Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙
Ir al canal en Telegram
● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸
Mostrar más213
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días
Archivo de publicaciones
ወጋ__ወግ………
ተኩላው ወደ አውራ ዶሮው ይመጣና……
"የሆነ ቀን እንደ አጋጣሚ አባትህ ሲጮህ ሰምቼው ድምፁ እንዴት እንደ ሚያምር!
ሌላ ቀን ያንን ድምፅ ናፈቀኝና በድጋሚ ልሰማው ቄያችሁ ስመጣ አባትህ እንደሞተ ተነገረኝ።" አለው።
አውራ ዶሮው……
"በነገራችን ላይ እኔም እንደ አባቴ መጮህ እችላለሁ።" አለ
ተኩላው………
"እባክህ አሰማኝና ሀሴት ላርግ።" አለው
አውራ ዶሮው ለመጮህ ተዘጋጀና ድምፁን አስተካክሎ ለማውጣት ዐይኖቹን ጨ ፈ ን ሲያደርግ ተኩላው ይዞት ተፈተለከ።
ተኩላው ዶሮው አንጠልጥሎ ሲሮጥ የተመለከቱ የቀዬው ውሾች ሁሉም እየጮሁ ከኋላ ተኩላውን ማሳደድ ጀመሩ።
ስቃይ ላይ የነበረው አውራ ዶሮ ለተኩላው……
"ውሾቹ እንዲመለሱልህ ከፈለክ እኔ ከእነሱ ብሄር እንዳልሆንኩ ንገራቸው" አለው።
ተኩላም ወደ ውሾቹ ዞሮ………
"ዶሮው ከእናንተ አይደለም" ሊላቸው አፉን ሲከፍት ነክሶ ይዞት የነበረው ዶሮ ወድቆ አመለጠው።
በዚህ ጊዜ………
ተኩላው……
"ዝም ማለት በነበረበት ጊዜ የተናገረ አፍ አላህ ይርገመው" አለ
አውራ ዶሮም………
"ኣሚን! መንቃት በነበረበት ጊዜ የተጨፈነ ዐይንም አላህ ይርገመው" አለ።
✍አቡ ዘከሪያ
ጥቂት እውነታዎች ስለ ረመዷን
~
1- የረመዷን ወር ፆም ከኢስላም አምስቱ ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ምሰሶ ነው።
2- ረመዷን በኢስላማዊው አቆጣጠር 9ኛው ወር ነው።
3- የረመዷን ወር ፆም የተደነገገው በ2ኛው አመተ ሂጅራ ነው። ነብያችን ﷺ ባጠቃላይ የፆሙት 9 ረመዷን ነው።
4- ረመዷን ቁርኣን የወረደበት ወር ነው።
5- ልዩ የሆነችዋ ለይለተል ቀድር የምትገኘው በረመዷን ወር ውስጥ ነው።
6- በረመዷን የተፈፀመ ዑምራ የሐጅ ደረጃ ወይም ከነብያችን ﷺ ጋር የተፈፀመ ሐጅ ደረጃ አለው።
7- ረመዷን የጀነት በሮች የሚከፋፈቱበት፣ የጀሃነም በሮች የሚዘጋጉበት፣ ሸይጧኖች የሚጠፈሩበት ወር ነው።
8- የረመዷን ወር ከኢዕቲካፍ ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።
9- ረመዷን እንደ የበድር ድል፣ የመካ መከፈት፣ የቃዲሲያ ድል፣ የዑዛ ጣኦት መወገድ፣ ሞንጎሎች የተሸነፉበት የዐይን ጃሉት ድል፣ ወዘተ ትልልቅ ክስተቶች የተከሰቱበት ወር ነው።
= Ibnu Munewor
ዳሩት!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إذا أتاكم مَن ترضونَ خلقَهُ ودينَهُ فزوِّجوهُ إلّا تفعلوا تَكن فتنةٌ في الأرضِ وفسادٌ عريضٌ﴾
“ስነምግባሩ እና ዲኑን የምትወዱለት ሰው ለትዳር መጥቶ ከጠየቃችሁ ዳሩት። ይህን የማታደርጉ ከሆነ በምድር ላይ ፈተናንና ብልሽትን ታሰፍናላችሁ።”
