es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

ፍኖተ-አማራ ሚዲያ (Finote Amhara Media)

Ir al canal en Telegram

የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)

Mostrar más
4 413
Suscriptores
+2224 horas
+437 días
+1 38430 días
Archivo de publicaciones
ከትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ አደረጃጀቶች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በሚያስተዳድራቸው የወረዳና የቀበሌ ከትግሉ
+3
ከትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ አደረጃጀቶች ተጠናክረዉ ቀጥለዋል‼️ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በሚያስተዳድራቸው የወረዳና የቀበሌ ከትግሉ ጎን ለጎን ህዝባዊ ውይይቶችን እና አደረጃጀት መዋቅሮች እየሰራ ይገኛል። የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ አንደኛ ኮር በቅርቡ ታሪካዊ ወረዳ የሆነችውን ግሽ ራቤል እና በዙሪያው ያሉትን ቀበሌዎች ከአብይ አህመድ አገዛዝ ነፀሠ አውጥቶ እያስተዳደረ የሚገኝ ሲሆን በዚሁም ግሽ ራቤል ወረዳ በፈርስ ቤት ቀበሌ የኮሩ አመራሮች በተገኙበት የማህበረሰብ አደረጃጀቶች በመፈጠር ሰፊ ሰራዎችን ሰርቷል። በውይይቱም አሁን ላይ አንኳር አንኳር ነጥቦች የተነሱ ሲሆን እነዚህም ነጥቦች 1. የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ወቅታዊ አቋም ምን ይመስላል 2. የአብይ አህመድ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰው ያለ ግፍ 3. የፋኖና የህዝብ ማህበራዊ ፖለቲካዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ትስስር የቀጣይ አቅጣጫ እነዚህንና የመሳሰሉ አንኳር አንኳር ነጥቦችን በማንሳት በዓጼ ዘራዓ ያእቆብ ፩ኛ ኮሩ አመራሮች እና በብሩኬደምሴ ክፍለጦር አመራሮች አማካኝነት አማካኝነት የህዝብ አደረጃጀቶች ተፈጥሮል። በመጨረሻም ማህበረሰቡ ከልጆቻችን ጋር አብረን ለአማራ የነፃነት ተምሳሌት ፋኖዎች ጋር እንመክራለን፣እንወያያለን፣እንደራጃለን፣እናቅዳለን፣ጠላትን ድባቅ እንመታለን በማለት ድርጅታዊ መዋቅር መሰረት ህዝባዊ አደረጃጀት በመስራት ተጠናቀዋል። መረጃው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ 1ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት ነው። " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ‎አፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ‎ ጥቅምት 24/ዐ2/2018 ዓ.ም

የ #ወለጋ ተፈናቃዮች '' ...የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት ልጆቻችን በረሀብ ሊሞቱብን ነው'' ሲሉ ገለፁ! 💔 በ2013 ዓ.ም ከኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ፣ በታጣቂዎች የተፈፀመባቸውን የጅምላ ፍ'ጅት በመሸሽ ተሰደው የመጡና ላለፉት አመታት ፣ በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ #ማሻ ከተማ 02 ቀበሌ ፣ በፕላስቲክ ድንኳን ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል። ተፈናቃዮቹን በመወከል ንግግር ያደረጉት አቶ ዘሪሁን አዳል በ2013 ዓ.ም ከወለጋ ሆሮጉድሩ ዞን ከአቤዶንጎሮ ወረዳ ከደቢስ ቀበሌ የሸኔን ጥቃት ሸሽተው እንደተሰደዱ በመግለፅ '' ...4 አመት ሙሉ በአሮጌ የሸራ ድንኳን ውስጥ ተጠልለን እንገኛለን። በመንግስትም ሆነ በሌሎች በጎ አድራጊ ተቋማት በኩል ትኩረት ተነፍጎናል። ባለፈው የካቲት 5 ቀን በመንግስት በኩል በእርዳታ ስም የተሰጠን የበሰበሰና ለምግብነት የማይውል በቆሎ ብቻ ነው። በቆሎው ለእንጀራም ሆነ ለቆሎ አይሆንም። የተበላሸ ስለሆነ ወፍጮ ቤቶች እንኳ አንፈጭም ብለውናል። ...FRS የተሰኘ ድርጅት ትንሽ ባይደግፈን ኖሮ እስካሁን ህፃናትና አቅመ ደካሞችን ጨምሮ ሁላችንም በረሀብ አልቀን ነበር።'' ሲሉ ገልፀዋል። 