cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ግጥም በሜሮን ዮሐንስ (ሜራ)

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
356
Suscriptores
-124 horas
-17 días
+530 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

20240710_071305.jpg7.98 KB
👍 3
❤️ቅናት አንድ ሰው በሚወዳቸው ሰዎች በምላሹ ተወዳጅ እንዳልሆነ ሲያስብ የሚሰማው ህመም ነው፣ ቅናት ሁሌም የሚመነጨው ከንፅፅርና ከውድድር ነው። ከልጅነታችን ጀምሮ እያነፃፀርንና እየተነፃፀርን መኖር ለምደናል። ስንማረው ኖረናል ። የሆነ ሰው የተሻለ ቤት አለው ። ውብ የሆነ ሰውነት ይኖረዋል። አንዳንዱ ከሌላው የበለጠ ገንዘብ አለው። ሌላው ደግሞ መስህብ ያለው የስብዕና ባለቤት ነው፣ እነዚህን ነገሮች እየተመለከትን ከእነዚህ ሰዎች ጋር እራሳችንን እያነፃፀርን ነው የኖርነው። 📍ማወዳደር ትልቅ በሽታ ነው፣  የራስህን ሕይወት በፍጹም ከማንም ጋር አታወዳድር ። ምክኒያቱም እራስንህን ከሌሎች ጋር ስታወዳድር የምታገኘው ውጤት ከዛ ሰው የተሻልክ ከሆነ ኩራት ሲሆን ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ ደግሞ ቅናት ነው የሚሆነው ። ሁለቱም መጥፎ ውጤቶች ናቸው፣ ቅናት ደግሞ ከንፅፅራዊ ባህሪ የሚመነጭ ተረፈ ምርት ነው። እራስህን ማነፃፀር ካቆምክ ግን የቅናት ስሜትህ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል፣ ከምንም በላይ ውበት የሚገለጸው  እራስን በመሆን ነውና ። 💎ቅናት፤ ተንኮል፤ ጥላቻ እና ቂም የሰውነትን ውበት እና ግርማ የሚሰርቁ ቀማኞች ናቸው። ፈገግታ የራቀው ኮስማና ፊት እንደው ዝም ብሎ የሚመጣ ነገር አይደለም፤ ኮስማና ሃሳቦችን ከማሰብ የሚመጣ እንጂ፣ ሰዎች ደስ የሚሉ ሃሳቦችን ሲያስቡ፤ ሰውነታቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ ይናገራል፤ የውስጥ ደስታቸው ደስ የሚል ግርማን ያላብሳቸዋል። ሰውነታችን በቀላሉ እንደአስተሳሰባችን ይለዋወጣል። መልካም እና ክፉ አስተሳሰቦች የየራሳቸውን ተጽዕኖ ያሳድሩበታል። 💡ከንጹህ ልብ፤ ንጹህ ሰውነት ይገኛል፤ ከጤነኛ አስተሳሰብ ጤነኛ ሰውነት ይወለዳል፣ መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው። ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ሴራ፣ ተንኮል እና ክፍት ህሊናና ልብህን ከሞላው ግን መንገድህ መሰናክል ይበዛዋል ፣ እናም በልብህ ጥላቻ ሳይሆን ፍቅርን፣በቀል ሳይሆን ይቅርታን ፣ ቅናት ሳይሆን ቅንነትን ፣ ስስት ክፋት ሳይሆን ደግነትን ፣ ትዕቢት ሳይሆን ትህትናን፣ ሁሌም በልብህ ብትሰንቅ ነገ መልሶ የህይወት ስንቅ ይሆናሃል። 👇👇👇     https://t.me/a_xae👈 ምንጭ የኢ/ያ ቤተ መፃህፍት
Mostrar todo...

