cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ማኅበረ ቅዱስ ፋኑኤል

Publicaciones publicitarias
204
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
+130 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
♦️አትፎካከሩ♦️...ለምን አልተሳካልኝም ለምትሉ ትልቁ ምስጢር ይህ ነው‼️👉መ/ር ኢዮብ ይመኑ (ተወዳጁ መምህር ) በእምባ የሰበኩት

#orthodox #ethiopia #rama

መለሰልኝ ስሙ ዑራኤል የሚባል መልአክ ወደ እኔ የተላከ ይህ መልአክ መለሰልኝ መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል.፪፥፩ አገራችን ኢየሩሳሌም በጠፋች በሰላሳ ዘመን እዝራ እባል የነበርኩ እኔ ሱቱኤል በባቢሎን ነበርኩ በመኝታዬም እኔ ተኝቼ ነበርኩ ፊቴ ግን ተገልጦ ነበር በልቡናዬም ሐሳብ ይወጣ ይወርድ ነበር ዕዝራ ሱቱኤል.፩፥፩ ነቢዩ ዕዝራ በልቡ አንድ ጥያቄ ነበረ በዚህ ጥያቄ የተነሣም ውስጡ ተወጥሯል ምንም እረፍት የለውም ቀንም ማታም አንድ ጥያቄ በልቡ እየተመላለሰ ነው ያለ በስደት ዓለም ነው በዚች በስደት ሀገር ወገኖቹ እስራኤላውያን እንደሰም እየቀለጡ እንደ ገል እየተቀጠቀጡ እንደጭቃ እየተረገጡ መከራ ይቀበሉ ነበር በዚህ ምክንያት የእስራኤል መከራ መቀበል መገፋት የወገኖቹ ሥቃይ እያሳሰበው እንቅልፍ አጥቶ ያድር ነበር በልቡም እንዲህ የሚል ጥያቄ ነበር እርሱም በባቢሎን የሚኖሩ ሰዎች ኃጢአትና የኛን ኃጢአት በሚዛን መዝን። ወዲያው በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች በፊትህ ያልበደሉ መቸ ነው? ወይም ሕግህን እንደዚህ የጠበቀ ማነው? እያለ የተለያዩ ሐሳቦችን እያሰበ የቀደመውን ኃጥያትና ጽድቅ እያነጻጸረ እንቅልፍ አጥቶ ቢተኛም ሳይተኛ ይኖር ነበር ።ዕዝራ.፩፥፴፬ ለምን ? ባቢሎናውያን ፈጣሪያቸውን ክደው ጣዖት እያመለኩ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እየሠሩ ተድላ ደስታ አግኝተው ምንም ሳይጎልባቸው በሕይወት ይኖራሉ እስራኤላውያን ግን ጥቂት ኃጢአት በመሥራታቸው እንደዚህ በባእድ ሀገር መከራ ይቀበላሉ ለምን ? የእነሱንና የእኛን ኃጢአት መዝን እይ ተመልከት የማን እንደሚበልጥ ሰላሳ ዘመን ሁሉ የሚኖሩት በደስታ ነው የጎደላቸው የለም ለምን ? እያለ ሰላሳ ዘመን ሙሉ ይህን ሐሳብ ሲያወጣ ሲያወርድ ኖሯል በእዚህ ሐሳብ የተነሳም እንቅልፍ አጥቶ ይኖር ነበር ። እንደዚሁ ሁሉ በዚህ ጊዜም ከሚተኛው የማይተኛው ይበዛል የሚተኛውም ጤነኛ እንቅልፍ አያንቀላፋም ልክ እንደ ዕዝራ ፊቱ ተገልጦ ዐይኑ ፈጦ ሐሳቡን ሲያወጣ ሲያወርድ ያድራል ለምን ካልን ዕዝራ ስለ እስራኤላውያን ጉስቁልና ስለ ኢየሩሳሌም ሙስና እንደዚሁ ደግሞ ስለ ባቢሎናውያን ተድላ ደስታ እንቅልፍ እንዳጣ ሁሉ የአሁን ዘመን ሰውም በተለያዩ ምድራዊ ሐሳቦች ተወጥሮ እንቅልፍ ሳያንቀላፋ ሲያወጣ ሲያወርድ ያድራል ። ለምን በውስጡ እሱ የሚያውቀው ሰው የማያቅለት ማንም ሰው የማይመልስለት መልሱልኝ ብሎ እንኳ ጥያዌውን ለሰው ቢነግር ለሰውም ቢያወያየው ይህ ጥያቄ አይመለስም ብሎ በአራት ነጥብ ዘግቶ እረ ተቸግሬአለሁ ድረሱልኝ ቢል እንኳ የሚረዳው የሚደርስለት ስለሌለው ጭንቀቱንም ችግሩንም ሐሳቡንም አምቆ እንቅልፍ አጥቶ የሚያድረውን ቤት ይቁጠረው እንጂ የትየለሌ ነው ። ነቢዩ ዕዝራም እንዴት እንደዚህ ይሆናል ብሎ የእግዚአብሔርን ፍርድ ለማወቅ እየተመራመረ ኃጥአን ተቀምጠው ጻድቃን እንዴት ይፈረድባቸዋል ጎስቋሎች ባቢሎናውያን ተቀምጠው ከባቢሎናውያን የተሻሉ እስራኤል ጥቂት ኃጢአት በመሥራታቸው እንዴት ይጠፋሉ እያለ በሐሳብ ያወጣል ያወርዳል። ከዚህ በኋላ በዚህ ጥያቄ እረፍት ያጣውን የዕዝራን ልብ ለማሳረፍ ሐሳቡን ለማሳካት መልአኩ ዕዝራ ተልኮ መጥቶ እንዲህ አለው ። የልዑል እግዚአብሔር የጌትነቱን ፍርድ መርምረህ ታውቀው ዘንድ ልቡናህ አደነቀን አለው ዕዝራም መልሶ አዎን ጌታዬ አለው ልብ በሉ ጌታየ ያለው መልአኩን ነው እሽ ሦስት ምሳሌዎችን እነግርሃለሁ እነዚህን ከመለስህ እኔም ያንተን ጥያቄ እመልስልሃለሁ አለው ዕዝራም ተስማማ ።