es
Feedback
Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Secrets of Truth - 𝘽𝙮 𝙍𝙚𝙨𝙝𝙖𝙙

Ir al canal en Telegram

● ዲናችንና በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን ➶ Current information about Muslims and Islam 🔗 ሌሎችንም አንገብጋቢ ጉዳዮችን የምንተዋወስበት Channel ነው‼️ ➞ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አጠር ያሉ ስንኞች (በተለይም ስለ ፈለስጢን 🇵🇸) 🎯 አላማዬ:- የእውነትን ሚስጥሮች ማጋለጥ ነው‼️ #Free_Palestine 🇵🇸

Mostrar más
213
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-430 días
Archivo de publicaciones
🌾የጁሙዓ ኹጥባ በአማርኛ  🌾              ቁ/241 🔆 የፈጅር ሰላትን በአግባቡ    ለመስገድ አጋዥ ነገሮች      እሁድ 26/5/1445 ዓ.ሂ 🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም 📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!" አል-ኢማሙ ማሊክ

🔰 የሰዎች ስላእኛ የሚያስቡት ነገር አላህ እንዲደሰትብህ ብለህ ለሰዎች መልካምነትህን ስታሳያቸውና እሺታ ስታበዛ...... እነሱ ያስባሉ አንተ ጅል እንደሆንክ!! አንዳንዴ አስመሳይ እንደሆንክ ያስባ
🔰 የሰዎች ስላእኛ የሚያስቡት ነገር አላህ እንዲደሰትብህ ብለህ ለሰዎች መልካምነትህን ስታሳያቸውና እሺታ ስታበዛ...... እነሱ ያስባሉ አንተ ጅል እንደሆንክ!! አንዳንዴ አስመሳይ እንደሆንክ ያስባሉ፣ አንዳንዴ ደግሞ፡ “አይ በራሱ ስለማይተማመንና እውቀት ስለሌለው ነው” ይሉሃል። ኢማሙ ሻፊዕይ እንደ ሚሉን: ❝አንተ ከጌታህ ያለህን ነገር አስተካክል እንጂ ሰዎች ስለሚሉህ ነገር አትጨነቅ።❞ ► እኛም እንደነሱ እንላለን። ብቻ ላአላህ ብለን መልካም እንድንሆን አላህ ያግዘን መገዱንም ያቅጣጨን። ወንድምና እህቶቼ በመልካምነታችን፣ በጥሩ ስብዕናችን የተነሳ የሚነሳውን ትችትና ወቀሳ ተወት እናድርገው ነገር ግን የጌታችንን ነገር አደራ‼️ ጌታችን አላህን ባለማስከፋት (ባለማመፅ) ዘወታሪዎች እንሁን‼️ \\ ከወንጀል እንራቅ፤ ሁሉም የሰው ልጆች ወንጀለኞች ናቸውና ወንጀል በፈፀምን ጊዜ አላህን ምህረትና እዝነት እንጠይቅ። ⭕️ ዛሬ ላይ በእሺታችንና በመልካምነታችን የሚያላግጡ ሁሉ አንድ ቀን ይደሰቱብናል። ያኔ ለኩራትና በራሳችን ላይ ለመገረም (ለመደነቅ) ሳይሆን ለመታዘብ አላህ ያብቃን‼️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል Join:- YouTube.com/@SecretsofTruth tiktok.com/@secretsof_truth Instagram.com/secretsof_truth t.me/Secretsof_Truth Fb.com/SecretsofTruth1 https://ummalife.com/ReshadMuzemil t.me/ReshadMuzemil

