cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፍኖተ ክርስትና

ይህ ቻናል ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ብቻ የምናወራበት ነው

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
325
Suscriptores
Sin datos24 horas
-57 días
-3930 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#ዝክረ_ቅዱሳን_ታኅሣሥ_13/፲፫ (ስንክሳር)
እንኳን ለፈታሄ ማህጸን #ለሊቀ_መላእክት_ለቅዱስ_ሩፋኤል ለቅዳሴ ቤቱና ተአምር ላደረገበት ዕለት፣ ለታላቁ አባት #ለአባ_መቃርስ_ገዳማዊ ዓመታዊ ለዕርገታቸው መታሰቢያ፣ ለመነኮስ #ለአቡነ_አብራኮስ_ገዳማዊ ለዕረፍታቸው፣ ለሰማዕት #ለቅዱስ_በጽንፍርዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"
#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ሩፋኤል
➯ታኅሣሥ ዐስራ ሦስት በዚህች ቀን በዚህች ዕለት ፈታሄ ማህጸን ሊቀ መልአክት ቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱና ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፡፡ ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው፡፡ "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ ጦቢት 12፡15፡፡ ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል መልአከ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ 6፡3፡፡ ➯ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ ሄኖክ 10፡13፡፡ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ጦቢት 3፡8-17፡፡ ➯ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ሄኖክ 3፡5-7፡፡ በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሄኖክ 2፡18፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነዉ፡፡ ➯የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ "ፈታሄ ማህጸን" ይባላል-እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡ እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡ ዳግመኛም "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ" ይባላል-ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው፡፡ ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል-ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው፡፡ እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል-ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው፡፡ ➯ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል እስኪፈፀም ድረስ በከበረ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ ዘመን በምድረ ግብጽ ውስጥ ከእስክንድርያ ውጭ በታናፀች አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ከአሳ አንበሪ ላይ የታነፀች ነበር፡፡ ነገር ግን በወደቡ አጠገብ ከነበረ ግዙፍ አንበሪ ጀርባ ላይ መታነጿን ቀድሞ ያነጿት ሰዎች ቢሆኑ ከካህናትም ቢኾን ያወቀ አልነበረም፡፡ ➯ያ አንበሪም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ በከበደው ጊዜ ፈጽሞ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከአሸዋማው መሬት ላይ በባህሩ ዳርቻ የታነፀች ይህች ቤተ ክርስቲያንም ከመሰረቷ አናወጻት፡፡ ያን ጊዜ ትልቁም ትንሹም ወንዱም፣ ሴቶችም፣ የተሾሙ ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ሕዝቡም ሁሉ ደነገጡ ታወኩ፡፡ አሣ አንበሪው ግን መንቀሳቀሱን አልተወም፡፡ በመንቀሳቀሱም የቤተ ክርስያኗ ሕንፃ እኩሌታ ይሰነጠቅ ዘንድ ጀመረ፣ ምድርን ተናወፀች፣ ንጉስና፣ ሊቀ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ዲያቆናቱም፣ ህዝቡም፣ ሁሉም ካሉበት በባህሩ ወደብ ከተሰራች ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መናወጥ የተነሳ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላያቸው ወረደ፡፡ ያ አንበሪ ግን በባህሩ ውስጥ ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም በጀርባው ላይ ነበረች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሉትም ሁሉ ያ አሳ አንበሪ ወደ ባሕሩ ውስጥ ሊያሰጥመን ነው ሲሉ አሠቡ፡፡ ያን ጊዜም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስዕል ፊት በጽኑ አለቀሱ፡፡ በአንድ ቃልም "ገናናው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ርዳታህ ፈጥኖ ይደርስልን ዘንድ በቅድስት ቤተክርስቲያን ወደተሰበሰብን ወዳጆችህ ተመልከት" እያሉ ይጸልዩ ጀመር፡፡ ➯ያንጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ ያችን ቤተክርስቲያን በብሩሃት ክንፎቹ እንደደመና ጋረዳት፡፡ በእጁ በተያዘ የብርሃን በትረ መስቀሉ ያን ኣሣ አንበሪ ወገቶ "በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል ከቦታህ ሳትንቀሳቀስ እስከትውልድ ፍፃሜ ዘመን ለዘለአለም ትኖር ዘንድ አዝዝሃለሁ" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያኗን ከነመዓዘኗ ከግርግዳዎቿ ከመሠዊያዋ በውስጧ ተተክለው ካሉት ሁሉ ጋር ከጀርባው ላይ እያለች ያንን አሳ አንበሪ ወግቶ በያዘበት ብርሃናዊ በትረ መስቀሉ ወደቀድሞው የባሕሩ ወደብ ጎተተው፡፡ ያንጊዜም ግንቡ ቦታውን ሳይለቅ እርስ በእርሱ ተጣበቀ፡፡ ➯ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አሣ አንበሪውን በቀድሞ ሥፍራው ያቺን ቤተክርስቲያን በቀደመ መሠረቷ ላይ አጽንቷቸዋልና፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም አዳኝ የሆነ የጌታው የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ጠርቶ ከሞት እንዳዳናቸው ሁሉም አስተዋሉ፡፡ በድንቅ ተዓምራቱ የዳኑ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በሊቀመላእክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ላይ አድሮ ድንቅ ተዓምራቱን ስለገለጸላቸው የቅዱስ ሩፋኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክም በዓለም ሁሉ በየአውራጃዎቹም ተሰማ፡፡ የቅርብም የሩቅም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የለመኑትን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ የነገሩትን ያማልዳቸው ዘንድ በውስጧ ይጸልያሉ፡፡ በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀንም ተአምራቶቹ ከተፈጸመባቸው ዕለታት አንዷ ናት፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ተከናውኗል፡፡ @kidstsilas comment : @ye24lig
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
፮ ❤️አርሴማ ነይ ነይ ወደእኛ!🙏🙏🙏 እንኳን ለሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን! ጥበቃዋም አይለየን አሜን!🙏🙏🙏 @kidstsilas comment : @ye24lig credit : @Finotetebebbb
Mostrar todo...
👍 4🙏 2
Photo unavailableShow in Telegram