😥 አቶ ዘሪሁን አክለውም '' ለዚህን ያህል አመት በእንደዚህ አይነት ስቃይ ውስጥ ስንቆይ በመንግሥት በኩል በዘላቂነት ለማቋቋምም ሆነ በጊዜያዊነት ረሀባችንን ለማስታገስ እዚህ ግባ የሚባል ድጋፍ እተደረገልን አይደለም። በመሆኑም ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ከረሀብ አደጋ ታደጉን!'' የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል። እንደሚታወቀው ላለፉት አመታት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከአሰቃቂው ጭፍ'ጨፋ አምልጠው በአማራ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በተመሳሳይ ችግር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ፣ የክልሉ መንግስት በተለያዩ ጊዜያት '' ተፈናቃዮቹን ወደነበሩበት ቦታ የመመለስ ስራ እየሰራሁ ነው!'' ሲል ቢደመጥም ፣ በአካባቢው ያለው የደህንነት ስጋት በነበረበት የቀጠለ በመሆኑ ፣ ''በረሀብ ከመሞት..'' ብለው በፈቃደኝነት ተመልሰው ለመሄድ የሞከሩት እንኳ ገሚሶቹ ለሞት ቀሪዎቹም ለዳግም ስደት ሲዳረጉ የነበረበት ሁኔታ የሚታወቅ ነው። በመቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ 02 ቀበሌ መጠለያ ካምፕ ከሚገኙት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተፈናዮችን ወክለው አስተያየት የሰጡት ሌላኛው አስተያየት ሰጪ '' በ2013 ተፈናቅለን እንደመጣን አካባቢ በተሻለ ሁኔታ የእለት ጉርሳችንን የሚሆን መጠነኛ ድጋፍ እናገኝ ነበር። ነገርግን ከዚያ በኃላ በ7 እና በ8 ወር እንኳ የሚያስታውሰን የለም። በአሁኑ ሰአት የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት ልጆቻችንን ጨምሮ ሁላችንም በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን። ወገኖቻችን ድረሱልን!'' የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። መረጃው ለሚመለከተው አካልና ለቅን የወገን ልቦች እንዲደርስ #ሼር በማድረግ ተባበሯቸው! #ሼር

ሰሜን እዝ ፋኖና ዐምሓራ ዐምሓራ ሀገር ወዳድ ሕዝብ እንደሆነ ካሳየባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሰሜኑ ጦርነት ነበር። በዚህ ጦርነት ጀማሪውም ጨራሹም ዐቢይና ያሳደዳቸው ጓዶቹ ሕውሓታውያን ናቸው። የኦነግና የትህነግ ሴራ ነበር። ኋላ ሻቢያም እጇን አስገብታ የምትፈልገን ያክል ተጫውታለች። ከእነዚህ ሁሉ አክተሮች የፋሲካው በግና ንጹሑ ታጋይ ለተወጉት ልጆቹ ፈጥኖ የደረሰው የዐምሓራ ሕዝብ ነበር። እናቶች የማያውቁትን ተሳዳጅ የመከላከያ ሠራዊት እርጎ ጠላ እንጀራ ምስር ወጥ ያገኝዑትን ሁሉ እየቀለቡ የታመመውን አስታመሙት፤ የሞተውን አልቅሰው ቀበሩት፤ የደከመውን አበረቱት። ወደ ቤቱ የሚሄደውንም መቀነታቸውን ፈተው አሳፈሩት። ቆይቶ ግን ሴራው አሁንም በኦነጋውያንና የኦሮሙማ  ቁማርተኞች ተቀምሞ ጦርነቱ መሀል ዐምሓራን አልፎ ወደ ሰሜን ሽዋ ወረደ። በዚህ መካከል የዐምሓራ ሕዝብ መክፈል የማይገባውን ዋጋ ለሀገር ሲል ከፈለ። ብዙ ተቋማት ወደሙ ብዙ ወጣቶች አለቁ። በጭናና በማይካድራ ንጹሐን በሺዎች ተጨፈጨፉ። ፋኖ ጫፍ ድረስ ተጉዞ የተከዳውን ወገኑን አዳነ፤ ከሞት ጎሮሮ አዳነ ወንድሜ ነው ብሎ ከመከላከያው ጋር በአንድ ጉድጓድ ተቀበረ። ግና ግና ያ ከዐምሓራ እናት እጅ እርጎና ሥጋ እየተመገበ ያገገመ ሠራዊት፣ ያ የዐምሓራ እናት መቀነቷን ፈታ ወደ እናቱ የላከችው መከላከያ፤ ያ ጓደኛው ሲሞትበት ሕዝብ ሆ ብሎ ፍትሐት ፈቶ ሲቀብርለት ያየ መከላከያ ሴራው ደርቶ አሁንም ግባና ያጎረሰህን እጅ ንከሰው፤ ያበላችህን እናት ግደላት፤ ውኃ በጀርባዋ ያመጣችልህን ወጣት ድፈራት ደፍረህም ጡቷን ቁረጣት ተብሎ ሲላክ እሽ ብሎ የተባለውን እየፈጸመ ይገኛል። በኢትዮጵ ታሪክ ለመከላከያ እንደ ቆሎ ተማሪ ስንቅ ቋጥራ ከሞት ያዳነች የዐምሓራ እናት ናት። ያቺ ደግ እናት ግን አሁን ጥቁር ለብሳ በኀዘን ብዛት ኮስሳ ፤ አንጀቷ አርሮ ፊቷ ተኮማትሮ ሠርታ እንዳትበላ ተከልክላ፤ ለልጆቿ ታበላቸው አጥታ ጎዳና ወጥታ ወድቃለች። እጇ አመድ አፋሽ ሆኖ ባዳነቺው ሠራዊት ትታረዳለች። ይህን ቀን ሰሜን ዕዝ የተጠቃበት ሆኖ ሳስበው ከዚያ ጥቃት ተርፈው አሁንም ከገዳዩ ጎን ተሰልፈው ወገናቸውን ያዳናቸውን የሚገድሉ የመከላከያ ጀነራል ተብየወች መኮነኖች ተራ ወታደሮችን ሳስብ ባትተርፉ ልል አስብና ሰብአዊነት ያግተኛል። ግን ታሪክ የማይረሳው ውለታበልነት በመከላከያ ሠራዊት አማካኝነት በዐምሐራ ሕዝብ ላይ ተፈጽሟል። የዐምሓራ እናት እንባ የራሄልን እንባ ሆኖ ይፈጃችኋል። አሁንም ውጡና የበደላችኋት እናታችሁን ካሷት። ©ባንተ አምላክ አያሌው

Profile Pic. መቀየር በሀገር ውስጥ ቋንቋዎችም ጽሁፎችን ማጋራት ጥሩ ሀሳብ ነው። ዜጎች ያለንበትን እንዲረዱ ያደርጋል። የበለጠ ግን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ስለጉዳዩ እንዲረዳ፣ ተጽእኖም እንዲያሳድር ፣ በተጨማሪም እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ ተሰንዶ እንዲቀመጥ Tweeter & Email Campaign ማድረግ የተገባ ነው። በዋናነት ከታች የተቀመጡትን Email Address የምንጠቀም ይሆናል። 🌍 International & Human Rights Organisations Human Rights Watch — hrwnyc@hrw.org Amnesty International — contactus@amnesty.org United Nations Human Rights (OHCHR) — InfoDesk@ohchr.org International Christian Concern — icc@persecution.org Christian Solidarity Worldwide — admin@csw.org.uk 🇪🇺 European Union European Commission (Religious Affairs) — vincent.depaigne@ec.europa.eu European External Action Service (EEAS) — nabila.massrali@ec.europa.eu, gesine.knolle@ec.europa.eu EU Agency for Fundamental Rights (FRA) — information@fra.europa.eu 🇺🇸 United States Government Tom Lantos Human Rights Commission — TLHRC@mail.house.gov U.S. Senate Committee on Foreign Relations — Web_Inquiry@foreign.senate.gov The White House — comments@whitehouse.gov, president@whitehouse.gov ... በተጨማሪም ሀገር ውስጥ ያሉ ኢንባሲዎችን ታርጌት አደርገን መልዕክታችንን በ English እናስቀምጥ። ለ Tweeter Campaign እነዚህን መጠቀም ትችላላችሁ Copy ለማድሰግ እንዲመች Comment ላይ አንድ በአንድ አስቀምጣቸዋለሁ 👇👇👇👇👇 This week in Arsi, Oromia, Ethiopia: reports say more than two dozen were massacred, homes emptied, churches burned. An entire community left in fear. Look at their faces. Remember their names. Demand justice. #OrthodoxTawahedoGenocide In Ethiopia, they came for the faithful in the night  mothers, fathers, little children massacred. Churches burned, holy places turned to ash. Our hearts bleed for lives stolen for no reason. Protect the worshippers. #OrthodoxTawahedoGenocide Hundreds of Ethiopian Orthodox Christians are killed every year  not as statistics, but as fathers, mothers, priests, children. Families