cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ጥርኝ ጥበብ

ጥርኝ ጥበብ ማለት አንድም እንደ ሽቶ መልካም የጥበብ መዓዛን እናገኝ ዘንድ በሽቶ ከምንገለገልባት ጥርኝ ስም ሰየምናት አንድም ከሞላ የህይወት ስብጥርጥር እና ካልገቡን የህይወት መራራነት በጥርኝ ወይም ደግሞ በትንሽ ጥበብ እፎይታን እናገኝ ዘንድ በዩቱዩብ https://www.youtube.com/@2112-trgn-tbeb በቴክቶክ tiktok.com/@trgntbebhiluabiy

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
421
Suscriptores
-124 horas
+27 días
-330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ያልፋል😁😍😍
Mostrar todo...
👍 6
አለሌ ነበርኩ ። ከህንድ እስከ እብድ የቀረኝ የለም የምል  አለሌ። የተኛኋቸው ሴቶች ጠቢቡ ሰለሞን ከተኛቸው የሚያንስ አይደለም አልቆጠርኳቸውም እንጂ። ጀንጅኜ መዳረሻዬ ማራኪ ሆቴል ነው ።ሆቴሏ ሸጎጥ ያለች  ሰዋራ ስፍራ ነች ፤ ከመኖርያዬም እሩቅ ነች  ። አስተናጋጆቹም ምቹ ናቸው። በእርግጥ ጉርሻ ምቹ የማያደርገው የለም ። ፈረንጁ እና መስኪ የሚባሉ አስተናጋጆችን የበለጠ አውቃቸዋለሁ  ። ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዱኛል ፤ በእርግጥ መስኪ የምትባለው ትንሽ ተለቅ ትላለች ። ፊት ከሰጠሁት ይጎነትለኛል ብላ ይሆን ፣ ተፈጥሮዋ ሆኖ ይሆን ፣ ነፍፍ  ቺክ ስለማመላልስ ይሆን ፣ ስለማጨስ ወይም ስለምጠጣ ይሆን እኔ'ንጃ ብቻ አትስቅልኝም   አትኮሳተርብኝም  ። ፊቷ ወጣትነትን  ቢሸኝም ውበቷ ግን እንዳለ ነው። መስኪ ምንም ያህል ቲፕ ብሰጣት አመሰጋገኗ ሆነ አስተያየቷ አይለይም ተመሳሳይ ነው ። ክላሴ ውስጥ አጭሼ ፣ ጠጥቼ ፣  ባልጌ ሹልክ ብለን በጓሮ እንሄዳለን ። በሌላ ቀን ሌላ ቺክ ይዤ እመጣለሁ ፣ ካልጠረረብኝ ቺክ አልገርብም ። ሁሉንም እንደሙዳቸው እና እንደፍላጎታቸው እሰክሳቸዋለሁ ። ላጤነቴ  በነፃነት ታየው አልታየው ብዬ  ሳልሳቀቅ  ለመባለግ አግዞኛል።  ጓደኞቼ ሁሉ  ሲያገቡ ፤ ቤተሰቦቼ የአታገባም ውትወታ የበረታ ወቅት ሶልያና የምትባል ልጅ ተዋወቅኩ ። ባገኘኋት በሁለተኛ ቀን ለመቾመስ በት በት አልኩ  አልተሳካልኝም ። በውስጤ ስንቷ እንደ አንቺ አካብዳ ጭኗን ሳትከፍት የቀረች የለችም ብዬ ፈገግ ስል ምነው አለቺኝ እርጋታሽ ደስ ይላል አልኳት ውስጤ እንደላዬ የተረጋጋ እንዳይመስልህ አለቺኝ ። ይሆናል ግን ውስጥም ላይም አንድ ላይ ከመንቀዥቀዥ ይሻላል አልኳት ከንፈሯን  ገለጥ አድርጋ ሳቅኩኝ አይነት አለቺኝ በነገራችን ላይ አንተም ረጋ ያልክ ነክ አለቺኝ... ስስቅ ። ውስጥህ ወዲ ወዲያ ስለሚል ነው እርጋታህ ያልታወቀህ አለችኝ  ። ይሆናል አልኳት ሶልያና  የበዛ እርጋታ አላት ፥ እርጋታዋ ይረብሸኛል ከደስታ ይልቅ ለድብርት አጋልጦ ነው  የሚሰጠኝ። አብሪያት የምሆነው  እስከምደክላት ብቻ ነበር።  