Love of the dunya by sheikh Ibn Bâz رحمه الله

በኢብኑ ተይሚያ ላይ የተሰነዘረ ሃሰተኛ ክስ ~ ኢብኑ በጡጣ (779 ሂ.) የታወቀ ሃገር አሳሽ ነው። በሙስሊሙ ዓለም ሰፊ የሆነ አሰሳ አድርጓል። የአሰሳው ዝርዝርም ሪሕለቱ ኢብኒ በጡጣህ በተሰኘ መድብል ተጠናቅሮ ተቀምጧል። በዚህ ስራ ውስጥ ከተጠቀሱት ነጥቦች ውስጥ አንዱ የኢብኑ በጡጣ የደማስቆ ጉብኝት ነው። በዚህ ክፍል ላይ በታዋቂው የደማስቆ መስጂድ (መስጂደል ኡመዊ) ውስጥ "ኢብኑ ተይሚያ ሚንበር ላይ ሆኖ 'አላህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል፤ ልክ እንደዚህ አወራረዴ' ብሎ አንድ ደረጃ ሲወርድ ተመለከትኩት" የሚል ሰፍሯል። [ሪሕለቱ ኢብኒ በጡጣ፡ 110] ይህንን ውንጀላ የኢብኑ ተይሚያ ጠላቶች በሰፊው ሲቀባበሉት ማየት የተለመደ ነው። ዛሬም ድረስ የሚያነሱት የጥመት አንጃዎች አሉ። ይሄ ውንጀላ ቅጥፈት እንደሆነ በአምስት መልኩ ማረጋገጥ ይቻላል። 🔻 አንደኛ፦ ኢብኑ በጡጣ ደማስቆ የገባው ረመዳን 9/726 ሂ. እንደሆነ መዝግቧል። ኢብኑ ተይሚያ ግን እሱ ደማስቆ ከመድረሱ ከወር በፊት ሸዕባን 6/726 ሂ. እስር ቤት እንደገቡ ኢብኑ ከሢር፣ ኢብኑ ዐብዲል ሃዲና ኢብኑ ረጀብ መዝግበዋል። ሞተው አስከሬናቸው እስከሚወጣ ድረስም ከወህኒ አልወጡም። ስለዚህ ሰውየው ከነጭራሹ አላያቸውም። "ውሸታም ጥሩ የማስታወስ ችሎታ ያስፈልገዋል።" 🔻ሁለተኛ፦ በኢብኑ ተይሚያ ታሪክ ውስጥ የሚታወቀው ወንበር ይዘው የሚያስተምሩ እንደነበሩ እንጂ ሚንበር ላይ ወጥተው ኹጥባ የሚያደርጉ አልነበሩም። 🔻ሶስተኛ፦ በወቅቱ ኢብኑ ተይሚያ ላይ ብዙ ቅጥፈት የሚለጥፉ ጠላቶች እዚያው ደማስቆ ውስጥ ነበሩ። ግና አንዳቸውም ይህን ክስተት አልገለፁም። የሌለ ፈጥረው የሚወነጅሉ ሰዎች ተጨባጭ ነገር ቢያገኙ ፈፅሞ አያሳልፉም ነበር። እንኳን እንዲህ ዓይነት ከባድ ርእስ አግኝተው በፊቅሃዊ ጉዳይ ልዩነት ወህኒ የሚወረውሩ፣ በዱላ የሚደበድቡ ናቸው። 🔻 አራተኛ፦ በኢብኑ ተይሚያ ኪታቦች ውስጥ አንድም ማመሳሰል የለም። ፈጣሪን ከፍጡር የማመሳሰል አቋም ቢኖራቸው ኖሮ በኪታቦቻቸው ላይ በግልፅ ያሰፍሩት ነበር። በህዝብ ፊት ሚንበር ላይ ወጥቶ የሚናገር ሰው አቋሙን በኪታቦቹ ውስጥ ለማስፈር አይሸማቀቅም። 🔻 አምስተኛ:- ይልቁንም በኪታቦቻቸው ውስጥ የምናገኘው ከዚህ ተቃራኒ ነው። አንድ ሁለት ንግግሮቻቸውን ልጥቀስ፦ وَنُزُولُهُ وَاسْتِوَاؤُهُ لَيْسَ كَنُزُولِنَا وَاسْتِوَائِنَا “የአላህ መውረድና ከላይ መሆን እንደኛ መውረድና ከላይ መሆን አይደለም” ብለዋል። [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 5/352] በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦ وصفات الله تعالى لا تماثل صفاتِ العباد، فإنَّ الله تعالى ليس كمثله شيء لا في ذاتـه، ولا صفـاتِه، ولا أفعالِه» "የላቀው አላህ መገለጫዎች የባሪያዎች መገለጫዎች ጋር አይመሳሰሉም። የላቀው አላህ በዛቱም፣ በመገለጫዎቹም፣ በተግባራቱም ምንም የሚመስለው የለም።" [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 12/65] ስለዚህ "ኢብኑ ተይሚያ ሚንበር ላይ ሆኖ 'አላህ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ ይወርዳል፤ ልክ እንደዚህ አወራረዴ' ብሏል" የሚለው ውንጀላ የለየለት የፈጠራ ክስ ነው ማለት ነው። በነገራችን ላይ አሽዐሪዮች የሐሰት ውንጀላ በመለጠፍ ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው። አቡል ወፋእ ኢብኑ ዐቂል - ረሒመሁላህ -  እንዲህ ይላሉ፦ “አሻዒራዎች ከአህሉል ሐዲሥ ጋር በሚያደርጉት ሙግት ላይ ይዋሹባቸው ነበር።” [አረድ ዐለል አሻዒራህ፡ 91] ባይሆን በቁርኣንና በሐዲሥ የተረጋገጡ የአላህን መገለጫዎች ማፅደቅ የጀህ -ሚያ ቡድን ተከታዮች ዘንድ ማመሳሰል ተብሎ ነው የሚጠራው። ታላቁ ሰለፍ አቡ ዙርዐ አራዚይ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦ “አራቋቾች (المعطلة) አላህ በቁርኣኑ እንዲሁም በነብዩ ﷺ አንደበት እራሱን የገለፀባቸውን መገለጫዎች ያስተባብላሉ። ከአላህ መልእክተኛ ﷺ ስለ አላህ መገለጫዎች የተላለፉ ትክክለኛ ዘገባዎችን ያስተባብላሉ። ቀድመው ካመኑት ጥመት ጋር በሚስማማ መልኩ የተገለበጡ እይታዎቻቸውን እየተጠቀሙ መልእክታቸውን ያዞራሉ። ዘጋቢዎቹንም በማመሳሰል ይወነጅላሉ። ጌታቸውን እሱ እራሱን በቁርኣኑና በነብዩ ﷺ አንደበት በገለፀበት መልኩ ያለማመሳሰል የሚገልፁ ሰዎችን በማመሳሰል የሚወርፍ ሰው እራሱ አራቋች ነው። እነዚያን ወደማመሳሰል በማስጠጋታቸው እነሱ አራቋቾች እንደሆኑ መረዳት ይቻላል።” [አልሑጃ ፊ በያኒል መሐጃ፡ 1/187] ልብ በሉ! አቡ ዙርዐ ረሒመሁላህ ከኢብኑ ተይሚያ 464 አመት ቀድመው በ264 ሂጅራ ነው የሞቱት። ሌላኛው ሰለፍ አቡ ሓቲም አራዚይም (277 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፦ “የጀህ.ሚያ ምልክት የሱና ሰዎችን አመሳሳይ ብለው መጥራታቸው ነው።” [ዐቂደቱ ሰለፍ ወአስሓቢል ሐዲሥ፡ 304 - 305] በዚህ መነሻ መሰረት በቁርኣንና በሐዲሥ የተረጋገጡ የአላህን መገለጫዎች የሚያፀድቁ ሙስሊሞችን በማመሳሰል ቢወነጅሉ ውንጀላቸው ቡድናዊ ጥላቻ የወለደው ፈጠራ እንጂ እውነታ እንደሌለው መረዳት ይቻላል ማለት ነው። Ibnu Munewor

