cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ለሁሉ Mindset

" ስብዕና ገንቢ እና መነቃቃትን የሚፈጥሩ ለሁሉም ፣ በሁሉም ከሁሉም የተገኙ ሀሳቦች በጥሩ ቋንቋ የሚቀርቡበት ቻናል ነው። "

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
283
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
-830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ፈልገህ ቅረባቸው! ብርቱ እጆች ይደጋገፉ ዘንድ፣ ህልመኛ ነፍሳት ይተሳሰሩ ዘንድ፣ ንቁ አዕምሮዎች ይግባቡ ዘንድ፣ ጠንካራ ልቦች አብረው ይጓዙ ዘንድ፣ አዋቂዎች እውቀትን ይመጋገቡ ዘንድ የግድ ነው። የሚመስልህን ለማግኘት ግዴታ በአዋጅ ማስነገር፣ ማስታወቂያ ማሰራት አይጠበቅብህም፤ ስሜትህ በእራሱ ይጠራዋል፤ ማንነትህ በእራሱ ያቀርበዋል። ነገር ግን ይህ ስሜት የማይዋዥቅ፣ ማንነትህም የማይዛባ መሆን ይኖርበታል። አንዴ ሰው አንዴ አፈር እየሆንክ የሚጠጋህን ሰው አታገኝም። ጓደኞችህን ተመልከት፣ በቅርበት የምትግባባቸውን ሰዎች አጢናቸው፣ ቀለል የሚሉህን ሰዎች አስተውላቸው ቅርበታቸው፣ ጓደኝነታቸው፣ ቅለታቸው ያለምክንያት ይመስልሃል? በፍፁም! የሚያመሳስላቹና የሚያቀራርባችሁ ብዙ ነገር ይኖራል። አብረውህ ያሉ ሰዎች አብረውህ የሆኑት፣ የቀረቡህ፣ የተወዳጁህ በምክንያት እንደሆነ አስተውል፤ ከዚህም በላይ ሌሎች ተጨማሪ ሰዎች እንደሚያስፈልጉህ እወቅ። እነዛን ያስፈልጉኛል፣ ይረዱኛል፣ ሃሳቤ ይገባቸዋል፣ ራዕይዬን ይጋሩኛል የምትላቸውን ሰዎች ፈልገህ አግኛቸው። እነዛን የእኔ ያልካቸውን፣ ይደግፉኛል ያልካቸውን፣ አገናኝ የጋራ ሃሳብ፣ ህልም፣ ራዕይ አለን ብለህ የምታስባቸውን ሰዎች ፈልገህ ቅረባቸው፣ ተወዳጃቸው፣ አብረሃቸው ሁን፣ አብረሃቸው ስራ፣ ደግፋቸው፣ ይደግፉህ። ብቻህን ጊዜ የፈጀብህ ነገር በህብረት፣ በትብብር፣ በአንድነት ወዲያው ይጠናቀቃል፣ ለተሻለው አፈፃፀምና ግብ ያዘጋጅሃል፣ ለላቀው ከፍታ ያቀርብሃል፤ ወኔና ብርታት ይሆንሃል። ሃሳብ እንኳን ሸክም ነው፤ ጭንቀት በእራሱ ህመም ነው፤ ለውጥን እየፈለጉ ሳያደርጉ መቅረትም የምኞት ስቃይ ነው። ደክሞሃል? ድካምህን የሚጋራ ብርቱ ደጋፊ ተወዳጅ፤ ሃሳብ በዝቶብሃል? ለሃሳብህ እውንነት ከጎንህ የሚቆመውን ሰው ቅረብ። ስራህ ሰልችቶሃል? በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎችን ተዋወቅ። ብቻህን ከምትሮጥ አሯሯጭ ፈልገህ አብረሀኸው ሩጥ፣ ብቻህን ከምትጀግን አንተን መሳይ ሌላ ጀግና ፈልገህ አብረኸው ጀግን፣ ብቻህን ከምታልም ህልመኛ ፈልገህ አብረኸው በትልቁ አልም። የተደጋገፉ እጆች ግንብ ይነቀንቃሉ፣ የተባበረ ክንድ ጠላትን ይረታል፤ አንድነት የእድገት መሰረት ነው። ብቸኝነትህ ሃይልህ ነው፤ ነገር ግን ሲደክምህ ድጋፍ ያስፈልግሃልና ከመደገፍ ወደ ኋላ እንዳትል፤ ያልገባህን ጠይቅ፤ ያልተረዳኸውን ተረዳ፤ ያላወከውን ከማንም እንዴትም እወቅ። ለከበደህ ነገር እጅ ከመስጠትህ በፊት ድጋፍ በመፈለግ ለማሸነፍ ሞክር። @lehuluMINDset
Mostrar todo...
