖ ኃይለሚካኤል ባየህ እና በ105ኛ ኮር አመራሮች አስተባባሪነት ተጠናቋል ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ በአንድ ወቅት ያስተላለፈው መልዕክት ነው። ለዛሬ እጅግ ጠቃሚ ነው! “ለአማራ ሕዝብ 3 የእሁድ ሰንበት መልዕክቶች አሉኝ፦ 1) አማራ ሆይ፥ በአስተሳሰብም በተግባርም አ
የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ በአንድ ወቅት ያስተላለፈው መልዕክት ነው። ለዛሬ እጅግ ጠቃሚ ነው! “ለአማራ ሕዝብ 3 የእሁድ ሰንበት መልዕክቶች አሉኝ፦ 1) አማራ ሆይ፥ በአስተሳሰብም በተግባርም አማራ ሁን። 2) ለኅልውናህ ከአንተ በላይ ስላንተ የሚቆረቆርልህም ሆነ የሚታገልልህ የለም። ይትባሃሉም «ባለቤት ያቀለለውን፥ ባለእዳ አይቀበለውም» ነው። 3) አማራ ሆይ፥ እባክህን የሚታገሉልህንና የምትታገላቸውን በውል ለይ። «በርባን ይፈታ፥ ክርስቶስ» ይሰቀል አካሄድህን በውል መርምረህ ማስተካከል ካልቻልህ ባርነትን ወደህ ፈቅደህ መምረጥህን እወቅ። ስንደማመጥ፣ ስንተማመንና ስንከባበር ከባዱ ቀላል ይሆናል!” ክርስቲያን ታደለ 💚💛❤

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ሃይል የማዕከላዊ ኮማንድ አባል እና የደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዋና መሪ ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ በርታልን አይበገሬው የጦር አርበኛ፣ የፅናት አስተማሪ፣ገደብ የሌለው ቅንነት እና ታታሪነት የኢ/ር ደሳለኝ መገለጫዎች ናቸው። በአማራ ፋኖ የህልውና ትግል ውስጥ ቀድመው አብዮቱን ከለኮሱት ጠንካራ ጦረኞች ውስጥ ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ ነው። የአማራ ህዝብ ትግል መደማደሚያው  ሸዋ በርካታ ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶች ተጋርጠውበት የቆየ ሲሆን በተለይም ዓላማ በሌላቸው ሰራጊ ሃይሎች የተፈተነው የኢ/ሩ ሰራዊት በከባድ መስዋአትነት ሃይል መሰብሰብ እና ማጠናከርን ቀጥሎበታል። በአፋብኃ ምስረታ ሰሞን የነበሩ የውስጥ ተግዳሮቶችን በመፍታት ረገድ  በፅናት ተቋቁሞ  በማለፍ ጠንካራ ሃይል እየገነባ ይገኛል። በቅርብ ወራት የተመሰረቱት የአሳምነው ዕዝ ግዙፉ ከሰም ኮር እና አፄ ዘረያቆብ 1ኛ ኮር ማሳያ ናቸው።   ከጠላት በቅርብ ርቀት ላይ ጠንካራ ወታደራዊ አደረጃጀቶችን መፍጠር የመሪዎች ትጋት እና የሰራዊት ጥንካሬ  ሲሆን አጠቃላይ የአማራ ህዝብ ትግል ትኩረቱን ሸዋ ላይ እንዲያደርግም ኢ/ር ደሳለኝ እና ሰራዊቱ በትኩረት እየሰሩ መሆናቸው ታውቋል። ወንድማማቾቹ የአፋብኃ መንትያ ዕዞችም ሃይላቸውን ወደ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ እንዲያደርጉ ሁለንተናዊ ወትሮ ዝግጁነቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተከናወነ መሆኑ ታውቋል። እንደሚታወቀው ጦረኛው ኢ/ር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ በአማራ ህዝብ ትግል ዓላማዎች እና በአማራነቱ የማይደራደር ትንታግ መሪ መሆኑም ይታወቃል። ክብር ለሚገባው ሁሉ ክብር እንሰጣለን!!🙏🙏 ስንደማመጥ እና ስንከባበር ከባዱ ቀላል ይሆናል!! ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ

ተሪ የስርዓቱ መቃብር ደሴት ሆናለች! ፅናት ክፍለ ጦርና 23ኛ ክፍለ ጦር ቃኞች የስርዓቱን አመራር ደመሰሱ! አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለጦር እና ልጅ እ
+1
ተሪ የስርዓቱ መቃብር ደሴት ሆናለች! ፅናት ክፍለ ጦርና 23ኛ ክፍለ ጦር ቃኞች የስርዓቱን  አመራር ደመሰሱ! አፋብኃ ምስርቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለጦር እና ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር የሻለቃ ቃኝዎች በጥምረት የብልፅግናና አከርካሪ ተሪ በረሀ ላይ ሰበሩ!! በፓትሮል አራት የመከላከያ አመራሮች ሲንቀሳቀሱ በአራቱም አመራሮች ላይ በተወሰደባቸው እርምጃ ተደምስሰዋል።የሚፈረጥጡባት ፓትሮልም እንደ አለቆቿ እርምጃ ተወስዶባታል። ህዳር 6/2018 ዓ/ም ከደላንታ እና ከተንታ ወረዳ መነሻውን አድርጎ ሲቀሳቀስ በነበረው የፋሽስቱ ሰራዊት ላይ ፋኖዎች በወሰዱት ጠንካራ ኦፕሬሽን ሙትና ቁስለኛ አደረጉት። ከአራቱ ከፍተኛ አመራሮች በተጨማሪ በርካታ የስርዓቱ ወታደሮች የተሪ ጅብ እራት ተደርገዋል። ከተማንና ህዝብን ምሽግ አድርጎ ሲማግጥ የነበረው የፋሽስቱ ሰራዊት ጭር ባለው የተሪ በረሀ ተቀጥቅጧል። ራሱን ብልፅግና እያለ የሚጠራው ጨፍጫፊው ስርዓት በአራቱም አቅጣጫ በቆፈረው ምሽጉ እየተቀበረ ይገኛል። ቆሎ ለናፈቀው ህዝብ የድሮን ቦብ የሚያዘበው ስርዓት ቃጠሎ ቤት ላይ ዘላ እደገባች እንቁራሪት ጣረሞት ላይ የሚገኘው የመድፍም ሆነ የድሮን አጀብ የፍርሀቱና የሞቱን መላዕክት ሊያስተጓጉሉለት አልተቻላቸውም። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር   እና የልጅ እያሱ ኮር ጥምር ቃኞች!! ህዳር 6/2018 ዓ.ም