cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Football First

➲ ሁሉንም አይነት እግርኳሳዊ ትንተና እና ፅሁፎች የሚያገኙበት ቻናል ነው። Football First | በ የካቲት 2016 የተመሰረተ !

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
6 663
Suscriptores
-924 horas
-1117 días
+64230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

01:31
Video unavailableShow in Telegram
የጨዋታውን ሃይላይት ጋበዝናችሁ 🙌🏽 @Football_First_1
Mostrar todo...
ZIDANE_S_SECOND_TRIUMPH_UCL_2017_FINAL_HIGHLIGHTS_XrKBZS_IWoQ_135.mp48.39 MB
👍 8
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ሪያል ማድሪድ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ከጣሊያኑ ጁቬንቱስ ጋር ቀንድ ለቀንድ በመነካከስ በካርዲፍ ከሚገኘው የዌልስ ብሔራዊ ቡድን ስታዲየም ውስጥ በቀጥታ ሲጫወቱ ማየት እና እንደዚያ ባለ ያልተለመደ ትዕይንት ማምሸት እውነቱን ለማናገር ያለ ጥርጥር ለማድሪድ እና ሮናልዶ ደጋፊዎች ከ La Decima እና Duo Decima ጋር የሚስተካከል ምሽት መሆኑን ክርስቲያኖ ሮናልዶ አሳይቶናል። የዕለቱ ጀርመናዊው አልቢትር ፌሊክስ ብሪች ጨዋታው መጀመሩ በፊሽካቸው አበሰሩ ፤ ጁቬንቱስ ጨዋታውን በተለመደው የጋለ ስሜት የጀመረ ሲሆን የቀድሞው የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ጎንዛሎ ሂጉዌን በኬይለር ናቫስ የግብ ክልል ላይ የማያቋርጥ ስጋት መፍጠሩን ተያይዞታል። አሮጊቶቹ በማሲሚላኖ አሌግሪ እየተመሩ ለሶስተኛ የውድድር አመት ቆይታ ቀድመው ጎል ለማስቆጠር በመሞከር እና መሪነታቸውን ለመጠበቅ በሚል ታክቲክ ሲጫወቱ ቆይተዋል። ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ጎል ለማግባት የግድ ከሁለቱ በአንዱ አጋማሽ ሙሉ ለሙሉ የማጥቃት እቅድ እና ታክቲክ አቅንበው ነበር የገቡት። ሪያል ማድሪድ ይህን ከአሮጊቶቹ የመጣውን ማዕበል ለመቋቋም ሊታወቅበት ከሚችለው የመልሶ ማጥቃት ሽግግር በ20ኛው ደቂቃ ከስፓንያርዳዊው ኢንተርናሽናል ተከላካይ ግሩም የሆነ ኳስ ወደ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተሻገረ ይህም በጁቬ የፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ የተገኘ ሲሆን ፤ ጂጂ ቡፎንን በሁለቱ ቋሚ ብረት መሀል አቁሞ በግራው የመሬት ክልል ቀለል ያለች ኳስ በመምታት አስቆጠረው። ቢሆንም ግን