ትፈልጋለች ብዬ የማስበውን እነግራታለሁ ። ሲኒማ እጋብዛታለሁ ፤ ትያትር ትጋብዘኛለች   ከንፈሯ ጋ ሳልደርስ ቀናቶች ነጎዱ በጭራሽ የወሲብ ወሬ ለማውራት አታመችም ። ወሲብ ነክ ከተወራ ለመቀጠል ፊቷ አይጋብዝም።ወሲብ ነክ ወሬ ካወራሁ  ለይሉኝታ እንኳን ፈገግ አትልም። መንፈሳዊ ጉባኤ ትጋብዘኛለች። ለእሷ ደስ እንዲላት አንዳንድ አሰልቺ ፣ አንዳንድ ማራኪ ስብከቶችን እሰማለሁ ። ቀልቧን ለመግዛት መንፈሳዊ መፅሃፍ እያነበብኩ ፤ በጉዳዩ ላይ ሰፊ እውቀት አለኝ ወሬ ሳወራት ቀልቧ ሲሳብ ወሬው ሲጥማት አያለው። ሳይታወቀኝ የኔን መንገድ እየተውኩ በእሷ መንገድ መመላለስ ቀጠልኩ ። ከሌሎች ስለተለየች  ይሆን ፣ እንደምፈልገው አለመሆኗ ይሆን ፣ የምፈልገውን ስላልሰጠቺኝ  ይሆን ብቻ ቀልቤን ገዝታዋለች። ውሎዋን ስራዬ ብዬ እከታተላለሁ ። ካልተደዋወልን ይታወቀኛል ። እንቅስቃሴዋ እየገቡኝ መጡ ። ሳላገኛት  የት እና ምን እያረገች እንደሆነ መገመት ቻልኩ ። ከደወለችልኝ ስግብግብ ብዬ አነሳለሁ ። በሂደት መንገዷ ምቾት ሰጠኝ ። ከተመላለስኩበት መንገድ በተሻለ ይሄኛው መንገድ ጣፈጠኝ የድሮ አመሌ ውል ሲለኝ የምቀመጭላቸው ቺኮች ውልብ ብዬባቸው ሲደውሉ  ሳላቅማማ የድሮ ስልክ ቁጥሬን  ቀየርኩ ። የትላንት የውድቀት  መንገዳችንን ካልቀየርነው ለለውጣችን ሳንካ ይሆናል ። አሁን ፈልጌ መፅሃፍ ቅዱስ አነባለሁ፤ እፆማለሁ ጉባኤ እከታተላለሁ ።መንፈሳዊ ጉዞ እሄዳለሁ ።  ከሶሊያና ጋ እንፋቀራለን። የትላንት መንገዴን አልተረኩላትም ለዛሬው ማንነቴ ግን  ማሃንዲሷ እሷው ናት ።   ለአምላኬ ስንቴ በእሷ ምክንያት ምስጋና እንዳቀረብኩለት። የትላንት ህይወቴን እንዴት አሁን እንደማልወደው ። ስለ ሴት አውልነት ሲነሳ ምንም ሃሳብ አልሰጥም ያ ዘመን ያሳፍረኛል። ሶልያና  አንድ እለት ስትፍነቀነቅ መጣች ምነው ስላት እቴቴ ስራ አገኘች አለቺኝ የት ስላት ባንክ በቀላሉ ፍንክንክ የምትል አይደለችም የእናቷ ጉዳይ ግን ስስ ጎኗ ነው። ብቻዋን ስላሳደገቻት ይሆን ሁሉ ነገሯ ስለሆነች ይሆን ብቻ ስፍስፍ ትልላታለች። ምን እንደምትሰራ አላውቅም ። በትምህርት ብዙ ያልገፋች ስለሆነች የት እና ምን ትሰራለች ብዬ አልጠየኩም ፤ እሷም ስራ ነች አልመጣችም ፣ ስራ ቀረች ነው እንጂ የት እና ምን እንደምትሰራ ነግራኝ አታውቅም  ። በጥንጡም በግዙፉም ወሬዎቾ መሃል  እቴት ሳትል አትውልም ። የድሮ ስራዋስ ስላት ። ውይ የድሮ ስራዋን እኮ አትወደውም ግድ ሆኖባት እንጂ አለቺኝ። ስለ እኔ እንደነገራቻት እና እንደወደደቺኝ  የነገረቺኝ እለት እንዴት ደስ እንዳለኝ ። ባሻዬ ብላ ቴክስት አደረገችልኝ ።  