cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የዘወትር ምንባብ

ይህ ቻነል በቤተ ክርስትያን የግጻዌ መጽሐፍ መሰረት የየዕለቱን የእግዚአብሔር ቃል ለማካፈል በማሰብተከፈተነል ነው። ሃሳብ አስተያየት ካለችሁ በ@ መስጠት ይቻላል

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
516
Suscriptores
Sin datos24 horas
-57 días
-430 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

“የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት።” — ዳንኤል 10፥13
Mostrar todo...
“ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።” — ዳንኤል 10፥21
Mostrar todo...
“በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል።” — ዳንኤል 12፥1
Mostrar todo...
“የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር፦ ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም።” — ይሁዳ 1፥9
Mostrar todo...
“በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥” — ራእይ 12፥7
Mostrar todo...
የሕይወት ሥነ ሥርዓት (29) ቀጠሮ ያለማክበር ችግር በዚህ ዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ቀጠሮዎች አሉ ። ከወዳጅ ጋር ያለ ቀጠሮ አለ ። በዚህ ቀጠሮ ውስጥ ታማኝ አለመሆን ወዳጅን ሊያሳጣ ይችላል ። ወዳጅን ማጣት በፍቅር ረሀብ መቀጣት ነው ። በቤተ ክርስቲያን ውግዘት የሚባለው ተመክሮ ተዘክሮ እንቢ አልመለስም ያለውን ሰው መለየትና ፍቅር በማጣት እንዲቀጣ ማድረግ ነው ። ፍቅርን ማጣት ወይም ወዳጅን ማሳዘን ራስን እንደ ማውገዝ ነው ። የፍርድ ቤት ቀጠሮ አለ ። የፍርድ ቤት ቀጠሮ የሚያስጠይቅ ፣ በምክንያት የማይቀርበት ነው ። ወደ ፍርድ ቤት በሄድን ጊዜ እንፈራለን ። አንድ ቀን እንደ እኛ ችሎት ፊት የሚቆም ምድራዊ ዳኛ እንዲህ ካስፈራን ሰማያዊው ዳኝነት ብርቱ ነውና ከግፍ መራቅ ይገባናል ። የፍርድ ቤት ቀጠሮ በብዛት ይከበራል ። የሥራ ቀጠሮ አለ ። የሥራ ቀጠሮ አንድ ሠራተኛ የሚመዘንበት የመጀመሪያው መለኪያ ነው ። ለሥራ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮ አርፍዶ የሚመጣ ራሱን በራሱ ከዚያ ዕድል ለይቷል ። በአንድ ቀን አቋሙ ቀጣይ ዘመኑን አውቀውታልና ሊቀጥሩት አይፈልጉም ። ቀጠሮ ስንሰጥ የሰጠነው ቃላችንን ነው ። ቃል የእግዚአብሔር ስም ነው ። የወልድም