አሮጊቶቹ በአንዴ ተስፋ አልቆረጡም ነበር ፤ ይልቁንስ በረጃጅም የኳስ ቅብብል በማሪዮ ማንዙኪች ውብ ጎልን ከመረብ አሰፈሩ እንጂ ፤ ኳሷ ከራሳቸው የግብ ክልል በመነሳት በረጅም ኳስ አሌክስ ሳንድሮ ጋር ደረሰች አሌክስ ሳንድሮ ያገኘውን እድል በፍጥነት የፍፁም ቅጣት ምት ውስጥ ላለው ለቀድሞ የሎስ ብላንካዎቹ ኮከብ ሂጉዌን አሻገረለት ፤ ሂጉዌን ኳሱን በደረቱ አሳርፎ ለማንዙኪች አቀበለው ፣ ማንዙኪችም በተራው በደረቱ አረጋግቶ የናቫስን ትንፋሽ በሚያቆራርጥ ደረጃ ግሩም የመቀስ ምትን አስቆጠረ። ሁለተኛው አጋማሽ ሪያል ማድሪድ በአዲስ ጉልበት ወደ ሜዳ የገባበት ጊዜ ነበር። አሰልጣኙ ዚነዲን ዚዳን መሪነቱን ከወሰደ በኋላ በፍጥነት ጎል በማስተናገዱ ምክንያት በነበረችው የ15 ደቂቃ የእረፍት ጊዜ ሙሉ ፀጉር ሊያራግፍ የሚችል ቁጣ እንደተቆጣቸው ምንም ጥርጥር የለውም። ሎስ ብላንኮዎቹ ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥረው ጎል የሚያገኙበትን እድል ፍለጋ ላይ ይገኛሉ ፤ አሮጊቶቹ ማዕበል ላይ ማዕበል እየተጨመረባቸው ስለሆነ ኳስ ራሱ በቅጡ ለመያዝ አልቻሉም ፤ የማጥቃት ማዕበሉን ተከትሎ ከትንሽ ቆይታዎች በኋላ ሞገዱ ሊከፈት ይቃጣዋል። እስከ መጨረሻዋ ሰአት ድረስ ንክኪውን ለማግኘት እየታገሉም ይገኛሉ። አሁን ግን ተንኳክቶ ተንኳክቶ በሩን የመበርገጃ ሰአት ደርሷል ፤ ካሪም ቤንዜማ አታሎ ለቶኒ ክሩስ የሰጠውን ኳስ ቶኒ ቢሞክረውም የአሮጊቷ ተከላካይ ባርዛግሊ ኳሱ ሲያፀዳው ብራዚላዊው ነውጠኛ ካርሎስ ኤንሪኬ ካሴሚሮ ከርቀት ፍፁም ጎል አስቆጠረ ፤ ይቺ ኳስ ካርዲፍ ከተማን በአንድ እግሯ አቆመች ስቴድየሙ በደስታ ንረት እንዲቀወጥ መንስኤ ሆነች። አሁን ሪያል ማድሪድ 2-1 በሆነ ውጤት መምራት ጀመረ። ከሶስት ደቂቃ በኋላ ሞድሪች የሀገሩ ልጅ የሆነውን ማንዙኪችን ሮጦ በማለፍ ወደ መጨረሻው 3 አካባቢ ሆኖ ከመስመሩ ጫፍ ለሮናልዶ አመቻችቶ በእርጋታ አቀበለው ክሪስ በጂጂ ቡፎን አቅራቢያ ኳሱን ከጁቬው ስድስት ያርድ ሳጥን ውስጥ በመሆን ነቀነቀው። CR7 አሁን በሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረ ሲሆን ሪያል ማድሪድ 3-1 በሆነ ውጤት ጨዋታውን እየመራ ዋንጫ ማንሳቱን እርግጠኛ ሆነ። የሻምፒዮንስ ሊጉን ምሽት ይበልጥ ያሳመረ ከብራዚላዊ ተከላካይ የተሻገረለትን ኳስ ማርኮ አሴንሲዮ ወደ ጎል ቀየረ የጨዋታው ውጤት መግለጫም ወደ 4-1 ተለወጠ። ከትንሽ ቆይታዎች በኋላ ጨዋታውን ሲመሩት የነበሩት የእለቱ አልቢትር ፌሊክስ ጨዋታው መጠናቀቁን አበሰሩ። ይህ ብዙ ሰው ያላወራለት ከሁለቱ የዴሲማ ምሽቶች ጋር የሚስተካከል ፤ የሪያል ማድሪድ እና የክርስቲያኖ ሮናልዶ ጀብድ የተፈፀመበት የሀያሉ ክለብ የ12ኛው የሻምፒዮንስ ሊግ ድል ምሽት ነው። @Football_First_1
Mostrar todo...
6👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ሪያል ማድሪድ በ1955/56 የውድድር ዘመን የመጀመሪያውን የአውሮፓ ዋንጫን ካሸነፈ በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ላይ የሰጠው የማይናወጥ ትኩረት የክለቡ መለያ ባህሪ ሆኖ ዘልቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲያ በሻምፒዮንስ ሊጉ ውድድር ካስመዘገቡት ስኬት ውስጥ ቁልፉን ሚና የተጫወተ የፊልሙ መሪ ተዋናይ ነበር ፤ እሱን በአጭሩ መግለፅ ከተፈለገም የአሸናፊነት አባዜ እና ሱስ የነበረበት ሪያል ማድሪድ ለነበሩት ስኬት ሁሉ ቁጥር አንድ ምክንያት የነበረ ፤ መጠርያ ስሙ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሚባል ሰው ነበር። ሻምፒየንስ ሊግ በአውሮፓ ኃያላን እና ታዋቂ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚደረግ የመጨረሻ እና የበላይነት ማረጋገጫ የሆነ ፈተና እንደሆነ በሁሉም እግር ኳስ ተመልካች ዘንድ ይታወቃል። የፖርቹጋላዊው ዓለም አቀፍ የድል ረሃብ ያለበት ፤ የአውሮፓ እግር ኳስን እጅግ ተወዳጅ ያደረገው ፤ የአውሮፓ እግር ኳስ ያለእሱ ባዶ ይሆናል ብለን እንድንሰጋ ያረገን ፤ የተጫወተባቸውን ውድድሮች የማሸነፍ ፍላጎት ያለው ሮናልዶ ከዚህ የሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ጋር ዝምድና አለው እስኪባል ድረስ ብቃቱን ያሳየውን ሰው ዛሬ በክለባችን ካደረጋቸው ከ5 ምርጥ ጨዋታዎቹ ውስጥ አንዱን በፅሁፍ መልክ ከቆይታዎች በኋላ እጋብዛቹሀለው አብራቹን ሁኑ። @Football_First_1
Mostrar todo...
6👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
🔴🚨: ሜሰን ግሪንውድ ከ ጁቬንቱስ ጋር ከፍተኛ ስምንንት ላይ ደርሰዋል:: 30m+addons እና 25% የሚቀጥለው ሽያጭ እንዲሁም መልሶ የመግዛት አንቀፅ ተካቶበታል:: ግሪንውድ በዝውውር ላይ ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት አለው:: [MAN UNITED FOREVER] Share||@ADONAY_ETHIOFOOTBALL
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
•|| ሰላም ውድ የ football 1st ቤተሰቦች ! የተወሰኑ አድሚኖችን ወደ ቻናሉ ለመቀላቀል የወሰንን ሲሆን ጊዜ ያለው እና ከኛ ጋር ቀጣይነት ያለው ስራ መስራት የሚፈልግ ሰው በአድሚንነት ለመቀላቀል አስበናል። ~ የቻናሉ content ለኔ ምቹ ነው እና መስራት እችላለው የሚል ሰው በ @hafiz_go በኩል ያናግረን።
Mostrar todo...
👍 4👎 1
Photo unavailableShow in Telegram
ለወትሮው 8 ሰአት ላይ ይቀርብ የነበረው የVOICE CHAT ፕሮግራም ዛሬ ትንሽ ችግር ስለገጠመን ወደ 9 ሰአት አሸገግረነወል ። በተለመደው ሰአት ባለመገኘታችን ይቅርታ እየጠየቅን 🙏 9 ሰአት ላይ በመገኛት ሁሌም በየ ሰምንቱ እንደምተረጉት ሃሳቦቹን እደተከፍሉን አይቀርም ።
Mostrar todo...
