ቢንት ኢብራሂም
"ወደ አሏህ የሚወስደው መንገድ ረጅም ነው።እኛ በእሱ ላይ እንደ ኤሊ እየተጓዝን ነው።አላማችን መንገዱን መጨረስ አይደለም።ይልቁንም መንገዱ ላይ ሁነን መሞት ነው።" ሸይኹል አልባኒ ረሂመሁሏህ
Mostrar más- Suscriptores
- Cobertura postal
- ER - ratio de compromiso
Carga de datos en curso...
Carga de datos en curso...
ይህንን ተላበስ ዛሬ ከሆንክ ወጣት
===///====///====///==///===>
ሌት ቀን የሚለፋ የተውሂዱ ጀግና
የማይደራደር በተውሂድ በሱና
በምንም አማራጭ የማይሰጥ ዋስትና
ለተውሂድ ይለፋል ብዙ ይሰራል ገና
እንመልከት እንጂ ቆይተን በደህና
===///====///====///==///===>
ለቢድዓ ኮተት አይንበረከክም
ለባጢል ባለቤት ልቡ አይሸበርም
ላድስ መጤ ነገር አይጨናነቅም
የጠፊዎች ብዛት አያታልለውም
ተንኮላቸው ሁሉ ልቡን አይንደውም
===///====///====///==///===>
ለግብስብስ ኢኽዋን ለስልጣን ጥመኛ
የሚያግበሰብሱት ለሆኑ የብዛት ሱሰኛ
የማይጨነቅ ነው ለነዚህ ዋሽቶ በላተኛ
ይፋለማቸዋል ሁል ጊዜ ለነሱ ሳይተኛ
በዚህም በትግል ተግባሩ ሆኗል እዲለኛ
===///====///====///==///===>
ለአህባሽ ለሱፍያ ለቀብር አምላኪ
የሚንቀሳቀሱት ይዘው ቲርኪሚርኪ
የጠንቋይ ጥርቅም የሰይጣን ተላላኪ
ለነዚህ ጉደኞች ሳይሆን ተንበርካኪ
ይታገላቸዋል ጥሩ በሆነ በሚባል አርኪ
===///====///====///==///===>
ማንም ይሁን ማንም ለጥመት አራማጅ
ለሚንቀሳቀሱት በስሜት አስገዳጅ
ባጢልን አንግበው በከንቱ ተራማጅ
ለሚያስፈልጋቸው የተውሂዱ ጋራጅ
ይለፋል ያጀግና እነሱን ለማረም
ካሉበት በሽታ በሀዲስ ለማከም
ሀቁን ሊያሳያቸው ከንቱውን ሊያጨልም
ይደክማል ሳይሰለች ባጢሉን ለማክተም
➶➚➶➶➚➚➶➚➶➚➶
ማንን ይመስልሀል እንዲህ የገለፅኩት
ከላይ ባለው መንገድ ላንተ ያብራራሁት
አንተን ወጣቱን ነው በል ስማ ወንድሜ
አስተውል ከልብህ ልምከርህ ደግሜ
===///====///====///==///===>
ታጥቀህ ተነሳና የህሊና ንቃት
ተላብሰህ ቁምና ጥሩ የሆነ ብቃት
አጥብቀህ ታንፀህ ጥርት ባለች እውቀት
ተውሂድ ሱናን አንግስ ጀግን አንተ ወጣት
ቢድዓን ተዋጋ ሁን እንደ ነብር ጣት
ሽርክን አንኮታኩት ሁን እንደነብሮ ጣት
ሰማኸኝ ወዳጄ!!! ሁን እንደ ነብር ጣት
✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️
✍ አቡ ዒምራን ሙሐመድ መኮንን ሀሰን
አላህ ይጠብቀው!
📱⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefyዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ
ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ
"ወደ አሏህ የሚወስደው መንገድ ረጅም ነው።እኛ በእሱ ላይ እንደ ኤሊ እየተጓዝን ነው።አላማችን መንገዱን መጨረስ አይደለም።ይልቁንም መንገዱ ላይ ሁነን መሞት ነው።" ሸይኹል አልባኒ ረሂመሁሏህ
✔️ ሰዎች አወደሱህም አወገዙህም በዲንህ ላይ ቀጥ በል!!