የኩነት መጠሪያው ነው ። ቃል ብርቱ ነገር ነው ። ቀጠሮ ከመሐላና ከጥብቅ አንቀጽ ጋር የሚወዳደር ነው ። ቀጠሮዎች በተለያየ ምክንያት እንቅፋት ይገጥማቸዋል ። በዚህ ዘመን ላይ ያሉ ወጣቶች የሁሉም ነገር ሥርና ቅርንጫፍ ገንዘብ እየመሰላቸው ይሳሳታሉ ። ወዳጅንም በገንዘብ እንደሚያመጡት ያስባሉ ። በገንዘብ የሚያስቅ ሰው ይገኝ ይሆናል ፣ የሚያስደስት ወዳጅ ግን አይገኝም ። በገንዘብ የሚከብብ ሰው ማግኘት ይቻላል ፣ ውስጥ የሚገባ የልብ ወዳጅ ግን አይገኝም ። ቀጠሮዎች ከሚሰረዙበት ምክንያት አንዱ ገንዘብን ማስበለጥ ወይም ምን አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ሊሆን ይችላል ። ፍቅር ግን ምን እሰጣለሁ እንጂ ምን አገኛለሁ ብሎ የሚያሰላ አይደለም ። ደስታ ያለው በመቀበል ሳይሆን በመስጠት ውስጥ ነው ። መርሳት የቀጠሮ እንቅፋት ነው ። መርሳት በዝንጉነት ጠባይ ፣ ብዙ አጀንዳና ወዳጅ በማብዛት ፣ ነሆለል ሰው በመሆን ፣ ሌላ ጊዜም በበሽታ የተነሣ የሚከሰት ነው ። መርሳትን ግን በጽሑፍና በደወል ማሸነፍ ይቻላል ። እየመረጥን የምንረሳ ከሆነም የእኛ ችግር ነው ። መርሳት ብዙ ጭንቀትና ውጥረት በማብዛት የሚመጣ በመሆኑ እኔ እኮ እረሳለሁ ብሎ የሚታለፍ አይደለም ። ያለ ዕድሜ የሆነ እንደሆነ ምንድነው ችግሬ ብሎ መጠየቅና መልሱን መፈለግ ያሻል ። አለማንበብ የመርሳትን ችግር ያመጣል ። ከሰዎች ጋር አለመገናኘትና አለማውራት መርሳትን ይወልዳል ። ወዳጅን ቀጥሮ ማናገር ራስን የማከምና የመፈወስ ትልቅ ዘዴ ነው ። ብዙ ውጥረቶች ይቀላሉ ። የመኖር ፍላጎት እየጨመረ ይመጣል ። ያለንን ነገር በደስታ መጠቀም ይቻላል ። ተቀጣጥሮ ስልክ መዝጋት ይህ የጠባይ ዝቅታ ውጤት ነው ። ይህን የሚያደርጉ አገልጋይ ነን የሚሉም አሉ ። እንዲህ የኮሩበት አገልግሎት አንድ ቀን እየፈለጉም አያገኙትም ። አገልግሎትም ጡር አለው ። ሁልጊዜ ሊመቸን አይችልምና አስቀድመን ማሳወቅ ይገባናል ። ሰውን ከሰው አወዳድረን መቅረት ግን ነውር ነው ። የሁሉም ሰው ክብሩ እግዚአብሔር ነው ። ስለዚህ ሰው ሁሉ እኩል ነው ። አስድመን የሰጠነውን ቀጠሮ ማክበር ይገባል ። አንዳንድ ሰዎችን ተቀይመናቸዋል ወይም እነርሱን ማግኘት እየጎዳን ተቸግረን ይሆናል ። ይህንን በግልጥ ነግረን ማረም ወይም ቀጠሮ አለመያዝ ተገቢ ነው ። ሰው ለሰላሙ ዋጋ መክፈል አለበት ። ሰላማችንን ሠውተን የምናደርገው ግንኙነት ውስጣችንን እየጨረሰው ይመጣል ። ደግሞም የሚያኖረን እግዚአብሔር ነውና የሚያውኩንን የተቀየምናቸውን ሰዎች በግልጽ መንገርና መፍታት አስፈላጊ ነው ። ቀጠሮአችንን ለማሳካት አለመቻላችንን መንገር ክብረት ነው ። እንዲሁ መቅረት ግን ያ ሰው ለእኛ ያለውን አመለካከት ዝቅ እንዲያደርግ ያስገድደዋል ። በመጀመሪያ ይበሳጭብናል ፣ ቀጥሎ ለእኛ ያሰበውን