es
Feedback
ኢት-መጽሐፍት | ETHIO-BOOKS

ኢት-መጽሐፍት | ETHIO-BOOKS

Ir al canal en Telegram

👉 "የምታነበው መጽሐፍ ለአንተ የሚያስብልህ ሳይሆን አንተ እንድታስብ የሚያደርግ ነው።" ሃርፐር ሊ Fiction (ልቦለድ), History (ታሪክ), Politics (ፖለቲካ), Psychology (ስነልቦና), Biography (ግለ-ታሪክ), Self-help(ራስ አገዝ),& Philosophy(ፍልስፍና) የሀገር ውስጥ & የውጪ ሀገር መጽሐፎችን ያገኛሉ!አስተያየትዎን እዚህ @Desutech_bot ያድርሱን

Mostrar más
2 003
Suscriptores
-124 horas
-137 días
-7830 días
Archivo de publicaciones
Repost from ĐESU ŦECH TIPS
ዩቲዩብ ለምትሰሩ እንዲሁም መስራት ላሰባችሁ አሪፍ አፕ ነው ! ስለ አፑ አጠቃቀም ለመረዳት ከታች ካሉት ሊንኮች በሚመቻችሁ ገብታችሁ እዩት...! Tiktok: https://vm.tiktok.com/ZMkfPdxwe/ Instagram: https://www.instagram.com/reel/DEjvF3mCDM3/?igsh=cXkwbXhiczV5d2hw @Desu_tech_tips @Desu_tech_tips

(አልነጋም!) ፦ አኩኩሉ!.......ነግቷል? ፦አልነጋም!! አኩኩሉ እያልሽ፣ ስሜን ሽህ ብትጠሪ አልነጋም ነው መልሴ፣ ድጋሚ ቁጠሪ እኔ እንደማንም ስባሪ ስላየው፣ ትንሽ ብርሃን ነገር ነግቷል አልልሽም፣ በአኩኩሉ ሃገር ፦አኩኩሉ....ነግቷል? ፦አልነጋም!! የአዕዋፍቱ ዜማ፣ ይነጋል ነው ፍቺው ነግቷል ብለሽ ኋላ፣ ህዝቡን እንዳትፈቺው በጭላንጭል ብርሃን፣ እንዳትስቺ በቃል በጨለማ ወጥቶ፣ ሃገር በጅብ ያልቃል! ¶ አኩኩሉ ስንል ሳይነጋ በድቅድቅ፣ ነግቷል ብለው መልሱን ስንት ጊዜ በሌት'፣ በጅብ አስጨረሱን! ለመፈትለክ ለነፃነት፣ በሩ ባይዘጋም ሞት አለ ከደጁ፣ እረፊ አልነጋም። ¶ ፦አኩኩሉ....ነግቷል? ፦አልነጋም!! ፍንትው ብሎ ቀኑ፣ ሰው ሁሉ ሲያወጋም ድቅድቅ ነው ተይ ለኛ' ገና ነው አልነጋም ኋላ ነግቷል ብዬ፣ ከእቅፌ ብትወጪ የገና ወፍ ነሻ፣ ለት' ለት' አትመጪ። አልነጋም! @et_books1 @et_books1