shattered, communities terrorized. The world cannot stay silent. #OrthodoxTawahedoGenocide Blood has stained the lands of Ethiopia. In Arsi Oromia families weep for fathers and mothers taken, for priests killed in holy service, for churches burned. Hundreds have been massacred this year alone. Faith should never cost a life #OrthodoxTawahedoGenocide When a church in Ethiopia is burned and a child’s laughter is silenced, all of humanity suffers. We mourn with the families. We will not let their deaths be forgotten or go unanswered. #OrthodoxTawahedoGenocide To those in power in Ethiopia: protect the innocent. To the world: bear witness. To survivors: you are not alone. Let our outrage become action for accountability, safety, and peace. #OrthodoxTawahedoGenocide In Ethiopia the horror continues. This year alone hundreds of Orthodox Christians have been slaughtered. Churches have been burned to the ground. Priests, mothers, fathers, and children killed in cold blood. Arsi Oromia cannot be silent. The world must see their pain #OrthodoxTawahedoGenocide In Arsi Oromia Ethiopia more than two dozen believers were massacred this week. Families torn apart. Churches set aflame. Every life taken a universe lost. We cannot turn away from this suffering. Stand for the innocent #OrthodoxTawahedoGenocide Ethiopia mourns again. Hundreds of Orthodox Christians have been slaughtered this year. Priests murdered. Churches destroyed. Children left orphaned. The faith that has lived for centuries faces terror and fire. Remember their faces. Remember their names #OrthodoxTawahedoGenocide Each church burned in Ethiopia is a wound in the soul of the world. Hundreds of Orthodox Christians massacred this year. Children, elders, priests slaughtered. In Arsi Oromia and beyond the pain is unimaginable. Let us witness. Let us act #OrthodoxTawahedoGenocide

ወገልጤና ከተማ ውስጥ በነበረ የጠላት ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈፀመ የሰርጎ ገብ ጥቃት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት
ወገልጤና ከተማ ውስጥ በነበረ የጠላት ወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈፀመ የሰርጎ ገብ ጥቃት በርካቶች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለጦር ዛሬ ጥቅምት 24/2018 ዓ/ም ወገልጤና ከተማ ውስጥ በነበረ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ካምፕ ድረስ ዘልቀው በመግባት በርካታ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጋቸውን በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪ በላከው መረጃ አስታውቋል። በዛሬው ጥቃት በርካታ የጠላት ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን ነው ዕዙ የገለፀው። (ምስል ከማህደር)

