es
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Ir al canal en Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Mostrar más
213
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días
Archivo de publicaciones
«የጀግናው ዙበይር አባት ነኝ ። ለሙስሊሙ የማስተላልፈው መልእክት እኔ እና እናቱንም አላህ ኻቲማችንን እንዲያሳምርልን ዱዓ አድርጉልን ። ልጄ የሞተበት መስጅዶቹ መሰራታቸው አይቀርም ። እናም ወደፊት
«የጀግናው ዙበይር አባት ነኝ ። ለሙስሊሙ የማስተላልፈው መልእክት እኔ እና እናቱንም አላህ ኻቲማችንን እንዲያሳምርልን ዱዓ አድርጉልን ። ልጄ የሞተበት መስጅዶቹ መሰራታቸው አይቀርም ። እናም ወደፊት መስጅዶቹ ሲገነቡ ለመስጅድ ብሎ በሞተው ልጄ ዙበይር ስም የሚሰየም መስጅድ ቢኖር ደስ ይለኛል።»

ሙእሚኖች ከሆናችሁ የበላዮች ናቸሁ‼ በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ዛሬ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ ይከታተሉ። t.me/ReshadIbnuMuzemil
ሙእሚኖች ከሆናችሁ የበላዮች ናቸሁ‼ በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ ዛሬ ምሽት ከ2፡30 ጀምሮ ይከታተሉ። t.me/ReshadIbnuMuzemil

አልጀዚራም ትናንት ይህንን ዘገባ ሠርቷል።

ታድያ ለምን ትጨነቃለህ? ⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡ ፊቱ ላይ ሀዘንና ጭንቀትን በተሸከመ ሰው አጠገብ ኢማም ኢብራሂም ኢብኑል አድሀም እያለፉ እንዲህ አሉት .. " አንተ ሰው ሶስት ጥያቄዎችን ጠይ
ታድያ ለምን ትጨነቃለህ?  ⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡⇡    ፊቱ ላይ ሀዘንና ጭንቀትን በተሸከመ ሰው አጠገብ ኢማም ኢብራሂም ኢብኑል አድሀም እያለፉ እንዲህ አሉት .. " አንተ ሰው ሶስት ጥያቄዎችን ጠይቅኸለው መልስልኝ! " ። " እሺ! " አለ ሰውዬውም ። " በዚህ ፍጥረተዓለም ውስጥ አላህ ማይፈልገው ነገር ይከሰታልን? " " በጭራሽ!  አይከሰተም! " አላቸው ። " አላህ ከወሰነልህ ርዝቅ ሚቀንሰው ሀይል አለን? " " በጭራሽ የለም! " አለ ። "  አላህ እንድትኖር ከፈቀደልህ ዕድሜ ላይ ሚቀንስብህ አንዳች ነገር አለን? " " ኧረ በጭራሽ የለም! " አለ ። " ታድያ ይሄ ሁሉ ሐዘንና ጭንቀት ምነው! "  አሉት። @ኡመር ያሲን t.me/ReshadIbnuMuzemil

