cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)

♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ) « ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ                  ቁርኣን[ 3:104 ] መወያያ ግሩፓችን ☞ https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
449
Suscriptores
+224 horas
+107 días
+4630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

01:43
Video unavailableShow in Telegram
ቁርአን ልባችን ላይ እንዲቀመጥ ከፈለኝ አካላችንን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም ማጽዳት አለብን! ቁርአን የሚነበብ ብቻ ሳይሆን ለሁለት ዓለም ስኬት የሚያበቃ የህይወት መንገድ ነው። የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ @ https://t.me/Xuqal
Mostrar todo...
ልዩ “ኸበር” - ከ6 ዓመት ሕፃን ዕድሜ የጀመረ የሐጅ ትዝታ ኤንዶኔዥያዊቷ እናት መርየም ሙሐመድ ሙኒር፣ ከሰሞኑ ሳዑዲ ዐረቢያ ተገኝተዋል፡፡ እናት መርየም ሳዑዲ የተገኙት ለዓመታዊው የሐጅ ሥርዐት ክንውን ነው፡፡ የ66 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እናት፣ ከ60 ዓመት በፊት በ6 ዓመታቸው በተመሳሳይ አሁን የተገኙት ሥፍራ ላይ ነበሩ፡፡ ያን ጊዜ ግን ዕድሜያቸው 6 ዓመት ብቻ ነበር፡፡ ክፉ እና ደግ የሚለዩም አልነበሩም፡፡ ወላጆቻቸው ለሐጅ ሲያቀኑ አስከትለዋቸው ነው፡፡ እናት መርየም በ6 ዓመት ዕድሜያቸው ጀምረው በተደጋጋሚ ለሐጅ እና ዑምራ ሳዑዲ ዐረቢያ ተመላልሰዋል፡፡ የሳዑዲ ዜና አገልግሎት እንዳለው ከሆነ ኢንዶኔዥያዊቷ እናት የዘንድሮው ጉዟቸው ለ22ኛ ጊዜ የተከናወነ ነው፡፡ እናት መርየም በእነዚህ ስድስት ዐስርት ዓመታት የቆየ የሐጅ ትዝታቸው ውስጥ፣ የሚያስገርሟቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ ተጠይቀው ነበር፡፡ ኢንዶኔዥያዊቷ እናት አንደኛው ጉዳይ ከሀገራቸው ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ለመጓዝ የመንገዱ ማጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እናት መርየም ከ60 ዓመት በፊት ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ሐጅ ሲጓዙ አሁን እንዳደረጉት በአውሮፕላን አልበረሩም፡፡ ባይሆን አነስተኛ መጠን ያላቸው መርከቦች እየተፈራረቁ አድርሰዋቸዋል፡፡ መርከቦቹ ከኢንዶኔዥያ ተነስተው ሳዑዲ ለመድረስ ሕንድን፣ ዐረቢያ እና ቀይ ባህርን ማቋረጥ ነበረባቸው፡፡ እንደ እናት መርየም አገላለጽ ያን ጊዜ የነበረው ከአምስት እስከ ስምንት ሰዓት የሚፈጅ የሐጅ ጉዞ፣ ከሚበላው ገንዘብ እና ጊዜ በተጨማሪ አደገኛ እና አስፈሪ ነበር፡፡ እናት መርየም ከ60 ዓመት በኋላ ከጃካርታ ሳዑዲ ዐረቢያዋ ቅድስት ከተማ መዲና ለመድረስ 9 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ብቻ በአየር ላይ በአውሮፕላን በርረዋል፡፡ የእናት መርየም ሀገር ኢንዶኔዥያ፣ በዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት እርሳቸውን ጨምሮ 241 ሺሕ ምዕመናንን ወደ ሐጅ ሥነ ሥርዐት ትልካለች፡፡ የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ @ https://t.me/Xuqal
Mostrar todo...
Bilaluna Edris (Xuqal.X.Qafarey)

♡_ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)(ﷺ) « ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ» ﷻ                  ቁርኣን[ 3:104 ] መወያያ ግሩፓችን ☞

https://t.me/+1qmNqy265XoyNGY0

Photo unavailableShow in Telegram
እውቀት ማለት የተሸመደደ ሳይሆን የተጠቀምክበት ነው !        ኢማሙ ሻፊዒይ ረሂመሁላህ
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ለተባበራችሁ ወንድም እና እህቶች ሁሉ አላህ ምንዳችሁን በሰፊው ይክፈላችሁ እናመሰግናለን
Mostrar todo...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
በስም ሳይሆን በመሆን፤በምላስ ሳይሆን በተግባር እንዴት ወንድ እንደሚኾን ያሳዩ ድምቅ መሪ።ሰዎች ግማሾቹ በዐረባዊ ብሔረተኝነት፤ሌሎቹንም በቡድናዊ ወገንተኝነት ተቆላልፈው በታሰሩበት ሰዓት ፐርሺያነታቸውና የሺዓ ቡድን ተከታይነታቸው ዐረብና የሱና ተከታይ የሆኑት የገዛ ወንድሞቻቸውን ከመርዳት እንደማያግዳቸው ያሳዩ ድንቅ ህዝቦች ሐገር መሪ! ሰይድ ኢብራሂም ከስማቸው ድርሻቸውን የወሰዱ ናቸው።በአንዱ ሞት የማይሞት የኡመት ስም ነው! አሏህ በሰፊው ራሕመቱ ይቀበሎት ሰይድ ኢብራሂም ረኢሲ የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ @ https://t.me/Xuqal
Mostrar todo...
👍 3 1
«አንድ ሰው  ከሚኖረው መልካም ነገራት ሁሉ  በላጩ በመከራ የማይንበረከክ ልብን ማግኘት  ዋነኛው ነው» ©أدهم شرقاوي
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
የአፋልጉኝ ጥሪ...... በአፋር ክልል ከወላጆቹ ጋር በሎጊያ ከተማ የሚኖረው ህፃን አፍረሂም ሙሀመድ አብዱ ዛሬ ጠዋት አካባቢ ወላጆቹ ለመልእክት ወደ ሱቅ ልከውት እስካሁን አልተመለሰም። ህፃን አፍረሂም ሙሀመድን ያየ ካለ ከታች ባለው ስልክ ቁጥር (+251910090080)ደውላችሁ ብታሳውቁን ወሮታውን ከፋይ ነን። ቤተሰቦቹ ሼር ሼር ሼር
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#BREAKING የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሁሰይን አሚር አብዱላሂ እና አብሯቸው የነበረው የልዑካን ቡድን በሙሉ በሄሊኮፕተር አደጋው መሞታቸውን የኢራን መንግስት ቴሌቭዥን አስታውቋል! #አልጀዚራ የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ @ https://t.me/Xuqal
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🇮🇷🇺🇸 የአሜሪካ አየር ኃይል ካርጎ የሆነው C-17 ግዙፍ ወታደራዊ አይሮፕላን ከዓመት በላይ ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አዘርባጃን ባኩ በዛሬው ዕለት ማረፉ ተሰምቷል።   የአሜሪካው ወታደራዊ ካርጎ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ራይሲ የተሳፈረበት ሄሊኮፕተር አዘርባጃንን ከመልቀቁ እና ከተከሰከሰበት ጊዜ ጋር መገጣጠሙ ጥያቄዎችን እየፈጠረ ይገኛል። #Ethiopia #Raisi #Iran #Helicoptercrash #SearchOperation #RescueOperation የቴሌግራም ቻናሌን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ @ https://t.me/Xuqal
Mostrar todo...