Tнє Cσmpαrαtσr¹
Ir al canal en Telegram
⎛ይህ ቻናል ሙስሊም|ሙእሚን ባልሆኑ አካላት ለሚነሱ ሀይማኖታዊ ጥያቄዎች፤ብሎም በነሱም ላይ ጥያቄ ለማንሳት እና እውነታ ለማስጨበጥ የተከፈተ ነው።⎠
Mostrar más734
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días
Archivo de publicaciones
ገና
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው❲بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيم❳
ذَٰلِكَ قَوْلُهُم بِأَفْوَٰهِهِمْ ۖ يُضَٰهِـُٔونَ قَوْلَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِن قَبْلُ
“ይህ በአፎቻቸው (የሚናገሩት) ቃላቸው ነው፡፡ የእነዚያን ከነሱ በፊት የካዱትን ሰዎች ቃል ያመሳስላሉ፡፡”❲Qūrān 9:30❳
-----------------------------------------------------
▪ገና"γέννα" የሚለው የግሪክ ቃል እንደ ዐውደ-ጽሑፉ የተለያየ ትርጉም ሊኖረው ይችላል። እሱም ገን"γεν-" ከሚለው ሥርወ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም"መወለድ" ወይም "ወደ መኖር መምጣት" ማለት ነው፤ኢየሱስ ወደዚህ ምድር የመጣበትም ቀን ከዚሁ ተጠቃሎ ገና ብለው ይጠሩታል።
▪በእንግሊዘኛው"Christmas" የሚለው ቃል"Cristes mæsse" ከሚል የጥንት እንግሊዝኛ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን"የክርስቶስ ቅዳሴ" ማለት ነው ይህም የክርስቶስን የልደት ቀን ለማወደስ የሚጠቀሙበትን ቀን በዚህ ስም ሰይመውታል።
-----------------------------------------------------
◌ነጥብ አንድ የተወለደበት ወር:
“በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ልጆች ነበረች፥ ስምዋም ኤልሳቤጥ ነበረ።”
— ሉቃስ 1፥5
“እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት።”
— ሉቃስ 1፥9
“የጌታም መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ታየው።”
— ሉቃስ 1፥11
“መልአኩም እንዲህ አለው፦ ዘካርያስ ሆይ፥ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ።”
— ሉቃስ 1፥13
▪የሉቃስ ወንጌል ምዕ.1 ከአብያ ዘር ስለ ነበረው ካህን ዘካርያስ እና መካን ስለ ነበረችው ሚስቱ ኤልሳቤጥ መጥምቁ ዮሐንስን እንደፀነሰች ይናገራል።
“ከዚህም ወራት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰችና፦ ነቀፌታዬን ከሰው መካከል ያስወግድልኝ ዘንድ ጌታ በተመለከተበት ወራት እንዲህ አድርጎልኛል ስትል ራስዋን አምስት ወር ሰወረች።”
— ሉቃስ 1፥24-25
▪ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በኤልሳቤጥ በስድስተኛው ወር እርግዝና ወቅት ገብርኤል ለማርያም ተገለጠለትና ኢየሱስን እንደምትፀነስ እንደነገራት ያስነብበናል።
“እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።”
— ሉቃስ 1፥31
▪ከዘካርያስ ክህነት እስከ ኢየሱስ ልደት ያለውን ጊዜ ግምት ውስጥ በማስገባት ኢየሱስ የሚወለድበትን ግምታዊ ወር ማወቅ ይቻላል።ይህም በአይሁድ ወግ ውስጥ ያሉ ካህናት ዓመቱን ሙሉ በቤተመቅደስ ውስጥ በሚያገለግሉ በ24 ምድብ ተደራጅተዋል። ዘካርያስ በ10ኛው ሳምንት የዑደታቸው ጊዜ ያገለገለው አብያ የሚባል ስምንተኛው ምድብ ነበር።
“ሰባተኛው ለአቆስ፥ ስምንተኛው ለአብያ፥”
— 1 ዜና 24፥10
▪ዘካርያስ መልአኩን ያየው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ሲሆን ይህ በወር ውስጥ 2 ጊዜ በሚደረግ የአይሁድ ወግ ነበር ይህም"ስምንተኛው አብያ" የተሰኘው ምድብ አራተኛው የአይሁድ ወር ማለትም ታሙዝ"תַּמּוּז" እንደሚውል ያስገነዝበናል ሆኖም በግሪጎሪያን አቆጣጠር ሐምሌ ላይ ይውላል ይህም መልአኩ ዘካርያስ ጋር ከመጣ በ6ኛ ወር መምጣቱ የኢየሱስን ፅንስ ጅማሬ ከጥር ያደርገዋል፦
“በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥”
— ሉቃስ 1፥26
▪ከጥር ጀምሮ ባለው የ9 ወር የእርግዝና ቆጠራ ስሌት የኢየሱስ መወለድ በጥቅምት መሆኑን እንገነዘባለን ይህም የሀገራችን የታህሳስ 29/28 የአውሮፓውያን December 25 የአርመንያ ኦርቶዶክስ ጥር 6 በእንቶ ፈንቶ የተሞላ መሆኑን ያስይዘናል!
