ቃለ:ጥበብ
Ir al canal en Telegram
329
Suscriptores
-124 horas
+47 días
+2230 días
Archivo de publicaciones
329
በልምላሜ ከበረሀ
እዮዋት ስትጓዝ በበረሀ
ለአለም የሰጠች የማየነጥፍ ውሃ
ሱለማጢስ ነች ደግ እመቤት
የዳዊት ተስፋ የአዳም ሀሴት
ብርሀን ነች ለአለም ፀሀይን ማያ
ከጠላት ቁርሾ ከሰይጣን ወጥመድ ታዛ ማምለጪያ
አረጋዊው ዮሴፍ ትሁቷ ሰሎሜ ደገኛዋ እናት
የአለም ንጉሥ ይዘው ይጓዛሉ በእምነት
ከላይ ፀዐዳ ሰማይ ከታች የጋለ መሬት
እልፍ አእላፍ ወታደር ጦሩን ሰብቆ ሲከተላት
ጫፍ ከሌለው ፍም በረሃ
ያቻትና ዳግሚት ሄዋን ይዛ አምሀ
ደግሞም አላለችም
ፈጣሪ ነህና በደመና እንጓዝ
ሁሉን ቻይ ነህና አቅልልኝ የስቃይ ጓዝ
ውሀ ጥሙ በረታብኝ
ጣፋጭ ውሃን አፍልቅልኝ
ሩህሩህ ናትና ደገኛ ናትና
መከራ ሲመጣ ትለምነዋለች በፍቃዱ ታምና
ከእስያ ስትባረር ሰይጣን ጮሆ ስለፈራ
በኮቲባ ስትሰደብ ያለ ግብሯ
አንኳን በረሃ ላደከመው እንኳን ስቃይ ላቆሰለው
ላልተነካ በሚሰብር ሲያስቀይሟት በቃላቸው
አምርሮ ከማንባት በቀር የለም ክፉ የምትለው
ለአለም ሰጥታ የ'ሷን ፍሬ
ተቀበለች ብዙ ፍዳ እናት ክብሬ
እመቤቴ ሱላማጢስ የአምላክ እናት
እንዴት ያለ ደግነት እንዴት ያለ እናትነት
የማይነጥፍ አቀብሎ ከጎደለ ላይ መጎንጨት
እንዴት ያሉ ትህትና ነው እንዴት ያለ መተናነስ
የማይነጥፍ መብልን ሰጥቶ ከሰዎች ትራፊ መጉረስ
ናትናኤል በላይነህ /ዜራክ
📜🖋🖋🖋፯\፪\፳፻፲፮
329
አሳድጄ አመለጥኳት
አመለጠችኝ ያሳደድኳት
ኗሪ ሆንኩኝ እንደ ፍየል
በነብርና ቅጠል መሀል
አቤት አለች ያልጠራዋት
የጠራሁዋት ድምፅም የላት
ራቂኝ 'ምላት ጎኔ ወድቃ
ቅረቢኝ 'ምላት ከኔ ርቃ
አንዴ ስታደን አንዴም ሳድን
እረፍት አጥቼ ስባክን
የእድሜ ጀንበር ብታዘባት
ልትጠልቅ ምንም አልቀራት
ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ ❤️❤️❤️
329
😣😖
ይብላኝ እንጂ ለኔ
ላውራጁ ኩነኔ
እሷ እንደው እሷ ናት አይገባትም የኔ
ይብላኝ እንጂ ለኔ ውስጣዊ ባዶነት
እሷን የተራበች ልቤን እንዴት ልሙላት
ይብላኝ እንጂ ለኔ ይብላኝ እንጂ ለኔ
ብዬ ዘረዘርኩት የልቤን በወኔ
ታድያ ምን ያረጋል ትካዜ ላይለቀኝ
የማለገኛትን ከሩቅ ሆኜ ብመኝ
ህመሜ አደባባይ በሽታዬ ድብቅ
ስንት አመት አለፈ ይችን ሴት ስጠብቅ
.
😑 .
.
ልቤ አቅም አቶ ድንገት ካለ በቃኝ
ንገሯት አደራ
የኔን አለም ትቼ የሷ እንደናፈቀኝ
ዘርፈሽዋል
329
«ጥላ ዝናብን አያስቆምም፣ ነገር ግን በዝናብ ውስጥ እንድንቆም ያደረገናል። ትዕግስት ፈተናን አያስቀርም ነገር ግን በፈተና ውስጥ የማለፍ ጥንካሬን ይሰጠናል።»
መልካም ቀን 😍
👑👑 . . Join us and share . . 👑👑
▬▬▬▮🌺🌺▮▬▬▬
329
🚫🚫የማይጠየቁ ጥያቄዎች ⁉️❓
🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱🔱
.
⛔️ ሰላማዊ እንቅልፍ ተኝተህ ስምህን አስር ጊዜ ጠርቶ ቀስቅሶህ ልክ ስትነቃ...