The 🌱 green #Makkah 🕋 you have never seen before. 😭😢
+2
The 🌱 green #Makkah 🕋 you have never seen before. 😭😢

🔰 አስቸጋሪ ጊዜያት ➝ እኛ የሰው ልጆች አቅመ ደካሞች ሆነን መታገስ ያቅተናል እንጂ እኛ ላይ የሚደርሱ ስቃይና መከራዎች ጥንካሬን ይወልዱልናል። በሉ እንደውም ምንም ያህል ከተራራ የገዘፉ ችግሮችን እንዴት መፍታት እንዳለብንና ከችግሩ መወጣጫ መሰላላ እንዴት ማበጀት እንዳለብን ያስተምሩናል። ► የተለያዩ ችግሮች በደረሱብን ጊዜ ስሜታችንን በተለያዩ መንገዶች ለመግለፅ እንሞክራለን። ችግሩን የሚፈታልን ይመስል ከልክ በላይ እንጨነቃለን እንጠበባለን። ► የደረሱብን ችግሮች መበጨነቃችንና በመተከዛችን የሚያበቁ ይመስል ራሳችንን እየወቀስንና “በቢሆን ኖሮ” ሀረግ ውስጣችንን እናደማዋለን። የደረሱብን ችግሮች የፈጠሩትን ቁስል የሚያክምልን እስኪመስል ድረስ እንበሳጫለን፣ እናለቅሳለን፣ ከሰው መግባባት ይከብደናል፣ ምናልባትም ራሳችንን በተለያየ ነገር እንጎዳለን። ► አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የሚደግፉን ሰዎች ከጎናችን ሆነው ሳለ እኛ ግን ህይወታችን ያከተመለት ይመስል የምንይዘው የምንጨብጠው እናጣለን። ወዳጆቼ የኛ መጨነቅና መጠበብ የሚቀይረው ነገር ካለ እሺ፤ ነገር ግን ምንም የሚቀይረው ነገር ሳይኖር በባዶ ሜዳ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ አግባብ አደለም። የኛ መጠበብ የሚቀይረው ነገር ቢኖር አንድ ነገር ነው እሱም እኛን ከጠንካራነት ወደ ደካማነት ይቀይረናል። ➤ከእርጋታ ይልቅ ብስጩነትን፣ ➤ ከአውንታዊ ይልቅ አሉታዊነትን፣ ➤ ከለጋስነት ይልቅ ንፉግነትን፣ ➤ ከትዕግሥት ይልቅ ትእግስት ማጣትን፣ ➤ ከጥሩ ልማድ ይልቅ መጥፎ ልማድን፣ ➤ ከሰናይ ስነምግባር ይልቅ ስነምግባረ ብልሹነትን ማንነታችን ያደርግብናል፤ እራሳችንን ቀይሮ መልካምነታችንን ከነ-አካቴው ከኛ ያርቅብናል። ታዲያ ይህ ሁሉ ውርደትና ዝቅጠት የሚፈጠረው ትዕግሥት ባለማድረጋችን ነው። ➰ አዎ ችግሮቹ ሊበዙብን ይችላሉ ግን እኛን ሊጠቅመን ወደ ብርኃን ጎዳና ሊመራን የሚችለው ብቸኛው መንገድ “ትዕግሥት” ነው‼️ ➰ እኮ አዎ እጅግ በጣም ፈታች የሆኑ ፈተናዎች ሊገጥሙን ይችላሉ ነገር ግን የነዚህን ፈተናዎች መውጫ መሰላሉን የሚያቅጣጨን ትዕግሥትን ያረገዘ ሙከራና ጥረት ነው። እናም እላችኋለሁ ......... 📒 በህይወታችን አስቸጋሪ የሚባሉ ግዜያትን የምልፍ እንደሆነ ያኔ ጠንካሮች መሆናችንን እናውቃለን። ⭕️ አላህ ሶብር ይስጠን!! ⭕️ አላህ መልካም ነገር ላይ ያፅናን!! በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል tiktok.com/@sharpswords1 https://t.me/SharpSwords1 www.youtube.com/@SharpSwords1 Instagram.com/sharp_swords1 https://ummalife.com/ReshadMuzemil

ለሰዎች ጥሩ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?
+6
ለሰዎች ጥሩ የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?

🔰 ባሮችህ ረገፉ በፈለስጢን ምድር - በአላህ ቤት በመስጂደል አቅሳ - ነብዩ ባረፉበት በካኃዲዋ እስራኤል - ረገፉ ህፃናት ቦምብ ዘነበባቸው - እንቅልፋቸውን በተኙበት ዓለምም ችላ አለው - ይህን የዘር ማጥፋት ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ ሙስሊም የሆኑ - ኢባዱ ራህማን ናቸው ሰው ናቸውና ያራሂም - ካጠፉም ማራቸው መንገድ ስተው እንደሆን - መንገድ አሳያቸው ሙስሊሞቹም ያንተ - ህፃኖች ያንተው ካንተ ውጭ ሌላ መጠጊያም ዬላቸው! አዎ ወጀለኞች ነን - ነብሳችንን በዳይ ድንበር አላፊዎች ነን - በሰጧን አታላይ ለብልጭልጭ ህይወት - በርከክ ባይ ለዚህች ለቀን ጤዛ - ደሞም ለዱንያ ላትሆነን መንገድ - ጀነትን መዝለቂያ እያጠለቀችልን - የአዛብ ሜዳሊያ ግን አንገሰፅም - ከዚህ ሁሉም ነገር በኛ ወንጀል የተነሳ - ሙስሊሙ ሲሸበር ጠላት ተጠራርተው - ሁሉም ባአንድ ሲያብር እኛ ስንባላ - በጎሳ በብሄር እኛ ስንከፋፋል - በቋንቋ በዘር አስክሬኖች በርክተው - አፈር ሲለብስ በዶዘር እኛ ቆይ የት ገባን - ቆይ የትስ አለቅን!? ቆይ ምን ዋጠን - ምንስ ላይ ሰመጥን!? ሙስሊም ረገፈ እኮ - እኛ በቁም እያለን ጂሃዱስ አይሳካ - ያአላህ ማለት አቃተን! የሙስሊም መሣሪያው - ዱዓ ነው እየተባልን፤ ያራህማን ያራሂም - እኛስ ቀሽሞች ነን፤ ሙስሊሞች ነንና - እባክህን ማረን አዛኝ ነህና - ያአላህ እዘንልን ውስጣችን ቆሰለ - ደም ዘነበ ከዓይን ወንድሞቻችን አለቁ - በከሃዲዎች ረገፉብን እነዛ የሰው አውሬዎች - ያንተን ቤት ደፈሩብን። ያረቢ የአላህ - ሰማዩ ሰማይህ ያራህማን ያራሂም - ምድሩም ምድርህ ያአላህ ያ! ራህማን - ቤቱም ቤትህ ድረስላቸው ጌታችን - ጀባሩ ያአላህ ከጭንቅ ጠብቃቸው - ከጭንቅ አውጪ ነህ ብዙዎች ቆሰሉ - ብዙዎች አለፉ በህይወት እያሉ - ባሮችህ ደም ተፉ በዘረጋሃው ምድርህ - ሙስሊሞች ተገፉ እነዛ አውሬዎች - ሬሳን አሰለፉ ሴትም አልቀራቸው - ህፃንም ቀጠፉ ገደልን እያሉ - በደስታም ደነፉ ⭕️ በባረከው ምድርህ - *ባሮችህ ረገፉ* ። በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ቀን: ጥቅምት 20/2016 E.C [Oct 31/2023 G.C]