👍 5
💡ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበረው አሉ፤ ይህ ዛፍ ህልውናው እንዳይጠፋ በእጅጉ ይንከባከበው ነበር። በቀን በቀን፤ ሲመሽም ሲነጋም ወደ ዛፉ እየሄደ ምርጥ ጊዜ ያሳልፋል። ከእለታት አንድ ቀን ግን፤ ይህን ግዙፍ ዛፍ ትክ ብሎ ሲመለከተው  አንዳንድ ቅጠሎቹ ቀለማቸውን እየቀየሩ እየጠወለጉ መምጣታቸውን ተመለከተ፤ ሰውየው ሃዘን ገባው። ምንም  እንኳን ዛፉ ትልቅ እና ግዙፍ ቢሆንም፤ እንደምንም ከዛፉ እላይ እየወጣ፤ የጠወለጉትን ቅጠሎች በውሃ ማራሱን ተያያዘው። ተመልሰው ነፍስ እስኪዝሩ ድረስ፤ ሽቅብ ወደ ላይ እየወጣ ቅጠሎቹን እየወለወለ በውሃ ያርሳቸዋል። ......ለብዙ ቀን እንዲህ ሲለፋ ቆየ፤ ምንም እንኳን የተቻለውን ያህል ቢለፋም ቅጠሎቹ አንድ በአንድ ከመድረቅ እና ከመጠውለግ አልዳኑም። በመጨረሻ ሰውየው ከልፋቱ ብዛት ደከመው፤ የነበረውም ውሃ በሙሉ አለቀበት። ቀስ በቀስ ዛፉ መሞት ጀመረ…….. 📍ይህ ሰው ሃይል እና ጉልበቱን እንዲሁም ሃብቱን በከንቱ አባከነው። የዛፉን ስር ውሃ እንደማጠጣት፤ የጠወለጉት  ቅጠሎች ላይ ጊዜውን በማጥፋቱ፤ ዛፉን በሙሉ አበላሸው። ምን አልባት ብልህ ሆኖ ስሩን በውሃ ቢያርሰው ኖሮ፤ የጠወለጉት ቅጠሎች መልሰው ባበቡ፤ ሌሎችም ከመጠውለግ በዳኑ ነበር። 💡አብዛኛዎቻችን እንዲህ ነን፤ ህይወታችን መታደግ የሚያቅተን፤ ትኩረታችን ሁሉ፤ ስራችን ላይ ሳይሆን ቅጠላችን ላይ ስለሆነ ነው። ቅጠሎቻችን ምንድን ናቸው? ባህሪያችን፤ ልምዳችን፤ ወይም ሌሎች የአስተሳሰባችን ውጤት የሆኑ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ስራችን ግን ማንነታችን የሚበቅልበት አስተሳሰባችን ነው። ባህሪዎቻችን ወይም ተግባሮቻችን ሲጠወልጉ፤ ስራችንን እንደማስተካከል፤ ጊዜ እና ጉልበታችንን ለውጥ በማያመጡ ነገሮች ላይ እናጠፋለን። 📍የሁላችንንም ቅጠል የሚያጠወልገው ነገር ይለያያል፤ አንዳንዶቻችን በሱስ እንጠወልጋለን፤ አንዳንዶቻችን በስንፍና፤ አንዳንዶቻንች በቂ ፍቅር ስለሌለን፤ አንዳንዶቻችን በራሳችን ባለመተማመናችን፤ አንዳንዶቻችን ተስፋ በማጣት፤ ብቻ በተለያይዩ ምክንያቶች መጠውለግ እንጀምራለን። መጠወለጉ ሲያንገፈግፈን እና እንደገና ለማበብ ስንወስን ደግሞ መላው ይጠፋብናል። በለፋን ቁጥር ይበልጥ እንጠወልጋለን፤ ልፋታችን ከንቱ ይሆንብናል። ምክንያቱም ብዙዎቻችን እንደ ሰውየው፤ ጊዜያችንን የምናጠፋው ለውጥ በማናገኝባቸው ነገሮች ላይ ነውና። 💡የሁሉም ነገር መሰረት አይምሮዋችን ነው። የጠወለገውን ክፍላችንን እንደገና ህይወት መስጠት የሚያስችለን ብቸኛው መፍትሄ አስተሳሰባችን መቀየር ብቻ ነው። እራሳችንን እንደዛፉ ብንመለከት፤ የትኛው የህይወታችን ክፍል ነው እየጠወለገ ያለው? ልፊያችንስ ከተበላሸው ባህሪያችን ማለትም ከጠውለገው ቅጠላችን ጋር ነው ? ወይስ ስር ከሆነው አስተሳሰባችን ጋር ነው
Mostrar todo...
