cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ንፍታሌም TUBE

Orthodox ⛪🙏 👉 የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ⚪የመዝሙር አልበሞች ⚫ የመዝሙር ቪዲዮዎች ⚪ አዳዲስ የነጠላ መዝሙሮች ⚫ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች ⚪የ ቅዱሳን ታሪክ ❖በዚህ ቻናል ያገኛሉ❖

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
201
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ኢትዮጵያ ሆይ.m4a1.61 MB
#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_ለሶልያና #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡ #ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤ #ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤ #ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡ ፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና አባቷ ወደተቀበሩበት ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲወስዷት አይሁድ አይተው፤ ልጇ ተነሳ፥ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው /ሌላውን ታሪክ በፍልሰታ ጾም ላይ ያንብቡ፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››/ ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና(ለማርያም) ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡ #ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡ *የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ሞትሰ ለመዊት ይደሉ፥ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡
Mostrar todo...
🙏ማሳሰቢያ🙏 በወቅታዊ የቤ/ክ ጉዳይ ቅዱስ ሲኖዶስ ከነገ ሐሙስ 18/5/15 እስከ ቅዳሜ ለ3ት ቀናት የፆምና ፀሎት እንዲሁም የሱባኤ አዋጅ ስላወጀ ሁላችንም የጣመ የላመ ከመብላት ተከልክለን ጠዋት በኪዳን ማታ በሰርክ ፀሎት በቤ/ክ ተገኝተን ምህላ እንድናደርስ ታዟል:: "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን" ፀሎተ ሐይማኖት
Mostrar todo...
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ፡- ኤልያስ ማለት ‹‹እግዚአብሔር አምላክ ነው›› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ቴስብያዊው ኤልያስ በሕይወት ሳለ በእሳት ሠረጋላ ወደ ሰማይ ያረገ ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ ንጉሡን አክዓብንና ሚስቱን አልዛቤልን ስለ ክፉ ሥራቸው ሁሉ አጥብቆ የተቃወማቸውና የገሠጻቸው ታላቅ ነቢይ ነው፡፡ አክዓብን ‹‹በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠልና ዝናብ አይሆንም›› ብሎ ከነገረው በኋላ ሰማይን ዝናብ እንዳይጥል በጸሎቱ ለጉሞታል፡፡ ለሦስት ዓመትም ዝናብ ሳይዘንብ ቀረ፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹ከዚህ ተነሥተህ ወደ ምሥራቅ ሂድ በዮርዳኖስም ትይዩ ባለው በኮራት ፈፋ ውስጥ ተሸሸግ›› የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣለት፡፡ ዳመኛም እግዚአብሔር ‹‹ከወንዙም ትጠጣለህ፣ ቍራዎችም በዚያ ይመግቡህ ዘንድ አዝዣለሁ›› ብሎ ስለምግቡ ነገረው፡፡ ቍራዎችም ጠዋት ዳቦ፣ ማታ ሥጋ እያመጡለት ብዙ ጊዜ ተቀመጠ፡፡ 1ኛ ነገ 17፡1-4፡፡ ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር ‹‹ተነሥተህም በሲዶና አጠገብ ወዳለችው ወደ ሰራፕታ ሂድ፥ በዚያም ተቀመጥ፤ እነሆም ትመግብህ ዘንድ አንዲት ባልቴት አዝዣለሁ›› ሲል ተናገረው፡፡ ተነሥቶም ወደ ሰራፕታ ሲሄድ እንጨት ስትለቅም አገኛትና ‹‹የምጠጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመጭልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ›› አላት፡፡ ውኃም ልታመጣለት በሄደች ጊዜ ወደ እርስዋ ጠርቶ ‹‹ቁራሽ እንጀራ በእጅሽ ይዘሽ ትመጭ ዘንድ እለምንሻለሁ›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹አምላክህ ሕያው እግዚአብሔርን! በማድጋ ካለው ከእፍኝ ዱቄት በማሰሮም ካለው ከጥቂት ዘይት በቀር እንጀራ የለኝም፡፡ እነሆም ገብቼ ለእኔና ለልጄ እጋግረው ዘንድ በልተነውም እንሞት ዘንድ ጥቂት እንጨት እሰበስባለሁ›› አለችው፡፡ እርሱም ያላትን ዱቄትና ዘይት ተጠቅማ ለእርሱና ለልጇ እንጎቻ እንድትጋግር ነገራት፡፡ በመታዘዝም አንዳላት አደረገች፡፡ ኤልያስም እንደተናገረው ቤቷን በበረከት ሞልቶላት ዱቄቱ ከማድጋው ሳያልቅ ዘይቱም ከማሰሮው ሳይጎድል ብዙ ቀን ሲመገቡ ቆዩ፡፡ ከዚያም በኋላ የሴቲቱ ልጇ ታሞ ሞተ፡፡ እርሷም ኤልያስን ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? ኃጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?›› አለችው፡፡ ኤልያስም ‹‹ልጅሽን ስጪኝ›› ካላት በኋላ ወደ ሰገነት አውጥቶ አስተኝቶት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ እግዚአብሔርም የኤልያስን ቃል ሰምቶ ብላቴናውን ከሞት አዳነው፡፡ ወስዶም ለእናቱ ‹‹እነሆ ልጅሽ በሕይወት ይኖራል›› ብሎ ሰጣት፡፡ 1ኛ ነገ 17፡1-24፡፡ ከሦስተኛውም ዓመት በኋላ ‹‹ሂድ ለአክዓብ ተገለጥ፣ በምድርም ላይ ዝናብ እሰጣለሁ›› የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣ፡፡ ኤልያስም ለአክዓብ ይገለጥ ዘንድ ሄደ፡፡ በሰማርያም ርሃብ ጸንቶ ነበር፡፡ ንግሥቲቱ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት እያሳደደች ባስገደለች ጊዜ እግዚአብሔርን እጅግ ይፈራ የነበረውና የአክዓብም የቤቱ አዛዥ የነበረው አብድዩ መቶውን ነቢያት ወስዶ አምሳ አምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጎ እንጀራና ውኃ ይመግባቸው ነበር፡፡ አብድዩም በመንገድ ሲሄድ ኤልያስን ተገናኘው፡፡ አብድዩም ዐወቆት በግምባሩ ተደፍቶ ሰላምታ ሰጠው፡፡ ኤልያስም ‹‹ሄደህ ለጌታህ ኤልያስ ተገኝቷል በለው›› አለው፡፡ ንጉሡ አክዓብም ኤልያስን ሊገናኘው መጣና ባየው ጊዜ ‹‹እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን?›› አለው፡፡ ኤልያስም ‹‹እስራኤልን ሁሉ፥ በኤልዛቤልም ማዕድ የሚበሉትን አራት መቶ አምሳ የበኣልን ነቢያት 400 የማምለኪያ ዐፀድን ነቢያት ወደ እኔ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብ›› አለው፡፡ አክዓብም ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ ልኮ ነቢያቱን ሁሉ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሰበሰበ፡፡ ኤልያስ ሐሰተኞቹ ነቢያትና እርሱ መሥዋዕት አቅርበው እግዚአብሔር የትኛውን መሥዋዕት እንደሚቀበል ያዩ ዘንድ ሲናገር ሕዝቡም በሃሳቡ ተስማሙ፡፡ ኤልያስም የበኣልን ነቢያት ‹‹እናንተ ብዙዎች ናችሁና አስቀድማችሁ አንድ ወይፈን ምረጡና አዘጋጁ የአምላካችሁንም ስም ጥሩ›› አላቸው፡፡ እነርሱም ወይፈኑንም ወስደው ካዘጋጁ በኋላ ‹‹ከጠዋትም እስከ ቀትር