cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ተዋሕዶን እንወቅ።

አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ሥረይ ለነ ኩሎ አበሳነ ኢታብአነ ውስተ መንሱት እግዚኦ አድህነነ እምዕለት እኪት ወባልሀነ ውስተ መንሡት። ✝በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ✝ የየእለቱን ስንክሳር፥ ውዳሴ ማርያም፥ ፀሎተ አርጋኖን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን፥ የጻድቃንና የሰማእታትን ገድል፥ የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄዎችን፥ የድሮ እና አዳዲስ መዝሙራትን የሚያገኙበት ቻናል ነው። ይቀላቀሉን።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
1 198
Suscriptores
Sin datos24 horas
+237 días
+11430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Repost from N/a
የጌታችንን አምላክነት የሚያሳዩ ጥቅሶች (ለክርስቲያን አድማጭ) /ክፍል ሦስት/ {አንድ አማኝ የሆነ አይሁዳዊ ሰው ሌላ ፍጡርን በየትኛውም መንገድ ‘አምላኬ’ ብሎ ሊጠራው አይችልም። በብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ቦታ ቢሆን ሰው ሌላ ፍጡርን ‘አምላኬ’ ብሎ ሊጠራው አይችልም። ካለ እስኪ ፈልጉና አምጡት ፥ ነገር ግን ያልኳችሁን አስተውሉ። ያልኳችሁ ‘አምላኬ’ ብሎ አንድ ከአሕዛብ ያልሆነ እግዚአብሔርን በጽድቅ የሚከተል ሰው ለሌላ ፍጡር ሲናገር እንጂ እግዚአብሔር ለሙሴ ‘በፈርዖን ላይ አምላክ እርጌሃለሁኝ’ እንዳለው ያለ አይደለም። ይህ ዐይነት ጥቅስ የማይሆነው ምክንያቱ አንደኛ ፈርዖን ሙሴን ‘አምላኬ’ አላለውም ፥ ዳግመኛም እግዚአብሔር ለሙሴ እያለው ያለው ‘ያለፈቃዱም ቢሆን ትገዛው አምላክ አድርጌሃለሁኝ’ ብሎ ነው እንጂ ፈርዖን በፈቃዱ አይደለም ሙሴን ‘አምላኬ’ እያለው ያለው። በመጨረሻም ደግሞ ፈርዖን እግዚአብሔርን የማያውቅ ከአሕዛብ ወገን ነው። ስለዚህ እስኪ ያልኳችሁን ፈልጉና አምጡ። አይሁዳዊ የሆነ አንድ እግዚአብሔር እንዳለ የሚያምን ቶማስ ጌታችንን ‘አምላኬ’ ብሎ ሲጠራው ያ ራሱ እግዚአብሔር ነህ እያለው መሆኑን መመልከት ይገባል። ጌታችን ቶማስ እንዳለው እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ ፈጥኖ ቶማስን መገሠጽ ይገባው ነበር። ምክንያቱም ፍጡርን ‘እግዚአብሔር ነህ’ ብሎ መጥራት እግዚአብሔር ላይ ሌላ አምላክ ማምለክ ነውና። ከዐሠርቱ ትእዛዛት የመጀመሪያውን መተላለፍ ነው ፥ ነገር ግን ጌታችን ምን ብሎ እንደመለሰለት ተመልከቱ። “ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።” ምን??? ጌታችን ይህንን የቶማስ ንግግር ተቀበለው ማለት ነው? እዚህ ጋር መረዳት የሚገባን ሁለት አማራጭ እንዳለን ነው ፥ ወይ ጌታችን እውነት አምላክ መሆኑን ነው። ወይም ደግሞ ይህንን በመቀበል አምላክን የሚሳደብ ቀጣፊ ነበር። የትኛውም ክርስቲያን ሁለተኛውን ሊመርጥ አይችልም ፥ ስለዚህ ያለን አማራጭ የመጀመሪያው ነው። ጌታችን እውነተኛው እግዚአብሔር ነው።