ፍኖተ- አማራ ሚዲያ (Finote- Amhara ) Midea
Ir al canal en Telegram
የተመሠረተው የአማራን ሕዝብ ለማንቃት፣ ለማደራጀት እና ለማስተባበር ነው። የአማራ ሕዝብን ✅ ፖለቲካዊ ✅ ማህበራዊ ✅ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊ ጥያቄዎችን ለማሰማት እና የአማራን ሕዝብ በማንቃት ሰፊውን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሰራል። ወደዱም ጠሉም የኃላ ታሪካችን በእኛ እጅ ይፃፋል። አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ( አፋብን)
Mostrar más3 678
Suscriptores
+2624 horas
+3797 días
+1 10930 días
Archivo de publicaciones
በነፃ ቀጠናዎች ህዝባዊ ዉይይቶች እንደቀጠሉ ናቸዉ፡፡
=====
206ኛ ከፍያለው ደሴ ኮር ገብርዬ ክፍለ ጦር ራስ -ጋይንት አርብ ገበያ ከተማ ህዝባዊ ውይይቶችን አስቀጥሏል፤
በአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ በራስ ጋይንት ኮማንድ ፓስት ከሚያስተዳድራቸው ከተሞች አንዷ የሆነችው ራስ ጋይንት በብዐደን አጠራር ታች ጋይንት ዋና ከተማ አርብገበያ ማህበረሰብ ጋር ሰፊ ውይይቶች ተደርገዋል።
ከባለፈው ነፋስ መውጫ ከተማ የህዝብ ውይይት በኋላ በጣም የተሻሻለ ፀጥታ እና መልካም አስተዳደር እንደሰፈነ የተናገሩት የወረዳዋ ከተማ ነዋሪዎች በሚከተሉት ጉዳዮች ውይይቶች ተደርገዋል።
1ኛ, የፈረሰው የብልፅግና ስርዐት እና የአማራን ህልውና መታደግ፤
2ኛ,የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማትን ማስጀመር እና ደህንነታቸውን መከታተል
3ኛ,የኮማንድ ፓስት ህፀፆችን ማስተካከል እና መገምገም
4ኛ,የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ድጋፍ ማስቀጠል እና የህዝብ አስተዳደር መዋቅሮችን መዘርጋት እና ፍትህን ማስፈን ፤
እንድሁም ሌሎች የፓለቲካ ጉዳዮች በስፋት በመወያዬት ከህዝባችን ጋር በሃሴት ውይይቶችን ጨርሰናል፤
በሚል የተደረገው ውይይት በኮማድ ፓስቱ ሰብሳቢ ፋኖ ደመወዝ ግዳፍ እና በገብርዬ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ
ክንድሰው ከፍያለው ደሴ በመምራት ህዝባችን በፍፁም ፍቅር፤ሞራል እና አስደሳች ውሳኔዎች ተከውነዋል።
የራስ ጋይንት ኮማንድ ፓስት
ድምጽ አልባው ሚሳኤል(ዋርካው)
በኢትዮጵያ ተራሮችና ሸለቆዎች ውስጥ ስሙ እንደ ነጎድጓድ የሚሰማው ምሬ ወዳጆ፣ የተራቆተውን የጀግንነት ታሪክ መልሶ ያለመለመ አንጀት አርስ መሪ ነው። የእርሱ ማንነት በቃላት ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን፣ በተግባር የተፈተነ የወርቅ ማዕድን ነው።
፩. አንደበተ ርቱዕነትና ሆደ ሰፊነት
ምሬ ወዳጆ መድረክ ላይ ሲቆም አንደበተ ርቱዕ ነው። የሚናገራቸው ቃላት እንደ ማር የጣፈጡ፣ እንደ ጦር የተሳሉ ናቸው። ህዝቡን የሚያጽናናበትና ጠላትን የሚያስበረግግበት ንግግሩ የቃላት ድርድር ሳይሆን የልብ ትርታ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በትግሉ ውስጥ የሚገጥሙትን ውጣ ውረዶችና የሰዎችን ስህተት በሆደ ሰፊነት የሚያልፍ ቻይ መሪ ነው። አይበሳጭም፣ አይቸኩልም፤ ሁሉንም በትዕግስት መዝኖ መፍትሄ ይሰጣል።
