es
Feedback
Bashewam Primary & Junior School 1-8

Bashewam Primary & Junior School 1-8

Ir al canal en Telegram

Bashewam School Grade 1-8

Mostrar más
2 759
Suscriptores
+124 horas
+117 días
+5830 días
Archivo de publicaciones
የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች ሒሳብ ትምህርት በቡድን ሲማሩ

አዎንታዊ አመለካከት (Optimism) ፡- የቴክኖሎጂ ልማትና መስፋፋት ለሰው ልጅና ለማህበረሰብ ጠቀሜታ አለው የሚሉ ብሩህ ታሳቢዎችን መሠረት ባደረገ ሁኔታ የሚደገፍ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስኬፕቲሲዝም (Skepticism)፡-ሰኬፕቲሲዝም ዕውቀትን ማግኘት አይቻልም፣የቴክኖሎጂ ማህበረሰብ የሚፈጠረው በዘር በሚገኝ ውርስ ነው የሚል አስተምሮ ነው፡፡ አግባብ የሆነ ቴክኖሎጂ(Appropriate technology)፡-ተስማሚ ቴክኖሎጂ በ20ኛው ክ/ዘመን የዳበረና በጣም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የተማከለ መሠረተ ልማቶችንና ከውጭ የሚገቡ ክህሎት የሚጠይቁ ቴክኖሎጂዎችን ከመጠቀም በማቆያ መንደር(the eco-village) ማስቀመጥ ይጠቅማል የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡ ውስብስብ የቴክኖሎጂ ስርዓቶች(Complex Technological Systems)፡ቴክኖሎጂ ችግሮችን መፍቻ ቁልፍ መሣሪያ በመሆኑ ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የራሱን ውስብስብ ባሕሪዎች ማወቅ ይጠበቃል፡፡ ከቀረቡ ቴክኖሎጂዎች ለችግሩ መፍቻ የትኛውን መጠቀም ይሻላል? ሁሉንም? ከፊሉን? ብሎ መጠየቅ ጠቃሚ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ቴክኖሎጂ በጠባቡ/በቁንጽል ይታያል፤ ቴክኖሎጂ የሰዎችን ብልሃት የሚጠይቅ የፈጠራ ሂደት ነው፡፡ ሰዎች ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የሚያስችል ጉልህ ሚና ያላቸው ናቸው፡፡ ተወዳዳሪነት (Competitiveness) ፡-ቴክኖሎጂ በአግባቡ ተግባር ላይ ከዋለ የሣይንስ ሥራዎችን ማስፈጸሚያ መሣሪያ ነው፡፡ ሣይንስ የተደራጀ ተግባር ላይ የሚውልና የሚታይ በመሆኑ ተወዳዳሪ የሆኑ ቴክኖሎጅዎችን መምረጥ የማይታለፍ ተግባር ነው፡፡ ቴክኖሎጂ በመጭው ጊዜ (Future Technology)፡- መጭው ጊዜ በከፍተኛ ቴክኖሎጂና ሣይንስ የሚመሠረት እንደሆነ የቴክኖሎጂ ንድፈ ሃሳብ (Theory of Technology) ያመለክታል፡፡ 4. የሣይንስናቴክኖሎጂ ንፅፅር (Science vs.Technology) ሣይንስና ቴክኖሎጂ አብዛኛውን ጊዜ በመተካካት ጥቅም ላይ ይውላሉ፤ ነገር ግን የሣይንስ ግብ ዕውቀት ማሳደድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ግብ ደግሞ ችግሮችን ለመፍታት ምርት መፍጠርና ለሰው ልጆች ህይወት መሻሻል ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በአጭር አነጋገር ቴክኖሎጂ የሣይንስ ማስፈጸሚያ መሣሪያ ነው፡፡ 5. ማጠቃለያ ሣይንስ በምልከታ ወይም በሙከራ የተደረሰበት የሰው ልጅ ዕውቀት ነው፡፡ መረጃ ውስብስብ እየሆነ መምጣት ምርምሮች በተሻሉ መሣሪያዎችና ተመራማሪዎች በቡድን ሥራ እንዲመሠረት አድርጎታል፡፡ ቴክሎሎጂ የቴክኒክና የክህሎት ጥምረት ላይ ተመስርቶ ሣይንሳዊ ምርምሮችን ማግኛ መሣሪያ በመሆኑ ምክንያታዊ ንድፈ ሃሳብን ፈልጎ በማግኘት የተገኘውን ዕውቀት በቴክኖሎጂ ወደ ተግባር መለወጥ ጊዜው የጠየቀው ግኝት መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ በመሆኑም ሣይንስና ቴክኖሎጂን አጣምሮ መጠቀም ለሰው ልጅ ልማትና ዕድገት ወሳኝ መሣሪያዎች በመሆናቸው ሁለቱንም ማወቅ፣ መተግበርና መጠቀም ብሎም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተደራሽነቱን ማስፋትና የህዝብ ግንዛቤ ፈጠራ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

ሳይንስና ፖሊሲ የሣይንስ ፖሊሲ ሣይንሣዊ ዕውቀትን መተግበር፣ከተፈጥሮ ሣይንስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ያካተተ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ለህዝብ የተሻለ አገልግሎትን እንዴት ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚቻል የሚያመለክት ነው፡፡ የሣይንስ ፖሊሲ አንድ የህዝባዊ ፖሊሲ አካል የሆነ በሣይንስ መስክ ስለተሰማሩ ድርጅቶች፣የምርምር ገንዘብ ድጋፍ፣የቴክኖሎጂ ፈጠራ፣የንግድ ልማት ማስተዋወቅ፣ጤና አጠባበቅ፣አካባቢያዊ ደህንነት፣ ወዘተ የሚመለከት ነው፡፡ መንግሥታት በዘርፉ የተለያዩ የሣይንስ ፖሊሲዎችን ለብዙ ሽህ ዓመታት ያደራጁ ቢሆንም ሣይንስ እንደ አንድ የሙያ መስክ ሆኖ የታየበት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ የሣይንስ ድርጅቶች መፈጠር ዘርፉን በገንዘብ መደገፍ፣ በምሁራን በኩል በኢንዱስረትሪ ዙሪያ የተካሄዱ ምርምሮችን ማጠናከር ለሣይንስ ዕድገት በጎ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ ሣይንስና ህዝብ አጠቃላይ የህዝብን ዕድገት ለመገመት የተከናወኑና የሚከናወኑ ተግባራት ሁሉ ሣይንስን መሠረት አድርገው ነው የሚቀመሩት፡፡ በዚህም የሣይንስ ተደራሽነት፣የህዝብ ግንዛቤ ፈጠራ፣የሣይንስ ግኝቶች አከባበር፣የሣይንሳዊ ጋዜጠኝነት ሥራዎች ሁሉ ወዘተ የሣይንስ ሥራ ውጤትች ናቸው፡፡ የሳይንስ ፍልስፍና መሠረታዊ የሆኑ ሣይንሳዊ መላምቶችን በሣይንሳዊ ዘዴ ለመፈተሸ የምንከተላቸው አሠራሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1. በሁሉም አስተዋይ ታዛቢዎች(rational observers) የጋራ የሆነ ተጨባጭ ዕውነታዎች መኖራቸውን መገንዘብ፣ 2. ይህ ተጨባጭ ዕውነታ በተፈጥሮ ህጎች የሚገለጽ መሆኑ፣ 3. እነዚህ ህጎች በስልታዊ አስተውሎቶችና(Systematic observation) በሙከራ አማካይነት የተገኙ መሆን፣ የሣይንስ ፍልስፍና ይሁንታዎች (assumptions) ትክክል(valid) መሆን አለመሆናቸውን በጥልቅ መመርመርና መረዳትን ይጠይቃል፡፡ እርግጠኝነት እና ሣይንስ (Certainty and Science) አንድ ሣይንሣዊ ንድፈ ሃሳብ በምልከታና በሙከራ (empirical) ሳይረጋገጥ እንደ አዲስ መረጃ ብቻ ከተወሰደና ከተያዘ የተጭበረበረ ወይም ለበለጠ መጭበርበር ክፍት ይሆናል፡፡ ማንኛውም ንድፈ ሃሳብ እርግጠኝነቱ በምልከታና በሙከራ ሳይረጋገጥ መቀበል ለስህተት ይዳርጋል፡፡ ሣይንሳዊ ዕውነት በምልከታና በሙከራ በመፈለግ የሚገኝ እንጂ እርግጠኝነትን (Certainty) በመፈለግ የሚገኝ አይደለም፡፡ ሳይንሳዊ ልማድ(Scientific Practice) አንድ ሥራ በእርግጠኝነት ላይ ተመስርቶ ከተጀመረ ጥርጣሬ ውስጥ ይወድቃል፤ በጥርጣሬም ከተጀመረ አጨራረሱም እርግጠኝነት ላይ ብቻ የተመሠረተ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ለብዙ ሽህ ዓመታት የታወቀንና የነበረን ጉዳይ(ችግር) ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር መለኪያዎችን በመጠቀም መፈታት ይኖርበታል፡፡ መሠረታዊ እና ተግባራዊ ምርምር(Basic and Applied Research) መሠረታዊ ምርምር ዕውቀት ለማግኘት የሚደረግ ፍለጋ ሲሆን ተግባራዊ ምርምር ይህን ዕውቀት በመጠቀም በተጨባጭ ችግሮችን መፍትሔ ለማግኘት የሚደረግ ፍለጋ ነው፡፡ የምርምር ልማድ (Research in practice) መረጃ ውስብስብ እየሆነ መምጣት፣የምርምር መሣሪያዎች ዘመናዊነት፣ምርምር የሚጠይቀው ወጪ የተመራማሪዎች ክህሎትና ስብጥር እያደገ መምጣትና በመሳሰሉት ወሳኝ የሆኑ ምርምሮች በግል ከሚሠሩ በቡድን ተመራማሪዎች ማካሄድ የተለመደ ሆኗል፡፡ ሣይንሳዊ ምርምሮች ዓለምን የለወጡና የወደፊትንም የሕይወት ተስፋ የፈነጠቁ ናቸው፡፡ 3. ቴክኖሎጂ ቴክኖሎጂ ማለት፡- የቴክኒክ፣የክህሎትና የአሠራር ዘዴዎች ስብስብ የሆኑ፤ ምርቶችን፣ አገልግሎቶችን፣ የሣይንሳዊ ምርምሮችን ዓላማ ማስፈጸም የሚያስችል መሣሪያ ነው፣ የዕውቀት ቴክኒክና ሂደት ሲሆን ማሽኖችን፣ኮምፒዩተሮችን፣መሣሪያዎችን፣በፋብሪካ ውስጥ ያሉ መሣሪያዎችን፣ ሲስተሞችንና ቴክኒካዊ ዘዴዎችን እንዲሁም በአጠቃላይ ወይም በተወሰኑ አካባቢዎች ሊተገበር የሚችል (የግንባታ ቴክኖሎጂ፣ የህክምና ቴክኖሎጂ ወዘተ) ተግባሮችን ያካትታል፣ የሰው ልጅ የተፈጥሮ ሃብቶችን ወደ ቀላል መሣሪያዎች ለውጦ መጠቀም ከጀመረበት ጊዜ በተለይም የእሳት መፈጠር፣ ምግብን ድንጋይ ላይ አብስሎ መጠቀም፣ለመጓጓዣ ጋሪ በመጠቀሙ በፍጥነት ተጉዞ አካባቢውን መቆጣጠር በመቻሉ ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ አውሏል፡፡ ቀስ በቀስ የህትመት መሣሪያዎች ስልክ፣ ኢንተርኔት መፈጠር በቴክኖሎጅ የመጠቀም ፍላጎትና ዕድገት እየጨመረ መጣ፡፡ ቴክኖሎጂ የሚለው ቃል ካለፉት 200 ዓመታት ጀምሮ የመጣ ነው፡፡ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን በፊት ቴክኖሎጂ የሚለው ቃል የማይታወቅና እንዲያውም “ጠቃሚ ጥበባት” በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ ቴክኖሎጂ የሚለው ቃል በ20ኛው ክ/ዘመን ከ2ኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ጋር የተፈጠረ ነው፡፡ በ1930ዎቹ ቴክኖሎጂ የኢንዱስተሪ ጥበባትን ማጥናት ብቻ ሣይሆን ራሳቸው የኢንዱስትሪ ጥበባት ቴክኖሎጂ መሆናቸው የተረጋገጠበት ነው፡፡ ቴክኖሎጂ ሰፋ ባለ ሁኔታ ሲገለጽ አዕምሮአዊና አካላዊ ጥረት ተጣምረው ቁሳዊና ቁሳዊ ያልሆኑ ነገሮችን ጠቀሜታ ወዳላቸው ነገሮች መቀየርና መጠቀም ነው፡፡ በዚህ አጠቃቀም ቴክኖሎጂ የዕውነተኛ ዓለም ችግሮችን ለመፍታት ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ መሣሪያዎችና ማሽኖችን ያመለክታል፡፡ ቴክኖሎጂ የሰዎችን ፍላጎትና ዓላማ ማሟላት የሚችል የቴክኒኮች ስብስብ(የቴክኒክ ዘዴዎች፣ክህሎት፣ሂደት፣መሣሪያና ጥሬ ዕቃዎች)፣የሰው ልጅ ዕውቀት ተሰባስበውና ተዋህደው ተፈላጊው ውጤት የሚገኝበት፣ችግሮች የሚፈቱበትና ፍላጎት ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ ቴክኖሎጂ ባህልን የለወጠ ተግባር ነው ተብሎ ሊታይ ይችላል፡፡ ቴክኖሎጂ ሂሳብ፣ሣይንስና ጥበብን መሠረት አድርጎ የህይወትን ጠቀሜታ ያረጋገጠ ነው፡፡ ለአብነትም መገናኛ ቴክኖሎጂ የግንኙነት እንቅፋቶችን በማስወገድ የሰዎችን መቀራረብ በኢንተርኔትና ኮምፒዩተር ላይ ተመስርቶ ለአዲስ የሳይበር ባህል መፈጠር ግኝት ነው፡፡ ሣይንስ፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ (Science, Engineering and Technology) ሣይንስ በምክንያት ላይ የተመሠረተ ቅኝት(Investigation) ወይም ሣይንሳዊ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ያለመ የተፈጥሮ ክስተቶች ጥናት ነው፡፡ ኢንጅነሪግ ዲዛይን በማድረግ መሣሪያዎችን በመስራት የአሠራር ሥርዓትን የተከተለ ብዙውን ጊዜ ተፈጥሯዊ ክስተቶች ላይ የሣይንስ ውጤቶችንና ዘዴዎችን የሚጠቀም ግብ-ተኮር ሂደት ነው፡፡ ቴክኖሎጂ የሣይንስና ኢንጂነሪግ ውጤት ሲሆን በሰዎች ዲርጊት ሁለቱንም ቀድሞ የሚገኝ ሣይንስና ግኝቶችን በዲርጊት የሚያሣይ ነው፡፡ ለምሳሌ ሣይንስ በኤሌክትሪክ ኮንዳክተር ውስጥ የኤሌክትሮን ፍሰትን ነባር መሣሪያዎችን በመጠቀም ማጥናት ይችላል፡፡ ፍልስፍና (Philosophy) ቴክኒሺያኒዝም፡- ቴክኒሺያኒዝም (በቴክኒክ ሥራ የሠለጠነና ብቁ ሆኖ መገኘት) በቴክኖሎጂ ችሎታው ራስን ለማህበረሰቡ ለጋሽ አድርጎ የማየት አስተሳሰብ ነው፡፡ ቴክኒሽያኒዝም ቴክኖሎጂን በመጠቀም ህልውና ላይ የሰው ልጆች ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ይችላሉ የሚል ዕምነት ነው፡፡ በሌላ አባባል የሰው ልጆች አንድ ቀን ሁሉንም ችግሮች ጠንቅቀው ምናልባትም ቴክኖሎጂን በመጠቀም የወደፊቱን ጊዜ መቆጣጠር ይችላሉ ማለት ነው፡፡

የሣይንስና ቴክኖሎጂ ምንነትና ግንኙነት ቅንብር፡- በጌታቸው ይመር 1. መግቢያ የሰው ልጅ ስለተፈጥሮ ምንነት ለማወቅ ያደረገው የዘመናት ትግል ለበለጠ ዕውቀት ራሱን እያበቃ ካለንበት ዘመን ላይ ደረሷል፡፡ ዕውቀት በሣይንሳዊ ዘዴ በምልከታ ወይም በሙከራ ተለክቶ የሚገኝ ነው፡፡ በምልከታ ወይም በሙከራ የተገኘ ዕውቀት ይበልጥ ተደራጊ እንዲሆን ለማስቻል የቴክኖሎጂ ፈጠራ ዕውን ሆኗል፡፡ ሣይንስና ቴክኖሎጅ የማይነጣጠሉ የነባሩ ዓለም መገንዘቢያና የተጠቃሚነት መግለጫ መሣሪያዎች ናቸው፡፡ ሣይንስና ቴክኖሎጅ ያላቸውን ግንኙነት ከማየታችን በፊት በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ትርጉማቸውን ማየቱ ተገቢ ይሆናል፡፡ 2. ሣይንስ ሣይንስ ስልታዊ አደረጃጀት ያለው አጽናፈ ዓለምን (Universe) መፈተሽ፣ ማብራሪያና ግምቶችን በመፍጠር፣ማደራጀትና በሣይንሳዊ ዘዴ ሙከራና ምርምር ተመስርቶ ዕውቀት ማዳበር የሚያስችል የተደራጀ ሥርዓት ነው፡፡ ሣይንስ የተፈጥሮ ክስተቶችን ለማስረዳት ምልከታና ሙከራ(observation and experimentation) በማካሄድ የዳበረ ዕውቀትን ያመለክታል፡፡ ሣይንስ ሰዎች ፍላጎታቸውን ለማሟላት ዕውቀት የሚያተርፉበት የተደራጀ ሥርዓት ነው፡፡ የሳይንስ መስኮች በሁለት ዋና ዋና መስመሮች የተመደቡ ናቸው:፡ እነዚህም 1. የተፈጥሮ ሳይንስ፡- (ባዮሎጂያዊ ሕይወትን ጨምሮ) የተፈጥሮ ክስተቶች ጥናት 2. ማህበራዊ ሳይንስ፡- የሰዎችን ባሕርይና የማኅበረሰቦች ጥናት ይህ አመዳደብ በተጠኑና በሙከራ የተረጋገጡ ሣይንሶች (Empirical Sciences) መሠረት ያደረገና በሌሎች ተመራማሪዎች ሲሞከር ተመሳሳይ ውጤት የሚያሳይ በመሆኑ ነው፡፡ ዘመናዊ ሣይንስ በሚከተሉት ዘርፎች ይከፈላል፡፡ 1. የተፈጥሮ ሣይንስ(natural Science)፡- ቁሳዊ ዓለምን የሚያጠና 2. ማሕበራዊ ሣይንስ(Social Science)፡- ስለሰዎችና ማኅበረሰቦች የሚያጠና 3. መደበኛ ሳይንስ(Formal Science):- መደበኛ ሥርዐትን ተከትሎ የሚያጠና እንደ ሎጂክ፣ሂሣብ፣ ስታቲስቲክስ፣ ኮምፒዩውተር ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን ቲዮሪና ኢኮኖሚክስ የመሳሰሉትን የሚመለከት የሣይንስ ዘርፍ ነው 4. የተተገበረ ሣይንስ(Applied Science):- አፕላይድ ሣይንስ ነባር ሣይንሳዊ ዕውቀትን በመጠቀም እንደ ቴክኖሎጂና ፈጠራዎች የመሳሰሉትን ተግባራዊ አፕሊኬሽኖችን በመጠቀም ሌሎች ሣይንሶችን ማልማት የሚያስችል የሣይንስ ዘርፍ ነው፡፡ (ኢንጂነሪግና ሜዲሲን) ሣይንስ ከብዙ ዘመናት በፊት ታሪካዊ ሥልጣኔዎችን እያመላከተ የነበረና አሁን ከተደረሰበት ዘመናዊ አቀራረብ የደረሰ ነው፡፡ የዘመናዊ ሣይንስ አቀራረብና በውጤት አደራደርም የራሱ መለያ ያለው ነው፡፡ የተፈጥሮና ማህበራዊ ሣይንሶች ኢምፒሪካል ሣይንስ ናቸው ማለትም በሳይንቲስቶች የተደረሰበት ዕውቀት በምልከታ ወይም በሙከራ በመረጋገጣቸው ነው፡፡ ሒሳብ መደበኛ ሳይንስ(Formal Science) ተብሎ የተመደበ ነው፡፡ ሒሳብ የተጠኑ ሳይንስ (Empirical Science) ተብለው ከተመደቡት የተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ጋር ተመሳሳይነትም ልዩነትም አለዉ፡፡ ተመሳሳይነቱ እንደ ተጠኑ ሁለቱ ሣይንሶች ዓላማ ያለው ዕውቀትን በሚያስገኝ አካባቢ በጥንቃቄና ስልታዊ ጥናት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ሲሆን ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ዕውቀትን ለማግኘት የሚተነትንበት ዘዴ በአንድ የአሠራር ቅደም ተከተል(Procedure) ላይ ተመስርቶ እንጂ እንደተጠና ሣይንስ በምልከታ ወይም በሙከራ የሚረጋገጥ ባለመሆኑ ነው፡፡ ሂሳብ በሳይንሳዊ ሞዴሎች አገላለጽ ውስጥ የሚጫወተው ሚና ለሳይንስ አንዱ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ በመመልከት እና በመለካት እንዲሁም መረጃ በመሰብሰብና በመተንበይ ብዙውን ጊዜ ሂሳብን በስፋት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ አርቲሜቲክ፣ አልጄብራ፣ ጂኦሜትሪ፣ ትሪጎኖሜትሪ እና ካልኩለስ ለፊዚክስ አስፈላጊ ናቸው፡፡ ስታትስቲካዊ ዘዴዎች በሙከራ ውጤቶች ውስጥ ልዩነት ያለውን ክልል ለመገምገም ያስችላሉ፡፡ መደበኛ ሣይንስ ስታቲስቲክስና ሎጂክን ጨምሮ ለተጠኑ ሣይንሶች(Empirical Sciences) ወሳኝ ናቸው፡፡ የመደበኛ ሣይንስ ዕድገት ለተጠኑ ሣይንሶች ዕድገት መሠረት ነው፡፡ መደበኛ ሣይንስ መላምቶችን ለመደርደር፣ንድፈ-ሃሳብን ለማጎልበት፣ህግን ለማውጣት፣ የተፈጥሮ ሣይንስ ግኝቶችን ለመግለፅና አሠራራቸውን ለማሳየት እንዲሁም በማህበራዊ ሣይንስ ሰዎች ስለአንድ ነገር እንዴት ማሰብና ማድረግ(think and act) እንደሚችሉ በመጠቆም በኩል ጠቀሜታቸው የጎላ ነው፡፡ እንደ ምሕንድስናና ሜዲስን የመሳሰሉት