} ይህንን ጥቅስ ለመመለስ ከሚሞከርባቸው መንገዶች መካከል ያሉትን እንመልከት፥ ሀ) ቶማስ ‘ጌታዬ’ ሲል ጌታችንን ፥ ‘አምላኬ’ ሲል ደግሞ በርሱ ያደረውን አብን ነው። ይህ መንገድ አንድ ሰው ሊሄድበት የሚችለው በጣም ሞኙ መንገድ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ስለዚህ ጌታችንን ‘አምላኬ’ ሲለው ጌታችንን ራሱን ሳይሆን በርሱ ያደረውን ‘አብን’ ነው ማለት ነው። እስኪ ይህንን ራሱን መንገድ ተጠቅሜ ሌሎች ጥቅሶችን ልመልከታቸው። /ዮሐ 14 ፥ 17/ “17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።” {እዚህ ጋር ጌታችን ለሐዋርያቱ መንፈስ ቅዱስን ታውቁታላችሁ ፥ እርሱ በውስጣችሁም ስለሚሆን እያለ እየነገራቸው ነው። ስለዚህ በሐዋርያቱ ላይ መንፈስ ቅዱስ አድሮባቸዋል ማለት ነው። ስለዚህ እኔ ቅዱስ ጴጥሮስን ‘መንፈስ ቅዱስ ሆይ’ እያልሁኘ መጥራት እችላለሁኝ ፥ ምክንያቱም እኔ እያልሁኝ ያለሁት ጴጥሮስን ሳይሆን በውስጡ ያደረውን መንፈስ ቅዱስን በመሆኑ ምክንያት።} /ዮሐ 14 ፥ 23/ “23 ኢየሱስም መለሰ አለውም፦ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።” {ስለዚህ አማኞችን በሙሉ ‘አምላኬ’ እያልሁኝ መጥራት እችላለሁኝ ማለት ነው። ምክንያቱም አብ ስለሚያድርባቸው ማለት ነው። ስለዚህ ወንድሞቼንና እኅቶቼን አምላኮቼ እያልሁኝ ብጠራቸው ችግር የለውም ፥ ምክንያቱም እያሉት ያለሁት ለእነርሱ ሳይሆን በውስጣቸው ላደረው ከአብ በመሆኑ ምክንያት። አያችሁት አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን እንደምልዐቱ ካልተመለከተ የሚፈጠረውን? መጽሐፍ ቅዱስን አዛብቶ ያርፈዋል።} ለ) ‘ጌታዬ’ ብሎ ጌታችንን አመሰገነ ፥ ‘አምላኬ’ ብሎ ደግሞ አብን አመሰገነ። ይህ ትንሽ ከቀደመው የሚለየው እኒህ የሚሉት ‘አምላኬ’ ብሎ የጠራው ጌታችንን አይደለም ፥ ይልቁንም አብን እየጠራ ነው እንጂ ማለታቸው ነው። የቀደሙት ያሉት ‘ቶማስ ጌታችንን አምላኬ ብሎታል ፥ ያለው ግን በውስጡ አብ በማደሩ እንጂ እርሱ አምላክ በመሆኑ ምክንያት አይደለም።‘ ነበር። የአሁኖቹ ደግሞ ‘ቶማስ ጌታችንን አምላኬ ብሎ አልጠራውም ፥ ይልቁንም ጌታዬ ሲል ጌታችንን አምላኬ ሲል ደግሞ ጌታችንን ሳይሆን አብን ነው’ ይላሉ። ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ክርክሩ የሚኖረው ‘አምላኬ’ የሚለው ቃል ለጌታችን ነው ወይስ ለጌታችን አይደለም የሚለው ላይ ነው። ይህንን ለመርታት በቀላሉ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ጥንታዊ ቋንቋ በመሄድ መርታት ይቻላል። የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 20 ቍጥር 28 እንዲህ ይላል። /ዮሐ 20 ፥ 28/ “28 ἀπεκρίθη Θωμᾶς καὶ εἶπεν αὐτῷ, Ὁ κύριός μου καὶ ὁ θεός μου.” {በግሪኩ ላይ κύριός μου(ኪሪዩስ ሙ) የሚለው ቃል ‘ጌታዬ’ የሚለውን ቃል ፥ Θεός μου(ቴዩስ ሙ) የሚለው ቃል ‘አምላኬ’ የሚለውን ቃል የሚወክለው ነው። አሁን Θεός μου የሚለው ቃል Θεέ μου ብሎ ቢጻፍ ኖሮ ወደሌላ አካል እያመላከተ እንደሆነ እንገምት ነበር ፥ Θεός μου ብሎ በመጻፉ ግን κύριός μου ጋር አንድ የሆነ አካልን እያመላከተ እንደሆነ እናውቃለን። ያ ደግሞ ሁለቱም እያመላከቱ ያሉት ሁለት ቃላት እርሱ የተባለውን (ማለትም ጌታችንን) ነው። ስለዚህ ይህንን ራሱን ግሪክ በሌላ ግልጥ በሆነው መንገድ እንተርጕመው ብንል ፥ ‘የእኔ ጌታና አምላክ’ ይሆናል ማለት ነው። ምናልባት ይህ ጥቂት ግራ የሚያጋባ ይመስለኛል ፥ ነገር ግን ይህንን በደንብ መረዳት ለምትፈልጉ ሰዎች የMurray J. Harrisን John: Exegetical Guide to the Greek New Testament የሚለውን መጽሐፍ መመልከት ይቻላል።