📚 ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል: 1614
✅ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦
🌐፦ https://bit.ly/4ayf0xJ
💬፦ https://bit.ly/486xnrS
🌐፦ https://bit.ly/41zEZkk
🌐፦ https://bit.ly/4arMbTx
🌐፦ https://bit.ly/41tIUPv
🌐፦ https://bit.ly/3UTTSwh
✨🌙
👉🏻ይደክመኛል ብለህ ሱና ፆሞችን ከተውክ …
👉🏻ለችግርህ ስትል ሰደቃ ካላወጣህ…
👉🏻ለነገ ስትል ተውበትህን ካዘገየህ…
👉🏻ለችኮላህ ስትል ሱና ሰላቶችን ካልሰገድክ…
👉🏻ለምቾትህ ስትል በኢባዳ ካልጠነከርክ…
👉🏻ቢዚ ነኝ ነኝ እያለክ ቁርዓንህን ካልቀራህ…
👉🏻አይመቸኝም እያልክ የዲን እውቀትን ካልፈለክ…
📌 ታድያ ስለየትኛው የጀነት እሽቅድድም ነው የምታወራው ⁉️
ጀነት በምኞት ብቻ አትገኝም ። በምኞት ብቻ የምትገኝ ብትሆንማ ጀነት የሚገቡ ሰዎች ስትሰሩት በነበረው ስራ ጀነት ግቡ ባልተባሉ ነበር ።
{ ٱدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ }
《 « ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡበ» ይባላሉ》
⚜ ጀነት ከአላህ እዝነት ቀጥሎ ስራ ትፈልጋለች ። በዚህ በተከበረ ወር ለኸይር ስራና አላህ በሚወደው ተግባር ላይ ልንቻኮል ይገባናል።
{ وَسَارِعُوٓا۟ إِلَىٰ مَغْفِرَةٍۢ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ }
《 ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ 》
©️ Toleha Ahmed
#ተስፋችን
{فما ظنكم برب العالمين }
የኛ ተስፋ
ወንጀላችንን እንደምትምረን፣ ይቅር እንደምትለን፣ ሲሳያችንን እንደምታበዛልን፣ ጤናችንን እንደምታሟላልን፣ ግድፈቶቻችንን እንደምትሞላልን፣ ነውሮቻችንን እንደምትደብቅልን፣ በጠላቶቻችን ላይ እንደምታግዘን፣ ቀጥተኛውን መንገድ እንደምትመራን፣ ጽናትን እንደምታድለን፣ ተውበታችንን እንደምትቀበለን፣ መልካሙን ሁሉ እንደምትሰጠን፣ መጥፎን እንደምታርቅልን፣ ፍጻሜያችንን እንደምታሳምርልን፣ መዳረሻችንን ጀነት እንደምታደርግልን ነው።
ባንተ ላይ ያለን ተስፋ ፍጹም ፍጹም መልካም ተስፋ ነው። አንተም ባሮችህ ባንተ ላይ ያላቸውን ተስፋ ከንቱ እንዳማታስቀር አውጀሃል።
Via : Copy
ወንበዴው የአህባሽ ቡድን በመስጂዳችን ላይ የፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት እነሆ ‼️
እንደምትመለከቱት ፎቅ ላይ ምንጣፍ የሚያነጥፉ ልጆችን ለማስቆም ሴቶች ጭምር ዱላ ይዘዋል፣ የቁርኣን ማስቀመጫ ወደ ፎቅ ወርውረዋል፣ ተንጠላጥለው ሊወጡ ሞክረዋል፣ የብልግና ስድብ መስጂድ ላይ ተሳድበዋል፣ እገልሀለው ሁላ እያሉ ዝተዋል፣ መሰላል ይዘው መጥተው ፎቅ ላይ ያሉ ልጆችን ወጥተው ጉዳት ለማድረስ ሲሞክሩም ቪድዮው ያሳየናል!!
ይህ ነው እንግዲ እውነታው እውነትን መቼም መደበቅ አይቻልም!!
