es
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Ir al canal en Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Mostrar mĂĄs
213
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 dĂ­as
-430 dĂ­as
Archivo de publicaciones
ትኩረት ያልሰጠነው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ‼ =========================== (ይህ ጉዳይ ከጸደቀ በኋላ ሌላ ዙሩ በከረረ ትግል ውስጥ ሳንገባ በፊት ከወዲሁ እምነታችንን በማይነካ መልኩ መዘጋጀቱን ማረጋገጥ አለብን!) || ✍ ካስታወሳችሁ ከአንድ ወር በፊት ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችና ከተለያዩ የኃይማኖት ተወካዮች ጋር በተናጠል ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ በተለይ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ከኛ ከእስልምና ኃይማኖት መሪዎቻችን ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች መንግሥት በቅርቡ ኃይማኖትን የተመለከተ ሕግ እንደሚያወጣ መናገራቸው ይታወሳል። በተለይ ከመጅሊስ መሪዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት መስጂዶች የሚያደርጉት የአዛን ጥሪ፣ እንዲሁም በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚከናወኑ ቅዳሴና አስተምህሮዎች ሌላውን ሰው ማወክ ስለሌለባቸው አስቡበት በማለት ስለሚወጣው ሕግ ይዘት ፍንጭ ሰጥተው ነበር።  መንግሥትና ሃይማኖት አንዱ በአንዳቸው ተግባርና እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ከኃይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ በፍትሕ ሚኒስተር በኩል ተዘጋጅቶ አሁን ላይ በሰላም ሚኒስተር አስተባባሪነት ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት መደረግ ተጀምሯል። ይህ አዲሱ አዋጅ በርካታ ክልከላዎችን የያዘ ሲሆን፤ የሙስሊሞችን በጀማዓህ ሶላት መስገድ፣ የእህቶችን ጂልባብና ኒቃብ መልበስ፣ ጀለቢያ፥ አማኢምና ኮፍያ መልበስና የመሳሰሉትን ለማገድ በር የሚከፍት ህግ ተካቶበታል። የነርሱ እሳቤ የሌላውንም እምነት ተከታይ ኃይማኖታዊ አለባበሱንና በቡድን ማምለክን ስለምንከለክል፤ ሙስሊሞችንም «እናንተን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ነው የከለከልነው!Âť በሚል ሽፋን በመሞገት መከልከል አስበዋል። እዚህ ላይ ያልገባቸው ነገር የእያንዳንዱ እምነት ዶክትሪን የተለያዬ መሆኑን አለማወቅ ነው። በተለይም የእስልምና እምነት ህግጋት በየትኛውም ታዕምር ቢሆን በሰው ሠልሽ ህግ የሚሻሩ አለመሆናቸውን መረዳት ተስኗቸዋል። እነርሱ ሲጀመር ከፊሎቹ ራቁታቸውን መሄድ ነው የቀራቸው። እንኳን ተከልክለው በፈቃደኝነትም እየተገበሩት አይደለም። ታዲያ እነርሱ ከተዘናጉ እኛም አብረን መታፈን አለብን? በጭራሽ! አይደለም ኢትዮጵያ አዲስ የምታዘጋጀው ህግ፤ የዓለም መንግስታት ተባብረው አዋጅ ቢያወጡ፤ እስልምናችንን ከተቃረነ ማንም አይሰማቸውም። የራሳቸውን እንደፈለጉ ያድርጉ። የኛን ግን እንዳያስቡት። በተጨማሪም 24 ሰዓት በካሴት ሳይቀር ተከፍቶ የሚለቀቅን የቤተ ክርስቲያን ቅዳሴና መዝሙር በቀን 5 ጊዜ 5 ደቂቃ ለማትሞላ አጋጣሚ የሚደረግን የአዛን ጥሪ አወዳድሮ አብሮ ጨፍልቆ ለመከልከል መጋጋጥ በየትም ተሰምቶ አይታወቅም። መንግስት አዛን ከከለከለን በተለይም በዐረቡና በሙስሊሙ ዓለም በኩል ያለውን ግንኙነት እንደሚያበላሽ ጠንቅቆ ይወቀው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሆነ መከራ እንዲለብስ ነው የሚሆነው። ቀድሞ ከሙስሊሙ ተወካዮችና ምሁራን በኩል የተሰጣቸውን ሃሳብ ወደ ጎን በተመው፤ ይህን ረቂቅ የሚያዘጋጁ አካላት።