cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አቡ ዑመይር

ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ (ሱረቱል ነህል 125) ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Yabekeir ስህተት ባያችሁም ጊዜ አርሙኝ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 798
Suscriptores
+124 horas
+97 días
-3430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

قال ابن السماك رحمه الله ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ሰማክ እንዲህ ሲል መከረ الدنيا كلها قليل ዱንያ ባጠቃላይ ትንሽ ናት والذي بقي منها قليل ከሷም የቀረው ደሞ ትንሽ ነው والذي لك من الباقي قليل ከቀረው ደሞ ያንተ የሆነው ትንሽ ነው ولم يبق من قليلك إلا قليل ከትንሽህ ደሞ አልቀረህም ትንሽ ቢሆን እንጂ سير أعلام النبلاء / 8/330. ሲየር አዕላም አኑበላእ 8/330
Mostrar todo...
4
ነገ ማክሰኞ የአሹራ ቀን ስለሆነ የቻልን ሁላችንም እንፁም
Mostrar todo...
👍 7🥰 2 1
"ኢብኑ ተይሚያህ ሞቱ ፊታቸውንም ገልጬ ሳምኩዋቸው ከተለያየናቸው ጊዜ በላይ ሽበት ወሯቸዋም ዱአ ሚያረግለት ሷሊህ ልጅን አልተወም ነገር ግን ዱአ ምታረግለትን ሷሊህ ኡማህ ትቷል" ኢብኑ ከሲር
Mostrar todo...
👍 5 2
"ልጆቻቹን መስጂድ በመሄድ ላይ ቁርአንን በመሃፈዝ ላይ አበረታቱዋቸው ለናንተም የነሱን አምሳያ አጅር አለላቹ" ነጅሙ ሻም ወዛሂዱሃ ናሲሩ ዲን አል አልባኒ
Mostrar todo...
🥰 5👍 4
አሹራ ማለት ቃላዊ ትርጉም፦ "አሸራ" ወይም 1ዐኛው ከሚል የመጣ ሲሆን ይህም ሊሆን የቻለው በሙሃረም ወር በ1ዐኛው ቀን ስለዋለ ነው። የሙሃረም ወር በሂጅራ አቆጣጠር የአመቱ የመጀመሪያ ወር ነው። --> የሙሀረምን ወር ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) የአላህ ወር ነው ሲሉ አልቀውታል። --> ከረመዳን በመቀጠል አላህ (ሱ•ዐ) ዘንድ በላጩ ፆም የሙሀረም ፆም ነው። የአሹራን ቀን በተመለከተ፦ [ ከኪታብ እና ከሱና ] * ኢብን አባስ (ረ•ዐ) እንደተናገሩት፦ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) ወደ መዲና እየመጡ እያለ በአሹራ ቀን የሁዲዎች ሲጾሙ አይተው። ለምንድነው የምትጾሙት ብለው ጠየቋቸው። የሁዲዎቹም፦ አላህ (ሱ•ወ) ነቢ ሙሳን (ዐ•ሰ) እና የበኒ ኢስራኢል ልጆችን ከጠላቶቹ ነጃ ያደረጋቸው ቀን በመሆኑ እና ነቢ ሙሳም (ዐ•ሰ) ይህን ቀን በመፆማቸው ነው አሏቸው። ነብዩም (ሰ•ዐ•ወ) ነቢ ሙሳ (ዐ.ሰ) ከእናንተ ይልቅ ለእኛ የቀረበ ነው አሉ። ያንንም ቀን (የሙሃረም 1ዐኛውን ቀን) ጾሙ ሙስሊሞችም እንዲጾሙ አዘዘ። [ ሀዲሱን ሰሂህ አል ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ ] * የአሹራ ቀን ቅዱስ በሆነው በሙሀረም ቀን ውስጥ ያለች ቀን ናት ለዚህም ማስረጃው፦ ነብያችን (ሰ•ዐ•ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "በአመት ውስጥ 12 ወራት አሉ፡፡ ከ12ቱ ውስጥ 4ቱ ወራት ቁድስ ናቸው፡፡ እነሱም ዙልቂዳ፣ ዙልሂጃ፣ ሙሃረም እና ረጀብ ናቸው።" [ሰሂህ አል ቡኻሪ] * በጃሂሊያህ ዘመን ቁራይሾች የአሹራን ቀን ይፆሙ ነበር፡፡ ይህንን የሚያደርጉትም የነብዩላሂ ኢብራሂም (ዐ•ሰ) ሱና ስለነበረ ነው፡፡ * የአሹራ ቀን ነቢ ሙሳ (ዐ•ሰ) እና የበኒ እስራኢል ልጆች ከፊርዓዎን ነጃ የወጡበት ቀን የአሹራ ቀን ነበር ለዚህም ማስረጃው በሱረቱል አሽ-ሹዓራህ የሰፈረው የአላህ ቃል ነው፦ 63. ወደ ሙሳም «ባሕሩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክንበት፡፡ (መታውና) ተከፈለም፡፡ ክፍሉም ሁሉ እንደ ታላቅ ጋራ ኾነ፡፡ 64. እዚያም ዘንድ ሌሎችን አቀረብን፡፡ 65. ሙሳንም ከእርሱ ገር ያሉትንም ሰዎች ሁሉንም አዳን፡፡ 66. ከዚያም ሌሎቹን አሰጠምን፡፡ * የአሹራ ቀን የነብዩላሂ ኑህ (ዐ•ሰ) መርከብ በጁዲ ተራራ ያረፈችበት ቀን ናት። ኢማሙ አህመድ እንዘገቡት የነብዩላህ ኑህ (ዐ•ሰ) መርከብ በጁዲ ተራራ ላይ ያረፈችበት ቀን የአሹራ ቀን ነበር፡፡ * እናታችን አዒሻ (ረ.ዓ) እንደዘገቡት፦ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) የአሹራን ቀን መፆማቸውን ጠቅሳለች፡፡ [ ሰሂህ አል ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ ] * ከረመዷን ቀጥሎ የአሹራን ቀን መፆሙ ትልቅ አጅር ያላት ቀን መሆኗን በሀዲስ ተገልጾአል፡፡ ነብዩ ሙሀመድ (ሰ•ዐ•ወ) እንተናገሩት ከረመዷን ቀጥሎ የሙሀረም ወር 1ዐኛው ቀን መጾም ትልቅ ደረጃ አለው፡፡ [ሰሂህ ሙስሊም ] * ኢብኑ አባስ (ረ•ዐ) እንደተናገሩት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) ከረመዷን ወር ውጪ ለአሹራ ጾም ቅድሚያ ይሰጡ ነበር፡፡ [ ሰሂህ አል ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ ] * የአላህ መልዕክተኛ (ሰ•ዐ•ወ) እንደተናገሩት አንድ ሰው በአሹራ ቀን ቤተሰቡን ለማስደሰት ሰደቃ ከሰጠ አላህ (ሱ.ወ) አመቱን በሙሉ በሱ ላይ በረከቱን ያበዛለታል። [ አል በይሃቂ ዘግበውታል፡፡ ] * የአሹራን ቀን መጾም ትናንሽ ወንጀሎችን ሙሉ በሙሉ ያብሳል ለዚህም ማስረጃው፦ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንደተናገሩት የአሹራን ቀን የጾመ ወንጀሉ ይማርለታል።[ በሰሂህ ሙስሊም ] * ኢማሙ ሻፊዕ፦ 9ኛው (ነገ ሰኞ) እና 1ዐኛውን (ማክሰኞ) ቀን መጾም ተወዳጅ መሆኑን ገልጸዋል። ነብዩ (ሰ•ዐ•ወ) 1ዐኛውን ቀን ብቻ መጾማቸውንም አላህ ለቀጣዩ ካደረሷቸው 9ኛውንም እንደሚፆሙ ተናግሯል፡፡ ማሳሰቢያ፦ የአሹራን ፆም መፆም ግዴታ ባይሆንም 9ኛውን እና 1ዐኛውን ቀን መጾም ተወዳጅ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው። @አቡ ዑመይር ( ቀን, ሐምሌ 28, 2014 ) https://t.me/Abu_Umair2
Mostrar todo...
አቡ ዑመይር

ወደ ጌታህ መንገድ በብልሃትና በመልካም ግሳጼ (በለዘብታ ቃል) ጥራ፡፡ (ሱረቱል ነህል 125) ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ @Yabekeir ስህተት ባያችሁም ጊዜ አርሙኝ።

😍 3👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
فَلَمَّا تَرَاءَى الْجَمْعَانِ قَالَ أَصْحَابُ مُوسَى إِنَّا لَمُدْرَكُونَ ሁለቱ ጭፍሮችም በተያዩ ጊዜ የሙሳ ጓዶች «እኛ(የፈርዖን ሰዎች) የሚደርሱብን ነን» አሉ፡፡ قَالَ كَلَّا إِنَّ مَعِيَ رَبِّي سَيَهْدِينِ (ሙሳ) «ተዉዉ! ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው፡፡ በእርግጥ ይመራኛል» አለ፡፡(አሹዓራእ 61–62) ...ሁሌም አትርሳ ከፊትህ ምን የገዘፈ እንቅፋት ቢኖር... ከኋላህ የምድር አምባገነን ከነ አጋዦቹ ቢያሳድድህ ...የሚመራህ የሚያግዝህ አላህ ከሁሉም በላይ ኋያል ብርቱ ነው ሁሉንም እንድትወጣው ያስችልሃል ...ሙሳን አስተዋልከው ከፊቱ ካለው ባህር እና ከኋላው ከሚያሳድደው አምባገነን በላይ ትኩረቱ የሚያግዘው አላህ ላይ ነበር ...ትኩረትህ ምኑ ላይ ነው? ...ሰዎች ሊያስፈራሩህ... ልትወጣው የማትችለው እንቅፋት ከፊትህ እንዳለ ሊነግሩህ ይችላሉ... በሙሉ ልብ እና እርግጠኝነት ንገራቸው ጌታዬ የእንቅፋትን ባህር ሁሉ ሰንጥቆ ያሻግረኛል አላህዬ ከኔ ጋር ነው በላቸው...