በራሳችሁ ወስኑ ! የተሳሳተ ውሳኔ መወሰን ከፈለጋችሁ ብዙ ሰው ጠይቁ፣ ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን ከፈለጋችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ብዙ ሰው ስላማከራችሁ የሚቀርላችሁ ውድቀትም ሆነ የምታመልጡት የተሳሳተ ውሳኔ የለም። ሰው ሲበዛ ሀሳብ ይበዛል፣ ሀሳብ ሲበዛ የግል አቋም ይሸረሸራል፣ የግል አቋም ሲሸረሸረ የተሳሳተ ውሳኔ ይወሰናል። ምን ያህል የሚያውቁትን ሰው በሙሉ አማክረው ተክክለኛ የሚጠቅማቸውን ውሳኔ የወሰኑ ሰዎችን ታውቃላችሁ? እናንተስ በምንም ነገር ዙሪያ ውሳኔ ማሳለፍ ስታስቡ ብዙ ሰው የማማከር ልማድ አላችሁ ወይስ በእራሳችሁ ትወስናላችሁ? ብዙ ሰው መደገፍ አቋም አልባ ልፍስፍስ እንደሚያደርግ አስታውሱ። በራሳቸው የሚተማመኑ፣ የማያወላዳ አቋም ያላቸው ሰዎች በምን ዙሪያ ማንን ማማከር እንዳለባቸው፣ ማንስ የተሻለ ሀሳብ ሊሰጣቸውና የበለጠ ሊያበረታታቸው እንደሚችልም ጠንቅቀው ያውቃሉ። የምታማክሩትን ሰው ካልመረጣችሁ መጨረሻ ላይ ምራጭ ሆናችሁ የምትቀሩት እናንተ ናችሁ። አቋም ይኑራችሁ፣ ለየትኛውም ውሳኔያችሁ ሃላፊነት መውሰድን ተለማመዱ። ውሳኔያችሁ ትክክል የሚሆነው ሰው ስላበዛችሁ ሳይሆን ማማከር ያለባችሁን ጥቂት ሰው ማወቅ ስለቻላችሁ ነው። መንገድ ጠፍቷችሁ ስትጠይቁ አላውቅም ማለት እየቻለ በማያውቀው አቅጣጫ የሚጠቁማችሁ ሰው በበዛበት በዚህ ጊዜ ብዙ ሰው አማክሬ የምፈልገውን ሀሳብ አገኛለሁ ብላችሁ አታስቡ። ስለማያውቀው ነገር አላውቅም ማለት ውርደት የሆነበት በጣም ብዙ ሰው አለ። በአላዋቂነት ተሞልቶ በአዋቂነት ሽፋን የሚመላለስ ብዙ ሰው አለ። አንዳንድ ውድቀትህን በጉጉት ይጠብቃል:: አንዳንዱም እንዲሁ አይነ ውሃህ አይጥመውም። ከምንም በላይ ተግባርን እመኑ። አንዳንድ ሰዎች በከንፈራቸው ስኳር በልባቸው መርዝን እንደሚያስቀምጡ አስታውሱ። የምትጠጓቸው ሰዎች ወይ ትንሿን የተስፋ ጭላንጭል ሙሉ ያደርጓታል አልያም ከነጭራሹ ያጠፏታል። እያላችሁ ካልሆነ ሳይኖራችሁ ለማይቀርባችሁ ሰው ብላችሁ የችግራችሁን ክብደት ከፈጣሪ ደብቃችሁ ሰው ጋር አትሩጡ። ሰው ህመምም መድሃኒትም ነው፣ እግዚአብሔር ግን መድሃኒት ነው። ከባድ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን፣ አጣብቂኝ ውስጥ ብትገባ፣ ነገሮች ቢምታቱብህ፣ ለውሳኔ ብትቸገር እንዲሁ ግራ ቢገባህ ወደ ምታውቀው ሰው ሁሉ ከመሮጥህ በፊት ከእግዚአብሔር አምላክህ ጋር ተወያይ፣ በፀሎት በልመና ፈጣሪህን አማክረው፣ በትክክለኛው መንገድ ይመራህ ዘንድ ተማፀነው። ወደድክም ጠላህም ህይወትህ የእያንዳንዱ ውሳኔዎችህ ጥርቅም ውጤት ነች። ለመወሰን ስታንገራግር እሷም ታንገራግራለች፣ እራስህን አጠንክረህ በድፍረት ስትወስን አሷም ታደፋፍርሃለች። በፈጣሪህ እገዛ የራስህን ጉዳይ ለራስህ ለመወሰን ደፋር ሁን። አንድ ነገር አስታውስ ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰን የተሳሳተ ጊዜ የለም። የውሳኔ ሰው ሁን፣ ሃላፊነት ውሰድ፣ መማር ካለብህም ቶሎ ወስነህ ከተሳሳተ ውሳኔህ ተማር። @lehuluMINDset
Mostrar todo...
እስክታሸነፍ እስክታሸንፍ ማንም ድካምህን አይረዳም፣ እስክታሸንፍ ማንም ጥረትህ አይገባውም፣ ውጤት እስክታመጣ ማንም ትኩረት አይሰጥህም፣ ተፅዕኖ መፍጠር እስክትጀምር ማንም ዞር ብሎ አያይህም። የዓለም ጨዋታ ሲበዛ ተሽለው ለተገኙት ያደላል፣ የሰው ልጅ ከጥረትህ በላይ ውጤትህን ያደንቃል። ምድራዊውን አሰራር መቀየር አትችልም ነገር ግን እራስህን መቀየር ትችላለህ፣ የዓለምን ህግ ተጋፍጠህ ማሸነፍ አትችልም አንተ ግን እራስህን አሸናፊ ማድረግ ትችላለህ። ስለለፋህ የምትሸለምበት መድረክ የለም፣ ያለማቋረጥ ስለደከምክ ስምህን የሚያነሳ አይኖርም። መድረክ ሁሉ የአሸናፊዎች ነው፤ ትኩረት የሚሰጠው በጥረታቸው ተፅዕኖ መፍጠር ለቻሉት ነው። ሳታሸንፍ መኖር ትችላለህ ነገር ግን የተሸናፊነትን ጠዓም መለማመድ ይኖርብሃል፤ ያለውጤት መድከም ትችላለህ ነገር ግን አንድ ቀን ድካምህ ውጤት እንደሚያመጣ ልታምን ይገባል። እስክታሸንፍ... ድጋፍ ብትፈልግም አታገኝም፣ እስክታሸንፍ... ቦታ እንዲሰጥህ ብትማፀን፣ ክብርን አብዝተህ ብትፈልግ፣ የተለየ እንክብካቤን ብትመኝም ማንም አይሰጥህም። ከምንም በፊት ትልቅ የቤት ስራ አለብህ። ምኞትህ እውን ይሆን ዘንድ ምንም ያህል ጊዜ ቢፈጅም እራስህን ለአሸናፊነት ብቁ ማድረግ ይኖርብሃል፣ የቱንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍልህ ክብርህን እራስህ መፍጠር አለብህ። ለምነህ የምታገኘው ክብር የለም፣ እየተሸማቀክ የምትጎናፀፈው ድል አይኖርም። ቀና