ድረስ። በኣል ሆይ፥ ስማን እያሉ የአምላካቸውን የበኣልን ስም ጠሩ፡፡ ድምፅም አልነበረም፥ የሚመልስም አልነበረም፤ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር፡፡ በቀትርም ጊዜ ኤልያስ ‹‹አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት አሳብ ይዞታል ወይም ፈቀቅ ብሎአል ወይም ወደ መንገድ ሄዶአል ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል›› እያለ አላገጠባቸው፡፡ እነርሱም በታላቅ ቃል ይጮኹ እንደ ልማዳቸውም ደማቸው እስኪፈስ ድረስ ገላቸውን በካራ ይቧጭሩ ነበር፡፡ ቀትርም ካለፈ በኋላ መሥዋዕተ ሠርክ እስኪደርስ ድምፅም አልነበረም፥ የሚመልስና የሚያደምጥም አልነበረም፡፡ ከዚህም በኋላ ኤልያስ ሕዝቡን ሁሉ ወደ እርሱ አቀርቦ ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠዊያ አበጅቶ ‹‹የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ሆንህ እኔም ባሪያህ እንደ ሆንሁ ይህንም ሁሉ በቃልህ እንዳደረግሁ ዛሬ ይገለጥ›› እያለ ጸለየ፡፡ በዚህም ጊዜ የእግዚአብሔር እሳት ወርዳ መሥዋዕቱንም እንጨቱንም ድንጋዮቹንም አፈሩንም በላች በጕድጓዱም ውስጥ ያለውን 18፡1-46፡፡ሕዝቡም ሁሉ ያንን ባዩ ጊዜ በግምባራቸው ተደፍተው ‹‹እግዚአብሔር እርሱ አምላክ ነው›› አሉ፡፡ ኤልያስም ‹‹ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዟቸው›› አላቸው፡፡ ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ አሳረዳቸው፡፡ 1ኛ ነገ 18፡1-46፡፡ አክዓብም ኤልያስ ያደረገውን ሁሉ ነቢያትንም ሁሉ በሰይፍ እንደ ገደለ ለኤልዛቤል በነገራት ጊዜ ‹‹ነገ በዚህ ጊዜ ነፍስህን ከእነዚህ እንደ አንዲቱ ነፍስ ባላደርጋት አማልክት ይህን ያድርጉብኝ›› ብላ ወደ ኤልያስ መልእክተኛ ላከች፡፡ እርሱም ፈርቶ ነፍሱንም ሊያድን ወጥቶ ሄደ፡፡ አንድ ቀን የሚያህል መንገድ በምድረ በዳ ከሄደ በኋላ ከክትክታ ዛፍ በታች ተቀመጠና ‹‹ይበቃኛል፤ አሁንም አቤቱ እኔ ከአባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ›› ብሎ እንዲሞት ለመነ፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹ለጣዖት ያልሰገዱ 70 ሺህ ሰዎችን አስቀርቻለሁና አትፍራ፣ ያንተንም ነፍስ ማንም ሊወስዳት የሚችል የለም፡፡ ነገር ግን በሥጋህ ሕያው እንደሆንክ ወደ ሰማይ አወጣሃለሁ›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ኤልያስ በክትክታው ዛፍ በታች ጋደም አለና እንቅልፍ ወሰደው፡፡ የታዘዘም መልአክ መጥቶ ምግቡን ከሰማይ ይዞለት መጥቶ ዳሰሰውና ተነሥቶ እንዲመገብ ነገረው፡፡ ኤልያስም ከበላና ከጠጣ በኋላ አንድ ጊዜ በተመገበው በዚያ ምግብ ኃይል እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ 40 ቀንና 40 ሌሊት ሄደ፡፡ 1ኛ ነገ 19፡1-8፡፡ ንጉሡ አክዓብ የወይኑን ቦታ ለመውሰድ ሲል ናቡቴን ቢጠይቀው እምቢ ስላለው ከሚስቱ ከኤልዛቤል ጋር ተማከረ፡፡ እርሷም ናቡቴን ‹‹እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቧል›› ብላ በሐሰት አስመስክራበት በድንጋይ አስወግራ አስገደለችው፡፡ ባሏንም የናቡቴን የወይኑን ቦታ እንዲወስድ ነገረችው፡፡ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስብያዊው ወደ ኤልያስ ‹‹እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ገድለህ ወረስኸውን? ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ስፍራ የአንተን ደም ደግሞ ውሾች ይልሱታል ብለህ ንገረው›› ሲል መጣ፡፡ ኤልያስም ሄዶ እንደታዘዘው ለአክዓብ ነገረው፡፡ አክዓብም የሞቱን
Mostrar todo...
