es
Feedback
EAES: Educational Assessment and Examinations Service Official

EAES: Educational Assessment and Examinations Service Official

Ir al canal en Telegram

Welcome to the official Telegram channel of the EAES. Get the latest news, announcements, exam schedules, guidelines, results, & resources for students, educators, & institutions. Join us for verified information and timely updates directly from EAES.

Mostrar más
3 225
Suscriptores
+124 horas
+187 días
+8530 días
Archivo de publicaciones
ማስታወቂያ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታል በትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደትን አጠናቋል። ምደባው ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ተከናውኗል። 1. የምደባው ዋና መስፈርቶች 1.1. የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫ የተማሪዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት ሆኖ ተወስዷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በምርጫቸው መሠረት የመመደብ ቅድሚያ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተቻለ መጠን ከመረጧቸው የመጀመሪያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። 1.2. የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅም የእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የተማሪ ቅበላ አቅም በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። በመሆኑም የተማሪው ውጤትና ምርጫ ከዩኒቨርስቲዎች የቅበላ አቅም ጋር በማጣጣም ምደባው ተከናውኗል። 1.3. የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በዩኒቨርሲቲዎቻችን ህብረ ብሄራዊነትን የሚያጸና እና የተማሪዎችን ሚዛናዊ ስርጭት ለማረጋገጥ፦ • 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ፤ • 30 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። በተጨማሪም የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። 1.4. የፆታ ሚዛን በዩኒቨርሲቲዎች የሴትና የወንድ ተማሪዎች ስብጥር ሚዛናዊ እንዲሆን በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። 2. ልዩ ምደባ 2.1. ማየት እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ማየት እና መስማት የተሳናቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርትና የድጋፍ አገልግሎት ሊያገኙ በሚችሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። 2.2. 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ አጠቃላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፣ ላስመዘገቡት የላቀ የአካዳሚክ ውጤት ልዩ ታሳቢነት በመስጠት፣ በመጀመሪያ ምርጫቸው ተመድበዋል። ይህ ልዩ የምደባ አሠራር ተማሪዎቹ በብሔራዊ ፈተናው ላስመዘገቡት የላቀ ውጤት ዕውቅና ለመስጠት እና ከፍተኛ አፈጻጸምን ለማበረታታት የተደረገ ነው። 3. የምደባ ውጤትን ስለመመልከት ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት በመጠቀም ማየት ይችላሉ። የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/view-placement 4. ቅሬታ ስለማቅረብ በምደባው ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት ብቻ ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን። የቅሬታ ማቅረቢያ ማስፈንጠሪያ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints • በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመምጣት የሚቀርብ የምደባ ቅሬታ የማይስተናገድ መሆኑን ተማሪዎችና ወላጆች እንዲገነዘቡ እናሳውቃለን። 5. ማሳሰቢያ ቅሬታ በሚቀርብበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ ነው። በቅሬታ ሂደት የሚቀርቡ መረጃዎችና ሰነዶች ትክክለኛነት የሚረጋገጥ ሲሆን፣ የሐሰት መረጃ ወይም ሰነድ አቅርበው የተገኙ ተማሪዎች ምደባቸው ሊሰረዝ ይችላል። በመሆኑም ሁሉም ተማሪዎች ቅሬታቸውን በእውነተኛና በተረጋገጠ መረጃ ላይ ብቻ በመመሥረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን። የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እያለ፣ በቀጣዩ የከፍተኛ ትምህርት ጉዟችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ መልካም ምኞቱን ይገልጻል። የትምህርት ሚኒስቴር

የ2019 ዓ.ም የሪሚዲያል (Remedial) ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ! ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስች
የ2019 ዓ.ም የሪሚዲያል (Remedial) ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ! ትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸውን የመቁረጫ ነጥብ በይፋ አውጥቷል። በዚሁ መሰረት የመቁረጫ ነጥቡ እንደሚከተለው ተወስኗል፦ 1. መደበኛ ተማሪዎች (General Cut-off Points) 👨‍🎓 ወንድ ተማሪዎች (ተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ): ከ 600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%) 👩‍🎓 ሴት ተማሪዎች (ተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ): ከ 600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%) 2. በልዩ ድጋፍ የሚታዩ ተማሪዎች (Special Support Regions & Conditions) ታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ): ከ 600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች: ከ 600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) ዓይነ ስውራን ተማሪዎች (ማህበራዊ ሳይንስ): ከ 500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%) የመስማት የተሳናቸው ተማሪዎች (ተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ): ከ 600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 🔗 ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገጻችንን ይከታተሉ! @FDRE_EAES_Official

Greetings , You can check your 2018 End-of-Year NGAT EXAM results by visiting the following portal: Portal URL : https://resu
Greetings , You can check your 2018 End-of-Year NGAT EXAM results by visiting the following portal: Portal URL : https://result.ethernet.edu.et Please note: certificate will be available on the portal if you passed the exam. Thank you.