👍 8 1
Photo unavailableShow in Telegram
Voice chat !  ዛሬ 8:00 ላይ ከ Football First ጋር!! => አዲሱ የአሰልጣኞች ትውልድ !! #ቲየጎ ሞታ 👉 ጁቬንቱስ #ቬሰንት ኮምፓኒ 👉 ባየር ሙኒክ #ኢንዞ  ማሪስካ 👉 ቼልሲ #ኬረን ማኬና 👉 እስፒች Tow አብዛኞቹ  በአዲስ ሀላፊነት ኮምፓኒ ፣ ኤንዞ ማሪስካ ፣ ቲየጎ ሞታ ያሉት በአዲስ ክለብ በሌላ ስራ እንደ ማኬና ያሉት ደሞ በዛው ክለባቸው ቆይተው ቀጣዩን የውድድር ዘመን ይጠብቀሉ እና የትኛው ይሳካለታል ?    => የቆያው የቴን ሀግ የውድድር  ዘመን ግምገማ !! እርሶ ቦታው ላይ ቢሆኑ ምን ይወስናሉ ? =>ፖግባን ያጣነው ይመስላል። ጥቁሩን አልማዝ ከዚህ በኋለ ሜዳ ላይ እናየዋለን ብላችው ታስበላችው?? => ሁሉንም ያሰካው REAL MADRID ምባፔን እና ኤንድሪክን ጨምሮ !! በእነዚህ ርዕሶች ዙሪያ ያላችሁን ሀሳብ እና አስተያየት  VOICE CHAT ፕርግራም ላይ በመገኛት ያካፍሉ !!        @Football_First_1
Mostrar todo...
😱 6👍 3💯 1
Photo unavailableShow in Telegram
Voice chat !  ዛሬ 8:00 ላይ ከ                                           Football First ጋር!! => አዲሱ የአሰልጣኞች ትውልድ !! #ቲየጎ ሞታ 👉 ጁቬንቱስ #ቬሰንት ኮምፓኒ 👉 ባየር ሙኒክ #ኢንዞ  ማሪስካ 👉 ቼልሲ #ኬረን ማኬና 👉 እስፒች Tow አብዛኞቹ  በአዲስ ሀላፊነት ኮምፓኒ ፣ ኤንዞ ማሪስካ ፣ ቲየጎ ሞታ ያሉት በአዲስ ክለብ በሌላ ስራ እንደ ማኬና ያሉት ደሞ በዛው ክለባቸው ቆይተው ቀጣዩን የውድድር ዘመን ይጠብቀሉ እና የትኛው ይሳካለታል ?    => የቆያው የቴን ሀግ የውድድር  ዘመን ግምገማ !! እርሶ ቦታው ላይ ቢሆኑ ምን ይወስናሉ ? =>ፖግባን ያጣነው ይመስላል። ጥቁሩን አልማዝ ከዚህ በኋለ ሜዳ ላይ እናየዋለን ብላችው ታስበላችው?? => ሁሉንም የሰካው REAL MADRID ምባፔን እና ኤንድሪክን ጨምሮ !! => በትንሹ ወደ ሀገራችን ዞር እንልና ሀሙስ የተደረገው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ!!    የጨዋታ ውጤት!! ጊኒ ቢሳው 0 እና ኢትዮጵያ 0 የአፍሪካ ዋንጫ መስረችዋ CAFን በብዙ የቀየሩት ፕረዚዳንት ይድነቃቸው ተሰማ ሀገር እንዴት የአለም ዋንጫ አንዴ እንኳን መግባት አቃታት ችግሩ ምንድነው ብለው ያስባሉ ? በእነዚህ ርዕሶች ዙሪያ ያላችሁን ሀሳብ እና አስተያየት  VOICE CHAT ፕርግራም ላይ በመገኛት ያካፍሉ !!        @Football_First_1
Mostrar todo...