የሚስቱ ቆንጆነትም ሆነ የሚስብ አካላቷ እንዲታይለት ከሚስቱ ጋር ፎቶ ተነስቶ የሚያሰራጭ (የሚፖስት) ወንድ
“የወንድ አልጫ”፣ እኔ
ወንድ አይደለሁም ወንድ የሆናችሁ እይዋት የሚል፣ ሚስቱን የጋራ እቃ ያደረገ ከንቱ ነው። ትክክለኛ ወንድ ግን ማነም እንዳያይበት ሸፍኖ ለግሉ ይጠቀማል።
✍አብዱረህማን ዑመር ሀፊዘሁሏህ
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefyበአሁኑ ሰዓት አብዛኛውን ሰው busy ካደረጉት የምዕራባውያን ኮተቶች መካከል “ፕራንክ” ❮prank❯ የሚሉት ነው።
➲ Prank ማለት ራሳቸው ምዕራባውያን እንደሚከተለው ይተረጉሙታል፦
«Prank is a mischievous trick or practical joke.»
ፕራንክ ማለት የተሳሳተ ተንኮል ወይም ተግባራዊ ቀልድ ነው።
➽ ይህ የተሳሳተ ተንኮል ሰዎች ባለወቁበት መልኩ የሚያስደነግጥ ነገር ይተገበርባቸዋል። ከደነገጡ ብሎም ካለቀሱ በኋላ prank ይባላሉ። በዚህ ተግባር በርካታ አላስፈላጊ ኮተቶች አሉ።
↪️ ሙስሊሞች በዚህ ተግባር መሳተፍ የለባቸውም በፍፁም አንዳንድ ሙስሊሞች ተሳትፈውበታል። የድሮ ፍቅረኛዬ ምናምን እያሉ ወንደላቸውን በሚዲያ የበተኑ ሙስሊም ሴቶችን አስተውያለሁ። ካፊር ሴት እያቀፈ የሚጃጃል ወንድም ተመልክቻለሁ። ሌሎችም
➪ ስለዚህ ከዚህ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አስፈላጊ ነው። የዚህን መሰል ፈሳድ ካፊሮች ሲያመጡ መከተል እነሱን ከመወዳጀት ነው። ይህ ደግሞ አደጋ መሆኑ ግለሰፅ ነው።
«وَمَنْ يَتَوَلَّهُمْ مِنْكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ»
[المائدة: 51]
❝ከእናንተ የተወደጃቸው ሁሉ እኮ እርሱ ከእነርሱ ነው❞
♻️ ነብዩ ﷺ ይህን አይነት መመሳሰል በግልጽ ማውገዛቸው ከማናችንም የሚሰወር አይመስለኝም።
عَنِ ابْنِ عُمَرَ قَالَ:- قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:- "مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ".
(صحيح أبي داود)
حسنه الألباني (3401)
ኢብኑ ዑመር ነብዩ ﷺ እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፏል፦
“ከሆኑ ሰዎች ጋር የተመሳሰለ ከነሱው ነው”
[ሶሂህ አቡ ዳውድ]
➜ ፕራንክ የምዕራባውያን ፍብርክ መሆኑ ግልፅ ነው። በዚህ ተግባር መሰለፍ ከእነሱ መመሳሰል ነው። ሲጀመር በውስጡ ያሉ ፈሳዶች ❪ጥፋቶች❫ ፕራንክ መራቅ ካሉብን ተግባራት መሆኑን ይጠቁሙናል።
ሌላ አንድ ሀዲስ እንጨምር፦
«عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:- ((لَتَتْبَعُنَّ سَنَنَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ شِبْرًا شِبْرًا وَذِرَاعًا بِذِرَاعٍ، حَتَّى لَوْ دَخَلُوا جُحْرَ ضَبٍّ تَبِعْتُمُوهُمْ)). قُلْنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى قَالَ:- ((فَمَنْ)).»
رواه البخار ٧٣٢٠
↪️ አብደላህ ብን ኹድሪይ እንዳስተላለፈው ነብዩ ﷺ የሚከተለውንብለዋል፦
“ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የአርጃኖ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቦጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!”