"ለፅንሰትከ። "ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ: በብሥራተ መልአክ ለተፀነስከው መፀነስህና በወርኃ ታኅሣሥ ለተወለድከው መወለድ ሰላም እላለሁ። "ክቡሩ አባት ሆይ: ስለዓሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደ ግብር እንደ ገበረ እኔም ፍጹም ልባዊ የሆነ እጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ። "የጻዲቁ አቡነ ገብረ _መንፈስ_ቅዱስ ምልጃ በረከት ረድኤታቸው ከኛ ጋር ትሁን አሜን 🙏 እንኳን አደረሳችሁ። @kidstilas comrnt : @ye24lig
Mostrar todo...
👍 3
#ዝክረ_ቅዱሳን_ታኅሣሥ_4/፬ (ስንክሳር)
እንኳን ለሊቀ ሐዋርያት ለቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ለተመሰገነ #ለቅዱስ_እንድርያስ_ሐዋርያ በምስክርነት ላረፈበት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"
#ቅዱስ_እንድርያስ_ሐዋርያ
➯ለዚህም ቅዱስ ይሰብክ ዘንድ ዕጣው በልዳ ሀገር ወጣ ከእርሷም ብዙዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ነበር አንደበቱ የሚጥም በሥራው ሁሉና በአምልኮቱ የተወደደ ያማረ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞና አብሮት ነበር ሐዋርያ እንድርያስም ከፍ ካለ ቦታ ላይ ወጥቶ ጣዕም ባለው አንደበቱ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንዲአነብ አዘዘው። ➯የጣዖታት ካህናትም የሐዋርያ እንድርያስን መምጣት በሰሙ ጊዜ አማልክቶቻቸውን ይረግሙ እንደሆነ ሊጣሏቸው ሽተው የጦር መሳሪያቸውን ይዘው መጡ። ➯በዚያንም ጊዜ ፊልሞና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከወርቅና ከብር የሰው እጅ ሥራ የሆኑ የአሕዛብ አማልክቶቻቸው አፍ አላቸው አይናገሩም፣ ዐይን አላቸው አያዩም፣ ጆሮ አላቸው አይሰሙም፣ አፍንጫ አላቸው አያሸቱም፣ እጅ አላቸው አይዳስሱም፣ እግር አላቸው አይሔዱም፣ በጉሮሮአቸውም አይናገሩም፣ የሚሠሩአቸውና የሚአምኑባቸው ሁሉ እንደእነርሱ ይሁኑ እያለ ሲያነብ ሰሙት። ➯ስለ ቃሉ ጣዕምና ስለ ንባቡ ማማር ልባቸው ከክህደት ማሠሪያ ተፈታ ወደ ቤተ ክርስቲያንም ገብተው ከሐዋርያ እንድርያስ እግር በታች ሰገዱ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አመኑ እርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው ከእሳቸውም ጋር ጣዖትን ከሚያመልኩ ውስጥ ብዙዎች አምነው ተጠመቁ። ➯በዚያ ወራትም እንዲህ ሆነ በልዳ አገር አቅራቢያ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ቄስ ነበረ ለእርሱም አንድ ልጅ አለው እርሱም ከባልንጀራው ጋር ሲጫወት በድንገት ገደለው የሟች አባትም ልጄን የገደለ ልጅህን አሳልፈህ ስጠኝ ሲል ቀሲስ ዮሐንስን ያዘው ቀሲስ ዮሐንስም የሀገር ሰዎችን ሔጄ ሐዋርያ እንድርያስን እስከማመጣው ዋስ ሁኑኝ እርሱ የሞተውን ያነሣልኛልና ብሎ ለመናቸው እነርሱም በተዋሱት ጊዜ ቀሲስ ዮሐንስ ወደ ሐዋርያ እንድርያስ ሒዶ ችግሩን ሁሉ ነገረው። ➯ሐዋርያ እንድርያስም ቀሲስ ዮሐንስን እንዲህ አለው ከእኔ ዘንድ የሚጠመቁ ብዙ ሕዝቦች ስላሉ ከአንተ ጋር እሔድ ዘንድ አይቻለኝም ግን ደቀ መዝሙሬ ፊልሞና አብሮህ ይሒድ እርሱ የሞተውን ያስነሣልሃል አለው። ➯ሐዋርያ እንድርያስም ከቄሱ ጋር ሒዶ የሞተውን ያስነሣለት ዘንድ ፊልሞናን አዘዘው ወደ ከተማውም ሲቀርቡ ቄሱንና ፊልሞናን ሰዎች በከተማው ውስጥ ሁከት ሁኗልና አገረ ገዥው እንዳይገድላችሁ ወደ ከተማ አትግቡ አሏቸው። ፊልሞናም እንዲህ አለ እኔ የመምህሬን ትእዛዝ መተላለፍ አልችልም የሞተውን ለማንሣት እሔዳለሁ እንጂ መኰንኑ ቢገድለኝም መምህሬ እንድርያስ መጥቶ እኔንም አስቀድሞ የሞተውንም ያስነሣናል። ➯ሲገባም መኰንኑን ኒቆሮስን ተገናኘውና ፊልሞና እንዲህ አለው ሀገርን ለምን ታጠፋለህ የሾሙህ ከክፉ ነገር ሁሉ ሀገርን ልትጠብቅ አይደለምን መኰንኑም ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል አለ ወታደሮችንም ይዛችሁ ሰቅላችሁ ግረፉት አላቸው ወታደሮችም ይገርፉት ዘንድ ይዘው ሰቀሉት። ➯ፊልሞናም ኒቆሮስ የተባለውን መኰንን እንዲህ አለው የበደልኩት በደል ሳይኖር ለምን ሰቅለህ ትገርፈኛለህ እኔ ታናሽ ብላቴና ስሆን ደቀ መዝሙሩን እኔን