cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኢትዮ መረጃ™️

እንኳን ወደ መረጃ ቻናላችን በደህና መጡ ቻናላችን ''ኢትዮ መረጃ'' ይሰኛል በቴሌግራም ያልተለመዱ እና አዳዲስ መረጃወችን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል። ሰላም ለኢትዮጵያ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
218
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በ2016 ዓ.ም የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመከታተል ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ያመለካታችሁ ወይም በሌላ ዩኒቨርሲቲ ፈተና ወስዳችሁ፥ የድህረ-ምረቃ ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ አመልካቶች ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ከህዳር 24 እስከ 26/ 2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። የድህረ-ምረቃ ፈተና (GAT) በየፕሮግራሙ ያለፉ አመልካቶች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ በሁሉም ፕሮግራም ተማሪ መቀበል አለመቻሉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡ ይሁን እንጂ በመደበኛው መርሐግብር በ2ኛ ዲግሪ ቁጥራቸው ሦስት እና ከዚያ በላይ በሆነባቸው አምስት ፕሮግራሞች ትምህርት የምንጀምር መሆኑ ተጠቁሟል። ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር ተማሪ የሚቀበልባቸው የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች፦ - MSc in Agricultural Economics - MSC in Information Technology - MBA General - MSc in Environmental Health - MPH in Nutrition የሚፈለገው ቁጥር ባልተሟላበት ፕሮግራሞች ውስጥ ያላችሁ አመልካቶች የመግቢያ መስፈርቱን ወደምታሟሉበት ፕሮግራም መዟዟር የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። @ethio_mereja1
Mostrar todo...
1
#RUSSIA ሩስያ ባለፈው ሳምንት ማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን #ሕገወጥ በማለት ፈርጃለች። የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዓለም አቀፍ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዷል። ይህ እገዳ ይፋ ከተደረገ በኃላ ባለፈው አርብ ምሽት የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦ ° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች) ° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች ° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ ማካሄዳቸው ተነግሯል። ፖሊስ በርካታ የተመሳሳይ ጾታ ክለቦችን ውስጥ በመግባት የተወሰኑትን ታዳሚዎች አጠር ላለ ጊዜ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ታውቋል። በተጨማሪም የአንዳንዶች ፖስፖርት ተወስዶ ፎቶ እንዲነሳ ተደርጓል ተብሏል። ፖሊስ የምሽት ክበቦች ላይ ዘመቻ ያካሄድኩት " አደንዛዥ እፅ ለመፈለግ ነው " ማለቱ ተነግሯል። ሩስያ ፦ - ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴ ጽንፈኛ ነው በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎች አግዷል። - እግድ የተላለፈው የፍትህ ሚኒስቴር ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ነው። - በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና #የለውም። - በሩሲያ #ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር። - እኤአ 2013 ላይ ከተለመደው ውጪ ያለ ጾታዊ ግንኙነት ላይ የሚደረግ ፕሮፖጋንዳን የሚከለክል ሕግ አውጥታለች። - የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን የሚያመለክቱ ይዘቶች ከመጽሓፍት፣ ከፊልሞች፣ ከማስታወቂያዎች እና ከቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እንዲሰረዙ ተደርገዋል። - በቅርቡ አንድ የሩሲያ የቴሌቪዥን ጣቢያ የፕሮፓጋንዳውን ሕግ ጥሷል ተብሎ እንዳይከሰስ በደቡብ ኮሪያ የፖፕ ሙዚቃ ቪዲዮ ላይ የነበረውን የተመሳሳይ ፆታ መግለጫ የሆነውን ቀለም እንዲለውጥ መገደዱን ገልጿል። መረጃው ከቢቢሲ / አስቶሮዥኖ ኖቮስቲ / ፣ ሮይተርስ፣ አልጀዚራ  የተገኘ ነው። @ethio_mereja1
Mostrar todo...
