es
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Ir al canal en Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Mostrar mĂĄs
213
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 dĂ­as
-430 dĂ­as
Archivo de publicaciones
ዙልሒጃ_ዘጠኝንየውሙ_ዓረፋንበምን_መልኩ_እናሳልፍ_በኡስታዝ_አሕመድ_ሸይኽ_ኣደም_1.mp37.45 MB

🌕 የዙልሒጃ 9ኛው የዐረፋ ቀን የፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 20/June 27 ይውላል ከሌሎች ቀናት ይበልጥ ለምላሽ በጣም ቅርብ የሆነው የዱዓ ወቅት የዐረፋ ቀን ነው፡፡ ከዐረፋ ቀን ተሸሎ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀንም የለም። ስለዚህ ይህን አጋጣሚ ዱዓእ በማድረግና ወደአላህ በመጠጋት ተጠቀሙበት 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 🌕 ሓጅ አድራጊዎች ያለ ፆም በዐረፋ ተራራ ላይ ከእኩለ-ቀን (ዙህር) አንስቶ መግሪብ እስኪደርስ ይቆያሉ፣ በዱዓም ጌታቸውን ይማጸናሉ፡፡ ጌታቸውም ወደነሱ ይቀርባል። አላህም በተከበሩት መላእክት ላይ የሚኮራበት፣ ባሮቹ የሚሰሩትን ስራ የሚወድበትና የሚቀበልበት ቀን ነው 📗ረሱል ﷺ በዐረፋ ምሽት ላይ አላህ ዐረፋ ላይ ወደቆሙት ሰዎች እያመላከተ “ወደባሮቼ ተመለከቱ ጸጉራቸው የተንጨባረረና አቧራ የለበሱ ሆነው ወደኔ መጥተዋል፡፡” እያለ በመላእክቱ ላይ ይኮራል ብለዋል 🍏 ሓጅ ያላደረጉት ደግሞ ቀኑን በፆምና በተለያየ ዒዳባህ ያሳልፉታል። በዚያም ቀን ብዙዎች በክፉ ተግባራቸው እሳት የተገባቸው፣ በአላህ ቸርነት ከእሳት ነጻ ይባላሉ። 📗ረሱል (ﷺ) ከዐረፋ ቀን ይበልጥ በዚያ ቀን ሸይጣን እጅግ አንሶ፣ እጅግ በጣም የሚርቅበት፣ እጅግ የሚዋረድበትና እጅግ የሚበሳጭበት ቀን የለም፡፡ ይህም የሚሆነው የአላህ እዝነት በመወረዱ፣ አላህም ሰዎችን ከሰሯቸው ትልልቅ ወንጀሎች ይቅር በማለቱ ነው፡፡ ብለዋል፡፡ 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 🌕 ይህ የዐረፋ ቀን ከሌሎች ቀናት ከሚለይባቸው ውስጥ፡- 1️⃣ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን መሆኑ፡- 📗 እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከዐረፋ ቀን ተሸሎ ብዙ ሰው ከእሳት ነጻ የሚባልበት ቀን የለም”። (ሙስሊም) 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 2️⃣ ዲኑ የተሟላበት ቀን መሆኑ፡- 🟢 ۞ "…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ። ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ። ለናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ…" ۞ (📖 ሱረቱል ማኢዳህ 5:3) 🍏 ይህ አንቀጽ የወረደው በዙል ሒጃ ወር፣ የመሰናበቻው ሐጅ በ 9ኛው ቀን፣ በዕለተ ጁምዓ በዐረፋ ተራራ ላይ ነበር 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 3️⃣ ፆሙ የሁለት አመት ኃጢአት ያስምራል፡- 📗 አቢ ቀታዳህ እንዳሉት የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም የሁለት ዐመት (ያለፈውንና የሚመጣውን) ኃጢአት ያስምራል”። (ከቡኻሪ በስተቀር ሁሉም የዘገበው) 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 4️⃣ የሙስሊሞች ዒድ መሆኑ፡- 📗 ዑቅበተ ኢብኑ ዐሚር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን፣ የእርዱ ቀን፣ ቀጣዮቹም 3ቱ ቀናት የኛ ዒዳችን ነው”። (ሶሒሑል ጃሚዕ 8192) 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 5️⃣ ለአምስት ቀናት የሚቆየው ተክቢራም የሚጀምረው በዚሁ በዐረፋ በዘጠነኛው ቀን ፈጅር ሶላት ጀምሮ ነው 🌕 በዚሁ ቀን ከፈርድ ሶላት በኋላ ሶስት ጊዜ አስተግፊሩላህ እንበልና ከዛም አላሁመ አንተ–ሰላም ...... ካልን በኋላ በቀጥታ ወደ ተክቢሩ በመግባት፡- 🗣 "አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር። ላ ኢላሀ ኢልለሏህ፣ አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ" እንበል 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 6️⃣ ከዱዓኦች ሁሉ በላጩ በዚህ ቀን መሆኑ:– 🌕 በማንኛውም ቀንና ለሊት፣ በማንኛውም ስፍራና ሁኔታ ወደ አላህ የሚደረገው ዱዓ በሩ ክፍት ነው። ተመላሽነት የለውም፣ ሆኖም በዐረፋ ቀን የሚደረገው ዱዓ ግን ከየትኛውም የተሻለ ነው 📗 ከዐብዱላህ ኢብኑ አምሩ ኢብኑል–ዓስ እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:– "ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓእ ነው፡፡ እኔና ከበፊቴ የነበሩት ነቢያት ከተናገርነው ቃላት ሁሉ በላጩ፡- ‹‹ላ ኢላሀ ኢልለሏሁ፣ ወሕደሁ፣ ላ-ሸሪከ ለህ፣ ለሁል-ሙልኩ፣ ወለሁል-ሐምድ፣ ወሁወ ዐላ-ኩሊ ሸይኢን ቀዲር›› የሚለው ነው" (ቲርሚዚይ 3585፣ ሶሒሑል-ጃሚዕ 3274) 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 🌕 ከዐረፋ በፊት ዱዓ ለማድረግ የምትፈልጉት ሃሳብና ጉዳዮችን መዝግቡ፡፡ በቃላቹ በሸመደዳቹት ቁርአናዊ እና ነቢያዊ ዱዓዎች ዱዓዎች ዱዓእ አድርጉ፡፡ በቃል ካልሸመደዳቹ ጽፋቹ ታገዙ። ስም እየጠራቹህ ለወላጅ፣ ለቤተሰብ፣ ለወንድም፣ ለወዳጅ መልካም የሆኑ ዱዓዎችን አርርጉላቸው፡፡ ምክንያቱም፡- በድብቅ ለወንድሙ ዱዓ ላደረገ ሰው መላኢካ፡- “ያደረክለት አምሳያ ላንተም ይሁን፡፡” ይለዋል፡፡ ለምድራዊው ሕይወትና ለወዲያኛው ዘላለማዊ ዓለም በሚጠቅም ነገር መልካም ዱዓእ አድርጉ፡፡ መልካም በሆኑት የአላህ ስሞች ዱዓእ ያድርጉ፡፡ ለምሳሌ፡- እጅግ አዛኝ የሆንከው አላህ ሆይ! እዘንልኝ፡፡ እጅግ በጣም መሐሪ የሆነከው አላህ ሆይ! ማረኝ፡፡ አንድን ዱዓእ ለብዙ ጊዜያት እየደጋገሙ ያድርጉ፡፡ አላህ በዱዓእ ላይ የሙጥኝ መባልን ሐያእ ያደርጋል፡፡ ዱዓእ ሲያደርጉ ልቦናዎን ወደ አንድ ቦታ ይሰብስቡና ወደአላህ ይቅረቡ፡፡ 🔜 በቀጣይ ፖስት ከቁርአን፣ ሐዲሥና የተመረጡ ከተሰበሰቡ ዱዓዎች መካከል የተወሰኑትን ፖስት አድርጋለው ኢንሻ’ አላህ 🔹🔹🔹🔸🔸🔸 📲 ሼር በማድረግ ለእህትና ወንድሞች እንዲደርሳቸው ያድርጉ፣ "ወደ ኸይር ያመላከተ (ኸይሩን) እንደሚሰራው ሰው ነው (አጅሩ አለው)" ይላሉ ነብዩ ﷺ ©️©️ t.me/ReshadIbnuMuzemil