“በጥንቷ ሮም ታኅሣሥ 25 የረዥም ቀናት መመለሻን የሚያመለክት የማትበገር ፀሐይ በዓል ነበር።ሰዎች የሚበሉበት እና ስጦታ የሚለዋወጡበትን ሳተርናሊያን ተከትሎ ነበር።”[¹]
-----------------------------------------------------
◌ነጥብ ሁለት የተወለደበት አመት:
¦1¦የሄሮድስ ዘመን:
“ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥...”
— ማቴዎስ 2፥1
በዘመኑ የቀን አቆጣጠር፦
▪AD:AD"Anno Domini" በላቲን "የጌታችን ዓመት" ማለት ነው።በጎርጎሪዮሳዊው የዘመን አቆጣጠር የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት ዓመት የሚገመቱትን ዓመታት ለመለየት ይጠቀሙበታል።
▪BC፡ BC"Before Christ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት ያለውን ጊዜ ያመለክታል።በጎርጎርዮስ አቆጣጠር ከ 1 ዓ.ም በፊት ያሉትን ዓመታት ለመለየት ይጠቅማል።
▪አብዛኞቹ የዘርፉ ምሁራን ታላቁ ሄሮድስ የኖረው ከ72-4 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደሆነ ይናገራሉ፦
“ታላቁ ሄሮድስ(ከ72-4 ክ/ል/በፊት)ሮማዊ አይሁድ የይሁዳ መንግስት ንጉስ ነበር።”❲Perowne 2003, pp. 92–93❳
▪ማቴዎስ የተወሰነ ቀን ባይናገርም ይህ ክፍል ግን ኢየሱስ የተወለደው በታላቁ ንጉሥ ሄሮድስ የግዛት ዘመን እንደሆነ ያመለክታል።ከታሪክ አኳያ ታላቁ ሄሮድስ ከ37 እስከ 4BC እንደገዛ ይታመናል።በዚህ መረጃ ላይ በመመስረት በአጠቃላይ ኢየሱስ የተወለደው በ4BC አካባቢ እንደሆነ ይታመን የነበረው ታላቁ ሄሮድስ ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ እንደተወለደ በማስረዳት ነው ሆኖም ክርስቶስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ4BC ተወለደ እያሉን ነው!
¦2¦የቄሳር አውግስጦስ ቆጠራ:
▪የሉቃስ ድርሰት የኢየሱስን ውልደት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ በወጣበት ጊዜ ጋር በማያያዝ የማርያምን እና የዮሴፍን ወደ ቤተልሔም መጓዝ ለማጣመር ሞክሯል፦
“በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች።”
— ሉቃስ 2፥1
▪ታሪክ"Census Of Quirinius" ተብሎ የሚታወቀው ቆጠራ 6-7AD እንደሆነ ያስረዳል።[²]ይህም ክርስቶስ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ6AD ተወለደ የሚል ከማቴዎስ የባሰ ውዝግብን በመፍጠሩ በተጨማሪም ሉቃስ በሰራቸው የታሪክ ብልሽቶች ምሁራን የሉቃስ ዘገባ ስህተት መሆኑን መስክረዋል!
-----------------------------------------------------
ዋቢ ይመልከቱ:
[¹] https://www.britannica.com/question/Does-Christmas-have-pagan-roots
[²] https://www.britannica.com/topic/biblical-literature/The-life-of-Jesus
-----------------------------------------------------
ወሰላሙ አለይኩም
©ከወንድም አህመድ(አነፃፃሪው)
t.me/TheComparator
“እነሆ፥ እኔ ካጠፋኋቸው አሕዛብ ሁሉ ጋር ከዮርዳኖስ ጀምሮ በፀሐይ መግቢያ እስካለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነገዶቻችሁ ርስት እንዲሆኑ የቀሩትን እነዚህን አሕዛብ በዕጣ ከፈልሁላችሁ።”
— ኢያሱ 23፥4