ደስ ስላት እና ስትቀልድ ባሻዬ ነው የምትለኝ ። ከእቴት ጋ እንደምንመሳሰል ነግሬህ አውቃለሁ ኣ ስትለኝ ሁሌ ብዬ የሳቅ ስቲከር ላኩላት ። እንደ እሷ ቆንጀ ነኝ ግን ብላ ፎቶዋን ላከችልኝ ። ማመን አልቻልኩም ክው ድርቅ አልኩ የላከችልኝ ፎቶውን አገላብጬ አየሁት ፤ አልቀየር አለ ። የማራኪ ሆቴል አስተናጋጅ መስኪ የሶሊያና እናት ናት ፤ ሁለት አብረው ሆነው እና አንድ የመስኪን  ማራኪ እንግዳ መቀበያ ጋ የተነሳችውን ፎቶ ላከችልኝ ። ውስጤ ታወከ ። ያ ሴት አውል አብርሃም ፤ ያ በየጊዜው ለቁጥር ስፍር የሌላቸውን ሴቶችን የሚያጋድመው ፣ የሚያጨሰው አብራሃም ፤ ያ በጥሩ አይን አይታው የማታውቀው አብራሃም ፤ የአንድ ልጇ ሶሊያና እጮኛ ነኝ ብሎ ፊቷ እንዴት ይቆማል?? ትላንቴ  ተከተለኝ። እግዜር በተፀፀትንበት ትላንታችን ይቀጣናል እንዴ? ስንቴ ያመሰገንኩበት ጉዳይ መጨረሻው እንዴት እንደዚህ ሆነ ?? የማደርገው ጠፋኝ ። ጠፋሁ ። አንዳንድ ትላንት ትላንት ላይ ብቻ አይቆምም።
Mostrar todo...
👍 11🥰 1👏 1
የመለያየት ጥላው ይከብዳል ለካ ቻው ማለት ይጨንቃል ከሽኝት የከፋ ነገር ምን አለና ቻው ማለት ክፉ ነው ትናንት ያስለፍናቸው ክፉም ሆነ ደግ ቀኖች ይናፍቃሉ። ሁሉ ስሜት አይፃፍም ሁሉ ስሜት አይነገርም ከማይነገሩ ስሜቶች የላቀው ስሜት ደግሞ የመለየት ስሜት ነው። መተዋወቅ እኮ ደግ እስከመለያየት ድረስ ብቻ ይጨንቃል ወንድነትን የሚፈታተን ስሜት አይንን የሚጠምቅ በግድም ቢሆን አንገት የሚያስደፋ መሬት የሚያስጭር ስሜት መለያየት ነው። መሸኘት ደግሞ ጨካኝነት ይጠይቃል እነዚያ የህይወትን ስንቅ የመገቡን እነዚያ የሳቃችን ምክንያት የሆኑ የልብ ልባችን ሲሄዱ ደህና ሁኑ ብሎ መለየት ይጨንቃል። ብቻ ልጅ እንደተሆነ አይቀር የሆነ የህይወት ደረጃ ከፍ አልን መልካም እድገት ይሁንልን። ቸር ይግጠመን ይግጠማችሁ። እወዳቸኋለሁ!😍😍😍
Mostrar todo...
7
Photo unavailableShow in Telegram
ብዙ ጊዜ ሻማወች በፎቶ ውብ ናቸው ማንም ሻማን ያስጠላል ብሎ አስቦ አያውቅም አንዳንድ ቀን ግን የተነሳህበት ካሜራ ጥሩ ሳይሆን ሲቀር ጥሩ አለመሆንህ ይገለጣል። ሻማዋም ጥሩ ካሜራ ስላጣች ጥሩ ውበት አልተነበባትም።ግን ውበት ስሌለላት ሳይሆን ካሜራዋ በትክክል ስለማያነሳ ነው። አየህ በህይወት ስትኖር አንዳንድ የእይታ ካሜራቸው ጥሩ ያልሆነ ሰዎች ይገጥሙሀል መልካምህን ማየት ትተው እንከንህን ያሳድዳሉ በእነርሱ ዘንድ ምንምህም ዋጋ ያጣል ግን ዋጋ ስለሌለህ ሳይሆን አንተን ያየህ ያየበት መንገድ ስለተሳሳተ ነው። መታየትን አትሻ ግን አትፍራው ዓቢይ አለሙ(ሚተራሊዮን)
Mostrar todo...