☑️ የአላህ እኛንም ወፍቀን‼️ t.me/ReshadIbnuMuzemil
☑️ የአላህ እኛንም ወፍቀን‼️ t.me/ReshadIbnuMuzemil

☑️ የአላህ እኛንም ወፍቀን‼️ t.me/ReshadIbnuMuzemil
☑️ የአላህ እኛንም ወፍቀን‼️ t.me/ReshadIbnuMuzemil

☑️ ልባችን የተንጠለጠለው (ማየት የጓጓነው)‼️ .....
☑️ ልባችን የተንጠለጠለው (ማየት የጓጓነው)‼️ .....

የአረፋ ቀን ትሩፋቱ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مِنْ يَوْمٍ أَكْثَرَ مِنْ أَنْ يُعْتِقَ اللَّهُ فِيهِ عَبْدًا مِنَ النَّارِ مِنْ يَوْمِ عَر
የአረፋ ቀን ትሩፋቱ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿مِنْ يَوْمٍ أَكْثَرَ مِنْ أَنْ يُعْتِقَ اللَّهُ فِيهِ عَبْدًا مِنَ النَّارِ مِنْ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَإِنَّهُ لَيَدْنُو، ثُمَّ يُبَاهِي بِهِمُ الْمَلَائِكَةَ، فَيَقُولُ : مَا أَرَادَ هَؤُلَاءِ﴾ “ከዐረፋ ቀን የበለጠ አላህ ባሪያውን ከአሳት ነፃ የሚያወጣበት ቀን የለም። እርሱም ይቀርባል። ከዚያሞ በነርሱ መላእክቶችን ይፎካከርባቸዋል። አንዲህም ይላል፦ ‘እነዚህ (ባሮቼ) ምን ፈልገው ነው?’” ‌📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1348 ©️©️ BuhariMuslimAmharic t.me/ReshadIbnuMuzemil ☑️ facebook.com/ReshadIbnuMuzemil ☑️ facebook.com/ReshadMuzemil2 ☑️ facebook.com/ReshadIbnuMuzemil1

THE SUPERIORITY OF Al-HAJJ Al-MABRUR  🕋 Allah's Messenger () said: "(The performance of) Umrah is an expiation for the sins committed between it and the previous one. And the reward of Al-Hajj Al-Mabrur (the one accepted by Allah) is nothing but Paradise." 📚: Sahih Bukhari 1773 Narrated Aisha (رضي الله عنها), the mother of the faithful believers: I said: "O Allah's Messenger ()! We consider Jihad as the best deed. Should we (women) not participate in Jihad?" The Prophet () said: "The best Jihad (for women) is Hajj Mabrur (the one accepted by Allah.)" 📚: Sahih Bukhari 1520 The Prophet Muhammad () said: "Whoever performs Hajj for Allah's sake only and does not have sexual relations with his wife, and does not do evil or sins; then he will return (after Hajj, free from all sins) as if he was born anew." 📚: Sahih Bukhari 1521 Al-Hajj Al-Mabrur most probably means the Hajj which is performed with the intention of seeking Allah's Pleasures only and is in accordance with the Prophet's legal ways; without committing sins and is acceptable to Allah ✨ t.me/ReshadIbnuMuzemil