ማለት፣ ቀናውን ማድረግ፣ እስከመጨረሻው መፋለም፣ መክፈል ያለብህን ዋጋ መክፈል፣ ያስከብረኛል፣ ህይወቴን ይቀይረዋል፣ ተፅዕኖ እንድፈጥር ያደርገኛል ብለህ ለምታስበው ነገር በማይዛነፍ ተነሳሽነት፣ በማይቀዘቅዝ ወኔ ልትፋለምለት ይገባል። የትኛውም ውድ ነገር ውድ ዋጋ ያስከፍላል፣ ማንኛውም ምርጥ ነገር ትልቅ ጥረት ይጠይቃል። ውድነትን የማይፈልግ የለም፣ ውድ ለመሆን የሚታለፈውን እልህ አስጨራሽ ጥረት ግን ማንም አይፈልግም፤ አሸናፊነት የሁሉም ሰው ምኞት ነው፣ ለአሸናፊነት የሚያበቃውን ውሳኔ የሚወስን ግን እጅግ ጥቂት ነው፤ ተፅዕኖ መፍጠር የማይፈልግ ሰው አይኖርም፣ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚያስችለውን ጉዞ የሚጓዘው ግን በጣም ትንሽ ሰው ነው። ብዙ ባልተሰራበት ሀገር ትንሽ መስራት ህይወትን ይቀይራል፣ ብዙ በተሰራበት ሀገር ግን ከልክ በላይ ሰርቶም ህይወት ላይቀየር ይችላል። አንተ የቤት ስራህን ሳትሰራ ማንም በሃዘኔታ ክብርና ሞገስን እንዲያጎናፅፍህ አትጠብቅ። የዋህነት ሲበዛ ወደ ጅልነት እንደሚቀየር አስታውስ። ተሽለህ እስካልተገኘህ፣ የሚታይ ውጤት እስካላመጣህ በዘርፉ አንቱታን ማግኘት አትችልም። ምናልባት ብዙ አቋራጭ መንገዶች ይኖሩ ይሆናል፣ ነገር ግን ትክክለኛው ስፍራ ሊያደርሱህ አይችሉም። ሳታሸንፍ ማንም ክብርና ቦታ እንዲሰጥህ እንደማትለምን ለራስህ ቃል ግባ፤ አድርጎ በማሳየት እንጂ በሃዘኔታ የሚገኝ ክብር እንደሌለ እመን። @lehuluMINDset
Mostrar todo...
👍 2
ብልጥ ሁን! የተሻለ ነገር ይገባኛል ብለህ የምታስብ ከሆነ ከእኔ ይሻላሉ ብለህ ከምታስባቸው ሰዎች ጋር ህብረት ፍጠር፣ የህይወቴን ጥራት መጨመር እፈልጋለሁ ካልክ ህይወታቸው ጥራት ያለውን ሰዎች ሆን ብለህ አጥና፣ ገቢዬን ማሳደግ አለብኝ ካልክ በአቋራጭ ከበለፀጉት ሳይሆን ልክ እንዳንተ ከዜሮ ተነስተው የራሳቸውን ቢዝነስ ከገነቡ ሰዎች ቁጭ ብለህ ተማር፣ ስኬታማ የፍቅር ወይም የትዳር ህይወት እንዲኖርህ ከተመኘህ ዝቅ ብለህ በትህትና የተሳካ የፍቅር ወይም የትዳር ህይወት ያላቸውን ሰዎች ህይወታቸውን መርምር፣ የመግባባት ደረጃቸውን አጥና፣ የአብሮነታቸውን ሃይል ተመልከት፣ እርስ በእርስ ያላቸውን የመከባበር ልማድ ላንተ በሚሆን መልኩ ወደ ራስህ ውሰድ። ብልህ ሰው ብልሃቱ የሚገለፅበት አንደኛው መንገድ ከእርሱ ከሚሻሉት ለመማር ያለው ትጋት ነው። ጤናማ ያልሆነ የበታችነት ወይም የበላይነት ፉክክር ከጥፋት በቀር ሌላ የሚያተርፍለት ነገር እንደሌለ ያውቃል። ጥራት ያላቸው ሰዎች ምን ያህል ህይወቱ ላይ ጥራትን መጨመር እንደሚችሉ፣ ምን ያህል ውጤታማና ስኬታማ የህይወት ተሞክሮዎችን እንደሚያካፍሉት በሚገባ ያውቃል። ብልጥ ሁን! የትም ብትሔድ፣ ምንም ብትሰራ፣ እንዴትም ብትሰራ ካንተ የሚያንስ እንዲሁም ካንተ የሚበልጥ ሰው መኖሩን እወቅ። በምትበልጠው ፊት ደረትህን አትንፋ፣ እራስህን የተሻልክና ምርጡ ሰው አድርገህ አትቆልለው ይልቅ በምትችለው መንገድ የበታችህን እርዳው። ለጌታም ጌታ፣ ለመሪም መሪ እንዳለ አስታውስ። እንዲሁ ካንተ የሚሻል፣ በልምድም በስራ ጥራትም፣ በገቢም በኑሮ ደረጃም፣ በእውቀትም በማስተዋልም የሚበልጥህ ሰው ብታገኝ እራስህን የበታችነት አዘቅት ውስጥ መክተት አቁም። ይልቅ ለራስህ ብለህ ብልጥ ሁን፣ ወዳጅህ አድርገው፣ ዝቅ ብለህ ከርሱ ተማር፣ ቀርበህ አካሔዱን መርምር፣ የሚጠቅሙህን የህይወት መርሆች ኮርጅ። ምንም ሰጣ-ገባ ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ማንም ከርሱ የሚሻለውን ወንድሙን ቢያሰናክለው አንድም የራሱ አሰናካይ ከፊቱ እንዳለ እያሰበ በጥርጣሬ ይጓዛል ሌላም በስራ ተሽሎ የመገኘትን መርህ ያዛባል። የተፅዕኖ ፈጣሪውን ስም ከማጥፋት እንዴት ተፀዕኖ መፍጠር እንደቻለ፣ እንዴት ለዛ ከፍታ እንደበቃ፣ እንዴት ያንን ስብዕና እንደገነባ መመርመር እጅግ ትልቅ ትርፍ አለው። ምቀኝነት ዞሮ ዞሮ መዘዙ ለራስ ነው፣ ለሰው ክፋትን መመኘት፣ በሰው ውድቀት እራስን ቀና ለማድረግ መሞከር፣ በበዛ ጥላቻ፣ በማይገባ ኢጎ (EGO) የተሻለ ሰው ነኝ ባዩ ቁጥር ድክመቱን መዘርዘርና በቅናት መንጨርጨር ከትርፉ ጉዳቱ የሚያመዝን ከንቱ ተግባር ነው። ብልጦች ቢሆንላቸው ዙሪያቸውን የተሻሉና ከፍታ ላይ ባሉ ሰዎች ቢሞሉት ይመርጣሉ። ከአሸናፊዎች ጎራ ከተቀላቀልክ አንተም አንድ ቀን አሸናፊ የማትሆንበት ምክንያት አይኖርም። የምር የህይወትህ እድገትና መሻሻል የሚያሳስብህ ከሆነ ጤነኛ ካልሆነው ፉክክር እራስህን አውጣ፣ በምትኩ ከምትፎካከራቸው ሰዎች ልምድ ውሰድ፣ ተማር፣ የቅርብ ወዳጅም አድርጋቸው። ልክ እንደ ብልሆቹ በሰዓቱ ዝቅ ብለህ በጊዜህ ከፍታን ተጎናፀፍ። @lehuluMINDset
Mostrar todo...
