cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Sharp Swords // ስለታማ ሰይፎች

↪️ አግራሞቴን በብዕር የእይታን አድማስ የሚያሰፉበት፣ ➝የጥሩነት ጥሩነት የሚያውቁበት፣ ➝የመጥፎነትን መጥፎነት የሚያውቁበት፣ ➝ለነገሮች ያሎትን ምልከታ የሚያሳድግ። ➝ደግነትን የሚዘክሩ፤ ክፋትን የሚያወግዙ ብሎም የሚጠሉ። ➝አንዳንዴ ደስታ፤ አንዳንዴ ደግሞ ሀዘን የሚቦርቅበት። ●የተደበላለቁ ስሜቶችን ባማረ የስነ-ፅሑፍ ዘይቤ የሚቀርብበት የናተው መድረክ! በናተው ወንድም:- በረሻድ ሙዘሚል

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
275
Suscriptores
+324 horas
+97 días
+830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

አግራሞቴን በብዕር ♻ ህይወት እንደ መፅሐፍ ናት!! የህይወት ፈተና ብዙ ነው!! ግን ተስፋ አትቁረጥ። ከዛሬ ነገ ይሻላልና። ምናልባት ዛሬ የፀሐይን ብርሃን ለማየት አልታደልክ ይሆናል፤ ግን እድል አለህ ነገ ልታያት ትችላለህና ተስፋ አትቁረጥ!! ምናልባትም ዛሬ ሰዎች ባማረ ንግግራቸው ይመፃደቁብህ ይሆናል፤ አንተ በውብ ዝምታህ ትበልጣቸዋለህና ተስፋ አትቁረጥ!! ምናልባትም ሰዎች በስልጣናቸው ተጠቅመው እንዳሻቸው ይጋልቡህ(ያዙህ) ይሆናል፤ ግን ስልጣን የሰጣቸው ፈጣሪ ነውና አሁንም ተስፋ አትቁረጥ!! አዎ ተስፋ አትቁረጥ ምታገኛቸውን መልካም እድሎች ሁሉ ተጠቀም፤ እድሎች እንደ ንጋት ጀምበር ናቸውና በጣም ረጅም ጊዜ ከጠበቁ ሊያመልጡህ ይችላሉ። የንስር አሞራ እድሜው 70 አመት እንደሆነ ታውቃለህን!? አዎ እድሜው 70 አመት ነው፤ ግን ይህን 70 አመት ለመኖር በ40ኛ አመቱ ለ5 ወር ያክል በጣም ከባድ መስዋዕትነት መክፈል አለበት።  ምክንያቱም የእግር ጥፍር በአግባቡ መስራች የሚችለው ለ40 አመት ብቻ ነው። ቀሪውን 30 ዓመት ለመኖሮ ያሻውን ቦታ ለመብረርና የፈለገውን ነገር ለመመገብ 5 ወር ሙሉ ወደ ከፍተኛ ተራራ ላይ ይወጣና ጥፍር ያበቅላል። ምናልባት አንተም የፀሐይን መውጣት አይተህ መግባቷን ለማየት ግን አልታደልክም ይሆናል ግን ተስፋ አትቁረጥ። ብቻ በአጭሩ የምልህ ነገር ቢኖር........ ◆ ህይወት አንደ መፅሐፍ ናት!! በህይወትህ መጥፎ ነገር ሲከሰት፤ መፅሐፉን አትዝጋው ሌላ ገፅ ገልጠህ አዲስ ምዕራፍ ጀምር!! ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
Mostrar todo...
አግራሞቴን በብዕር ◆ ከቤት አንፃር በር በጣም ትንሽ ነው!... የቁልፍ ጋን  ከበሩ አንፃር በጣም ትንሽ ነው!...ቁልፍ ደግሞ ከሁሉም አንፃር በጣም ትንሽ ነው። ነገር ግን ቁልፍ የቤቱን መግቢያ በር ይከፍታል። ➤ ትንሽ ሀሳባዊ መፍትሔ ትልቅ ችግርን ሊፈታ ይችላል። ችግሮች ገዝፈው ይታዩህ ይሆነል መፍትሔውን ግን ከእጅህ ላይ ፈልግ። ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል
Mostrar todo...
አግራሞቴን በብዕር . . .   "ሁል ግዜ እንደምነግርህ ዛሬም አዲስ ቀን መጥቷልና አንተም ከአዲሲቷ ፀሀይ ጋር በአዲስ መንፈስ ተዋሀድ!. . . ከትናንቱ ጊዜ መልካሙን ነገር ብቻ ውሰድ. . . ...... ለእውነት እንጂ ለውሸት አትገደድ!! ....... ስለ ነገ እያሰብክ ዛሬ ላይ ተራመድ!! ....... ነገን ስትደርስ ትላትን አታስወግድ!! ..... ዛሬውኑ ተነስ ወደስኬት ሂድ!! ...... ካጋጠሙህ ነገራቶች ምትወስደው መልካም መልካሙን ከሆነ አንተንም ደስተኛ ያደርጉሃል። ...... ካጋጠሙህ ነገራቶች መጥፎ መጥፎውን እየወሰድክና ስለሱ እያሰብክ ምትኖር ከሆነ በገዛ ፍቃድህ ጭንቀታም እንድትሆን ፈቅደካል ማለት ነው። ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ለአስተያየት: t.me/ReshadMuzemil ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 YouTube: youtube.com/@SharpSwords1 Instagram: Instagram.com/sharp_swords1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil
Mostrar todo...
𝐑𝐞𝐬𝐡𝐚𝐝 𝐌𝐮𝐳𝐞𝐦𝐢𝐥