🗣TAKBEERAT REMINDER💡 ⊰᯽⊱┈──╌❊╌──┈⊰᯽⊱ ✨تكبيرات✨ ♦️الله اكبر الله اكبر الله اكبر♦️ ♦️لااله الا الله والله اكبر♦️ ♦️الله اكبر♦️ ♦️ولله الحمد♦️ 💬 Takbeerat all the way till the 13th of Dhul Hijjah ✨‎ إِنْ شـــــــآء اللّٰــــــــه ✨ ⊰᯽⊱┈──╌❊╌──┈⊰᯽⊱ It Is Recommended For The Men To Raise Their Voices When Saying The Takbīr During The First Ten Days Of Dhū al-Ḥijjah Imām al-Bukhāri رحمه الله said: "Ibn 'Umar رضي الله عنه and Abū Hurayrah رضي الله عنه would go out to the market place on the ten days of Dhū al-Ḥijjah saying the takbīr. Upon hearing them, the people would do likewise." ● [صحيح البخاري ٣٢٩/١] #Dhul_Hijjah Join:- t.me/ReshadIbnuMuzemil

🎀Qur'an Recitation🎀 Surah Al Baqarah Ayah-107 By Abdullah Khalaf #Recitation #Dhul_Hijjah #Hajj Join:- t.me/ReshadIbnuMuzemil

The Excellence Of The Day Of ‘Arafah Allaah, The Most High states in His Book: ﴿وَالْيَوْمِ الْمَوْعُودِ وَشَاهِدٍ وَمَشْهُود﴾‏ ❝And by the Promised Day [i.e. the Day of Resurrection]; And by the witnessing day [i.e. Friday], and by the witnessed day [i.e. the day of 'Arafat [Hajj] the ninth of Dhul-Hijjah]…❞ [Qur’ān, Surah Al-Burooj, (2-3) | Translated By Dr. Muhammad Muhsin Khan] - From Abee Hurairah [رضي الله عنه] who said that the Prophet [ﷺ] said: ❝The Promised Day is: The Day of Resurrection; and the day which is witnessed is: the day of ‘Arafah; and the witness is: the day of Friday. And the sun has not risen nor has it set upon a day that is better than it. In it is an hour in which a believing servant does not coincide supplicating to Allaah for good – except that Allaah will answer him; and nor does he seek refuge from anything except Allaah will grant him refuge from it.❞ [Reported By At-Tirmidhee | Al-‘Allaamah Al-Albaanee: 'Hasan' In His Saheeh Sunan At-Tirmidhee, (No. 3339) | Translated By Abū Haatim M. Farooq] - Ibn Rajab [رحمه الله] said: ❝Upon this basis; if the day of ‘Arafah falls on a Friday – then there is incorporated into that day the witness and the witnessed.❞ [Lataa-if Wal Ma’aarif, (Page: 375) | Translated By Abū Haatim M. Farooq] - From ‘Umar Bin Al-Khattaab [رضي الله عنه] that a man from the Jews said to him: ❝'O leader of the believers; there is an Aayah in your Book which you read; if it had been revealed to the like of us Jews then we would have taken that day as an ‘Eid.' So he said: 'which Aayah is that?' he said: ﴿الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإسْلامَ دِينًا﴾‏ «This day I have perfected for you your religion and completed My favour upon you and have chosen for you Islaam as your religion» [Al-Maa-idah: 3] So ‘Umar said: 'Indeed we know of that day as well as the place in which it was revealed upon the Prophet [ﷺ] - and he was standing at ‘Arafaat on a Friday.'❞ [Reported By Al-Bukhārī, (No. 45) | Muslim, (No. 7443) | Translated By Abū Haatim M. Farooq] - From ‘Aisha [رضي الله عنها] who said that the Messenger of Allaah [ﷺ] said: ❝There is no day in which Allaah sets free more slaves from the Hell-Fire than He does on the Day of ‘Arafah.❞ [Reported By Muslim, (No. 1277) | Translated By Abū Haatim M. Farooq] ©️©️ t.me/ReshadIbnuMuzemil