[ቡኻሪ፡ 7320]
➲ ከዚህ ሀዲስ አንፃር የት ነን!? በፕራንክ ጉዳይ busy የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ሀዲስ ልትገሰፁ ይገባል። እስከመቼ ይሁዳ እና ነሷራ ተከትለን እንጓዛለን!? ደግሞ ሙሉዕ የሆነ ዲን እያለን!!! እስልምና ያጓደለው ምንም የለም። እስልምና ያልስተማረው ካለ ካለና ከሰራነው በትክክል ጥመት ነው። በጥመት ተግባር መሳተፋችንንም ማወቅ አለብን። ነገሮችን ቀለል ማድረግ ትተን ከፕራንክ እና መሰል ኮተቶች መራቅ አለብን።
↪️ በነገራችን ላይ በዚህ ፕራንክ በሚሉት ኮተት ብዙ ጊዜ የሚከሰቱበት ሁለት ተግባሮች አሉ እነሱም፦
❶ኛ ሰዎችን ማሸበር ወይም ማስደንገጥ እና
❷ኛ በውሸት ቅንብር ማሳቅ ነው።
☑️ እነዚህ ሁለት ተግባራት ደግሞ በእስልምና የተከለከሉ ናቸው። ማስረጃዎችንእንመልከት፦
✅ የመጀመሪያውን በተመለከተ ሙስሊም ሌላ ሙስሊምን ማስጨነቅ ወይም ማሸበር አይፈቅድም፦
عن عبدالرحمن بن أبي ليلى قال:- قال رسول الله ﷺ "لا يحلُّ لمسلمٍ أن يروِّعَ مسلمًا"
صححه الإمام الألباني
سنن أبي داود
አብዱረህማን ኢብኑ አቢ ሌይላ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦
"አንድ ሙስሊም ሙስሊምን ማሸበር አይፈቀድለትም"
ሱነን አቢ ዳውድ
ኢማም አልባኒ ሶሂህ ብለውታል
✅✅ ሁለተኛው ደግሞ ሰዎችን ለማሳቅ በሚል ውሸት እየፈጠሩ መናገር በኢስላም አይፈቀድም። ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ»
"ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!"
አቡነ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ
ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡
➧ በሌላ በኩል ደግሞ የሚከተለውን ሀዲስ እናገኛለን፦
عن أبي أمامة رضي الله عنه قال:- قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم:-
"أنا زعيم ببيت في ربض الجنة لمن ترك المراء وإن كان محقا، وببيت في وسط الجنة لمن ترك الكذب وإن كان مازحا، وببيت في أعلى الجنة لمن حسن خلقه".
سنن أبي داود
وحسنه الألباني.
♻️ አቡ ኡማማህ ረዲየሏሁ ዐንሁም እንዲህ ብለዋል፡- የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ብለዋል፡-
"እኔ እውነተኛ ቢሆን እንኳን ክርክርን ለተወ ሰው በጀነት ዙሪያ ወይም ዳርቻ ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ። ስነ ምግባሩ ላማረለት ደግሞ በጀነት የላይኛው ክፍል ውስጥ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።"
ሱነን አቢ ዳውድ
አል-አልባኒ ሀሰን ብለውታል።
➲ በዚህ ሀዲስ ❸ ነጥቦች ጎልተው ተጠቅሰዋል።
❶ኛ ክርክር
❷ኛ ውሸት
❸ኛ ስነ-ምግባር
✅ ውዱ ነብይ ﷺ ❝ቀላጅ እንኳን ቢሆን ደግሞ ውሸትን ለተወ ሰው በጀነት መሀል ላይ ቤት እንደሚኖረው ዋስ ነኝ።❞ በማለት በቀልዳችን መዋሸት እንደሌለብን አስረድተዋል። ስለዚህ ውድ እህት ወንድሞች በፕራንክ ቀልድ የሚደረጉ ውሸቶች ትክክል አይደሉም። እኛም ተጠንቅቀን ሌሎችንም ልናስጠነቅቅ ይገባል።
📝 አቡ ዒምራን ሙሐመድ መኮንን
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefyዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ🌹
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ
🌹
@bintibrahimmالسلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም
https://telegram.me/bahrutekaTu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.