ሰቅለው ሲገርፉኝ ይመለከት ዘንድ ለመምህሬ እንድርያስ ማን በነገረው አለ ። ወደ ወታደሮችም ፊቱን መልሶ እንዲህ አላቸው ከውስጣችሁ የሚራራና የሚያዝንልኝ የለምን በመሰቀልና በመገረፍ እንዳለሁ ሒዶ ለመምህሬ እንድርያስ ስለ እኔ ይነግረው ዘንድ አለ ከቃሉ ጣዕም የተነሣ ወታደሮች ተሰብስበው መጥተው አለቀሱ። ➯በዚያንም ጊዜ አዕዋፍ ሁሉ መጥተው እኛን ላከን ብለው ተናገሩት ድምቢጥ ቀርባ እኔ በአካሌ ቀላል ነኝና እኔን ላከኝ አለችው አንቺስ አመንዝራ ነሽ ከወገንሽ በመንገድ አንዱን ያገኘሽ እንደሆነ ከርሱ ጋር ትጫወቺአለሽ ፈጥነሽ አትመለሽም አላት ከዚህም በኋላ ቁራ ቀርቦ እኔን ላከኝ አለው ፊልሞናም እንዲህ አለው አንተም በቀድሞ ዘመን በተላክህ ጊዜ ለአባታችን ኖኅ የመልእክቱን መልስ አልመለስክም አለው። ➯ፊልሞና ግን ርግብን ጠርቶ እንዲህ አላት እግዚአብሔር የዋሂት ብሎ ስም ያወጣልሽ ከአዕዋፍ ሁሉ የተመረጥሽ ወገን አንቺ ለአባታችን ኖኅ በመርከብ ውስጥ ሳለ መልካም ዜና አድረሰሽለታልና አባታችን ጻድቅ ኖኅም ባርኮሻልና አሁንም ወደ ልዳ ከተማ ወደ መምህሬ እንድርያስ ሔደሽ ንገሪው ሰቅለው እየገረፉኝ ነውና ወደ እኔ ወደ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞና ይመጣ ዘንድ። በዚያን ጊዜ ርግብ ሒዳ ለሐዋርያ እንድርያስ ነግራ የመልእክቱን መልስ ይዛ ተመለሰች የተባረከች ርግብም ለፊልሞና መምህርህ እንድርያስ እኔ እመጣለሁና አይዞህ በርታ ብሎሃል አለችው። ➯በዚያንም ጊዜ ርግብ በሰው ቋንቋ ለፊልሞና ስትነግረው ኒቆሮስ መኰንን ሰማት እጅግም አደነቀ ፈጥኖ ተነሥቶም ራሱ በእጁ ፊልሞናን ፈትቶ ከተሰቀለበት አወረደው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አመነ። ➯ሰይጣን ግን ቀና በመኰንኑ ሚስት ልቡና አድሮ አሳበዳትና ልጅዋን ገደለች አገልጋዮቹም ሒደው የሆነውን ሁሉ ለመኰንኑ ነገሩት ፊልሞናም አትፍራ አይዞህ አለው። ከዚህም በኋላ ርግብን ጠርቶ ወደ መኰንኑ ቤት ሒጂ እንዳይሸበሩ በጸጥታ እንዲቆዩ ንገሪያቸው አላት ርግቢቱም ሒዳ ፊልሞና እንዳዘዛት ለሕዝቡ ነገረቻቸው ሕዝቡም ርግቢቱ በሰው ቃል ስትናገር በሰሙ ጊዜ እጅግ አድንቀው ፊልሞና ወዳለበት ተሰበሰቡ። ➯በዚያንም ጊዜ ሐዋርያ እንድርያስ ደረሰ አስቀድሞ የሞተውን ያስነሣው ዘንድ ደቀ መዝሙሩ ፊልሞናን አዘዘው እርሱም ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን በመጸለይ ከሞት አስነሣው ሁለተኛም ወደ መኰንኑ ቤት ሔዱ ሐዋርያ እንድርያስም የመኰንኑን ልጅ እናቱ የገደለችውን አስነሣው የመኰንኑንም ሚስት አዳናት ከእርሷ የወጣውንም ያንን ጋኔን ይዞ በሰው ሁሉ ፊት ምድርን ከፍቶ ወደ ጥልቅ አዘቅት አሰጠመው። ➯ከዚህም በኋላ ሐዋርያ እንድርያስ ርግብን ጠርቶ ዕድሜሽ ስንት ነው አላት እርሷም ስምንት ዓመት ነው አለችው ። እርሱም ለደቀ መዝሙሬ ስለታዘዝሽ ወደ ዱር ሒጂ ለዓለም ሰዎች ከመገዛት ነጻ ሁኚ አላት ወዲያውኑ ሔደች ሕዝቡም ይህን ድንቅ ሥራ አይተው አምነው ሁሉም የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቁ። ➯ከዚህም በኋላ ከእርሳቸው ዘንድ ወጥቶ አክራድ አክሲስ አክሳስያ ሴኒፎሮስም ወደ ተባሉ አገሮች ሒዶ አስተማረ ከሐዋርያ በርተሎሜዎስም ጋር ተገናኝቶ ጋዝሪኖስ ወደ ሚባል አገር በአንድነት ሔዱ የሀገር ሰዎች እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከተመለሱ ድረስ ረዳት ከተደረገላቸው ገጸ ከልብ ጋር ገብተው ወንጌልን ሰበኩ ድንቅ ተአምራትንም አደረጉ። ➯ከዚህም በኋላ ሐዋርያ እንድርያስ ወደ ሌሎች አገሮች ሒዶ አስተማረ በፍጻሜውም ወደ አንዲት አገር ገብቶ ቅዱስ ወንጌልን ሰበከ የዚያች አገር ሰዎች ግን እጅግ የከፉ ስለሆኑ ትምህርቱን አልተቀበሉትም። ➯ከቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስም ድንቅ ተአምራትን ስለአዩ ያመኑ አሉ ያላመኑ ግን ወደእነርሱ እንዲመጣና እንዲገድሉት በቅዱስ እንድርያስ ላይ ክፉ ምክርን መክረው በተንኩል ወደርሱ መልእክተኞችን ላኩ መልእክተኞችም ወደ ቅዱስ እንድርያስ ሲደርሱ ማራኪ የሆነ ትምህርቱን ሰሙ ፊቱንም ብርሃን ሁኖ አዩትና ክብር ይግባውና በጌታችን አመኑ ደቀ መዝሙሮችም ሆኑት ወደላኳቸውም አልተመለሱም። .........
Mostrar todo...