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከአማራ ፋኖ በወለጋ የተሰጠ ጥብቅ መግለጫ‼ ጥቅምት 24/2018ዓ.ም
+1
በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ከአማራ ፋኖ በወለጋ የተሰጠ ጥብቅ መግለጫ‼ ጥቅምት 24/2018ዓ.ም  

አሳዛኝ ዜና በጎጃም ቋሪት ወረዳ ከነጭ ዉሃ ቀበሌ ወደ ገበዘ ማሪያም ከተማ ለገበያ ሲጓዙ የነበሩ በቁጥር ያልታወቁ ግን በርከታ ሰዉ በአገዛዙ አራዊት ሰራዊት ተረሽነዋል ። ይህንንም ቢዛሞ ሚዲያ ከወረዳው ኗሪዎች  አረጋግጣለች።

በአውደ ውጊያ ዝነኛዋና ጥንቅቅ ያለችው ፅናት ክፍለ ጦር በሰርጎ ገብ ኦፕሬሽን እጅን በአፍ የሚያስጭን ጀብድን በወገልጤና ከተማ ፈፅማለች!!! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ
በአውደ ውጊያ ዝነኛዋና ጥንቅቅ ያለችው ፅናት ክፍለ ጦር በሰርጎ ገብ ኦፕሬሽን እጅን በአፍ የሚያስጭን ጀብድን በወገልጤና ከተማ ፈፅማለች!!! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለጦር! ጥቅምት 24/2018 ዓ/ም ወገልጤና ከተማ ከፋሽስቱ ሰራዊት ካፕ ድረስ ዘልቀው የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። የደጋው መብረቅ ኮር ከተመሰረተበት እለት አንስቶ በጥላት ላይ ከፍተኛ ጥቃትንና የሞራል ውድቀትን ባሉት የአናብስት ክፍለጦር ስብስቦች እያደረሱበት ሲገኙ። በዛሬው እለት ከሁለት በላይ የፋሽስቱ ሰራዊት በካፓቸው ውስጥ እስከወዳኛው የተሸኙ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ከፍተኛ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። ቅስፈታዊ ጥቃት እንደ እንደ መብረቅ ከፋኖዎች የተሰነዘረበት የፋሽስቱ ሰራዊት የሚረግጠውን ምድር ሁሉ እየተጠራጠረ ፈንጅ ወረዳ እደገባ እየተበዣበዠ ይገኛል። ወገልጤና ለፋሽስቱ ሰራዊት ገሀነብ ሆናበት ንፍስ ግቢ ውጭ እያለ ይገኛል። ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

በአውደ ውጊያ ዝነኛዋና ጥንቅቅ ያለችው ፅናት ክፍለ ጦር በሰርጎ ገብ ኦፕሬሽን እጅን በአፍ የሚያስጭን ጀብድን በወገልጤና ከተማ ፈፅማለች!!! አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለጦር! ጥቅምት 24/2018 ዓ/ም ወገልጤና ከተማ ከፋሽስቱ ሰራዊት ካፕ ድረስ ዘልቀው የብርሀኑ ጁላን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። የደጋው መብረቅ ኮር ከተመሰረተበት እለት አንስቶ በጥላት ላይ ከፍተኛ ጥቃትንና የሞራል ውድቀትን ባሉት የአናብስት ክፍለጦር ስብስቦች እያደረሱበት ሲገኙ። በዛሬው እለት ከሁለት በላይ የፋሽስቱ ሰራዊት በካፓቸው ውስጥ እስከወዳኛው የተሸኙ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ከፍተኛ ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። ቅስፈታዊ ጥቃት እንደ እንደ መብረቅ ከፋኖዎች የተሰነዘረበት የፋሽስቱ ሰራዊት የሚረግጠውን ምድር ሁሉ እየተጠራጠረ ፈንጅ ወረዳ እደገባ እየተበዣበዠ ይገኛል። ወገልጤና ለፋሽስቱ ሰራዊት ገሀነብ ሆናበት ንፍስ ግቢ ውጭ እያለ ይገኛል። ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) የደጋው መብረቅ ኮር ፅናት ክፍለ ጦር ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