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን ጥር 6-ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ የፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ + በጸሎታቸው አራት ሙታንን በአንድ ጊዜ ከሞት ያስነሡትና በየዓመቱ በዕረፍታቸው ዕለት ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ የሚዘንብላቸው ታላቁ አቡነ ኢዮስያስ ልደታቸው ነው። + ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ልደቷ ነው፡፡ + ጻድቁ ኖኅ በዓለ ዕረፍቱ ነው፡፡ + ነቢዩ ቅዱስ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ያረገበት ዕለት ነው፡፡ + ቅዱስ ባስልዮስ ቀዳማዊ ዘቂሳርያ ዕረፍቱ ነው፡፡ + ዳግመኛም በዚህች ዕለት ስንክሳሩ ‹‹በበረሃ ስልሳ ዘመናት የኖረ አባ ሙሴ ዐረፈ፤ እርሱም የቅዱሳንን ልቡና ከማየቱ የተነሣ አደነቀ፡፡ ፊቱም ተለውጦ እንደእሳት ፍሕም ሆነ›› ብሎ በአጭሩ የገለጸው አባ ሙሴ ዕረፍቱ ነው፡፡ ጌታችን ወደ ቤተ ቅዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ እንደፈጸመ፡- ለብዙዎች ጌታችን ወደ ቤተ ግዝረት እንዳልገባና እንዳልተገረዘ ይመስላቸው ነበር፡፡ እነርሱ እንዳሰቡት ቢሆን ኖሮ አይሁድ ታላቅ ምክንያትን የሚያገኙ በሆኑ ነበር፡፡ ጌታችን ግን የግዝረትን ሕግ ፈጸመ፡፡ ልሳነ ዕፍረት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› ብሎ እንደተናገረ፡፡ ጌታችን ለእኛ በግዝረት ፈንታ የክርስትና ጥምቀትን ሰጠን፡፡ የፋሲካውንም ቀጣ በላ፤ በእርሱም ፈንታ አማነዊውን ሥጋውንና ደሙን ሰጠን፡፡ የከበረ ወንጌል ‹‹8ኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት፣ ሳትፀንሰው መልአኩ እንዳወጣለት ስሙን ኢየሱስ አሉት›› እንዳለ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ማርያም ጻድቅ አረጋዊ ዮሴፍን ‹‹እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙን እንድንሰይመው ብልህና አዋቂ የሆነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ›› አለችው፡፡ አረጋዊ ዮሴፍም ሄዶ የሚገርዝ ባለሙያ አመጣ፡፡ ያ ባለሙያም ሕፃኑን ልጅ ጌታችንን በእናቱ ክንድ ባየው ጊዜ ‹‹እንዲገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቄ ያዙት›› አላቸው፡፡ ሕፃን ጌታ ኢየሱስም ‹‹ባለሙያ ገራዥ ሆይ! ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን? በዚያች ዕለት ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና ጎኔን በጦር ሲወጉኝ ያንጊዜ ውኃና ደም ይፈሳል ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆቹ መድኃኒት ይሆናልና›› አለው፡፡ ጌታችንም ይህንን የተናገረውን ገራዡ በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ፡፡ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ እግር በታች ሰገደ፡፡ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደውኃ ሆኑ፡፡ ባለሙያውም ክብርት እመቤታችንን ‹‹ከሴቶች ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ ይህ ልጅሽ ስለእርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው›› አላት፡፡ ሕፃኑም መልሶ ለዚያ ባለሙያ ‹‹እኔ ነኝ፣ ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ? ወይስ የአባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ?›› አለው፡፡ ባለሙያውም ‹‹የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው? አለው፡፡ ሕፃን ጌታችንም ‹‹አብርሃም፣ ይስሃቅ፣ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው፤ ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው›› አለው፡፡ ባለሙያውም ‹‹እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ሕልውና መንፈስ ቅዱስ አለና›› አለው፡፡ ያንጊዜም ሕፃን ጌታችን ዐይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ ‹‹አባት ሆይ ለአብርሃም፣ ለይስሃቅ፣ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያችን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ›› አለ፡፡ ያንጊዜ ያለሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች፡፡ የእመቤታችን ድንግልናዋ ሳይለወጥ ከድንግል ማኅፀን እንደመውጣቱ የጌታችን ግዝረቱም የማይመረመር ሆነ፡፡ እንዲሁ በተዘጋ ቤት መግባቱና መውጣቱ እንደማይመረመር እነዲሁ እንደፈቀደ ከረቀቀ ጥበቡ ችሎታውን በመገረዝ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቆረጥ ገለጠ፡፡ አዳምንና ልጆቹን ያድናቸው ዘንድ በፈቃዱ ከጎኑ በመስቀል ላይ የሚፈሰው ደምና ውኃ ካልሆነ በቀር ብዙም ሆነ ጥቂት ሊሆን አይችልም፡፡ እርሱ በፈቃዱ ሕጉ እንዲፈጸም አስቀድሞ አዘዘ እንጂ፡፡ ያም ባለሙያ ገራዥ ይህንን ተአምር ባየና የሕፃኑንም ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ፡፡ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር ሦስት ጊዜ ሰገደና ‹‹በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ የእስራኤል ንጉሥ ነህ›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ከጌታችን ከተአምራቱ ያየውንና የሰማውን እየተናገረ እየመሰከረ ወደቦታው ሄደ፡፡ ለሕፃኑ ጌታችን ከቸር አባቱ ጋራ ማኅየዊ ከሆነ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡ @Abukizedebresina
Mostrar todo...
ነገር ከኤልያስ በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ ገላውን ማቅ አለበሰ፣ ጾመም፣ በማቅ ላይም ተኛ፡፡ ‹‹አክዓብ በፊቴ እንደ ተዋረደ አየህን? በፊቴ የተዋረደ ስለሆነ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመጣለሁ እንጂ በእርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላመጣም›› የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስብያዊው ወደ ኤልያስ መጣ፡፡ 1ኛ ነገ 20፡-1-29፡፡ አክዓብም ከሞተ በኋላ የሞዓብ ሰዎች አመፁ፡፡ ንጉሡ አካዝያስ ታሞ በሰማርያ በእልፍኙ ተኛ፡፡ እርሱም ይሞት ወይም ይድን እንደሆን ይጠይቁለት ዘንድ ወደ ጠብቋይ ወታደሮቹን ላከ፡፡ በዚህም ጊዜ አልያስ ‹‹እንደማትድን ዕወቅ›› ብሎ ላከበት፡፡ ንጉሡም ኤልያስን ይጠሩለት ዘንድ 50 ወታሮችን ከአለቃቸው ጋር ወደ ኤልያስ ላከ፡፡ ኤልያስም በተራራ ላይ ተቀምጦ አገኙትና ‹‹ንጉሡ ይጠራሃልና