} ሐ) ቶማስ ይህንን የተናገረው በድንጋጤ ምክንያት ነው ፥ ስለዚህ አስቦበት አይደለም። ይህንን መርታት በጣም ቀላል ነው ፥ ምክንያቱም እንዳሉት ቢሆን ኖሮ ጌታችን ቶማስን ይገሥጸው ነበር። ጌታችን ቶማስን ባለመገሠጹ ምክንያት ያንን የቶማስ ንግግር እንደተቀበለው እንመለከታለን። ምክንያቱም ይህ የተፈጠመባቸው ሐዋርያት ይህ ዐይነት ንግግር ሲደረግላቸው እንዴት እንደመለሱ እንመልከት፥ /ሐዋ 14 ፥ 11 - 15/ “11 ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ፦ አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል አሉ፤ 12 በርናባስንም ድያ አሉት፤ ጳውሎስንም እርሱ በመናገር ዋና ስለ ነበረ ሄርሜን አሉት። 13 በከተማውም ፊት ቤተ መቅደስ ያለው የድያ ካህን ኮርማዎችንና የአበባን አክሊሎች ወደ ደጃፍ አምጥቶ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ወደደ። 14 ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ 15 እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።” ይቀጥላል •••
Mostrar todo...
👍 1
01:29
Video unavailableShow in Telegram
"ትዕቢት ምንድነው ?" #በየግሩፑ_ያጋሩ ! ¶ Tik Tok [ http://tiktok.com/@applied_ortodox ] JOIN [ @menfesawi_tik_tok ] ✧━━━━━━━━━━━━━━━━━━✧     ❍ㅤ             ⎙ㅤ              ⌲         ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ          ˢᵃᵛᵉ              ˢʰᵃʳᵉ
Mostrar todo...
oAS7bBCc1vUExZEZjTNmyBQGiiQgzUQAEILDC.mp42.30 MB
የይስሐቅ ዕድሜ 1979 ዓመተ ዓለም (ዓ.ዓ.) - ሰዶምና ገሞራ ጠፍተው አብርሃምና ሣራ ከቤቴል (ሎዛ) ተነሥተው በቤርሳቤ ሠፈሩ፣ ይስሐቅ ተወለደ። 1982 ዓ.ዓ. - የይስሐቅ ታላቅ ወንድም እስማኤልና እናቱ አጋር ወደ ፋራን ምድረ በዳ ተሰደዱ። 2003 ዓ.ዓ. - አብርሃምና ይስሐቅ ወደ ደብረ ጽዮን ተጓዙ፤ ወደ ቤርሳቤ ተመለሱ። 2010 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከቤርሳቤ ወደ ኬብሮን ተመለሰ። 2027 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ከካራን የነበረችውን ርብቃን አገባት። 2046 ዓ.ዓ. - ያዕቆብ (እስራኤል)ና ዔሳው (ኤዶምያስ) ለይስሐቅ ተወለዱ። 2060 ዓ.ዓ. - አብርሃም አረፈ። 2073 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ከኬብሮን ወደ ቤርሳቤ ተመለሰ። 2081 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ በጌራሮ ሠፍሮ ከፍልስጥኤማውያን ንጉሥ አቢሜሌክ ጋር ስምምነት ተዋዋለ። 2101 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ከጌራሮ ወጣ። 2108 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤ ተመለሰ። 2114 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ያዕቆብን ለዔሳው ስቶ ርስቱን ሰጠው። 2162 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ አረፈ።
Mostrar todo...