Repost from N/a
𝚃𝚊𝚙𝚑𝚊 𝙰𝚛𝚜𝚎𝚗𝚊𝚊𝚕 𝕧𝕤 𝚗𝚎𝚠𝚌𝚊𝚜𝚝𝚎𝚕 𝚠𝚊𝚓𝚓𝚒𝚒𝚗 𝚚𝚊𝚋𝚞𝚏 𝚔𝚊𝚕𝚕𝚊𝚝𝚝𝚒𝚒𝚗 𝚍𝚊𝚋𝚊𝚛𝚜𝚞𝚏 𝚚𝚘𝚙𝚑�
𝚃𝚊𝚙𝚑𝚊 𝙰𝚛𝚜𝚎𝚗𝚊𝚊𝚕 𝕧𝕤 𝚗𝚎𝚠𝚌𝚊𝚜𝚝𝚎𝚕 𝚠𝚊𝚓𝚓𝚒𝚒𝚗 𝚚𝚊𝚋𝚞𝚏 𝚔𝚊𝚕𝚕𝚊𝚝𝚝𝚒𝚒𝚗 𝚍𝚊𝚋𝚊𝚛𝚜𝚞𝚏 𝚚𝚘𝚙𝚑𝚒𝚒 𝚡𝚞𝚖𝚞𝚛𝚎𝚎 𝚓𝚒𝚛𝚊 𝚋𝚊𝚔𝚔𝚊 𝕃𝕀𝕍𝔼 𝙹EDHU TUQUUN AKKA NAMA DIRREE JIRUTI NU WAJJIIN DAWWADHA👇👇

ልደተ ክርስቶስ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ! @et_books1 @et_books1
ልደተ ክርስቶስ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ! @et_books1 @et_books1

🔶ጥያቄ ቁጥር 1 ብሩህ አዕምሮ ያላችሁ ፈጠን ብላችሁ መልሷት 1=5 2=10 3=15 4=20 5= ? ቀድሞ ለመለሱ 5 ሰዎች የ ካርድ ሽልማት አለ Request to Join ያድርጉ

Repost from N/a
Oduu gammachiisaa deeggartoota Piriimiyerliigii Ingiliiz 🔥 Chaanaalii haaraan taphoota Piriimiyerliigii Ingiliiz hundaa chaa
Oduu gammachiisaa deeggartoota Piriimiyerliigii Ingiliiz 🔥 Chaanaalii haaraan taphoota Piriimiyerliigii Ingiliiz hundaa chaanaalii bilisaan agarsiisu argameera. Guutuu isaa salphaatti arguuf 👇👇👇

Repost from N/a
⚽️ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል በአዲሱ የውድድር ዘመን ለረጅም ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዡን የሚመራው ቡድን ማነው ? Comment below👇
⚽️ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሷል በአዲሱ የውድድር ዘመን ለረጅም ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዡን የሚመራው ቡድን ማነው ? Comment below👇

Repost from N/a

Waqtiin jijjiraaa amajii banamee Jira odefannoo jijjiraaa kilabaa kamii argachuu Barbaddu 👇
Waqtiin jijjiraaa amajii banamee Jira odefannoo jijjiraaa kilabaa kamii argachuu Barbaddu 👇

Repost from N/a
🌐Online irraan hojii jalqabuu barbadumoo❓ Online teessanii guyyaatti qarshii 2000(kuma lamaa) ol hojjechuun salphaa dha❗️ Ho
🌐Online irraan hojii jalqabuu barbadumoo❓ Online teessanii guyyaatti qarshii 2000(kuma lamaa) ol hojjechuun salphaa dha❗️ Hojii kanas ammuma jalqabaa❗️👇

