es
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Ir al canal en Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Mostrar mĂĄs
213
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 dĂ­as
-430 dĂ­as
Archivo de publicaciones
ይህ ነው ዑመራችን! ~ አገሩ ወዲያ ነው - ከመካ በረሃ ክንዱ የሚፋጀው - የሚያሰኘው ውሃ! . ዑመር ብኑል ኸጣብ ከመስለማቸውም በፊት በሃይለኝነታቸው በአይበገሬነታቸው የሚታወቁ ነበሩ። አቡ ጀህልም እንዲሁ ነበር። አቡ ጀህል ስሙ ዐምር ብኑ ሂሻም ብኒል ሙጊራ አልመኽዙሚይ ነው። ነብዩ ﷺ የነዚህን ሁለት ሰዎች መስለም በእጅጉ ይፈልጉ ነበር። ይህም የሆነው በጊዜው እንግዳ ለሆነው ኢስላም ክብርና አይደፈሬነትን ይሰጣል በሚል መነሻ ነው። ለዚህም ነበር የአላህ መልእክተኛ ﷺ “አምላኬ ሆይ! ኢስላምን ከነዚህ ሁለት ሰዎች አንተ ዘንድ በተወደደው አስከብረው'' ማለታቸው። በአቡ ጀህል ወይም በዑመር ብኑል ኸጣብ! ከሁለቱ እሱ ዘንድ የተወደደው ዑመር ሆነ፡፡ [ቲርሚዚይ፡ 3681] ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ዑመር እስከሚሰልም ድረስ ከዕባ አካባቢ መስገድ አንችልም ነበር፡፡ ዑመር ሲሰልም ግን ቁረይሾችን ተፋለማቸው፡፡ ከዚያም ከዕባ ዘንድ ሰገደ፡፡ ከሱም ጋር ሰገድን።” “ዑመር ብኑል ኸጣብ ከሰለመ ጀምሮ የተከበርን ሆነናል፡፡” [ቡኻሪ፡ 3684] ኡሙ ዐብዲላህ ቢንት አቢ ሐስማህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች:- “ወላሂ ወደ ሐበሻ ምድር ልንሰደድ እየተዘጋጀን ነበር፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሆነ ጉዳያችንን ሊፈፅም ወጥቶ ሳለ ዑመር መጣና ቆመ፡፡ በሺርኩ ላይ እንዳለ ነው፡፡ ከሱ ፈተናና ስቃይ ይደርስብን ነበር፡፡ ከዚያም፡ * “የምርም መጓዛችሁ ነው ኡሙ ዐብዲላህ?” አለኝ፡፡ - “አዎ ወላሂ! አላህ መውጫ እስከሚያደርግልን ድረስ ከአላህ ሀገሮች ወደ አንዱ እንወጣለን፡፡ አስቸገራችሁን አሰቃያችሁን!” አልኩት፡፡ * “አላህ አብሯችሁ ይሁን” አለ፡፡ ቀድሜ አይቸው የማላውቀው መቆርቆር አየሁበት፡፡ ከዚያም ተመልሶ ሄደ፡፡ ሳስበው መውጣታችን በርግጥም አሳዝኖታል፡፡ ባለቤቴ ዓሚር የሄደበትን ጉዳያችንን ፈፅሞ ሲመጣ፡ - “የአብደላህ አባት ሆይ! እንዲያው ዑመርን ቅድም ብታየው፣ ለኛ መቆርቆሩንና ማዘኑን” አልኩት፡፡ * “ይሰልማል ብለሽ ከጀልሽ እንዴ?” አለኝ፡፡ - “አዎ” አልኩት፡፡ * “የኸጣብ አህያ ሳይሰልም ያ ያየሽው ሰውዬ አይሰልምም!” አለኝ፡፡ “በኢስላም ላይ የሚያደርሰውን ጭካኔና ድርቅና በማየት ተስፋ ቆርጦ ነው።” ዐብዱላህ ብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ዑመር ሲሰልም ቀድሞ በክህደት የተቀመጠባቸውን ስብሰባዎች አንድም ሳያስቀር መስለሙን ሊያውጅባቸው ለነብዩ ﷺ ቃል ገብቶ ነበር፡፡ እናም በሰለመ ጊዜ፡ - 'ከቁረይሽ እጅግ ወሬ አራጋቢ የሆነው ማነው?' ሲል ጠየቀ፡፡ * 'ጀሚል ብኑ መዕመር ነው' አሉት፡፡ ቀጥታ ወደሱ ሄደ፡፡ ምን እንደሚሰራ ለማየት ከስር ከስሩ ተከትየው ሄድኩኝ፡፡ በጊዜው የማየውን ሁሉ በደንብ የማስተውል ልጅ ነበርኩ፡፡ ጀሚል ጋ መጣና፡ - 'ጀሚል ሆይ! መስለሜን አወቅክ? ወደ ሙሐመድ ሃይማኖት ገባሁ'ኮ!' አለው፡፡ ወላሂ ከዚያ በኋላ ጀሚል ለዑመር አልመለሰም፡፡ ቀጥታ ኩታውን እየጎተተ ወጣ፡፡ ዑመር ተከተለው፡፡ እኔም ዑመርን ተከተልኩት፡፡ ጀሚል ከመስጂዱ በር ቆመና ድምፁን በጣም ከፍ አድርጎ ጮኸ፡- * 'የቁረይሽ ህዝብ ሆይ! አዋጅ! የኸጣብ ልጅ አፈንግጧል' አለ፡፡ እነሱ በከዕባ ዙሪያ ተሰብስዋል፡፡ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ከኋላው እየተከተለ፡ - “ዋሸ! ባይሆን እኔ በርግጥም ሰልሜያለሁ፡፡ ከአላህ ውጭ በሐቅ የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆነ መስክሬያለሁ” አለ። ዑመርን ሮጠው ከበቡት። ሲታገላቸው ሲታገሉት እኩለ ቀን ሆነ፡፡ ዑመር አቃተውና ቁጭ አለ፡፡ በራሱ ላይ ወጡበት፡፡ እሱ ይህኔ እንዲህ አላቸው፡- * “የታያችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡ በአላህ እምላለሁ! በርግጠኝነት ሶስት መቶ ወንዶች ብንሆን መካን ወይ እንተውላችኋለን፣ ወይ ትተውልናላችሁ!” በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ አንድ የቁረይሽ ሽማግሌ መጣ፡፡ የተቀለመ ሙሉ ልብስ ለብሷል፣ ቀሚስ ጋር፡፡ ቀጥታ ካጠገባቸው ቆመና፡ - “ምን እየሆናችሁ ነው?” አላቸው፡፡ * “ዑመር አፈንግጦ ነው” አሉት፡፡ - “ቢሆንስ?! እረፉ! አንድ ሰው ለራሱ የሆነ ነገር መረጠ፡፡ ታዲያ ምንድን ነው የምትፈልጉት? ይህን ሰውዬ እንዲህ ስታደርጉት የዐዲይ ጎሳ ሰዎች ዝም የሚሉ መሰላችሁ? ከሰውየው ዞር በሉ!” አላቸው፡፡ ከዚያም በአላህ ይሁንብኝ ልክ ከላዩ ላይ እንደተገፈፈ ልብስ ሆኑ! (ባንዴ ለቀቁት)፡፡ አባቴ ወደ መዲና ከተሰደደ በኋላ: * “አባዬ ሆይ! ያኔ መካ የሰለምክ እለት እነዚያን ሲታገሉህ የነበሩትን ሰዎች የተቆጣቸው ሰውዬ ማነው?” አልኩት፡፡ - “ያማ አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚይ ነው የኔ ልጅ” አለኝ፡፡ (አልዓስ ብኑ ዋኢል አሰህሚይ ማለት የብልሁ ፖለቲከኛ የዐምር ብኑል ዓስ አባት ነው።) = (ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 1/2006) የቴሌግራም ቻናል :- * ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor * ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL * ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