00:26
Video unavailableShow in Telegram
#እንድታውቁት በልጆች ላይ ሊስተዋሉ የሚችሉ #የልብ_ሕመም ምልክቶች ምንድናቸው ? የልጆች የጤና የማያሳስበው ወላጅ የለም። እነዚህን የሕፃናት የልብ ሕመም ምልክቶችን በማወቅ የልጆችን ልብ "ያዳምጡ"። - በጡት መጥባት ወቅት ማላብና የትንፋሽ ማቆራረጥ - ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ፣ የትንፋሽ ማጠር እና የሰውነት እብጠት - የክብደት እና የቁመት ውስንነት እነዚህ የተዘረዘሩትን ምልክቶች በልጅዎ ላይ ካስተዋሉ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ። ይህ መልዕክት የቀረበው ፤ በኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል ነው። ማዕከሉ በህዝብ እገዛ ለ34 ዓመታት ለ5,000 በላይ ሕፃናት መድረስ ችሏል። አሁንም ከ8000 በላይ ወረፋ የሚጠብቁ ሕፃናት ይጠብቁታል። 6710 ላይ OK ብለው SMS በመላክ በቀን 1 ብር ይለግሱ። @ethio_mereja1
Mostrar todo...
4.52 KB
👍 2
#አህያ🫏 በአዲስ አበባ ከተማ ከተለመደው " የከብት ስጋ ውጪ ህገወጥ እርድ እየተፈፀመ ነው " የሚል ጥርጣሬን ተከትሎ ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ማሳወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል። ህገወጥ እርድ የሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚጣለው ቅጣት መሻሻሉንም ባለስልጣኑ የገለፀ ሲሆን ህገወጥ እርድ የሚፈፀም ወይም የሚያቀርብ ማንኛውም አካል እስከ 15ሺ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልበት አመልክቷል። የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፤ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚደረግን ህገወጥ እርድ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ብሏል። ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጋር በመሆን ህገወጥ እርድን የመቆጣጠርና የማስወገድ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ ፤ ከእንስሳት ዝውውር፣ ግብይትና ዕርድ ጋር በተያያዘ የወጡ ደንቦች ተሻሽለዋል ፤ ደንቦቹን ተላልፈው የተገኙ አካላትም እስከ 15 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ሲል ገልጿል። ከህገወጥ ዕርድ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ በከተማዋ ከተለመደው የከብት ስጋ ውጪ እየተሸጠ ተድርጎ ቢወራም  ከዚሁ ጋር  ተያይዞ ባለስልጣኑ ምንም ጥቆማ እንዳልደረሰው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል። ነገር ግን ባለስልጣኑ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው እንደሆነ አስታውቋል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ በ119 ወረዳዎች እንዲሁም በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለባለስልጣኑ የደረሰው  ጥቆማ አለመኖሩን ገልጿል። በሌላ በኩል ፥ የስጋ ነጋዴዎች " የአህያ ስጋ በአዲስ አበባ እየተሸጠ ነዉ " በሚል ምክንያት የቀድሞ ገበያችን በከፍተኛ ደረጃ ተቀዛቅዟል ሲሉ ለ ' ካፒታል ጋዜጣ ' ተናግረዋል። " በኢትዮጵያ ከተሞች በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ የአህያ ስጋ ለምግብነት እየቀረበ ነዉ " በሚል ተሰራጭቷል በተባለው መረጃ ሳቢያ የዕለት ገበያቸዉ ከቀድሞ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ " ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ ከገበያዉ እንድንወጣ ሊያደርገን ይችላል " ብለዋል። " አሁን እስከ 80 ሺህ ብር የተገዛው ሰንጋ በሬ ወደ ተጠቃሚዎች በሚቀርብ ጊዜ የአህያ ነዉ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እናስተናግዳለን " በዚህ ምክንያት ሳይሸጥ የሚያድርበት ቀናቶች በርካታ ናቸዉ " በማለት ተናግረዋል። ከገቢ አንፃር ምን ያህል አጣችሁ ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸዉ ሁለት የስጋ ሽያጭ ሉካንዳ ቤቶች "ከገቢ አንፃር ብቻ ሳይሆን በፊት ለገበያ የምናቀርበው ሁለት ሰንጋ ከብቶች በህጋዊ መንገድ በቄራ እርድ ተፈፅሞ ቢሆንም አሁን ግን አንዱን በትግል ነዉ የምንጨርሰዉ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ሁኔታዉ አሳስቦናል ያሉት የስጋ ነጋዴዎቹ  ከገቢ አንፃር ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነዉን ማጣታቸዉን ለ 'ካፒታል ጋዜጣ' ገልጸዋል። ከሰሞኑን፤ 'ብሩክ ኢትዮጵያ' የተሰኘ የአህያ መብት ተሟጋች ተቋም በኢትዮጵያ በመንግስት ዕውቅና ተሰጥቶት ስራ የጀመረው የአሰላ የአህያ ቄራ ምንም እንኳን ለውጭ ገበያ ታስቦ ቢከፈትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሰላ አካባቢ ያሉ ስጋ ቤቶችም ስጋውን ለሽያጭ ሲያቀርቡ እንደተገኙ ተናግሯል። በአህያ ቆዳ ንግድ ሳቢያ አህዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ መመናመን እየታየ ነው ብሏል። በመንግስት እውቅና የተሰጠው የአሰላ የአህያ ቄራ በቀን ከ100 - 300 አህዮች ለእርድ ያቀርባል፤ በዚህ የተነሳ ከዚህ ቀደም ከ2 ሺህ እስከ 3 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው አህያ አሁን ከ9,000 እስከ 11,000 ብር እየተሸጠ ነው ተብላል። ለቻይና ባሕላዊ ሕክምና እና ለኮስሞቲክስ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ጄልቲን ‘ኢጂአኦ’ ለማምረት የአህያ ቆዳ ተፈላጊ እንደሆነ ይነገራል። Credit - #Capital #EthioFM @ethio_mereja1
Mostrar todo...
#ትግራይ የትግራይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ፤ ሁሉም የወረዳ ትምህርት ፅህፈት ቤቶች የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ እንዲያካሂዱ አዘዘ። የ12ኛ ክልፍ ፈተና በጥር ወር ውስጥ እንደሚሰጥም አሳውቋል። ኤጀንሲው ህዳር 12/2016 ዓ.ም ለሁሉም የክልሉ የወረዳ የትምህርት ፅህፈት ቤቶች በላከው ሰርኩላር ደብዳቤ እንደስታወቀው ፤ በጦርነቱ ምክንያት ከመላ አገር በትግራይ ዘግይቶ የተሰጠው ፈተና በተማሪዎቹ ላይ የፈጠረው ጫና እንዳይደገም የትምህርት ፅህፈት ቤቶቹ በጥር ወር 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ጨምሮ ሁሉም ቅድመ ሁኔታዎች እንዲያጠናቅቁ ሲል አስገንዝቧል። ኤጀንሲው በምዝገባው ሂደት እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ ፦ ✔ የ8ኛ ክፍል ክልለዊ ፈተና የወሰደበት የምስክር ወረቀት ✔ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ክፍል የተማረበት ውጤት የያዘ ትራንስክሪፕት ✔ በ2011 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የወሰደበት የምስክር ወረቀት፣ ✔ የምሽት ትምህርት ተማሪዎች የ10ኛ ክፍል የምስክር ወረቀትና ተያያዥ ጉዳዮች በሟሟላት ለፈተና ሊዘጋጁ ይገባል ተብሏል። ኤጀንሲው የተጠቀሱት መስፈርቶች ያላሟላ ተማሪ ጥር 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መቀመጥ አይችልም ማለቱ ሰርኩላር ደብዳቤው ጠቅሶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።  በትግራይ ክልል በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በሦስት ዙር ይሰጣል መባሉ አይዘነጋም። በ2012 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪ የነበሩ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ፈተናውን ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም መውሰዳቸው ይታወሳል፡፡ በ2012 ዓ.ም የ11ኛ ክፍል ተማሪ ለነበሩ ተማሪዎች በጥር 2016 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር የመልቀቂያ ፈተናው ይሰጣል የተባለ ሲሆን፣ በግንቦት 2016 ዓ.ም መጨረሻ ደግሞ ሦስተኛው ዙር ፈተናን በ2012 ዓ.ም 10ኛ ክፍል ለነበሩ ተማሪዎች ይሰጣል፡፡
Mostrar todo...