🔽እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ📊 ከዱባ ወጥ ቀጥሎ ኢቶጲስ ውስጥ የማይወደድ ነገር ቢኖር ትምህርት ነው። አለመማር አንድ ነገር ሁኖ ሳለ የተማሩት ላይ መሳለቅ ደግሞ የሚገርም ነው። 🔽 ትምህርት አያስፈልግም ብለው የሚናገሩ ሰዎች በኩራት የሚያነሷት ነጥብ "የተማሩ ሰዎች የት ደረሱ" የምትለዋ ቀሽም የማሸማቀቂያ ምክንያት ስትሆን፤ የተማሩት የት እንደደረሱ አብረን እንመልከት። ከመሰረታዊ ጥናቶች እንጀምር። ⚠️ 1. ወንጀል በ2021 Institute for Securities Studies (ISS) ባሳተመው ጥናት መሰረት 92.7% ገደማ ከባድ ወንጀሎች የሚፈፀሙት ዩንቨርስቲ ባልቀመሱ ግለሰቦች ሲሆን፤ 6.5% ወንጀሎች ዲግሪ ባላቸው እና ቀሪው 0.8% ብቻ ደግሞ ማስተርስ እና ከዛ በላይ ባላቸው ግለሰቦች የሚፈፀሙ ናቸው ይላል። ይሄ ጥናት ኢቶጲስ ውስጥም የሚሰራ መሆኑን ለማወቅ፤ ስልክ ለመስረቅ ብሎ አንገት በጩቤ የሚወጉትን እና ወጡ ላይ ጨው አበዛሽ ብለው ሚስታቸውን በዘነዘና ከሚገሉት ሰዎች ጀምሮ መመልከት በቂ ነው። እዚህ ጋር የተማረ ሰው ምን አተረፈ ካልክ? "ህሊና" የሚባል ነገር እልሀለሁ። 💵💵 2. ገንዘብ ሌላኛው የተማሩ ልጆች ላይ የመዘባበቻ ነጥብ፤ ስራ እና ገንዘብ የማጣታቸው ጉዳይ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ይሄ የነሱ ድክመት ሳይሆን የሀገሪቱ ድክመት ነው፤ እሱን ትተን ወደ ንግድ እንኳ ብንመለስ፤ ንግድ ላይም የተማረ እና ያልተማረ ሰው ቢሳተፍ የተማረው ሰው የተሻለ successful የመሆን እድል እንዳለው የሚያሳዩ ብዙ ዳታዎች አሉ። 🚩 ለምሳሌ አለማችን ላይ ካሉ ቢሊየነሮች መሀል 71 ፐርሰንቱ ከዩንቨርስቲ ዲግሪ እስከ PhD የጨረሱ ጎበዝ ተማሪዎች ናቸው። Bill Gates ወይም ማርቆስ Zuckerበርግ አይነት በጣም ጥቂት ባለሀብቶች በእርግጥ ከኮሌጅ ት/ት አቁመዋል፤ ነገርግን እነዚህ ግለሰቦች ት/ት ያቆሙት ከ Harvard እና Yale እንጂ ማትሪክ ወድቀው አይደለም። 🚩 ታዲያ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን ሀብታሞቹ ደንቆሮ ሆኑ ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፤ አግባብም ነው። ለዚህ ቀላሉ መልስ "ቁጥር 1ን" ተመልከት ነው፤ የኛ ሀገር ሀብታም በአመዛኙ ደፋር፣ ወንበዴ፣ አጭቤ፣ አምታች ነው። ይሄንን ውንብድና ደፍሮ እንዲሰራ የሚያደርገው ደግሞ አለመማሩ ነው። 🚩 ኢትዮጲስ ውስጥ ለምን generational wealth እንደሌለ ታውቃለህ? አባት ሀብታም ሲሆን ልጆቹን ጥሩ ቦታ ያስተምራል፤ ከዛ ልጆች ህሊና ይኖራቸዋል፤ ከዛ የአባታቸውን የወንበዴ ቢዝነስ ማስቀጠል ይከብዳቸዋል፤ አለቀ። የተማረ ሰው ቁጥር ማነስ ከPolitical Stability፣ ከPoverty Alleviation፣ ከInnovation & ከEntrepreneurship እና አጅግ ብዙ አሁን ላለንበት አዘቅት ምክንያቶች ጋር በብዙ ጥናቶች አስደግፎ ማስረዳት ይቻላል። 🚩 በአጭሩ ት/ት ምን ያደርጋል የሚልህ ነጋዴ ሂሳቡን የሚያሰራው በተማረ Accountant ነው፣ ሲከሰስ ተከራክሮ ንብረቱን የሚያስመልስለት የተማረ ጠበቃ ነው፣ ህንፆውን የሚያስገነባው በተማረ ኢንጂነር ነው፣ ሲያመው የሚሄደው የተማረው ዶክተር ጋር ነው፤ ከዛ አልፎ ልጁን አጥና እያለ የሚጨቀጭቀው እና ፅድት ያለ international school ልኮ የሚያስተምረው ይሄው ራሱ ሰውዬ ነው። እና ምን ልልህ ነው፤ አለመማር አያኮራም⚠️⚠️🟢 እንኳንም ዩንቨርስቲ አልገባሁ አይባልም፤ ነውር ነው። 🚨🚨🚨 በ ናትናኤል አፈወርቅ Natnael Afework ✨

