cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የእንሴኖ የሱና እቁዎቹ ጀመዓ

✅እውቀት ከመናገርም ከመስራትም ይቀድማል። "ኢማሙል ቡኻሪ" (ረሒመሁላህ)

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
201
Suscriptores
Sin datos24 horas
-27 días
-330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሸዋል በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ ሚሽነሪዎች የማያውቁትን ከመጠየቅ ይልቅ፦ “ዘካህ ከመቶ 2.5% ስጡ የሚል መረጃ የለም፣ ሪባ ማለት አራጣ ማለት እንጂ ወለድ ማለት አይደለም፥ የቁርኣን አወራረድ ሁለት አይነት ነው የሚል መረጃ ከቁርኣንም ከሐዲስም መረጃ የለም” እያሉ ዲስኩራቸውን ሲደሶክሩ ነበር። ለእናንዳንዱ አርስት ከቁርኣና ከሐዲስ ከዚህ ቀደም ምላሽ ሰተናል። ዛሬ ደግሞ፦ “ሸዋልን ጹሙ! የሚል ቁርኣን ላይ የለም” እያሉ ይደሶክራሉ። ሚሽነሪዎች ሆይ! ጮቤ ረግጣችሁ አንባጒሮ አትፍጠሩ። ተረጋጉ! የጅብ ችኩል አትሁኑ! በሰላና በሰከነ መንፈስ ጠይቁ መልስ ይሰጣችኃል። ከሆያ ሆዬ ወደ አንቺ ሆዬ ትንሽ እንኳን እደጉ። የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ዐሥራ ሁለት ወር ነው፥ እነዚህም፦ 1ኛ ወር ሙሐረም 2ኛ ወር ሰፈር 3ኛ ወር ረቢዑል-አወል 4ኛ ወር ረቢዑ-ሣኒ 5ኛ ወር ጀማዱል-አወል 6ኛ ወር ጀማዱ-ሣኒ 7ኛ ወር ረጀብ 8ኛ ወር ሻዕባን 9ኛ ወር ረመዷን 10ኛ ወር ሸዋል 11ኛ ወር ዙል-ቀዒዳህ 12ኛ ወር ዙል-ሒጃህ ናቸው፦ 9፥36 *የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነርሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው*፡፡ إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ከእነዚህ አስራ ሁለት ወራት አንዱ 10ኛ ወር “ሸዋል” ነው፥ “ሸዋል” شَوَّال ማለት “ማንሳት” ወይም “መሸከም” ማለት ሲሆን የወር ስም ነው። ነቢያችን”ﷺ” እንድናደርገው ሙስተሐብ አድርገው ከሰጡት ሱና መካከል ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን መጾም ነው፦ ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 78 አቢ አዩብ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ማንም ረመዷንን የጾመ ከዚያም ከሸዋል ወር ስድስት ቀናትን ያስከተለ ዋጋው ዓመቱን ሙሉ እንደጾመ ነው”*። عَنْ أَبِي أَيُّوبَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ فَذَلِكَ صِيَامُ الدَّهْرِ ‏ የረመዷን ሰላሳ ቀን እና የሸዋል ስድስት ቀን ጾም ጾመን ዓመት እንደጾምን የሚያስቆጥርበትን ስሌት ማወቅ ይቻላል። አምላካችን አላህ አንድ መልካም ሥራ ምንዳው አሥር እጥፍ እንደሆነ በቅዱስ ቃሉ ነግሮናል፦ 6፥160 *”በመልካም ሥራ የመጣ ሰው ለእርሱ ዐሥር ብጤዎችዋ አሉት”*፡፡ በክፉ ሥራም የመጣ ሰው ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡ مَن جَاءَ بِالْحَسَنَةِ فَلَهُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا ۖ وَمَن جَاءَ بِالسَّيِّئَةِ فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ ስለዚህ አንድ መልካም ሥራ አሥር ብጤዎች ካሉት የረመዷን አንድ ወር መጾም የአሥር ወር ምንዳ አለው። 1×10=10 ወር ይሆናል። እንዲሁ የሸዋል ስድስት ቀን መጾም የስድሳ ቀን ምንዳ አለው፥ ስድስት ቀናት በአሥር እጥፍ ስድሳ ቀን ነውና፥ 6×10=60 ቀን ወይም 2 ወር ይሆናል። ሲጠቀለል የረመዷን የአሥር ወር ምንዳ እና የሸዋል ሁለት ወር ምንዳ 12 ወር ይሆናል፥ 10+2=12 ወር ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ 12 ወር መሆኑ እሙን ነው። አሊያም ሠላሳ የረመዳን ቀን እና ስድስት የሸዋል ቀን በአስር ምንዳ ሲባዛ 360 ቀናት ይሆናሉ፥ 36×10= 360 ይሆናል። አንድ ዓመት ደግሞ ጨረቃ ወፀሐይ"lunisolar" የሆነው የአይሁዳውያን አቆጣጠር 360 ቀናት መሆኑ ቅቡል ነው። አምላካችን አሏህ በተከበረ ቃሉ፦ “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት” ይለናል፦ 59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ ስለዚህ ኢሥላም ሰው ሠራሽ ሕግና ሥርዓት ሳይሆን ዐቂደቱ አር-ረባንያህ ነው። ይህንን ስንል አርቲ ቡርቲና ቶራ ቦራ የሆነ ስሑትና መሪር የቡና ወሬ ይዘን ሳይሆን ቁርኣንና ሐዲስን ያማከለ ስሙርና ጥዑም ማስረጃ ይዘን ነው
Mostrar todo...