«የአዲስ አበበ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኢማሞች ህብረት የተሰጠ የአቋም መግለጫ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘዉን የመስጅድ ፈረሳ በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ አንዋር እና ኑር መስጅዶች ህዝበ-ሙስሊሙ ድምፅ በማሰማቱ ምክንያት በተከሰተዉ ችግር በሰዉ ሕይወት እና አካል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ብዙ ዜጎች በህግ ጥላ ስር ይገኛሉ፡፡ በሸገር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘዉ የመስጆዶች ፈረሳ ፍፁም ተገቢ ባለመሆኑ የምናወግዝ መሆኑን እየገለፅን የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የኢማሞች ሀብረት ጥያቄውን ያቀርባል፣ በተጨማሪም የኢማሞች ሀብረት በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘዉን የመስጅድ ፈረሳ እና ከዚህ ጋር በተያያዘ በምዕመናን ላይ የተወሰደዉን ተገቢ ያልሆነ እርምጃ በፅኑ እያወገዘ የሚከተሉትን ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥቷል፡፡ 1. ከዛሬ ቀን ጀምሮ እስከ ዙልቂዕዳ ወር መጨረሻ ድረስ በሁሉም መስጅዶች ቁኑት እና ዱዓ አንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፣ 2. በሁሉም መስጂዶች የፊታችን ጁሙዓ የኩጥባ ይዘት በሠላም፣ በአንድነት እና በሰብር ላይ እንዲያተኩር እና ህብረተሰባችን ይበልጥ በሚረዳው በአማርኛ ቋንቋ ዳዕዋ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 3. በነገዉ እለት ሐሙስ ዙልቂዕዳ 19 ፤ 1444 ዓ.ሂ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመፆም፤ በሰደቃ፣ በዱዓ እና በኢስቲግፋር ወደ አላህ በመቃረብ እና አላህ የተፈጠረውን ችግር እንዲያነሳልን እንዲለምን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 4. በተፈጠረዉ ችግር ሕይወታቸዉ ያለፈ እና የተጎዱ ቤተሰቦችን ሙስሊሙ ማህበረስብ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባዘጋጀው የባንክ ቁጥሮች እንዲረዳ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፡፡ 5. በመጨረሻም የጁምዓ ሰላታችን በሠላም ተሰግዶ አንዲጠናቀቅ እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሰላም ወደ ቤቱ እንዲመለስ ጥሪያችንን እያቀረብን አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የመጣውን በላእ እንዲያነሳልን እና እንዲመልስልን እንለምነዋለን፣ አላሁ አክበር !!!» ©: የአዲስ አበበ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

ይሄ ጋዜጠኛ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ጥሩ ዘገባ ሠርቷል። ሙሉውን አዳምጡት! እያንዳንዷን ክስተትና ከጀርባዋ ያለን ሴራ አጋርቷል። ትክክለኛውን መረጃ የሷጣችሁት ሰዎች ጎበዞች ናችሁ። የሟቾች ቁጥር ላይ ቢሳሳትም ሌላውን እንደ ወረደ ነው የዘገበው። || t.me/MuradTadesse

ኒቃብ አካልን እንጂ አዕምሮን አይሸፍንም‼ ============================= ✍ ይህቺ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ሙሉ ሰውነቷን በኒቃብ የተዋበች እህታችን የሳዑዲ ዓረቢያ ዜጋ ስትሆን፤
ኒቃብ አካልን እንጂ አዕምሮን አይሸፍንም‼ ============================= ✍ ይህቺ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ሙሉ ሰውነቷን በኒቃብ የተዋበች እህታችን የሳዑዲ ዓረቢያ ዜጋ ስትሆን፤ በሃገረ አሜሪካ በተካሄደው ከ16 ሃገራት የተውጣጡ 200 ቡድኖች (ቲሞች) በተሳተፉበት የሮቦቲክስ ውድድር አንደኛ ወጥታለች። A veiled Saudi student won first place in an international robotics competition in America among more than 200 teams from 16 countries. በኒቃብ የተነሳ ከ2, 000 በላይ ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው በማፈናቀል አመት ያስቆጠሩት የጉራጌ ዞን ጽንፈኞች ከዚህ ምን ይማሩ ይሆን⁉️ አንደኛ የወጣችው እንደነርሱ በምቀኝነት ሳይሆን ከባድ ከሚባሉት መስኮች አንዱ በሆነው በሮቦቲክስ ነው። ለመሆኑ ክበደቱንስ የት ያውቁታል፤ በፊዚክስ ክላስ በመስኮት ወጪውና ወንበር ላይ ተጋዳሚው እልፍ ነው¡ ኒቃብ ከባለጌዎች መከለያ እንጂ አዕምሮን የማይሸፍን መሆኑን በተጨባጭ የሚያስመሰክሩ በርካታ ሱመያዎች ያስፈልጉናልና እህቶቻችን በተሰማራችሁበት መስክና በዲናችሁ ጠንክሩልን። ጠላት ወዶ ሳይሆን ተገዶ በጥንካሬያችሁ የሚማረክበት ቀን በአላህ ፈቃድ ሩቅ አይሆንም። || MuradTadesse t.me/ReshadIbnuMuzemil

አካሄዳችን ልክ ነው ⁉️ ኡስታዞች የሚሉንን እያደመጥን በመሪዎቻችን ብንመራ የተሻለው መንገድ እሱ ነው በችኮላ ወዳልሆነ መንገድ ከመሄዳችን በፊት #Pass_it_on: ኑር ሚድያ ብርሀናዊ 20ት t.me/ReshadIbnuMuzemil