ጊዜ ውሰድ አሁን አሁን ብክነት የሁላችን ክፍተት ሆኗል። ስራ የሰራን ቢመስለንም የበለጠውን ጊዜ በማይረባ ዋጋቢስ ነገር ስናሳልፈው እንገኛለን። እንዲሁ ስንባክን ዘመናት ያልፋሉ፣ ጊዜያት ይነጉዳሉ። ምናልባት ብክነታችን ለመልካም ነገር ቢሆን ጥሩ ነበር ነገር ግን አንዳች የሚረባ ነገር ለማናገኝበት ጉዳይ ውዱን ጊዜያችንና ስሜታችንን ስናባክንበት ይነጋል ይመሻል። እሴት ያለው፣ ትርጉም የሚሰጥ ህይወት ሳንኖር የድካም ጊዜ ይመጣብናል። ወደድንም ጠላንም በግዞት ስር ነን። ለዛውም መፈናፈኛ የማይሰጥ፣ ገፅን ሳይሆን ውስጥን የሚቀይር እጅግ አደገኛ ግዞት ስር ነን። ለእራሳችን ጀብደኛ፣ ሃይለኛ፣ ጠንካራ እንደሆንን እንናገር ይሆናል ማንነታችን ግን ከነዚህ ከፍታዎች ወርዷል፣ በህይወታችን እንደዚህ አይነት ጥራት መመልከት ከብዶናል። የተጫነብን ባዕድ አስተሳሰብና ልማድ የነበረንን መልካም ሃሳብና ሀገረኛ እሴት ቀምቶናል። ጊዜ ውሰድ! ለእራስህ የሚሆን፣ ውስጥህን የሚያንፅ፣ የፈጠራ አቅምህን የምታጎለብትበት፣ ስሜትህን የምትገራበት፣ ከልብህ የምትረጋጋበት ጊዜ ውሰድ። እንዲሁ በማህበራዊ ድረገፆች ሶስ፣ በማይመለከትህ የባህር ማዶ አጀንዳዎች፣ በህይወትህ ላይ ቅንጣት ታህል ለውጥ የማያመጣ መጨረሻ የሌለው ዜና ላይ መባከንህን አቁም። ለማሰብ ጊዜ ውሰድ፣ ለማቀድ፣ ነፃ ለመሆን ጊዜ ውሰድ። ውጤታማ በማያደርግህ ነገር እራስህን Busy አታድርገው። ስልክ የያዝከው ይበልጥ ህይወትህን እንዲያቀለው፣ ለመረጃ ቅርብ እንድትሆንና እውቀትና መረዳትህን እንድታሻሽልበት ሆኖ ሳለ አንተ ግን በተቃራኒው ህይወትህን እንዲያመሰቃቅለው ከፈቀድክ አደጋ ውስጥ እንደሆንክ አስተውል። ቴክኖሎጂ ለገባውና ለተጠቀመበት ማንም የማይሰጠውን ሃይል ይሰጠዋል፣ እራሱ እንዲጠቀመው ለፈቀደው ደግሞ እራሱንና ሌላውን እንዲያጠፉ ነገሮችን ያመቻችለታል። ስንት ሰው ነው አንድ ቀን ስልኩን ሳይጠቀም መዋል የሚችል? ስንት ሰው ነው ማህበራዊ ድህረገፅ ሳይገባ ቀኑን ማሳለፍ የሚችል? ስንት ሰው ነው የእራሱን፣ የልቡን፣ የውስጡን ዜናና ፍላጎት ብቻ እያዳመጠ ሙሉ ቀኑን ማሳለፍ የሚችል? ያለምንም ጥርጥር የዚህ ዘመን ጀግና አስቦበትና አቅዶ በየጊዜው ይህን የሚያደርግ ሰው ነው። የከፋው የባህር ማዶ ግዞት ስር ከመውደቃችን በፊት በቶሎ እንንቃ፣ ማንም ተነስቶ በሪሞት ከሚጫወትብን እኛው እራሳችን ማገናዘብ እንጀምር፣ በአስገዳጅ ጫናዎች ህይወታችን አቅጣጫ ከመሳቱ በፊት እኛው ደርሰን አናስቁመው። ከዘመናዊው የቀኝ ግዞት እራስህን አድን፣ እራስህን ሆነህ፣ እራስህን መስለህ፣ መሃበራዊ ባህል እሴቶችህን ጠብቀህ በየቀኑ የፈጠራና የአዲስ ግኚቶች ባለቤት በመሆን ዋጋህን ጨምር፣ የህይወትህን ጥራትም አሻሽል። @lehuluMINDset
Mostrar todo...