❗️እናስተውል ❗️ - ሞት እድሜ ና ሁኔታ አይገድበውም እና ቀጣይ ረመዷን ለመሳተፋችን ምንም ዋስትና የለውም። - ምናልባት አላህ ይህ 30ኛ ቀን የወፈቀን ላንተ/ላንቺ መቸረሻ ማሳመርያ እንዲሆንልን ነው። በኸይር ስራ ላይ እንበርታ እንደ ትርፍ ወይም ዋዛ አንየው። - በዒድ ዝግጅቶች ብቻም ግዝያችንን ልናባክነው አይገባም። ማስቀደም ያለብን እናስቀድም !
Mostrar todo...
ዘካተል ፊጥርን የሚመለከቱ ነጥቦች ~ 1- ምንነቱ፦ ሙስሊሞች ከዒደል ፊጥር በፊት ለችግረኞች የሚሰጥ የእህል / የምግብ ሶደቃ ነው። 2- ሑክሙ፦ በሚችል ሰው ላይ ግዴታ ነው። [አልቡኻሪይ፡ 1503] [ሙስሊም፡ 984] 3- በማን ላይ ነው ግዴታው? 3.1. በትንሽ በትልቁ፣ በሴት በወንዱ፣ በሁሉም ሙስሊም በሆኑ የቤተሰብ አባላት ቁጥር የሚወጣ ሶደቃ ነው። 3.2. ገና ያልተወለደ ፅንስ እዚህ ግዴታ ውስጥ አይገባም። 3.3. አንድ ሰው የሌሎችን ዘካተል ፊጥር (ለምሳሌ ከሱ ጋር ያልሆኑ ቤተሰቦቹን ወይም የአገልጋዮችን) ማውጣት ይችላል። ግን እንደሚያወጣላቸው ማሳወቅ ይገባል። 4- ምን ያህል አቅም ባለው ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው? ለራሱም ለቤተሰቡም ለዒድ ሌሊትና ቀን የሚበቃ ቀለብ ባለው ላይ ግዴታ ነው። 5- ለማን ነው የሚሰጠው? የእለት ጉርስ ለሌለው ድሃ። 5.1. ዘካ እና ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው ለሙስሊም ብቻ ነው። ሌሎች ሶደቃዎችን ሙስሊም ላልሆኑ አካላት መስጠት ይቻላል። 5.2. ሑክሙን ባለማወቅ ወይም የሚግገባው አካል ስለማያገኙ ለሰራተኞቻቸው ዘካተል ፊጥር የሚሰጡ ሰዎች አሉ። ሰራተኞቻቸው የማይገባቸው ከሆኑ የተሰጣቸውን ለሚግገባቸው አሳልፈው መስጠት ይኖርባቸዋል። 6- የሚሰጡ የእህል / የምግብ አይነቶች፦ ተምር፣ ዘቢብ፣ አይቤ እንዲሁም በሃገር በአካባቢው ለቀለብነት የሚውሉ፣ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይበላሹ መቆየት የሚችሉ የእህል / የምግብ አይነቶች ሁሉ ይገባሉ። ምክንያቱም "ከምግብ አንድ ቁና" የሚል ሐዲሥ አለና። [አልቡኻሪይ፡ 1508] [ሙስሊም፡ 985] በዒዱ እለት መመገብ የሚችሉት አይነት ቢሆን ተመራጭ ነው። 7- መጠኑ፦ አንድ ቁና (ሷዕ) ነው። በአራቱ ኸሊፋዎች ዘመን በዚህ መልኩ ነው ሲፈፀም የኖረው። 7.1. በራስ ፈቃደኝነት ጨምሮ ቢሰጥ ይቻላል። 7.2. የሚሰጠው መጠን በኪሎ ግራም:- በሐዲሥ የመጣው በስፍር ስለሆነ የክብደት መለኪያ ስንጠቀም እንደ እህሉ አይነት መጠኑ ይለያያል። ወደ ኪሎ ሲቀየር ዱቄት ላይ 2.5 ኪሎ አቅራቢያ ይመጣል። ይሄ የአንድ ሰው መጠን ነው። 10 ቤተሰብ ያለው ሰው 25 ኪሎ ማለት ነው። 8- ጊዜው፦ ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻ እለት ተጠናቆ የዒዱ ሌሊት ሲገባ ነው። ልብ በሉ! በኢስላማዊው አቆጣጠር የአንድ እለት ቀዳሚው ክፍል ቀኑ ሳይሆን ሌሊቱ ነው። 