#Part4 በዛሬዉ የ Behind The Scenes ፕሮግራማችን የ 2018ቱን የማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊግ ጉዞ የመጨረሻዉን ክፍል ወይም ክፍል አራትን የምናስቃኛቹ ይሆናል አብራቹን ቆዩ። ስቶንስ እንደ ሜንዲ ሁላ የእግር ጉዳት አስተናግዷል እናም የህክምና እርዳታ እየተረገለት ይገኛል። ማንችስተር ሲቲ ቁልፍ ጨዋታዎችን እንዲያሸንፍ ራሂም ስተርሊንግ ዋነኛዉን ሚና ተወጣ። ስተሪሊንግ ለሲቲ ለተከታታይ 3 ጨዋታ ከ80ኛዉ ደቂቃ በኋላ 3 ጎሎችን አስቆጥሮ ለሲቲ የቁርጥ ቀን ልጅ መሆኑን ተያይዞበታል። ማንችስተር ሲቲ ጨዋታዎችን ማሸነፉን ቀጠለ ተቀናቃኙን ማንችስተር ዩናይትድን ከሜዳዉ ዉጪ ገጥሞ ድል መቀዳጀትም ቻለ። ሊጉ ሊጠናቀቅ 6 ጨዋታ ብቻ ቀርቷል ሲቲ ከተከታዩ ማንችስተር ዩናይትድ በ 11 ነጥብ በልጦ አንደኛ ደረጃን ይዟል ሲቲ ከቶትነሀም ከሜዳዉ ዉጪ ይጫወታል እናም በ 25 ደቂቃ ሁለት ጎሎችን አስቆጥረዉ ቶትነሀምን መምራት ቻሉ ከዛ ግን 42ተኛዉ ደቂቃ ላይ ቶትነሀም በኤሪክሰን አማካኝነት ጎል አስቆጥረዉ በድቅድቅ ጨለማ ጭላጭል ተስፋን ማሳየት ቻሉ ሲቲ ግን በራሂም ስተርሊንግ ድንቅ ጎል አማካኝነት ግብ አስቆጥረዉ ቶትነሀምን 3-1 ማሸነፍ ቻሉ። ፔፕ ወንበር ተደግፎ በዚ አመት በፕሪሚየር ሊጉ በታሪክ ብዙ ነጥብ የሰበሰበ ቡድን መሆን አለብን 100 ነጥብ ደርሰን የአለማችንን ትልቁን ፕሪሚየር ሊግ ማሸነፍ አለብን ይላል። ተጫዋቾቹ ፊት ላይ መነሳሳት ይታያል ፔፕ እንደምናሳካዉ እርግጠኛ ነኝ ብሎ አጨብጭቦ ተለያቸዉ። ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ማሸነፉን ካረጋገጠ ሰንበትበት ብሏል እናም ይህ የመጨረሻ የሊግ ጨዋታቸዉ ነዉ። ሲቲ ከሳዉዝሀምፕተን ጋር በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ እናም ጨዋታዉ ተጀመረ። ሲቲ ይሄንን ጨዋታ ባለፉት 57 አመታት ታይቶ የማይታወቅ ሪከርድ ይሰብራል ይሄም 32 ጨዋታዎችን በሊጉ አንድ የዉድድር አመት ማሸነፍ ነዉ። ከሱ በተጨማሪ 100 ነጥብ አሳክቶ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ያሸነፈ የመጀመሪያዉ ክለብ ያደርገዋል። ሲቲ ሳዉዝሀምፕተንን መደብደቡን አያይዞታል ስተርሊንግግግግግ አንግል መለሰበት ፔፕ ተጨንቋል ደጋፊዎች እጃቸዉን ጭንቅላታቸዉ ላይ አድርገዋል ነገር ግን ባለቀ ሰአት በጭማሪ ደቂቃ ጋብሪየል ጄሱስ ሚገርም ቄንጠኛ ጎል አስቆጥሮ ሲቲ አሸነፈ ሪከርዱንም ሰበረ። ሲቲ ሪከርዶችን እየሰባበሩ የሊጉን ዋንጫ ማሳካት ቻሉ። ደጋፊዎቻችን እኛን ማየት ይወዳሉ ጥሩ ግዞ ላይ ነን ሁላቹንም አመሰግናለዉ ቀላል የሚባል ነገር የለም እመኑኝ ህይወት ካለፋን ካልጣርን ትርጉሙን አናየዉም እኛ አሁንም የምንፈልገበት ደረጃ ላይ አደለንም ነገር ግን በትክክለኛዉ መንገድ እየሄድን ነዉ ሁላቹንም አመሰግናለዉ ሲል ፔፕ ንግግሩን ቋጨ። @Football_Fist
Mostrar todo...
👍 8