👍 3
......... ➯ሁለተኛም በእሳት ሊአቃጥሉት ተማከሩና ተሰብስበው ወደርሱ ሔዱ እርሱ ግን የልባችሁን ክፋት ትታችሁ ትድኑ ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እመኑ ይህ ካልሆነ ግን ለእኔ ያላችኋት ይቺ እሳት እናንተን ትበላለች አላቸው። ቃሉንም ባልሰሙ ጊዜ ከሰማይ እሳት ወርዳ እንድታቃጥላቸው ክብር ይግባውና ጌታችንን ለመነው ወዲያውኑ እሳት ወርዳ አቃጠለቻቸው በዚያች አገር አውራጃዎች ሁሉ ዜናው ተሰማ እጅግም ፈርተው ብዙዎች ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ። ➯የጣዖታት አገልጋዮች ግን ይህን ሁሉ ድንቅ ተአምራት አይተው አላመኑም ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስን ሊገድሉት ፈለጉት እንጂ። ከዚህም በኋላ ተሰብስበው መጡና ቅዱስ ሐዋርያ እንድርያስን ይዘው ወሰዱት ታላቅ ግርፋትንም ገርፈው በከተማው ሁሉ ራቁቱን አዙረው ከወህኒ ቤት ጨመሩት በማግሥቱ የሚሰቅሉትን ሰው ልማዳቸው እንዲሁ ነውና ሰው ሊገድሉ በሚሹ ጊዜ ወስደው በእንጨት ላይ ይሰቅሉታል እስከሚሞትም ድረስ በደንጊያዎች ይወግሩታል። ➯በዚያችም ሌሊት የተመሰገነ ሐዋርያ አባታችን እንድርያስ እንደ ፊተኞቹ እሳት ወርዳ እንድትበላቸው ክብር ይግባውና ጌታችንን ክርስቶስን ለመነው ክብር ይግባውና ጌታችንም ተገለጠለትና ከዚህ ዓለም የምትለይበት ጊዜ ደርሷልና አትዘን አለው ሰላምታም ሰጥቶት ከእርሱ ተሠወረ የተመሰገነ የሐዋርያ እንድርያስም ልቡናው ፈጽማ ደስ አላት። ➯ንጋትም በሆነ ጊዜ ወስደው በዕንጨት ላይ ሰቀሉት እስከ ሞተ ድረስም በደንጊያዎች ወገሩት አማንያን ሰዎችም መጥተው ሥጋውን ወስደው ገንዘው ቀበሩት ከእርሱም ታላላቅ የሆኑ አስደናቂዎች ተአምራት ተገለጡ። ➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ በሐዋርያ እንድርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ታኅሣሥ 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፦ 1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 2.አባ ጻዕ 3.አባ ያዕቆብ 4.ቅድስት ታኦድራ ወርኀዊ በዓላት፦ 1.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ 2.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 3.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ (ሰማዕት) ➯ "ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሲናገር ሰምተው ጌታ ኢየሱስን ተከተሉት። ጌታ ኢየሱስም ዘወር ብሎ: ሲከተሉትም አይቶ፦ "ምን ትፈልጋላችሁ?" አላቸው። እነርሱም፦ "ረቢ ወዴት ትኖራለህ?" አሉት። ትርጓሜው "መምህር ሆይ!" ማለት ነው። "መጥታችሁ እዩ" አላቸው። መጥተው የሚኖርበትን አዩ። በዚያም ቀን በእርሱ ዘንድ ዋሉ። አሥር ሰዓት ያህል ነበረ። ከዮሐንስ ዘንድ ሰምተው ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ።" (ዮሐ. ፩፥፴፯-፵፩)                 ወስብሐት ለእግዚአብሔር                   ወለወላዲቱ ድንግል          ወለመስቀሉ ክቡር አሜን። @kidstsilas comment : @ye24lig ታኅሣሥ 4 ቀን
Mostrar todo...