8.1. ከዒድ ሶላት ማሳለፍ አይፈቀድም። ረስቶ በጊዜው ያላወጣ ሰው ሲያስታውስ ቢሰጥ ወንጀል አይኖርበትም። አውቆ ወይም ችላ ብሎ ወቅት ካሳለፈ ግን ወንጀል ላይ ወድቋል። ቢሆንም ግን የድሃ ሐቅ ስለሆነ ወቅቱ ቢያልፍም ሊያወጣ ይገባል። 8.2. ተቀባዩ በመራቁ የተነሳ በእለቱ ለማድረስ የሚቸገር ሰው "የት ላድርግልህ?" ብሎ ይጠይቅና ከወከለበት ቦታ ያደርግለታል። በዚህን ጊዜ በእለቱ ባይወስድም ችግር የለውም። 8.3. አስቀድሞ መስጠት ይቻላል? ለሚሰበስቡ አካላት አንድ ቀን ሁለት ቀን ቀድሞ መስጠት ይቻላል። ከዚህ ውጭ በጊዜው መስጠት እየተቻለ ቀደም ብሎ መስጠት አይገባም። ነገር ግን በእለቱ ለመስጠት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲኖሩ ትንሽ ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል። እንዲሁም በውጭ ሃገራት ያሉ ሰዎች ለሚሰጥላቸው አካል ቀደም ብለው መላክ ይችላሉ። ወኪሉ ግን በተቻለ መጠን ወቅቱን መጠበቅ አለበት። 9. ከቤተሰብ ርቃችሁ ለምትገኙ ተማሪዎች ወላጆቻችሁ ዘካተል ፊጥር የማያወጡላችሁ ከሆነና የማውጣት አቅሙ ካላችሁ ዘካተል ፊጥር ማውጣት እንዳትረሱ። 10. አስገዳጅ ወይም አንገብጋቢ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር በገንዘብ ማውጣት አይቻልም። ዝርዝሩ በቀጣይ የሚታይ ይሆናል ኢንሻአላህ። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Mostrar todo...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

Photo unavailableShow in Telegram
🔑      ስንት ቁልፍ ትወስድ ነበር??          አንድ በወርቅ የተሞላ ሳጥን አለ እንበል; …… አስር የመክፈቻ ቁልፍ ተሰጥቶህ   "ከእነዚህ አስር ቁልፎች በአንዱ ይከፈታል ሞክር" ብትባል ስንት ቁልፍ ትወስድ ነበር??   አንድ? ሁለት? ሶስት? ወይም አምስት ቁልፎች ብቻ ይዘህ ትሄዳለህ❓ ወይንስ………       አስሩንም ወስደህ ትሞክራለህ??        👇   👇   👇   👇   👇   👇 💎«ለይለተል ቀድር ከአስሩ ሌሊቶች በአንዱ ይገኛል» ሲባል ልክ እንዲሁ ነው። በየትኛዋ ሌሊት እንደሆነ አይታወቅም። እናም………   አስሩንም ሌሊቶች ላይ ወጥረህ 🕌ስገድ      📖ቅራ         🤲ለምን!!
Mostrar todo...
قال ابن القيم رحمه الله : "لو كانت ليلة القدر بالسنة ليلة واحدة لقمت السنة حتى أدركها .. فما بالك بعشر ليال .. ኢብኑል ቀይም : ለይለተል ቀድር (የምትገኘው ) በአመት አንዲት ሌሊት ውስጥ ቢሆን እሷን ለማግኘት አመቱን በሙሉ በቆምኩ (ሌሊት በሰገድኩ .. አላህን በለመንኩ ) ነበር ... በአስር ሌሊቶች ውስጥ ሆናማ ነገርህ እንዴት ይሆናል ?! ይላሉ * የተቀሩትን ሌሊቶች አላህን በመፍራት የቻልነውን ሁሉ እናደርግ አላህ ይምራን https://t.me/Muhammedsirage
Mostrar todo...