ሙስሊሙን የሚጨፈልቅ ህግ ማውጣታቸው አላማቸው ምን እንደሆነ ግራ ያጋባል። ባለማወቅ ነው እንዳይባል ቀድሞ መረጃ ተሰጥቷቸዋል፤ ግን ወደ ጎን ብለውት በራሳቸው አካሄድ መሄድን መርጠዋል። በርግጥ ፍትሕ ሚኒስተር ውስጥ እነማን እንደሆኑ እናውቃለን። ከአሁን በፊትም ኡማውን ከወያኔ ጀምሮ ሲጨቁኑ የነበሩ አካላት አሉበት። በአጭሩ እየመጣ ያለው ረቂቅ አዋጅ የእምነት ነፃነትን የሚጋፋና ኃይማኖቶች ከእምነታቸው አስተምህሮ ይልቅ በሃገሪቱ መንግስት ቁጥጥር እንዲዳኙ የሚያደርግ አደገኛ አዝማሚያ ያለው ነውና ከወዲሁ እንዲስተካከል ማድረግ አለብን። እኛ በደፈናው ባልተጻፈ ህግ ሲጨቁኑን የነበረውን ጉዳይ ጽፈው በግልፅ አስተካክለው ይመጣሉ ስንል፤ ጭራሽ በግልፅ ከልክለውና ሌላም ዱብእዳ አክለው መጡ። ማንም አይሰማቸውም! ህዝብ መረጃ ይኑረው። በደንብ መረጃዎችን አንሸራሽሩ። ረቂቅ አዋጁ ነገ ከኃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋል ተብሏል። እዛም ላይ የኛ ተወካዮች በደንብ ጉዳዩን ያንሱት። አላህ የደነገገው ሸሪዓህ በተራ ሰዎች ህግ በፍፁም አይሻርም፤ አይሻሻልም። ሸሪዓን የሚቃረን ህግ ካለ ልሹ ይቀየር እንጂ ሸሪዓህ አይቀየርም። እኛ ሸሪዓን አልደነገግነውም፤ የደነገገው አላህ ነው። ያልደነገግነውን አናሻሽልም። እነርሱ ግን ረቂቁን ያወጡት ራሳቸው ስለሆኑ ራሳቸው አሻሽለው ይምጡ። Period‼ || t.me/MuradTadesse x.com/MuradTadesse fb.com/MuradTadesseOfficial

የትዕግስተኞች ምንዳ ⇢ ኢብኑ አሳኪር ( تاريخ دمشق ) አዘሃቢ ደግሞ ( تذكع؊ الحفاظ)  በሚለው መፅሐፋቸው የሚከተለውን ታሪክ አስፍረዋል ፦ ኢማሙል አውዛኢ ሲናገሩ አንድ ጥበበኛ እንዲህ አለኝ ፦ " ጂሃድን አስቤ ወጣሁ ። መንገዴ ላይም አንዲት ድንኳን አየሁኝ በውስጧም ሁለት እግሮቹ ፣ ሁለት እጆቹና አይኖቹ ያጣ ሰው አገኘሁ። እሱም እንዲህ ይል ነበር ፦ " ጌታዬ ሆይ!  በዋልክልኝ ፀጋ ልክ በዛ ያለ ምስጋና ይድረስህ "  እኔም የኢማኑን ትክክለኛነትና የትዕግስቱን እውነተኝነት ለማረጋገጥ ፈለኩና እንዲህ አልኩት ፦ " ለየትኛው ፀጋ ነው አላህን የምታመሰግነው?  አላህ ምን እንዳደረገብህ አላስተዋልክም እንዴ? " እሱም ፦ " በእርግጥ አላህ አወዳሽ የሆነን ምላስና መከራ ላይ ትዕግስት የሚያደርግን አካል ሰጥቶኛል። ከሰማይ እሳትን አውርዶ ቢያቃጥለኝ እንኳ ለእሱ ውዴታን እንጂ አልጨምርም ። እኔም አንተ ጋር አንድ ጉዳይ አለኝ ። ትፈፅምልኛለህን?  " áŠ áˆˆáŠá˘ እኔም " እሺ በደስታ " አልኩት ። ከዛም አለ " ለሰላቴ ውዱኤን እንዳደርግ የሚያግዘኝና በምበላም ጊዜ ምግቤን የሚከታተልልኝ ልጅ አለኝ ። ከትላንት ጀምሮ ግን አላገኘሁትም ። እንደው ፈልገህ ሾለሹ መረጃን ብታመጣለኝ " እኔም ልጁን ለመፈለግ ወጣሁ ።  አሸዋ የተከመረበት ቦታ ላይ ስደርስ አንድ አውሬ አድኖት እየበላው አገኘሁት! ። ከዛም ኢና ሊላህ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን አልኩና እንዴት ልነግረው ነው ብዬ ተጨነኩኝ። ሳላረዳው በፊት ላፅናናው እንደሚገባ አላህ በልቤ አሳወቀኝ ። ከዛም ወደሱ ሄድኩና ሰላም አልኩት ሰላምታዬን መለሰልኝ ። ቀጠል አደረኩና " የሆነ ነገር ብጠይቅህ ትመልስልኛለህ?  ብዬ ጠየቁት ። እሱም " እውቀት ካለኝ አው እነግረሀለሁ " አለኝ ። ከዛም እኔ " አላህ ዘንድ አንተ ነህ የበለጠ ቦታ ያለህ ወይስ ነብዩላህ አዩብ? " ብዬ ስጠይቀው እሱ " አዩብ ነው እንጂ ከእኔ የበለጠ ቦታ ያለው"  አለኝ ። እኔም  ጠየኩት "ማንም አጫዋች እስከማይኖረው ድረስ አላህ ፈትኖት ትዕግስት አላደረገምን?  "  እሱም " አው " አለኝ ። " ልጅህ አውሬ በልቶታል " አልኩት ። እሱም " በልቤ ላይ ከዱንያ ተስፋ መቁረጥን ላደረገልኝ አላህ ምስጋና ይገባው " አለና እስትንፋሱ ቀጥ አለ … ሞተ !! እኔም እሱን ለማጠብና ለመከፈን የሚያግዘኝን ሰው መፈለግ ጀመርኩ ። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ የኔ ብጤ የሆኑ ለጂሀድ የወጡ ሰዎችን አገኘሁ ። ጠሯኃቸውና መጡ ። ስለሱም ነገርኳቸው ዱአ አደረጉለትና ከእኔም ጋር ተነስተው አጠብነውና ቀበርነው… በዛች ሌሊት ላይ በሕልሜ አረንጓዴ ልብስ ለብሶ ጀነት ውስጥ ሁኖ አየሁት!  " አንተ ያ ባልደረባዬ አይደለህ? " ብዬ ጠየቁት እሱም " አው " አለ " ይችን ደረጃ እንድትደርስ ያደረገህ ምንድን ነው?  " ስለው " ይችማ በመከራ ጊዜ ትዕግስት የሚያደርጉና በምቾች ጊዜ አመስጋኝ ለሆኑ ሰዎች ያለች ደረጃ ነች ! " አለኝ አውዛኢም እንዲህ ይላሉ ፦ " ያ ጥበበኛ ሰው ይህንን ንግግር ከነገረኝ ጀምሮ መከራ የሚደርስባቸውን ሰዎች ከመውደድ አልተወገድኩም  " ✍ أدهم شرقاوي ትርጉም ፡ ቢንት አብደላህ ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛

ከቀናቶች ሁሉ በላጭ በሆነው ጁሙዐ ቀን #ሶልዋት ስለማብዛት የተነገረበት! 🎙በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ   ŰŠ ŰŠ ŰŠ ŰŠ ŰŠ ŰŠ ŰŠ Umma Life] 👇 https://ummalife.com/umma1698048635              [Telegram] 👇 https://t.me/Mahfuzmuhdin               [Tik Tok] 👇 https://vm.tiktok.com/ZM6C7vsw2/

.............ትነቃ እንደሁ ንቃ.......... ይሄው ሊግጥህ ነው ቀን እያመቻቼ፣ ድምፁን ዝቅ አድርጎ ለነገ እያስመቼ፣ ሊሀልልህ ባዋጅ ቦሩ ሜዳ ጥሎ፣ ይኸው ቦረቦረህ ዝንጋታህ ሀይሎ። አንተ
.............ትነቃ እንደሁ ንቃ.......... ይሄው ሊግጥህ ነው ቀን እያመቻቼ፣ ድምፁን ዝቅ አድርጎ ለነገ እያስመቼ፣ ሊሀልልህ ባዋጅ ቦሩ ሜዳ ጥሎ፣ ይኸው ቦረቦረህ ዝንጋታህ ሀይሎ። አንተ ስትባላ ወንድምህ ሲናቆር፣ እንትና ከንትና መካፈልህ ሲከር፣ የዋህዳውን ኢስላም ስትበትን ስትበትን፣ ይኸው ጠላት ገባው ስትል እንትና እንትን። ትነቃንደሁ ንቃ ፅልመት ሳይበረታ፣ ግራ ቀኝ አማትር ሳትሆን ከርታታ፣ ስማኝ ሊበላህ ነው ንቃ ሳትረታ፣ ብዕሬን አትናቅ አልሻም ገለታ። የስም ተቃራኒን የስብስብ እርኩስ፣ ተጠንቀቅ ጧት ማታ ዳግመኛ እንዳይነግስ፣ ካንዣበበው ወጥመድ ከጎኑ ሳትደርስ፣ ይልቅ ይህን ጊዜ ነቅተህ ሀሳብ አፍስ። ለኢስላም ለነስሩ ድርሻ አለህ እንደኔ፣ አንግበሀል እና አደራና ወኔ፣ አትልፈስፈስ ከቶ ቅዋ ሁን ከጎኔ፣ ወንድም ነው ለወንድም ካብ ብለዋል ዘይኔ።ﷺ ገመድህን አጥብቅ ከቶ እንዳታላላ፣ ኢልሙን ከአሊሞች አትኳትን ከሌላ፣ ያንተን የድርሻህን አውቀህ ተንቀሳቀስ፣ ያለ ኢልምህ መግባት አያመጣም መንገስ። ችግራችን እኮ ይኸው ነው ወንድሜ፣ ያለ እውቀት መዳከር ሲያሰጠን ስያሜ፣ በኛ እንዳልነበረ ህመምህ ህመሜ፣ ይኸው ሆነ ባንተ አጣሁኝ ሰላሜ። ትነቃእንደሁ ንቃ ኢስላም ያው ኢስላም ነው፣ የዘመን ድሪቶ የማይሸፋፍነው፣ ከጥንት የከበረ ቃሉን አንድ አድርጎ፣ ኸሊቁ አላህ ነው ሌላን መች ፈልጎ። ------------------------------- ተፃፈ➲ #በፈትሁዲን_ዑመር 13/09/2015አ.ል

ሰው እንዴት ሙታን ይማፀናል? ~ ሙታን የሚጣሩ ብዙ ወገኖች አሉ። ሙታኖች አይጠቅሙም፣ አይጎዱም። ሙታን ምን አቅም አላቸው? እንኳን እነ ሸይኽ ጫሊ፣ አና፣ ዳና፣ ቃጥባሬ፣ አብሬ፣ አናጂና፣ ገታ፣ መጂት፣ ሸህ ዐሊ ጎንደር፣ ደገር፣ ... ታላቁ የአላህ ነቢይ ዒሳም እናታቸው መርየምም አይጠቅሙም አይጎዱም። ይሄው ጌታችን አላህ ዒሳንና መርየምን የሚያመልኩ ሰዎችን ሁኔታ ከተነተነ በኋላ እንዲህ ይላል፦ {قُلۡ أَتَعۡبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا یَمۡلِكُ لَكُمۡ ضَرࣰّا وَلَا نَفۡعࣰاۚ وَٱللَّهُ هُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡعَلِیمُ} {“ሰሚውና አዋቂው አላህ ሆኖ ሳለ ከአላህ ሌላ ለናንተ መጉዳትንና መጥቀምን የማይችልን