cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Damot News24

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
202
Suscriptores
+124 horas
Sin datos7 días
+430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Photo unavailableShow in Telegram
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባል፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው👇 "ከአገራዊ ምክክር በፊት "እምነት መገንባት" ይቀድማል፤መንግስት በህዝብ ዘንድ አመኔታ አልፈጠረም ብለን እናስባለን፤ ለዚህም ማሳያው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ነው ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የፓርላማ አባሉ ተናግረዋል። በጅምላ የንጹሀን ግድያን ጨምሮ ዘረፋ፣ ውድመት፣ እገታ እና ሌሎችም ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች በአማራ ክልል ተንሰራፍቷል ብለዋል። በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳቢያ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች፤ እንዲሁም ዜጎች በማንነት እየተለዩ እየታሰሩ ነው በማለትም የባልደረባቸውን ክርስቲያን ታደለ ጉዳይ በማንሳት የመንግስትን ሀብት ከምዝበራ የመጠበቅ ሀላፊነትን ወስዶ ሲሰራ የቆየን ሰው ለአንድ ዓመት ገደማ በእስር እየማቀቀ ነው ብለዋል። ከብልጽግና መንግስት ጋር አብረው እየሠሩ የሚገኙ ሰዎችም ስህተት አለ በማለታቸው ታስረዋል፤ ሀብታሙ በላይነህ የተባለው የአብን እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልም ለአራት ወራት የት እንዳለ የማይታወቅ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እንዲሰጡ እንማጸናለን ብለዋል"። #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 #ድል_ለክንደነበልባሉ_ፋኖ💪 27/10/16 ዓ.ም
Mostrar todo...
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባል፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው👇 "ከአገራዊ ምክክር በፊት "እምነት መገንባት" ይቀድማል፤መንግስት በህዝብ ዘንድ አመኔታ አልፈጠረም ብለን እናስባለን፤ ለዚህም ማሳያው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ነው ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የፓርላማ አባሉ ተናግረዋል። በጅምላ የንጹሀን ግድያን ጨምሮ ዘረፋ፣ ውድመት፣ እገታ እና ሌሎችም ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች በአማራ ክልል ተንሰራፍቷል ብለዋል። በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳቢያ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች፤ እንዲሁም ዜጎች በማንነት እየተለዩ እየታሰሩ ነው በማለትም የባልደረባቸውን ክርስቲያን ታደለ ጉዳይ በማንሳት የመንግስትን ሀብት ከምዝበራ የመጠበቅ ሀላፊነትን ወስዶ ሲሰራ የቆየን ሰው ለአንድ ዓመት ገደማ በእስር እየማቀቀ ነው ብለዋል። ከብልጽግና መንግስት ጋር አብረው እየሠሩ የሚገኙ ሰዎችም ስህተት አለ በማለታቸው ታስረዋል፤ ሀብታሙ በላይነህ የተባለው የአብን እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልም ለአራት ወራት የት እንዳለ የማይታወቅ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እንዲሰጡ እንማጸናለን ብለዋል"። #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 #ድል_ለክንደነበልባሉ_ፋኖ💪 27/10/16 ዓ.ም
Mostrar todo...
“በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል” - አቶ አበባው ደሳለው፤ የአብን የፓርላማ አባል በዛሬው የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥያቄ ያቀረቡት 16 የፓርላማ አባላት ሲሆኑ ሁለቱ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮች ናቸው። የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ አባሉ አቶ አበባው ደሳለው፤ መንግስት “የህሊና እስረኞችን ለመፍታት፣ የጅምላ ግድያ እና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማቆም ምን ወስኗል?” ሲሉ ጠይቀዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ኃይሎች ባለፉት 10 ወራት “ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል” ያሉት አቶ አበባው፤ ከጥሰቶቹ ውስጥ “የጅምላ ግድያ” እንደሚገኝበት ተናግረዋል። በበርካታ የአማራ ክልል ከተሞች “ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል” ሲሉ የፓርላማ አባሉ ወንጅለዋል። ለዚህ በማሳያነትም በእርሳቸው ምርጫ ክልል ጅጋ፣ በፍኖተሰላም፣ በመርዓዊ፣ በደብረ ኤልያስ፣ በደብረሲና፣ ጎንደር እና ወሎ ተፈጽመዋል ያሏቸውን ግድያዎች ጠቅሰዋል። ጾታዊ ጥቃት እና ድብደባን ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውንም አቶ አበባው አመልክተዋል። በተለይ በአማራ ተወላጆች ላይ ይፈጸማል ያሉትን “የጅምላ እስር” ጉዳይንም የፓርላማ አባሉ አንስተዋል። አቶ አበባው “ለወራት በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ” ካሏቸው ውስጥ የምክር ቤት አባላት፣ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና አንቂዎች ይገኙበታል። “የምክር ቤት አባላትን ስናነሳ፤ የምክር ቤት አባላችን አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግስት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኖ መንግስትን ከምዝበራ ያዳነ፣ በሰላማዊ ትግልም በእጅጉ የሚያምን ሰው ነው። አንድ አመት ለሚሞላ ጊዜ በእስር እየማቀቀ ነው ያለው” ሲሉ አቶ አበባው የፓርቲያቸውን የፓርላማ ተመራጭ አስታውሰዋል። “ሌሎችም በለውጡ ከእርሶ ጋር አብረው የሰሩ፤ እንደ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፣ ዶ/ር ካሳው ተሻገር እና አቶ ታዬ ደንደአ ያሉም ‘ለውጡ ስህተት ፈጽሟል፤ በትክክለኛው ጎዳና እየሄደ አይደለም’ ብለው ስለሞገቱ ብቻ ለወራት ታስረዋል” ሲሉም የአብን የፓርላማ አባሉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ተናግረዋል። አቶ አበባው የአማራ ክልል ምክር ቤት እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑትን የአቶ ሀብታሙ በላይነህ ጉዳይንም በማንሳት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተማጽኖ አቅርበዋል። የአብን አባሉ አቶ ሀብታሙ “ላለፉት አራት ወራት የት እንደገባ አይታወቅም” ያሉት አቶ አበባው፤ ይህን ጉዳይ ቤተሰቡም እኔም ለተለያየ የመንግስት ኃላፊዎች አቤት ብለናል ምላሽ አላገኘንም። ዛሬ እርሶ ምላሽ ይሰጡናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
Mostrar todo...