ረመዿን 6 🌙 هل تدركه بعد ذلك 🌙 ከዚህ በኃላ የሚመጣውን ረመዿንን ታገኘዋለህ ወይ? 🌌 لا ندري هل سنعيش إلى رمضان آخر. 🌌 كم فقدنا من عزيز أو جار أو قريب في رمضان እስከመጪው ረመዿን ድረስ መኖራችንን አናውቅም በዚሁ ረመዿን ስንትና ስንት ወዳጆችን፣ ጎረቤት እና ቅርብ ሰዎችን አጥተናል! ይህ የተባረከ ወር በ ዓመት 1 ግዜ ብቻ የሚያልፍ የሆነ ወር ነው ቀጣይ ዓመት ይህን ወር ድጋሚ ማግኘትህን ወይም ደግሞ ከዚያ በፊት መሞትህን አታውቅም ስለዚህ በዚህ ወር ልትጠነክር እና ወደ አላህ የሚያቀርቡህን ነገራቶች በመተግበር ልትፈጥን ይገባል፤ እንዲሁም ከአላህ ቅጣት የሚያድኑህን ሰበቦችን ለመስራት ልትበረታ የአላህ መሃርታን የሚያስገኙ ወንጀልህን ሊያሰርዙ የሚችሉ መልካም ስራዎችን ልትሰራ ይገባል ምክንያቱም ቀጣይ ዓመት ይህን ወር ድጋሚ ማግኘትህን አታውቅም! በዚህ ወር ለሙስሊሞች የተወደደ ነው፤ ሌሊቱን በሰላት ሊቆሙ በላጩ ፤11 ረክዓ ሊሰግዱ ሁለት ሁለት እያደረጉ፤ በውስጧም ቁርዓንን አስተካክለው ባማረ መልኩ በኹሹዕ ሊያነቡ ይገባል በሰላቱም ሩኩዕ እና ሱጁድ ሲወርዱ በእርጋታ እና በኹሹዕ ሊሆን ይገባል በሰላታቸው አይቻኮሉ ጎንበስ ቀና ብቻ አያድርጉት፤ ዋናው የሚፈለገው ልክ ነብያችን ሲሰግዱ እንደነበረው በኹሹዕ በዕርጋታ እና ልባቸውን ሰጥተው በጥሞና ያማረ አቀራርን እየቀሩ እያስተነተኑ መሆን አለበት እንጂ አንዳንድ ሰዎች በሰላት ተራዊህ እንደሚሰግዱት የችኮላ ጎንበስ ቀና ሰላት መሆን የለበትም፤ ምናልባትም እንዲህ አይነት ሰላት ተቀባይነት የሌላትና የማትበቃ ሰላት ትሆናለችና። 🔈 የተከበሩ ሸይኽ አብዱልዓዚዝ ቢን ባዝ አላህ ይዘንላቸውና

Tens of thousands of worshippers perform the evening and Taraweeh prayers in Al-Aqsa Mosque, despite the restrictions and obs
+2
Tens of thousands of worshippers perform the evening and Taraweeh prayers in Al-Aqsa Mosque, despite the restrictions and obstacles imposed by the Israeli occupation forces in occupied Jerusalem.

«ወላሂ! ቀብር ላይ ያሉ ሰዎች ተመኙ ቢባሉ አንዲትን የረመዿን ቀን ባገኘን ብለው ይመኙ ነበር!» ይላሉ፤ ኢብኑ-ል-ጀውዚ!

ፍትሃዊው ጌታ! ረሱል () እንዲህ ብለዋል፦ ﴿اللَّهَ لَا يَظْلِمُ مُؤْمِنًا حَسَنَةً، يُعْطَى بِهَا فِي الدُّنْيَا، وَيُجْزَى بِهَا فِي الْآخِرَةِ، وَأَمَّا الْكَافِرُ فَيُطْعَمُ بِحَسَنَاتِ مَا عَمِلَ بِهَا لِلَّهِ فِي الدُّنْيَا، حَتَّى إِذَا أَفْضَى إِلَى الْآخِرَةِ لَمْ تَكُنْ لَهُ حَسَنَةٌ يُجْزَى بِهَا﴾ “አላህ አማኝን በመልካም ስራው አይበድልም። በዱንያም በሷ ይሰጠዋል። በአኺራም በሷው ይሸልመዋል። ከሃዲ ግን አላህን አስቦ በሰራቸው መልካም ስራዎች ዱንያ ላይ ያበላዋል። ወደ አኺራ ሲሄድ ግን የሚመነዳበት መልካም ሾል የለውም።” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል:  2808 💸 በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 🌐፦ https://bit.ly/4ayf0xJ 💬፦ https://bit.ly/486xnrS 🌐፦ https://bit.ly/41zEZkk 🌐፦ https://bit.ly/4arMbTx 🌐፦ https://bit.ly/41tIUPv 🌐፦ https://bit.ly/41yPkNg

"A human life became worth a flour bag. People lose their lives for a flour bag." A testimony of last night's four massacre at Al Kuwait roundabout, when Israeli helicopters and tanks opened fire at hungry civilians while waiting for aid.

+1
ይህ በትላልቅ የተፃፈ ዱዓእ ነው አውርደው ይጠቀሙት። 🍃ለእኛ  በየጁምአው ሶስት እዝነቶች አሉልን… 🍀 በነቢዩ   ሰለዋት ማውረድ 🌼 ሱረቱል ከህፍን መቅራትና 🍀 ከአስር በኃላ የምትጠበቀዋ ዱዓ ተቀባይነት የምታገኝበት ሰአት ናት ያለነው ደግሞ በረመዷን ወር ውስጥ ነው 🌱 በጨለማው ጊዜ ብርሀንን የምትፈልግ ከሆነ በጁምአ ቀን ሱረቱል ከህፍን እንድትቀራ እጋበዘሃለሁ  ✨🌺 🌱የጌታህ እዝነት እንዲከብህም ከፈለክ በውዱ ነቢይህ ላይ ሰለዋት ማብዛትን አትርሳ 💐 ‏﷽ ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝  https://t.me/tolehaahmed

ትናንት ወደ አኺራህ የሄዱት የሳዑዲ የታላላቅ ዑለማዎች ኮሚቴ አባል ሸይኽ ዐብደ-ል'ሏህ ቀሲር (ረሒመሁ-ል'ሏህ) ታመው ሳለ ሸይኽ ሷሊሕ ፈውዛን (ሐፊዘሁ-ል'ሏህ) ሲጠይቋቸው!