ይህ ሁሉ ነገር የተፈጠረው መስጂድን የብጥብጥ አውድማ ለማድረግ የመጨረሻ ካርዱን በመዘዘው የአህባሽ ቡድን ነው።
ሼር‼️ ሼር‼️
#አሊ_መስጂድ_ወጣቶች_ጀማዐ
➞ አግራሞቴን በብዕር ፤➞ ከትዝብቴ ማህደር
🔰 የሰዎች ስላእኛ የሚያስቡት ነገር
አላህ እንዲደሰትብህ ብለህ ለሰዎች መልካምነትህን ስታሳያቸውና እሺታ ስታበዛ......
እነሱ ያስባሉ አንተ ጅል እንደሆንክ!!
አንዳንዴ አስመሳይ እንደሆንክ ያስባሉ፣
አንዳንዴ ደግሞ፡ “አይ በራሱ ስለማይተማመንና እውቀት ስለሌለው ነው” ይሉሃል።
ኢማሙ ሻፊዕይ እንደ ሚሉን: ❝አንተ ከጌታህ ያለህን ነገር አስተካክል እንጂ ሰዎች ስለሚሉህ ነገር አትጨነቅ።❞
► እኛም እንደነሱ እንላለን። ብቻ ላአላህ ብለን መልካም እንድንሆን አላህ ያግዘን መገዱንም ያቅጣጨን።
ወንድምና እህቶቼ በመልካምነታችን፣ በጥሩ ስብዕናችን የተነሳ የሚነሳውን ትችትና ወቀሳ ተወት እናድርገው ነገር ግን የጌታችንን ነገር አደራ‼️
ጌታችን አላህን ባለማስከፋት (ባለማመፅ) ዘወታሪዎች እንሁን‼️ \\ ከወንጀል እንራቅ፤ ሁሉም የሰው ልጆች ወንጀለኞች ናቸውና ወንጀል በፈፀምን ጊዜ አላህን ምህረትና እዝነት እንጠይቅ።
⭕️ ዛሬ ላይ በእሺታችንና በመልካምነታችን የሚያላግጡ ሁሉ አንድ ቀን ይደሰቱብናል። ያኔ ለኩራትና በራሳችን ላይ ለመገረም (ለመደነቅ) ሳይሆን ለመታዘብ አላህ ያብቃን‼️
በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
t.me/SharpSwords1
tiktok.com/@sharpswords1
ummalife.com/ReshadMuzemil
በበሽታ ምክንያት የረመዷን ፆም መፆም ያልቻለ ምን ማድረግ ነዉ ያለበት??
መልስ
ከበሽታዉ ጋር መፆም የሚችል ከሆነ መፆም ግዴታ ይሆንበታል
ነገር ግን አሁን ያለበት ፆም ወይም ያለፈዉን ቀዷ መፆም የማይችል ከሆነ ዘዉታሪ በሆነ በሽታ በየቀኑ ሁሌ ሚስኪን ያበላል መጠኑ 1ኪሎ ከግማሽ ከምግብ በአጠቃላይ ወሩ 45 ኪሎ ከምግብ
ያለፈዉን ረመዷን መፆም የማይችል ከሆነ
ትኩሱን ሮመዷን መፆም የማይችል ከሆነ
ምሳሌ ዘዉታሪ የሆነ በሽታ
በእድሜ የገፉ ሽማግሌ
አሏህ ሱብሀነሁ ወታዕላ እንድህ ይላል
وَعَلَى الَّذِينَ يُطِيقُونَهُ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ ۖ በእነዚያም ጾምን በማይችሉት ላይ ቤዛ ድኻን ማብላት አለባቸው፡፡
👇👇👇
https://t.me/HuzeyfaAhmed
የ አደብ አስፈላጊነት
-------------------------------------------------
ኡስታዝ አብዱሽኩር ሱልጣን
۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩ ۩
☀ ሁዳ መልቲሚዲያ
----------------------
በቴሌግራም
t.me/huda4eth
በፌስቡክ
fb.com/huda4etb
በዩትዩብ
https://goo.gl/WK5K5N
በ ቲክ ቶክ
@huda4eth
ያግኙን
እዚህ አጠገባችን ላሉ እህት ወንድሞቻችንን ጥላቻ እናሳያቸዋለን (እንባላለን)፤ እዛ ፈሐስጢን ወንድም እህቶቻችን ይረግፋሉ።❗️
መዲና ሆኖ ለሞተ…
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَنِ اسْتَطَاعَ أَنْ يَمُوتَ بِالْمَدِينَةِ فَلْيَمُتْ بِهَا ؛ فَإِنِّي أَشْفَعُ لِمَنْ يَمُوتُ بِهَا﴾
“መዲና መሞት የቻለ፤ እዛ ሆኖ ይሙት። እኔ እዛ ለሞተ ሸፍዓ (አማላጅ) እሆነዋለሁ።”
📚 ቲርሚዚ ሶሂህ ብለውታል: 3917
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
O Allah, the revealer of the Holy Book, and the swift in reckoning, and the mover of the clouds, and the defeater of the clans; defeat them, and shake them, and grant us victory over them.