የአብርሃም ዕድሜ በመጽሐፈ ኩፋሌ 1876 ዓመተ ዓለም (ዓ.ዓ.) - አብራም ለአባቱ ታራ እና ለእናቱ ኤድና በዑር ከላውዴዎን ተወለደ። 1886 ዓ.ዓ. - ሦራ (በኋላ ሣራ) ተወለደች (?)። 1891 ዓ.ዓ. - አብራም ወጣት ሆኖ በከብት የሚስብ ማረሻ ፈጠረ። 1903 ዓ.ዓ. - አብራም አባቱን ታራን በጣኦታት ለምን ታምናለህ ብሎ ጠየቀው። 1925 ዓ.ዓ. - አብራም ሦራንን አገባት። 1932 ዓ.ዓ. - ሎጥ ተወለደ። 1936 ዓ.ዓ. - አብራም የዑርን አረመኔ መቅደስ አቃጠለና ወደ ካራን ሸሸ። 1950 ዓ.ዓ. - የሰናዖር ንጉሥ አምራፌልና የኤላም ንጉሥ ኮሎዶጎምር የሰዶምን አካባቢ በከነዓን ያዙ። 1951 ዓ.ዓ. - እግዚአብሔር አብርሃምን ባረከው፣ አብርሃምም ሰማያዊ ቋንቋ ለመማር ጀመረ። 1953 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከካራን ወደ ከነዓን ተጓዛ። 1954 ዓ.ዓ. - ኬብሮን በከነዓን ተሠራ። 1956 ዓ.ዓ. - አብርሃም ወደ ግብፅ ሄደ። 1961 ዓ.ዓ. - ጣይናስ በግብጽ ተሠራ። 1963 ዓ.ዓ. - አብርሃም ወደ ከነዓን ወደ ቤቴል ተመለሰ። ሰዶም በኤላም ላይ አመጸ። 1964 ዓ.ዓ. - የነገስታት ጦርነት፦ የአብርሃም ሠራዊት አምራፌልን ወዘተ. አሸነፉ። አብርሃምም በምላሽ ስንኳ አንዳችም ሲባጎ ከሰዶም ንጉሥ እንዳይወስድ አሻፈረኝ ነገረለት ። መልከ ሴዴቅ አብርሃምን ባረከው። 1965 ዓ.ዓ. - እስማኤል ተወለደ። 1979 ዓ.ዓ. - እሳት ከሰማይ ወርዶ ሰዶምንና ገሞራን አጠፋ። አብርሃም ወደ ቤርሳቤ ሄደ፣ ይስሐቅ ተወለደ። 1982 ዓ.ዓ. - እስማኤልና እናቱ ሀጋር ወደ ፋራን ምድረ በዳ ተሰደዱ። 2003 ዓ.ዓ. - አብርሃምና ይስሐቅ ወደ ደብረ ጽዮን ተጓዙ፤ ወደ ቤርሳቤ ተመለሱ። 2010 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከቤርሳቤ ወደ ኬብሮን ተመለሰ። 2024 ዓ.ዓ. - ሣራ ዐረፈች፤ ለመቃበርዋም አብርሃም ዋሻ ከኬጢያውያን ሰው ከኤፍሮን ገዛ። 2027 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ርብቃን አገባት፣ አብርሃምም ከጡራን አገባት። 2046 ዓ.ዓ. - ያዕቆብና ኤሳው ለይስሐቅ ተወለዱ። 2060 ዓ.ዓ. - አብርሃም አረፈ።
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
#አብርሃም በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በዑር ከላውዴዎን አብራም ተብሎ ተወልዶ በኋላ ወደ ካራንና ወደ ከነዓን ግብፅም የሄደው የዕብራውያንና፣ የእስማኤላውያን የብዙ ሕዝቦች አባት ነበረ። የመጀመሪያ ስሙ አብራም በኋላ አብርሃም፤ አባቱ ታራ፤ ባለቤቱ ሳራ፤ የትውልድ ቦታ ዑር ከላውዴዎን፤ ያረፈበት ቦታ ኬብሮን የአብርሃም ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ አብርሃም ሕይወት ብዙ ምዕራፍ ይሰጣል። #ሣራ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የአብርሃም ሚስትና የይስሐቅ እናት ነበረች። በዑር ከላውዴዎን ተወልዳ ስሟ በመጀመርያ ሦራ (ወይም በዕብራይስጡ ሣራይ፥ «ልዕልቴ») ሲሆን በኋላ እግዚአብሔር ወደ «ሣራ» (ዕብራይስጥ ሣራህ፥ «ልዕልት») ቀየረው። #ይስሐቅ (ዕብራይስጥ፦ יִצְחָק, /ዪጽሓቅ/) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የአብርሃምና የሣራ ልጅ ነበረ። ርብቃን አግብቶ መንታ ልጆቻቸው ዔሳው እና ያዕቆብ በሌላ ስማቸው ኤዶምያስና እስራኤል የተባሉትን ኹለት ልጆች ወለዱ። የይስሐቅ ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ ይስሐቅ ሕይወት ብዙ ተጽፏል። እንኳን ለቅድስት ሥላሴ (ለአብርሃሙ ሥላሴ) በዓል አደረሳችሁ። ✍ተጻፈ በቀሲስ ኢዩኤል ሰሎሞን