ፈጥነህ ወርደህ ና›› አሉት፡፡ ኤልያስም ‹‹የእግዚአብሔር ነቢይ ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዳ እናንተን ታቃጥላችሁ›› አላቸው፡፡ እሳትም ከሰማይ ወርዳ አቃጠለቻቸው፡፡ ንጉሡም ዳግመኛ 50 ወታሮችን ከአለቃቸው ጋር ወደ ኤልያስ ላከ፡፡ ኤልያስም እንደመጀመሪያው ሲናገር አሁንም እሳት ከሰማይ ወርዳ አቃጠለቻቸው፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ የተላከው 50 አለቃ ግን በኤልያስ ፊት በትሕትና ሰግዶ ከተራራው ይወርድ ዘንድ ለመነው፡፡ ኤልያስም ስለትሕትናው ወርዶለት ወደ ንጉሡ ዘንድ አብረው ሄዱና ኤልያስ ንጉሡን እንደሚሞት ነገረው፡፡ ንጉሡም ሞተ፡፡ ከዚህም በኋላ ኤልያስ ወደ ሰማይ የሚወጣበት ጊዜ ሲድርስ ከደቀ መዝሙሩ ከኤልሳዕ ጋር ሆኖ ወደ ዮርዳኖስ ደረሱ፡፡ ኤልያስም መጠምጠሚያውን አውርዶ በመጠቅለል የዮርዳኖስን ወንዝ ቢመታው ለሁለት ተከፈለና ሁለቱም በደረቅ ተሻገሩ፡፡ ኤልያስም ጥር 6 ቀን በእሳት ፈረስና በእሳት ሠረገላ ተነጥቆ በሚያርግበት ጊዜ መጠምጠሚያውን ለደቀ መዝሙሩ ለኤልሳዕ ሰጥቶት በኤልያስ ያደረ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ሆኖ በኤልሳዕ አድሮበታል፡፡ በብሉይ ዘመን ኑሮው በበረሃ የነበረው ይህ ታላቅ ነቢይ በኋለኛው ዘመን ከሄኖክ ጋር ይመጣ ዘንድ አለው፡፡ መጥተውም ሐሳዌ መሢሕን ይቃወሙታል፣ እርሱም ይገድላቸዋል፡፡ አስክሬናቸውንም በአደባባይ ጥሎ ሦስት ቀን ይቆያል፡፡ እነርሱም ከሞት ሲነሡ ትንሣኤ ሙታን ይሆናል፡፡ የነቢዩ ኤልያስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን! @Abukizedebresina
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
💚እንኳን ለብርሃነ 💛ልደቱ በሰላም አደረሰን❤️ ታህሳስ 29/2015 ዓ.ም
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
ፍፁም ፍቅሩንም ሰጠኝ ኃጢአተኞችን ለማዳን ወደ እዚህ ዓለም መጣህ ስለዚህ እኔንም ልታድነኝ መጣህ.. የጠፋውን ፈልገህ ልታድን መጣህ።  ስለዚህ እኔንም ልትፈልገኝ መጣህ እኔ ከጠፉት ውስጥ አንዱ ነኝና። አቤቱ አምላኬ ፈጣሪዬ ሆይ!  ሕግህን የተላለፍኩ ወደ አንተ ልመጣ ይገባ ነበር።  ከእግርህ በታችም ወድቄ በፊትህ ራሴን ጥዬ፣ በትህትና ይቅርታንና ምኅረትን መለመን ይገባኝ ነበር... አንተ ግን ጎስቋላና የማልጠቅም ከንቱ ባሪያ  ወደ ሆንኩት ወደ እኔ መጣህ።   ጌታዬ ጠላቱና ከሃዲው ወደ  ሆንኩት ወደ እኔ መጣ።  ፍፁም ፍቅሩንም ሰጠኝ። [_አባ ቲኮን_] @Nolawiiher
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
መዝሙር 119 ¹⁶⁹ አቤቱ፥ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትቅረብ፤ እንደ ቃልህም አስተዋይ አድርገኝ። ¹⁷⁰ ልመናዬ ወደ ፊትህ ትድረስ፤ እንደ ቃልህ አድነኝ። ¹⁷¹ ሥርዓትህን አስተምረኸኛልና ከንፈሮቼ ምስጋናን አወጡ። ¹⁷² ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና አንደበቴ ቃልህን ተናገረ። ¹⁷³ ትእዛዛትህን መርጫለሁና እጅህ የሚያድነኝ ይሁን። ¹⁷⁴ አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ ሕግህም ተድላዬ ነው። ¹⁷⁵ ነፍሴ ትኑርልኝ ታመሰግንህማለች፥ ፍርድህም ይርዳኝ። ¹⁷⁶ እንደ ጠፉ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ ትእዛዛትህን አልረሳሁምና ባሪያህን ፈልገው። አሜን !
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.