ድልድዩን ተጠቀም! አሸናፊውን ከተሸናፊው፣ ስኬታማውን ስኬታማ ካልሆነው፣ ተፅዕኖ ፈጣሪውን ከመደበኛው ሰው የሚለይ አንድ ነገር አለ። እርሱም ምን ይባላል? "ተግባር"። እድሜ ዘመንህን ለምን ትልቅ ነገር እያሰብክ አትኖርም፣ ሁሌም ከመተኛትህ በፊት ለምን አላማህን በምናብህ እየተመለከትከው አትተኛም፣ ለምን በየቀኑ ሳታቋርጥ ህልምህን እያለምክ አትቀጥልም ስራ እስካልጀመርክ ድረስ ምንም ነገር፣ እደግመዋለሁ ምንም ነገር ወደ ህይወትህ መጥቶ አንተን እድለኛ ሊያደርግህ አይችልም። እድለኛ መሆን ከፈለክ ማብቂያ የሌለውን የሃሳብ ዥረት አቁመህ ወደ ተግባር መግባት ይኖርብሃል። ብዙዎች ዛሬ ነገ በማለት እየጠበቁ ዛሬ የማይፈልጉትን ይኖራሉ፣ ብዙዎች እቅድ በማውጣት፣ ንድፍ በመንደፍ፣ አላማን በመዘርዘር ተጠምደው ዋናውን ስራ ችላ ብለውታል። ልዩነት ፈጣሪዎች ግን የሚያቅዱት ብቻ አይደሉም፣ ስኬታማዎች ግን በትልቁ የሚያስቡ ብቻ አይደሉም፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ግን ዛሬ የሚሉ ብቻ አይደሉም። ይልቅ የተግባር ሰዎች ናቸው፣ ይልቅ ከማሰብ በላይ ስራ ላይ የሚያተኩሩት ናቸው። ድልድዩን ተጠቀም! ከስኬት አልባነት ወደ ስኬታማነት፣ ከተራነት ወደ ተዓምራዊነት፣ ከመካከለኝነት ወደ ከፍታው፣ ከተመሪነት ወደ መሪነት፣ ከድህነት ወደ ብልፅግና መሻገር ከፈለክ ጊዜ ሳታጠፋ ድልድዩን ተጠቀም፣ ሳታመነታ ተግባር ጀምር። እድሎችን ስትጠብቅ እድሜህ ይሔዳል፣ ሰውን ስትተማመን፣ መንግስትን ስትጠበቅ እደሎች ያመልጡሃል። በምንም ሁኔታ ውስጥ እርምጃ መውሰድ፣ በየትኛውም አቅም ወደ ስራ መግባት፣ እንዴትም ያለውን አሰባስቦ ጥረት መጀመር ለዓመታት ከሚታሰበው ሃሳብ፣ ዘወትር እየታደሰ ከሚጣለው እቅድ፣ ሁሌም በወሬና በፉከራ ብቻ ከሚገለፀው ህልም እጅጉን የተሻለ ነው። ምናልባት የማይሆንህን ስራ በሃሳብ ብቻ ዓመታትን ብትፈጅ ወደ ተግባር ብተገባ እንኳን አለመስራቱን የምትገነዘበው ሞክረህ ካየኸው በኋላ ነው። በዚህ ሰዓት ሙከራው ላይ ከሚጠፋው ጊዜ በሃሳብ የባከነው ጊዜህ ያስቆጭሃል። ሁለት ያጣህ አትሁን። ሀሳብህን በጊዜ አቅጣጫ አስይዘው አልያም ሌላ ካንተ ማንነት ጋር የሚሔድ፣ ለመተግበር የሚቀልህን ነገር ጀምር። ነገ የተመቻቸ ጊዜ የሚመጣ ሊመስልህ ይችላል፣ በቀጣይ ዓመት የተሻሉ እድሎች እንደሚፈጠሩ ልታምን ትችላለህ ነገር ግን ብልጥ ከሆንክ ከዛሬውም የባሰ ጊዜ ሊመጣ እንደሚችል ታስባለህ፣ ከጥበቃው በላይ በጊዜያት ሂደት የምታገኘውን ልምድና እውቀት ታስበልጣለህ። ህይወት እንደ ጤዛ ነው። ጤዛ ጠዋት በድምቀት ይታያል፣ ፀሃይ ሲወጣ፣ ሙቀቱ ሲጨመር፣ በረሃኑ ሲያይል ቦታውን ይለቃል። የሆነ ጊዜ ትኩረቶች ሁሉ ወደኛ ይሆናሉ፣ በብዙዎች እንፈለጋለን፣ ተፅዕኗችን ይጎላል ነገር ግን ሁሉም ነገር በዛው ልክ አይቀጥልም። ከእያንዳንዱ ተፈላጊነታችን ጀርባ ምናልባትም እውቀታችን ሊኖር ይችላል፣ ምናልባትም የሚያምረው ቁመናችን፣ ማራኪው ገፃችን ወይም ታታሪነታችን ሊኖር ይችላል። እነዚህም ጥራቶቻችን በጫና ብዛት፣ በተሻሉ ሰዎች መምጣትና በእድሜ ጉዳይ በቀነሱ ቁጥር ተፈላጊነታችንም ይቀንሳል፣ ተፅዕኗችንም እንዲሁ እየወረደ ይመጣል። ተፅዕኖህን ለማቆየትም ሆነ በሃሳብህ ልክ ውጤታማ ለመሆን ሁሌም ተግባርን አይነተኛ ምርጫህ አድርገው። @lehuluMINDset
Mostrar todo...