ትገዛላችሁን?” በላቸው፡፡} [ማኢዳህ፡ 76] ወገኔ ሆይ! ለሁሉ የሚበቃ ህያው ጌታ እያለህ ሙታን ሰፈር ምን አልከሰከሰህ? ወላሂ አብሬት አልከው ጫሊ፣ ደገር አልከው ዳኒይ፣... እድሜ ልክህን ብትጮህ ማናቸውም አይሰሙህም። ቢሰሙህ እንኳ ምላሽ የሚሰጡበት አቅሙ የላቸውም። ይሄ የኔ ቃል አይደለም። ሃያሉ ጌታ ምን እንደሚል ተመልከት፦ {وَٱلَّذِینَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا یَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِیرٍ (13) إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا یَسۡمَعُوا۟ دُعَاۤءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُوا۟ مَا ٱسۡتَجَابُوا۟ لَكُمۡۖ وَیَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ یَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا یُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِیرࣲ (14)} {እነዚያም ከርሱ ሌላ የምትገዟቸው የተምር ፍሬ (ስሷ) ሽፋን እንኳን የላቸውም። ብትጠሯቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም። ቢሰሙም አይመልሱላችሁም። በትንሳኤ ቀንም እነሱን ከአላህ ጋር ማጋራታችሁን ይክዳሉ። እንደ ውስጠ-አዋቂው ማንም አይነግርህም።} [ፋጢር፡ 13-14] እንዲያውም እወቅ! እነዚህ ዛሬ ለጭንቅ ለችግር ይደርሱልኛል ብለህ የምትማፀናቸው አካላት ነገ በቂያማ ቀን ጠላቶችህ ነው የሚሆኑህ። ከራሴ አይደለም የማወራው። ምስክሬ ቁርኣን ነው፦ {وَمَنۡ أَضَلُّ مِمَّن یَدۡعُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَن لَّا یَسۡتَجِیبُ لَهُۥۤ إِلَىٰ یَوۡمِ ٱلۡقِیَـٰمَةِ وَهُمۡ عَن دُعَاۤىِٕهِمۡ غَـٰفِلُونَ (5) وَإِذَا حُشِرَ ٱلنَّاسُ كَانُوا۟ لَهُمۡ أَعۡدَاۤءࣰ وَكَانُوا۟ بِعِبَادَتِهِمۡ كَـٰفِرِینَ (6) وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَیۡهِمۡ ءَایَـٰتُنَا بَیِّنَـٰتࣲ قَالَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ لِلۡحَقِّ لَمَّا جَاۤءَهُمۡ هَـٰذَا سِحۡرࣱ مُّبِینٌ (7)} {እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ለሱ የማይመልስለትን ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ይበልጥ የጠመመው ማነው? እነሱም (ተጠሪዎቹ) ከጥሪያቸው የዘነጉ ሆነው ሳለ?! ሰዎች (ቂያማ) በተሰበሰቡ ጊዜም ለነሱ ጠላቶች ይሆናሉ። መመለካቸውንም የሚክዱ ይሆናሉ።} [አሕቃፍ፡ 5-6] ግዴለህም ከፍጡር አትነካካ። {ህያው በሆነው በዚያ በማይሞተው ላይ ተመካ።} [ፉርቃን፡ 58] ደግሞ እወቅ። ለጭንቅ ለችግር መጣራት፣ ሪዝቅ ፈልጎ፣ አደጋን ፈርቶ መማፀን፣ ዱዓእ ማድረግ ዒባዳ ነው፣ አምልኮት። ዒባዳ ደግሞ የፈጣሪ ሐቅ ስለሆነ ለፍጡር አይሰጥም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- الدُّعاءُ هو العبادةُ {ዱዓእ በእርግጥም አምልኮት ነው።} [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1329] ታዲያ ዱዓእ አምልኮት ከሆነ ለፍጡር መሄድ አለበትን? በጭራሽ! ልክ እንደ ሶላቱ፣ እንደ ፆሙ ለአላህ እንጂ ለማንም ሊሰጥ አይገባውም። ኃያሉ ጌታ እንዲህ ይላል {فَلَا تَدۡعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدࣰا} {ከአላህ ጋር አንድንም አትጣሩ!