IQRA〖اقرأ〗
Ir al canal en Telegram
2 841
Suscriptores
+324 horas
+137 días
+3430 días
Archivo de publicaciones
2 844
በጦርነት ብትደቅም፣ የሞት ጥላ ቢጋርዳትም፣ ጥልቅ ህመም በየደጃፏ ቢበረታባትም፣ ስቃዩም ቢበዛባት ጋዛ ዛሬም አልተንበረከከችም። ጋዛ የህይወትን ፀዳል፣ የመኖርን ተስፋ ያነገቡ እንስት የህክምና ዶክተሮችን ከእስላማዊ ዩኒቨርሲቲዋ ለ15ኛ ዙር በዛሬዉ ዕለት አስመርቃለች።
ይህ ትዕይንት ጋዛ በቦምብ እና በሚሳይል መሬቷ ቢታረስም ጥንካሬዋ ግን ሊሰበር እንደማይችል ለዓለም ያሳየችበት የታሪኽ ምዕራፍ ነው። መድሀኒትና የህክምና ቁሳቁስ በሌለበት፣ ሆስፒታሎች በወራሪዎች ድብደባ በፈረሱበት፣ የሰው ልጅ መኖር በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ የህይወት አድን ባለሙያዎችን ማፍራት፤ የፅናት ማረጋገጫ ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል።
የጋዛ ሁኔታ በታሪኽ ውስጥ የኸንደቅን ዘመቻ ቁልጭ አድርጋ ታስታውሰናለች። በዚያን ወቅት ሶሃቦች በረሃብ፣ በቅዝቃዜ፣ በከበባ፣ በጠላቶች ድቅድቅ ጨለማ ተከበው ፍርሃት ልባቸውን በጨበጠበት ወቅት የአሏህ መልእክተኛ 🤍 በዚያ ተስፋ አስቆራጭ ወቅት ድንጋዩን ሲሰብሩ አሏሁ አክበር የፋርስን ቁልፍ ተሰጠሁ አብሽሩ እያሉ የድልንና የነፃነትን ፀዳል ያበስሩ ነበር።
ዛሬም በጋዛ እየሆነ ያለው ልክ እንዲያ ነው። በወራሪዎች ተከበዉ፣ በአረብ ወንድሞቻቸዉ ዝምታ ታንቀዉ፣ በየሰከንዱ የሞት ድግስ በሚያንዣብቡበት ምድር ላይ ሆነዉ ተስፋ ሳይቆርጡ ዶክተሮችን ማስመረቅ ማለት፤ በኸንደቅ ዘመቻ ወቅት የተወረወረውን የድል መዶሻን በዘመናችን በተግባር ማሳየት ማለት ነው።
ጋዛ ህመምዋ ጥንካሬዋን፤ እንባዋ ደግሞ የስቃዩ ማብቂያ እንደሆነ እያስመሰከረች ነው። ጨለማው ምንም ያህል ቢከብድም ከጀርባው የሚያበራው የነፃነት ብርሃን የማይቀሬ መሆኑን የጋዛዉያን ፅናት ምስክር ነው።
✍IbnuHashm

t.me/IbnuHashm
2 844
🩶😢🩶😢🩶😢የመጨረሻው ቀጠሮ😢🩶😢🩶😢🩶
😢ረሱሉﷺ በጠና ታመው ራሳቸውን ስተው አሊይና ፈድል ደግፈዋቸው ወደ ዐኢሻ ረ.ዐ ቤት ሲወስዷቸው ሰሃቦች ተመልክተው በጣም ይጨነቃሉ...🥺
🩶ረሱሉﷺ ሲነቁ የሰዎችን ድምፅ ሰሙና ምንድነው ሲሉም ጠየቁ ...
😢"ያረሱለላህ ባልደረቦችህ ናቸው መታመሞን ሰምተው ስጋት አድሮባቸው ነው" ሲሉ መለሱላቸው
🩶አዛኙ ነብይም" ወደ ባልደረቦቼ ይዛቹኝ ሂዱ" አሉ
.....ሚንበር ላይም ቆመው እንዲህ ሲሉ ተናገሩ...