ፈልግት ብቻ! እንዴት እንደሚሆን፣ ማን እንደሚያሳካላችሁ፣ እንዴት በእጃችሁ እንደሚገባ ማሰብና መጨነቅ አቁሙ። የምትፈልጉት ላይ በማተኮር ብቻ የምትፈልጉትን ወደ ራሳችሁ ሳቡ። እንዴት እንደሚሆንላችሁ የማብሰልሰሉ ሃላፊነት የእናንተ ሃላፊነት እንዳልሆነ እወቁ። ወደድንም ጠላንም ህይወታችን ከትኩረታችን የሚቀዳ ጭልፍታ ነው። ምንም ነገርን በስሜት ስትፈልጉት ወደ ህይወታችሁ ይመጣል፣ እራሳችሁን በርሱ ጉዳይ Busy ስታደርጉት ያለ የሌለ አቅማችሁ ወደዛ ይጓዛል፣ ሳታስቡት የሚተባበሯችሁን ሰዎች ታገኛላችሁ፣ ሁኔታዎች ሲመቻቹላችሁ ትመለከታላችሁ። ትኩረታችሁ ፍረሃታችሁን ያሸንፋል፣ ትኩረታችሁ ክህሎታችሁን ያሻሽላል፣ ትኩረታችሁ መንገዳችሁን ይጠርጋል። ትኩረታችሁን ስታሰለጥኑ፣ ስሜታችሁን ስትቆጣጠሩ፣ ሃሳባችሁን በሙሉ መሰብሰብ ስትችሉ ትክክለኛው አቅማችሁ ሲገለጥ ትመለከቱታላችሁ። ትኩረት ብቻ ሁለመናችሁን ይቀይረዋል፣ መርጣችሁ የምትጓዙበት የህይወት አቅጣጫ ብቻ የምትፈልጉበት ቦታ ያደርሳችኋል፣ በእያንዳንዱ ውሳኔያችሁ ብቻ መዳረሻችሁን መወሰን ትችላላችሁ። የሰው ልጅን አንድ ከሚያደርጉ ውድ ስጦታዎች ውስጥ አንዱ ትኩረት ነው። ምናልባት እንዳለን ልምድ ትኩረት የማድረግ አቅማችን ቢለያይ እንጂ ሁላችንም ትኩረት በማድረግ የምንፈልገውን ነገር ወደ ህይወታችን ማምጣት እንችላለን። ማንም እናንተን መማርክ ቢፈልግ በዋናነት የሚያደርገው ነገር ትኩረታችሁን መሳብ ነው። ትኩረታችሁን ለሳበ ነገር ጊዜያችሁን ትሰጣላችሁ፣ ገንዘባችሁን ትሰጣላችሁ እንዲሁ ስሜታችሁን ትሰጣላችሁ። ትልቁ ሃይላችሁ ትኩረታችሁ ውስጥ እንደሆነ እወቁ፣ የምታስቡት ነገር ከመዘግየቱ በላይ መሆኑን የምትፈልጉ ከሆነ በውስጣችሁ ያለው የእግዚአብሔር መንፈስ እውን እንዲያደርግላችሁ ከልባችሁ ፈልጉት፣ እያንዳንዱን ተግባራችሁን ከርሱ ጋር አገናኙት። የነፍስን ሃይል ስትረዳ፣ ደመ-ነፍስህ ያለው አቅም ሲገባህ ትኩረትን እንዴት መጠቀም እንዳለብህ ይገለጥልሃል። ደጋግመው ስለመታመማቸው የሚያስቡ ሰዎች ትኩረታቸው በሙሉ ህመሙ ላይ ነውና መታመማቸው አይቀርም፤ ታመው ደህና እንደሆኑ በስሜት የሚናገሩ፣ ጤንነታቸው ላይ የሚያተኩሩ ሰዎች በቀላሉ ከሚታየው ህመማቸው ሲድኑ ተመልክተናል። እምነት ከምንም ነገር ያድናል፣ ትኩረት ማድረግ ደግሞ አንደኛው እምነታችንን የምናሳይበት መንገድ ነው። ምንም ነገር ላይ ካላመንክ ትኩረት ልታደርግበት አትችልም። ትኩረትህን ሰብስብ፣ የምትፈልገው ነገር ላይ አውለው፣ ሃይልና ብርታት እንዲሆንህ አድርግ። ብዙ ነገር በያዘ፣ ብዙ ነገር ባሳደደ ሳይሆን አንዱን የያዘውን ነገር ጠበቅ አድርጎ በያዘና አንዱን ነገር አሳዶ በእጁ ባስገባ ነው። ትኩረትህን በሚገባ ተጠቀም የምትፈልገውን ነገር የህይወትህ አንድ አድርገው።
Mostrar todo...
👍 1
ከጥቂቶቹ ተቀላቀል! ተለይቶ መውጣት ድፍረት ይጠይቃል ነገር ግን መለየት ካልቻልክ የአብዛኛው እጣ ይገጥምሃል፤ ከተለመደው አካሔድ ማፈንገጥ አይን ውስጥ ያስገባል፣ ለብዙ አደጋ ያጋልጣል፣ የተለየ ስም ያሰጣል ነገር ግን ከተለመደው መንገድ ካልወጣህ የተለየ ነገር ልታገኝ አትችልም። ጥቂት አስጨብጫቢዎች ባሉባት ዓለም ከጥቂቶቹ ጎራ ካልተቀላቀልቅ ዘመንህ በሙሉ በአጨብጫቢነት ሲያልቅ ትመለከታለህ፣ ጥቂት አስከታይ ብዙ ተከታይ ባለባት ዓለም መከተልህን አቁመህ እራስህን ወደ አስከታይነት ካልቀየርክ ሁሌም አውሪ እንጂ አድራጊ ሆነህ ልትገኝ አትችልም። ዓለም ክብርን አጥብቀው ለሚፈልጉ፣ ከልባቸው ዋጋ ለሚከፍሉ፣ ለርሱ ብለው እስከ መጨረሻው ለሚታገሉ ሰዎች የመስጠት ችግር የለባትም። ተፈጥሮ ፍላጎትህን ታከብራለች። ከአብዛኛው ጎራ ሆነህ አድናቂና ተከታይ ብቻ መሆን የምትፈልግ ከሆነ ሁሌም በሯ ክፍት ነው፤ ከአብዛኛው ተለይተህ፣ ጥቂቱን መርጠህ በእራስህ መንገድ መጓዝ ከፈለክም ማንም የሚያስቆምህ ሰው የለም። መለየትን አትፍራ፣ ከጥቂቶቹ ተቀላቀል፤ አሸናፊነትን አትሽሽ ዋጋ ከፍለህ በእጅህ አስገባው። የሚያዋጣህን ምርጫ ስትመርጥ፣ የሚበጅህን ውሳኔ ስትወስን፣ በፈለከው መንገድ መጓዝ ስትጀምር ብዙ ቢያይህም የሚያስተውለው ጥቂቱ ነው። ዛሬ ተፅዕኖ መፍጠር የቻሉ፣ ዛሬ ተሰሚነት ያላቸው፣ ዛሬ ህዝብ ከልቡ የሚወዳቸው፣ ዛሬ የአሸናፊነትና የፅናት ተመሰሳሌት የሆኑ ሰዎች የሆነ ጊዜ እንዳንተው ለአሸናፊዎች የሚያጨበጭቡ፣ የብዙሃኑን ሃሳብ የሚያስተጋቡና ሂዱ በተባሉበት የሚሔዱ ነበሩ። ነገር ግን አነርሱም አሸንፈው ማስጨብጨብና መደነቅ እንደሚችሉ ባመኑ ጊዜ የአሸናፊነት ጉዟቸውን በአምላካቸው ድጋፍ ጀመሩት፣ ለአመታት ያለማቋረጥ ተጓዙ፣ ብዙ ጫናዎችን ተቋቋሙ፣ ደጋግመው በተስፋ መቁረጥ ተፈተኑ በስተመጨረሻ ግን እንደቀደሙት ተምሳሌቶቻቸው የአሸናፊነቱን መድረክ መቆጣጠር ቻሉ። ጥቂቶች ደፍረው የሚመርጡትን መንገድ ለመምረጥ አታመንታ፣ ለፈተናዎች እራስህን አዘጋጅ፣ ተለተይቶ በመውጣትም ጥቂቶች የደረሱበት ስፍራ እራስህን አስቀምጥ። @lehuluMINDset