ኢማም አህመድ (ረሂመሁሏህ)ተጠየቁ:-
ጠያቂው: ከሰዎች ሰላም ለመሆን መንገዱ እንዴት ነው?
እንዲህ ብለው መለሱ:
ትሰጣቸዋለህ ከነሱ አትወስድም፤ አዛ ያደርጉሀል አዛ አታደርጋቸውም፤ ጥቅማቸውን ታስጠብቅላቸዋለህ ያንተን ጥቅም እንዲያስጠብቁልህ አትጠይቃቸውም።
ጠያቂው: ኢማም ሆይ ይሔ ይከብዳል
ኢማም አህመድ: ታዲያ እንዴት ሰላም ትሆናለህ (ሰላም አትሆንም)!!
(سير أعلام النبلاء / الجزء 11 الطبقة 12)
[ ሲየር ሚን አዕላሚ-ኑበላእ / 11ኛ ጁዝዕ ]
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
✍ በረመዿን ፆም ዙርያ ጥያቄና መልስ፦
1ኛ - ጥያቄ፦ባጠቃላይ ፆም የሚያበላሹ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
መልስ:- ፆም የሚያበላሹ ነገሮች:
1. እያወቁ መብላትና መጠጣት ፡፡
2. የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ፡፡
3. አውቆ ከብልት ፈሳሽ ማስወጣት ፡፡
4. የአይን፣ የጆሮ፣ እና የአፍንጫ ጠብታ ተንሸራቶ ወደ ጉሮሮ መግባት ፡፡
5. እንደ ግሉኮስ አይነትና ምግብ ነክ መርፌ መውሰድ፡፡
6. ዋግምት ማድረግ፡፡
7. በወር አበባና በወሊድ ደም ወቅት፡፡ ( መፆሙ ሐራም ነው!)
8. አውቆ ማስታወክ ናቸው ፡፡ (ገፍቶ የመጣ ትውከት ፣ ረስቶ መብላትና መጠጣት ፆም አያበላሹም።)
2ኛ - ጥያቄ፡- :-የአይን ኩሁል ሽቶ ኮስሞቲክ የመሳሰሉት ለፆመኛ ይፈቀዳል?
መልስ:- ኩሁል አይን ላይ ሲኳሉት ወደ ጉሮሮ ይዘልቃል። ስለዚህ ብዙ የዲን ዕውቀት ባለቤቶች ከልክለዋል ፓውደር ሽቶ የመሳሰሉት ለፆመኛ ምንም አይደለም። ሴቶች ግን ሽቶ ተቀብተው ከቤት መውጣታቸው ሐራም ነው። ሴቶች ከቤታቸው ውጪ ሲወጡ ከማጋጌጥና ሽቶ ከመቀባት መራቅ አለባቸው። አላህም በቁርአኑ ፡-
قال تعالى: {..وَلا تَبَرَّجْنَ تَبَرُّجَ الْجَاهِلِيَّةِ الأُولَى ...}
«...እንደፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥን በማጌጥ አትገለጡ...። ይላል።
[አል-አሕዛብ: 33]
قال صلى الله عليه وسلم: (لا تمنعوا إماء الله مساجد الله وليخرجن تَفِلات)
ረሱልም ﷺ «ሴት የአላህ ባሮችን መስጅድ አትከልክሉ። ያላጌጡትም ሆነው ይውጡ!» ብለዋል። [ሱነን አቡ ዳውድ]
3ኛ - ጥያቄ:-ፆመኛ በአደጋም ሆነ በጭረት ከሰውነቱ ደም ቢፈስ ፆሙ ይበላሻል?
