cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍቅርን በግጥም ❤️

እዚህ ቻናል ላይ ፍቅር በግጥም እንገልፃለን እናስረዳለን እንገልፃለን ይህንን ቻናል ለምትወዷቸው ሰዎች ሼር በማድረግ ይህ ቻናል ለብዙሀኑ እንዲደርስ ማድረግ ትችላላችሁ On this channel, we express love through poetry. By sharing this channel with your loved ones, you can make this channel reach the masses.

Mostrar más
Etiopía13 525Amárico9 421La categoría no está especificada
Publicaciones publicitarias
200
Suscriptores
Sin datos24 horas
+27 días
-130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ላንተ ከተፃፈው 1ኛው    ........✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍ . . .የፃፍኩልክ ላንተ  .... ቢሆንም ባይሆንም .... ፍቅርን መጠርጠር .... መቼም አያቅትም .... መፈቀርክን ማመን ... ቢከብድም ቢቀልም... መውደድን ማሰብ... ለክፉ አይጥልም .... ሁሌ እንደማስብክ... ብታውቅም ባታውቅም..... ላንተ ያለኝን ነገር ..... መጠርጠር አይጎዳም .... እኔን ለመቀበል .... ብቶድም ብትጠላም.... ከኔጋር መሆንን እግዜሩ አይፈቅደውም.........
Mostrar todo...
05:43
Video unavailableShow in Telegram
Downloaded via: @downloader_tiktok_bot
Mostrar todo...
#ግማሽ ጨረቃ ከጨረቃ በታች..... ወጥነት የሳተ ብጥስጣሽ ደመና አርጅቶ እንዳፈጀ አሮጌ ጎዳና የሻገተ ነገር ጊዜው ያለፈበት ያለማማር ወጉ ውበት ያልሻረበት..... ከሱ ማዶ አጀብ እዛ እና እዚህ ኮከብ ማየት ሲያደካክም ያንቺን ነገር ማሰብ። የሌለሽን አንቺ በፍለጋ ሂሳብ ከሩቅ እንደ መሳብ ማውጣት፣ ማውረድ ለጉድ ከጊዜ መካለብ፣ በሰኞ እና በእሁድ። ላልበጠስ ውጥር ፣ ላይለይልኝ ነገር ብዳከር ለዘመን አይቀየር፣ አይሻር ብደበቅ ከማመን ግማሽ ጨረቃ ነው ትዝታሽ በተመን። የተሳነው መሙላት፣ ያልሆነለት መጉደል ጎኑን የደፈረው የጨለማ ገደል መራቅ ያላጠፋው መቅረብ የመሰለ ልዳብሰው ስሻ እንደመሄድ ያለ የቀረበኝ ስለው የራቀኝ ከዘመን ግማሽ ጨረቃ ነው ትዝታሽ ሲተመን
Mostrar todo...
00:36
Video unavailableShow in Telegram
00:20
Video unavailableShow in Telegram
                
