cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

THIQAH

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
11 689
Suscriptores
+224 horas
+2867 días
+24630 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሁቲ የአሜሪካን አውሮፕላን መትቶ መጣሉን አስታወቀ፡፡ አሜሪካና እንግሊዝ ከጥቃቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባደረሱት የአየር ላይ ጥቃት 16 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። የአጸፋ ምላሽ የሰጠው በኢራን ይደገፋል የሚባለው የየመን ታጣቂ ቡድን ሁቲ፤ በአሜሪካ አውሮፕላኖች ላይ በሚሳዔል የታገዘ ጥቃተ ፈጽሚያለሁ ብሏል፡፡ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን በጉዳዩ ላይ በሰጡት ሀሳብ፣ አሜሪካና እንግሊዝ በወሰዱት እርምጃ የሁቲን የመሬት የሚሳዔል መተኮሻዎች፣ ማዘዣ ስፍራዎችና ሌሎች ቁሳቁሶችን አውድመናል ብለዋል፡፡ #TimesOfIsrael @ThiqahEth
Mostrar todo...
🔥 15👍 5 4😁 1
Photo unavailableShow in Telegram
ስሎቫኒያ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅናን ሰጠች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ጎሎብ ፍልስጤም ራሷን የቻለች ግዛት ሆና እውቅና ሊሰጣት እንደሚገባ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡ ስሎቫኒያ የስፔን፣ አየርላንድና ኖርዌን ፈለግ መከተሏ፣ ፓርላማው ግን ገና እንዳላጸደቀው ተገልጿል። ጎሎብ በእስራኤልና ሀማስ መካከል ያለው ግጭት ቁሞ ታጋቾች እንድለቀቁም ጠይቀዋል፡፡ #MiddleEastMonitor @ThiqahEth
Mostrar todo...
👍 38🥰 7😁 4
Photo unavailableShow in Telegram
ተ.መ.ድ በደቡብ ሱዳን ላይ የጣለውን ማዕቀብ አራዘመ። በፈረንጆቹ 2018 የተጣለው ማዕቀቡ የንብረት፣ የጦር መሳሪያ፣ የጉዞ እገዳዎችን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል። የፀጥታው ምክር ቤት ይህ በደቡብ ሱዳን ተጥሎ የቆየው ማዕቀብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት እስከ 2025 ድረስ እንድቆይ ወስኗል። ውሳኔውን ዘጠኝ ሀገራት የደገፉት ሲሆን፣ ስድስት የሚሆኑት ሀገራት ደግሞ ድምፅ ተዓቅቦ አድርገዋል።#AnadaoluAgency @thiqaheth
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
የደቡብ አፍሪካ ገዢ ፓርቲ አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ (ኤኤንሲ) ከ30 ዓመታት በኋላ በፓርላማው የነበረውን አብላጫ ድምፅ ሊያጣ መሆኑ ተገለጸ። ሐሙስ ዕለት የደቡብ አፍሪካ ምርጫ ገሚስ ውጤት ይፋ የሆነ ሲሆን ገዢው ፓርቲ አብላጫ ድምፁን እያጣ እንደሆነ ውጤቶቹ አመላክተዋል። ከምራጭ ቀጣናዎች 50 በመቶው ድምፅ የተቆጠረ ሲሆን ኤኤንሲ በ42 በመቶ ሲመራ ዲሞክራቲክ አላያንስ (ዲኤ) በ23 በመቶ ይከተላል። የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ጃኮብ ዙማ ፓርቲ የሆነው ኤምኬ 11 በመቶ ሲያገኝ፤ ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ አሊያም ኢኤፍኤፍ እስካሁን ባለው ቆጠራ 10 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል። የምርጫው አጠቃላይ ውጤት ቅዳሜና እሑድ ሊገለጥ እንደሚችል ተነግሯል። በርካታ መራጮች ኤኤንሲ ፦ ➡️ በሙስና ተዘፍቋል፣ ➡️ ወንጀል እንዲሰፋፋ አድርጓል ➡️ በሀገሪቱ ላለው ሥራ-አጥነት ተጠያቂ ነው ሲሉ ይወቅሱታል። ላለፉት 30 ዓመታት ደቡብ አፍሪካን በበላይነት ያስተዳደረው ኤኤንሲ በአውሮፓውያኑ 2019 በተደረገው ምርጫ ያገኘው ድምፅ 57 በመቶ ነበር። ነገር ግን በዘንድሮው ምርጫ ከ42 በመቶ ብዙም ያልዘለለ ድምፅ እንደሚያገኝ ተገምቷል። ይህ ማለት ኤኤንሲ ከአንድ ፓርቲ አሊያም ተጨማሪ ፓርቲ ጋር ተጣምሮ ቅንጅት በመመሥረት የፓርላማውን አብላጫ ወንበር መያዝ አለበት ማለት ነው። #ቢቢሲ @thiqahEth
Mostrar todo...