ሱብሀናላህ !! እነዚህ መፅሀፎች ምነኛ ያማሩ እና የተዋቡ ናቸው ፣ የሱናን ብርሀን ሲገልፁ ፣ ሽርክን ሲያንናኮታኩት 🚦አሕባሽ ስታየው መፈርጠተጧ ኢብኑ ተይሚያን ፣ ተውሂድ እና ሽርክ ፣ መውሊድ ፣የተሰኙትን መፅሀፍ 🚦ሀጁሪዮች መቆሚያ መቀመጫ ያጡላት አልበያን 🚦ኢኽዋኖች አይለያየንም ብለው የዘመሩለት መውሊድ ትክክለኛ ማንነቷ የተብራራባት መውሊድ የተሰኘው ኪታብ 🚦ለተሚዮች በእሳት ሊያቃጥሉ ደፋ ቀና ያሉላት እነዚህ ብርቅዬ መፅሀፎች ኢንሻአላህ ገና እስክትቃጠሉ እስክታሩ ድረስ ይበተናሉ  ሁሉም ደፋ ቀና ይላል ሀቅን ለመናድ ፣ ሀቅ ግን አንገቱን ደፍቶ አይሸማቀቅም በ አላህ ይረዳል የባጢል  አካላቶች  ለመናድ ቢታገሉም አይችሉም ። በቃ ሀቅ እዲህ ነው  قال الإمام ابن عثيمين رحمه الله " الحق منصور وإن قلّ أتباعه والباطل مخذول ولو كثر أتباعه https://t.me/Abuzekeriya01
Mostrar todo...
1 ለሊት >1000 ወር አሏህ ከዋለልን ተቆጥረው ከማያልቁ ፀጋዎቹ መካከል አንዱ በዚህ የተከበረ ወር የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ውስጥ የምትገኘው የመወሰኛይቱ ለሊት አንዷ ናት።ይህች ለሊት አሏህ ዘንድ ያላትን ክብር ከሚገልፁልን ነገራቶች መካከል ቁርኣን ውስጥ ስለ እርሷ ደረጃ ብቻ የሚያትት አንድ ሙሉ ምዕራፍ ማግኘታችን ነው።ይህ ምዕራፍ "የውሳኔ ምዕራፍ" ይሰኛል።አሏህ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ስለ መወሰኛይቱ ለሊት እንዲህ ሲል ያብራራልናል إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ለሊት አወረድነው፡፡ وَمَا أَدْرَاكَ مَا لَيْلَةُ الْقَدْرِ መወሰኛይቱም ለሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ? لَيْلَةُ الْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ መወሰኛይቱ ለሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ( ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡ سَلَامٌ هِيَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ الْفَجْرِ እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡ ★አሏህ በለይለቱል ቀድር የሚሰራ አንድ ዒባዳ በሌላ ጊዜ አንድ ሺህ ወር ( ከ 83 አመት በላይ) ከሚሰራ ዒባዳ ይበልጣል እያለን ነው።ይህች ለሊት አሏህ ከወፈቀን በእርሷ ውስጥ የምንሰራው ዒባዳ ምናልባትም እድሜ ልካችን ከምንሰራው ዒባዳ ይበልጣልና ጎበዝ አንሳነፍ‼ ሌላ ምዕራፍ ላይ ደሞ የተባረከች ለሊት ሲል ይጠራታል إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةٍ مُّبَارَكَةٍ ۚ እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ለሊት ውስጥ አወረድነው፡፡ [አድዱኻን ፤ 3] መልዕክተኛውም (ዐለይሂሶላቱ ወሰላም) ስለዚህች ለሊት ሲናገሩ እንዲህ ይሉናል ✔"من قام ليلة القدر إيمانا واحتسابا غُفِر له ما تقدم من ذنبه" متفق عليه "ለይለተል ቀድርን በአሏህ ያመነና አጅሩንም ከአሏህ የከጀለ ሆኖ ቆሞ ያሳለፈ የሆነ ሰው ያለፈው ወንጀል ይማርለታል" [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል] ※ ቆሞ ማሳለፍ ማለት ዚክረ መዘከር፣ ቁርኣን መቅራት፣ዱኣ ማድረግ፣ሶላት መስገድ.............