cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አዲስ መረጃ ሰበር ዜና Addis Mereja

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
3 331
Suscriptores
-424 horas
+3057 días
+1 49230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በ #አማራ ክልል የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ወደ 2.5 ሚሊዮን ማሻቀቡ ተገለፀ‼️ በአማራ ክልል በድርቅና በተለያዩ የፀጥታ ችግሮች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 2 ሚሊዮን 500 ሺህ ማደጉን የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ። መንግስት ለእነዚህ ወገኖች በየወሩ 2 ቢሊዮን 2 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግም ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ኮሚሽን፣ ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል እንደሚሉት የአማራ ክልል በ2016 ዓ.ም  ሦስት ዋና ዋና ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ “... አንደኛው በክልሉ ያለው ግጭት ነው፣ የሰዎችን እንቅስቃሴ በመገደቡ ምክንት ግብዓትና የምግብ እህል በወቅቱ እየቀረበ አይደለም፣ የቀን ሰራተኛው ሰርቶ እየበላ አይደለም፣ አርሶ አደሩ የምርት ስራውን በተሟላ መንገድ እየሰራ አይደለም፣” ብለዋል፡፡ ሁለተኛው እንደችግር የሚወሰደው ደግሞ እንደ ኮሚሽነሩ፣ የዝናብ እጥረቱን ተከትሎ በክልሉ ያጋጠመው ድርቅ ነው፡፡ “ ሶስተኛው እንደ ችግር የሚወሰደው በተለያዩ አካባቢዎች በተነሱ ግጭቶች ክልሉ በርካታ በርካታ ተፈናቃዮችን መቀበሉ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ በዚህ ዓመት በአማራ ክልል የተከሰተው ድርቅ ሰፊ ቦታ የሸፈነ ሲሆን 1 ሚሊዮን 850 ሺህ ያህል ወገኖችን የእርዳታ እህል ጠባቂ አድርጓቸዋል ብለዋል ኮሚሽነር ተስፋው፡፡ ኮሚሽነር ተስፋው ትናንት በሰጡት መግለጫ በዚህ ዓመት የተከሰተው ድርቅ በአማራ ክልል በዘጠን ዞኖች፣በ43 ወረዳዎች፣ በ429 ቀበሌዎች የሚኖሩ አንድ ሚሊዮን 846 ሺህ 955 ሰዎች የድርቁ ቀጥተኛ ተጠቂ ሆነዋል ማለታቸውን ዶቸ ቨለ ዘግቧል፡፡ Join👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial
Mostrar todo...
👍 5 1😱 1😢 1
የትግራይ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ‼️ ለሶስት አመታት ከስራ ውጪ ተንሳፈው የቆዩት የትግራይ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ መወሰኑ ተሰምቷል። 👉"ፈጣን እና እውነተኛ ሀገራዊ መረጃ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"👇👇👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial
Mostrar todo...
👍 3🤯 2😢 1
#Raya እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ሪፖርት መሰረት ከራያ አላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በልጧል። 42 ሺህ ዜጎች ቆቦ ፤ 8,300 ሰዎች ሰቆጣ ይገኛሉ። የተፈናቀሉት ከራያ አላማጣ፣ ዛታ፣ ኦፍላ ነው። አብዛኞቹ ህጻናት ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ናቸው። #UNOCHA @tikvahethiopia
Mostrar todo...
👍 5 5🔥 3
#Update‼️ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ተረፍ በሚባል ቦታ እንዲሁም በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ መስኖ በሚባለው ቀበሌ ትናንት ጠዋት ጀምሮ የነበረው ውጊያ ትናንት ማታ ጀምሮ መቆሙን የአካባቢው ነዋሪዎቹ ገልፀውልኛል። ትናንት በነበረው ውጊያ ሰብዓዊ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በተለይ የሚሊሻ አባላት በብዛት ተጎድተዋል ብለዋል። መከላከያ ሰራዊት ወደ መኮይ ከተማ ገብቷል ብለዋል። ዛሬ ተኩሱ በአንፃራዊነት ጋብ ብሏል ብለዋል። መኮይ ስምንት ሰዎች በውጊያው ሞተዋል ብለዋል። 👇 👉የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ??👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial
Mostrar todo...