፪. ልበ ሙሉነትና በራስ የመተማመን ችሎታ
መከራ በጸናበትና ሞት አፋፍ ላይ በቆመበት ሰዓት እንኳ ምሬ ልበ ሙሉ ነው። ፍርሃት በፊቱ ላይ አይታይም። ይህ በራስ የመተማመን ችሎታው ደግሞ ከዕብሪት ሳይሆን ካመነበት ዓላማ የመነጨ ነው። "እኛ እናሸንፋለን" የሚለው ጽኑ እምነቱ በተከታዮቹ ዘንድ እንደ ሰደድ እሳት ተስፋን ይጭራል።
፫. ፊት አይቶ አዳሪነትና ሀቀኝነት
ምሬ ወዳጆ የራሱን ምቾት ሳይሆን የባልደረቦቹን ስሜት የሚረዳ ፊት አይቶ አዳሪ (ለሰው አክብሮት ያለውና ስሜት ተገዢ) ነው። ከታጋዮቹ ጋር እኩል አፈር እየላሰ፣ እኩል እየራበው የሚዋጋው ለሰው ልጅ ካለው ጥልቅ ክብር የተነሳ ነው። ይህ ሀቀኝነቱና እውነተኛነቱ በጠላት ዘንድ እንኳ ሳይቀር የሚመሰከርለት ግብሩ ነው። ቃሉን አይበላም፣ የቆመለትን ዓላማ በገንዘብ ወይም በስልጣን አይለውጥም።
፬. ጽናት፣ ወንድነትና ሀገር ወደድነት
የምሬ ወዳጆ ትልቁ ሀብቱ ሀገር ወደድነቱ ነው። ስለ ኢትዮጵያ ክብር ሲል የግል ህይወቱን ትቶ በበረሃ የተንከራተተው ለዚሁ ነው። በብርድና በቸነፈር ውስጥ ያሳየው ጽናት፣ ከምንም በላይ ደግሞ በቁርጥ ቀን ለወገኑ የደረሰበት ወንድነቱ በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም ይጻፋል።
ምሬ ወዳጆ ለህዝቡ አንጀት አርስ፣ ለጠላቱ ደግሞ የማይበገር ልበ ሙሉ ጀግና ነው።
Dawit Amhara አፋብን የመኖር ነፃነት ድርጅታዊ ቤታች የቴሌግራም ገፃችን👉
https://t.me/httpsuYkZrGfSZrNjNjFk

የጎፍ ክፍለ ጦር ከደሴ በ45 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የጠላትን ምሽግ በመስበር ድል አስመዘገበ::
አፋብን ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር የጎፍ ክ/ጦር የካቲት 04/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ጥላት ይመካበት የነበረውን ፉርሴ ተራራ ምሽግ ከተኮሱ እጥላት ኪስ ውስጥ መክተት የሚችሉት ሞርተረኞች ምሽጉን ታርጌት በማድረግ በደቂቃዎች በመስበር ጥላት አንድ ጥይት ሳያፈነዳ ወደ አልብኮ ወረዳ ሳልመኔ ፈርጥጧል።በሌላኛው ግንባር የገባው የክፍለጦሩ መክት ሻለቃ ነጋሽ ከተማን በደቂቃዎች ውስጥ የተቆጣጠሩ ሲሆን የክፍለጦር ቃኝነ፣ስበርና መክት ሻለቃ ደግሞ ደጋጋ ከተማን ተቆጣጥረዋል።
ከተቆጣጠሩ ቡሀላም የኦህደድ ብልፅግና ቡድን የአማራን ህዝብ ለመጨፍጨፊያ መሳሪያና ተተኳሽ መግዣ የህዝቡን ኑሮና አቅም ያላገናዘበ ዋጋ ተምኖ ሊቸበችብ የነበረ ማዳበሪያ ከደበቀበት በከተማው ዙሪያ ለሆኑ አርሶ አደሮች በነፃ አከፋፍሏል።በዚህም ፋኖ ምን ያክል ለህዝብ አዛኝ እና አሳቢ መሆኑን አሳይቷል።የዚህ የግለሰብ ዙፋን ጠባቂ ጨፍጫፊ ቡድን ከተማውን ለቆ ሲፈረጥጥ ውጭ ላይ ያገኛቸውን ንፁሀን ላይ እየተኮሰ የጥላቻ ብትሩን አሳርፏል።