🎯 ንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር ቆላ ሃሙሲት ከተማ ላይ የጠላትን ምሽግ በመደርመስ በርካታ የብልጽግና አገልጋዮችን ደመሰሰ።         ትላንት ጥቅምት 23 ለ 24 /2018 ዓ.ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ላይ የዳግማዊ ቴዎድሮስ ፭ ኮር  አንዱ አካል የሆነው ንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር  ከጓህላ በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኘው ቆላ ሃሙሲት ከተማ ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን የብልጽግና ሰራዊት ጋር ለ5 ሰዓታት ያህል የወሰደ አውደ ውጊያን በማካሄድ በርካቶችን ገድሎ ፤ በርካቶችንም አቁስሎ በምርኮ የሚሊሻ አባላትንም ገቢ አድርጎ ውጊያውን በበላይነት አጠናቋል ።          🎯  ንስሮቹ 3 የጠላት ኮንክሬት ምሽጎችን በመስበር የጠላትን ኃይል ለቅሶ በለቅሶ  ከማድረጋቸውም በላይ ጠላት ሲጠቀምበት የነበረውን ወታደራዊ ቁሳቁሶችንና የሎጅስቲክ አቅርቦቶችንም መማረክ ችለዋል።           🎯  በዚህ ውጊያ እንደ ስማቸው ከፍ ብለው የበረሩት ንስሮቹ እስከ ጠዋቱ 3:30 ድረስ ከተማዋን በቁጥጥር ስራቸው አድገው የቆዩ ሲሆን ጠላት አስከሬኑንና ቁስለኛውን ለቃቅሞ ለመውጣት አውደ ውጊያው ከተደረገበት በ20 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከምትገኘው ጓህላ ከተማ  ተጨማሪ ኃይል ይዞ በመንቀሳቀሱ ወታደራዊ ጥበብን በመጠቀም ከተማዋን ለቀው እንደወጡ የክ/ጦሩ ቃል አቀባይ ገልጿል።            🎯 በዚህ ውጊያ  ከተገኙ ድሎች:-               ** 18 የመከላከያ አባላት የሞተ               **  7 የሚሊሻ አባላት የሞተ               **  5 የሚሊሻ አባላት እስከነ ሙሉ ትጥቃቸው ተማርከው አሁንም በክ/ጦሩ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።      በመጨረሻም ጠላት በመላው የበለሳ አካባቢዎች ጠራርገን ለማስወጣትና ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ ወታደራዊ ግዳጁን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን የክ/ጦሩ ቃለ አቀባይ ጨምሮ ገልጿል።    ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።       አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ   ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

~~~~|| በጎንደር አማራ ፋኖ አደረጃጀቶች መካከል የተፈጠረው ሰክኖ በርን ዘግቶ ከመወያየት እና የተለያየ ፍላጎት ካላቸው ቡድኖች በተላቀቀ መልኩ መሬት ላይ ባሉ ኃይሎች ብቻ በመከናወኑ ይሄን የፀና የአንድነት አደረጃጀት ሊፈጥር ችሏል።  ይሄ ወደፊት የፖለቲካ ሁኔታዎችን በራስ አቅም ለመበየን እንዲያስችል የጣልቃ ገብ ያልተቀደሱ እጆችን የማሳጠር ትልቅ እርምጃ ነው። በሸዋ እና በወሎ ተመሣሣይ የመዋህድ ሂደቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚኖሩ ተስፋችን ከፍ ያለ ነው። የተከፋፈለ ሃይል በሃገራዊ ፖለቲካ ውስጥም ተመራጭ የመሆን ዕድል ስለሌለው ይሄን መከወን ለነገ የሚባል አይሆንም። አሸናፊነታችን ያለው ከአንድነታችን ላይ ያለ በመሆኑ ፤ ከአንድነት ውጭ በተበጣጠሰ አካሄድ መንቀሳቀስ ነገ ለተያዩ ሃይሎች ነጣጥሎ መጫዎቻ እና ማዳከሚያ የማድረግ  ፍላጎት ተጋላጭነትን ስለሚጨምር አማራነት መርህ ላይ ማዕከል ባደረገ መልኩ አንድነት ፍቱን መከላከያ የብረት አጥር ነው። የአንድነት ሂደቶች ሁሌም ያስደስቱናል! በዛብህ በላቸው

የአረመኔው አብይ አህመድ ጦር በየቀኑ እየፈረሰ ወደ ፋኖ በመቀላቀል ላይ ይገኛል። በትላንትናው ዕለትም ፦ ‎1. አየነዉ ግርማ/ አካፋ ክላሽንኮቭ እና 100 ፍሬ ‎2. አብርሃም ቢተዉ/ሁለት እግር ክ
የአረመኔው አብይ አህመድ ጦር በየቀኑ እየፈረሰ ወደ ፋኖ በመቀላቀል ላይ ይገኛል። በትላንትናው ዕለትም ፦ ‎1. አየነዉ ግርማ/ አካፋ ክላሽንኮቭ እና 100 ፍሬ ‎2. አብርሃም ቢተዉ/ሁለት እግር ክላሽንኮቭ 70 ፍሬ በመያዝ የቢትወደድ አያሌዉ መኮንን ብርጌድን ተቀላቅለዋል። አፋብኃ|ቴዎድሮስ ዕዝ ሕ.ግንኙነት መምሪያ            ጥቅምት 24/2018 ዓም