👍 9🔥 1
ራያ‼️ የህወሓት ታጣቂዎች ከፍተኛ ዝርፊያ ፈፀሙ‼️ በርካታ ዝርፊያ ከፈፀሙ በኋላ የተወሰነ ወደ ኋላ አፈግፍገዋል:-የአይን እማኝ❗ የህወሃት ታጣቂዎች በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በአላማጣ ከተማ ዙሪያ በሚገኙ ቀበሌዎች በአየር ማረፊያ ፣ቓጅማ ፣ ጋንዳጋሮ ፣ህብረት ፣ ባላ ፣ፋጫ ከፍተኛ በተባሉ ቀበሌዎች በ10 ሺህ የሚቆጠሩ በሬ፣ላም፣ ፍየል በግ፣አሃያና ግመል ነድተው ወስደዋል ሲል አንድ የአይን እማኝ ለአዩዘሀበሻ ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ በየሰው ቤት በመግባት እህል፣ ወርቅ፣ስልክ፣ገንዘብ ..ወዘተ ዘርፈው የተወሰነ ወደ ኋላ ተመልሰዋል። ከዚህ በተጨማሪ የገበሬ እርሻ በቆሎ እና ቲማቲም የበሉትን በልተው ቀሪውን አውድመውት ሄደዋል ብለዋል። ትናንት ሲቪል ልብስ በመልበስ 5 እና 6 እየሆኑ ወደ አላማጣ ከተማ የገቡ ታጣቂዎች ስለመኖራቸው የመረጃ ምንጮቹ ገልፀውልኛል[አዩዘሀበሻ]። ፎቶ:-ከፋይል 👇 👉የቴሌግራም ቻናሉን join አድርጉ፣ለሌሎች ጋብዙ??👇 http://t.me/ayuzehabeshaofficial http://t.me/ayuzehabeshaofficial
Mostrar todo...
👍 4 1
በአዲስ አበባ ከተማ ጫት በማስቃም እና ሺሻ በማስጨስ ቦሌ እና ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች  ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ ተነገረ‼️ በአዲስ አበባ ባሉ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  አዋኪ ድርጊት ያላቸውን  ጫት ማስቀም  ፣ ሺሻ ማስጨስን ጨምሮ ተመሳሳይ ድርጊትን  በሚፈጽሙ አካላት ላይ   ከፍተኛ  ቁጥጥር  እያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል። በ2016 በጀት ዓመት ባለፈው ዘጠኝ ወራት ውስጥ 6 ሺ 9 መቶ 22 ቤቶች ተቋሙ አዋኪ ሲል የሚጠራቸውን ትምህርት ቤት አካባቢ ቁማር ማጫወት እንዲሁም በየትኛውን ሰፈር እና ቦታ ላይ ሺሻ ማስጨስ ላይ የነበሩ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ተናግረዋል። ወላጆችም በተደጋጋሚ በሚያቀርቡት ቅሬታ እንዲሁም በተደረገው የቁጥጥር ስራ  በተለይም  ትምህርት ቤቶች አካባቢ የነበረው   የቁማር እንዲሁም የጫት ማስቃም  ተግባር  እየቀነሰ መምጣቱም ተጠቁሟል። ይሁን እና አሁንም በድብቅ በህገወጥ መልኩ  የሚሰሩ መኖራቸውንም አክለዋል። በ2016 በጀት ዓመት በተደረው የቁጥጥር  ስራ ላይ በሁሉም ክፍለ ከተማዎች ላይ እርምጃ የተወሰደ ቢሆንም በቦሌ እና ቂርቆስ እንዲሁም  በተወሰነ መልኩ አራዳ ክፍለ ከተሞች ጫት በማስቃም እና ሺሻ በማስጨስ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙ መሆናቸውንም አቶ የምስራች ግርማ  ጨምረው ተናግረዋል።
Mostrar todo...
👍 5 1😁 1
በመዲናዋ ደንብ በመተላለፍ ከተቀጡ ሰዎች 27 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ‼️ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከ27 ሚሊየን ብር ከቅጣት መሰብሰቡን አስታወቀ‼️ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 27 ሚሊየን 194 ሺህ 567 ብር ከቅጣት ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። ገቢው በዘጠኝ ወራት ውስጥ በከተማዋ ከተፈጸሙ የተለያዩ የደንብ ጥሰቶች የተሰበሰበ ነው ተብሏል። በዚህ ጊዜ ውስጥ በድምሩ ከ34 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ያገኘ ሲሆን፥ በ7 ሚሊየን 228 ሺህ 686 ብር ደግሞ የመንግስት ግዢ መፈጸሙን አስታውቋል። ባለስልጣኑ ህገወጥ ግንባታ፣ ህገወጥ የመሬት መስፋፋት፣ ህገ ወጥ እንስሳት ዝውውርና እርድ እንዲሁም አዋኪ ድርጊቶች ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አመላክቷል።
Mostrar todo...