ትልልቅ ነገሮች መሰረዝ ይጀምራል ። ማንም ሰው ዋጋ የሚከፍለው ለአክባሪው ነው ። ሰዎች ቀጥረውን ቢቀሩ አንዳንድ ጊዜ ለበጎ ሊሆን ይችላል ። ሰብቅ ይዘውብን እየመጡ ከሆነ ለቀጣይ አንድ ዓመት ሰላማችንን ሊሰርቁት ነውና ቢቀሩ ይሻላል ። ወረኞችን አሉህና አሉሽ ማለት የሚወዱትን አለመቅጠርና አለማግኘት መልካም ነው ። ወሬውን እስኪነግሩን እንቅልፍ የላቸውም ፣ እኛ ሰምተን እንቅልፍ ስናጣ ግን ያን ጊዜ ይተኛሉ ። አምልኮተ እግዚአብሔርና ቃለ እግዚአብሔር በምንሰማበት ሰዓት ቀጠሮ መያዝ ክልክል ነው ። ካልሞትን በቀር ቤተ ክርስቲያን መቅረት የለብንም ። ስንሞትም የምንቀበረው እዚያው ነው ። በቀጠሮአችን ሰዓት ወዳጅነታችን እንዲቀጥል የማንስማማባቸውን ርእሶች መተው ይገባናል ። ክርክር አንዳንድ ጊዜ እኔ የበላይ ልሁን የሚያሰኝ የሥጋ ሥራ ነውና ፍቅርን ይጎዳል ። ቀጠሮን የሚጎዳው ሌላው ነገር ማርፈድ ነው ። አንዳንድ ማርፈድ የመቅረት ያህል ነው ። የአበሻ ቀጠሮ የሚባል የለም ። ቀጠሮ ፣ ቀጠሮ ነው ። ማርፈድን መዘናጋት ፣ መተኛት ፣ ጊዜን መለካት አለመቻል ፣ ወቅቱን አለማገናዘብ የሚወልደው ነው ። ማርፈድ ተጨማሪ ወጪ ነው ። አርፍደው አውሮፕላን ያመለጣቸው ተጨማሪ ወጪ ያወጣሉ ። ጓደኛቸው ተበሳጭቶባቸው የሄደባቸው ተጨማሪ ይቅርታና ማሳመን ያስፈልጋቸዋል ። ማርፈድ ጠባዩ ነው መባል ሞት ነው ። ሙሽሮች በሰዓቱ መድረስ የጠሩትን ሰው ማክበር ነው ። እስከማውቀው ድረስ ምግብ እያዩ ሙሽራን መጠበቅ የአገራችን ባሕል አይደለም ። እየበሉ እየጠጡ መጠበቅ ተገቢ ነው ። በሰርጉ ቀን ያረፈደ ፣ ትዳሩም ላይ ብዙ ማርፈድ ይገጥመዋል ። ሰውን ማክበር ለራሳችን ያለን ክብር ውጤት ነው ። ቀጠሮ ማክበር ራስን ማክበር ነው ። ያደጉ አገሮች ሁሉ ያደጉት ቀጠሮን ወይም ሰዓትን በማክበር ነው ። ሰዓት ዋጋ ያጣው እኛ አገር ነው ። ማደግ ፈልገን በሰዓት ቀልደን አይሆንም ። ባለጉዳይ የቀደመው ሠራተኛ ማፈር አለበት ። አገር በዘፈን ሳይሆን በመሥዋዕትነት ታድጋለች ። ሌላ አገር ያለን ይመስል አንዷን አገራችንን ማጎሳቆል ሊበቃ ይገባዋል ። ይቀጥላል ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም.
Mostrar todo...
ሉቃስ 24 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵¹ ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። ⁵² እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ ⁵³ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ። እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በሰላም አደረሳችሁ 😍🙏
Mostrar todo...