መልስ፡- በአደጋ ምክንያት የሚፈስ ደም በፍላጎት ስላልሆነ ፆም አያጠፋም ፡፡ ደም መስጠትና ዋግምት ግን ስለሚያደክምና ስለሚያስፈጥር በፆም ወቅት ክልክል ነው ፡፡
4ኛ - ጥያቄ፡- በየፋርማሲው የሚሸጥ የአፍ ሽታ የሚያጠፋ የሚነፋ ፈሳሽ (ስፐሬይ) ፆም ያበላሻል?
መልስ፡- ፈሳሹን ለአፍ መጠቀም እንደመፋቂያ ስለሆነ ይቻላል። ወደ ጉሮሮ ዘልቆ እንዳይገባ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ፡፡ እዚህ ላይ ፆመኛ የአፉን ጠረን በጣም መጥላት የለበትም። ምክንያቱም አላህን የመታዘዝ ምልክትና የተወደደም ነውና ፡፡
خلوف فم الصائم أطيب عند الله من ريح المسك) قال صلى الله عليه وسلم :
ረሱልም (ﷺ) «የፆመኛ የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከምስክ ሽቶ የተሸለ ነው።» ብለዋል! [አል-ቡኻሪይ እንደዘገበው]
5ኛ - ጥያቄ፡- አንዲት ሴት ከወር አበባ ወይንም ከወሊድ ደም ከጠራች በኋላ የሚያጠራጥር ነገር ካየች እንዴት ትሆናለች?
መልስ፡- የወር አበባ ባስለመደው ቀን ጊዜውን ጨርሶ ምልክት አሳይቶ ከቆመ በኋላ መስገድም ሆነ መፆም ትችላለች። ምናልባት የሚያጠራጥር ነገር ካየች ያለማወላወል ጾሟን መቀጠልም ሆነ መስገድ ትችላለች። ነገር ግን ከወሊድ ደም ጠርቻለሁ ካለች በኋላ የሚያጠራጥር ነገር ካየች የግድ አርባ ቀን መሙላት አለባት ከአርባ ቀን በኋላ አጠራጣሪ ነገር ብታይም ሳታወላውል ጾሟን መቀጠልም ሆነ መስገድ ትችላለች፡፡
أم عطية رضي الله عنها: (كنا لا نعد الكدرة والصفرة بعد الطهر شيئًا)
ኡሙ ዓጢያ (ረዲየ-ል'ሏሁ ዓንሃ) «ከወር አበባ ከጠራን በኋላ አረንጓዴውን ፈሳሽ (ኩድራ) እና ቢጫውን ፈሳሽ (ሱፍራን) እንደ ወር አበባ አንቆጥረውም ነበር።) ብላለች!
6ኛ - ጥያቄ፡- የአሥራ አራት አመት ኮረዳ እያለሁኝ የወር አበባ ታየኝ በዛኑ አመት ረመዳን ሲመጣ አልፆምኩም። መፆም እንደሚገባኝ እኔም ሆንኩኝ ቤተሰቦቼ አናውቅም። አሥራ አምስት አመት ሲሞላኝ መፆም ጀመርኩኝ። ከዛም ሴት ልጅ የወር አበባ ከታያት ዕድሜዋ ባይደርስም መፆም አለባት! የሚል ፈትዋ ሰማሁኝ ታድያ አሁን ምን ላድርግ ?
መልስ፡- ጠያቂዋ የወር አበባ ሲታያት ለአካለ መጠን መድረሷ” ባለማወቋ እንደ ጥፋት አይቆጠርም። ያለማወቅ ነውና! ስለዚህ አሁን ለአካለ መጠን ስለደረሰች ያልፆመችውን አመት ፆም ቀዿ ማውጣት አለባት ፡፡
ሴት ልጅ ለአካለ መጠን መድረሷ የሚታወቅበት አራት ነጥቦች አሉ፡፡
ሀ. ዕድሜዋ አሥራ አምስት አመት ሲሞላት፡፡
ለ.ፀጉር ስታበቅል (ብልት አካባቢ)
ሐ.በስሜት ማፍሰስ ስትጀምር (በብልት በኩል)
መ.የወር አበባ ሲታያት ናቸው ፡፡
ከአራቱ አንዱ ከተከሰተ ሴት ልጅ ልክ እንደ ትልቅ ሴት ግዴታ የሆኑ ዒባዳዎችን ሁሉ መፈፀም አለባት ፡፡
7ኛ - ጥያቄ፡- ያለፉትን ብዙ ረመዿኖች ለዓመታት አልፆምኩም አሁን ተውበት አድርጌ በደንብ መፆም ከጀመርኩኝ ገና ዓመቴ ነው። ታድያ ያለፉትን ዓመታት ቀዿ እንዴት ነው የማወጣው?