👍 3💯 1
#ዝክረ_ቅዱሳን_ታኅሣሥ_3/፫ (ስንክሳር)
እንኳን አምላክን ለወለደች #ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም (በዓታ ማርያም) ወደ ቤተ መቅደስ ለገባችበት ቀን፣ ለሊቀ መላእክት #ለቅዱስ_ፋኑኤል ለበዓሉ መታሰቢያ ቀን፣ እና #ለጻድቁ_አቡነ_ዜና_ማርቆስ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"
#በዓታ_ለእግዝእትነ_ማርያም
➯ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና። ➯እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ። ➯ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ። ➯ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም በመኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲፈጸምላት እርሷ ለእግዚአብሔር የተሰጠች የስዕለት ልጅ ናትና ለሚጠብቃት ይሰጧት ዘንድ ካህናት እርስበርሳቸው ተማከሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ በርሷ ላይም ይደርስባታል ብለው ስለፈሩ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይተዋት ዘንድ ለእርሱ ትክክል መስሎ አልታያቸውም ስለዚህም ሊጠብቃት ለሚገባው በእርሷ ላይ እጮኛ ሊአኖሩ ወደዱ። ➯ከዚህም አስቀድሞ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልጄ ማርያም ሆይ አንቺ እንዳደግሽና ለአካለ መጠን እንደደረስሽ ዕወቂ ልትታጪ ትወጃለሽን እግዚአብሔርን የሚፈራ መልካም የሆነ የተባረከ ጐልማሳ እንፈልግልሽን ወይም በሕይወትሽ ዘመን ሁሉ በቤተ መቅደስ ተቀምጠሽ እግዚአብሔርን ልታገለግዪው የምትሺ ከሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሰው በሚደርስብሽ ወራት ወደ ቤተ መቅደስ ደጅ ከመግባት ትጠበቂ ዘንድ በኦሪቱ የተጸፈውን የርግማን ሥርዓት በአንቺ ላይ እንሠራለን አላት። ➯ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊታችሁ ነኝ አባትና እናት የሉኝም ስሙ ቡሩክ ምስጉን ከሆነ ከእግዚአብሔር በታች በእናትና አባት ፈንታ እናንት ናችሁና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደምታውቁ አድርጉ ብላ መለሰች። ➯ካህናቱና ማኅበሩም ሁሉ ዘካርያስን ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ ስለዚች ብላቴና ማርያም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት ዘካርያስም ገብቶ ሲጸልይ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ ወጥተህ ከዳዊት ወገን ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሁሉ ወንዶች ሰብስብ የየአንዳንዱንም በትር ከስሙ ጋር ውሰድ ወደ ቤተ መቅደስም በምሽት አግብተህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይበት በነጋ ጊዜም በትሮቻቸውን አውጣ እግዚአብሔርም በበትሩ ላይ ምልክት ለገለጠልህ ለዚያ ሰው ማርያምን ተቀብሎ ሊጠብቃት ይገባዋል። ➯ካህኑ ዘካርያስም ወጥቶ አንድነት ለተሰበሰቡት ሕዝብ የእግዚአብሔር መልአክ የነገረውን ነገራቸው በዚያንም ጊዜ ከዳዊት ወገን ጐልማሳም ቢሆን ሽማግሌም ቢሆን ሚስቱ የሞተችበት ሁሉ በኢየሩሳሌም ወደአለ ቤተ መቅደስ ይሒድ እያሉ ዓዋጅን ዙረው የሚናገሩ በእስራኤል አገር ሁሉ ላከ። ➯ከዳዊት ወገን የሆነ ጠራቢው ዮሴፍም በሰማ ጊዜ በትሩን ይዞ ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ካህኑ ዘካርያስም የሁሉንም በትሮች ተቀብሎ ስማቸውን በላያቸው ጻፈ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሆነ ዘካርያስም በትሮችን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ውጭ ቁመው ይጸልዩ ነበር ዘካርያስም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ ለየአንዳንዱ በትራቸውን አውጥቶ ሰጠ ጠራቢው ዮሴፍም በትሩን ሊቀበል በቀረበ ጊዜ ከእርሷ ነጭ ርግብ የመሰለች ተገለጠች እየበረረችም ሒዳ በጠራቢው ዮሴፍ ራስ ላይ ተቀመጠች ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ አይተው እጅግ አደነቁ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ➯ዘካርያስም ዮሴፍን ዮሴፍ ሆይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እንደ ተናገረ ድንግል ማርያምን ወደ ቤትህ ወስደህ ጠብቃት አለው ዮሴፍም ቅድስት ድንግል ማርያምን ከካህናት እጅ ተቀበላት በእርሱም ዘንድ ኖረች። ከዚህም በኋላ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ስለ እግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሁኖ ስለመወለዱ በዮሴፍ ቤት አበሠራት። @kidstsilas comment : @ye24lig
Mostrar todo...