በኢትዮጲያ ውስጥ ከነበሩት ታላቅ መኳንት መካከል የተቀመጠ አንድ ንጉስ ነበር። ይህ ንጉስ ህንድ፣ አረብ አገራት እና ግብፅን ጨምሮ ገዝቷል። እና የሆነ ግዜ ላይ ትልቅ የሚባል ውሸት የሚናገር አንድ ሰው ካለ የግዛቴን ግማሽ እሰጠዋለሁ። ግን ይሄ የሚሆነው ከእኔ ውሸት ከበለጠ ነው ብሎ አወጀ። -በድንገት አንድ እረኛ ወደ እርሱ መጣና እንዲህ አለው፡- “ንጉስ ሆይ ሺህ አመት ንገስ። አባቴ ረጅም ዱላ ነበረው ወደ ሰማይ የሚዘረጋ ከዋክብትን የሚነካ” ንጉሱም፡- “ምን አይነት እንግዳ ነገር ነው። ግን የሆነው ሆኖ የእኔ አያት ደግሞ ከምድር ወደ ከዋክብት የሚያወጣ መሰላል ነበረው።” እረኛው ምንም ሳይይዝ ሄደ። -አንድ ልብስ ሰፊ ወደ ንጉሱ መጣና እንዲህ አለው፡- “ይቅርታ አድርግልኝ ንጉስ ሆይ ስራ በዝቶብኝ ነው የዘገየሁት። ትላንትና አውሎ ንፋስ ሰማይ ላይ ተነስቶ ነበር እና በአንድ ድምፅ አቁም ስለው ቆመ” ንጉሱ፦ “አዎ በደመና እየተራመድኩ አይቼሃለሁ መልካም አድርገሃል።” ልብስ ሰፊውም ምንም ሳያገኝ ሄደ። በድንገት አንድ እብድ ባዶ በርሜል እየገፋ ገባ። ንጉሱም የፈጠነ ውሸት ፈጥሮ እንዲህ አለው፡- “አንተና በርሜሉ የት ሄዳችሁ?” እብዱም መልሶ፦“አንተ ጋር ነዋ እዳ አለብህ ታውቃለህ። ቢሆንም እኔ የእናንተን የውሸት ጨዋታ አልፈልግም። የወርቁን በርሜል እወስድ ዘንድ መጥቻለሁ ስለዚህ ስጠኝ” ንጉሱም፦“የወርቅ በርሜል እዳ አለብኝ?” እብዱም፦ “አዎን” አለ ንጉሱ፦ “አይሆንም ይህ ውሸት ነው!” እብዱ፦ “ይህ ውሸት ከሆነ ግማሽ ግዛትህን ስጠኝ” ንጉሱ ወዲያው እንዲህ ሲል መለሰ፦“አይ አይ ልክ ነህ ይህ እውነት ነው” እብዱ፦ “ይህ እውነት ከሆነ ወርቅ የያዘው በርሜል ስጠኝ” 🤓 @et_books1 @et_books1

''99% የዳይመንድ ምርት የሚገኘው በአፍሪካ ቢሆንም አፍሪካዊያን ግን የሚያብለጨልጩት በቫዝሊን ነው።'' 💎 #ሮበርት_ሙጋቤ