ለእናትዬ  👩‍🍼
  በአርምሞ ሆኜ ተፈጥሮሽን ሳሰላስል የኑሮሽን ክታብ መዝገብሽን ስቆነፅል ለማኖር መሞትን ከግብርሽ ስቀፅል ልገልጽሽ ሻትኩና ልጮህ ላነበንብ ግብርሽን ሚከስት ቃላት ልሰበስብ እውቀቴን አሰሳ ምናቤን ጋልቤ ሀረጋት ሳዋቅር ከቃላት መዝገቤ ይገልጹሻል ብዬ ያሰብኳቸው ቃላት መግለጽ ተሳናቸው የእድሜዬን ብድራት።                ውለታሽን በቃል በፊደል ልፈትል                ስለ ክብርሽ ልጽፍ ሙሉ የግጥም መድብል                በሆሄ ውቂያኖስ ምናቤን ላሰጥም                ቃላት ገጣጥሜ ግጥምን ልገጥም                ሀረግ ላረገርግ በቃል አለም ላርግ                ለውለታሽ አቻ በቃል ላደገድግ                ቃል እየዘራሁኝ ስሜትን ላሰክር                ለውለታሽ ዝክር ስንኝ ልሰድር                እማ ያንቺን ዉለታ በቃል ልመዘብር                ከቶ በምን ይሆን ልቤ የተመካ                በምን ሚዛን ይሆን ፍቅርሽን የለካ? ይቅር በዪኝ እማ ይቅር በዪኝ ይቅር ስላንቺ ልናገር ያደረግሽልኝን በቃላት ልዘክር ውለታሽን ላውጅ ለኔ ስለሆንሽው ሆሄ ላመሰጥር አስቤ ነበረ ለውለታሽ ምላሽ ላበረክት መባ ስለኔ የሆንሽውን በሆሄ ላሰፍር በቃል ላስተጋባ አስቤ ነበረ በአቡጊዳ ቀመር ፍቅርሽን ላሰላ፣ ተዘነጋኝ እንጂ የሆሄው ውሀልክ የፊደል ቅጸላ። ግን ግን ምን ልገልጽሽ ብሻ ልጽፍሽ ብመኝም አንቺን የሚገልጹ ቃላቶች የሉኝም። ሞልተው የሚተርፉ እልፍ ቃሎች ባውቅም የፍቅርሽን ያክል ጠልቀው አልተገኙም ከፍቅረሽ ትርጉም ጋር አይስተካከሉም።        እንደ ቅዱስ ያሬድ ጥኡም አንደበቱ        ዜማ እንዳወረሱት ስሉስ አዋፋቱ        እስኪገለጽልኝ የቃል አቡሻህር የፊደል እትብቱ        ጥቂቷን ቆንጥሬ በየውጣ እስካውቀው ቅኔን ከነስልቱ        ይቅርብኝ መናገር ስላንቺ ማውራቱ        ግፍ ከሚሆንብኝ የዕድሜሽን ሁዳዴ በቃላት መግደፉ         ይቅርብኝ ልከልከል አንቺን ከመጻፉ         አንደበቴ እስኪያድብ ከመጎላደፉ።                         አፈር ዘዱዳሌብ                          ናዝሬት
Mostrar todo...
00:12
Video unavailableShow in Telegram
😔😔
Mostrar todo...
ሲከፋህ ቀን ጠብቅ                                      መቼም በዚች ምድር መኖር ስትጀምር... አለ ብዙ ጉዳይ አለ ብዙ ነገር አንደ ስትደሰት አንደ ስትቸገር አንደ ስትከፋ ሌላ ጊዜ ስትስቅ፣ ስንት አለ ሚያስደንቅ፤ ደግሞ በስተጀርባ፦ እልፍ ጉዳይ አለ አንተን የሚያስጨንቅ፤ እናም ወዳጄ ሆይ... መልካሙን ግለጠው መጥፎውን ግን ደብቅ ሲደላህ ተደሰት ሲከፋህ ቀን ጠብቅ።
Mostrar todo...
1
00:21
Video unavailableShow in Telegram
ከዳት አትበሉኝ ይኸው  ትላንትና ከትላንትናም በስቲያ ያዩኝ ሠዎች ሁሉ ከእቅፌ ጉያ ፍቅራችንን አይተው አይለያችው ያሉን እንኳን ሠው ንፋስ የቀናብን እስክንመስል ያኔ በፍቅራችን  የተገረሙብን ዛሬ በያኔው በፍቅር መንገዳችን በፍቅር ጎጃችን ብቻሺን ሲያዩሽ እጅግ አዝነውልሽ🥺 ያ ክፉ ከድቶታል ብለው ከንፈር  መጠውልሽ ስሜን ጥለውብሽ😕 ይህው በመንገድ ላይ እንደ እብድ  አስለፈለፋት ይህው  አንገቷን  አስደፋት😏 እንዲህ ሊጎዳት እንዲ ሊከዳት  ለምን ቀረባት እያሉ ሲከሡኝ😔 መከሰሡን ይክሰሡኝ  ብቻ እንዳይፈርዱብኝ ጠበቃዬ  ሆነሽ ተከራከሪልኝ  እሱ አይደለም እኔ ነኝ በያቸው💔 ሲያምነኝ ከዳውት ሲቀርበኝ የራኩት እኔ ነኝ ልቡን የሠበርኩት ቃሌን ያጠፍኩበት ቅስሙን ሠባብሬ ሽባ ያደረኩት☹️ ሀጥያቴ በዝቶ ነው ብቻዬን ማውራቴ አትበሉት ከዳት አትዘኑ ለኔ እሱን  አላያቹሁት😒
Mostrar todo...