cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
587
Suscriptores
Sin datos24 horas
+77 días
+2930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mana keetii eebbifamne Barruu keerraa nyaanne dhugne Mana  keetii eebbifamne Nu hin gatini nuti keeti Bakka nuyi deemnu hundatti Bakka kana dhufuun keenyaa Fedha keeti wal arguun keenyaa Nu eebbisi nuyi ijoollee keeti Adda nun baasin samii irratti Gatii dadhabbii bu'aa hojii keenyaa Utuu ati hin jirre eessaan as geenya Bu'aa ba'ii heddu argine Guyyaa ulfaataa siin darbine Ebbaaf uumtee nu eebbifte Barruu keetiin nu ceesifte Warra sin barre of barsiisi Daandii dhugaatti deebisi Ammas abdiin keenya eenyu Sirra adda bane eessa hin geenyu Mana keetti nu dhabini Ibsa keenyaas hin dhaamsini         ==•|•==
Mostrar todo...
👎 1
በአሰበ ተፈሪ ማህበረ ቅዱሳን ስያስተምር የነበረው የአንድነት ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች አስመረቀ ። በምርቃቱም ላይ የማህበሩ ሰብሳቢ ዲ/ን ዳንኤል ሞጎስ ተማሪዎች ከዝ ከወጡ በኋላ በሄዱበት ሁሉ ቤተክርስቲያን ጎን እንድቆሙ እንድሁም በተለያየ በሄዱበት ቦታ በወረዳ ማዕከላት በሰንበት ቤት በሰበካ ጉባዔ ገብቶ እንድ አገልግሉ መልዕታቸውን አሳልፏል። የሐደራ መስቀል በመስጠት በያሉበት ሁሉ እናንተ ጎን ነን ብሏል። 👇👇👇👇👇👇
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ሐምሌ 4/2016 #ወንጌላዊዉ_ቅዱስ_ዮሐንስ 👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱስ ዮሐንስ ስም ለምናመሰግንበት ለወንጌላዊዉ ለፍቁረ እግዚእ ቅዱስ #ዮሐንስ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን 👉በመጀመሪያው ቃል ነበረ፣ቃልም #በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፣ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፣ቃልም ስጋ ሆነ ዮሐ1፥1-14 👉ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ የተለያዩ ስሞች አሉት ከነዚህም ጥቂቶቹ ✝️ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ✝️ ፍቁረ እግዚእ ✝️ ታኦሎጎስ ✝️ አቡቀለምሲስ ✝️ ቁፅረ ገፅ ✝️ ዮሐንስ ዘንስር 👉 #ቅዱስ_ዮሐንስ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ በአንድ ቤት ልጅ ሆኗት 15 ዓመት የኖረ ቅዱስ አባት ሐዋርያ ነዉ የአለሙን ገዢ ወልዳ ያሳደገች በፀጋ ተሞላታ ተቀድሳ የኖረች እናታችን #ማርያምን በእናትነት የተቀበለ ወንጌላዊው #ቅዱስ_ዮሐንስ በረከት እና ፀሎቱ አይለየን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
Mostrar todo...
ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡ ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡ አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡ የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቀፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡ እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡ በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳ እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡ ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡ የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡ ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’ ብዬ ላመስግነው፡፡ ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡ አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡ የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ” ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የብርሃን እናት - ገፅ 305-308 👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Mostrar todo...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