😢"እናንተ ሰዎች ሆይ !የቀጠሮ ቦታችን እዚህ አይደለም ቀጠሯችን ቦታ ሀውድ ላይ ነው እዛ እንገናኝ "አሉ🥺
🤍አላህ ዱንያላይ ማየት ያልታደልነውን ፊታቸውን በአኼራ ያሳየን 🥺🤲
🩶በዱንያ ላይ ማግኘት ያልቻልነውን ጉርብትናቸውን በጀነት ይሸልመን 🥺🤲
🤍ሀውድ ላይ ቀጥረውናልና... ሀውዳቸው ላይ ተገኝተው ከሀውዱ ከሚጠጡት ያድርገን🤲🥺
🤍ዕልፍ አዕላፍ የሆነ ውዳሴ ፣ አፅናፍንም ሁሉ የሞላ ሰላም ሀውድ ላይ በቀጠሩን አዛኙ ነብይﷺ ላይ ይስፈን🥰
🤍🩶🤍መልካም ጁመዐ🩶🤍🩶
2 844
ከሐራም ነገር ከባዱ የመጀመሪያው ነው። ከዚያ ሲደጋገም እየቀለለ ይሄዳል። ከዚያ እንዲሁ ተራ ነገር ይሆናል። ከዚያ ልማድ ይሆናል። ከዚያ ይጣፍጣል። ከዚያ ልብ ይሸፈናል። ከዚያ ልብ ሌላ ሐራም መፈለግ ይጀምራል።
አንድ ሷሊሕ ሰው እንዲህ ይላል፦ "ነፍስህ ወደ ወንጀል ከጋበዘችህ በዚች አንቀፅ አጭር ቃለ መጠይቅ አድርግላት :-
{ أَذَ ٰلِكَ خَیۡرٌ أَمۡ جَنَّةُ ٱلۡخُلۡدِ ٱلَّتِی وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۚ }
"ይሄ ነው የሚሻለው ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት የዘለዓለሟ ጀነት?" [አልፉርቃን፡ 15]
በዚህ ሐራም ነገሮችን መዳፈር በበዛበት ዘመን ይህቺን አንቀጽ ማስተዋል ምንኛ አንገብጋቢ ነው ?!
2 844
ራትኮ ሚላዲች ሞተ!
"የቦስኒያው አረመኔ" ወይንም "The Butcher of Bosnia " እየተባለ የሚጠራውና ከሙስሊሞችና ካቶሊኮች የፀዳች ኦርቶዶክሳዊት ሰርቢያን ለመፍጠር በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀልን የመራው ራትኮ ሚላዲች ሄግ በሚገኘው አለምአቀፉ የወንጀል ፍርድቤት የእድሜ ልክ እሰራት ተፈርዶበት ሲማቅቅ ከኖረ በሗላ በዛሬው እለት በ 84 አመቱ እዚያው እስርቤት እያለ ምቷል።
ስለ ስሬብሬኒካ ጄኖሳይድ ብዙ ጊዜ በሰፊው ፅፌ አስነብቤያችሗለሁ። ያንን ጄኖሳይድ የመራው ራትኮ ሚላዲች ነበር።
ራትኮ ሚላዲች ካቶሊካዊቷን ክሮሺያን ለመጠቅለል ያደረገው ሙከራ አልሳካለት ሲል ሙስሊሞች የሚበዙባት ቦስኒያ ላይ ዘመተ። በሩሲያ የሚደገፈው የሰርቢያ ጦርም የቦስኒያ ዋና ከተማ ሳራጄቮን ለ 1,435 ቀናት ወይንም ለ 203 ሳምንታት በመክበብ ከ 12,000 በላይ ነዋሪዎቿን ጨፈጨፈ። ይህም በዘመናዊ የሰው ልጆች ታርክ ረጂሙ ከበባ ነበር።
ከዚያም አልፎ ስሬብሬኒካ ላይ ሙስሊሞችን በመክበብ ከ 8,000 በላይ ወንዶችንና ህፃናትን በጅምላ ጨረሳቸው። ወታደሮቹ ሙስሊም ሴቶችን በጅምላ እየደፈሩ ረሸኗቸው።
ይህ ግፍ አውሮፓ ምድር ላይ ሲከሰት ኔቶ ጣልቃ ገባና የሰርቢያን ጦር ደበደበ። አሜሪካ ቱርክ ኢራንና ሌሎችም ሀገራት የቦስኒያ ሀይሎችን በማስታጠቅና በማሰልጠን የሰርቢያን ጦር የሚመክትና የሚያሸንፍ ሀይል እንዲገነባ አደረጉ። ሳኡዲ አረቢያ እና ሌሎችም የአረብ ሀገራትም የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
በዚህም 1995 ላይ የሰርቢያ ጦር ግስጋሴ ተገታና ቦስኒያ ሄርዝጎቬኒያ ራሷን የቻለች ሀገር ሆና ተመሰረተች።
ሰርቢያን የኦርቶዶክስ ሀገር እንዳደርግ ከእግዚአብሔር ተልኪያለሁ ይል የነበረው ጀኔራል ሚላዲች " ሙስሊሞችን ግደሉና አቃጥሏቸው ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጠኝ ትእዛዝ ነው" ይል ነበር።