👍 4 1👏 1
መጠበቅ መመርቀዝም አለዉ ።ይመጣሉ ባልናቸዉ ሰአት ቀርተዉ ባልጠበቅንበት ወቅት ደርሰዉ ለመናገር አደለም ለማሰብም ያዳግተናል ። ትናንት ሳንጠብቃቸዉ ተገኝተዉ የመደነቅ ደስታን የመጠማትን ጥግ አስጎብኝተዉን በጠበቅናቸዉ ዛሬ መራቅን አርድተዉን ነገን የሚሰብሩብን መጠበቆች እልፍ ናቸዉ ። ብቻዉን የቆመ ዛሬ የለም ወይ ትዝታን ወይ ተስፈን ወይ ትናንት ላይ ተንጠልጥለን ወይ ለነገ ተመዝነን። ህሊና (ትዝታ)
Mostrar todo...
👍 4🥰 1
ጠርሙስ ጨብጣ ቡራካርዮ ስትል የምናውቃት እድሜ ነው ህመም ፀጥ አለች ዛሬ ምን አስረመማት የህፃናት ሳቅ የሚያሽካኩባት ፊቷን መእያዩ ሞታለች አሉ ሾ ሸምቱ ሙለቅሶን ገብዩ ያች ሳቃቸው በውልግድግዷ የሚዝናኑባት የባሏ መሞት መሳለቂያ አድርጎ ማለቂያ ሆናት አገረመመች እንዳትመለስ ቅንድብ ተደፋ እንዴ ባሏ ክንድ አረፍ አለችው ጠርሙስ ታቅፋ ለሙሾ አውራጆች ግጥም አቀባይ ለቅሶ አድማቂ እንዲህ አለችው የሟችን አንጀት የልብ አዋቂ "እስኪ አታልቅሱ ከመቃብሬ እምባ አይዥጎድጎድ ከሞትኩ ቆየሁ ዛሬ ብሄድም ከባሌ ጉድጓድ እስከመች ድረስ የብቻ አለንጋ የሚቸበችበኝ ጀርባዬ እስኪላጥ ልሄድ ከባሌ እቅፉን ልሙቅ ጠርሙስ ይቀመጥ አይውረድ ሙሾ በእኔን ዋይታ ቀብሬን አትንኩት ባሌን ቀብሬ ስተነፍስ ነው እኔ የሞትኩት" ግጥሙን ሰሚ አጃኢብተኛው የሩቅ የቅርቡ ሟችን ለመርሳት ቆሎ ለመዝገን ከዳስ ቀረቡ እንዲህ ነው ህይወት
Mostrar todo...
🥰 2 1
ይነጋል ያላሉት ሌሊት ነግቶልን ፅባህ አይተናል ያባራል ያላሉት ዝናብ አባርቶ ፀሀይ ሞቀናል እመ አምላክ እቅፍሽ ሞቆኝ እትትትት ሳልል አለፈ በምልጃሽ ቀሚስ ስከለል ጠላቴ ክንዱ ታጠፈ
Mostrar todo...
🥰 2🙏 1
የሆኑ ከባክብቶች አሉ ወደ ፀሀይነት ለመሻገር መፍዘዛቸውን ስንማፀን ይልቁንስ የሚደምቁ የሆኑ ሰዓታቶች አሉ ማለቃቸውን ስንማፀን ይልቁንስ ግትር የሚሉ ነገሩ እኛ ነን ጥፋተኞች ነገ ይዞት የሚመጣውን የመቋቋም ጉልበት ያለን ይመስል ስለ ነገ እንቸኩላለን። ዛሬን ማጣጣም ከሁሉ ይበልጣል
Mostrar todo...
🥰 2 1
ተስፋ የሆነ መዳፍ ከቶ እንዳይታጠፍ ለልጆችሽ ብርታት የሆነን ልመና ዘወትር የማይታጠፍ መዳፍሽ ነውና
Mostrar todo...