Mostrar todo...
Repost from N/a
የጌታችንን አምላክነት የሚያሳዩ ጥቅሶች (ለክርስቲያን አድማጭ) /ክፍል ሁለት/ [በቅዱስ ሉቃስ በወንጌልም ቢሆን ያ የሚመጣው ድምፅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ እንደሆነ ፥ እርሱ መንገዱን የሚጠርገው ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ መመልከት ይቻላል። አሁን ይህ ከኢሳይያስ የተጠቀሰው ትንቢት ምን እንደሆነ እንመልከት፥] ለ) በወንጌላቱ ላይ የተጠቀሰው ትንቢት የትኛው ትንቢት ነው? በእኒህ ወንጌላት ላይ የተጠቀሰው ዋነኛው ጥቅስ ከኢሳይያስ ትንቢት ነው ፥ ነገር ግን የኢሳይያስን ትንቢት ሌላም ቦታ ላይ ደግመን እናገኘዋለን። ሁለቱን ትንቢታት እስኪ እንመልከታቸውን የሚያመላክቱትን እንመልከት፥ /ኢሳ 40 ፥ 3 – 5/ “3 የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። 4 ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤ 5 የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና” /ሚል 3 ፥ 1/ “እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡” [በኢሳ 40 ፥ 3 ላይ ያለው የአዋጅ ነጋሪ ቃል ለማን ነው መንገዱን ጥረጉ እያለ ያለው? መንገዱን ጥረጉ ብሎ ‘እግዚአብሔር’ ይመጣል ብሎ ነገረን። ለዚያ ነው ‘የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ።‘ እያለ እየተናገረ ያለው። በሚል 3 ፥ 1 ላይም ራሱን ነገር ነው የምንመለከተው ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አለ ‘“እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል።’ ስለዚህ ከእነዚህ ትንቢቶች በግልጥ እንደምንረዳው በምድረ በዳ የተላከው ድምፅ መንገዱን እየጠረገ ያለው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ነው ማለት ነው።] ሐ) አሁን ይህ ወሳኝነቱ ምንድን ነው? በትንቢተ ኢሳይያስና በትንቢተ ሚልክያስ እንደተመለከትነው በምድረ በዳ የሚጮኸው ድምፅ መንገዱን እየጠረገ ያለው መንገዱን እያስተካከል ያለው ለአምላካችን እግዚአብሔር ነው። በወንጌላቱ ደግሞ ያ በምድረ በዳ የሚጮኸው ድምፅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ እንደሆነ ተነግሮናል። አሁን ምን እያመላከተን እንደሆነ ተመልከቱ። በምድረ በዳ የሚጮኸው ድምፅ እንደኢሳይያስና እንደሚልክያስ አስተምህሮ መንገዱን እየጠረገ ያለው ለእግዚአብሔር ነዋ? ‘አዎን’ በወንጌላት ደግሞ ያ ድምፅ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንደሆነ ነግሮናል አይደል? ‘አዎን’ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ መንገዱን እየጠረገ ያለው ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው አይደል? ‘አዎን’ ስለዚህ ቅዱስ ዮሐንስ (በምድረ በዳ የሚጮኸው ድምፅ) መንገዱን እያስተካከለ ያለው እግዚአብሔር ለሆነው ለጌታችን ለኢዩስ ክርስቶስ ነው ማለት ነው። ስለዚህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያ በብሉይ ኪዳን እመጣለሁኝ ያለው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ደግሞ የሚደንቀው ወንጌላቱ ሁሉ ገና ከመጀመራቸው የጌታችንን አምላክነት ተናግረው መጀመራቸው ነው። ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ያንን በግልጥ ቃል ‘በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበር’ ብሎ ነገረን። አያችሁ? አራቱም ወንጌላት ገና ከመጀመራቸው የጌታችንን ፍጹም አምላክነት አስተምረው ይጀምራሉ። አያችሁ የወንጌላቱ መሰናሰል? ምን ዐይነት ተመሳሳይ የሆነ ውብ መልእክት እንደሚያስተላልፉ? ስለዚህ ከዚህ በኋላ በጣም በቀላሉ ከማቴዎስ ከተባላችሁ ከማቴዎስ፣ ከማርቆስ ከተባላችሁ ከማርቆስ፣ ከሉቃስ ከተባላችሁ ከሉቃስ ከዮሐንስ ከተባላችሁ ከዮሐንስ ወንጌል በቀላሉ ማሳየት ትችላላችሁ ማለት ነው። ይህንን አምላክነቱን ከጫፍ እስከጫፍ የሚያስተምር ቅዱስ መጽሐፍን የሰጠን የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ለዘለዓለሙ የገነነ ይሁን።} ይህንን ጥቅስ ለመመለስ ሰዎች እንዲህ ለማለት ይሞክራሉ “በኢሳይያስና በሚልክያስ ትንቢት ላይ እግዚአብሔር እየተባለ የሚጠራው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነው እንጂ ቃል በቃል እግዚአብሔር አይደለም። ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስም አንድ ሰው ሌላ ሰውን ልኮ መልእክት ቢያደርስ ያ ራሱ ሰውዬ መልእክት አደረሰ ይባላልና። ለምሳሌ ፥ አበበ እኅቱ ሰላምን ወደ ጓደኛው ከበደ ቢልክ በመጽሐፍ ቅዱስ ባሕል አበበ ወደ ከበደ ሄዶ መልእክቱን ተናገረ ማለት ይቻላልና።” ይህ መንገድ በኢሳይያስና በሚልክያስ ትንቢት ላይ እንደማይሠራ እናሳይ። እስኪ ጥቅሱን መልሰን እንመልከተው፥ /ኢሳ 40 ፥ 3 – 5/ “3 የአዋጅ ነጋሪ ቃል፦ የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። 4 ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤ 5 የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና” {የአዋጅ ነጋሪ ቃል የተባለው ለእግዚአብሔር መልእክተኛው ነው። እንደነዚህ ሰዎች አተረጓጐም ደግሞ እዚህ ጋር እግዚአብሔር የተባለው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነው። እስኪ ጥያቄ እንጠይቅ ፥ ‘የአዋጅ ነጋሪ ቃል የተባለው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነው ፥ እግዚአብሔር የተባለው ደግሞ ራሱ ሌላ የእግዚብሔር መልእክተኛ ነው። ስለዚህ የአዋጅ ነጋሪ ቃል የተባለው የእግዚአብሔር መልእክተኛ ከሆነ እዚህም ጋር ‘እግዚአብሔር’ተብሎ መጠራት ይችላል ማለት ነው። እንደነዚህ ሰዎች አካሄድ ከሆነ ለምንድን ነው የመጀመሪያው መልእክተኛ እግዚአብሔር ሳይባል ሁለተኛው መልእክተኛ እግዚአብሔር የሚባለው? አያችሁ ጥቅሱን እንዴት ግራ እንደምታጋቡት በዚህ ዐይነት አካሄድ። ይህ የአተረጓጐም መንገድ ምንኛ ጥቅሱን እንደሚያበላሸው አያችሁ? እንደነዚህ ሰዎች ፍልስፍና ‘የመጀመሪያው መልእክተኛ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሆኖ ሳለ እግዚአብሔር ተብሎ አልተጠራም ፥ ነገር ግን ሁለተኛው መልእክተኛ እንደመጀመሪያው መልእክተኛ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ሆኖ ሳለ እርሱ ብቻውን እግዚአብሔር ተባለ።‘ በጣም አሳማኝ የትርጓሜ መንገድ ነው ባካችሁን? ደግሞም ኢሳይያስ ‘እግዚአብሔር ብቻ’ ብሎ አያበቃም። ‘ለአምላካችንም’ ብሎ ያጸናዋል። ስለዚህ እንደነዚህ Eisteinኦች አካሄድ የእግዚአብሔር መልእክተኛ የሆነ ሰው ‘አምላካችን’ ተብሎ ሊጠራ ይችላል ማለት ነው። ስለዚህ ሐዋርያት የእግዚአብሔር መልእክተኛ እንደመሆናቸው ‘አምላኮቻችን’ ብለን መጥራት እንችላለን ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ስለነበረ ‘አምላኬ’ ብዬ መጥራት እችላለሁኝ ማለት ነው። አያችሁት ምን ዐይነት አስቂኝ የትርጓሜ መንገድ ፥ አሳዛኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ቡጨቃ እንደሆነ? ስለዚህ ይህንን ጥቅስ እንደዚህ መተርጐም የመጽሐፍ ቅዱስን አተረጓጐም በሙሉ ማበላሸት ነውና ይህ የመልስ ሙከራ አይሠራም።} 2) ጌታችን ከቶማስ ‘አምላኬ መባልን ተቀብሏል’ /ዮሐ 20 ፥ 27 – 29/ “27 ከዚያም በኋላ ቶማስን፦ ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው። 28 ቶማስም፦ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት። 29 ኢየሱስም፦ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው።” ይቀጥላል •••
Mostrar todo...
👍 1
መሐላ በመጽሐፍ ቅዱስ “የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።”   — ዘጸአት 20፥7 “በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ የአምላካችሁንም ስም አታርክሱ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”   — ዘሌዋውያን 19፥12 “እስራኤል ሆይ፥ አንተ ብታመነዝር ይሁዳ አይበድል፤ እናንተም ወደ ጌልገላ አትግቡ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ፥ ወይም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብላችሁ አትማሉ።”   — ሆሴዕ 4፥15 ማቴዎስ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³³ ደግሞ ለቀደሙት፦ በውሸት አትማል ነገር ግን መሐላዎችህን ለጌታ ስጥ እንደተባለ ሰምታችኋል። ³⁴ እኔ ግን እላችኋለሁ፦ ከቶ አትማሉበሰማይ አይሆንም የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤ ³⁵ በምድርም አይሆንም የእግሩ መረገጫ ናትና፤ በኢየሩሳሌምም አይሆንም የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና፤ ³⁶ በራስህም አትማል፥ አንዲቱን ጠጉር ነጭ ወይም ጥቁር ልታደርግ አትችልምና። ³⁷ ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው። “ከሁሉም በፊት፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በሰማይ ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፥ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።”   — ያዕቆብ 5፥12
Mostrar todo...
🙏 1
Repost from Janderebaw Media
Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለቅዱሳን ሐዋርያት ለቅዱስ  ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! የዮና ልጅ ጴጥሮስ ሆይ ደምህ በመስቀል ጽዋ ተቀዳ የጳውሎስ ደም ደግሞ ወደ ሰማያት ጮኸ - ቅዱስ ያሬድ
Mostrar todo...
🙏 3
በዓለ_ዕረፍቶሙ_ለብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ.pdf2.69 KB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.