ኒቃቧን ትለብሳለች...ትምህርቷንም ትማራለች። አላህ የደነገገውን የዲን ድንጋጌ የሰው ሰራሽ ህግ አይሽረውም።

Photo unavailableShow in Telegram
እንዴት ነሽ ያ! አቅሳ⁉️ እንዴት ነሽ ፈለስጢን⁉️ ድምፃችን ደርሷል - ከዚህ ይሰማሻል፣ የአላህ የሚሉ - አጆች ይታዩሻል፣ እዛ ደርሶ ይሁን - ከአንደበታችን ቃል፣ ጌታቸውን የሚማፀኑ - የረብ  እያሉ ፣ በህመምሽ የታመሙ - ክፉኛ የቆሰሉ፣ በሁኔታው አዝነው - መድማትሽ ያደማቸው፣ በህፃናት ለቅሶ - ያዘነ ውስጣቸው፣ ካንቺ ስለራቁ - አቅም የከዳቸው። ለእውነት የቆሙ - ውሸት አንበርካኪዎች፣ የሀቅ ጓደኛ - የአይሁድ ጠላቶች፣ ጌታችን እያሉ - የነፃነት እጆች፣ ያአላህ የሚሉ - የጨቅላ አንደበቶች፣ ያዓዚዝ የሚሉ - የህፃናት ምላሶች፣ ከጎንሽ እኮ ናቸው - የአላህ ባሮች። አቅም አንሷቸው ነው - ጦር ሜዳ ያልገቡት፣ እሩሩሩሩቅ ስላሉ ነው - አንቺን የራቁት፣ ሙስሊሞች ናቸው - ረስተውሽ አይደለም ሰላምታ ደርሶሻል? - አሰላሙ አለይኩም። ዝም ያሉ መስሎሽ ነው - የታመምሽ ክፉኛ⁉️ ምድርሽ ተበክሎ - በአይሁድ መጋኛ፣ ደምሽን አፍስሰው - በሬሳ ሲረማመዱ፣ የዘናጋው እንዳይመስልሽ - እያየ ነው ሶመዱ። ቁስልሽ ያቁስለን - ውሎሽን ንገሪን፣ አጫውቺን የሆንሽውን - መድማትሽ ያድማን፣ አንገትም እንድፋ - ማዘንሽ ያሳዝነን፣ ማማረር እናቁም - የንቺን ስቃይ አውቀን፣ እንዴት ነሽ በአላህ - ያ! አቅሳ ንገሪን⁉️ እንዴት ነሽ ፈለስጢን - ያ! አቅሳ ንገሪን⁉️ ። በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ቀን:- እሁድ/ የካቲት 24/2016 ዓ.ል
Mostrar todo...
👍 4
Photo unavailableShow in Telegram
💻 አውፍ በይን አቅሳ 🇵🇸 አንቺ እየቆሰልሽ - እኛ ፈገግ እንላለን፤ አንቺ እያለቀስሽ - እኛ  እንስቃለን፣ በማይረባ ነገር - እርሰበርስ እንባላለን፤ ትላንት አዝነንልሽ - ዛሬ ጨክነናል፤ ባለፈ ዱዓ አድርገን - ዛሬ ዘግተናል፤ አውፍ በዪን ፈለስጢን - እኛ ጨክነናል፤ ይህ ሁሉ ሳያንሰን- በወንጀል ተዘፍቀናል፤ አወይ የኛ ክፋት - ምንኛ ጨካኝ ነን⁉️፤ ለወንድሞቻችን ወድቀት - ቀመር እንቀምራለን፤ በእህቶቻችን አይብ - እንሳለቃለን፤ ሰዎችን ለመጣል - ሴራ እናሴራለን፤ በዚያ ግን ትቀጠፋለች - የኛዋ ፈለስጢን። አቅሳ፣ ፈለስጢንን እያየን - ለሰዎች አናዝንም⁉️፤ አላህ ነስሩን እንዲሰጠን - ማመፅ አናቆምም⁉️፤ ወደ ጌታችን ተመልሰን - የአላህ አንልም⁉️፤ አረ ይበቃናል - በቁማችን ሞትን፤ መቃብር ሳንገባ - አፈርም ለበስን፤ ህይወት አላቸው እንዲሉ - እየተንቀሳቀስን፤ ክፋታችን ከፍቷል - ረሳናት ፈለስጢንን፤ ልባችን ጨከነ - ዘነጋናት አቅሳን። ለአላህ ስትይ - አቅሳ አውፍ በይን፣ አንቺ እየቆሰልሽ - እኛ ፈገግ እንላለን፤ አንቺ እያለቀስሽ - እኛ  እንስቃለን፣ ትላንት አዝነንልሽ - ዛሬ ጨክነናል፤ ባለፈ ዱዓ አድርገን - ዛሬ ዘግተናል፤ አውፍ በይን ፈለስጢን - እኛ ጨክነናል፤ አውፍ በይን አቅሳ - እኛ ጨክነናል። 🇵🇸  🇵🇸  🇵🇸  🇵🇸   🇵🇸  🇵🇸   🇵🇸  🇵🇸 📙 በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል 🕤 ቀን:- ማክሰኞ/ የካቲት 26/2016 ዓ.