cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም

በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 265
Suscriptores
Sin datos24 horas
+147 días
+8330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

➡️ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከካም ሴራሚክ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር  በመሆን ከ2 ቢሊዮን  በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት  የሴራሚክ አምራች ፋብሪካ አቋቋሙ። ⏺ የፋብሪካው ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ወደ ምርት እንደሚገባ በስካይ ላይት ሆቴል  በተደረገው ይፋዊ የአክሲዮን  የመመስረቻ ስነ ስርአት ላይ ተገልጿል። ⏺ በስምምነት የፊርማ ስነ-ስርአቱ የተከበሩ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሥራ መመሪያ እና የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ⏺ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ  ወ/ሮ  መልእክት ሳህሉ ተገኝተዋል።
Mostrar todo...
👍 2🥰 1
Photo unavailableShow in Telegram
በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ለሚገነባ ኩባንያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ፈሰስ ተደርጎበት ለሚገነባ ኩባንያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ። የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም፣ የኮርፖሬት ሀብት አስተዳደር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አለማየሁ ሰይፉ እና የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ቤተልሄም ጥላሁን የመሰረተ ድንጋዩን አስቀምጠዋል። የሚገነባው ማምረቻ ከጤፍ የተለያዩ ስናኮችንና ደረቅ የምግብ ዓይነቶችን የሚያመርት ሲሆን በፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ እና ትሬዲንግ ኩባንያ አማካኝነት ነው የሚገነባው። በዚሁ ወቅት የኮርፖሬሽኑ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም÷ ወደ ኮርፖሬሽኑ ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረቻውን በ11 ሄክታር የለማ መሬት ላይ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የፔሪ ሜትር ኮንሰልቲንግ ኩባንያ ከ1 ኘጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበትም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡ የግንባታ ስራው ተጠናቆ በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ምርቶቹን ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና የሩቅ ምስራቅ ሀገራት እንደሚልክ ተገልጿል። (FBC)
Mostrar todo...
👍 1👏 1
እንኳን ደስ አለን!!! የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግዥና ንብረት ባለስልጣን ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ ምክር ቤቱ ዛሬ ሰኔ 4/2016ዓ/ም ባካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ የባለስልጣኑን አዋጅ ማጽደቁ ተሰምቷል፡፡ የጸደቀዉ አዋጅ በአፈጻጸም ትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለማረምና ከዘመነ አሰራር ጋር ለመራመድ የሚያሥችል፣ ብሎም የሃገር ዉስጥ ተወዳዳሪዎች ያላቸዉን ተሳትፎ ለማበረታታት የሚያስችል ድንጋጌ ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የጸደቀዉ አዋጅ በመንግስት ልማት ድርጅቶች  ጭምር ተፈጻሚ መሆኑንና የሚከሰቱ የሕግ ጥሰቶች የሚያስከትሉትን አስተዳደራዊ ተጠያቂነት ያካተተ አዋጅ መሆኑም ተነግሯል፡፡ የባለስልጣኑ ረቂቅ በአዋጅ ቁጥር 1333/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን የተገኘዉ መረጃ ያመላክታል፡፡ (መግንባ)
Mostrar todo...
👍 2
Photo unavailableShow in Telegram
👉 የዛሬ የሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችን 🚧 ይህ የሬድዮ ፕሮግራም የሀገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ የተለያዩ የግንባታ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ተግዳሮቶች ውስጥ የግንባታ ግብዓት ችግር፣ የቴክኖሎጂ ዕጥረት፣ ብቁ የሆነ ባለሙያ አለመገኘትና የግንባታ ደህንነት ወይንም ሴፍቲ እና ሌሎችም ጉዳዮች የሚነሱበት ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው፡፡ ⏺ ወቅታዊ በዛሬው ወቅታዊ ፕሮግራማችን ላይ የምንመለከተው የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ሰሞኑን በአዳማ ከተማ ያካሄደውን መድረክ በተመለከተ ወደ እናንተ የምናደርሰው መረጃ ይኖረናል፡፡ 👷የእንግዳ ሰዓት -  ኢ/ር ጀበል ጀማል የጀጀኮን ኮንስትራክሽን ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ እና ኢ/ር ሀብታሙ ታደሰ የቲዌይ ኮንስትራክሽን ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ጋር በእንግዳ ሰዓት ፕሮግራማችን ላይ በቀጥታ ስርጭት የምናደርገው ቆይታ እንደተጠበቀ ነው፡፡ ዛሬም እንደተለመደው ስራ ተቋራጮች በተመለከተ የምናነሳቸው ጉዳዮች ይኖራሉ፡፡ በዚህ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ደግሞ ማንሳት የምትፈልጉት ጥያቄም ካለ እንደተለመደው አድርሱን፡፡ እንቀበላለን፡፡ 🥍📻 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችንን ትከታተሉ ዘንድ ከወዲሁ በአክብሮት እጋብዛለሁ፡፡
Mostrar todo...