} [ጂን፡ 18] ነብዩም ﷺ {ስትለምን አላህን ለምን} ይላሉ። [ሚሽካቱል መሷቢሕ፡ 5302] ቀድሞ ነገር ፍጡር ማንስ ቢሆን ምን ሊፈይድ ይጠራል? አዛኙ ጌታ:- * {ለምኑኝ እመልስላችኋለሁ} አላለምን? ይህንን አታምንም? * {ባሪያዬ ስለኔ ከጠየቀህ እኔ ቅርብ ነኝ} አላለምን? ትጠራጠራለህ? * {አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን?} እያለ ነው። "አዎ በቂ አይደለም" ነው መልስህ? ከበቃህ ታዲያ ፍጡር ዘንድ ያውም ሙታን ሰፈር ምን ትሰራለህ? ለራስህ ስትል እወቅበት። ቁርኣንን ጥለህ ከአባት፣ ከአያት በመጣ ውርስ አትሸነፍ። በህሊናህ ላይ አትሸፍት። ሰው እንዴት በዚህ ዘመን ሙታን ይደርስልኛል ብሎ ያምናል? ልክፍት ነው! = ( Ibnu Munewor ፣ ሸዋል 18/1444 (ሚያዚያ 30/ 2015 ))

ይህ ከአንድ ሺህ አመት በፊት የነበረ የትኩስና የቀዝቃዛ ውሀ ቧንቧ ነው !! ኢብኑል ጀውዚ وصف دار ابن أفلح الشاعر 535 አመተ ሂጅራ ላይ ጠቅሶታል ። "بِثيون " ብሎም ሰይሞታል።
ይህ ከአንድ ሺህ አመት በፊት የነበረ የትኩስና የቀዝቃዛ ውሀ ቧንቧ ነው  !! ኢብኑል ጀውዚ    وؾف داع ابن أفلح الشاعر  535  አመተ ሂጅራ ላይ ጠቅሶታል ። "بِثيون " ብሎም ሰይሞታል። ወደ ቀኝ ካዞርከው ሙቅ ውሀ ሁኖ ይፈሳል። ወደ ግራ ካዞርከው ደግሞ ቀዝቃዛ ውሀ ሁኖ ይፈሳል። 📖 المنتظم ቀዳሚዎች በነበርንበት ጊዜ … !!! ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 ┏━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┓        @tolehaahmed ┗━ 🍃 ━━━━ 🍃 ━┛

ጥንቃቄ ለሴቶች! ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿أُرِيتُ النَّارَ فَإِذَا أَكْثَرُ أَهْلِهَا النِّسَاءُ يَكْفُرْنَ ". قِيلَ : أَيَكْفُرْنَ بِا
ጥንቃቄ ለሴቶች! ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿أُرِيتُ النَّارَ فَإِذَا أَكْثَرُ أَهْلِهَا النِّسَاءُ يَكْفُرْنَ ". قِيلَ : أَيَكْفُرْنَ بِاللَّهِ ؟ قَالَ : " يَكْفُرْنَ الْعَشِيرَ ، وَيَكْفُرْنَ الْإِحْسَانَ ؛ لَوْ أَحْسَنْتَ إِلَى إِحْدَاهُنَّ الدَّهْرَ، ثُمَّ رَأَتْ مِنْكَ شَيْئًا قَالَتْ : مَا رَأَيْتُ مِنْكَ خَيْرًا قَطُّ﴾ “ወደ ጀሀነም እሳት ተመለከትኩ በውስጧ ከሃዲ የሆኑ ሴቶችን በዝተው ተመልክቻለሁ። እንዲህ ተባሉ፦ የሚክዱት አላህን ነውን? እሳቸውም አሉ፦ ባሎቻቸውን ይክዳሉ፣ የተዋለላቸውን በጎ ውለታ ይክዳሉ። ከመካከላቸው አንዷ እድሜ ልኳን መልካም ሲዋልላት ከርሞ፤ አንድ ግዜ የሆነ ነገር ጎድለት ከተመለከተች ካንተ ምንም መልካም ነገር ሲደረግልኝ አይቼ አላውቅም ትላለች።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 29 ✅በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ ❤️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ 😔፦ https://bit.ly/486xnrS 📱፦ https://bit.ly/41zEZkk ✅፦ https://bit.ly/4arMbTx ❌፦ https://bit.ly/41tIUPv 👀፦ https://bit.ly/3UTTSwh

⚠️Where is UNICEF? Where is international law? Where is the Geneva Convention? Where are the human rights organizations? Where is the Universal Declaration of Human Rights? Where is the United Nations I spit on? Where are the 57 Islamic countries? 2 billion Islamic world?