የሕይወት ሥነ ሥርዓት (28) 14. ቀጠሮ አክብር ቀጠሮ የተጀመረው በእግዚአብሔር ነው ። ይህ ዓለም በመለኮታዊ ቀጠሮ የተፈጠረ ዓለም ነው ። ዘመን የሌለው ጌታ ዘመንን ለሰዎች ሰጠ ። ሰው በበደል በወደቀ ጊዜ ለመዳን ቀጠሮ ተሰጠው ። ሰው ከእግዚአብሔር ሳይለይ ከእግዚአብሔር ተለየ ። ለሆዱ እንጀራን ፣ ለአፍንጫው እስትንፋስን የሚያገኘው ከእግዚአብሔር ነው ። እንኳን በምድር በሲኦልም የሚኖረው በእግዚአብሔር ሕይወት ነው ። ጌታችን ወደ ምድር የመጣው ለሰዎች እንጀራ ለመስጠት ሳይሆን ራሱ ኅብስተ ሕይወት መሆኑን ለመግለጥ ነው ። 5500 ዘመን ሰው እንጀራ እየበላ ነበር ። ነፍሱ ግን ስደተኛና ረሀብተኛ ነበረች ። ሰው እግዚአብሔርን የሚክደው ከእግዚአብሔር የተቀበለውን እስትንፋስ መልሶ ሳይሆን በእግዚአብሔር ሕይወት ላይ ቆሞ ነው ። “በማን ላይ ቆመሽ ማንን ታሚያለሽ!” ይባላል ። እርሱ የካዱትን ቢክድ ኖሮ ፍጥረት በምድር ላይ ባልቆየ ነበር ። እግዚአብሔር ቀጠሮን መጀመሩ ብቻ ሳይሆን የሺህ ዘመናት ቀጠሮን የሚሰጥ አምላክ ነው ። የሰው ልጅ በምድር ላይ ከሚኖረው ዕድሜ የረዘመ ቀጠሮ ተሰጠው ። ይህ ብዙ ፍቺ አለው ። የመጀመሪያው የሰው የህልውናው መጨረሻ መቃብር አይደለም ። በሥጋው ያጣውን በነፍሱ ሊክሰው የሚችል አምላክ አለው ። ዛሬ በሥጋ ጉድለታችን ስንፈራ ስንጨነቅ ጌታ ግን አይጨነቅም ። ምክንያቱም በሰማይም ሊጋብዘን ይችላልና። እኛ ምንም ሳናደርግላቸው የሄዱት ወገኖቻችን የእግር እሳት ሆነውብን ይሆናል ። ደግነታችንን መቃብር ገድቦት ይሆናል ። በሰማያዊው ዓለምም የሚሰጥ አምላክ ግን ሞት ገደቡ አይደለም ። ከሰው ዕድሜ የሚረዝመው ቀጠሮ ለምን ተሰጠ ካልን ከ5500 ዘመን በኋላም የሚኖረው ሰው አዳም ስለሆነ ነው ። ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ ያላቸው እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚኖሩ ሆነው አይደለም ። የእነርሱን ሥራ የሚያስቀጥል ሁሉ ሐዋርያ ስለሆነ በደቀ መዛሙርቶቻችሁ ላይ አድሬ እሠራለሁ ማለቱ ነው ። ስለዚህ ጴጥሮስ ይህን ሲሰማ ብሞትም ሕያው ነኝ ፤ የመንፈስ ልጅ አለኝ ብሎ ይጽናናል ። የአዳምን ቀጠሮ ክርስቶስ ሲሰቀል የነበሩ ሁሉ ፍጻሜውን አይተዋል ። አንድ አዳም ነን ። አንድ ስለሆንን የአዳም በደሉና ጥፋቱ አግኝቶናል ። የአዳም መዳኑና ካሣው ነጻ አውጥቶናል ። በሞት አንድ ሁነን በኑሮ መለያየታችንና መከፋፋታችን ይገርማል ። የእግዚአብሔርን ቀጠሮ ልዩ የሚያደርገው የማይረሳ አምላክ መሆኑ ነው ። እኛ ቀጠሮአችንን በመርሳት ፣ ባለመመቸት ፣ ባለመፈለግ ፣ በመስጋት ፣ ሌላውን ጉዳይ በማስበለጥ እንሰርዛለን ። እግዚአብሔር ግን መርሳት የሌለበት የሕሊናት ሁሉ ባለቤት ነው ። አይመቸውም አይባልም ፣ እርሱ የሌለውን ና ብሎ መጥራት የሚችል አምላክ ነው ። በሰጠው ተስፋ አይጸጸትምና አልፈልጋችሁም አይለንም ። የሚሽረው የለምና አይሰጋም ። የዘላለም ጉዳዩ እኛ ነንና የእርሱ ውዶች ነን ። እግዚአብሔር ቀጠሮን የሚያከብር