ወዘተ የገራልንን ዒባዳ እየሰራን ማሳለፍ ማለት ነው ✔"ﺗَﺤﺮُّﻭﺍ ﻟﻴﻠﺔَ ﺍﻟﻘَﺪْﺭ ﻓﻲ ﺍﻟﻌَﺸْﺮ ﺍﻷﻭﺍﺧِﺮ ﻣﻦ ﺭﻣﻀﺎﻥَ " ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱُّ ﻭﻣﺴﻠﻢ ‏ "ለይለተል ቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ተጠባበቁ" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) ✔ "ﺗَﺤﺮُّﻭﺍ ﻟَﻴﻠﺔَ ﺍﻟﻘَﺪْﺭِ ﻓﻲ ﺍﻟﻮَﺗْﺮ ﻣﻦ ﺍﻟﻌَﺸﺮِ ﺍﻷﻭﺍﺧِﺮِ ﻣﻦ ﺭﻣﻀﺎﻥَ " ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱُّ ‏ "ለይለተል ቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ፣ በጎዶሎዎቹ ቀናት ተጠባበቁ" [ቡኻሪ ዘግበውታል] ★ ለይለቱል ቀድር ላይ ልናደርገው የሚገባን ዱዓ ሲያመላክቱን እንዲህ ይሉናል ✔عن ﻋﺎﺋﺸﺔَ ﺭﺿِﻲَ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋﻨﻬﺎ ﻗﺎﻟﺖ : ﻗﻠﺖُ : ﻳﺎ ﺭﺳﻮﻝَ ﺍﻟﻠﻪ، ﺃﺭﺃﻳﺖَ ﺇﻥْ ﻋﻠﻤﺖُ ﺃﻱَّ ﻟﻴﻠﺔٍ ﻟﻴﻠﺔُ ﺍﻟﻘﺪْﺭ؛ ﻣﺎ ﺃﻗﻮﻝ ﻓﻴﻬﺎ؟ ﻗﺎﻝ : ﻗﻮﻟﻲ : ﺍﻟﻠَّﻬُﻢَّ ﺇﻧَّﻚ ﻋﻔُﻮٌّ ﺗﺤﺐُّ ﺍﻟﻌﻔﻮَ، ﻓﺎﻋﻒُ ﻋﻨِّﻲ ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ ‏ ﻭﺍﺑﻦ ﻣﺎﺟﻪ እናታችን ዓኢሻ እንዲህ ትለናለች "አንቱ የአሏህ መልዕክተኛ (ዐለይሂሶላቱ ወሰላም) ሆይ ለይለቱል ቀድር የትኛው ለሊት እንደሆነ ካወቅኩኝ ምን እንደምል ንገሩኝ " አልኳቸው እሳቸውም "አሏህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ፤ ይቅር ማለትን ትወዳለህ ፤ ይቅር በለኝ" በዪ አሉኝ (ቲርሚዚና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል) ስለዚህ በእነዚህ ለሊቶች ይህንን ልብ የሚነካ ዱዓ ከማብዛት አንዘናጋ‼‼ እናም ወንድሞቼ አላማዬ ማስረጃዎችን መደርደር ብቻ አይደለም ፤ ይልቁንስ ሀሳቤ እነዚህ ማስረጃዎችን ከልብ ተረድተን ወደ ተግባር በመቀየር ከዚህ ትልቅና ምናልባትም በሕይወታችን ድጋሚ ላናገኘው ከምንችለው የአሏህ ችሮታ እንቋደስ ነው። ማንቂያ ደውል‼ 1— ለይለቱል ቀድርና ሰማይ ላይ የሚታይ ብልጭታ ምንም የሚያገናኛቸው ነገር የለም።ለይለቱል ቀድር ማለት እንደሌሎች ለሊቶች ከመጝሪብ ሰኣት ጀምሮ እስከ ንጋት ድረስ የሚቆይ እንጂ ብዙ ሰዎች እንደሚመስላቸው ሰማይ ላይ አንዴ ብልጭ ብሎ የሚጠፋ ቅፅበታዊ ክስተት አይደለም።በዚህም መሰረት አንዳንድ ሰዎች በተለይም ገጠራማ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች ለይለቱል ቀድርን ለመጠባበቅና ብልጭ ሲል እጃቸውን ዘርግተው ዱዓ ለማድረግ በማሰብ ለሊቱን እሳት እያቀጣጠሉ በረንዳ ወይም ውጪ ላይ ማሳለፍ ምንም አይነት ሸሪዓዊ መሰረት ያለው ተግባር አይደለምና ልናስተምራቸው ይገባል። 2—ለይለቱል ቀድር የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት ውስጥ በጎዶሎዎቹ ቀናት ላይ ተጠባበቁ የሚለውን ንግግር በመያዝ ጎዶሎ ቀናቶችን ብቻ እየጠበቁ መስጂድ መሄድ ተገቢ አይደለምና እንስተካከል።