- ሞትን ማስታወስ። የዱንያን ለዛ ቆራጭ የሆነውን ሞትን የሚያስታውስ ሰው ለወንድሙ ክፋት የሚያስብበት ድፍረት አያገኝም። - የአላህን ውሳኔ መውደድ። አንዱን ድሃ አንዱን ሀብታም፣ አንዱን ቆንጆ አንዱን ፉንጋ፣… ያደረገው ሁሉን ቻዩ ጠቢቡ አላህ ነው። ሰዎች በምርጫቸው ብቻ አይደለም ከሌላው የሚበልጡት። ስለሆነም ሰዎችን በያዙት ፀጋ መመቅኘት በዚህ መልኩ ፀጋዎችን የከፋፈለውን ጌታ ውሳኔ መፃረር ነው። ይህን ከግምት ያስገባ ሰው ከምቀኝነት ክፉ ቫይረስ ራሱን ይጠብቃል። ከውስጡ እሳቱ ቢቀጣጠል እንኳን ስሜቱን ረግጦ ይይዛል። - የዱንያን ርካሽነት፣ ዝቃጭነት መረዳት - ለአማኞች መልካምን ማሰብ፣… = (ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 24/2008)

ምቀኝነት ፍትሃዊ ልክፍት! ~ ምቀኝነት የመጀመሪያው አላህ የታመፀመበት ወንጀል ነው። ጌታችን አላህ “ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ ለፈጠርኩት እንዳትሰግድ ምን ከለከለህ? ኮራህ? ወይስ ከትእቢተኞቹ ሆንክ?” ሲለው የሰጠው መልስ ያገጠጠ ምቀኝነት ነበር። “እኔ ከርሱ (ከኣደም) በላጭ ነኝ። ከእሳት ፈጠርከኝ። እሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው!” ነበር ያለው። [ሷድ፡ 75 - 76] ለመስገድ አሻፈረኝ ማለቱ ለኣደም በተሰጠው ክብር ቅናት ስለገባው ነበር። ምቀኝነት ጥንታዊ በሽታ ነው። የአባታችን አደም ልጅ ወንድሙን የገደለው በምቀኝነት ምክንያት ነው። ዩሱፍን ወንድሞቻቸው ከውሃ ጉድጓድ የጣሏቸው በምቀኝነት ተነሳስተው ነው። “ዩሱፍና ወንድሙ ወደ አባታችን ዘንድ ከኛ ይበልጥ የተወደዱ ናቸው” በሚል መነሻ። [ዩሱፍ፡ 8] አይ.ሁዶች የነብዩን ﷺ ነብይነት ለመቀበል “አሻፈረን” ያሉት በምቀኝነት ሰበብ ነው። ከኛ ዘር ሳይሆን ከዐረብ ሆነ በሚል ሰበብ። የመካ አጋሪዎች የሙሐመድን ﷺ ነብይነት ለመቀበል የዘጋቸው ቀዳሚው ምክንያት ምቀኝነት ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡- {وَقَالُوا۟ لَوۡلَا نُزِّلَ هَـٰذَا ٱلۡقُرۡءَانُ عَلَىٰ رَجُلࣲ مِّنَ ٱلۡقَرۡیَتَیۡنِ عَظِیمٍ (31) أَهُمۡ یَقۡسِمُونَ رَحۡمَتَ رَبِّكَۚ نَحۡنُ قَسَمۡنَا بَیۡنَهُم مَّعِیشَتَهُمۡ فِی ٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَاۚ وَرَفَعۡنَا بَعۡضَهُمۡ فَوۡقَ بَعۡضࣲ دَرَجَـٰتࣲ لِّیَتَّخِذَ بَعۡضُهُم بَعۡضࣰا سُخۡرِیࣰّاۗ وَرَحۡمَتُ رَبِّكَ خَیۡرࣱ مِّمَّا یَجۡمَعُونَ (32)} “ 'ይህም ቁርኣን ከሁለቱ ከተሞች በታላቅ ሰው ላይ አይወረድም ኖሯልን?' አሉ። እነሱ የጌታህን ችሮታ ያከፋፍላሉን?! እኛ በቅርቢቱ ህይወት ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል። ከፊላቸውም ከፊሉን ሰራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች አስበለጥን። የጌታህም ፀጋ ከሚሰበስቡት በላጭ ናት።” [አዙኽሩፍ፡ 31 - 32] የመፃህፍቱ ሰዎች በሙስሊሞች ላይ ለሚያደርሱት ሁሉ ቀዳሚው ምክንያት ምቀኝነት ነው። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- {وَدَّ كَثِیرࣱ مِّنۡ أَهۡلِ ٱلۡكِتَـٰبِ لَوۡ یَرُدُّونَكُم مِّنۢ بَعۡدِ إِیمَـٰنِكُمۡ كُفَّارًا حَسَدࣰا مِّنۡ عِندِ أَنفُسِهِم مِّنۢ بَعۡدِ مَا تَبَیَّنَ لَهُمُ ٱلۡحَقُّۖ} “ከመፅሀፉ ባለቤቶች ብዙዎቹ እውነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ ከነፍሶቻቸው በሆነው ምቀኝነት ከእምነታችሁ በኋላ ከሃዲዎች አድርገው ሊመልሷችሁ ተመኙ።” [አልበቀራህ፡ 109] ምቀኝነት