ጥቅም 24 አብይና ጌታቸው የኢትዮጵያ የደሀ ልጆች ያስጨፈጨፉበት ቀን ነው ቀኑ እንዲረሳ ጥቅም 24 የፕሪቶራያ ስምምነት ተፈራረሙ። ዛሬ ደግሞ ጌታቸው ረዳ እና አብይ አህመድ ሌላ ዙር እልቂት ለመፈፀ
+4
ጥቅም 24 አብይና ጌታቸው የኢትዮጵያ የደሀ ልጆች ያስጨፈጨፉበት ቀን ነው ቀኑ እንዲረሳ ጥቅም 24 የፕሪቶራያ ስምምነት ተፈራረሙ። ዛሬ ደግሞ ጌታቸው ረዳ እና አብይ አህመድ ሌላ ዙር እልቂት ለመፈፀመም አብረው እያሴሩ ነው። የኢትዮጵያ እናት ስንቶች ያለ ቀባሪ ቀሩ ።

አብይ አህመድን የተከተሉ ሁሉ ሲበለፅጉ ያየንበት አንዳችም ሃይል አላየሁም። አሁን ላይ አብይ አህመድ በመኖርና ባለ መኖር ላይ ያለ የዘመኑ ሳጥናዬል ብለው ማጋነን አይሆንብኝ። እንዲያው ለነገሩ እኔ
አብይ አህመድን የተከተሉ ሁሉ ሲበለፅጉ ያየንበት አንዳችም ሃይል አላየሁም። አሁን ላይ አብይ አህመድ በመኖርና ባለ መኖር ላይ ያለ የዘመኑ ሳጥናዬል ብለው ማጋነን አይሆንብኝ። እንዲያው ለነገሩ እኔ ከኦሮሞ ማር አልጥብቅም እንጅ ከእሱ ጋር የተሰለፉ የአማራ ባለስልጣናት ለዚህ ሁሉ በእየቀኑ ለሚሞተው ህዝብ ለማሰብ ምን ተሳናቸው ይሆን። እናም ምን ልላችሁ መሰለችሁ አንድ ሞኝ ናዳ መጣልህ ቤሉት ተወው ተከናንቤዋለሁ አለ ይባላል ሲል አንድ ወቅት አርበኛ ዘመነ ካሴ ሲናገር ስምቻለሁ። የተከናነበውን የአማራ ጠላት የምናባርረው ብቻችን ሁነን ሳይሆን አንድ ላይ በአራቱም ማዕዘን በመሰለፍ ነው። ወደ አንድ ጠላት መንደር ገብቸ የአይን ቅጥረኛ መከላከያ አገኘሁና እንዲት ናችሁ ሰላም ብዬ ሰላምታ ተለዋወጥን መለዋወጥ አንበለው መከላከያ በአሁኑ ስዓት የእኛን አንድነትም እየጠበቀ ያለ ይመስላል። እናም አንድነት ኃይላችን ነው።

የድል ዜና!! ዛሬ ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም 206ኛ ኮር በርካታ ምርኮዎችን ማረከ!! የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ዮፍታሄ 206ኛ ኮር  ጦር አካላት የሆኑት የደጋ መብረቆቹ የስናን አባጅሜና የንጉስ ተክለ ሃይማኖት ብርጌድ አናብስቶች የጡት ቆራጩን የብልጽግና ሠራዊት የጠድ፣ የደማንና አራት አልጋ በሚባሉ ቦታዎች ታላቅ ውጊያ በመክፈት ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅተዋል። ይህ ወራሪ ሠራዊት ላለፉት ቀናት ያክል ከደብረ ማርቆስ ከተማ ወደ ረቡዕ ገበያ ሬሽን ለማቀበል እንቅስቃሴ ቢያደርግም የሕዝብ ልጆች ጀግኖቹ የስናን አባጅሜና የንጉስ ተክለ ሃይማኖት ፋኖዎች መንገድ ላይ ደፈጣ በመጣል ውሃ ጋን ላይ ተወሽቆ እንዲቆይ አድርገውት የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት በ03 BTR፣ 107 ሮኬት፣ በዙ- 23፣ በ03 ሞርተርና በሌሎች ሞተራይዝድ መሳሪያዎች ታጅቦ የሞት ሽረት እንቅስቃሴ ቢያደርግም በእነዚህ የጦር ግምባሮች ላይ ከፍተኛ ምት ደርሶበት፤ ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናግዶ አስከሬኑን፣ ተሽከርካሪዎቹንና መሳሪያውን እያዝረከረከ ወደ ረቡዕ ገበያ ከተማ ፈርጥጧል። በጠዋት በተጀመረው ውጊያ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ ቃል ተናጋሪ ሆነው የሚሰሩት ሁለቱ ብርጌዶች በመናበብና ትስስር በመፍጠር  ከፍተኛ የሆነ የድል ውጤትን አስመዝግበዋል። በርካታ የጠላት ሠራዊት በተደመሰሰበት በዚህ ውጊያ ብዙ የጠላት ሠራዊት የቆሰለ ሲሆን ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ተቃጥለዋል፤ ሌሎችም በጀግኖቹ ጥይት ከጥቅም ውጭ ሆነዋል። በተጨማሪም በአውደ ውጊያዎች የተደመሰሰ የጠላት አስከሬንና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን የጫኑ መኪኖችም በጀግኖቹ ጥይት ተመተው ከጥቅም ውጭ ሆነዋል። በተያያዘ ዜና ሁለቱ ብርጌዶች ይህን ገድል ባደረጉበት ተመሳሳይ ሰዓት ጀግኖቹ የበረኸኛው  ጅበላ ሙተራ ብርጌድ ፋኖዎች በየቦ በኩል ደብረ ማርቆስ ከተማ በመግባት በጠላት ጥቃት ፈጽመዋል። ጊዜያዊ የድል መረጃ 👉 02 ብሬን ተማርኳል 👉 ከ60 በላይ ክላሽ ተማርኳል 👉 