➖ #ልዩ_ጥቆማ_ከሰይጣን በሚደርስብን ጥቃት ታግሰን በሱና_ለመጽናት!
〰〰〰〰
ጹሑፉን በትእግስት እንዲታነቡትና ለሌሎችም እንዲታደርሱት በትህትና እጠይቃለሁ!.
ካፊሮችና ሙብተዲዖች ሲህር (ድግምትን)ና ዓይንናስን ለምን ያስተባብላሉ? ወይስ በአላህ ፈቃድ እንደሚጎዳ ውድቅ ለማድረግ ለምን ዙሪያ ጥምጥም ይላሉ?
ምክንያቱም ሰይጣን ካፊርም ሙብተዲዕም ከሆንክ ከዛ ወዲያ ምን ይፈልጋል ካንተ? ለዛ ነው።
ሲህር የሚሰራው
በዋናነት ካፊር እንዲኮን ከዛም ሙብተዲዕ አንዲኮን ከዛም ወንጀለኛ እንዲኮን ነው። ስለዚህ ቁጥር አንድና ሁለት ደረጃ ከተቀመጥክለት ከዛ ውጭ ሰይጣን ካንተ ምን ይፈልጋል።?
እውነተኛ ስትሆን ነው እንጅ በውሸት ላይ ከሆንክ
ካፊር (ጼንጤ ኦርቶዶክስ) ከሆንክ
ወይም
ሙብተዲዕ (ሺዓ/ራፊዷ፣ኸዋሪጅ፣ አህባሽ/ሱፍይ፣ ኢኽዋን፣ተብሊግ፣ ሙመይዓ፣ ሀጃዊራህ) ከሆንክ ሰይጣን ካንተ ሀጃ የለውም። ከዛ ውጭ ምን ይፈልጋል ካንተ? ለምን ይወሰውስሃል? ሂድ ከክርስቲያን ሰፈር ለሚጠየቁት ሁሉ ገንዘባቸውን ሲያወጡ፤ በለቅሶ ሲራጩ ትመለከታለህ፣ በሱፍይነት ዓለም ሂድ አስገራሚና አወዛጋቢ ነገር ትመለከታለህ! ይሄን በሁኔታው ላይ ኖረንበት ያየነው ነው። ኢኽዋን ውስጥም ምን እንዳለ አይተነው ወጥተናል! ስለዚህ ሱቢሂ ሶላት ስለተገራልህ፣ ሌሊት በመቆም፣ በቁርአን በዚክር በእንባ መታጠብህ፣ ከሌሎች ወንጀሎችም መራቅህና እነሱን በጣም መጥላትህ ብቻውን እንዳያታልልህ! ይሄ ሁሉ ብቻውን መለኪያ አይሆንም!
ነብዩ (ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም) ኸዋሪጆችን እንዴት እንደገለጿቸው ተመልከት፡- “ሶላታችሁን ከሶላታቸው፣ ፆማችሁን ከፆማቸው፣ ስራችሁን ከስራቸው (ብታነፃፅሩት የናንተን) ያስንቋችኋል፡፡ ቁርአንንን ሲቀሩ ከጉሮሯቸው አይወርድም።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ሆኖም ግን እውነተኛ ሙስሊም ሰለፍይ የሱና ተከታይ ከሆንክ በኋላ፤ ምንም ቢክብድህም ሰይጣን ትግል ቢይዝምህም በእነዚህ ዒባዳዎች በሶላት በዚክር ሌሊት በመቆም ቀን በመፆም፣ በሶደቃ ላይ ለመጠንከር መታገል፣ ከወንጀሎች ሁሉ ለመራቅ መታገል፣ በምላስህ ሰዎችን ከማማትና ከመጉዳት ከመበደል መራቅ፤። ይሄ ሁለቱ! ትክክለኛው ሱና ላይ መቆምህና ተቅይ መሆንህ ሲሟላልህ የሰሀቦችን መንገድ አሟልተሃል ይባላል።! ሌላው ጎድሎህ ሱናው ላይ ከቆምክ በሰሀቦች መንገድ ላይ ቆመሃል ግን ብዙ ነገር ጎድሎሃል ይባላል። ይሄው ነው ያለው ግንዛቤህ ሰፋ ሲል!
አላህ ዲኑን ያስገንዝበን!
عن مُعَاوِيَةَ بن أبي سفيان رضي الله عنهما قال: سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ : (مَنْ يُرِدِ اللَّهُ بِهِ خَيْرًا يُفَقِّهْهُ فِي الدِّينِ رواه مسلم (1037)
አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ሙዓውያህ ኢብኑ አቡ ሱፍያን ባወሩት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፦
{{አላህ መልካም የሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል!}} (ሙስሊም ዘግቦታል 1037)
ከራስህ እንቅስቃሴ አንድ ነገር ላስታውስህ! በተወሰነ መልኩ ከመጥፎ መከልከል ዘንጋ ስታደርግና በሱና መጠንከርን ችላ ስትል እንደት ሰይጣን ጉትጎታውን እንደሚተውህ አስተውለሃል?