ይህ አልበቃ ብሎት ከደሴ መድፍና ተጨማሪ ሀይል በማምጣት አቧራ እሚባል ቦታ ላይ በማጥመድ በደመነፍስ ወደህዝብ በመተኮስ ጥላቻውን ያሳዬ ሲሆን የሰው ሂወት ባይጎዳም በርካታ የንፁሀን ንብረት አውድሟል።በደፈጣ፣በቆረጣ፣በስቦ መምታትና መልሶ ማጥቃት የተካኑት የጎፎች ይህንን ተረኛ አጥፊ ቡድን አሳፍረው አሯሩጠው ክንዳቸው እንደማይቀመስ አሳይተውታል።ህዝባችንም በልጆቹ እንድኮራ አድርገዋል።
መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብን ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ ዕያሱ ኮር የየጎፍ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 6/2018ዓ.ም
ይህ ትውልድ በታሪክ መጋረጃ ፊት ቆሞ የታላቁን አማራ ህዝብ የነገ የመኖርና ያለመኖር እጣ ፈንታ የሚወስንበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል። እኛ ዛሬ የተሸከምነው ኃላፊነት ተራ የፖለቲካ ተሳትፎ ሳይሆን፣ ትውልድን ከጥፋት የመታደግና የታሪካችንን አቅጣጫ የመቀየር ከባድ የታሪክ አደራ ነው። ይህ ምዕራፍ የትግላችን ማሳረጊያ፣ የነፃነታችንም መባቻ ነው።
ባለፉት ዓመታት ህዝባችን ያለፈበት መንገድ በተለይም በመተከል የተሰራብን ግፍ በኤፍራታና በአጣዬ ምድር የፈሰሰው ደም፣ በደራ የተከፈለው መስዋዕትነት፣ በራያና በወልቃይት አውድማዎች የታየው ግፍና መከራ ለቁጥር የሚያዳግት ነው። በነዚህ ቦታዎች ያልገበርነው ህይወት፣ ያልከሰከስነው አጥንትና ያላፈሰስነው እንባ የለም። ይህ ሁሉ መከራ ግን ህዝባችንን ለማንበርከክ ሳይሆን፣ ይበልጥ እንዲጸናና ለነፃነቱ እንዲነሳሳ የሚያደርገው የእሳት ጥምቀት ሆኖ አልፏል።
ዛሬ የምንገኝበት የታሪክ ምዕራፍ ልዩ ነው። ትላንት በመከራና በስቃይ ማዕበል ውስጥ ሆነን የዘራነው የጽናት ዘር፣ ዛሬ ለነፃነት ማማ መቆም መሰረት ሆኖናል። የነፃነት ማማችን የሚፈልቀው ከደረሰብን ግፍ ሳይሆን፣ ያንን ግፍ ተቋቁሞ ለክብሩ ከቆመው የአማራ ህዝብ ጽኑ ልብ ውስጥ ነው። አሁን ላይ ቆመን የምናየው ብርሃን የብዙ ሺዎች መስዋዕትነት ውጤት ነው፤ ይህንን የነፃነት ፀሐይ ደግሞ ማንም ሊያጨልመው አይችልም።
የአማራ ፌኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አርበኛ ኤፍሬም ባዩ
ከየካቲት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የታወጀው የአፋብን የምህረት አዋጅ የንብረት ባለቤትነትን ጭምር ያረጋገጠ መሆኑ በርካታ ኃይል ከጠላት እየከዳ ፋኖን እንድቀላቀል ያስችላል የሚል እምነት አለኝ:: ትጥቃችንን ካልነጠቃችሁን እንመጣለን የሚሉት ሁሉ በቂ ምላሽ አግኝተዋል:: ኑ! አብረን ቆመን የጋራ ጠላታችንን እንታገል ከዛ ዉጭ መፍትሄ የለንም ወገኖች 🙏👥
ለአፋብን ደ/አ/ቀ/አሳምነው እዝ ከሰም ፪ኛ ኮር በሥሩ ላሉ ክፍለ ጦሮችና፧ ብርጌዶች የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክ‼️‼️‼️