1
ሶስተኛዋ ሴት ክፍል አራት ክላስ ገብቼ መማር አቃተኝ አቋርጨው በእግሬ እየተጓዝኩ ደወልኩለት ስልኩ እንደተነሳ ከአንድ የመንገድ ዳር ወንበር ላይ ቁጭ አልኩኝ። አነሳውናጤና ይስጥልን አልኩት ያንን ውብ ድምፁን መስማት እየቋመጥኩ "አብሮ ይስጥልን ማን ልበል" አቤት መኮሳተር ነገሩ ፖሊስ አይደል ! inspector Shakir ነሃ "አዎ ነኝ ይቅርታ  አላወኩሽም" Amanda ነኝ "በድጋሜ ይቅርታ Amanda ማን" በምን ላስታውሰው ስለ Rihana ላንሳ ወይስ ስለ Charlious አንድ ነገር ትዝ አለኝ ለራሴም ከበሬታ ለመስጠት አሰብኩና... ቅድም በጥላ ያስፈራራሁህ አልኩት " እ  ሽፍታዋ ነሽ እንዴ?" እንዴ የምን ሽፍታነት ነው የምታወራው "ጥሻ ለጥሻ እየተደበቁ ሰውን ማስፈራራት ያውም ፖሊስን ራሱ  ማስፈራራት ከዚህ የበለጠ ምን ሽፍታነት አለ እና ከመሸ ምን አጋጠመሽ" አለኝ። ከእኔ በላይ ለነገሩ ትኩረት የሰጠው ስለመሰለኝ ደስ አለኝና ... ቅድም ስለጀመርነው ነገር እንድንጨርስ "እኔ እና አንች ደግሞ ምን ጀመርን"(የፌዝ ሳቅ እየሳቀ እንደሆነ ያሳብቅበታል) ይቅርታ አልቀለድኩም የጀመርነውን ወሬ እንድንቀጥል እፈልጋለሁ "እኔም ይቅርታ ለወሬ ጊዜ የለኝም ቅር ካላለሽ ልዝጋው?" ሰውዬ ያምሀል እንዴ አልቀለድኩም እና ያልኩህ ነው ሰውዬ?! አዎ ሰውዬ ትሰሚኛለሽ እኔ inspector Shakir እባላለሁ instructerነትህን ጎዝጉዘው እሽ ስለምን ወሬ ጀምረህ እንዴነበር ረሳኸው እንዴ ስለአባሄ ነው ገባህ አ   ባ     ቴ! ለአመታት አይኑን እንኳን ባየሁት ብዬ ስለምመኘው አባቴ በዚያ ላይ ለጭንቅላቴ የፈጠርካቸውን ጥያቄዎች ትመልስልኛለህ።ስማኝ ቀጣይ ሳገኝህ በጥላ ላስፈራራህ አይደለም አባቴ ይሙት አለቅህም ጭንቅላትህን እቦረቅሰዋለሁ የጀግና ወታደር ልጅ Amanda መሆኔን አታውቅም።!(ሳላስበው ነው እልህ ውስጥ የገባሁት ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀምሯል) እናት በቃ ተረጋጊ" እናትህን ሂድና ፈልግ እሽ እ እሽ እሽ ተረጋጊ በቃ ነገ ተገናኝተን እናወራለን አሁን ወደቤትሽ ግቢና እረፍት አድርጊ(የመለማመን ንግግሩ በአንድ ጊዜ ነው ያሰከነኝ ደግሞ አሳቢ ለመምሰል መሞከሩን ወደድኩት)... ወደ ቤቴ ስገባ እናቴ ተኝታለች ቀጥታ ወደ ክፍሌ አመራሁ በጥያቄዎች ተወጠርኩኝ ቆይ እነ ማን ናቸው... Rihana,charlious ማን ናቸው እኔ ራሱ ማን ነኝ?! ይቀጥላል ሀሳብ አስተያየት ካላችሁ እባካችሁ በ comment box ወይም @habeshawiii ላየ inbox ብታደርጉልኝ ይደርሰኛል። ቻናሉን ለማግኘት ጥርኝ ጥበብ ብለን መፈለግ ወይም .me/trigntbeb በዚህ ሊንክ በመግባት ማገኘት ይችላሉ። ጥርኝ ጥበብ
Mostrar todo...
ጥርኝ ጥበብ

ጥርኝ ጥበብ ማለት አንድም እንደ ሽቶ መልካም የጥበብ መዓዛን እናገኝ ዘንድ በሽቶ ከምንገለገልባት ጥርኝ ስም ሰየምናት አንድም ከሞላ የህይወት ስብጥርጥር እና ካልገቡን የህይወት መራራነት በጥርኝ ወይም ደግሞ በትንሽ ጥበብ እፎይታን እናገኝ ዘንድ በዩቱዩብ

https://www.youtube.com/@2112-trgn-tbeb

በቴክቶክ tiktok.com/@trgntbebhiluabiy

👍 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.