"ህፃናቱን እንዳትምሩ ሲያድጉ የናንተው ጠላቶች ነው የሚሆኑት" እያለም በርካታ ህፃናትን ጨረሰ።
ራትኮ ሚላዲች ለ16 አመታት ተደብቆ ከኖረ በሗላ በ 2011 አለምአቀፉ ፍርድቤት በድብቅ ተከታትሎ በቁጥጥር ስር አውሎታል። በዚህ ከበርካታ የሰርቢያ መሪዎች ጋር የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ነበር። ራሳቸውን ፍርድቤት ላይ ያጠፉም መሪዎች ነበሩ።
ሚላዲች ከተያዘ ከ 15 አመታት በሗላ በእስር ላይ እያለ ዛሬ ህይወቱ አልፏል።
2 844
+1
የሳኡዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሸይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊ በሞት እንዲቀጡ ጠይቋል።
ሸይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊ በአሁኑ ሰአት በሳኡዲ እስርቤት ውስጥ ሆነው ጤናቸው ክፉኛ መቃወሱን የሳኡዲ እስረኞችኝ የሚከታተለው የህሊና እስረኞች አስታውቋል።
ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ አቃቤህጉ ሸይኹ እንዲገደሉ ፍርድቤቱን ጠይቋል።
ሽይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊ በዘመናችን ከሚገኙ ታላላቅ አሊሞች አንዱ ሲሆኑ በጥልቅ የፊቅህና የሀዲስ ዘርፍ በጣም ሊቅ ናቸው።
ሸይኹ ሳኡዲ አረቢያ እየሄደችባቸው ያሉትን ከኢስላም የሚጣረሱ አካሔዶች የሚተችና አልአረቢያ ቴሌቪዥን እያሰራጨ የሚገኘውን ከኢስላም ያፈነገጡ ፊልሞችና አስተምህሮቶችን የሚተቹ ፅሁፎችን ካስነበቡ በሗላ ከ 10 አመት በፊት ወህኒ ቤት ተወርውረዋል። እዚያም ምንም ክስ ሳይመሰረትባቸው የ 10 አመታት ስቃይ ቢያሳልፉም አሁን ላይ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሞት እንዲቀጡ ፍርድቤትን መጠየቁ ብዙዎችን አስደንግጧል።
ከሸይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊ በተጨማሪ ሸይኽ ሰልማኑል አውዳ ፤ ሸይኽ ኻሊድ አልራሽድ ፤ ሸይኽ አዋድ አልቀርኒ ፤ የመስጅደል ሀረም ኢማም ሸይኽ ዶክተር ሳልህ አልጧሊብ ፤ ሸይኽ ሰፈር አልሀዋሊ ይገኙበታል።
በእስር ላይ እያሉ ተሰቃይተው በቶርቸርና በረሀብ የሞቱ በርካታ ኡለማኦች ያሉ ሲሆን ከነዚህም መካከል
ሸይኽ ፈህድ አልቃዲ ለሳኡዲው ንጉስ የምክር ደብዳቤ በመፃፋቸው ታስረው የነበሩ
ሸይኽ አህመድ አልአማሪ
ፕሮፌሰር ሸይኽ ሙሳ አልቀርኒ
ዶክተር አብዱሏህ አልሀሚድ ወዘተ ይገኙበታል።
ሸይኽ አብዱልአዚዝ አልጦረፊን ጨምሮ ሸይኽ ሰልማኑል አውዳ ፣ ሸይኽ አዋድ አልቀርኒ እና ሸይኽ አሊ አልኡማሪ የሞት ቅጣት የሚጠብቃቸው ኡለሞች ናቸው።
ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
2 844
أَفْضَلُ الصَّلَاةِ وَأَتَمُّ التَّسْلِيمِ عَلَى سَيِّدِنَا وَمَوْلَانَا مُحَمَّدٍ، الْمُصْطَفَى الْمُخْتَارِ، وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينَ.