መልስ፡- ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ትንታኔ ያስፈልገዋል ያለፉትን ሳትፆም ያሳለፍካቸው ረመዿኖች በዛን ወቅት ሰላት የማትሰግድ ከሆነ ከኢስላም ውጪ ስለሆንክ ብትፆምም ፆምህ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን ባለፉት ባልፆምክባቸው ረመዿኖች ዘመን ሶላትህን አስተካክላ የምትሰግድ ከሆነ ያልፆምካቸውን ረመዿኖች ሁሉ ቀዿ ማውጣት አለብህ። ቀዿ ስታወጣ ቀዿውን ያዘገየህበት ምክንያት ከሌለህ በእያንዳንዱ ቀን ምስኪን ማብላት አለብህ። ቀዿውን በምክንያት ካዘገየህ ምስኪን ባታበላም ምንም አይደለም ፡፡
8ኛ - ጥያቄ፡- ፈርዽ የሆነ ፆም ቀዿ በማውጣት ላይ ያለ ሰው ቀን ላይ ፆሙን ማቋረጥ ይችላል? የሱንና ፆም (ነፍል) ቢሆንስ?
መልስ፡- ፈርዽ የሆነ ፆም ቀዿ በመፆም ላይ ያለ ሰው ፆሙን ማቋረጥ አይችልም። ፈርዽ ነውና! ነገርግን የሱንና ፆም (ነፍል) ከሆነ ቀን ላይ ማቋረጥ ይችላል ፡፡
9ኛ - ጥያቄ፡- እናቴ የስልሳ አመት አዛውንት ናት። አባቴን ካገባች ጀምሮ በወር አበባ ሰበብ ያልፆመቻቸውን ፆሞች ለሃያ ዓመት ቀዿ አላወጣችም። ምክንያቱ አባቴ ከፋራ ካደረግሽ በቂ ነው ይላት ነበር። አሁን ታድያ ምን ማድረግ አለባት?
መልስ፡- እናትህ በወር አበባ ሰበብ ያልፆሙትን ቀን በሙሉ መፆም አለባቸው። እንዲያውም ቀዿውን ስላዘገዩ በያንዳንዱ ቀን ምስኪን ማብላት አለባቸው ፡፡ አባትህን በተመለከተ በማያውቁት ነገር ፈትዋ መስጠታቸው ትልቅ ስህተት ተሳስተዋል ፡፡
10ኛ - ጥያቄ፡- አንድ ሰው በሕመም ምክንያት ሐኪም ከልክሎት የአራት ዓመት ረመዿኖችን አልፆመም አሁን ጤንነቱ ስለተሟላ ምን ማድረግ አለበት?
መልስ፡- በሕመም ምክንያት ያሳለፋቸው ፆሞች ጤናው ከተመለሰ ቀዳዿ ማውጣት ግዴታው ነው። አላህም በቁርአኑ ፡-
{....وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ}
«ከናንተ ውስጥ በሽተኛ ወይንም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ከሌሎች ቀኖች የተወሰነውን መፆም አለበት .... ―
[አል-በቀራህ: 185]
ቀዿ ሲወጣ ግን እንደፈለጉ አከታትሎም ሆነ አቆራርጦ መፆም ይቻላል። አላህ ከአቅም በላይ አያዝም። በቁርአኑም፦
{. فَاتَّقُوا اللَّهَ مَ اسْتَطَعْتُمْ}
«አላህንም የቻላችሁትን ያክል ፍሩት።» ብሏል!
[አ-ት'ተጛቡን: 16]
ምንጭ፦ የረመዿን ስንቅ
ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇
tiktok.com/@secretsof_truth
Instagram.com/secretsof_truth
t.me/Secretsof_Truth
Fb.com/SecretsofTruth1
ummalife.com/ReshadMuzemil