ምክንያቱም ለይለቱል ቀድር ከሌሎቹ ቀናቶች በበለጠ መልኩ ዒባዳ ላይ የምንጠነክርበት ለሊት እንጂ ሌሎቹን ለሊቶች ትተን በእርሱ ብቻ ኢባዳ የምንፈፅምበት ለሊት አይደለምና።ከመልዕክተኛውም (ዐለይሂሶላቱ ወሰላም) ፈለግ የተማርነው የመጨረሻዎቹ የረመዷን አስርት ቀናት ላይ ሁሉ ዒባዳ ላይ መበርታትን እንጂ ጎደሎ ቀናቶችን ብቻ መጠባበቅ አይደለም። 3— ለረመዷን አስርቱ ለሊቶች አሏህ በሰላም አድርሶናልና በዒባዳ ላይ የተቻለንን ሁሉ ለማድረግ እራሳችንን እናዘጋጅ።መልዕተኛችን (ዐለይሂሶላቱ ወሰላም) እነዚህን የተከበሩ ለሊቶች በምን አይነት ሁናቴ ያሳልፉት እንደነበረ እንዲህ ተብሎ ተዘግቦልን እናገኘዋለን ✔ ﻛﺎﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ : ﻳﺠﺘﻬﺪ ﻓﻲ ﺍﻟﻌﺸﺮ ﺍﻷﻭﺍﺧﺮ ﻣﺎ ﻻ ﻳﺠﺘﻬﺪ ﻓﻲ ﻏﻴﺮﻩ‏» رواه مسلم "መልዕክተኛው (ዐለይሂሶላቱ ወሰላም) የመጨረሻዎቹ አስርት ለሊቶች ላይ ከሌሎቹ ለሊቶች በበለጠና በተሻለ መልኩ ዒባዳ ላይ ይበረቱ ነበር " [ ሙስሊም ዘግበውታል] ✔« : ﻛﺎﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺇﺫﺍ ﺩﺧﻞ ﺍﻟﻌﺸﺮ ﺷﺪَّ ﻣﺌﺰﺭﻩ، ﻭﺃﺣﻴﺎ ﻟﻴﻠﻪ ﻭﺃﻳﻘﻆ ﺃﻫﻠﻪ ‏". ‏ رواه البخاري ومسلم "መልዕክተኛው (ዐለይሂሶላቱ ወሰላም) የመጨረሻዎቹ አስርት ለሊቶች ሲገቡ ትጥቃቸውን ያጠብቃሉ፤ ለሊቱን በዒባዳ ሕያው ያደርጋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ለዒባዳ ይቀሰቅሱ ነበር" [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል] ስለዚህ እኛም በነዚህ አስርቱ ለሊቶች ከሌላው ጊዜ የተሻለ ነገር ሰርተን ለማሳለፍ እንጣር። አሏህ ለመልካም ነገራቶች ሁሉ ይወፍቀን‼
Mostrar todo...
ውዷ እህቴ !! ይሄ ሁሉ ላንቺ ክብር ሲባል ነው ፤ የማንም ጫት ቃሚና ወጠጤ አፍ መክፈቻ እንዳትሆኚ ፤ እንዲሁም ወንዶች ባንቺ እንዳይፈተኑ ነውና ለመልዕክተኛው ትዕዛዝ ከአሁኑ ሰዓት ጀምሮ ሰምቻለው ታዝዣለው በይ።ልብስሽም ረጅም ፣ ወፍራም ፣ መላ አካልሽን የሚሸፍን ፣ ሰፊ ይሁን።ይህ ሳይሆን ከቀረ ግን የመልዕክተኛውን ትዕዛዝ በመጣስሽ እንዲሁም ወንዶችን በመፈተንሽ ከአሏህ የሆነ ቁጣ በማትረፍሽ "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች " እንደሚባለው ትሆኚያለሽ።ማለትም ሱና የሆነን ነገር እሰራለው(ተራዊሕ እሰግዳለው) ብለሽ አሏህ ሐራም ያደረጋቸውን ነገሮች ሰርተሽ ኪሳራ በኪሳራ ሆነሽ ትመለሻለሽ። እህቴ አሏህ ከዘልዛሎች ይጠብቅሽና ተስተካከዪ እሺ ‼ አሏህ በሁሉም ነገራችን ላይ ለሱ ህግጋቶች ተገዢ ያድርገን‼ ኣሚን
Mostrar todo...
ተራዊሕ ሶላት ላይ እየተለመዱ የመጡ                   ስህተቶች ‼ ➊ ሰፍን ማበላሸት ልክ ሶፍን ማዘበራረቅ ሱና ነው የተባለ ይመስል በተለያዩ መስጂዶች ላይ ተራዊሕ በሚሰግገድበት ሰዓት ቅጥ ያጡ ሰፎችን ማየት እየተለመደ መጥቷል።ይህ ተግባር ሰፍን ማሰተካከል አስመልክቶ የመጡ ሐዲሶችን ካለማወቅ ወይም አውቆም ቦታ ካለመስጠት(የአብዛኞቻችን መርራር ሁኔታ) የመጣ ነው።ያላወቀቱን ለማሳወቅ የረሱትን ለማስታወስ የተወሰኑ ሰፍ ማሰተካከልን አስመልክተው የመጡ ማስረጃዎችን እንይ፦ (1) "ألا تصفون كما تصف الملائكة عند ربها ؟" فقلنا يا رسول الله وكيف تصف الملائكة عند ربها؟ قال" يتمون الصفوف الأول ويترصون في الصف" رواه المسلم መልዕክተኛው ﷺ እንዲህ አሉ ፦ " ( ሶላት ላይ) መላኢኮች ጌታቸው ዘንድ እንደሚሰለፉት አትሰለፉምን? " እኛም " መላኢኮች ጌታቸው ዘንድ እንዴት ነው ሚሰለፉት?" አልናቸው እሳቸውም "የመጀመሪያ የመጀመሪያ ሰፎችን( ከፊት ለፊታቸው ያለውን ሰፍ) ይሞላሉ ፤ በሰፋቸውም ይጥጠጋጋሉ" አሉ (  ሙስሊም ዘግበውታል) (2) "سووا صفوفكم فإن تسوية الصف من تمام الصلاة" متفق عليه "ሰፎቻችሁን አስተካክሉ፤ሰፍን ማስተካከል ሶላትን ከሟሟላት ነው" ( ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) "فإن تسوية الصف من إقامة الصلاة"  "ሰፍን ማስተካከል ሶላትን ቀጥ አድርጎ ከመስገድ ነው" (ቡኻሪ ዘግበውታል) (3) "لتسون صفوفكم أو ليخالفن الله بين وجوهكم"متفق عليه "ሰፎቻችሁን ታስተካክላላቹ ፤ ወይም( የማታስተካክሉ ከሆነ) አሏህ ፊቶቻችሁን ይቀያይረዋል"( ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) ★ "አሏህ ፊቶቻችሁን ይቀያይረዋል" ለሚለው የመልዕክተኛው ﷺ ንግግር ከተሰጡ ማብራሪያዎች መካከል አንዱ "በመካከላቹ አለመግባባትን ይፈጥራል" የሚለው የኡለሞች ማብራሪያ ይገኝበታል። (4) "لا تختلفوا فتختلف قلوبكم"رواه أبو داود "በሰፎቻችሁ አትለያዩ ፤ ልባችሁ ይለያያል"                          (አቡ ዳውድ ዘግበውታል) ስለዚህ እነዚህ ሐዲሶች ውስጥ ከተጠቀሱት ዛቻዎች ለመትረፍ ሰፎቻችንን ቀጥ ማድረግና ማስተካከል ይኖርብናል።ይሞቃል፣ይጨንቃል፣አየር ፍለጋ፣……… ወዘተ በሚል ውሃ የማያነሳ ምክንያት ሰፎችን አናዘበራርቅ ፤ መስጂድ ሳይሞላ በረንዳ ላይ አንስገድ። ➋ ቁርኣንን ከኢማም ጋር  አብሮ ማንበብ ድምፅ ከፍ ተደርጎ ቁርአን የሚነበብባቸው ሶላቶች ላይ  ተከታዮች ማድረግ ያለባቸው ፋቲሃን ከቀሩ በኋላ የኢማሙን ቂርኣት ማዳመጥ ነው።ከፋቲሃ በኋላ ኢማሙ ረጅምም ሱራ ይቅራ አጭር ፤ የምናቀውንም ይሁን የማናቀውን ሱራ ይቅራ እኛ ማድረግ ያለብን ሓሳባችንን ስብስብ አድርገን የኢማሙን ቂርኣት ማዳመጥ ነው።አንዳንድ ሰዎች ኢማሙ ረጅም ሱራ የሚቀራ ከሆነ እነሱ የሚያውቁትን አጭር ሱራ እየደጋገሙ ይቀራሉ።ይህ ትክክል አይደለም።የኛን ቂርኣት ትተን የኢማሙን ቂርኣት ነው ማድመጥ ያለብን።ፋቲሃ ከቀራን በኋላ ዝም ብለን የኢማሙን ቂርኣት የምናዳምጠው እኛ የማናቀውን ሱራ ሲቀራ ብቻ ሳይሆን የምናቀውንም ሱራ ሲቀራ ጭምር ነው። ➌ መስጂድ ውስጥ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማውራት ብዙ ሰዎች ተራዊሕ እየተሰገደ ሲደክማቸው እረፍት ይወስዳሉ።ይህ ምንም ችግር ያለው ነገር አይደለም ፤ ችግሩ ያለው ለእረፍት በተቀመጥንበት ሰአት ዝም ብሎ ቁጭ ከማለትና የኢማሙን ቂርኣት ከማዳመጥ ይልቅ የተለያዩ አጀንዳዎችን እያነሱ የሰጋጆችን ቀልብ በሚሰርቅ መልኩ ማውራቱ ነው።ይህ ተግባር አንድ ሊሰግድ መስጂድ ከገባ ሰው የሚጠበቅ አይደለምና ከዚህ ድርጊት እንቆጠብ።"አተርፍ ባይ አጉዳይ" አንሁን ‼ መስጂድ የሄድነው ሰግደን ወደ አሏህ ለመቃረብ እንጂ ሰጋጆችን አዛ አድርጎ የአሏህን ቁጣ ተሸክሞ ለመመለስ አይደለም። ስለዚህ የቻልነውን ያህል ሰግደን ሲደክመን ዝም ብለን በመቀመጥ እረፍት ማድረግ ነው ያለብን።አሏሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ቁርኣን ሲቀራ ምን ማድረግ እንዳለብን ሲነግረን እንዲህ ይለናል ፦ " وَإِذَا قُرِئَ الْقُرْآنُ فَاسْتَمِعُوا لَهُ وَأَنصِتُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ " ቁርኣንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡( አል አዕራፍ 204) ከዚህም ብሶ ሶላት እየተሰገደ መስጂድ ወስጥ ሶሻል ሚዲያን መጠቀም ደግሞ ምንኛ የከረፋ ሸይጧናዊ ተግባር ነው!? ለመሆኑ ሁለመናችንን የሚከታተል አምላክ እንዳለን ዘነጋን?? ለአሏህ ቤት ያለንስ ክብር ምን ዋጠው!? ከቶውኑ የሙስሊም ተግባር ነውን!?... ብቻ አሏህ ይድረስልን!!ቁጭ ብሎ ጠብቆ ጠብቆ ኢማሙ ሩኩዕ ሲያደርግ እየሮጡ መጥቶ ሶላቱን መቀላቀል። እንዲህ የምናደርግ ሰዎች ከዚህ ተግባራችን ልንታቀብ ይገባል ምክንያቱም መልዕክተኛው ﷺ እንዲህ ይሉናልና ﻳﻘﻮﻝ ﷺ : " ﻻ ﺻﻼﺓ ﻟﻤﻦ ﻟﻢ ﻳﻘﺮﺃ ﺑﻔﺎﺗﺤﺔ ﺍﻟﻜﺘﺎب" متفق عليه "ፋቲሃን ላልቀራ ሰው ሶላት የለውም" ( ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል) ስለዚህ ቁጭ ብለን ጠብቀን ጠብቀን ኢማሙ ሩኩዕ ሊያደርግ ሲል እየሮጥን ሄደን  ፋቲሃን ሳንቀራ ሩኩዕ ብናደርግም ረከዓውን አላገኘነውም ነው ሚባለው ፤ ስለዚህ ያንን ረከዓ መድገም ይጠበቅብናል። ከመጀመሪያው ጀምረን ሶላቱን ከኢማሙ ጋር መከተል ካልቻልን ማድረግ ያለብን  ቢያንስ ቢያንስ ፋቲሃ ለመቅራት የሚያስችለን ያህል ጊዜ አስቀርተን ወደ ሶላቱ እንቀላቀል።ያለበለዚያ ግን ረከዓውን መድገም ይኖርብናል። ማስታወሻ‼ ከቤቱ እየመጣ ወይም ዉዱዕ ለማድረግም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ከመስጂድ ወጥቶ ሲመለስ ኢማሙን ሩኩዕ ላይ ቢያገኘውና  ሳይነሳ ከደረሰበት መቀላቀል ይችላል።ረከዓውንም የግድ ድገም አንለውም ምክንያቱም ፋትሃውን የተወው ሆን ብሎ አይደለምና።ነገር ግን ይህም ሆኖ ሳለ ረከዓውን ደግሞ ቢሰግድ ምንም ችግር የለውም ፤ ይልቁንም ከኡለሞች ልዩነት ለመውጣት የተሻለ ይሆናል።ረከዓውን በግዴታነት ይድገም የሚባለው ሆን ብሎ ቁጭ ብሎ ጠብቆ ኢማሙ ለሩኩዕ ሲወርድ ተንደርድሮ የሚመጣውና ሶላቱን የሚቀላቀለው ነው። ➎ ሽቶ ተቀባብቶ ፤ ተገላልጦ መውጣት( ሴቶችን ብቻ የሚመለከት ነው) በመሰረቱ ሴቶች መስጂድ ከሚሰግዱት ይልቅ ቤታቸው ውስጥ ተሰትረው የሚሰግዱት ሶላት ይበልጣል።ነገር ግን መስጂድ ሄደን እንሰግዳለን ካሉ አንከለክላቸውም።ባይሆን ወደ መስጂድ ሲሄዱ እንዴት መሄድ እንዳለባቸው አስመልክቶ መልዕክተኛችን ﷺ እንዲህ ይላሉ ፦ "ﻻ ﺗﻤﻨﻌﻮﺍ ﺇﻣﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﺴﺎﺟﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﻟﻜﻦ ﻟﻴﺨﺮﺟﻦ ﻭﻫﻦ ﺗﻔﻼﺕ" رواه أبو داود "የአሏህ ሴት ባሮችን  የአሏህን መስጂዶች አትከልክሏቸው( ከመሄድ) ፤ ነገር ግን እነሱ "ተፊላት" ሆነው ይውጡ" (አቡ ዳውድ ዘግበውታል) ✔ "ተፊላት" ለሚለው የመልዕተኛው ﷺ ንግግር ከተሰጡት ማብራሪያዎች መካከል —ሽቶ ሳይቀቡ —ወንዶችን የሚፈትን የትኛውንም ነገር ሳይጠቀሙ — ከቃሉ ቋንቋዊ መሰረት ተነስተው መጥፎ ጠረን ያለው፣ ማድቤት በሚሰሩበት ልብስ ይውጡ የሚል ትርጉም ሰጥተውታል።
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.