የኅልውና የማጥፋት ዘመቻ ከታወጀብን ቀን ጀምሮ የአማራ ፋኖ ራሱን ለማሥከበር በዱር በገደሉ በደምና በአጥንት እዬተዋደቃችሁና እዬታገላችሁ ይህንን ሥርዓት ለማፈረካከስና ለመገርሰስ የተሰለፋችሁ የፋኖ አመራሮች፣የፋኖ ሰራዊት፣እንዲሁም የአባት አርበኛና የተከበርከው ውድ የአማራ ህዝብ አሁን ካለው ይልቅ የሚመጣው ይከፋልና ይህ ጭራቅ የሆነ የአገዛዙ የጉሬላ ሰራዊት መንገዱ ላይ የተገኜውን ማንኛውም የአማራ ህዝብ ህፃን፣አዛውን፣ወጠት፣እርጉዝ እንዲሁም ሀይማኖት ጭምር ሳይመርጥ እዬረሸነና እያጠፋ እንዲሁም እያፈሰ ስለሚገኝ የከሰም ኮር የነፃነት ታጋይ የፋኖ አመራሮችም ሆነ ሰራዊት ማንኛውም የታጠቀ ሠራዊት በመጠርነፍና ወደ አንድ እዝ ወይም ካምፕ በማሥገባት መቆጣጠርና ህዝባችንም ካላሥፈላጊ ብዝበዛና እልቂት ማዳንና ግንዛቤ መፍጠር ይኖርብናል።
በዚህም መሠረት በቀጠናችን ፋኖ በተቆጣጠረባቸው ቦታዎች የሰዓት እላፊ ገደብና መሿለኪያ ኮሪደሮች ተዘግተው በንቃትና በጥንቃቄ መጠብቅ አለበት እያልን በዘህም መሰረት የሰዓት እላፊ ገደብ ከምሽቱ 1:00_እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት መንቀሳቀስ የማይቻል ሲሆን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ የሚንቀሳቀስ ማህበረሰብ የተገኜ ከጠላት እኩል የሚታይና መረጃ የሚሰጥ መሆኑን እናሳስባለን‼️‼️‼️
*ጠላት የተቆጣጠረባቸው ቦታዎች*
*በነበልባል ክፍለ ጦር*
1ኛ. አረርቲ ከተማ
2ኛ.አራዳ በር
3ኛ.ቦሎ ጊወርጊሥ
4ኛ.ባልጭ ከተማ
*ሀይለማርያም ማሞ ክፍለ ጦር*
1ኛ.ሾላ ከተማ (01)
2ኛ.ኮረማሽ ከተማ
3ኛ. ቱለፋ ታዳጊ ከተማ
*ቡልጋ ክፍለ ጦር*
1ኛ.መተህ ብላ ከተማ
2ኛ.ምንታምር ቀበሌ
3ኛ.04 ቀበሌ
4ኛ ጊናገር ከተማ
ሲሆኑ ከነዚህ ቦታዎች ውጭ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት ገደብ መጣሉን እናሥታውቃለን‼️‼️‼️
*የከሰም ፪ኛ ኮር ዋና መሪ መቶ አለቃ ይላቅ ብርሃኔ*
"የምህረት አዋጁን የተቀበለው የጥምር ጦሩ ዘመቻ መሪ አብርሃም ታመነ 206ኛ ኮርን ተቀላቀለ"
የካቲት 6/2018 ዓ.ም
===================================
የአፋብን ያስተላለፈውን የምህረት አዋጅ ተከትሎ የአረመኔውን ሰራዊት በማገልገል ህዝባቸውን ሲገድሉ የነበሩት የአገዛዙ ወታደሮች አዋጁን ተቀብለው ትግሉን እየተቀላቀሉ ሲሆን አብርሃም ታመነ የአማኑኤል፣ የደብረ ኤልያስ ፣እና የስናን ወረዳ ጥምር ጦር ዘመቻ መሪ 206ኛ ኮር 34ኛ ክ/ጦርን በዛሬው እለት ተቀላቅሏል።
በተላለፈው ድርጅታዊ አዋጅ መሰረት ግበረ ኃይል በማቋቋም አዋጁን ያለ እንከን ለማስፈፀም ሰፊ እንቅስቃሴ የጀመረው 206ኛ ኮር በስሩ ያሉ ክ/ጦሮችን በማስተባበር የምህረት አዋጁን ተቀብለው ትግሉን የሚቀላቀሉ የአገዛዙን ወታደሮች እየተቀበለ ይገኛል።
ህዝባችሁን ከአረመኔው ጋር በመሆን ስትጨፈጭፉ የነበራችሁ የአገዛዙ ወታደሮችና ካድሬዎች ይህንን የምህረት አዋጅ ተቀብላችሁ ትግሉን እንድትቀላቀሉ በድጋሚ ጥሪ የሚያቀርበው 206ኛ ኮር አስፈላጊውን ትብብርና ልዩ ጥበቃ እንደሚሰጥ በማረጋገጥ ጭምር ነው።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 206ኛ ኮር ህዝብ ግንኙነት
በይፋት ግንባር በተደረገ ተጋድሎ ታዳጊዋ የለን ከተማና ሌሎች አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ገቡ!