ሑጃጆች ልብ ይበሉ! ▪️የቂራን ወይም የተመቱዕ እርድ ግዴታ የሆነበት ሰው የማረድ አቅም እያለው ማረዱን ትቶ መጾም አይፈቀድለትም:: ምክንያቱም የቁርኣን አንቀጹ "የሚያርደውን እንሰሳ ያላገኘ... ይ
+1
ሑጃጆች ልብ ይበሉ! ▪️የቂራን ወይም የተመቱዕ እርድ ግዴታ የሆነበት ሰው የማረድ አቅም እያለው ማረዱን ትቶ መጾም አይፈቀድለትም:: ምክንያቱም የቁርኣን አንቀጹ "የሚያርደውን እንሰሳ ያላገኘ... ይጹም" ነውና የሚለው። -(አልበቀረህ 196-) ማረድ እየቻሉ ወደ ጾም መሸጋገር የሚቻለው እንደ- ጸጉርን መላጨት፣ ሽቶ መቀባትና ወዘተ. መሰል በኢሕራም ምክንያት የተከለከሉ ነገሮችን ላደረገ ሰው ነው። ገንዘብ እያለ በመሰሰት ወይም ገዝቶ እራስ ማረድን እንኳ ባይችሉ ፈቃድና እውቅና ላላቸው ተወክለው ለሚያርዱ ተቋማት አለመስጠት ሐጅ/ዑምራን ያጎድላል (ወንጀለኛ ያደርጋል)። ▪️ልክ እንደዚሁ የሐጅ ቀናት ሳይጠናቀቁ በፊት መጾም አለበት የተባለን ጾም በግዴለሽነት ሳይጾም የሐጅ ቀናት ያለቁበት ሰው ወንጀለኛ ይሆናል። ፈጥኖ መቶበትና ጊዜው ቢያልፍም ያለበትን ጾም መክፈል ይኖርበታል። ✍️ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ©️©️ ዛዱል መዓድ             📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው! አል-ኢማሙ ማሊክ t.me/ReshadIbnuMuzemil

Arafat Khutbah to be translated in 20 languages! 1. English 2. French 3. Malay 4. Urdu 5. Persian/ Farsi 6. Chinese 7. Turkis
Arafat Khutbah to be translated in 20 languages! 1. English 2. French 3. Malay 4. Urdu 5. Persian/ Farsi 6. Chinese 7. Turkish 8. Russian 9. Hausa 10. Bengali 11. Swedish 12. Spanish 13. Swahili 14. Amharic 15. Italian 16. Portuguese 17. Bosnian 18. Malayalam 19. Filipino 20. German የዓረፋ ኹጥባ ከዓረብኛ ወደ ሌላ ቋንቋ ከሚተረጎሙ ቋንቋዎች አማርኛ እንደሚገኝ Haramain Sharifain አሳውቋል ©️©️ t.me/ReshadIbnuMuzemil