Mostrar todo...
👍 1
እስራቱን ፍታ! በትናንት ወይም በአሁን ሁኔታህ ውስንነት አይሰማህ፣ ጠፍንጎ ያሰረህን የአመለካከት እስራት ፍታ። ማንም ሰው አዲስ ነገር መሞከር ሲፈልግ ስጋት አለበት፣ ማንም ሰው ወደ ፊት መጓዝ ሲፈልግ ፍረሃት ይይዘዋል። የዚህ ስጋትና ፍረሃት ዋነኛ መነሻውም የአመለካከት ውሱንነት ነው። አዕምሮህ በሃሳብ ደረጃ የሚያመላልሳቸው ነገሮች አንድም እስራትህን ፈተው ነፃ ያወጡሃል ሌላም ይባስ አጥብቀው አስረው መፈናፈኛ ያሳጡሃል። ምንም ደፋር፣ ጠንካራና ባለራዕይ ብትሆን የአመለካከት ውሱንነት ካለብህ በድፍረትና በጥንካሬ ብቻ የምታሸንፈው ነገር አይኖርም። ከሁሉ የሚቀድመው ትግል የአመለካከት ትግል ነው፤ ከየትኛውም አሸናፊነት የሚልቀው የስነልቦና አሸናፊነት ነው። ብዙዎች ምንም የሚያስፈራቸው የግል ጉዳይ በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ከሰዎች በተለየ መልኩ የሀገርን ወይም የዓለምን ሁኔታ እንደ ፍረሃታቸው ምንጭ ይጠቀሙታል። ከውስንነት ውጣ፣ እንዲሁ በባዶ መስጋትህን አቁም። "ፍረሃት ባይኖር ምን አይነት ህይወት እኖር ነበር?" ብለህ እራስህን ጠይቅ። ያለ ፍረሃት ህይወት ቀላልና አሰልቺ ነች፤ ከፍረሃት ጋር ግን ከባድና በጀብድ የተሞላች ነች። እነዛ ከፍረሃታቸው በላይ የሆኑ ሰዎች ልበ ሙሉዎች ናቸው፣ በራስ መተማመናቸው በየጊዜው ይጨምራል፣ በሁኔታዎች አይገደቡም፣ ከትናንትና ከአሁን የላቀ ስፍራ ላይ መድረስ እንደሚችሉ ያምናሉ። እምነት ከፊት ለፊት የተደቀነባቸውን አደጋ የሚያልፉበት ሁነኛ መሳሪያቸው ነው። ከመታሰራቸው በፊት የእስራታቸው መፍቻ ምን እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። በፍረሃት፣ በስጋት፣ በጭንቀትና በውሱንነት ዓለም ውስጥ ከሆንክ ማድረግ የሚጠበቅብህ አንድ ነገር ብቻ ነው። ለእያንዳንዳቸው ያለህን አመለካከት አስተካክል። የምትፈራው ለምንድነው? የምትሰጋው ምን እንዳይመጣብህ ነው? ተጨንቀህ የምታገኘው ወይም የመታተርፈው ነገር ምንድነው? ከውሱንነትህ ብትወጣ ምን የሚፈጠር ይመስልሃል? ለእያንዳንዱ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ባዘጋጀህ ቁጥር የአመለካከት ለውጥህን ታስተውላለህ። የትም ሂድ፣ ምንም አድርግ፣ ከማንም ጋር ሁን አንተ በፍቃድህ እስካልቀየርከው ድረስ የማይቀየረው አመለካከትህ ሁሌም አብሮህ ይኖራል። አመለካከት ትንሽ ነገር ሊሆን ይችላል የሚፈጥረው ልዩነት ግን እጅግ ግዙፍ ነው። ካለህበት ነባራዊ ሁኔታ በላይ ልዩነት ፈጣሪ የሚያደርግህ ነገር በሁኔታው ዙሪያ የምታራምደው አመለካከት ነው። አሸናፊዎች ደጋግመው የሚያሸንፉት፣ ተሸናፊዎችም ደጋግመው የሚሸነፉት በአሸናፊነት ዙሪያ ባላቸው አመለካከት ነው። ሁሌም እራስህን እንደ አቅመ-ቢስና ደካማ ሰው የምትመለከት ከሆነ በምንም ተዓምር ጠንካራውንና ብርቱውን አንተ ልትፈጥረው አትችልም። የሰው ከራሱ አስተሳሰብ በላይ አቅሙን የሚገድብ፣ ውስንነቱን የሚያጎላና የበታችነትን የሚጭንበት ነገር የለም። አመለካከትህን አስተካክል፣ አስተሳሰብህን ሞግተው፣ በፍረሃት ካጠረህ የውሱንነት ዓለም ውጣ። ወድቀው የቀሩትን ሳይሆን ተነስተው ግባቸውን የመቱትን፣ ከፍረሃት ወለል በታች የሚዋትቱትን ሳይሆን ፍረሃትን አሸንፈው ቀና ብለው የሚራመዱትን፣ ስኬትን ለእነርሱ እንደማይቻል፣ አሸናፊነትም ለእነርሱ እንደማይሆን የሚያምኑትን ሳይሆን ከምንም ተነስተው ስኬታማ የሆኑትን፣ በአመለካከታቸው ልህቀት አሸንፈው የተገኙትን ብርቱ ሰዎች ተከተል፣ በእነርሱ መንገድ ተጓዝ፣ ከውስንነት ክልል ወጥተህም እራስህን አሳይ። @lehuluMINDset
Mostrar todo...