የማለዳ ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⓵⑤∅⑤]👌 #ቁርኣን

Jerusalem Waqf Department: "70,000 worshippers performed Taraweeh prayers at Al-Aqsa Mosque tonight, despite the restrictions
Jerusalem Waqf Department: "70,000 worshippers performed Taraweeh prayers at Al-Aqsa Mosque tonight, despite the restrictions and obstacles imposed by the Israeli occupation."

🇵🇸🇵🇸 የዚህ ዓመት ረመዷን እንደሌሎች ዓመታት ረመዷን አታስበው ይህ ረመዷን ከ 5 ወር በፊት ፆም ጀምረው እስካሁን ያላፈጠሩ ወንድሞች እንዳሉህ ሊያስታውስህ ነው የመጣው! አላህ ሆይ እርዳታህ
🇵🇸🇵🇸 የዚህ ዓመት ረመዷን እንደሌሎች ዓመታት ረመዷን አታስበው ይህ ረመዷን ከ 5 ወር በፊት ፆም ጀምረው እስካሁን ያላፈጠሩ ወንድሞች እንዳሉህ ሊያስታውስህ  ነው የመጣው! አላህ ሆይ እርዳታህን ለግሳቸው በጠላቶቻቸው ላይ የበላይነትን ስጣቸው በዚህ በተባረከ ወር በመልካም ዱዓችን እናስታውሳቸው

40,000 worshipers performed Taraweeh prayers at Al Aqsa mosque despite the Israeli restrictions.

እኛ ዱዓ በማድረግ ላይ ተስፋ ቆርጠናል.... ፈለስጢናዊያን ግን .... 🇵🇸 🇵🇸 አላህ ድሉን ቅርብ ያድርግላችሁ ፈለስጢናዊያን እህት ወንድሞቻችን። ➞ ለአላህ ስንል እንወድሻለን ፈለስጢን። �
+2
እኛ ዱዓ በማድረግ ላይ ተስፋ ቆርጠናል.... ፈለስጢናዊያን ግን .... 🇵🇸 🇵🇸 አላህ ድሉን ቅርብ ያድርግላችሁ ፈለስጢናዊያን እህት ወንድሞቻችን። ➞ ለአላህ ስንል እንወድሻለን ፈለስጢን። 🇵🇸 ➞ ለአላህ ስንል እንወዳችኋለን ፈለስጢናዊያን 🇵🇸 ummalife.com/ReshadMuzemil

ኢፍጣር ጋዛ በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ቢኮንም መተግበሩ አይቀርም
+1
ኢፍጣር ጋዛ በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ቢኮንም መተግበሩ አይቀርም

ረመዿን 3 🌙 تفطير الصائمين 🌙 ፆመኞችን ማስፈጠር ልክ እንደዚሁ (ቀደምቶቻችን) ለረመዿን ከሚዘጋጁበት ነገሮች አንዱ ፆመኛን በማስፈጠር ላይ ነው ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው ምንዳው ያስፈጠረውን ሰው ምንዳ ፤ከእሱ ምንም ሳይቀነስ ያገኛል። ልክ እንደዚሁ (ቀደምቶቻችን) ራሳቸውን አላህን በማውሳት ላይ ይጠምዱ ነበር በሌሎች ኢባዳዎች፣ ከነብያችን በተገኙ አዝካሮች ፤የጠዋት እና የማታ ዚክር፣ የመኝታ ዚክርን ይመስል እንዲሁም ከነብያችን በተገኙ በሆኑ ዱዓዎች በዚህ ምርጥ በሆኑ ወቅቶች አላህን ይለምኑት ነበር ። በነዚህ ጊዜያቶች አላህ ለባሮቹ ስራቸውን እጥፍ ድርብ የሚያደርግበት ወቅት ስለሆነ ማለት ነው። አላህ ስለዚህ ወር ካወራ በኋላ እንዲህ ይላል፦ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا لِي وَلْيُؤْمِنُوا بِي لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡ ይህ ከአላህ የሆነ ቃልኪዳን ነው፤ እሱን ለጠየቀው ፣ለለመነው ባርያው ጥያቄውን ሊቀበለው እና የጠየቀውን እንደሚሰጠው ያረጋገጠበት ነው። 🔈 ሸይኽ አብደሏህ ኢብን ጀብሪን አላህ ይዘንላቸውና