የአላህን ውሳኔ መፃረር ነው። አላህ ለፈለገው ይሰጣል፣ ከፈለገው ይነሳል። አንድን አካል አላህ በሆነ መልኩ ፀጋውን ከዋለለት በኋላ በዚያ ላይ ቂም ማርገዝ፣ በክፋት መመልከት የሰጪውን ጌታ ውሳኔ በይሁንታ አለመቀበል ነው። ምቀኛ ውስጡን ያቃጥላል እንጂ ምንም ጠብ የሚያደርገው ነገር የለም። ምቀኛ በማያገባው ገብቶ ሲብከነከን በከንቱ ራሱን ያቃጥላል። እውነት ለመናገር እንዲያውም ምቀኝነት ፍትሃዊ በሽታ ነው። በብዛት ከሚመቀኙት አካል ይልቅ ምቀኛውን ራሱን ነው ይበልጥ እንቅልፍ የሚነሳው፣ ሰላም የሚያሳጣው። ምቀኛ ሰው ሲበዛ የሚገርም ፍጡር ነው። ከራሱ ማግኘት ይልቅ የሚያሳስበው የጓደኛው ማጣት ነው። ምቀኛ እንግዳ የሆነ ፍጡር ነው። የሚደርስብህን ወይም ያለብህን ብዙ ችግር ችላ ብሎ ያለችህ ጥቂት መልካም ላይ የክፋት አይኑን ይጥልብሃል። ደግነቱ በብዛት ውስጡን የሚያቃጥለው፣ በሀሳብ የሚያብከነክነው ራሱን ነው። ምቀኛ ሰው ሴረኛ ነው! ከወንድሙ ላይ ያለውን ፀጋ ለማጥፋት ብዙ ይዳክራል። ምቀኛ ሰው አታላይ ነው። ምቀኝነቱ እንዳይታወቅበት የሚመቀኘውን አካል ህፀፅ እየለቀመ አቃቂር እያወጣ ሊጎዳው፣ ሊያሳጣው፣ ሊተናኮለው ያስባል። የሚመቀኘው አካል ዘንድ ያለው ወንጀል አላህ ለሱ መልካም መዋሉ ነው። አለቀ። ነገር ግን ምቀኛ ምቀኝነቱ እንዲታወቅ አይሻምና ለጥፋቱ የተለያዩ ሽፋኖችን ይሰጣል። በጣም የሚያስጠላው ደግሞ ለዲን ለኢስላም በመቆርቆር ስም የሚፈፀም ምቀኝነት ነው፡፡ ይሄ ድርብ የሆነ አስቀያሚ ጥፋት ነው። ምቀኝነቱ ብቻውን በቂ ጥፋት ነበር። ኢስላማዊ ሽፋት ሲሰጠው ደግሞ ሌላ ሸፍጥ ታክሎበታል። በሱና ስም የሚፈፀሙ ምቀኝነቶች በሽ ናቸው። በመካከላቸው የሚገኙ ከባባድ ጥፋቶችን ከቡድን አጋራቸው ስለመጣ ብቻ እንዳላዩ እያለፉ ለሌሎች አቃቂር የሚያወጡት የስሜት ተከታዮች ናቸው። በሱና ስም የምቀኝነት ፈረስ የሚጋልብ ብዙ ሰው አለ። ከሱ ወይም ከወዳጁ ቢመጣ የማይቃወመውን ነገር ከማይወደው አካል ስለመጣ ብቻ መቃወም ምቀኝነት ካልሆነ ምን ሊባል ነው?! ከጓደኛው ቢወጣ የማይቃወመውን ነገር ከሌላ ስለመጣ ብቻ መቃወም ምን ማለት ነው?! አላህ ስሜትን ከመከተል ይጠብቀን። በ“ቃለላህ” እና በ “ቃለ ረሱሉላህ” ሽፋን ምቀኝነታቸውን ሊሸፍኑ አጉል የሚታገሉ የዋሆችን መመልከት የተለመደ ነው። በሱና ዑለማዎች ስም የምቀኝነት ገበያቸውን የሚያሟሙቁ ሰዎች ይሄው ብርቅ አይደሉም ዛሬ። ዛሬ ላይ በምቀኝነት መንሰኤ እየተለያዩ ልዩነታቸውን ዲናዊ ሽፋን የሚሰጡ ወንድማማቾች በተጨባጭ ያጋጥማሉ። ብቻ በየዘርፉ የበዛውን ምቀኝነት ስናይ ቆም ብለን ወደ ውስጥ እንድንመለከት ደወል ሊሆነን ይገባል። ስለዚህ አላማዬ ራሴን ጨምሮ ወንድም እህቶች በሙሉ ውስጣችንን እንድንፈትሽ ማስታወስ ነው። መቼም ከዚህ ክፉ በሽታ የሚተርፍ ሰው ማገኘት አዳጋች ነው። ልዩነቱ ውስጥን ከማሸነፍ ወይም ስሜትን ከማስተናገድ ላይ ነው፡፡ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ “(ምቀኝነትን) ወራዳው ግልፅ ሲያወጣው ክቡሩ ግን አምቆ በመያዝ ይሰውረዋል” ይላሉ። [አልመጅሙዕ፡ 10/124] ምቀኝነት ከአማኝ የማይጠበቅ ቆሻሻ ባህሪ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- لا يجتمعان في جوف عبدٍ الإيمان والحسد “በአንድ አማኝ ባሪያ ልብ ውስጥ ኢማን እና ምቀኝነት ባንድ ላይ አይሰባሰቡም!” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7616] ምቀኝነት የኸይር ስራ ሁሉ ፀር ነው። ነብዩ ﷺ ምቀኝነት “ምላጭ ነው! ፀጉርን ይላጫል ማለቴ አይደለም፡፡ ይልቁንም ዲንን ይላጫል!” ይላሉ። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3361] በነገራችን ላይ ከምቀኞች ምቀኝነት እተርፋለሁ ብለህ ነፍስህን እንዳታስከጅላት። የማይሆን ነገር እየተመኘህ አጉል አትባዝን። በተለይ ደግሞ ሰዎች ዘንድ የሌለ የሆነ ኒዕማ አላህ ከዋለልህ ያለጥርጥር ምቀኛህ ይበዛል። ስለዚህ ሌሎች ዘንድ ካለው የሚበልጥ ሀብት፣ ስልጣን፣ እውቀት፣ ተሰሚነት፣ ከሰዎች ዘንድ መወደድ፣ ውበት፣ ቁንጅና፣ ታዋቂነት፣ ወዘተ ከኖረህ ያለጥርጥር ምቀኛህ ይበዛል። ቀታዳህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “በሰዎች ላይ ፀጋዎች አይበረክቱም፣ ጠላቶቻቸው የሚበረክቱ ቢሆን እንጂ።” [አልዒለል ሊልኢማም አሕመድ፡ 116] ራስን ከምቀኝነት ማፅጃ መንገዶች

► « ዶክተር ነበር መሆን የምፈልገው» ‼️ « ቆይ እኛ ምንድነው ያደረግናቸው » ⁉️ « እሺ እኔ ምንድነው የማደርገው!? ቤተሰቦቼን መርዳት አልችል፣ ምንም ነገር ማድረግ አልችልም ምክንያቱም 10 አመቴ ነው‼️ » ⭕️ አለም ትኩረት ከነፈጋት ቀዬ 〽️ ቤተሰቦቿ በፍርስራሽ ከተቀበሩባት ታዳጊ! ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Join:- YouTube.com/@SecretsofTruth tiktok.com/@secretsof_truth Twitter.com/Secretsof_Truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 ለየትኛውም ለአስታየትና ድጋፍ:- t.me/ReshadMuzemil

ምግብ አያነውሩም! ከአቡ ሁረይራ (رضيﷲ عنه) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦ ﴿ما عابَ النبيُّ (ﷺ) طَعامًا قَطُّ؛ إنِ اشْتَهاهُ أكَلَهُ، وإلّا تَرَكَهُ.﴾ “ነ
ምግብ አያነውሩም! ከአቡ ሁረይራ (رضيﷲ عنه) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦ ﴿ما عابَ النبيُّ (ﷺ) طَعامًا قَطُّ؛ إنِ اشْتَهاهُ أكَلَهُ، وإلّا تَرَكَهُ.﴾ “ነቢዩ (ﷺ) ምግብን አነውረው አያውቁም። ከፈለጉ ይበሉታል ካልፈለጉ ይተውታል።” 📚 ቡኻሪ (3563) ሙስሊም (2064) ዘግበውታል

ምላስህን በዚክር አርጥብ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿خيرُ العملِ أن تُفارِق الدنيا ولسانُك رَطبٌ من ذكرِ اللهِ﴾ “መልካም ስራ ማለት ከዱኒያ ቆይታህ እየተለየህ
ምላስህን በዚክር አርጥብ! ረሱል () እንዲህ ብለዋል፦ ﴿خيرُ Ř§Ů„ؚملِ ŘŁŮ† ŘŞŮŮŘ§ŘąŮŮ‚ Ř§Ů„دنيا ولسانُك رَطبٌ من ذكعِ اللهِ﴾ “መልካም ሾል ማለት ከዱኒያ ቆይታህ እየተለየህ ምላስህ በዚክር (አላህን በማውሳት) መርጠቡ ነው።” 📚 ሶሂህ አልጃሚ: 3282 ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Tikto: tiktok.com/@secretsof_truth Instagram: Instagram.com/secretsof_truth Telegram: t.me/Secretsof_Truth Facebook: Fb.com/SecretsofTruth1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil

ባለ ነገር መብቃቃት! ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿والذي نَفْسِي بيَدِهِ، لَأَنْ يَأْخُذَ أحَدُكُمْ حَبْلَه، فيَحْتَ
ባለ ነገር መብቃቃት! ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿والذي نَفْسِي بيَدِهِ، لَأَنْ يَأْخُذَ أحَدُكُمْ حَبْلَه، فيَحْتَطِبَ على ظَهْرِه؛ خَيْرٌ له مِن أنْ يَأْتيَ رَجُلًا، فيَسْأَلَه، أعْطاهُ أوْ مَنَعَه.﴾ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ከናንተ አንዳችሁ ሌላ ሰው ከሚለምን ይልቅ ሰጠውም አልሰጠውም እስር እንጨት በጀርባው እየተሸከመ (ኑሮን ቢገፋ) ይመረጣል።” 📚 ቡኻሪ (1480) ሙስሊም (1042) ዘግበውታል በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