አምላክ ነው ። የእርሱ ተከታዮች እርሱን ይመስላሉና ቀጠሮን ያከብራሉ ። “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤” ገላ 4፡4 ። አንተም ቀጠሮ መስጠትን ልመድ ። ምክንያቱም አንተ እንደ ተመቸህ ያ ሰው አይመቸውምና በድንገት ውረድ ፍረድ አትበል ። ዓመት ሙሉ የረሳኸውን ሰው ዛሬ ስታገኘው አልላቀቅህም ብለህ ስሜታዊ አትሁን ። ቀጠሮ መስጠት ለሰውዬው ምቾት ፣ ለጉዳዩ ክብደት ነው ። ቀጠሮ በሰጠህ ጊዜ ወዳጅህ ተኝቶ እንዲያድር ወይም ተዘጋጅቶ እንዲመጣ ርእሱን ንገረው ። የምፈልግህ በዚህ ምክንያት ነው ብለህ አሳውቀው ። ምናልባት ስጦታ ልትሰጠው ሊሆን ይችላል ። ለምን እንደ ቀጠርከው ካላወቀ ግን የሞት ያህል ያስጨንቀዋል ። ስትቀጥረውም አንተም እርሱም የማትረበሹበት ቦታ ይሁን ። ያ ወዳጅህ የማይፈልገው ሰው ካለ ይዘህበት አትሂድ ። የማይፈልገውና ከዚህ በፊት ተነጋግራችሁበት የተዘጋ ነገርን አታንሣበት ። የቀጠሮውን ርእስ ለመንገር የማይቻል ከሆነ በሻይ ቡና ርእስ አግኘው ። እየጋበዝህ ግን ነገር አታብላው ። በምድር ላይ እጅግ ባለጌ የሆኑ ሰዎች ምግብ እየጋበዙ ነገር አብረው የሚያበሉ ናቸው ። አንድ ኪሎ ሥጋ ጋብዘው አራት ኪሎ ሚጥሚጣ ነስንሰው ይሄዳሉ ። ቀጠሮ ስትሰጥ ያ ሰው ተጨንቆ እንደሆነ ለማረጋገጥ “ይመችሃል ወይ?” ብለህ ጠይቅ ። ምቾቱን ፍላጎቱን የምትነካበት ሰው እየጠላህ ይመጣል ። ሰው ከምንም በላይ ነጻነቱን የሚወድድ ፍጡር ነው ። ቀጠሮ እጅግ አድርገህ አክብር ። ቀጠሮህን እንዳትረሳ የሚያስታውሱ ማስታወሻዎች አድርግ ። በጸሎት ስፍራህ ወይም በቢሮህ ጠረጴዛ ላይ የቀጠሮህን ወረቀት አስቀምጥ ። ሊያነቃህ የሚችል ደወል ሙላ ። ሴቶች በማስታወስ ጎበዝ ናቸውና አስታውሱኝ ብለህ ንገራቸው ። ቀጠሮ ማክበር የመንፈሳዊነትም የሥልጣኔም መለኪያ ነው ። ምናልባት ያ ሰው ቢያረፍድ ደግሞም ቢቀር ጊዜህን እንዳታባክን የምትሠራውን ሥራ ፣ የምታነበውን መጽሐፍ ይዘህ ውጣ ። ቀረ ብለህ አትቀየም ። ለሰውም አትናገር ። ምናልባት በአደጋ ተሰናክሎ ይሆናል ። ወደ ቀጠሮህ ስትሄድ ጸልይ ። ንግግር ከመጀመራችሁ በፊትም ከዳኅፀ ልሳንና ልቡና እንዲሰውርህ አምላክህን ለምን ። በይበልጥ ለመጨዋወት ቀጠሮ መያዝ መልካም ነው ። አንዳንድ ጉዳዮች በስልክም ሊያልቁ ይችላሉና ለሁሉም ነገር ቀጠሮ ይያዝልኝ አትበል ። ዶሮ በጋን እንዳይሆንብህ ። ሰው እፈልግሃለሁ ሲልህም አትኩሮት ስጥ ። ምናልባት ላለመኖር እየወሰነ ይሆናል ። ያንተ ቀጠሮ የሰውን ዕድሜ ማስቀጠል ከቻለ ከዚህ በላይ የምትኖርበት ዓላማ የለም ። ዛሬ ቢሞት ለመቅበር ይመችሃል ፣ ተጨንቄአለሁ ሲልህ አይመቸኝም አትበለው ። ያለችው ቀን ይህች ብቻ ልትሆን ትችላለች ። ብቻ ቀጠሮ አክብር ። ክቡርነትህን ማሳያ ነው ። ወላጆችህ ቀጠሮ ይከብዳቸው ነበር ። ሌሊቱን ሙሉ ሳይተኙ ሲንቆራጠጡ ያድሩ ነበር ። የሰውን ዋጋ ስላወቁ ዕድሜ ተሰጣቸው ። ለሰው ክብር የሌለው ዘመኑ አጭር ነው ። ይቀጥላል ዲያቆን አሸናፊ መኰንን ግንቦት 26 ቀን 2016 ዓ.ም.