🔔የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆኑ። በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተ
🔔የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ሆኑ። በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች  ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አሳውቋል።  በተያያዘም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ያሳውቃል።  ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡- 📌በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et 📌ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram 📌አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms             የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት  ሁልጊዜ ትክክለኛ የትምህርት ምዘናናነ ፈተናዎች መረጃን ለማግኘት የትምህርት ምዘናና ማህበረዊ ትስስር ገጾችን ይከታተሉ። 📍 https://t.me/FDRE_EAES_Official 📍https://eaes.et 📍https://web.facebook.com/eaes.eaes 📍http://www.youtube.com/@eaes.ethiopia 📍https://x.com/eaesEt

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ። በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.6
+1
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ   ወይም 70, 544 ተማሪዎች የማለፊያ ወጤት ማምጣታቸው ተገለጸ። በዘንድሮው ፈተና ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በተፈጥሮ ሳይንስ ሆኖ ተመዝግቧል። ----------------------------- // ------------------------------- ‎ ‎(ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በማስመልከት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ 12.8 በመቶ   ወይም 70, 544 ተማሪዎች 50% እና በላይ ወጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል። ‎ ‎ባለፈው ዓመት በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 8.9 በመቶ ተማሪዎች ማለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ በዚህ ዓመት የማለፊያውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ከ20 ሺህ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። ‎ ‎በዚህ ዓመት ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ 16.58 በመቶ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 8.33 በመቶ መሆኑንም ተናግረዋል። ‎ ‎በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ከፍተኛ ውጤት 591.64 በወንድ  ፤ 583.03  በሴት  ሆኖ የተመዘገበ  መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ600 ከፍተኛ በወንድ 576.25 በሴት 569.17 ሆኖ መመዝገቡን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1EmG2EkeY7/ @FDRE_EAES_Official

#NGAT_Registration_Extended የተከበራችሁ ዉድ የሁለተኛ ድግሪ አመልካቾች የNGAT መመዝገቢያ ቀን እስከ ራቡዕ መራዘሙንና የመፈተኛ ቦታ/ዩኒቨርሲቲ መቀየር ለምትፈልጉ እስከዛው ቀን የሚቻል መሆኑን ተገልጿል። የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም ተራዝሟል። የመመዝገቢያ ሊንክ 👇 https://ngat.ethernet.edu.et ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ ያስፈልጋል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር ሲሆን፤ በምዝገባ ወቅት በቴሌብር በኩል መክፈል ይጠበቅባችኋል። ምዝገባው በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። የፈተና መስጫ ጊዜው በቀጣይ እንደሚገለፅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡ @@FDRE_EAES_Official

