es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Ir al canal en Telegram
925
Suscriptores
Sin datos24 horas
+47 días
+930 días
Archivo de publicaciones
ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አንበልታ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በከፊሉ፦

በክልሉ ፈጠራና ፍጥነት በመጨመር የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸም ውጤታማ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሸው ጣሰው (ዶ/ር ) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅዶች አፈጻጸም ግምገማ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሸው ጣሰው (ዶ/ር ) በውይይት መድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት በክልሉ ፈጠራና ፍጥነት በመጨመር የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸም ውጤታማ ነው ብለዋል። መላውን ህብረተሰቡ በማሳተፍ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ ስለመሆናቸው የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ውጤት ያለው ስራ ቆጥሮ በመስጠት እና በመቀበል ረገድ የታየው መነቃቃት አበረታች ነው ብለዋል። የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ስኬታማ እንደነበሩ ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል። በክልሉ ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች ውስጥ ምርታማነትን መጨመር የሚያስችል ጥናት በማካሄድ ለስኬታማነቱ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል። የሌማት ትሩፋት ፣ የግሪን ሌጋሲ እንዲሁም የከተማ ግብርና ልማት ስራዎችን በማጠናከር የኑሮ ውድነት ለማርገብ በልዩ ትኩረት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። በክልሉ ልዩ ትኩረት ከሚሰጣቸው አበይት ጉዳዮች ውስጥ የገቢና የስራ እድል ፈጠራን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የተሟላ ዝግጅት በማድረግ ለውጤታማነቱ መስራት ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል። በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ለ400ሺ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። በክልሉ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት ላይ የአመራሩን የእለት ተዕለት ተግባራት ሊሆን እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። የንግድ ስርዓቱን በማዘመን በዘርፉ ተጠቃሚ መሆን የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባም አሳስበዋል። የሰንበት ገበያ ማስፋፋት ከሚኖረው ጠቀሜታ አንጻር ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል። ኢንቬስትመንትን ለማስፋፋት የተጀመረው ጥረት ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም አመላክተዋል። የገጠር እና የከተማ ኮሪደር ስራ በላቀ ቁርጠኝነት መፈጸም ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል። በክልሉ የተጀመረው የመሰረተ ልማት ስራ ውጤታማ እንዲሆን መትጋት ይገባል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበውን ጥሪ መሰረት በማድ የገጠር ኮሪደር ልማት ስራ ለማስፋፋት አመራሩ ባለሀብቱ እና የአካባቢ ተወላጆችን በማስተባበር መስራት ይገባል ብለዋል። በክልሉ የመንገድ፣የውሃ እና የመብራት መሰረተ ልማት ስራዎችን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ማጠናከር ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል። ጠንካራ ትውልድ ለመፍጠር በትምህርት፣በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ እና መሰል ተቋማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት ተገቢ ነው። በጤና ልማት የመከላከልና የህክምና ስራ ሊተኮርበት ይገባል ያሉት ርዕዕሰ መስተዳድሩ ኮደርስ ፣ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ በትውልድ ግንባታ ላይ ያላቸውን ሚና በመረዳት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል። በክልሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በክረምት ወራት ብቻ ሳይወሰን ከአመት ወደ አመት እንዲሸጋገር መስራት ተገቢ ስለመሆኑም አብራርተዋል። በሰላምና ጸጥታ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝቡ ሙሉ ትኩረትን በልማት ስራ ላይ እንዲያደርግ መስራት ይገባል ብለዋል። ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር እየተካሔደ ያለው ጥረት ስኬታማ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ዜጎችን በዘላቂነት ማቋቋም ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሰባቱም ማዕከላት ተግባራዊ ማድረግ ላይ ትኩረት ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ ጠቁመዋል። በክልሉ የመልካም አስተዳደርን ማስፈን አብይ ጉዳይ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አስረድተዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የገጠር እና የከተማ ኮሪደር፣በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት፣የእርሻ መሳሪያዎች አቅርቦት ላይ ፕሮጀክት በመቅረጽ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ መስራት ይገባል ብለዋል። በክልሉ ወጣቶችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የእርሻ መሳሪያ አቅርቦት ልዩ ትኩረት ያሻል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። በክልሉ ለቀርከሀ ልማት የሚሆን ቦታ በመለየት እና ከዘርፉ የሚገኘውን ሀብት ለማሳደግ መስራት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የካዳስተር ፕሮጀክት በመቅረጽ የገቢ ስርዓትን ማሳደግ ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል። በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች ዋና አስተዳዳሪዎች እና የክልሉ ካቢኔ አባላት ተገኝተዋል ። መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ነው።

ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመስኖ ቅድመ ዝግጅት አሁናዊ ሁኔታ በከፊል፦

‎ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም ‎የህብረተሠቡን የንጹህ መጥ ውሃ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየተደረገ ያለውን ርብርብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ገለጸ። ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎ይህ የተገለጸው የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እና የወረዳው ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት የማኔጅመንት አካላት ከህብረተሰቡ በተሰበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው። ‎ ‎የውይይቱ አላማ ለህዝብ አስተያየት ክብርና ምላሽ በመስጠት መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች በማረም በተቻለ መጠን የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በተገቢው መመለስ ነው። ‎በውይይት ወቅት የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባስ ለሙ ከተለያዩ የህብረተሰቡ ክፍሎች የተሠበሰቡ የህዝብ አስተያየቶች በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ‎ ‎መንግስት የዜጎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ለማረጋገጥ የመንግስት አቅም በመጠቀም፣ ተወላጅ ባለሀብቶችን እና ረጅ-ድርጅቶች በማስተባበር እያከናወናቸው ባሉ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገ ይገኛል። ‎ከተከናወኑ አንኳር ስራዎች መካከልም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከፍተኛ በጀት በመመደብ የመሀል አምብ ከተማና በዙሪያዉ ያሉ ቀበሌ ነዋሪዎችን የንጹህ መጥ ውሃ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ሁሉም ተጠናቆ ቀሪ  የ3 ትራንስፎርመር ግዥና ዝርጋታዎች  ከተከናወኑ በቅርቡ  ለአገልግሎት የሚበቃበት ሂደት ላይ መገኘቱ፣ የኮምበል ከተማ ህዝብን የውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የክልሉ ዋን ዋሽ ፕሮግራም አለልቱ ላይ 27 ሊትር ፐር ሰከንድ የማመንጨት አቅም ያለው ጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራ መከናወኑ በአውንታ ቢወሰድም ቀሪ ስራዎችን ለመስራት ከማ/ሰቡ ጋር በመወያየት መፍትሔ አንደሚያስፈልግ ተነስተዋል። ‎ ‎በአንፃሩ በውይይቱ ከህብረተሰቡ የተሠበሠቡ አስተያየቶች መካከል የመሀል አምባ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ችግር፣ በተለያዩ ቀበሌዎች የውሃ ቦኖዎች ብልሽት፣ ገሬኖ ቀበሌ ቦልጫመኝ ውሃ በተደጋጋሚ የጄኔሬተር ብልሽት ምክኒያት አገልግሎት መስጠት አለመቻሉ፣ የከንትዋት ቀበሌ የንጹህ መጥ ውሃ ስራው የተጠናቀቀ ቢሆንም ህብረተሰቡ ውሃ መጠጣት አለመቻሉ፣በወረዳችን በአብዛኛው ቀበሌዎች የውሃ ተጠቃሚ አለመሆናቸው፣ ጅማ ከተማ የንጹህ መጥ ውሃ ጥያቄ ለመፍታት የማብራት ዝርጋታው ቢያልቅም ቀሪ ስራ መኖሩ፣ የኮምበል ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ሙሉ በሙሉ ያለመፍታት፣የጊጬ ዲምቱ መጠጥ ውሃ መቋረጥ እንዲሁም በዞን እና በክልል የሚገነቡ የአረዳ እና ሠፍቶ ቀርሳ ቀበሌዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ያለመጀመራቸው ተጀምረው ያልተጠናቁ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ችግሮቻቸው ተለይተው እልባት ሊሰጥባቸው እንደሚገባ በአሉታ የተነሱ ሲሆን ጥልቀት ያለው ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል። ‎ ‎የወረዳዉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ አ/ጀሊል ቱሉ የቀረበውን የህዝብ አስተያየት ትክክለኛና ተገቢ መሆኑን ጠቅሠው በተቋም ደረጃ የተሠጡንን አስተያየቶች በመውሠድ በዘንድሮ አመት ምላሽ ለመስጠት በሚቻልባቸው ጉዳዮች በቁርጠኝነት እንዲሚሠሩ ጠቅሠው ከተቋሙ አቅም በላይ የሆኑ ፕሮጀክቶች የወረዳው መንግስት፣ተወላጅ ባለሃብቶችና ረጂ ድርጅቶችን እንዲሁም ህብረተሠቡን በተገቢው በማሳተፈ በወረዳው የሚገኙ ጥልቅ ጉድጓዶች በነዳጅ ዋጋና በጄኔሬተር ብልሽት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈጠረ በመሆኑ ወደ ሶላር ወይም ማብራት እንዲቀየር አቅዶ መስራት ያስፈልጋል ያሉት አቶ አ/ጀሊል ለተግባሩ መሳካት ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ከሁሉም ባለድርሻ አካላት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል። ‎ ‎በውይይት መድረኩ ላይ ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል። ‎ዘገባው የወረዳው መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