ከተዋቀሩት ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ መጅሊሱ ሙሐመድ አባተ በዚህ በአዲስ ሚዲያ በተሰራጨው ቪድዮ ጉዳይ ይህን ብሏል፦ «በግንቦት 28/2015 በጠቅላይ ም/ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ የተዋቀረው ኮሚቴ ከሰላም ሚኒስትር ጋር በወቅታዊ የሙስሊሞች ጉዳይ ዙሪያ ግልፅ ውይይት ማድረጉ ይታወቃል። ውይይቱ ከ2 ሰአት በላይ የፈጀ ሲሆን የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በብቸኝነት በቦታው በመገኘት ቀረፃ አድርጓል። ከዚህ ገንቢ ከነበረ ውይይት ጋር ተያይዞ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክን መነሻ አድርጎ በተለያዩ የሚዲያ አውታሮች ለህዝብ የተላለፈው መልእክት ብዥታ መፈጠሩን ተገንዝቤአለሁ። በመሆኑም ብዥታውን ለማጥራት ያህል:ከ2 ሰአት በላይ በተደረገ ገንቢ ውይይት ከላይ በተጠቀሰው መልኩ የቀረበው ሚዛናዊ ያልሆነና የውይይቱን አጠቃላይ ይዘት የማይገልፅ ዘገባን ከማስተካከል አንፃር በውይይቱ ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች እና ጥያቄ ያስነሳውን ነጥብ የቀረበበትን አግባብ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። አያይዤም ህዝበ ሙስሊሙ መሰረታዊ ጥያቄዎቹ ላይ ትኩረት እንደሚሰጥና የጎንዩሽ ጉዳዮች መስመር እንደማያስቱት ያለኝን ጠንካራ እምነት ለመግለፅ እወዳለሁ። ኮሚቴው ከሰላም ሚንስትር ጋር በነበረው ገንቢ የውይይት መድረክ ያነሳቸው ዋና ዋና ነጥቦች:- 1)በፀጥታ አካላት የተወሰደው እርምጃ ኮሚቴውንም ሆነ ህዝበ ሙስሊሙን እጅግ በጣም ያሳዘነ መሆኑን እና በቀጣይም በህግ አግባብ ተጠያቂነት መኖር እንዳለበት። 2)የችግሩ ምንጭ የሸገር ከተማ መስጂዶችን ከማፍረሱ ጋር የተያያዘ በመሆኑ የመስጂድ ፈረሳው በአስቸኳይ እንዲቆም እንዲደረግ። 3)የፈረሱ መስጂዶች በቦታቸው እንዲተኩ/ምትክ እንዲሰጥ። 4)የሸገር ከተማ ማስተር ፕላን መስጂዶችን ያካተተ መሆኑ መረጋገጥ እንዳለበት እና 5)በቀጣይ በሚደረጉ ውይይቶች መፍትሄ ማበጀት።የሚሉ ናቸው። በዋናነት በዚህ ከ2 ሰአት በላይ በፈጀ ውይይት ኮሚቴው ጠንከር ብሎ በጋራ ያነሳቸው እና የውይይቱ ማጠንጠኛ ነጥቦች ከላይ የተጠቀሱት ሲሆኑ ከአንዋር እና በኒ መስጂድ ጋር ተያይዞ የተነሳው ነጥብ የውይይቱ አካል ሆኖ የተነሳ ሳይሆን ከአዲስ አበባ መጅሊስና የመስጂዶች መዋቅራዊ ዝርጋታ ሂደት በእግረ መንገድ የተነሳ እንጂ የውይይቱ ዋና ማጠንጠኛም ሆነ የውይይቱ መነሻ አልነበረም። በመጨረሻም ኮሚቴው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ጉባኤ የጣለበትን አደራ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር በመነጋገር መፍትሄ ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ በሆነ አግባብ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ከዚህ ባሻገር ከመዋቅር ዝርጋታ ጋር ተያይዞ ያሉ ክፍተቶች በውስጥ ውይይትና ተቋማዊ አሰራርን ተከትሎ የሚፈቱ በመሆናቸው ህዝበ ሙስሊው በመሰል ወቅታዊ ጉዳዮች የሚያሳየውን የተለመደ የስነ-ልቦና ከፍታ በመላበስ አጀንደውን የውስጥ የንትርክ አጀንዳ እንዳይሆን በጋራ ጉዳይ ላይ ተኩረቱን እንዲያደርግ ለማስታወስ እወዳለሁ። አመሰግናለሁ።»