📢 የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ማስታወቂያ! ​📅 የምዝገባ ጊዜ: ​ከ ሀምሌ 15 እስከ ሀምሌ 25 / 2018 ዓ.ም ብቻ! ​🔗 የምዝገባ ሊንክ: ​👉 https://n
📢 የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ማስታወቂያ! ​📅 የምዝገባ ጊዜ: ​ከ ሀምሌ 15 እስከ ሀምሌ 25 / 2018 ዓ.ም ብቻ! ​🔗 የምዝገባ ሊንክ: ​👉 https://ngat.ethernet.edu.et ​⚠️ በጣም አስፈላጊ ማሳሰቢያዎች: ​1️⃣ የፋይዳ መታወቂያ (Fayda ID): ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ቅድመ-ሁኔታ በመሆኑ ከወዲሁ ያዘጋጁ። ​2️⃣ የአገልግሎት ክፍያ: 750 ብር (ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) ሲሆን፣ ክፍያው በምዝገባ ወቅት በቴሌብር (Telebirr) ይፈጸማል። ​3️⃣ የፈተና ጣቢያ: ምዝገባው በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚካሄድ ሲሆን፣ የተመዝጋቢዎች ቁጥር ታይቶ የፈተና ጣቢያው ከምዝገባ በኋላ ይወሰናል። ​4️⃣ የፈተና ቀን: የፈተናው መስጫ ጊዜ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ ዙሮች በሰላም እየተካሄደ አንደሚገኝ ተገለጸ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ያሉ የ
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተለያዩ ዙሮች በሰላም እየተካሄደ አንደሚገኝ ተገለጸ። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ያሉ የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በአብዛኛው በስድስት ዙሮች በበይነ መረብ በተሳካ ሁኔታ በሰላም እየተፈተኑ ይገኛሉ። የተወሰኑ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትና የኮምፕዩተር እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች በአራት ዙሮች በወረቀት ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል። በተያያዘም በትግራይ ብሔራዊ ክልል በበይነ መረብ ለመፈተን ለተመዘገቡ 14,755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23 2018 ዓ/ም ጀምሮ እየተሰጠ ያለ ሲሆን በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15,325 ተፈታኞች ሐምሌ 22-24/2018 ዓ/ም በመቀሌና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በወረቀት እንዲፈተኑ ዝግጅት ተደርጓል። ተፈታኞች ወደመቀሌና አክሱም ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ 20/2018 ላይ በመግባት እና በሐምሌ 21/2018 ዓ/ም ላይ ኦሬንቴሽን በመውሰድ መፈተን የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል። የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል! የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሰኔ 2018 ዓ/ም @FDRE_EAES_Official

የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ነገ ሰኔ 23 ይጀምራል። (ሰኔ 22/ 2018 ዓ.ም )የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ
የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ነገ ሰኔ 23 ይጀምራል። (ሰኔ 22/ 2018 ዓ.ም )የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በ607 የፈተና ማዕከላት በስድስት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። ለፈተናው በድምሩ 563,501 ተፈታኞች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 306,456 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 257,045 የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ናቸው። አገልግሎቱ ለፈተናው የሚያስፈልጉ ሁሉንም ዝግጅቶች ማጠናቀቁንና የፈተና አስፈጻሚዎችን ወደ ፈተና ማዕከላት ማሰማራቱን ገልጿል። ተፈታኞች ወደ ፈተና ማዕከላት ሲቀርቡ የመፈተኛ መግቢያ ካርዳቸውን (Admission Card)፣ የተማሪ ወይም ህጋዊ መታወቂያ፣ በፈተና አስተዳደሩ የተፈቀደ እስክሪብቶ እና ባዶ ወረቀት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ሞባይል ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ፍላሽ ዲስክ፣ ሜሞሪ ካርድ፣ የግል ላፕቶፕ ወይም ታብሌት እና ሌሎች ያልተፈቀዱ መሳሪያዎችን ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አይፈቀድም። ፈተናው በበይነ መረብ በ6 ዙር የሚሰጥ ሲሆን፣ በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 1 እስከ 3፣ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ደግሞ ከሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም ተፈታኞች መልካም እድል እየተመኘ፣ ፈተናውን በመረጋጋት፣ በሥነ ምግባር እና በራስ መተማመን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

Greetings, Your 2018 End-Year Exit Examination result is now available. You can view your result by providing your username a
+2
Greetings, Your 2018 End-Year Exit Examination result is now available. You can view your result by providing your username and download a temporary certificate from the results portal using the link below: Link: https://result.ethernet.edu.et Please note: If you have any complaints regarding your result, you can submit them online while viewing your results, as indicated on the portal. You do not need to come in person to submit a complaint. Thank you.

ማስታወቂያ የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EX
ማስታወቂያ የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EXIT EXAM ፈተናዎች የምሰጥባቸው ቀናት እንደምከተለው የተሸጋሸጉ መሆኑን እናሳውቃለን። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት @FDRE_EAES_Official

ማስታወቂያ የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EX
ማስታወቂያ የሪሜዲያል ፈተና እና የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) የምሰጥበት ቀን የተቀየረ መሆኑ ተገለጸ። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ምክክር በማድረግ የሪሜዲያል እና EXIT EXAM ፈተናዎች የምሰጥባቸው ቀናት እንደምከተለው የተሸጋሸጉ መሆኑን እናሳውቃለን። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት @FDRE_EAES_Official