የኡዱሒያን እርድ የሚመለከቱ ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች ~ ኡዱሒያ ማለት በዒደል አድሓ ቀን ወደ አላህ ለመቃረብ ታስቦ የሚታረድ እርድ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ በተግባር ፈፅመውታል፡፡ መዲና ላይ አስር አመት ሲኖሩም ኡዱሒያን ያርዱ ነበር፡፡ [ሚሽካት፡ 1475] እንዲፈፀምም አዘዋል፡፡ ስለዚህ አቅም ያለው ሰው ሊፈፅመው ይገባል ማለት ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “አቅሙ እያለው ኡዱሒያን ያላረደ ሰው መስገጃችንን እንዳይቀርብ” ብለዋል፡፡ ኡዱሒያ ብዙሃን ዑለማኦች ዘንድ የጠነከረች ሱና ነች። ከፊል ምሁራን ዘንድ ደግሞ ግዴታ ነች። ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - ከሁለቱ ሃሳቦች የሚጎላው ግዴታ ነው የሚለው ነው ይላሉ። ግዴታም ቢሆን ታዲያ ያልቻለ ሰው ኡዱሒያ ለማረድ ብሎ እዳ እንዲገባ / እንዲበደር አይገደድም። ለኡሑዲያ የሚታረደው እንስሳ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት 1. የሚታረደው እንስሳ ከበግ፣ ፍየል፣ ከብት እና ግመል ውስጥ ብቻ መሆን አለበት። 2. ከብትና ግመልን በጋራ ማረድ የፈለገ አንዱ ቢበዛ ለ7 ሰው ነው መሆን ያለበት፡፡ ከዚያ መብለጥ የለበትም። አንዱ ለ 7 ሰው ከተቻለ ቁጥራቸው ከ 7 ያነሰ ሆነው ቢያርዱ የበለጠ ያብቃቃል። ፍየልና በግ ለጋራ ማረድ አይቻልም፡፡ 3. የሚታረደው እንስሳ እድሜው የደረሰ መሆን አለበት፡፡ በግ 6 ወር፣ ፍየል 1 አመት፣ ከብት 2 አመት፣ ግመል ከሆነ 5 አመት የሞላው መሆን አለበት፡፡ 4. የሚታረደው እንስሳ መታወሩ ግልፅ የሆነ፤ ህመሙ ግልፅ የሆነ በሽተኛ፤ ግልፅ የሆነ አንካሳ፤ በጣም ያረጀ፣ አብዛሃኛው ወይም ግማሽና ከዚያ በላይ የሆነ ጆሮው፣ ጅራቱ፣ ላቱ፣ ቀንዱ፣ የተቆረጠ ወይም የተሰበረ መሆን የለበትም፡፡ ትንንሽ እንከኖች ችግር አይሆኑም። የተኮላሸ መጠቀም ይቻላል። ነብዩ ﷺ ሁለት የተኮላሹ በጎችን አርደዋል። [ሱነኑል በይሃቂይ] 5. የሚታረደው የግድ በተገደበው ጊዜ መሆን አለበት፡፡ እሱም ከዒድ ሶላት በኋላ እስከ ዙልሒጃ 13 ባለው ነው፡፡ ነብዩ ﷺ (ዒድ) ከመሰገዱ በፊት ያረደ በሷ ቦታ (እርዱን) ይድገም፡፡ ያላረደ ይረድ” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪ] 6. ያለ ምንም ልዩነት ከሁለቱም ፆታ ከወንድም #ከሴትም ለኡዱሒያ ማረድ ይፈቀዳል፡፡ [ኢብኑ ባዝ፣ ፈታዋ ኑሩን ዐለ ደርብ፡ ካሴት ቁ. 72] 7. ቆዳውንም ይሁን የትኛውንም ክፍሉን መሸጥ አይፈቀድም፡፡ ለአራጁ የሚከፈለውም ከኡዱሒያው ቆዳ ወይም ሌላ ክፍሉ መሆን የለበትም፡፡ ነብዩ ﷺ “የኡዱሒያውን ቆዳ የሸጠ ኡዱሒያ የለውም!” ብለዋል፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2/1055] ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ከኡዱሒያው ስጋ፣ ሞራ፣ ቆዳ፣ ወይም ሌላ ነገር መሸረጥ ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም ለአላህ ያወጣው ገንዘብ ስለሆነ ልክ እንደ ሶደቃ መመለስ አይቻልም፡፡ [ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 25/162] ባይሆን ስጦታ የተሰጠው ሰው ቢሸጥ ምንም ችግር የለበትም፡፡ 8. ስጋው ምን ይደረጋል? በእለቱ ከቤት ይበላል። ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ለምስኪን ይሰድቃል ወይም ስጦታ ይሰጣል። ቀሪ ከኖረ ያስቀምጣል፡፡ ስጦታ የተሰጠው ሰው ግን መሸጥን ጨምሮ ሐላል በሆነ መልኩ ለፈለገው አገልግሎት ማዋል ይችላል፡፡ 9. ኡዱሒያውን እራሱ ባለቤቱ ቢያርድ በላጭ ነው፡፡ ካልቻለ ወይም ካልተመቸው ግን ሰው መወከል ይችላል፡፡ ከተለያዩ ፈትዋዎች የተሰበሰበ ነው፡፡ = ©️©️ Ibnu Munewor ፣ ጳጉሜ 2/2008 t.me/ReshadIbnuMuzemil