▶W𝙖𝙭𝙖𝙗𝙖𝙟𝙟𝙞𝙞 30 ▶Ayyaana Waggaa Yohaannis Cuuphaa Baga Geessan!!! ▶Waa'ee Qulqulluu Yohaannis Cuuphaa Dhugaa kana beektuu? ➠Seenaa Dinqisiisoo, qabsuura fi jireenya Yohaannis Cuuphaa ✍️Qulqulluu Yohaannis cuuphaan qulqulloota kaan irraa seenawwan adda ta’ee fi baay’ee nama dinqu qaba. Eebbi qulqulluu Yohaannis cuuphaa nu irra haa buluuti, dhugaa qulqullicha Yohaannis waa muraasa kitaaba qulqulluu irraatifii waan manni kiristaanaa kenna dabalataan barsiiftu akka armaan gadiitti dhugaawwan ajaa’ibaa sinii dhiyeessa: ▶Qulqulluu Yohaannis Cuuphaan ➝1. Haatii fi abbaan isaa erga dulloomanii,yeroon daa’ima argachuu isaanii darbee booda isa argatan(Luq 1:18) ➝2. Missiraachoo ergamaatiin dhalate,maqaan isaas ergamaadhan mogga’e (Luq 1:13) ➝3. Osoo gadaamessa keessa jiru afuurri qulqulluudhan guutame(Luq 1:15) ➝4. Osoo gadaamessa keessa jiru ennaa sagalee Dubroo Maariyaam dhagahutti ni utaale (Luq 1:41) ➝5. Gooftaan mataa isaatiin warra dubartoota irraa dhalatan hundumarraa(Gooftaa Iyyasuusii gaditti) kan caalu isa ta’uusa jecha isaa hin haalamne sanaan dhugaa baheeraafi.Kuni eenyufuu hin dubbatamne. (Mat 11:11) ➝6. Nama ta’ee osoo jiru Waaqa Ilma(Iyyasuus Kirstoosin) kan cuuphe Yohaannis isadha. Mat 3:15 ➝7. Uffatni isaa fi sooratni isaa kan namootarraa adda ture. Mat 3:4 ➝8. Hamma waggaa 30tti gammoojjii keessa jiraate ➝9. Akka abbootni mana kiristaanaa barsiisanitti mataansaa erga muramtee boodee gammoojjii Arabiyaa keessatti waggaa 15 barsiifte ➝10. Gooftaa Iyyasuusiin firooma dhiigaa qabu.(Luq 1:36) ➝11. Sirbituu kan turte intalli Heerodiyaadaa, mooticha waan gammachiifteef, mootichi gammadee ennaa “maalan si ‘shallama’ jedhee ishee gaafatutti, “mataa Yohaannis cuuphaa irraa muri naa kenni” jetteen. Sababa kanaan mataan Yohaannis cuuphaa mana hidhaa osoo jiru mataansaa muramee ‘waciitiidhaan’ dhiyaatee kennameef. Yaa daba namaa, osoo waa meeqa qabeenya meeqa kan ishee fayyadu mooticharraa gaafachuu dandeessu,hammeenyaan mataa Yohaannis cuuphaa gaafatte. (seenaa isaa Wangeela Marqos 6:16) irraa dubbisadhaa. ➝12. Biyya keenya keessatti xaballi maqaa qulqulluu kanaan burqu seenaa heddu hojjechaa jira.Dhukkubsataa heddus fayyisaa jira. Eebbi Qulqulluu Yohaannis cuuphaa nurra haa bulu! 👇👇👇👇👇👇👇👇share join godha https://t.me/othodox12
Mostrar todo...
ተዋሕዶ ሀይማኖቴ TEWAHIDO AMANTAA KOO❤️

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ለማግኘት join አርጉ♥ Barumsa ortodoksii tewahidoo ta’e fi Farfannaa ta’ee fi gorsaa Abbota argachuuf join godha .