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ، عَدَدَ مَا فِي عِلْمِ اللَّهِ، صَلَاةً دَائِمَةً بِدَوَامِ مُلْكِ اللَّهِ.
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَيْهِ وَعَلَى آلِهِ وَأَصْحَابِهِ، وَارْضَ اللَّهُمَّ عَنْهُمْ أَجْمَعِينَ.
وَاجْعَلْنَا اللَّهُمَّ مِنْ أَهْلِ مَحَبَّتِهِ وَاتِّبَاعِ سُنَّتِهِ، وَاحْشُرْنَا فِي زُمْرَتِهِ، وَاسْقِنَا مِنْ حَوْضِهِ شَرْبَةً هَنِيئَةً لَا نَظْمَأُ بَعْدَهَا أَبَدًا.
اللَّهُمَّ ارْزُقْنَا شَفَاعَتَهُ، وَأَكْرِمْنَا بِرُؤْيَتِهِ، وَاجْمَعْنَا بِهِ فِي الْفِرْدَوْسِ الْأَعْلَى مِنَ الْجَنَّةِ، يَا أَرْحَمَ الرَّاحِمِينَ.
وَصَلَّى اللَّهُ وَسَلَّمَ وَبَارَكَ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ أَجْمَعِينَ
2 844
የእባብ ንክሻ ሲያጋጥመን ማድረግ ያለብን አፋጣኝ እና ትክክለኛ እርምጃዎች!
የእባብ ንክሻ በድንገት ሊከሰት የሚችል እና ፈጣን ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ ለከፍተኛ አደጋ አልፎ ተርፎም ለህይወት መጥፋት የሚዳርግ የጤና ችግር ነው።
ማህበረሰባችን ስለ እባብ ንክሻ ትክክለኛውን የመጀመሪያ እርምጃ ማወቅ እና መርዛማና መርዛማ ያልሆኑ እባቦችን መለየት መቻል ይኖርበታል!
📌 ይህንን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ 'Share' በማድረግ ህብረተሰባችንን ከእባብ ንክሻ አደጋ እንጠብቅ! 🏥❤️
🔍 መርዛማ እና መርዛማ ያልሆኑ እባቦችን እንዴት እንለያለን?
