cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

FutureX

The future starts here!

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
8 095
Suscriptores
+3624 horas
+2087 días
+72330 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የማትሪክን ፍርሀት ማሸነፍ! የማትሪክ ፈተና በተለይ ሲደርስ ውስጥህ በጣም ሊፈራ ይችላል፤ አንድ ቀላል መፍትሄ ልንገራችሁ። ለፈተና ዝግጅት የምትችለውን ጥረት ሁሉ ካደረክ "ከፈጣሪ ጋር በደምብ ሰርቼ እወጣለው" ብለህ ጠዋት ስትነሳ፣ ማታ ልትተኛ ስትል እየደጋገምክ ለራስህ ንገረው፣ በወረቀት ፃፈው። አይምሮህ የነገርከውን ስለሚያምን ፍርሀት ይጠፋል፤ በትኩረት ፈተናውን ሰርተህ ትወጣለህ። ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Mostrar todo...
🏆 27🙏 10👍 6👏 5🥰 2
በፈተና ደስ ይበልህ! እውነተኛ ለውጥ በፈተናና በችግር የተሞላ ነው፤ ከንብ ማር መውሰድ የሚፈልግ ሰው ንድፊያዋን መታገስ አለበት።  ወዳጄ ነገሮች ከባድ ሲሆኑ ብታዝን፣ ብታማርር ወይ ራስህን ብትጎዳ ምንም አትፈጥርም! ትዕግስትህን በሚፈትኑ ችግሮች ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም ጠንካሮች ናቸው የሚፈተኑት! ጣፋጭ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Mostrar todo...
👍 57 14🔥 6🕊 2❤‍🔥 1🤯 1
የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ሁልጊዜም ምርጫህ ህይወትህን ይወስነዋል፤ ዛሬ የምትወስነው እያንዳንዱ ውሳኔ ውጤቱን የሚያሳይህ ነገ ነው። ትምህርት የዚህ አለም መጨረሻ አይደለም! ግን ጊዜህን ሰጥተህ እየተማርክ እስከሆነ ድረስ በደምብ ተማር! የምትችለውን ካደረክ ራስህንና የሚወዱህን ማስደሰት ትችላለህ። የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @Futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Mostrar todo...
👍 70👏 10🔥 3🕊 2
የትኛውን ትመርጣለህ? በሰዎች መካከል ትልቁን ልዩነት የሚፈጥረው ለአንድ ተመሳሳይ ነገር የሚመርጡት ምርጫ ነው። ነገን አስበህ አሁን ከለፋህ፤ የፈለከውን ሁሉ ታሳካለህ። አሁን የማይጠቅምህን በማድረግ ጊዜህን ካሳለፍክ ነገ በሌሎች ስኬት ትቀናለህ። ተማሪ ከሆንክ አጥና! ፈተና ከደረሰ ብዙ ጥያቄ ስራ! ራስህን በአይምሮና በስነልቦና ለፈተና አዘጋጀው! ነገ ስታስበው የሚያኮራህን ነገር አሁን ምረጥ። የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 FutureX ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Mostrar todo...
👍 76 14🔥 11
ለፈተና ምን ያህል ተዘጋጀህ? ጊዜያዊ ስሜትህን ተቆጣጠር! አሁኑኑ ልደሰት ማለቱን አቁም! ከጥናት የሚያዘናጉህን ነገሮች እምቢ በል! ሁሉም ከፈተና በኋላ ይደርሳል፤ እንደልብህ ፈታ ትላለህ። አሁን ግን በትኩረት አጥና፣ ብዙ ጥያቄ ስራ። ማትሪክ ማለት ብዙ ጥያቄ የሰራ ተማሪ የሚሰቅለው ፈተና ነው፤ አንተ ምን ያህል እየተዘጋጀህ ነው? የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 FutureX ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Mostrar todo...
103👍 26🔥 9🙏 2
ጥረትን መቀጠል! ራሳችንን ለማሳደግ ከኛ የሚጠበቀውን በየቀኑ በትንሹ እያደረግን ከቀጠልን ሁላችንም ያሰብነው ከፍታ ላይ እንገናኛለን! ትንሽ ጠብታ ልፋት ተጠራቅሞ ተዓምር ይሰራል። እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በሂደት እንጂ በድንገት አይደለም! ስለዚህ ጥረታችንን አናቆምም💪 ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Mostrar todo...
👍 71🥰 11 4🕊 2
ፅናት! "አሁን የምነግራችሁን የስኬት ሚስጥር ምንም ነገር አይተካውም። ጉብዝና አይተካውም! የአይምሮ ብስለት አይተካውም! እድለኛ መሆን አይተካውም! በቃ እሱን የሚተካ የለም....ፅናት ይባላል" ይለናል ካልቪን ኮሊጅ የተባለ የአሜሪካ መሪ። በዚህ ምድር የተነሳ የትኛውንም ስኬታማና ታላቅ ሰው ብትመለከቱ ከየትኛውም ችሎታው ይበልጥ ለአላማው ያለው ፅናት የሚፈልግበት አድርሶታል። ምርጥ ውጤት ለማምጣት በየቀኑ በፅናት መዘጋጀት አለብህ! ማራኪ ምሸት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Mostrar todo...
👍 100 16👏 10
ከባዱ ችግርህ ካንተ በላይ የሆነ ይመስልሀል እንጂ አንተን ማንበርከክ አይችልም! ከሞት በላይ ምን ከባድ ችግር አለ? አትርሳ ወዳጄ እሱ እንኳን ተሸንፏል እኮ! ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ድንቅ የትንሳኤ በዓል ተመኘን🙏 @futureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Mostrar todo...
🥰 65👍 23 11😱 5🤔 3🔥 2
ተዓምር መስራት! ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?! በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው! ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Mostrar todo...
👍 117 22🤝 8🕊 6🥰 4👏 3
ስንፍናን ማሸነፍ! ሮኬት ወደ ህዋ ሲሄድ አብዛኛውን ጉልበት የሚጨርሰው እስኪነሳ ነው፤ የመሬትን ስበት አሸንፎ በሚገርም ፍጥነት ከፍ ማለት ከጀመረ በኋላ ያንን ፍጥነቱን ማስጠበቅ ቀላል ነው። በህይወትም እንዲ ነው ራስህን ለመለወጥ ስትነሳ መጀመሪያ አካባቢ የሚገጥምህን ስንፍና እና መሰልቸት ካሸነፍከው በቃ የምትፈልገውን ነገር ከማግኘት የሚያቆምህ ነገር የለም! ብሩህ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Mostrar todo...
👍 96🙏 11🕊 5 3🔥 2