"ውይ! ተኝተሀል እንዴ?" የሚል ሰው አያበግናችሁም? ባልተኛ ነው የቀሰቀስከኝ ታድያ❓
.
⛔️ "የማትፈልገው እንትን አለህ?"
(ሲጀመር የማልፈልገው ነገር አይኖረኝም! ከኖረኝ በኋላ እንደማልፈልገው ካወቅሁም እስካሁን እጥለው ነበር)
.
⛔️ ሻወር ቤት ገብተህ አንዱ ያንኳኳና "Friend ጨርሰሻል?" ይልሀል:: (ከጨረስኩ ምን እሰራለሁ?)
.
⛔️ በር ሳንኳኳ ከውስጥ "ማነው?" እያለ ሊከፍት የሚመጣ. ሰው ይገርመኛል!
ሌባ ብሆን "ሌባ ነኝ!" እንድለው ነው? መክፈቱ ካልቀረ ማንስ ብሆን ምን ይጠቅመዋል? "መጣሁ!" ማለት አይሻልም?
.
⛔️ "አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" ብለህ አትጠይቅ! 'አንድ' ካልክ እኮ በቃ "አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" ስትል ጥያቄህን ጨረስካ::
.
⛔️ ቂቅ ብለህ ዘንጠህ መጥተህ "አምሮብኛል አይደል?" ብለህ ከነ መልሱ አትጠይቀኝ:: "አምሮብኛል?" የሚለው ጥያቄ ብቻ ይበቃል:፡ "አይደል?"ን ከጨመርክ እኮ ሼም ይዞኝ "አዎ" እንድል እያስገደድከኝ ነው:: ወይም ደግሞ እንዳማረብህ አውቀሀል ማለት ነው:: ታዲያ ለምን ታደርቀኛለህ ?
.
⛔️ እርቦኝ; ጠምቶኝ; ደክሞኝ ልክ ቤት ስገባ "መጣህ?" አትበሉኝ:: እንግዲህ እኔ እስከማውቀው ድረስ ስለመጣሁ ነው የታየኋችሁ ! ይልቅ የሚበላ የሚጠጣውን አቅርባችሁ ፈውሱኝ::
.
⛔️"ሰዓት ስንት ነው?" ስልህ "አሁን?" አትበለኝ::. ታዲያ መቼ ሊሆን ይችላል? ወይስ አቆጣጠሩን ስለማታውቅበት ጊዜ ለመፍጀት ነው!
.
⛔️ 'Password'ህን ንገረኝ? አይባልም:: ከነገርኩህማ ምኑን password ሆነው ታዲያ?
.
⛔️ ምን ልጋብዝህ? አይባልም:: ግብዣ በጋባዥ እንጂ በተጋባዥ ውሳኔ አይካሄድም! ሼም ይዞኝ የወረደ ነገር እንዳዝ ፈልገህ ካልሆነ በስተቀር!
.
⛔️ ለቅሶ ቤት ሄደህ የአሟሟቱን detail አትጠይቅ! ማስተዛዘን እኮ ሀዘን ማረሳሳት እንጂ ማባባስ አይደለም::.
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
〰〰Join us 〰〰
〰〰〰〰〰〰〰
329
329
ቀንም ጠማማ አለኝ
ያቺ የቀን መሰሪ የቀን መርዶ አብሳሪ
የእለት ጎዶሎ ሀዘን አስነጋሪ
የቀትር አውልያ የሌሊት ተጋሪ
የጠዋት ዱካካም የምሽት ገርጋሪ
የእድል ጠማማ መርገም ያቆሰላት
የተረገመች ቀን ያቺ ሸረኛ እለት
#ዜራክ 26/01/2016🖋🖋🖋
329
♥️እኔና እንቺ❤️🔥
===//===
አንቺ ማለት ጨረቃ:እኔ ማለት ፀሐይ፡
አብረን #የማንወጣ አብረን የማንታይ፡🤦♂
#ሥጠልቂ ምወጣ #ሥወጣ ምጠልቂ፡
ሢከፋሽ ምደሠት #ሣዝን የምትሥቂ፡😃
መቼም #ማንገናኝ አብረን የማንሆን፡😔
እኔና አንቺ ማለት ፍፁም ተቃርኖ ነን💔
(------)
329
በረፋድ ሰአት ላይ ቡና ሁነሽ ምጪ
___
በልቤ ዙፋን ላይ ከተመኘሽ ስልጣን
ከቶ እንዳታስቢ መሆን ጂኒ ሰይጣን
አደረጉ ብለሽ እኩይ እንደረቢ
መስተፋቅር ትብታብ ከቶ እንዳታስቢ
ማህሌት ቋሚ ነኝ በአያቴ ጋቢ
እጣንም እንዳትሆኝ በአፍንጫው በኩል ልግባ ብለሽ ልቤ
ብርጉድ ነው ልማዴ የመቅደሱን ከርቤ
አንዱርስ ብትመስይ ቅፍቋፍ ብትሆኝም
ከማውቀው መአዛ በልጠሽ አትገኝም
ምስልም እንዳትለቂ ሁነሽ ፓሪስ ዱባይ
ቀልብያዬ እንጂ አይመራኝም ነዋይ
በእንቁ እንዳትመሰይ በሶፎር ከርከዴን
ዋጋው አልቦ ተመን አትገዢውም ልቤን
ይቅር ከተመኘሽ አንቺን እንፈቅር
ምስጢሯ አሐቲ እንደ ሶምሶም ፀጉር
በረፋድ ሰአት ላይ ቡና ሁነሽ ምጪ
በልቤ ዙፋን ላይ ያለተቀናቃኝ እንድትቀመጪ
መፅሐፍ :- የርሷ ስም
በዳዊት ጥኡማይ
329
የህይወት ትርጉም ምንድን ነው.?