እንኳን ደስ አላችሁ ‎የጉራጌ ዞን ትራንስፖርት መንገድ መምሪያ ባካሄደው 2017 ዓ.ም የተግባር አፈፃፀም ሴክቶሪያል ጉባኤ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ኣ ወረዳ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ጽ/ቤት በአጠቃላይ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የዋንጫና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በተጨማሪም አቶ ሁሴን አህመድ በወረዳው ፍቴ ቀበሌ 6 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ በመስራት ተሸላሚ መሆን ችለዋል። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ

በገዳባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሶዶ አይብገረን ቀበሌ እየለማ የሚገኝ የጤፍ ማሳ አሁናዊ ቁመና በምስል፦

ፋኦ ለኢትዮጵያ "ዘላቂ የደን ልማት አያያዝና አጠቃቀም" በሚል ዘርፍ እውቅና ሰጠ ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ለኢትዮጵያ "ዘላቂ የደን ልማት አያያዝና አጠቃቀም" በሚል ዘርፍ እውቅና ሰጠ። በተባበሩት መንግሥታት ስር የሚገኘውና መቀመጫውን ጣሊያን ሮም ያደረገው ፋኦ ለኢትዮጵያ የሰጠውን የእውቅና ሽልማት ኢትዮጵያን ወክለው የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተቀብለዋል። ‎ ፋኦ ከዚህ ቀደም ‎በምግብ ዋስትና፣ በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦትና በስንዴ ምርት ፈጣን አፈጻጸም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ላሳዩት ቁርጠኝነት ‎የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳሊያ መሸለሙ ይታወሳል። ኤፍ ኤም ሲ