2
💥የሳይት መሐንዲስ ሚና 🌟የሳይት መሐንዲስ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ፣ በበጀት እና በጥራት ደረጃ መጠናቀቁን በማረጋገጥ በግንባታው ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። 🚧በግንባታ ላይ የሳይት መሐንዲስ ዋና ዋና ኃላፊነቶች መካከል፡- 🌟1. የግንባታ ሥራዎችን የመቆጣጠር፡ የሳይት መሐንዲስ በየእለቱ የሚከናወኑ የግንባታ ሥራዎችን የመቆጣጠር፣ በፕሮጀክት መሥፈርቶችና በፕሮጀክት መሥፈርቶች መሠረት መከናወኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የጊዜ መስመር. 🌟2. የጥራት ቁጥጥር፡- የሳይት መሐንዲሱ ሥራ በፕሮጀክት ዝርዝር መግለጫዎች እና በኢንዱስትሪ ደንቦች የተቀመጡ የጥራት ደረጃዎችን የማሟላቱን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። 🖱የፕሮጀክቱን ጥራት ለማረጋገጥ ሥራን መፈተሽ፣ ፈተናዎችን ማካሄድ እና ማንኛውንም ችግር መፍታት ይችላሉ። 🌟3. ጤና እና ደህንነት፡- ⏺የሳይት መሐንዲሱ የጤና እና የደህንነት ደንቦች በቦታው ላይ መከበራቸውን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። ⏺ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን የመለየት እና የመፍታት፣ የደህንነት እርምጃዎችን የመተግበር እና የደህንነት ፍተሻዎችን የማካሄድ ሃላፊነት አለባቸው። 🌟4. ግብዓቶችን ማስተዳደር፡- የሳይት መሐንዲሱ ፕሮጀክቱ በተያዘለት መርሃ ግብር እና በበጀት ውስጥ እንዲቆይ ለማድረግ እንደ ቁሳቁስ፣ መሳሪያ እና ጉልበት ያሉ ሀብቶችን በብቃት የመምራት ሃላፊነት አለበት። 🌟5. ከባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት፡ የሳይት መሐንዲሱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ማለትም ደንበኞችን፣ ተቋራጮችን፣ አቅራቢዎችን እና የቁጥጥር አካላትን ጨምሮ እንደ መገናኛ ነጥብ ሆኖ ያገለግላል። ⏺የፕሮጀክት ሂደትን የማሳወቅ፣ ጉዳዮችን የመፍታት እና የሚነሱ ችግሮችን የመፍታት ሃላፊነት አለባቸው። 🫵በአጠቃላይ የሳይት መሐንዲሱ የግንባታ ሥራዎችን በመከታተል፣የጥራትና የደኅንነት ደረጃዎች መሟላታቸውን በማረጋገጥ፣ሀብትን በመምራትና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገናኘት የግንባታ ፕሮጀክቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
Mostrar todo...
👍 8 3👏 1
Mostrar todo...
Ethio con Tender

የግንባታ ጨረታዎችን የምታገኙበት ቻናል ነው። የቻናሉ ቤተሰብ ይሁኑ!

➡️ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ2 ሺ 700 ጊጋ ዋት በሰዓት በላይ ኃይል አመንጭቷል። 👉 ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት አሥር ወራት ከ2 ሺህ 700 ጊጋ ዋት በሰዓት በላይ ኃይል ማመንጨቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡ 👉በሁለት ተርባይኖች ኃይል እያመነጨ የሚገኘው የህዳሴ ግድብ፤ በ2016 በጀት ዓመት አስር ወራት ከዕቅዱ የ26 በመቶ ብልጫ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል አመንጭቷል፡፡ 👉የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ የዕቅድ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሺፈራው እንደገለጹት፤ ግድቡ 2 ሺ 711 ጊጋ ዋት በሰዓት አመንጭቷል። 👉ግድቡ የተሻለ ውሃ መያዙና ሁለቱ ተርባይኖች በሙሉ አቅማቸው ኃይል እንዲያመነጩ ተደርጓል። 👉 ባለፋት አስር ወራት በአጠቃላይ ከመነጨው የ16 ሺህ 900 ጊጋ ዋት በሰዓት የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ16 በመቶ ድርሻ እንዳለው ተጠቁሟል። 👉 ኃይል በማመንጨት ላይ የሚገኙት የግድቡ ሁለቱ ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 375 ሜጋ ዋት የማመንጨት አላቸው። 👉 በግድቡ ላይ የሚተከሉት ቀሪ 11 ዩኒቶች ኃይል ማምረት ሲጀምሩ አሁን በሀገሪቱ ያለውን የማመንጨት አቅም በ83 በመቶ ያሳድገዋል። 👉 የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ 5ሺህ 150 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም የሚኖረው ሲሆን፤ ዓመታዊ የኃይል ምርቱም 15 ሺህ 760 ጊጋ ዋት በሰዓት ይሆናል። (EBC)
Mostrar todo...