የሚተገበሩ ሳይንስ (Applied Sciense) ውስጥ የሚመደቡ የሳይንስ ዘርፎች ናቸው፡፡ ሣይንስ በሰፊ ትርጉሙ ሒሳብና የተፈጥሮ ሣይንስን ጨምሮ መሠረታዊ ሣይንስ (Fundamental Science) ተብሎም ይጠራል፡፡ ሣይንሳዊ ዘዴ (Scientific Method) ሳይንሳዊ ዘዴ ማለት ክስተቶችን የመመርመር አዲስ ዕውቀት ማዳበር ወይም ቀዳሚ ዕውቀትን ለማረም፣ለማቀናጀትና ለማዋሃድ የሰው ልጆች የሚጠቀሙበት የቴክኒክ አካል ነው፡፡ አንድ ዘዴ ሳይንሳዊ ሊባል የሚችለው የሚለካ፣ተጨባጭ ማስረጃ የሚቀርብበትና ምክንያታዊ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ሣይንሳዊ ዘዴ በመላምት ላይ የተመሠረተ የአንድን ነገር ሁኔታ በአሠራር ቅደም ተከተል፣በሥርዓት የተደራጀ ምልከታን፣ ልኬታን፣ሙከራንና በጥንቃቄ የተደራጀና የተፈተሸ መሆኑን የሚገልጽ የተፈጥሮ ሣይንስ መለያ ነው፡፡ ሣይንሳዊ ዘዴ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለና እያደገ የመጣ የአሠራር ሥርዐት ነው፡፡ ሳይንሳዊ ዘዴ አብዛኛውን ጊዜ ስለ ተፈጥሯዊ ዓለምና ክስተቶች ምልከታዎች ላይ የሚጀምርና በማብራራት እያደገ የሚሄድ ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው፡፡ የሣይንሳዊ ዘዴ አሠራር ዋና ዋና ቅደም ተከተሎች 1. በሙከራ ወይም በምልከታ ደረጃ የሚገለጽ ወይም የሚብራራ ሃሳብ ይቀመጣል፣ 2. ትንበያዎች ሙከራ ወይም ምልከታ ከመካሄዱ በፊት ይቀመጣሉ፣(ትንበያዎች ሃሳቡን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል አስፈላጊ መረጃዎች ናቸው) 3. ሙከራ ወይም ምልከታ ይካሄዳል፣ 4. መላምቱ/ትንበያው ተቀባይነት ሊያገኝም ሆነ ሊያጣ ይችላል፣ 5. ትንበያው ተቀባይነት ካገኘ በሣይንሣዊ ንድፈ ሃሳብ(theory) ማዕቀፍ ይቀመጣል፣ ሳይንሳዊ ማህበረሰብ (Scientific Community) ሳይንሳዊ ማህበረሰብ ሲባል በሁሉም መስተጋብር የሳይንቲስቶች ቡድን ነው፡፡ ይህ በተወሰነ ሳይንሳዊ መስኮች ላይ በተለይም ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ብዙ ንዑስ ማህበረሰቦችን ያካትታል፡፡ ሣይንስና ማህበረሰብ (ሣይንስና ሴቶች) ያለፍንበት አብዛኛው ክፍለ ዘመን ሣይንስ በወንዶች የበላይነት ተይዞ ሴቶች ያደረጉት አስተዋጽዖ ሁሉ ውድቅ የተደረገበትና ዋጋ ያልተሰጠበት ነበር፡፡ ሴቶች ለቤት ወስጥ ሥራ ብቻ የተፈጠሩ ተደርጎ የተወሰነበት ዘመን ረጅም ነው፡፡ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ጀምሮ የሴቶችን ተሳታፊነት ያረጋገጠ ተቋማዊ ለውጥ በመፈጠሩ የሴት ሣይንቲስቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡

ABOUT AIR POLLUTION HAPPY LEARNING

የተማሪዎች መመገቢያ