👍 10 2😱 1
Photo unavailableShow in Telegram
ፕሬዝዳንት ዥ በእስራዔልና ፍልስጤም መካከል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሁለት ሀገርነት መፍትሄን መተግበር ያስፈልጋል አሉ፡፡ የቻይናው ፕሬዝዳንት ዥ ጀፒንግ ሀገራቸው በእስራዔልና ፍልስጤም መካከል ያለውን አለመግባባት ለመቅረፍ ሁነኛው መንገድ የሁለት ሀገርነት መፍትሄን ትደግፋለች ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በ10ኛው የቻይና-አረብ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ “ጦርነት መቀጠል፤ ፍትህ መጓዴል የለበትም“ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ዥ በጋዛ ያለው ጦርነት እንዲቆም መጠየቃቸውን፣ ከጦርነቱ በኋላ ስለሚኖረው የመልሶ ግንባታ ሂደት ላይ መተባበር ይገባል ማለታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ @ThiqahEth
Mostrar todo...
🥰 31👍 16😁 5🙏 4🤔 2
Photo unavailableShow in Telegram
እስራዔል ጋዛን ከግብጽ የሚያዋስናትን “ቁልፍ ድንበር“ ተቆጣጥሪያለሁ አለች፡፡ በድንበሩ ኮሪደር አካባቢ ሃማስ የሚጠቀምባቸው የጦር መሳሪያዎችንና ቁሳቁሶችን ማገኘቷን አስታውቃለች፡፡ እስራዔል ይህን የፊላደልፊ ስትራቴጅክ ቦታ መቆጣጠር የሃማስ ሚሊሻ ቡድንን ለማጥፋት ያግዘኛል ማለቷ ተነግሯል። ግብጽ በበኩሏ፣ "እስራዔል የፊላደልፊን ኮሪደር መቆጣጠር የለባትም፤ ለቃ መውጣት ይኖርባታል" በሚል ከእስራዔል ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብታለች፡፡ #Scrippsnews @thiqaheth
Mostrar todo...
21👍 15😡 9
በህንድና ባንግላዴሽ በአውሎ ነፋስ አደጋ የ55 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ ከሳምንት ጀምሮ ባጋጠመው አደጋ ከህንድ 40፣ ከባንግላድሽ ደግሞ 15 ሰዎች እንደሞቱ፣ የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት አስታውቀዋል። የአውሎ ነፋስ አደጋው ዛፎችና ቤቱችን በእጅጉ ጎድቷል። ባለስልጣናቱ የተከሰተው ከባድ ዝናብና ወጀብ አሁን ድረስ አለመብረዱን ተናግረዋል፡፡ #YeniSafak @ThiqahEth
Mostrar todo...
😭 19👍 3 2😢 2
በፓኪስታን የአውቶብስ አደጋ ሳቢያ 28 ሰዎች ሞቱ፡፡ ከቱርባት ወደ ኩዌታ ከተማ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ ሸለቆ ውስጥ ገብቷል፡፡ አውቶብሱ 54 ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበር፣ አደጋው በተከሰተበት ወቅት በስፍራው የተገኙት የጤና ባለሙያ ኖሩላህ እሳዛይ ተናግረዋል፡፡ አስር ሰዎች በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ መሆናቸውንም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡ #Aljazeera @thiqaheth
Mostrar todo...
😭 19👍 7😢 5
ስፔን ለፍልስጤም በይፋ የሀገርነት እውቅና ሰጠች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ "እስራዔል በፍልስጤም መካከል ሰላም እንዲሰፍን በመጣር ነጠላ ግብ ያሳካ ታሪካዋዊ ውሳኔ ነው" ብለዋል፡፡ ሳንቼዝ በ1967 በነበረው የድንበር ወሰን ጋዛና ዌስት ባንክ አንድ ላይ መሆን እንዳለባቸውና ዋና ከተማዋ ምሥራቅ እየሩሳሌም መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ አውሮፓዊቷ ሀገር ስፔን ባሳለፍነው ሳምንት ከኖርዌና አየርላንድ ጋር በመሆን ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና መስጠታቸውን አስታውቀው ነበር፡፡ #Aljazeera @ThiaqhEth
Mostrar todo...
👍 105 12👌 8🥰 3🙏 3😁 2🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ኒታንያሁ የጦር ካቢኒያቸውን ለመበተን እያሰቡ ነው ተባለ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደዚህ ውሳኔ ሊገቡ የተገደዱት የጦር ካቢኔው አባል የሆኑት ቤኒ ጋንትዝ እንደሚለቁ ካስጠነቀቁ በኋላ መሆኑ ተሰምቷል። ኒታንያ አሁን ያለውን የጦር ካቢኔ በትነው በሚወጡት ሰዎች ምትክ ለማስገባት አቅደዋል ተብሏል፡፡ ካቢኔው እስራዔል በጋዛ ፈጽማዋለች ለተባለው ግፍ ኃላፊነቱን ይወስዳል በሚል በተደጋጋሚ ወቀሳ ቀርቦበታል፡፡ #MehrNews @thiqaheth
Mostrar todo...
👍 16😁 3