አንተ ምን ያህል ግዜ ጌታህን ምህረት ትጠይቃለህ? ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ አለ፦ ﴿واللَّهِ إنِّي لَأَسْتَغْفِرُ اللَّهَ
አንተ ምን ያህል ግዜ ጌታህን ምህረት ትጠይቃለህ? ከአቡ ሁረይራ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ: ረሱል (ﷺ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ አለ፦ ﴿واللَّهِ إنِّي لَأَسْتَغْفِرُ اللَّهَ وأَتُوبُ إلَيْهِ في اليَومِ أكْثَرَ مِن سَبْعِينَ مَرَّةً﴾ “በአላህ እምላለሁ! እኔ በቀን ውስጥ ከሰባ ግዜ በበዛ እስቲግፋር ‘ጌታዬን ምህረት መጠየቅ’ እና በተውበት ‘በንስሃ ወደ ጌታዬ’ መመለስ አደርጋለሁ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 6307 ጆይን፦ t.me/BuhariMuslimAmharic

➺🌸┊↷ የጧት ዚክር አይርሱ..!!   []…ዚክር፦ የቀልብ ብርሀን፣ የልብ መድሀኒት፣ የአካል ብርታት፣ የምላስ ጌጥ ነው። ‏أصبحنا وأصبح المُلك لله ربِّ العالمين، اللهم إني أسألك خير هذا اليوم فتحه ونصره ونوره وبركته وهداه، وأعوذ بك من شرِّ ما فيه و شرِّ ما بعده، لا تنسَ اذكار الصباح. ▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

Shaykh Muqbil رحمه الله said: “Whoever wants to be honored by Allāh and his status be raised, then upon him is this Qur’ān.“
Shaykh Muqbil رحمه الله said: “Whoever wants to be honored by Allāh and his status be raised, then upon him is this Qur’ān.“ [Shareet as-Sa’ādah]

“የሰፊውን ህዝብ ልብ መግዛት ከፈለጋችሁ… የመሪዎቻችሁን ነውር አደባባይ አውጥታችሁ ተናገሩ። ለነርሱ ያላችሁን ንቀት አሳዩ!” የሁዲው ዐብደላህ ኢብኑ ሰባእ (የኸዋሪጅ መስራች) 🔴 “የሚያሳዝነው ይህ አይሁዳዊ ምክርና መርህ በኸዋሪጆች እና በእነርሱ ተፅእኖ ስር የወደቁ ተራ ሙስሊሞች እስከእለታችን እየሰሩበት ይገኛል።” 🎙አሸይኽ ሱለይማን አር–ሩሓይሊይ የቁባእ መስጂድ ኢማምና ኸጢብ tiktok.com/@sharpswords1 https://t.me/SharpSwords1 www.youtube.com/@SharpSwords1 Instagram.com/sharp_swords1 https://ummalife.com/ReshadMuzemil