“#የፕሪቶርያው ስምምነት ትግበራ በየደረጃው ድርድር የሚያስፈልገው ነው እንጂ አልጋ ባልጋ የሆነ አይደለም” - ጀነራል ታደሰ ወረደ‼️ 👉በደቡብ ትግራይ ተኩስ ያደረጉት የተፈናቀሉ ታጣቂዎቻችን ናቸው። #የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ትላንት ሚያዚያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት ሁሉንም ችግሮች የሚፈታ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። የፕሪቶርያው ስምምነት ትግበራ በየደረጃው ድርድር የሚያስፈልገው ነው እንጂ ልሙጥ የሆነ አይደለም ሲሉ በአተገባበሩ ዙሪያ ስለሚታዩ ችግሮች አብራርተዋል። ከስምምነቱ አበይት ነጥቦች መካከል በሀይል ተይዘው በሚገኙ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ጉዳዮች ናቸው ሲሉ ያብራሩት ጀነራል ታደሰ በስምምነቱ የተፈራረምነው በህገመንግስቱ መሰረት ይፈታል የሚል ነው፤ እስካሁን ተነክቶ የማያውቀው የስምምነት ክፍል እሱ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ደቡብ ትግራይ ጋር በተያያዘ ሁኔታው መለወጥ እንዳለበት ብናምንም በሀይል ልናደርገው አንፈልግም፣ ለምሳሌ ኮረም አከባቢ የተወሰኑ የፖሊስ ሀይሎች ብቻ እንዳሉ እናውቃለን፤ እዚያ አከባቢ ያለውን የመከላከያም ይሁን የፌደራል ፖሊስ በሀይል የማስለቀቅ ተልእኮ የተሰጠው ሀይል የለንም ሲሉ አብራርተዋል። በርተክላይ፣ ጨርጨርም ይሁን ቺኮማጆ የተቀመጠ ሀይል አለን ሲሉ የጠቆሙት ጀነራል ታደሰ ነገር ግን በዘላቂነት መፍትሔ እንዲያገኝ ነው የምንፈልገው፤ ይህን ከግምት ውስጥ አስገብተን ነው የምንቀሳቀሰው፣ ከፌደራል መንግስቱ ጋር በተስማማንበት መልኩ ነው መሄድ የምንፈልገው ብለዋል።
Mostrar todo...
👍 1
ህወሃት "ከደቡብ ትግራይ ዞን የተፈናቀሉ ተፈናቃዮች የፕሪቶሪያ ስምምነት ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ዛሬ በኩኩፍቱ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ" ሲል ዘግቧል። 👉ሰልፉን ያደረጉት ከሌላ አካባቢ የመጡ ሰዎች ናቸው:-ነዋሪዎቹ ይህን መረጃ መሰረት በማድረግ አዩዘሀበሻ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉት ሰዎች ከተለያዩ ቦታዎች የተውጣጡ ታጣቂዎች እንጂ ተፈናቃዮች አይደሉም ሲሉ ይገልፃሉ። ይህን ሰልፍ ያካሄዱት ከመሆኒ ፣ ማይጨው ፣ ሌሎች የትግራይ አከባቢዎችና ኩክፍቶ አከባቢ ያሉ የወያኔ ወታደሮች ናቸው በስመ ተፈናቃይ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉት ብለዋል። ከትናንት ጀምሮ ኩኩፍቱ ላይ ማንም ሰው እንዳይቀር ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ቢታዘዙም ሰልፍ ላይ የተገኘ ሰው ባለመኖሩ ከ10 በላይ fsr ከማይጨው እና መሆኒ አካባቢዎች ተጭነው መጥተው ነው ሰልፍ ያደረጉት ብለዋል። የማንነት ጥያቄ ያለባቸው የአላማጣ፣የራያ አዘቦ እና ሌሎች የራያ ወረዳዎች ማንነታችን ይከበር፣የህወሓትን ትንኮሳ መንግሥት ያስቁምልን በሚል ባሳላፍነው ሳምንት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።
Mostrar todo...
👍 1