👉👉 ሁሉም እባቦች መርዛማ አይደሉም፤ ሆኖም አደገኛዎቹን በቅርፃቸው መለየት ህይወትን ይታደጋል፦
🔺 1. የመርዛማ እባቦች ገጽታዎች፡
የራሳቸው ቅርጽ (Head Shape): አብዛኛዎቹ መርዛማ እባቦች (እንደ እፉኝት ያሉ) ራሳቸው ሰፊ፣ ባለ 3 ማዕዘን (ትሪያንግል) ቅርጽ አላቸው።
የዓይን ቅርፅ (Pupils): አይኖቻቸው ልክ እንደ ድመት ቆንጥጦ የተሰነጠቀ (Vertical/Slit pupils) ቅርጽ አላቸው።
የጥርስ ምልክት (Fangs): ሲነክሱ ጥልቀት ያላቸው ሁለት ዋና ዋና የጥርስ ቀዳዳዎችን (የመርዝ ማስተላለፊያ) ይተዋሉ።
🟢 2. መርዛማ ያልሆኑ እባቦች ገጽታዎች፡
የራስ ቅርጽ: ራሳቸው ጠበብ ያለ (የተስተካከለ ክብ ቅርጽ ያለው) እና ከሰውነታቸው ጋር የተሳሰጠ ነው።
የዓይን ቅርፅ: አይኖቻቸው ክብ ቅርጽ (Round pupils) አላቸው።
🚨 እባብ ሲነክሰን ወዲያውኑ መደረግ ያለባቸው አፋጣኝ እርምጃዎች! 🚨
👉 ፈጣን እና ትክክለኛ እርምጃ መውሰድ መርዙ በሰውነት ውስጥ እንዳይሰራጭ ትልቁን ሚና ይጫወታል፦
🛡 1. ተረጋጉ እና ከቦታው ይራቁ፦ እባቡ ከነከሰ በኋላ መደናገጥ የልብ ምትን በመጨመር መርዙ በደም ስር ውስጥ በፍጥነት እንዲዘዋወር ያደርጋል። ከእባቡም መገኛ ራቅ በማለት ራስዎን መጠበቅ ያስፈልጋል።
🛌 2. የተነከሰውን የሰውነት ክፍል አትንቀሳቀሱ (Immobilize)፦ እጅግ ወሳኙ ጉዳይ የተነከሰውን እግር ወይም እጅ ልክ እንደ ስብራት ማንቀሳቀስ ማቆም ነው። እንቅስቃሴ የደም ዝውውርን አፋጥኖ መርዙ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች እንዲደርስ ያደርጋል።
💍 3. ጌጣጌጦችን እና ጥብቅ ልብሶችን ያስወግዱ፦ የተነከሰውን አካባቢ (ለምሳሌ ጣት ወይም እጅ) ማበጥ ስለሚጀምር ቀለበቶችን፣ ሰዓቶችን እና ጥብቅ ልብሶችን በፍጥነት ማውልቅ ይገባል።
⏱ 4. ወዲያውኑ ወደ ህክምና ተቋም ይሂዱ፦ ከባህላዊ ህክምና ይልቅ ሰዓት ሳይባክን በአቅራቢያ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ወይም ሆስፒታል በመሄድ ፀረ-እባብ መርዝ (Antivenom) መውሰድ ብቸኛው የህክምና መፍትሄ ነው።
🛑 በፍጹም መደረግ የሌለባቸው አደገኛ ስህተቶች! | Don'ts! 🛑
🚫 በጭራሽ መርዙን ለመጥባት አትሞክሩ፦ የተነከሰውን ቦታ በአፍ መጥባት ወይም መምጠጥ መርዙን አያወጣም፤ ይልቁንም በአፍ ውስጥ ላሉ ቁስሎች ሊተላለፍና አደጋውን ሊያባብሰው ይችላል።
🚫 በጣም አጥብቆ ማሰር (Tourniquet) አይቻልም ፦ የተነከሰውን ቦታ በገመድ ወይም በጨርቅ አጥብቆ ማሰር የደም ዝውውርን ሙሉ በሙሉ በማስተጓጎል የሰውን እጅ ወይም እግር መክሰስ (የሕብረ ሕዋስ መሞት) ሊያስከትል ይችላል።
🚫 መቁረጥ ወይም ኬሚካል መቀባት የተከለከለ ነው ፦ የተነከሰውን ቦታ በምላጭ መቁረጥ፣ እሳት ማንደድ ወይም የተለያዩ ኬሚካሎችንና ቅመሞችን መቀባት ለከባድ ኢንፌክሽን ይዳርጋል።
🚫 አልኮል ወይም ቡና/ሻይ መስጠት አይመከርም ፦ ህመምተኛውን ለማረጋጋት በሚል አልኮል ማጠጣት የደም ዝውውርን ስለሚያፋጥነው መርዙ እንዲሰራጭ መንገድ ይከፍታል።
📚 መረጃው የተወሰደባቸው ምንጮች | References:
- World Health Organization (WHO) - Snakebite Envenoming Guidelines
- Centers for Disease Control and Prevention (CDC) - Venomous Snakes and First Aid
- Mayo Clinic - Snakebites First Aid Treatment
በረከት ከፈኔ-የቀዶ ጥገና ነርስ

በረከት ከፈኔ: የቀዶ ጥገና ነርስ
Telegram: t.me/HakimEthio