👍 1🙏 1
🌤If you can't make people smile, at least don't be the reason why they cry. If you can't give people reasons to remain positive, then don't add more negativity to their lives. ☀️Be someone's strength, someone's inspiration, someone's reason to remain hopeful. If you can't be the sunshine in people's life, at least don't cause the storm. 💫In times of pain and struggles, people only seek those who care and who will always be there, can you be that person people will look up to in their difficult and trying times? ✨If you can make a difference in someone's life, make sure it is either a positive one or none. You will always be remembered for two things, the problem you solved or the ones you created. ✨You can always make a positive difference in the life of others, but it is better to do nothing than to make things worse.               Happy Now!!❤️
Mostrar todo...
👍 3
ወጣትነት ማለት... ____ ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም! . . ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም! . . ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም... . . ወጣትነት ባህር ነው። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው። . . ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው። ወጣትነት ብርሃን ነው። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው። ወጣትነት እሳት ነው። ወጣትነት ቤንዚል ነው። ወጣትነት ቅጠል ነው። ወጣትነት ጤዛ ነው። ወጣትነት ታክሲ ነው። ወጣትነት ምርጫ ነው። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ...። ➮ ➮ምንጭ ከ ኤጭ መጽሐፍ 👇👇👇👇
Mostrar todo...
❤‍🔥 3👍 1🙏 1
📍አንዳንድ ወቅት አለ ስሜት የሚነዳ ፤ የሂወት ድግግሞሽ እንደጦስ ዶሮ የሚያዳክር፤  እጅ እና እግር እንደተጠፈረ  አቅም አልባነት የሚበላ ፤ አካባቢ ላይ ምን እንደተካሄደ የማይገባህ ። አንዳንድ ወቅት አለ ማጤን ማመዛዘን ያንተ የማይሆንበት ፤ የመረጥከው ምርጫ የሚያድሞከሙክኽ።  መባተልን የምትመስልበት፤   የመጣህበት መንገድ አሳስቶህ የማትመለስበት ። አንዳንድ ወቅት አለ ምርጫ የሚያባትልህ ፤   የመፍዘዝ ስሜት የሚሰማህ ፤   ሰው ሁሉ  የጠላኽ የሚመስልህ ፤  ኃላ  የመቅረት ስሜት የሚንጥህ ። አንዳንድ ወቅት አለ  ማድረግ እንደሌለብህ እያወክ  የምታከናወነው ፤ የስሜትህ ባርያ የምትሆንበት ፤ መገኘት እንደሌለብህ እያወክህ የምትገኝበት  ። እንዳንድ እለት አለ ብልጥ ነኝ ባዮች የሚበልጡ ፤ አራዳ ነኝ ባዮች የሚያሞኝህ፤ በዝባዦች የሚበዘብዙህ፤ ባለጡንቻዎች አቅማቸውን የሚለኩብህ እንዲም ሁሉ ሆኖ ሳለ በግዜ እናምናለን ። ግዜ ሃያል ነው ። ሁሉም ይስተካከላል፣ መስመር መስመር ይይዛል  ።አይነጋም ያልነው ጨለማ ስንቴ ነግቷል። Join 👇❤️👇❤️👇❤️👇❤️👇❤️  
Mostrar todo...
🇪🇹🇪🇹🇪🇹የኢትዮጵያ 📚📚📚መፃሕፍትና ወግ💁‍♀💁‍♀💁‍♀

አላማ አንባቢና ምክንያታዊ ትውልድ መፍጠር ነው: ሲጮሁ የማይጮህ እና ጠበቆችህነን የሚሉትን የሚሞግት ትውልድ መፍጠር::

ምናብ አለሚቱ✍️ ከህንድ ጠጉርሽን ፣ ከአሜሪካ አፍንጫ አይኖችሽ ካውሮፓ' ፣ ቀለምሽ ሃር ቢጫ ከንፈርሽ ከእስያ ፣ ጡቶችሽ ከአረብ ከየሩሳሌም ስር፣ እንዲኖርሽም ረብ ሃበሻ ተላብሰሽ፣ እንድል ገራገሬ ልብሽ ከኢትዮጵያ፣ ከዚው ከሃገሬ        (ቢቻል የጣይቱን) እንትንሽን ከሰማይ ፣ ከሌለበት ማንም               ለምን? እስክትመጪ ድረስ፣ እኔ ሰው አላምንም። ' ' ከሁሉም ስብጥር ፣ የሳልኩሽ እንደዛ ምናብ አለም ሚስቴ ፣ የኔ ሞናሊዛ እኒያ ጓደኞቼ ፣ አግባት ከተባለህ ወደፊት ምን አይነት ሚስት ታገባለህ? ብለው ሲጠይቁኝ በልጅነት ልቤ በአፍላነት ቀልቤ እንዲያ ብትሆን ብዬ፣ እንደዛ የሳልኩሽ ከአልጋዬ በላይ፣ እንዲያ የሰቀልኩሽ (አንቺዬ) በውኑ አለም ላይ ላገባ ነውና፣ ከምናቤ ውጪ ውጪ ብዬ ስልሽ   ፣   ዳግም እንዳትመጪ             (አግብቻለው) የመጣሽ ለት' ግና ከኔና አንቺ አዳር የት አባቱ ትዳር (ግን እንዳትመጪ) (ከመጣሽ ግን!) እግዚያሩም አይወደው፣ የኔና አንቺን ነገር አስጠፍርሻለው እሪ!..ብዬ በሃገር (እንዳትመጪ) (ከመጣሽ ግን ነይ) እንግዳዬሁ ዘሪቱ ✍️
Mostrar todo...
¶✍️                    ባለፈው ለት' ፈራሻለው ስልሽ፣ እንዲያ አኩርፈሻል                 ትላንትና ደሞ' ውብ ቆንጆ ነሽ ስልሽ እንደዚያ ስቀሻል             ዛሬም ልድገምልሽ እፈራሻለው ከሩቅ፣ አፍርሻለው በደምብ እንደዚያ ባይሆንም፣ የወንድ ወግና ደምብ              አኮረፍሽኝ እንዴ?             ምነው እንዲህ ባንዴ?    የፈሩትን ሁሉ ፣ ይጠሉታል እንዴ?    (ያከበሩትን ሰው አይወዱትም እንዴ?)      በማስፈራትማ  እዝጌሩም  ያስፈራል    ውበቱ ግን ረቂቅ መውደድን ይጭራል                  (  አንቺዬ...) ርቀቷን ሳጠብቅ ፣ ብርሃንሽ ተገልጣ ፀሐይን ደፍሬ ፣ ለምን አይኔን ልጣ?          ደሞ አስቢበት ብርሃንን ስትለቂው ፀሐይ ከሰው ልጆች እንደምን ይርቃል? እዝጌሩን ጠይቂው!        "ሰይጣንምኮ  ያስፈራል" ብለሽ ለጠየቅሽው ፍቅር እያወጉ ሰይጣን አይነሳም፣ ወደዚያ መልሽው              እንዲያ ባፈቅርሽም        ታስፈሪኛለሽ ይቅር አላይሽም        ግን ደግሞ አልጠላሽም። እንግዳዬሁ ዘሪቱ✍️
Mostrar todo...
🥰 3😍 1
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.