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል። -------------------------- // ------------------------- (
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል።       -------------------------- // ------------------------- (ግንቦት 07/2018 ዓ.ም) ደጋግሞ መለማመድ የእውቀትን እና የክህሎትን ጉድለት ይሞላል፤ በራስ መተማመንን ያሳድጋል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዚህም ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል። ተማሪዎች ፈተናውን ለመለማመድም በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉም ገልጿል። ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን በየጊዜው ተማሪዎች የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የምንሰጥ መሆኑንም አገልግሎቱ አብራርቷል። በመሆኑም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን። @FDRE_EAES_Official

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል። -------------------------- // ------------------------- (
የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል። -------------------------- // ------------------------- (ግንቦት 07/2018 ዓ.ም) ደጋግሞ መለማመድ የእውቀትን እና የክህሎትን ጉድለት ይሞላል፤ በራስ መተማመንን ያሳድጋል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዚህም ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል። ተማሪዎች ፈተናውን ለመለማመድም በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉም ገልጿል። ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን በየጊዜው ተማሪዎች የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የምንሰጥ መሆኑንም አገልግሎቱ አብራርቷል። በመሆኑም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘና
የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርተፊኬት (12ኛ ክፍል ፈተና) ከሰኔ 24 እስከ ሃምሌ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቆናል። በሌላ በኩል ፦ - የሬሜዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም ➡️ ግንቦት 19 ኢድ አልአድሃ - የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ/ም - የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና (NGAT) ከሃምሌ 29 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም - የመሰረታዊ የንባብና የስሌት ክህሎት ምዘና ጥናትና ምርምር መረጃ መሰብሰብ ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ... ይሰጣል።

#EAES የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና የሚዘጋጅባቸው የትምህርት አይነቶች እና የክፍል ደረጃዎች ይፋ ሆነዋል። ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፦ በተፈጥሮ ሳይንስ
#EAES የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና የሚዘጋጅባቸው የትምህርት አይነቶች እና የክፍል ደረጃዎች ይፋ ሆነዋል። ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፦ በተፈጥሮ ሳይንስ እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ እና ፊዝክስ በማኅበራዊ ሳይንስ እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ እና ኢኮኖሚክስ የመልቀቂያ ፈተናው በየትምህርት አይነቱ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች የሚሸፍን ይሆናል። የዝግጅት አግባቡ 9ኛ ክፍል ላይ የቀድሞው እና የአዲሱ ስርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘት (Common Contents) ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፤ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ያለው በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ይሆናል። የኢኮኖሚክስ የትምህርት አይነት ግን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ሆኖ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን የሚሸፍን እንደሚሆን አገልግሎቱ ጠቁሟል። @

Greetings, Your 2018 Mid-Year Exit Examination result is now available. You can view your result by providing your username a
+2
Greetings, Your 2018 Mid-Year Exit Examination result is now available. You can view your result by providing your username and download a temporary certificate from the results portal using the link below: Link: https://result.ethernet.edu.et Please note: If you have any complaints regarding your result, you can submit them online while viewing your results, as indicated on the portal. You do not need to come in person to submit a complaint. @

#Notice ‼ #NGAT_Registration የድኅረ ምረቃ ፕሮግራም የመግቢያ ፈተና (NGAT) የአመልካቾች ምዝገባ ተጀምሯል! ምዝገባው የሚጠናቀቀው፦ ጥር 14/2018 ዓ.ም ለመመዝገብ የሚከተለውን link ይጠቀሙ 👇 https://ngat.ethernet.edu.et 🔥 አሁን ላይ ምዝገባው ዝግ ስለሆነ ቆይተው ይሞክሩ 👉 ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን ወደፊት የሚያሳውቅ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

ዛሬ ይጠናቀቃል! የተራዘመው የ2018 አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል። የምዝገባ ጊዜው ዛሬ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት የሚያ
ዛሬ ይጠናቀቃል! የተራዘመው የ2018 አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል። የምዝገባ ጊዜው ዛሬ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት የሚያበቃ ይሆናል። የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች እንዲሁም በድጋሜ የምትፈተኑ የግል ተፈታኞች በቀሩት ሰዓታት ምዝገባችሁን አድርጉ።