አሁንም እያስተዋልን‼ =============== (በሁሉም አጀንዳ በሚዲያ መወቃቀስ ያዳክመናል፤ ይከፋፍለናል!) || ✍ መስጅድ አፍራሹ ኃይል የሚፈልገው እርስ በርሳችን ተወነጃጅለን ራሱን ከጥፋተኝነት ነፃ ማውጣት ነው። ለዚህ መደላድል የሚሆነው መንገድ ከተከፈተለት ደግሞ ይፈልገዋል ብቻ ሳይሆን መንገድ ከፋቹን ቢሸልመው ሁላ ደስ ይለዋል። ምክንያቱም ምናልባት ጠያቂ ካለ ከተጠያቂነት ስለታደገው! በሰላም ሚኒስተር፣ በአዲስ አበባ ከተማ ጸጥታ ዘርፍና መጅሊሱ ባቋቋማቸው ኮሚቴዎች መካከል ትናንት የተደረገውን ውይይት በተመለከተ አዲስ ቲቪ ቆራርጦ ያሰራጨውን ቪድዮ ተመልክቼ ነበር። ደስ አላለኝም ብቻ ሳይሆን ተስፋ ያጨልማል። አውቃለሁ! አዲስ ቲቪ የመንግስት ቲቪ ስለሆነ ቆራርጦ ማቅረብ ያለበት እርሱን ሊደግፉ የሚችሉ ሃሳቦችን እንጂ ጠንካራ የኮሚቴው አባላት የተናገሯቸውን ጠንካራ ሃሳቦች እንዳልሆነ! እንኳን የሚደግፈው ሃሳብ አግኝቶ ቢያጣ እንኳ ለማግኘት መድከሙ አይቀርም ነበር። ያም ሆነ ይህ የሰማሁትን ቁራጭ ቪድዮ ጀስቲፋይ ማድረግ አልሻም። የማደርግበትም መንገድ ስለሌለ! የተሟላው ቪድዮ ቢገኝም ይዘቱን አይቀይረውም። ይልቁንም በጀግንነት ሐቁ የተናገሩ አባላት አይጠፉምና የነርሱን ንግግር አፈላልጋችሁ ስጡንና የቆሰለውን አንጀታችንን እናለስልስበት። ለማንኛውም፦ ለወደፊቱ መጅሊስ ራሱ በሚሳተፍባቸው መድረኮች ላይ የራሱን ካሜራ ይያዝ ወይም ኢስላማዊ ሚዲያዎችን ይጋብዝ። እንደዛ ከሆነ ሙሉ ውይይቱንና የተደረሰበትን ማወቅ ይቻላል። ኮሚቴው ስለደረሰበት የትናንቱ ውይይትም ከመንግስት በኩል እንደሰማነው ሁሉ በነርሱ በኩል ያለውን የውይይቱን ዕለታዊ ድምዳሜ መደበኛ ባልሆነ መልኩም ቢሆን ቢያሳውቁን የተሻለ ነው። አለበለዚያ «በነርሱ በኩል አዲስ ነገር የለም፣ ያው በመንግስት በኩል እንደሰማነው ነው!» ማለትን ያሲዛል። ከዚያ ውጭ ግን በሚዲያ መጥተን በዘመቻ መልክ በኛው ሰዎች ላይ የትግል ቀስታችንን ባናዞር መልካም ነው። ጠላት የሚፈልገውም ይሄንኑ ስለሆነ! ያለፈው ቢያልፍም እነዚህ የኮሚቴው አባላት መንግስት ፊት ሲቀርቡ የባጡን የቆጡን ከማውራትና እንደ ጨው ከመሟሟት ተቆጥበው በአንድነትና በጀግንነት እውነታውን ብቻ ተመርኩዘው ይቀጥሉ። አለበለዚያ የሚያስጠቃ ካለ ራሱን ያግልልና ጀግና ይተካበት። ከመንግስት አካላት ጋር ከመቅረባቸው በፊት በደንብ ሊወያዩና ወጥ አቋም ይዘው ሊገቡ ይገባል። እንዳውም ከነርሱ ውጭ ራሱ ያሉ ጠቃሚ ሰዎችን ቢያማክሩ ሁሉ ቆንጆ ነው። ይህን ያልኩት የነዚህን ሰዎች ንግግር ሁሉም ኮሚቴ ያምንበታል ብዬ ስላላሰብኩ ነው። ሲወያዩ ያለ አግባብ ዘርጣጭና አስጠቂ ካለ፤ ከወዲሁ ማስወገድና ከተቻለ በሌላ መተካት ነው። ሌላው የሚያጨሰን አንሶን የኛው የምትባሉት አታጭሱን። ጭራሽ ባልጠበቁትና የኛው በሚባል ሰው መጨስ በጠላት ከመጨስ ህመሙ የከፋ ነው። የተያዘው አጀንዳ የሁለት መስጅዶች ሳይሆን የ60+ ሚሊዮን ሙስሊሞች የህልውና እና የክብር ጉዳይ ነው። ስሜታዊነትና ቡድንተኝነት የራሱ ቦታ ስላለው በቀላል ትግል ማስተካከል የሚቻለውን የአንዋርና በኒ መስጅዶች ጉዳይ አጋጣሚው ተገኘ በሚል እሳቤ ብቻ በትልቅ አጀንዳ መሃል መግባት የለበትም። የአንዋርና በኒ አስተዳደራዊ ጉዳይ ከተፈታ የ20+ መስጅዶች መፍረስ፣ የ6+ ወንድሞች መገደል፣ የመቶዎች መጎዳትና የሺዎች መታሰር እንዲሁ ሊቀር ነው? በትልቅ ትግል ትልቅ ፍሬ ማፍራት እየተቻለ መንደር ለመንደር መልከስከስን ምን አመጣው? ቀስድ አታሳንሱ‼ እኛ ግን ጉዳዩን እንደ ዘመቻ አናድርገው። ከዋናው ዘመቻ ያስቆመናል፤ ያቀዛቅዝብናል፤ ይከፋፍለናል። አስፈላጊ ከሆነ በቡድን በመሆን በአካል ተገኝቶ እነዚህ ኮሚቴዎች የወከሉትን የመጅሊስ አካል ማብራሪያ መጠየቅ ይሻላል። የሚዲያውን እናርግበው። የምናረግበው ትክክል ስለሆኑ ሳይሆን የልዩነት መንስዔ እንዳይሆንና ከዋናው አጀንዳችን እንዳያዘናጋን ነው። አሁንም ፍትሕ እንሻለን። ከፊታችን ጁሙዓህ በፊት በመጅሊስ በኩል ፍሬ ያለው ተጨባጭ ድምዳሜ ላይ ደርሶ ቢያሳውቀን የተሻለ ነው። አሊያ ግን ያልተጠናና ያልተናበበ ትግል በየጁሙዓው ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርምና ከወዲሁ ይታሰብበት። እኛ ግን አደራ! በቃ በነዚህ ሰዎች የተነሳ ያለውን ዘመቻ እናቁመው። መዓ ሰላም! || t.me/MuradTadesse

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማስታወሻ በኢብኑ ሙነወር

እኔ አንተ አንቺ ምን አለን? ለ16 አመት ልጅ ጥይት t.me/ReshadIbnuMuzemil

ከጂማ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓህ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ! t.me/ReshadIbnuMuzemil
+1
ከጂማ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓህ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ! t.me/ReshadIbnuMuzemil

መርካቶ ከረዩ እና እዛ አካባቢ ያላችሁ በር እየገነጠሉ እያፈሱ ነው ስለተባለ ተጠንቀቁ። በሌሎች የሙስሊም ሰፈሮችም በራችሁን አትክፈቱ።

ተጨማሪ «Selam aleykum werahmetullahi weberekatu Africa hbret ategeb yalew adisu mesjid egna nejashi mesjid new mnlew ena eza rasu beakal mnawkew kafir police kewendochu ga lk endemuslimu civil lebso tekelaklo gebto segdol mn asbo endeneber banawkm»