Mostrar todo...
ዮሐንስ 21 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው። ¹⁶ ደግሞ ሁለተኛ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ¹⁷ ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ፦ ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም፦ በጎቼን አሰማራ። ¹⁸ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ አንተ ጐልማሳ ሳለህ ወገብህን በገዛ ራስህ ታጥቀህ ወደምትወደው ትሄድ ነበር፤ ነገር ግን በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፥ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል አለው። ¹⁹ በምን ዓይነት ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህን አለ። ይህንም ብሎ፦ ተከተለኝ አለው። 😍 @gitsawei 😍🙏
Mostrar todo...
+++ "ስንሞት ያመናል እንዴ?" +++ ሕፃናት መጠየቅ ይወዳሉ። አንዴ መጠየቅ ከጀመሩ በኋላ ደግሞ ከእነርሱ የሚወጣው "ለምን ሆነ?" የሚለው የጥያቄ ዝናብ እንዲህ በቀላሉ ቶሎ የሚያባራ አይደለም። እኛም በእነዚህ ጥያቄዎቻቸው ቶሎ ተሰላችተን ወይም ተበሳጭተን ይሆናል። ይሁን እንጂ ጉዳዩ ግን የሕፃናቱ አዲስ አእምሮ ራሱን የሚያሳድግበትና የነገ ማንነታቸውን የሚቀርጽበት ወሳኝ ሂደት ነው። የነገ ወጣቶችን ማንነት የሚቀርጹት ዛሬ "ለምን?" እያሉ ለሚጠይቁ ሕፃናት የምንመልሳቸው መልሶች ናቸው። ስለዚህ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል። በጠና የታመመ ሕፃን ልጅ ያላት አንዲት እናት ነበረች። ይህች እናት በምትችለው ሁሉ ልጇን አሳክማና ተንከባክባ ለማዳን ብትጥርም፣ ይህ ልፋቷ ግን ሊሳካላት አልቻለም። ልጇን የያዘው በሽታ መድኃኒት ስላልነበረው ወደ ሞት አፋፍ አቅርቦታል። ታዲያ አንድ ቀን ሕፃኑ ልጅ እናቱን እንዲህ ሲል ጠየቃት :- "እናቴ፣ መሞት ምን ይመስላል? ስንሞት ያመናል እንዴ?" በእናትየው ዓይኖች እንባዎች ሞሉ። ፊቷም በኃዘን ደፈረሰ። የረሳችው ነገር ያለ ይመስል "ቆይ መጣኹ" ብላ ሮጣ ከክፍሉ ወጣች። ብቻዋን ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ልጇ የጠየቃትን ጥያቄ መመለስ እንዳለባት ብታውቅም ለዚህ ለጋ አእምሮ እንዴት አድርጋ መልስ እንደምትሰጥ ግራ ገብቷታል። እንደ ምንም ራሷን አረጋግታና ጥበቡን እንዲሰጣት ወደ ፈጣሪዋ ተማጽና ተመልሳ ወደ ልጇ ክፍል ገባች። ሕፃኑ መልሱን በጉጉት ይጠብቃል። እናትየውም የውስጧን ኃዘን ለመሰወር ለይምሰል ፈገግ ብላ እንዲህ አለችው "ልጄ፣ ታስታውሳለህ አንድ ጊዜ ጎረቤት ያለ ጓደኛህ ቤት ሄደህ ስትጫወት አምሽተህ ስለደከመህ በዚያው እንቅልፍ ወስዶህ ነበር። ከዚያም በማግስቱ ግን ስትነቃ ራስህ ያገኘኸው በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ ስለሆነ 'እንዴት እዚህ መጣኹ?' እያልክ ስትጠይቀኝ ነበር። እኔም አባት ወደዚያ መጥቶ በጥንካራ ክንዶቹ ተሸክሞህ የአንተ ወደ ሆነው ቤትህ እንዳመጣህ ነግሬሃለኹ። አስታወስክ?" ልጅየው :- "አዎን እናቴ" እናትየው ቀጠለች :- "የኔ ልጅ፣ ሞትም እንደዚሁ ነው። እኛ መኖሪያችን ባልሆነች በዚህ ዓለም ሆነን እናንቀላፋለን። የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር ደግሞ ብርቱ በሆኑ እጆቹ አቅፎ ወደ ሰማይ ይወስደናል። ከዚያም ነግቶ እንደ ገና ስንነቃ ራሳችንን በገዛ አባታችን ቤት ውስጥ እናገኘዋለን" አለችው። እውነት ነው! ሞት ለክርስቲያኖች ሁሉ የሚኖረው ትርጉም ይህ ነው። ከእግዚአብሔር ተልከን ወደዚህ ዓለም እንደ መጣን ወደ እርሱ መመለሳችን ደግሞ የማይቀር ነው። ሞት ማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ድንኳን" ብሎ ከገለጸው ከጊዜያዊው መቆያችን ወደ እውነተኛው መኖሪያ አገራችን መሸጋገር ነው። በ2ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ግሪካዊው ፈላስፋ አርስጣደስ በጊዜው አዲስ ሃይማኖት ስለሆነበት ስለ ክርስትና እና ይህ የክርስትና እምነት በሞት ላይ ስላለው እሳቤ ለአንድ ወዳጁ በጻፈለት ደብዳቤ ላይ እንዲህ የሚል ንግግር አስፍሮ ነበር። "ከክርስቲያኖቹ ውስጥ አንድ ጻድቅ የሆነ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ ምእመናኑ ደስ ይሰኛሉ። ለፈጣሪያቸውም ምስጋናን ያቀርባሉ። ያም ሰው ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ቅርብ ሥፍራ የተሸጋገረ ይመስል ሰውነቱን በመዝሙራትና በምስጋና አጅበው ይሸኙታል" ይላል። ክርስትና እንዲህ ነዋ! ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ክርስቲያኖች በሞት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ እይታ ሲናገር "ከእኛ መካከል አንድ ሰው በሞተ ጊዜ፣ የማያምነው ሬሳ ሲያይ ክርስቲያኑ ግን ያንቀላፋ ሰውነት ይመለከታል። ያላመነው "የሞተው ሰው ሄደ" ይላል። በርግጥ በዚህ እኛም እንስማማለን። ነገር ግን ወደ የት እንደሚሄድም እናውቃለን። የሚሄደው ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ እንዲሁም ሌሎች የቅዱሳን ማኅበር ወደ አሉበት ነው። በኋላም ተስፋ መቁረጥ ባለበት እንባ ሳይሆን፣ በክብርና በማንጸባረቅ እንደሚነሣ እናስባለን!" +++ "ለባሪያዎችህ ሞት የለባቸውም ፍልሰት እንጂ" +++ ዲያቆን አቤል ካሳሁን [email protected]
Mostrar todo...