#ትግራይ በትግራይ ክልል ፤ ማንኛውም የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጪ በጫነው ትርፍ ልክ በአንድ ሰው ብር 200 እንዲቀጣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ወስኗል። የክልሉ የመጓጓዣና መገናኛ ቢሮ ትላንት ህዳር 12/2016 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው  ፤ ውሳኔው ይፋ ከሆነበት ሰአትና ቀን ጀምሮ (ማለትም ህዳር 12) የከተማ ታክሲ ፣ ባጃጅና ከከተማ ወደ ከተማ የሚያገለግሉ የህዝብ መጓጓዣዎች ትርፍ ጭነው ከተገኙ በጫኑት ልክ በአንድ ሰው ብር 200 ፣ ከመደበኛ መቀመጫ ውጪ በእቃ መጫና ጭነው የተገኙ በአንድ ሰው ብር 1000 እንዲቀጡ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር በፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ በተፈረመ መመሪያ ውሳኔ ማፅደቁ አስታውቋል።    ከዚህ ባለፈ በመመሪያው ፤ ከመደበኛ መቀመጫ ውጪ ሲጓጓዝ የተገኘ ተገልጋይ በተገኘበት ቦታ እንዲወርድ ይደረጋል ተብሏል።               @ethio_mereja1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር
በ2016 የትምህርት ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ በ187 ተደራሽ ሀገር አቆራጭ መስመሮች ተማሪዎቹን ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለማድረስ ዝግጅት መጠናቀቁን በሚኒስቴሩ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪ እና ተሽከርካሪ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚ ከድልማግስት ኢብራሂም ለኤፍቢሲ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉት በመናኸሪያ ብቻ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡  ተማሪዎቹ ከትራንስፖርት ጋር በተያያዘ ችግር ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ መስመር 9719 ላይ በመደወል ማሳወቅ ይችላሉ ብለዋል፡፡ @ethio_mereja1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#WolkiteUniversity በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2015 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2014 ዓ.ም የመጀመርያ ሴሚስተር በውጤት እና በተለያዩ ምክንያቶች Withdrawal በመሙላት ላቋረጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ህዳር 24/2016 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡ ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➤ መሰናዶ ያጠናቀቃችሁበት ሰርተፍኬት፣ ➤ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ ➤ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውን ኮፒው፣ ➤ አራት 3x4 ፎቶግራፍ፣ ➤ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡ @ethio_mereja1
Mostrar todo...
#AddisAbaba #Update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በውክልና ሰጥቶ የሚያሰራቸው የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶች የትኞቹ ናቸው ? የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ሰኞ ዕለት ካሳለፋቸው ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ የአስተዳደሩ ተቋማትን አገልግሎቶችን ለ3ኛ ወገን ማስተላለፍ የሚለው እንደሆነ ይታወሳል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃል ፤ በካቢኔው ስብሰባ ላይ የተወሰኑ አገልግሎቶቻቸውን በውክልና ለግል ተቋማት እንዲያስተላልፉ ውሳኔ ላይ የተደረሰባቸው የከተማ አስተዳደሩ 5 መሥሪያ ቤቶች እና ሆስፒታሎች መሆናቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህ የከተማ አስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የንግድ፣ የትራንስፖርት እንዲሁም የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮዎች ይገኙበታል ብለዋል። የግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲሁም አሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድ እና ቁጥጥር ባለሥልጣን አገልግሎቶቻቸውን በከፊል ለግሉ ዘርፍ ከሚያስተላልፉት ውስጥ መካተታቸውን ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ስር የሚገኙት የካቲት 12 እና የራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታሎችም የዚህ ዕቅድ አካል ናቸውም ብለዋል። ተቋማቱ ለግሉ ዘርፍ እንዲያስተላልፏቸው የተመረጡት የመንግሥት አገልግሎቶች 46 እንደሆኑ የገለፁት ወ/ሮ ሂክማ  ከእነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ የንግድ ፈቃድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና እድሳት እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩን የግብይት ማዕከላት የማስተዳደር አገልግሎቶች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን ማስተለለፍ ለምን ተፈለገ ? ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ፦ - የተመረጡ አገልግሎቶችን ለግል ተቋማት ለማስተላለፍ የተወሰነው የመንግሥት ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ፍጥነት፣ ጥራት እና ውጤታማነት የተሻለ ለማድረግ ሲባል ነው። - ሕብረተሰቡ ከአገልግሎት ውጤታማነት፣ ከአገልግሎት ተደራሽነት ጋር የሚያነሳቸው ጥያቄዎች አሉ። እነዚህን የአገልግሎት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አንዱ መፍትሄ አውትሶርስ አድርገን የግሉ ዘርፍ እንዲሰራቸው ማድረግ ነው። - ይሄንን ሥራ የሚወስደው የግል ዘርፍ ለትርፍ የሚሰራ አካል ነው። ለትርፉ ሲል ሕብረተሰቡ ጋር የበለጠ ተደራሽ ይሆናል። - መንግሥት ሁሉም ነገር ላይ ትኩረት አድርጎ ላይሰራ ይችላል ፤ እነዚህ አገልግሎቶች ወደ ግል ተቋማት ሲተላለፉ የመንግሥትን የመቆጣጠር እንዲሁም ሕግ እና ሥርዓትን ተግባራዊ የማድረግ አቅምን ጠንካራ ያደርጋል የሚል እምነት አለ። - የተመረጡ አገልግሎቶች ከሚተላለፍላቸው አካላት መካከል #የግል_ባለሀብቶች ይገኙበታል። ባለሀብቶች አገልግሎቱን ተረክበው እንዲሰሩ የሚመረጡት #በጨረታ ነው። - በተጨማሪ አገልግሎቶች ከሚተላለፉላቸው አካላት መካከል ተደራጅተው የሚሰሩ የንግድ ዘርፍ ማኅበራት፤ የተለያዩ አካላት ሊኖሩ ይችላሉ። እነሱም ሥራውን ወስደው መሥራት የሚችሉበት ዕድል ይኖራል። ለወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ለሚሳተፉም ዕድል አለ። - የከተማ አስተዳደሩ የተመረጡ አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን አካላት የሚያስተላልፍ ቢሆንም አገልግሎት አሰጣጡን ይቆጣጠራል። ለምሳሌ ፦ የንግድ ፈቃድ ስታንዳርዶችን የሚያወጣው መንግሥት ነው። የግሉ ዘርፍ ይህንን ስታንዳርድ አሟልቶ ለመጣ ሰው ፈቃዱን ይሰጣል። አውትሶርስ አድርገው አገልግሎቱን ለመስጠት የወሰዱ ተቋማት በስታንዳርዱ መሠረት ‘ሰሩ አልሰሩም’ የሚለውን ቁጥጥር የሚያደርገው እና ፈቃዶችን ቼክ የሚያደርገው መንግሥት ነው። መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው። @ethio_mereja1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለሰባት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። የዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ የምሁራኑን የማስተማር ሥራ፣ የምርምር ተሳትፎ፣ የማህበረሰብ አገልግሎት እና በተቋማዊ ጉዳይ ያላቸውን አስተዋፆ በመገምገም የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው፦ 1. ዶ/ር ኢንጂነር ፍቃዱ ፋፋ 2. ዶ/ር መንበሩ መንገሻ 3. ዶ/ር ኦሉ ኢማኑኤል 4. ዶ/ር ደጀኔ ገመቹ 5. ዶ/ር ደምሰው አመኑ 6. ዶ/ር ቸርነት ቱጌ 7. ዶ/ር አበራ ጉሬ @ethio_mereja1
Mostrar todo...