በር ዜና በአንቡላንስ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የብልጽግና አመራሮች እንዳሉ ፋኖዎቻችን ቀድሞ መረጃው ደርሷቸው ቦታ ይዘዋል፤ ቀኑ ዛሬ ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ሲሆን ሰዓቱ ደግሞ አመሻሽ 12:30 ነበር። አመራሮቹ በጉጉት ወደሚጠበቁበት ቦታ ደረሱ… ከዛም ያነጣጠሩ የነበልባሎቹ አፈሙዞች የሁለቱን አመራሮች አናት ነደሉ፣ ነዳደሉ። አንዱ አመራር በአዊ ዞን የአዘና ከተማ አስተዳዳሪ አቶ የትነበርህ ሞላ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የከተማው የሎጅስቲክስ ኃላፊ ነበር። አመራሮቹ ብቻውን አልሄዱም ከአጃቢዎቻቸው ጋር እንጅ። ይህንን ትርፍ አንጀት የመቁረጥ ኦፕሬሽን የፈፀመው የጓጉሳ ብርጌድ ቻባችባሳ ሻለቃ ነው። bw
Mostrar todo...
01:31
Video unavailableShow in Telegram
ፋኖ እያረሰው ነው። በአንድ እጁ ሞፈር በሌላ እጁ ነፍጡን ይዞ መሬቱንም የአገዛዙ ሰራዊትንም እያገላበጠው ነው።
Mostrar todo...
Aman.mp416.25 MB
Mostrar todo...
በመንግሥት ውስጥ ያለው አደገኛ የእገታ ቡድን!"የፀጥታ ኃይሉ እየተናደ! እየከዳን ነው"ብልጽግና!3 July 2024

በመንግሥት ውስጥ ያለው አደገኛ የእገታ ቡድን!/"የፀጥታ ኃይሉ እየተናደ! እየከዳን ነው"ብልጽግና/ልዩ ልዩ የኢትዮ ኒውስ መረጃዎች! Ethio News_ኢትዮ ኒውስ ቻናል 2@ethionewschannel2 [email protected]

#ዋብር…‼️ በጎጃም ዋብር ከበባ አደርጋለሁ ብሎ የገባው የኦነግ ብልጽግና አራዊት ሰራዊት በተደረገበት ጥቃት ድባቅ ተመቷል:: በትላንትናው ዕለት ዋብር ዙሪያ ጮቄ አካባቢ ተግተልትሎ የገባው የኦነግ  ብልፅግና መከላከያና የባንዳው ስብስብ በአማራ ፋኖ በጎጃም ከ7 በላይ ብርጌዶች የተወጣጡ የፋኖ አናብስት ሲለበለብ ውሏል:: የአማራ ፋኖ በጎጃም የመዝገቡ ዋለልኝ ብርጌድን ጨምሮ ከተለያዩ የአማራ ፋኖ በጎጃም ብርጌዶች የተወጣጡ ነበልባል ፋኖዎች በተሳተፉበት ውጊያ ከ200 በላይ የኦሮሙማ ጎመን ታጭዶ ሙትና ቁስለኛ ተደርጏል።
Mostrar todo...