†  እንኳን ለስደተኛው ሊቀ ዻዻሳት "አባ ቴዎዶስዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  †
🕊   †  አባ ቴዎዶስዮስ   †   🕊 ጻድቁ ሊቀ ዻዻሳት ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ከልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ በመንኖ ጥሪት የሚኖር ደግ ሰው ነበር:: ያ ዘመን መለካውያንና ልዮናውያን [ክርስቶስን ፪ [2] ባሕርይ የሚሉ] የሰለጠኑበት ዘመን ነበር:: በአንጻሩ ደግሞ ተዋሕዶን የሚያምኑ ሊቃውንትና ምዕመናን ቁጥራቸው የተመናመነ ነበር:: ችግሩ ግን ይህ ብቻ አልነበረም:: በጊዜው ተዋሕዶን አምኖ መገኘት እስከ ሞት የሚደርስ ዋጋንም ያስከፍል ነበር:: ለዚሕም ነው ሮማውያን ሃይማኖትን በግድ ለማስለወጥ ከነገሥታቱ ጋር የተቆራኙት:: ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጋግራ ደሴት ውስጥ ከተገደለ በሁዋላ በግብፅ የተሾሙ ሊቃነ ዻዻሳት አብዛኞቹ መከራና ስደትን ቀምሰዋል:: ትልቁን ቦታ ግን አባ ቴዎዶስዮስ ይወስዳል:: አባ ቴዎዶስዮስ ለእስክንድርያ [ግብፅ] ፴፫ [33] ኛ ፓትርያርክ ነው:: እረኝነት [ዽዽስና] እንዳሁኑ ዘመን ሠርግና ምላሽ አይደለምና ገና እንደ ተሾመ የቀረበለት ጥያቄ አንድ ነበር:: "ተዋሕዶን ትተህ መለካዊ ትሆናለህ ወይስ የሚከተልብህን ፍርድ ትቀበላለህ?" አሉት:: ይህንን ያሉት ከንጉሡ ዮስጢያኖስ የመጡ መልእክተኞች ነበሩ:: መልሱ ፈጣን ሆነባቸው:: "እኔንም ሆነ ሕዝቤን ከቀናችው እምነታችን በምንም ልትለዩን አትችሉም" አላቸው:: በዚህ ምክንያት በቀጥታ ግዞት [ስደት] ተፈረደበት:: ወደ በርሃ ሲያግዙት ካህናት : መምሕራንንና ምዕመናንን አደራ ብሏቸው ነው የሔደው:: መናፍቃኑ እሱን ካሰደዱ በሁዋላ ሕዝቡን ለመቀየር ብዙ ደክመዋል:: ግን ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም አደርነትን የማይረሱ ደጋግ መምሕራን ነበሩና ነው:: በዚያ ላይ አባ ቴዎዶስዮስ ጦማር [መልእክት] በየጊዜው ይጽፍላቸው ነበር:: እጅግ ብዙ ከሆኑት መልእክቶቹ የተወሰኑት ዛሬም ድረስ ሃይማኖተ አበው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ:: በዚሕ አስቸጋሪ ዘመን መልካም ነገሮችም ነበሩ:: ቀዳሚው ማሕቶተ ተዋሕዶ ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ ሲሆን ፪ [2] ኛው ደግሞ የንጉሡ ሚስት የተባረከችው ታኦድራ ናት:: አባ ቴዎዶስዮስ በግዞትና በስደት ሳለ ንግሥቲቱ ትራዳው : ምዕመናንንም ትንከባከብ ነበር:: ቅዱስ ያዕቆብ ከሊቀ ዻዻሱ ዘንድ ክህነትን ተቀብሎ ከሶርያ እስከ ምድረ ግብጽ ስለ ተዋሕዶ ሕልውና ተጋድሏል:: ምናልባትም ከሐዋርያው ቅዱስ ዻውሎስ በሁዋላ በፈሊጥ ክርስትናን በማስፋፋት ቀዳሚ አባት ነው:: [በነገራችን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማዕተብ ማሰርን ያስተማረ አባትም ነው] ፪ [2] ቱ [አባ ቴዎዶስዮስና ቅዱስ ያዕቆብ] ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ስለ ደከሙ የዘመኑ ምዕመናን በስማቸው "ያዕቆባውያን እና ቴዎዶስዮሳውያን" ተብለው ተጠርተዋል:: አባ ቴዎዶስዮስ ግን ሲታሠር ሲፈታ : ሲሰደድ ሲመለስ ብዙ ተሰቃየ:: ሕዝቡን ግን በመልካም እረኝነት ጠብቆ : ከተኩላ አፍ ታደገ:: በዚህች ቀንም ዐርፎ ተቀብሯል:: በፓትርያርክነት ያገለገለባቸው ዘመናት ፴፪ [32] ዓመታት ሲሆኑ ከእነዚህ ዓመታት ፳፰ [28] ቱ ያለቁት በስደትና በመከራ ነው::
እግዚአብሔር የአባቶቻችን ስደት አስቦ ከነፍስ ስደት ይሰውረን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
†  ሰኔ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩. አባ ቴዎዶስዮስ ሊቀ ዻዻሳት ፪. ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዳይ ፫. ቅዱስ ባስልዮስ ፬. ቅዱስ ባሊዲስ †  ወርኀዊ በዓላት ፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን ፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ] ፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ ፬. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ ፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]
"ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዷችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና::" [ማቴ.፭፥፲] (5:10)
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † 👇👇👇👇👇👇share join https://t.me/othodox12
Mostrar todo...
👍 2 2
ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልአክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ፡፡ ኃጢአት ያደቀቃት በኀዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት፡፡ ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ ‘ያለ ኃጢአት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል?’ ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ፡፡ በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ፡፡ አንቺን ድንግልናን ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጢአት ይጋርደኝ፡፡ አንቺን አምላክን ለመውለድ ያጸናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ፡፡ አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንሰው ፍቀጂልኝ፡፡ የፀነስሁትን የኃጢአት ሃሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ለምኚልኝ፡፡ ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቀፈሽው ነበር፡፡ እኔ ግን ለአንድ ቀን እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጂልኝ፡፡ እርግጥ ነው ወደ እኔ ልጅሽን ይዘሽ ስትመጪ እንደ ቤተልሔም የእንግዶች ማደሪያ የእኔም ልብ የብዙ እንግዳ ኃጢአቶች ማደሪያ ነውና ልጅሽን ለማስተኛት ቦታ የለኝም ብዬ የልቤን በር ልዘጋብሽ እችላለሁ፡፡ በሩን ብዘጋውም ግን ልጅሽ እንደሆነ ‘በደጅ ቆሞ ማንኳኳት’ እንደማይሰለቸው አውቃለሁ፡፡ ራእ.፫፥፳ እኔ ፈቅጄ ባልከፍትለትም እንኳን የድንግልናሽን ማኅተም ሳይከፍት እንደተወለደ የእኔን የተዘጋም ልብ ሳይከፍተው መግባት አይሳነውም፡፡ ስለዚህ ዐመፄና እምቢታዬን ቸል ብለሽ ለልጅሽ ማደሪያ አድርጊኝ፡፡ አንቺ እርሱን ከወለድሽ ወዲያ በታተመ ድንግልና ጸንተሽ እንደኖርሽ ለልጅሽ ማደሪያ ሆኜ ለሌላ የኃጢአት ፅንስ ዳግም ማደሪያ እንዳልሆን ነፍሴን አትሚልኝ፡፡ የወለድሽው መድኃኒት እኔን ዙፋኑ አድርጎ ቢቀመጥ ሰዎች በእኔ እቅፍ ስላለ ብቻ በእኔ ምክንያት እንደ ሰብአ ሰገል እንደሚሰግዱለት በአንቺ ሲሆን አይቻለሁና ሰዎች በእኔ ምግባር ምክንያት ፈጣሪን መስደብ ትተው እጅ መንሻ ያቅርቡለት፡፡ ለልጅሽ በቀረቡ ሥጦታዎች ተከብቤ ከአንቺም ጋር ፦ ‘ጌታ ሆይ ለአንተ የሚሰግዱልህ ሰዎች ዙሪያዬን ከበቡኝ ፤ ለአንተ በቀረቡ ሥጦታዎችም ዙሪያዬን ታጠርኩ’ ብዬ ላመስግነው፡፡ ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሔሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው፡፡ እኔ በልቤ ያነገሥሁት ‘የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ’ ስላልሆነ ሔሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም፡፡ የሔሮድስን ሥልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም፡፡ አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሔሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው፡፡ የልቤን ክርስቶስ ሔሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንደ አንቺ ልሰደድ፡፡ እሱን አቅፌ መከራ ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ፡፡ ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዞር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ” ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የብርሃን እናት - ገፅ 305-308 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/othodox12
Mostrar todo...
የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች

"ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን" 2ኛ ቆሮ. 2:14 This channel is not run by D/n Henok Haile. YouTube

https://www.youtube.com/@Min22111

Telegram Group

https://t.me/D_n_henok_hiyla

Photo unavailableShow in Telegram
✞ ኢትዮጵያዊ ሱራፊ ✞ ኢትዮጵያዊ ሱራፊ ተክለሃይማኖት እስመ ነቢይ ወሐዋርያ ዘተፈነውከ ውስተ ምድርነ ሥጋ መለኮትን ለሰዉት እጆችህ ደመ መለኮትን ለቀዱ ጣቶችህ ለታጠቅከው ቅናት ለደረብከው ካባ ሰላም እንላለን ባርከነ አባ    አዝ= = = = = ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስቅዱስ የሕግ መምህር ኢትዮጲያዊ ጳውሎስ ብጹዕ ሐዋርያ የአምላክ አገልጋይ ወንጌልን በምድር ቅዳሴን በሰማይ      አዝ= = = = = ኢትዮጲያዊ ሱራፊ በምድር ላይ መልአክ መንበረ ሥላሴን በማዕጠንት ያጠንክ አእራጌ ጸሎት ሰማያዊ ካህን ሰባኬ ሃይማኖት በሃይማኖት አጽናን 👇👇👇👇👇👇👇👇
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ነገ ሰኔ 23 ሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው~ እንኳን አደርሳችሁ <=== ሰማዕታት ማለት ምስክር ማለት ነው፡፡ ይኸውም አምላካገችን ክርስቶስ በማቴ ወንጌል ፲:፴፪ ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤በማለት :እንዳስተማረና :በሹሙ በጲላጦስም ፊት “እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል አለው።ዮሐንስ ፲ :፴፯ እነርሱም አምላካቸውን ክርስቶስን በመምሰልና በመከተል :አምላካችሁ ክርስቶስን ካዱ ለጣኦት ስገዱ በሚሉት በዓላውያን ነገሥታት :በዓላውያን መካንንት አደባባይ ሳይፈሩና ሳያፍሩ ስለፈጣሪያቸው :በመመስከር ከመገረፍ ጀምሮ በደንጊያ :እስከ መወገር በእሳት እስከ መቃጠል :በተሳለ ሰይፍ እስከ መቆራረጥ :በአውሬ እስከ መበላት :በመድረስ እስከ መጨረሻው የእስትንፋሳቸው መቃረጥ :ድረስ ስለ ሃይማኖታቸው የመሰከሩ ናቸው ፡፡ከእነዚህ ሰማዕታት አንዱ ሊቀ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው፡፡ በረከቱ ይደርብን     ✝አኮቴት✝
Mostrar todo...
2
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.