ል ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Tikto: tiktok.com/@secretsof_truth Instagram: Instagram.com/secretsof_truth Telegram: t.me/Secretsof_Truth Facebook: Fb.com/SecretsofTruth1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አግራሞቴን በብዕር በሰዎች ልብ ውስጥ መልካም አሻራን ትተህ ማለፍ ካቃተህ በልባቸው ውስጥ የማይረሱ ህመሞችን አትዝራ። በህይወትህ ውስጥ ለሰዎች የደስታቸው ምክንያት እንጂ የጭንቀታቸው (የውድቀታቸው) ምክንያት አትሁን።💡 ሌሎችን ለማስደሰት እንጂ ለማስጨነቅ አትጣር። ምክንያቱም........ ➤ ለሌሎች ደስታ ካንተ ደስታ ላይ አይወሰድም፣ ➤ ሐብት ማግኘታቸው ከሐብትህ ላይ ምንም አይቀንስም፣ ➤ ጤነኛ መሆናቸው ጤናህን አይወስድም፣ ➤ ቅን በመሆንህም ትጠቀም እንጂ አትጎዳም። ስለዚህ ጥርት ያለና ንፁህ ልብ ይኑርህ፤ ለሌሎችም ጥሩን ተመኝ ላንተም ባላሰብከው መንገድ ጥሩ ነገር ይመጣልሃል። ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ለአስታያየት:- t.me/ReshadMuzemil ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 YouTube: youtube.com/@SharpSwords1 Instagram: Instagram.com/sharp_swords1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
🔰 የዘራናቸው ዘሮች ⬛️ የዘራሃቸውን ዘሮች ዱካቸው ከጠፋህ ዝናቡ የት እንደዘራህ ይነግርሃል። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ◆ የዘራናቸውን ዘሮች ዱካቸው ከጠፋን ዝናቡ የት እንደዘራን ይነግረናል። ➷➷▮▮ ልክ እንዲሁ መልካምነትን በየትኛውም ምድር፣ ከሰማዩ በታች፣ በምንም አይነት ሁኔታ እና ከማንም ጋር መዝራትን ልማዳችን ልናደርገው  ግድ ይለናል ..... 〽️ ምክንያቱም የዘራነው መልካምነት የት እንደምናገኘው እና መቼ እንደምናገኘው ግራ ቢገባን ዱካው ቢጠፋን ፈጣሪ በፈቀደው ጊዜ ወቅቱ ሲደርስ የዘራነው መልካምነት እራሱ መንገዱን ያቅጣጨናል። ▮ ስለዚህ በሄድንበት ሁሉ መልካም ነገር እንስራ። የልባችንን ህመም ለመገላገል ከፈለግን የግድ በሌሎች እግር ስር የተሰካውን እሾህ መንቀል ይኖርብናል። የመልካምነትን ዘር ባገኘነው ማሳ ላይ እንዝራ መልሶ እኛውኑ ከመጥፎ ነገር ይጠብቀናል። ምላሽ ሳንጠብቅ ሰዎችን ስንደግፍም መጀመሪያ *የምንደገፈው* እኛው ነን! ▮▮እናም ለራሳችን ሀሴትና ተድላ ስንል ሰዎችን እንዲደላደሉ ቆሻሻ ያለበትን መንገድ እንድንጠርግላቸው ይገባናል። በሐዘንም ሆነ በደስታ ጊዜ ከጎናቸው ሆነን ልናበረታቸው «አብሹሩ ከአላህ በታች እኛ ከጎናችሁ ነን» ልንላቸው ይገባናል‼️ ▬▬ይችህ ዛሬ ላይ *በትንሽዬ ማሳ የዘራናት መልካምነት* *የነገ ቀን ዘሩ አድጎና በብዙ እጥፍ በርክቶ ሌላ ዘርን ይተካል*። *ያኔ ከእኛ ጀምሮ ለብዙ ሰዎችም መትረፍ ይችላል*‼️ ስለዚህ ወገኖቼ መልካምነትን ባገኘነው ማሳ ላይ እንዝራ..... *ትንሽ እናንተ* .... *ትንሽ ደግሞ እኛ* ፤ እነዚህ ሁለት ትንንሾች ተደምረው ብዙ ይሆናሉና‼️ በኢብኑ ሙዘሚል Telegram: t.me/SharpSwords1 TikTok: tiktok.com/@sharpswords1
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
አግራሞቴን በብዕር // ከትዝብቴ ማህደር አንዳንዴ እንዲህ ይመስላል ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ሲሉ አብረውን የሚጓዙ! .... ... ጥቅሙን ያጡ ጊዜ ወይም ከእኛ ይፈልጉት የነበረውን ነገር ሲያገኙ የአብሮነታቸውን ገመድ ይቆርጡታል። ተሳክቶላቸው ከሆነ ገመዱን የቆረጡት፤ አልሃምዱሊላህ። የተሳካላቸው መስሏቸው ብቻ ከሆነ ደግሞ፤ አላህ ለነሱ ኸይር (መልካም) የሆነ ስኬትን ያጎናፅፋቸው። ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ummalife.com/ReshadMuzemil
Mostrar todo...
👍 2
አግራሞቴን በብዕር // ከትዝብቴ ማህደር አንዳንዴ እንዲህ ይመስላል ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ሲሉ አብረውን የሚጓዙ! .... ... ጥቅሙን ያጡ ጊዜ ወይም ከእኛ ይፈልጉት የነበረውን ነገር ሲያገኙ የአብሮነታቸውን ገመድ ይቆርጡታል። ተሳክቶላቸው ከሆነ ገመዱን የቆረጡት፤ አልሃምዱሊላህ። የተሳካላቸው መስሏቸው ብቻ ከሆነ ደግሞ፤ አላህ ለነሱ ኸይር (መልካም) የሆነ ስኬትን ያጎናፅፋቸው። ✍️ በረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ummalife.com/ReshadMuzemil
Mostrar todo...
Reshad Muzemil

First name: Reshad Muzemil. Nikname: @ReshadMuzemil | One Ummah — One Network - was created as a response to the Internet technology needs of Muslims and all adherents of traditional value

አግራሞቴን በብዕር ⚔️የመጀመሪያ ህይወት እስትፋሳችን ከተጀመረበት ጀምሮ የመጨረሻ ሞት ከመሞታችን በፊት፤ በዚህ መሃል ጥሩና መጥፎ ለይቶ ማወቅ ነው የሰው ልጅ ህይወት!! እኛ ባደረግነው ጥፋት የተነሳ የኛ ህይወት የፈለገ ነገር ይሁን፤ ግን የሌሎች ህይወት ምንም አይነት ጉዳት ሊገጥመው አይገባም‼️🛤🗝 ✍ ረሻድ ኢብኑ ሙዘሚል ለአስታያየት:- t.me/ReshadMuzemil ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇 share👇 Telegram: t.me/SharpSwords1 Tiktok: tiktok.com/@sharpswords1 YouTube: youtube.com/@SharpSwords1 Instagram: Instagram.com/sharp_swords1 Ummalife: ummalife.com/ReshadMuzemil
Mostrar todo...

Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.