👍 2
✈️ 23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ሊገነቡ ነው፡፡ ከፍተኛ የአውሮፕላን ማረፍያ በሌለባቸው ነገር ግን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች አሉባቸው በሚባልባቸው አካባቢዎች ትናንሽ አየር ማረፍያዎች እንደሚገነቡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡ 👉 የትራንስፖርትና ሎጂስትክስ ሚኒስትር ዶ/ር አለሙ ስሜ የኢትዮጵያ መንግስት ለአዳዲስ የአውሮፕላን ማረፍያዎች ግንባታ የሚሆን በጀት አለመያዙን ተናግረው አሁን የሚገነቡ ትናንሽ አየር ማረፍያዎች በተለያዩ ወጪዎች የሚሸፈኑ ይሆናል ብለዋል፡፡ 👉 በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የሚገነቡት 23 ትናንሽ አውሮፕላን ማረፍያዎች ተለይተው መታወቃቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ የአዋጭነት ጥናት የመሬት ጥናት እና ሌሎችም ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ 👉 እነዚህ ግንባታዎች በራሳቸው ወጪ ለማከናወን የክልል መንግስታት ፍላጎት ማሳየታቸው የተነገረ ሲሆን ባለሃብቶችም ጭምር ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተነገረው፡፡ (ኢትዮ ኤፍ ኤም)
Mostrar todo...
👍 2 1
1:04:31
Video unavailableShow in Telegram
ኢትዮ ኮን ግንቦት 26፤2016
Mostrar todo...
191.96 MB
👏 1
Photo unavailableShow in Telegram
👉 የዛሬ የግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችን 🚧 ይህ የሬድዮ ፕሮግራም የሀገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ የተለያዩ የግንባታ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ ተግዳሮቶች ውስጥ የግንባታ ግብዓት ችግር፣ የቴክኖሎጂ ዕጥረት፣ ብቁ የሆነ ባለሙያ አለመገኘትና የግንባታ ደህንነት ወይንም ሴፍቲ እና ሌሎችም ጉዳዮች የሚነሱበት ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው፡፡ ዛሬ በሶስት ምዕራፍ የተከፈሉ ፕሮግራሞች አሉን፡፡ 🔷ወቅታዊ ⌨በዛሬው ወቅታዊ ፕሮግራማችን ላይ የምንመለከተው የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ሰሞኑን በአዳማ ከተማ ያካሄደውን ፕሮግራም እንመለከታለን፡፡ 👷የእንግዳ ሰዓት -  ኢ/ር ጀበል ጀማል የጀጀኮን ኮንስትራክሽን ባለቤትና ዋና ስራ አስኪያጅ እና ኢ/ር ሀብታሙ ታደሰ የቲዌይ ኮንስትራክሽን ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ጋር በእንግዳ ሰዓት ፕሮግራማችን ላይ በቀጥታ ስርጭት በክፍል ሶስት ቆይታ እናደርጋለን። ዛሬም ከሳምንት የቀጠሉ ጉዳዮችን እያነሳን ቆይታ ይኖረናል፡፡ 🏗 ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚቀርበው ልዩ ዝግጅት የፕሮግራማችን አንድ አካል ነው። ኮርፖሬሽኑን በእጅጉ እናመስግናለን! ✳️ በዚህ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ደግሞ ማንሳት የምትፈልጉት ጥያቄም ካለ እንደተለመደው አድርሱን፡፡ 🥍📻 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችንን ትከታተሉ ዘንድ ከወዲሁ በአክብሮት እጋብዛለሁ፡፡
Mostrar todo...
👍 2🙏 2 1