ክፍል - 1
ስለ ህይወት ብዙ ሰዎች ብዙ ነገሮችን ብለዋል ብዙ ፅሁፎችን ፅፈዋል ብዙ ስልጠናዎች ሰተዋል ነገር ግን እውነታውን ያገኙት ጥቂቶች ናቸው
->ህይወት መወለድ ነው?
-> ወይስ ማደግ ነው?
->ህይወት መማር ነው ?
ወይስ
->ስራ ማግኘትና ባለፀጋ መሆን ነው ?
-> ማግባትና መውለድ ነው ?
ይሄ ሁሉ እውነተኛ የህይወትን ፍቺ አይሰጠንም
በእነዚ ሁሉ ውስጥ የህይወትን እወነተኛ ትርጉም አናገኝም
ነገር ግን ብዙዎቻችን የህይወታችንን ግብ እነዚህን ነገሮቸ አድርገን እየኖርን ነው
ብዙዎቻችን እንማራለን ከዛም በተማርነው የትምሀርት መስክ ስራ እናገኛለን ጥሩ ደሞዝ ተከፋይ እንሆናለን ከዛም ጊዜው ሲደርስ እናገባለን እንወልዳለን እንኖራለን ለልጆቻችንም እኛ የመጣንበትን መንገድ አሲዘናቸው ቀናችን ሲደርስ ይቺን አለም እንሰናበታለን
የተቀረነው ደግሞ በትምህርቱ አለም ማሳካት የልቻልነውን ነገር የንግዱን አለም በመቀላቀል እናሳካዋለን ጥሩ ገቢ እናገኛለን ከዛም ጊዜው ሲደርስ እናገባለን እንወልዳለን ለልጆቻችንም እኛ የመጣንበትን መንገድ አሲዘናቸው ቀናችን ሲደርስ ይቺን አለም እንሰናበታለን
አላስተዋልንም እንጂ እገዚ ነገሮች እውነተኛ የሀይወት ተርጉም እንዳልሆኑ ባደጉት ሀገሮች በደንብ መመልከት እንችላለን
እነAmerica እነ chaina እነ korea እነ Russia እና የመሳስሉት ሀገራት እጅግ ምሁር የሆኑና በትምህርቱ አለም በጣም የመጠቁ በሀብትና በገንዘብ እጅግ የበለፀጉ ናቸው እኛ ልናሳካቸው ምናስባቸውን ነገሮች ሁሉ በሚገባ አሳክተዋቸዋል
ነገር ግን የሚያሳዝነው ይህን ሁሉ ካደረጉ በኃላ ህይወት ተስፋ የላትም በማለት እራሳቸውን ወደ ማጥፋትና የልተገቡ ነገሮችን ወደ ማድረግ ነው የገቡት ይሄ ሀሉ የሆነው ደግሞ እውነተኛውን የህይወትን ተርጉም ባለማግኘታቸው ነው
-->> ታድያ እውነተኛ የህይወት ትርጉም መንድን ነው ?
329
✍አሪፍ ምክሮች
✔️ለብልግና ደፋር አትሁን ☞ሰዎች አንዳትመለስ አድርገው ይተፉሀል ።
✔️ ዝንጉ አትሁን ☞መግባባት አትችልም
✔️ ቸልተኛ አትሁን ☞ቀጠሮና ስራህን ትረሳለህ
✔️ በጣም ኮስታራ አትሁን ☞በሩቅ ይሸሹሀል
✔️ ፈሪ አትሁን ☞ለመሪነት አትበቃም
✔️ ችኩል አትሁን☞ማመዛዘን ይሳንሀል
✔️ ወሬ አታብዛ☞ሚስጥርህን አብረህ ታወጣለህ
✔️ለሁሉም አስተዋይ ☞ሁን ይበጅሀልና።