👍 4
#ዝክረ_ቅዱሳን_ታኅሣሥ_2/፪ (ስንክሳር)
እንኳን #ለቅዱሳን_ሠለስቱ_ደቂቅ (#አናንያ፣ #አዛርያ፣ #ሚሳኤል) ለመታሰቢያቸው ቀን፣ በላይኛው ግብጽ ከሚኖሩ ሰዎች ወገን ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_አባ_ሖር ለእረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"
#ቅዱሳን_ሠለስቱ_ደቂቅ (#አናንያ፣ #አዛርያ፣ #ሚሳኤል)
➯ታኅሣሥ ሁለት በዚህች ቀን ናቡከደነፆር ከአባታቸው ጋር ለማረካቸው ሦስት ለሆኑ ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም ልጆች ለአናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል እግዚአብሔር ኃይልን አደረገላቸው። ➯እሊህም ለይሁዳ ንጉሥ ለኢዮአቄም ልጆቹ ናቸው። ዳንኤልም የእኅታቸው ልጅ ነው። በምርኮ ጊዜም ከእስራኤል ልጆች ጋራ ተማርከው ወደ ባቢሎን ወረዱ። ➯ከእስራኤል ልጆች ምርኮ ውስጥ በመብልና በመጠጥ እያስተማረ አሳድጎ በሠራዊቱ መካከል ጭፍሮቹ ያደርጋቸው ዘንድ ነውር ነቀፋ የሌለባቸውን ወጣቶች ንጉሥ መረጠ። እሊህም ከተመረጡት ውስጥ የተቆጠሩ ሆኑ የእኅታቸው ልጅ ዳንኤልም ነበር። ምግባቸውን በሚሰጧቸው ጊዜ አረማውያን ከአረዷቸው ውስጥ መብላትን አልወደዱም። ከንጉሥ ማዕድም ከሚመጣ ከሥጋው እንዳያበላቸውና እንዳያጠጣቸው አለቃውን ለመኑት። ➯እግዚአብሔርም በባለሟሎች አለቃ ፊት ቸርነቱን አደረገላቸው። የባለሟሎች አለቃም ንጉሡ ጌታዬን እፈራዋለሁ የምትበሉትንና የምትጠጡትን ምግባችሁን ስለ አዘዘ ከባልንጀሮቻችሁ እናንተን ከስታችሁ ቢያያችሁ ንጉሥ ራሴን ይቀጣኛል አላቸው። ➯በእነርሱ ላይ የተሾመ አሚሳድን እንዲህ አሉት እኛን ባሮችህን ዐሥር ቀን ፈትነን ከምድር ዘር ሽምብራን ይስጡን እንበላ ዘንድ ውኃንም እንጠጣ ዘንድ። ቃላቸውንም ሰምቶ ዐሥር ቀን ፈተናቸው ዐሥር ቀንም ከአለፈ በኋላ የንጉሡን ማዕድ ከሚመገቡ ከእነዚያ ልጆች ይልቅ ሰውነታቸው ወፍሮ መልካቸውም አምሮ ታየ። ➯ከዚህ በኋላ አሚሳድ የሚበሉትን ምግብ የሚጠጡትን ወይን እየወሰደ ለአራቱ ሁሉ ልጆች ሽምብራ ይሰጣቸው ነበር። እግዚአብሔርም ዕውቀትንና ጥበብን መጻሕፍትን በማንበብ ሁሉ ማስተዋልን ሰጣቸው። ከዚህ በኋላ ንጉሥ ያዘዘው ቀን በተፈጸመ ጊዜ ወደርሱ አመጡአቸው የባለሟሎችም አለቃ ወደ ንጉሡ ወደ ናቡከደነፆር አገባቸው። ➯ንጉሡም ጠየቃቸው በሰው ሁሉ ዘንድ እንደ አናንያና እንደ ዳንኤል እንደ ሚሳኤልና እንደ አዛርያ ያለ አልተገኘም። በንጉሡም ፊት ቆሙ። ንጉሡም የፈለገውን የምክርና የጥበብን ነገር ሁሉ በግዛቱ ካሉ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሰዎች ሁሉ ይልቅ በነሳቸው ዘንድ ዐሥር እጥፍ አገኘ። ንጉሡም እጅግ ወደዳቸው በባቢሎን አገር ሁሉ ላይ ገዢዎች አድርጎ ሾማቸው። ➯ንጉሥም ጣዖትን ከወርቅ ባሠራ ጊዜ ሰዎችን ሁሉ እንዲሰግዱለት አዘዛቸው። ሦስቱ ልጆችም ለዚያ ጣዖት ባልሰገዱ ጊዜ የሚቀኑባቸው ወደ ንጉሥ ነገር ሠርተው በንጉሥ ፊት አቀረቧቸው። ስለ አልሰገዱለትም ጠየቃቸው። እነርሱም "እኛስ ለሠራኸው ለወርቅ ምስል አንሰግድም" አሉት። ንጉሥም ተቆጥቶ ከምትነድ የእሳት ምድጃ ውስጥ ይጨምሩአቸው ዘንድ አዘዘ። ➯እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ የእሳቱን ነበልባል አጠፋው በጥዋት ጊዜ እንደሚቀዘቅዝ በእሊህ በሦስቱ ልጆች ዘንድ እንደ ጥዋት ውኃ ቀዝቃዛ አደረገው። ከዚያም የእሳቱ ነበልባል አርባ ዘጠኝ ክንድ ያህል ከፍ ከፍ ብሎ በውጪ ያሉትን አቃጠላቸው። እሊህን ሠለስቱ ደቂቅን ግን ምንም አልነካቸውም። ➯ንጉሥም ይህን ድንቅ ሥራ አይቶ በፊታቸው