Mostrar todo...
5🔥 1🥰 1
| | እናታችን እንዲህ ትላለች "ነፍሶቻቸውን ለመልክተኛው በሚሰጡ ላይ በጣም እቀና ነበር እንዲህም እል ነበር ሴት ልጅ ነፍሷን ትሰጣለችን? ቅናት 😁
Mostrar todo...
3🥰 2
ዑለማዎች 3 አይነት ናቸው 1ኛ፦ ዑለማኡል ሚለህ ፦ ማለትም የእስልምና ለእልምና ሚተጉ ኡለማዎች 2ኛ፦ ዑለማኡ ደውለህ ፦ ማለትም ኡለማኡ ሰላጢን ፈታዋቸውን እና እውቀታቸውን በሱልጣኖች ፍላጎት ላይ የገነቡ ሱልጣኖች ሚፈልጉትን ያያሉ ፍርዳቸውን በሱልጣኖቹ ስሜት ላይ ያረጋሉ መረጃዎችን አንገቱን አንቀው ሱልጣኖች በሚወዱት መልኩ ያረጋሉ ከጊዜያት በፊት የሰጡትን ፈትዋ ሱልጧኑ እንዲጥመው ብለው ኢጅትሃድ በምትባል ቅፅል የዳቦ ስም ይቀይሩዋታል እነዚህ የእስልምና ሳይሆን የሱልጣኖች ኡለማዎች ናቸው 3ኛ፦ ዑለማኡል ኡማህ ፦ እነዚህ ደግሞ ፈታዋቸውን በህ ዝቡ ፍላጎት ላይ ይገነባሉ ህ ዝቡ ይህንን ሀላል እንዲሆን ይፈልጋል? ሀላል ያረጉታል ሀራም እንዲሆን ይፈልጋል? ሀራም ያረጉታል ፨ 2ኛዎቹ እና 3ኛዎቹ እስልምናን ያፈርሳሉ ኡመትን ያዋርዳሉ ዙልምን ያነግሳሉ ሃቅን ይቀብራሉ በስተመጨረሻም ግን በዱንያም በአኼራም ይዋረዳሉ ፨ 1ኛዎቹ ለስልምና ጌጥ ናቸው አብሪ ኮከብ ናቸው እስካሉ ድረስ ምድር በነሱ ታጌጣለች ይሰቃያሉ በዟሊሞች ይታሰራሉ ይገደላሉ ቢሆንም ግን ለሙእሚን ኩራት ናቸው ! ዑለማዎች በትልቁ ሊጠነቀቁት ሚገባው ነገር ግምባር ቀደሙ ከሱልጣኖች መራቅ ነው ወደ ሱልጣኖች መግባት ሚያዘወትርን መጠርጠር ግድ ነው ምክንያቱም መልክተኛው አቡ ዳውድ ቲርሚዚ አህመድ በዘገቡት ዘገባ እንዲህ ብለዋል "ወደ ሱልጣኖች በር የመጣ ፈተና ላይ ወድቋል" ዩኑስ ኢብኑ ዑበይድ ደግሞ እንዲህ ይላሉ "ሱልጣኖችን እና የቢድአ ባልተቤቶችን አትቀማመጡ" ጁሙዐን በሰለዋት እናሳልፍ
Mostrar todo...
👍 4
~ከጀርባችሁ ሆነው ስለ እናንተ መጥፎ ወሬ ስለሚያወሩ ሰዎች አትጨነቁ፡፡ ከጀርባችሁ የሆኑት እኮ በምክንያት ነው።ስለ እነሱ ማሰብና ለወሬያቸው ምላሽ መስጠት ማለት እነሱ ወዳሉበት ወደ ኋላ መመለስ ማለት ነው፡፡ ወደ ፊት!!
Mostrar todo...
9🥰 2
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.