መልአኩም እንዲህ ብሎ ሦስት ጥያቄዎችን ጠየቀው 1 እሳቱን በሚዛን መዝነህ አሳየኝ 2 ነፋሱንም በላዳን ይዘህ አሳየኝ 3 ያለፈችዋንም ቀን እንደዛሬዋ አድርገህ አሳየኝ አለው ። ይህንማ ከሴት የተወለደ ሊያደርገው አይችልም አለው መልአኩም አከታትሎ ብዙ ነገሮችን ከነገረው በኋላ በባሕርይህ ያለውን ይህን ካላወቅህ የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዴት ታውቃለህ የእግዚአብሔር የፍርዱን ምስጢር ማወቅ እንደምን ይቻልሃል የምትፈርስ የምትበሰብስ አንተ የማይፈርስ የማይበሰብስ የእግዚአብሔርን ፍርዱን ማወቅ አይቻልህም ብሎ ሲነግረው ይህን በሰማ ጊዜ እርሱም በግምባሩ ፍግም ብሎ ወደቀ ።ዕዝራ.፪፥፰ አዎ የእግዚአብሔርን ፍርድ መመርመር አይቻለንም የእኛ ድርሻ የእርሱን ፍርድ መመርመር ለምን እንደዚህ አደረገ ብለን ብይን መስጠት ሳይሆን የተሰጠንን ሥራ መሥራትና ቃሉን በተግባር መግለጽ ፍርዱን ማድነቅ ነው ጥዋት ሦስት ሰዓት ለመጣውም ስድስት ሰዓት ለመጣውም ዘጠኝ ሰዓት ለመጣውም አስራ አንድ ሰዓት ለመጣውም ዋጋውን እኩል የሚሰጥ እርሱ ነውና ለምን እንደዚህ ሆነ ብለህ መጠየቅ አትችልም።ሲጀመር ምን አቅለብልቦህ ትጠይቃለህ እረ ምጠይቅ ነኝ ብለህ ብጠይቅም አንተ ምቀኛው ነህን ትባላለህ ማቴ.፳፥፩-፲፭ አርፈህ ተቀመጥ ወዳጄ ስትቅለበለብ ያቅለበልብሃል ጹም ተብለሃል ጹም ጸልይ ተብለሃል ጸልይ አምልክ ተብለሃል አምልክ ስገድ። ያንተ ድርሻ ለጌታህ መገዛት እንጂ ፍርዱን መመርመር አይደለም ምክንያቱምና መልካም አባት እርስቱን ለልጆቹ የሚያወርሳቸው እኩል ነውና አንተ በመጀመርያ ነው የተወለድህ ብዙ ውሰድ፥ አንተ ቀጥለህ ነው የተወለድህ አሳንሼ እሰጥሃለሁ ፥ አንተ የመጨረሻ ልጅ ነህ ጥቂት ውሰድ አይልም ሁሉም ልጆቹ ናቸው እኩል ይሰጣቸዋል ከዚህ በኋላ እነርሱ ጠንክረው እየሰሩ ሀብታቸውን ያካብታሉ አንተም ጠንክረህ ሠርተህ ሰማያዊ ሀብትህን አካብት። ማቴ.፮፥፳ የዕዝራን የሰላሳ ዘመን ጥያቄ የመለሰ መልአክ የእኛንም የዘመናት ጥያቄዎቻችንን ወደእኛ ተልኮ መጥቶ ይመልስልን እኛም ጥያቄያችን ተመልሶልን ሐሳባችን ተሳክቶልን እንደ ነቢዩ ዕዝራ እንዲህ ለማለት ያብቃን። ስሙ ዑራኤል የሚባል መልአክ ወደኔ የተላከ ይህ መልአክ መለሰልኝ ። የመለሰለት ጥያቄውን ብቻ ሳይሆን በልቡ መታወክ በሐሳቡ መረበሽ ምክንያት የጠፋውን እንቅልፉንም ጭምር ነው ። አዎ መልአኩ ይመልስላችኋል ሲመልስላችሁም እንዲህ በሉ መልአኩ መለሰልኝ Be ermiyas ✍️ ✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥✨💥
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
"…ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 1ኛ ቆሮ 15፥ 21-22 • ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን • አሰሮ ለሰይጣን ~አግአዞ ለአዳም • ሰላም ~እምይእዜሰ • ኮነ ~ፍስሐ ወሰላም።
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.