በውሸት አትደልለው! ካንተ የተሰወረ ነገር ያለ ይመስል የማያሳምኑ ምክንያቶችን እየደረደርክ እራስህን የበታችና አቅመ-ቢስ አታድርገው። ለእራስህ የምትናገረው እያንዳንዱ ነገር ቀጥታ ከውስጣዊ ሃይልህና ተነሳሽነትህ ጋር እንደሚገናኝ እወቅ። ለተወሰነ ጊዜ እራስን መዋሸት ወይም ለአጭር ጊዜም እራስን መደለል ይቻል ይሆናል ነገር ግን በፍፁም እስከመጨረሻው እራስን እየዋሹና እያስመሰሉ መኖር አይቻልም። ምንም ነገር ከማድረግህ በፊት በነገርየው ዙሪያ ያለህን ግንዛቤ ከአንተ አቅም ጋር ማስማማት ይኖርብሃል። የማያውቁትን ስራ መጀመር በአየር እንደተሞላ ፊኛ አየር ላይ ያንሳፍፋል። ማስመሰል በማንኛውም ሰው ህይወት ውስጥ ይኖራል። የሌለውን እንዳለው፣ ያልደረሰበትን እንደደረሰበት፣ ያላሳካውን እንዳሳካው፣ ያልያዘውንም እንደያዘው አድርጎ የሚያወራው ሰው ጥቂት አይደለም። እውነታውን ልቡ ያውቀዋል ነገር ግን ለሰዎች ብሎ እውነታውን ይክዳል፣ ያለበት ነባራዊ ሁኔታ ለእርሱ ግልፅ ነው ነገር ግን ሌሎችን እያምታታ መኖርን ይፈልጋል። ሌሎችን በማታለል ምኞቱን ለማሳካት ይጣጣራል። ያልሆነውን ማንነት እየሰጠህ ለከፋው ውድቀት አታመቻቸው፣ ለሰው ብለህ የገዛ እራስህ ጠላት አትሁን። እራስህን ክደህ፣ ትክክለኛ ማንነትህን ንቀህ፣ መገለጫዎችህን ጥለህ የምታገኘው ክብርም ሆነ ፍቅር ምንህ ነው? ሁሌም ከራስ ጋር ድብብቆሽ መጫወት አይሰለችምን? በየጊዜው ሆን ብሎ እራስን ማጥቃት አያሳምም? ማንም የተቀባባ ማንነትህን ቢቀበልህ ከልቡ እንደማያደርገው ውስጥህም ያውቀዋል። እንኳን ሰውን ለማስደነቅ ለመኖር ይቅርና በቅጡ እራሳችንን ለማስደሰት ለመኖር እንኳን ያለችን ጊዜ አጭር እንደሆነች አስታውስ። ካልዋሸህ የማይወድህ፣ ካላስመሰልክ የማይቀበልህ ማህበረሰብ ያለ ይመስል በየሔድክበት የውሸት ቅባትህን መቀባት አቁም፤ ያገኘኸውን ሁሉ በማይመስል ታሪክ ማምታትህን አቁም። ለእራሱ ያልታመነ ሰው በምንም መንገድ በህይወቱ እምርታን ሊያመጣ አይችልም። ድብብቆሹ ይብቃህ፣ ለእራስህ ባዳ መሆን ይብቃህ፣ እራስህን መደለል አቁም። በማስመሰል ሰዎችን ልትገዛ ትችላለህ እራስህን ግን መግዛት አትችልም፤ በውሸት ብዙዎችን ልትማርክ ትችላለህ እራስህን ግን ልትማርክ አትችልም። እራስን ሳያሸንፉ ዓለምን ለማሸነፍ መሯሯጥ ትርፉ የውስጥ ስብራትና ባዶነት ነው። ማንም ከሚያውቅህ በላይ እራስህን ታውቀዋለህ፣ ማንም ከሚረዳህ በላይ እራስህን ትረዳዋለህ። ከእያንዳንዱ ያልተገባ እርምጃ ጀርባም ምን እንደሚመጣብህ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። በማታለል ገፅህ ሊያሸበርቅ ይችላል ውስጥህ ግን መረጋጋት ይርቀዋል፣ በማስመሰል ንብረት ልታፈራ ትችላለህ ሰላምን ግን ታጣለህ። ስለራስህ የምታውቀውን እያወክ እንዳላዋቂ መኖር አቁም፤ የሚሰማህን ስሜት መግፋት፣ የእራስ ግንዛቤህን ችላ ማለት፣ ከእራስ በላይ ሌሎችን በእራስህ ላይ ማንገስ አቁም። ለእራስህ ታመን፣ ከነእንከኑ እውነተኛው ማንነትህን ተቀበል፣ እንዳቅምህም በሂደት እያሻሻልከው ተጓዝ። @lehuluMINDset
Mostrar todo...