ጥቅምት 05/2018 ዓ.ም ከተሞችን በሚፈለገዉ ደረጃ በማልማት ለነዋሪዎች ምቹና ማራኪ ለማድረግ የሚደረገውን ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ጽህፈት ቤቱ ይህንን ያለው ዓመታዊ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት ባካሄደበት ወቅት ነው። የወረዳዉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተማም አደም የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸው እንዳሉት ጽ/ቤቱ በሃገር ዓቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ድርሻው የላቀ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህንን የተጣለበት ራዕይ ለማሳካት የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ ነድፎ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። በ2017 ዓ/ም ዘርፈ- ብዙ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ያከናወነ ሲሆን በተዋረድ ያሉ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር በመናድ መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በማድረግ የተገኙ ውጤቶችና የተጀመረውን ህዝባዊ ትግል አቀጣጥሎ በማስቀጠል ተፈላጊውን ዉጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል። የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው መንግስት ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ አጽንኦት ሰጥቶ እየሰራ ባለው ዘርፈ-ብዙ ስራ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገብ መቻላቸውን ጠቅሰዋል። መንግስት የከተሞች ሁለንተናዊ ልማትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በልዩነት እየሰራ እንደሚገኝ ያወሱት ዋና አስተዳዳሪው የከተሞች ደረጃ ሽግግር ላይ ይሰራልም ብለዋል። በመድረኩ የጽ/ቤቱ ባለሙያ አቶ መቻል ደገፋ የ2017 ዓ/ም ዕቅድ አፈፃፀም እና የፅህፈት ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ሚፍታ ደሬሳ የ2018 ዓ/ም ዕቅድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል። ከተሳታፊዎች ከተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች መካከል ኢንቨስትመንት ከማልማት ረገድ ያለው ጉድለት ተወስዶ ሊታረም እንደሚገባው፣ የመሀል አምባ ከተማ ከፈርጅ 4 ወደ ፈርጅ 3 ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል ያሉት ተሳታፊዎቹ እየተከናወኑ ያሉ ካፒታል ፕሮጀክቶች ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። በመድረኩ ማጠቃለያ ወቅት የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ከተሞችን በሚፈለገው ደረጃ በማልማት ለነዋሪዎች ምቹና ማራኪ ለማድረግ የሚደረገውን ርብርብ በየደረጃዉ የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። አያይዘውም በመመሪያው መሰረት ነባር እና አዲስ ኢንቨስትመንቶች መልማት ይኖርብቸዋል ያሉት አቶ ሚፍታ ሁሴን መላው ህብረተሰቡን በማስተባበር በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል። መንግስት እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍና  ክትትል የሚቀጥል ስለመሆኑም አብራርተዋል። የስኬች ፕላን ከተሞችን በስኬች ፕላን አተገባበር መሰረት በትኩረት መሰራት እንዳለበት ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው የስኬች ፕላን ከተሞች ወደ ማዘጋጃ ቤት ሽግግር ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰው የመላው ህብረተሰብና ባለድርሻዎች ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተማም አደም የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ አጽንኦት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ገልጸዋል። አክለውም የማዘጋጃ ቤቶች የፈርጅ ሽግግር ማለትም ከደረጃ 5 ወደ ደረጃ 4 እና ከደረጃ 4 ወደ ደረጃ 3 ሽግግር ላይ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። የከተሞችን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ የተጀመረውን ልማት ማቀጣጠል እንደሚገባ በማንሳት ካፒታል ፕሮጀክቶች የዲዛይንና ጥራት ቁጥጥር ስራ አጽንኦት ተሰጥቶት ይሰራልሜ ብለዋል። በመጨረሻም የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ዕቅድ ታቅዶ እየተሰራ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የዲጂታል ስርዓት አስጀመረ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቋማዊ አሰራሩን በማዘመን ወቅቱን የጠበቀና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የዲጂታል ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ፡፡ ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ያበለጸገውን ዲጂታል የሰነድና ማህደር አስተዳደርና ወረቀት አልባ የአሰራር ስርዓትን ዛሬ ይፋ አድርጓል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ ሚኒስቴሩ የተቋማዊ ሪፎርም አካል የሆነ የዲጂታል አሰራር ትግበራ መጀመሩን ገልጸው÷ ለዚህም ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ዲጂታል ስርዓት ማልማቱን ተናግረዋል፡፡ የሰነድና ማህደር አስተዳደር ስርዓቱ በሚኒስቴሩ ከመዝገብ አያያዝ እስከ ሚሲዮኖች የመረጃ ለውውጥ ድረስ የነበረውን የወረቀት አሰራር በማስቀረት ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት ስርዓት መፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡ ወቅቱን የዋጀ ስርዓት ዘመናዊ የሰነድ አያያዝ ሥርዓቱ ከመፍጠር ባለፈ ጊዜንና ወጪን እንደሚቆጥብ ጠቁመዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወሻዎች፣ ጥናቶችና ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸው ትልልቅ ሰነዶች የመነጩበት ተቋም መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ የሶፍትዌር ስርዓቱ የተቋሙን ተሞክሮዎችና ታሪኮች በዘመናዊ መንገድ ለመሰነድ የጎላ አበርክቶ እንዳለው አንስተዋል፡፡ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት ልምድና አገልግሎት ለዲፕሎማቶች ለማሸጋገር የማይተካ ሚና እንዳለውም መግለፃቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡ ሚኒስቴሩ በዲጂታል የሰነድ አስተዳደር፣ በውስጥና በውጪ ግንኙነት እና በደብዳቤ ልውውጥ እንዲሁም በተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የጋራ አቅም ለመፍጠር ያለመ የወረቀት አልባ ስማርት አሰራርና የዲጂታል የሰነድ ልውውጥና አያያዝ ስርዓት ላይ ያተኮረ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።(ኤፍ.ኤም.ሲ)