ዛሬ ላይ ኹጥባ ላይ ወጥቶ ወደ ከፊል የክርስትና እምነት የሚጣራ አካል፤ ኒቃብ ለባሾች የራሳቸውን ድክመት ነው እንጅ ድግምት አይጎዳም ወይም ለማሳመኛ እንዲሆነው በሙዓውዘተይን ድምጥማቱን ማጥፋት ይቻላል! ያለው ግለሰብ! በርግጥ ሁለተኛውን በተመለከተ ትክክል ነው። በጥቅሉ የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነው የምንለው፤ ሆኖም ግን ይሄን ሰውየና መሰሎቹን የምንጠይቃቸው እስኪ አዑዙ ቢላህ በሉና ውቅያኖት ከሆነ ቢድዓችሁና በዲን ላይ ጥፋታችሁ ለመመለስ ሞክሩ! ሰይጣንን አሸንፉ!! የእህቶቻችን ትምህርትን ማቋረጥኮ ከእናንተ ዲንን ከምትገድሉት ጋር በፍጹም አይገናኝም! ኧረ ስንቱ ይኸራል የናንተ!
https://t.me/Abdurhman_oumer/2111?single
👆
ሌላውን ትተነው ሁርየቱል ዒዕቲቃድን ኹጥባ ላይ እየሰበክ ሌሎችን የእምነት ድክመት ነው። በማለት ጀግና ጀግና ያጫውተሃል እንደ?
➖ፖለቲካ የኢስላም ዋናው ክፍሉ ነው
➖ነብያቶች ቢመጡ፤ ከኢስላም ውጭ የሆነ አካል (ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ) የሰጠንን እድል ሊሰጡን አይችሉም።
➖እኔ ሡፍይ ነኝ የሡፍይ ልጅ ነኝ ወጣቱን ሁሉ ሡፍይ ማድረግ አለብን!
➖እየሱስ ሰላምን የሰበከ ጌታ ነው፤ ሁላችንም የፈጣሪ ልጆች ነን!
➖ሰሀቦችን ስትፈልገ ሰነፎች በላቸው
የሚሉ ሰዎችንና ሌሎቹም እነዚህን ጅላጅል አይደሉም በእድሜ የበሰሉ ናቸው የሚሉ፤ በተቃራኒው ለሱና የሚታገሉ ሰዎችን የረድ ጉረኞች፤ በእድሚያቸው ልክ የማያስቡ፤ የውሃ ላይ ሸንበቆ የሚል ሰው ዘንድ ሰይጣን ሀጃ የለውም። ሰይጣን ለዲን የሚታገሉ ሰዎችን ነው የሚፈልገው በተቻላችሁ “መዳኺሉ ሸይጧን” የሚለውን የሸይኽ ሁሴንን ኪታብ ጎብኙት!
👇
https://t.me/shakirsultan/1534
ስለዚህ ወስዋስ ስለበዛብህ ምንም አይነት ነገር በዲንህ ስለደረሰብህ ተስፋ ቆርጠህ እንዳትንሸራተት ተጠንቀቅ! የብዙዎች መንሸራተት ምክንያት አንዱ ይሄ ነው።
የተከበራችሁ የአላህ ባሮች ሆይ፦ መጨረሻ ላይ ተስፋ የማስቆረጥ ደረጃ የሚያደርስ ነገር ሲገጥማችሁና አማራጩ መንሸራተት እንደሆነ ሹክ ሲላችሁ መፍትሔ ሁሉ ፈልጉለት፤ የሚሰማችሁን ስሜትና ያላችሁበትን ተጨባጭ ትታችሁ ዲኑን አስታውሱ! ዲኑን ሱናን ካስታወሳችሁም በኋላ ራሳችሁን አጽናኑ አላህ ለጥበቡ ነው ያደረገው ፈተና ነው በሉ! በተጨማሪ ይህችን የሸይኽ ሱለይማን አሩሀይሊን ጥቆማ ተጠቀሙባት!!
👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/5455
ሰይጣን ኸይር ስያይብህ ነው በከፍተኛ እየጣለህ እየተነሳህ ድረስ ትግል የሚገጥምህ!! ይህ ሲሆን ታዲያ አሃ በኸይር ላይ ስለሆንኩ ነው እንደ ብለህ እንዳትተኛ! ራስህን እንዳትሸውድ ቀብር ብቻህን ነው የምትገባው የቂያማ ቀን ራቁትህን የምትመጣው ራስህ በሰረሃው ስራ ምክንያት ፍርድ ልታገኝ ነው።
አላህን የምትሸውደው አምላክ አይደለም እየቻልክ መደበቂያ ያገኘህ መስሎህ ብትደበቅ!
يعلم خائنة الأعين وما تخفي الصدور
(አላህ) የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል፡፡ [ ሱረቱ አል-ሙእሚን - 19 ]
وَلَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ وَنَعْلَمُ مَا تُوَسْوِسُ بِهِ نَفْسُهُ ۖ وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ الْوَرِيدِ
ሰውንም ነፍሱ የምትጎተጉተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡ [ ሱረቱ ቃፍ - 16 ]
https://t.me/Abdurhman_oumer/4934
👆
እወቁ! ንቁ! በጥሩ እንደማዘዝና በመጥፎ እንደመከልከል እንዲሁም እንደ ሰለፍዮች አንድነት የሰይጣንን ወገብ የሚሰብር የለም። በጥሩ ማዘዝና በመጥፎ መከልከል በሚለው ዙሪያ “የሰለፍያ እውነታ!” መጽሐፍ ላይ በተቻለኝ ዳስሻለሁ! የአላህ ፈቃዱ ከሆነ በሚዲያም የምመለስበት ይሆናል። ይሄ ጉዳይ ምን ያህል ትልቅ ጉዳይ እንደሆነ ስትረዱ ሰይጣንማ ለምን አይታገልም ትላላችሁ!!
አላህን በጣም የሚያስደስትና ሰይጣንን በጣም የሚያበሳጭ ሰው ወንጀል ሰርቶ ቶብቶ የሚመለስ ነው።
አላህን በሁሉም ጉዳይ ላይ ጠንካራነትንና በሀቅ ላይ ጽናቱን እንለምነዋለን!
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abdurhman_oumer/5853
.