በተጋድሎው 22 አየር ወለድ ኮማንዶ አባላት ሲገደሉ፡ በሁለት አይሱዙ ኤፍኤስ አር ተሽከርካሪ ሙሉ ቁስለኛ ኮማንዶዎች ለሕክምና ወደ ሸዋሮቢት ይፋት ሆስፒታል መወሰዳቸውን የመረብ ሚዲያ የጦር ግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።
በውጊያው የቆሰሉ ኮማንዶዎች ብዛት ከንፃር፡ በሆስፒታሉ አልጋ ይዘው እየታከሙ የነበሩ ንፁኋን ታካሚዎች አልጋቸውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸው ታውቋል።
ዐብይ አህመድ ሳይቀር "የባለ ምጡቅ አዕምሮ ባለቤቶች" በሚል የሚያሞካሻቸውና "የመጨረሻ የጥንካሬችን ማሳያ" በሚል የመከላከያ ሰራዊት ተቋም የሚመካባቸው የአየር ወለድ ኮማንዶዎችና የሪፐብሊካን ጋርድ አባላት የሸዋ አፈር ሲሳይ ሆነው እየቀሩ ነው።
+1
አፋብን የምህረት አዋጅ ማወጁን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊቱ እየፈረሰ ፋኖን እየተቀላቀለ ነው!!
ምኒልክ ዕዝ አሳምነው ክ/ጦርን የተቀላቀሉ ናቸው!!
በመጀመሪያው የአፋብን የምህረት አዋጅ የመጀመሪያው ተጠቃሚ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቀለ!!
===============
በዛሬው ዕለት በቀን 05/06/2018 የወጣውን የአፋብን የምህረት አዋጅ መሰረት በማድረግ ደረጀ ዘላለም የተባለ ፍኖተሰላም ከተማ ከመሸገው የጠላት ሀይል ጋር በመሆን አምባገነኑን የብልጽግና ስርዓት ሲያገለግል የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን ተቀላቅሏል።ወጣት ደረጀ፤ አብይ አህመድ ከኤምሬትስ በብድር ያመጣውን ሁለት እግር ክላሸንኮቭ ከእነ ተተኳሹ በመያዝ የወጣ ሲሆን በ109ኛ ኮር አመራሮችና በ77ኛ ክ/ጦር አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
በመጀመሪያው የአፋብን የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ በመሆኑና ልዩ እንደሚያደርገው እና ደስተኛ እንደሆነ ወጣት ደረጀ ተናግሯል።
👉የብልጽግና አመራሮች ቤተሰቦቻቸውንና ልጆቻቸውን ውጭ ሀገር ልከው እያሰተማሩ ሲሆን የድሀውን የኢትዮጵያ ወጣት በሀይል እየታፈነ የስልጣናቸው ማስጠበቂያ የጥይት እራት እያደረጉት እንደሆነ አውቆ ሁሉም አካል የወጣውን የምህረት አዋጅ በመጠቀም ህይወቱን እንዲያተርፍ በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር ህ/ግንኙነት
የካቲት 6/2018ዓ.ም
የአንድ ሥርዓት መዝጊያ እና የሕዝብ ንቃት፦ ከአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ማግስት ምን ይጠብቀናል?