08 ምርኮኛ ተማርኳል 👉 01 ኦራል ሙሉ በሙሉ ተቃጥሏል 👉 በውጊያው የተደመሰሰ የጠላትን አስከሬን የጫነ አንድ ሲኖትራክም በተመሳሳይ ተመቶ ከጥቅም ውጭ ሆኗል 👉 ከ100 በላይ ጡት ቆራጭ የመከላከያ ሠራዊት ተደምስሷል 👉 አንድ የጠላት ፓትሮል ተመታ በፔምፒ ተጎትታ ወጥታለች 👉 ቁጥሩ ያልታወቀ የጠላት ኃይል ቆስሏል 👉 ከ5000 በላይ የክላሽና የብሬን ተተኳሽ  በፎቶና በቪዲዮ የምንገልፅ ይሆናል። አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ! አፋብኃ| ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ34ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል
+3
የአፋብኃ  ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ34ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። በአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ሂደት በመገባደድ ላይ  ይገኛል። ክፍለጦሩ በአምስት ሻለቃዎች የተደራጀ  ሲሆን ውህድ ሆነው የተደራጁት ሻለቆች በቀጣይ ለሚሰጣቸው ድርጅታዊ ስምሪትም  ዝግጁ መሆናቸውን  አመራሮች እና አባላት አረጋግጠዋል ። ክፍለ ጦሩን መልሶ ለማደራጀት የተገኙ የአፋብሀ ምራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ ዕዝ አመራሮች  1 አርበኛ ምናልባት ይታየው የዲያሰፖራና ውጭ ግንኙነት መምሪያ ሀላፊ 2 አርበኛ ሰለሺ ከበደ የቴዎድሮሰ ዕዝ ም/አደረጃጀት መምሪያ ሀላፊ 3 መቶ አለቃ እሱባለው ዋለ የቴዎድሮሰ ዕዝ የሰው ሀይል ኃላፊ እና የ206ኛ ኮር አመራሮች በተገኙበት የአፋብኃ  ምዕራብ አማራ ቀጠና የቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር የ34ኛ ክፍለጦር ምስረታ ተጠናቋል ። ድል ለአማራ ፋኖ!! አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!!

‎የአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለ ጦር በኦሮሚያ ክልል ገብቶ ውጤታማ የሆነ ኦፕሬሽን ሰራ። ‎=========== ‎የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለ ጦር ኦሮሚያ ክልል  በመግባት የብልጽግና መራሹ የጥፋት ቡድን ላይ ስኬታማ እና የጠላትን ቅስም የሚሰብር ኦፕሬሽን አከናውኗል:: ‎ ‎የኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለ ጦር 3ተኛ የሰላም ሰው አንዳርጌ ሬጅመንት በኦሮሚያ ክልል ሀሙስ ገበያ አቅራቢያ ልዩ ቦታው ዘንጎ ኪዳነ ምህረት አካባቢ ዘልቆ በመግባት ለሁለተኛ ጊዜ የተጠናና ውጤታማ ኦፕሬሽን ፈፅሟል:: ‎ ‎ኦፕሬሽኑን የፈጸመው የኃይለ ማርያም ማሞ ክፍለ ጦር የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ጠንካራ ይዞታ በነበረው የኦሮሚያ ክልል  በመግባት ነው:: ‎ ‎በዚህም ልዩ ኦፕሬሽን የተደናገጠው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና የአብይ አህመድ ዙፋን አስጠባቂ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛውን ጥሎ ፈርጥጧል:: ‎ ‎መራር ሽንፈቱን መቀበል ያቃተው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና የአብይ አህመድ ግትልትል ሰራዊት በንፁሀን ላይ የሚያደርገውን ጭፍጨፋ በመቀጠል ንጹሃንን በማሰር እና የ8 ዓመት ልጅ በግፍ በመግደል የተለመደውን ግፍ ፈጽሟል:: ‎መረጃውን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የኃይለ ማሪያም ማሞ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት አድርሶናል። ‎         " ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን" ‎አፋብኃ ደቡብ  አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ዜና ክፍል    ጥቅምት 23/2018 ዓ.ም