ሾልኮ የወጣው ሚስጥራውዊ ደብዳቤ (በኢትዮ 251 ሚዲያ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ "ከአቅሜ በላይ ነው" በማለት ለመከላከያ ዋና ጤና መምሪያ የላከው ሚስጥራዊ ደብዳቤ በኢትዮ 251 ሚዲያ እጅ ላይ ገብቷል። ደብዳቤውን አሾልኮ በማውጣት ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ላደረሱ የውስጥ ምንጮች በአድማጭ ተመልካቾቻችን ሥም ከልብ ማመስገን እያመሰገን መረጃውን ወደማጋለጥ እንገባለን። ደብዳቤው በአስርሺዎች ስለሚቆጠሩ የብልጽግና ሰራዊት ቁስለኞች የጉዳት ሁኔታ በዝርዝር ያሳያል፦ ሚስጥራዊው ደብዳቤው👇 ➽ በአማራ ክልል የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሪፈራል ሆስፒታሎች በብልጽግና ሰራዊት ቁስለኛ መጨናነቃቸውን፤ ➽ ቁስለኛ ባለባቸው ሆስፒታሎች፤ የሆስፒታሎች አልጋ በሙሉ ተይዞ፤ ኮሪደር፤ አዳራሽ፤ ድንኳን፤… ሜዳዎች ላይ ጭምር እየታከሙ እንደሆነ፤ ➽ በቁስለኞች ብዛት የተነሳ ሆስፒታሎች የመድሐኒት በጀታቸው (ስቶክ) ተሟጦ ያለቀ እንደሆነ (ይህንም ደብዳቤው ላይ እንደሚገልጸው ከአቅም በላይ ሆኗል) ይገልጸዋል፤ ➽ ሆስፒታሎቹ በራሳቸው የበጀት ግብዓትና የሰው ኃይል አቅም የሚያደርጉት የህክምና ድጋፍ ከአቅም በላይ እንደሆ፡፡ ➽ ጤና ቢሮው ይህን በክትትልና ድጋፍ ስራው ላይ እንዳረጋገጠ፤ ➽ ለሠራዊቱ ቁስለኞች ሚደረጉ የህክምና ድጋፍ ወጭዎች ከአንድ ዙር (ደብዳቤ ቁጥር አብክመ 13/374 ተጠቅሶ እንደተገለጸው) በጥቅምት ወር ከተላከው የመድሐኒት አቅርቦት ውጭ ምንም ዓይነት ድጋፍ እንዳልተደረገ፤ (በነገራችን ላይ የመድሐኒት አቅርቦቱ ከጤና ሚኒስትር በመከላከያ ትዕዛዝ የሚላክ ነው) ©ኢትዮ 251 ሚዲያ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
"ውሸት ነው" መነን ኃይሌ የጀኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት መነን ኃይሌ አዲስ አበባ ከምትኖርበት ቤቷ ሲቪል በለበሱ ሀይሎች ታፍና መወሰዷን አዳሩን በርካታ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲቀባበሉት አድሯል። ይሁን እንጅ የሸማቂው ኮማንዶ ባለቤት በሰላም ቤቷ የምትገኝ መሆኑን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን ይህ በ ሰፊው ተዛምቶ ያደረው የታፍናለች ወሬ በብልፅግናው ቤት የተፈበረከና ነገ ከነገ ወዲያ አንድ ነገር ብትሆን ማንነታቸው እንዳይታወቅ መሆኑ ተረጋግጧል። ከሰሞኑ የብልፅግናውን ቤት እያመሰ የሚገኘው የጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለቤት ወ/ሮ መነን ሃይሎ ቤቷ እንደምትገኝ ለማረጋገጥ ተችሏል። ሞገሴ ሽፈራው
Mostrar todo...
የብልፅግናው ጦር መሰነጣጠቅ ጀመረ!! የጄኔራሉ ፋኖን መቀላቀል ተከትሎ የስምንት ብርጌድ የልዩ ሃይል አመራሮች ለሊቱን ጠፍተው ማደራቸው ተሰምቷል። በቀድሞው የአማራ ልዩ ሃይል አዛዥ ጄኔራል ተፈራ ማሞ ስር ይተዳደሩ የነበሩና በእርሳቸው ሰልጥነዋል የተባሉት አሁን ላይ በብልፅግናው ቤት በአድማ ብተናና በመከላከያ ስምሪት ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሃይሎች የቀድሞው መሪያቸውንና አሰልጣኛቸውን ፈለግ በመከተል ፋኖን መቀላቀል መጀመራቸው ተሰምቷል። በዚህም በአማራ ፋኖ በጎጃም የአዴት ዙሪያ ቀጠና አድማ ብተናዎች ፣ በደቡብ ጎንደር ፤ በወልዲያ፣ በመርሳ እና በጎንደር ከተማ አካባቢ የነበሩ በርካታ የልዩ ሃይል አባላት መጥፋታቸው ተነግሯል። ከዚህ በተጨማሪ አሁንም በስምሪት ቀጠና ውስጥ የሚገኙ በርካታ የአማራ ተወላጅ ወታደሮችንና የመከላከያ አመራሮች ፋኖ ለመቀላቀል ጊዜና ቦታ እየጠበቁ እንደሚገኙ ለዳሞት ቲቪ በላኩት መልዕክት ለማወቅ ተችሏል። ሞገሴ ሽፈራው
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.