እኛ አማራዎች የታሪክን መዝገብ ስንገልጥ የምንማረው አንድ ትልቅ እውነት አለ፤ እርሱም "ጦርነትን ማንም ሊጀምረው ይችላል፣ ፍጻሜውን ግን ማንም ሊወስነው አይችልም" የሚል ነው።
ዛሬ በሀገራችን ያለው ሁኔታም ይህንኑ እውነት እያሳየን ነው።
1. የታገደው የጦርነት ጉሰማ እና የጊዜያዊ ጸጥታ ተንኮል (የቀሩትን በፋኖ የሚረሸረሹትን ጭነዉ ለምን አላመጡልንም?)
አሁን የሚታየው አንጻራዊ የጦርነት ጉሰማ መቀዝቀዝ ወይም ከወደነሱ መሸነፍ፣ ወታደር ስላለቀ ሳይሆን የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ አዲስ አበባ ላይ በመሆኑ ዓለምን ለማታለል የተደረገ "የዲፕሎማሲያዊ መጋረጃ" ነው። ስብሰባው እንዳለቀ ነገሮች በፍጥነት ሊቀያየሩ ይችላሉ። ኢንተርኔት የመዘጋትና ዳግም የማጥቃት ሙከራዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ከወዲሁ መገመት ስልታዊ ብልህነት ነው።
2. የአማራ ክልል ወደ ሕዝባዊ አስተዳደር የመሸጋገሪያ ሰዓት
አሁን ያሉት ተጨባጭ ሁኔታዎች የሚጠቁሙት የአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ በፋኖ እጅ የሚገባበት ጊዜ መቃረቡን ነው። ይህ ድል ግን ትልቅ ኃላፊነትንም ጭምር ይዞ የሚመጣ ነው። አካባቢው በሕዝባዊ ኃይሉ ቁጥጥር ስር ሲውል፣ ከወታደራዊ ድል በበለጠ "የአስተዳደር ድል" ያስፈልገናል።
3. ተቋማዊ ጥበቃ እና የባለሀብቶች ደህንነት
ሥርዓቶች ይወድቃሉ፣ ሕዝብና ሀገር ግን ይቀጥላሉ።
ስለዚህ፦
የመንግሥት ተቋማት፦ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች እና የመገልገያ ተቋማት የሕዝብ ንብረት እንጂ የገዥው አካል አይደሉም። እነዚህ ተቋማት እንዳይወድሙና እንዳይዘረፉ ሕዝቡ በየቀበሌው ተደራጅቶ ጥበቃ ሊያደርግ ይገባል።
የባለሀብቶች ንብረት፦ የአማራ ባለሀብቶችና ንብረቶቻቸው እኩይ ዓላማ ባላቸው ግለሰቦች እንዳይወሰዱና ትርምስ እንዳይፈጠር ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የግል ንብረት መከበር የሥልጣኔ መጀመሪያ ነው።
4. ለድንገተኛ መፈራረስ ዝግጁ መሆን
በወታደራዊ ድጋፍ ብቻ የቆመው የአብይ አገዛዝ፣ ከታሰበው ጊዜ በፊት ፈጥኖ ቢፈርስ አማራዎች ሀገርን ለማረጋጋትና ወደ ባሰ ትርምስ እንዳንገባ ከወዲሁ በሃሳብ መዘጋጀት አለብን። ታጋዮች እና ምሁራን በዚህ ሽግግር ወቅት ሕዝቡን በመምራትና ስርአት በማስያዝ ረገድ ታሪካዊ ድርሻ አለባቸዉ።
የመጨረሻ መልዕክት፦
ድል የሚረጋገጠው በወታደራዊ የበላይነት ብቻ ሳይሆን፣ ሕዝብን በማረጋጋትና ሀገራዊ ተቋማትን በመጠበቅ ጭምር ነው። የአማራ ልጆች ሆይ! በአስታዋይ ልቦና፣ ለነገዉ ሥርዓት ባለው ድል ከወዲሁ እንዘጋጅ!
አዲስ✍️