ሰገደ። የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔርንም አመነ። ለእሊህም ልጆች ሹመታቸውን ከፍ ከፍ አድርጎ ክብርን ጨመረላቸው። ከዚህም ዓለም የሚወጡበት ጊዜ ሲደርስ በበዐታቸው እየጸለዩ ሳሉ ሰግደው ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ➯ወዲያውኑ ታላቅ ንውጽውጽታ በባቢሎን አገር ሆነ። ንጉሡም ፈርቶ ስለ ምን ይህ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ብሎ ዳንኤልን ጠየቀው። ነቢይ ዳንኤልም "ይህ ሦስቱ ልጆች ስለ አረፉ ከዓለም ለመውጣታቸው ምልክት ነው።" ብሎ ነገረው። ንጉሡም ወደርሳቸው ደርሶ ታላቅ ኀዘንን አዘነ። ከዝሆን ጥርስም ሦስት ሣጥኖችን እንዲሠሩላቸው፣ በሐር በግምጃ ልብሶች ገንዘው ቅዱሳኑን በሣጥኑ ውስጥ እንዲያኖሩአቸው አዘዘ። ንጉሡ እንዳዘዛቸውም አደረጉ። ➯ሁለተኛም የወርቅ ሣጥን ሠርተው እርሱ በሚሞት ጊዜ ሥጋውን በውስጡ አድርገው በከበሩ ሠለስቱ ደቂቅ መካከል እንዲያኖሩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉለት። @kidstsilas comment : @ye24lig
Mostrar todo...
👍 3
#ዝክረ_ቅዱሳን_ታኅሣሥ_1/፩ (ስንክሳር)
እንኳን #ለነቢይ_ቅዱስ_ኤልያስ በእስራኤል ፊት ለተገለጠበት፣ ለእስራኤላዊ #ለቅዱስ_ናቡቴ ለዕርፍቱ፣ ለእስክንድርያ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_አባት_ዮሐንስ ለዕረፍቱ፣ ለጋዛ ቅዱስ አባት #ለኤጲስቆጶስ_ጴጥሮስ ለዕረፍቱ፣ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"
#ቅዱስ_ኤልያስ_ርዕሰ_ነቢያት
➯በዚህችም በታኅሣሥ አንድ ቀን በእስራኤል ፊት ነቢይ ኤልያስ የተገለጠበት ነው። ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ ቶና ነው። ➯ስለርሱም እንዲህ ተነገረ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ። እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን፣ በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን፣ ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ። ➯በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ ነገሥት ተጽፎአል። ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል። ➯በኋላ ጊዜም ስለሚሆነው ሞቱ ራእይን በሕይወቱ ያየ ዮሐንስ ከኄኖክ ጋር እንደሚመጣና ሐሳዊ መሲሕን እንደሚቃወሙት ተአምራትንም እንደሚያደርጉ ተናግሮአል። ሁለቱ የዘይት ዕንጨቶች በምድር ላይም የተሾሙ በእግዚአብሔር ፊት የሚያበሩ ሁለት መብራቶች ናቸው አለ። ➯ከጠላቶቻቸውም ወገን ሊጣላቸው የወደደውን እሳት ከአፋቸው ወጥታ ታጠፋቸዋለች የሚጠሏቸው እንዲህ ይጠፋሉ። ትንቢት በሚናገሩበት ወራት በምድር ላይ ዝናም እንዳይዘንም ይዘጓት ዘንድ በሰማይ ላይ ሥልጣን አላቸውና ዳግመኛም ደምን ያደርጉት ዘንድ በውኃው ላይ ሥልጣን አላቸው የፈለጉትን ያህል በመቅሠፍቱ ሁሉ ምድርን ያስጨንቋታል። ➯ምስክርነታቸውንና ትንቢታቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከባህር የወጣው አውሬ ከእሳቸው ጋር ይጣላል ድል ነስቶም ይገድላቸዋል። አስከሬናቸውንም ፍጥሞ በምትባል በታላቂቱ አገር ያስጥለዋል ይችውም በምሥጢር ሰዶም ግብጽ የተባለች ጌታቸው የተሰቀለባት ናት። ➯አስከሬናቸውንም ሕዝብና አሕዛብ በሀገርም ያሉ ነገዶች ሦስት ቀን ተኩል ያዩታል አስከሬናቸውንም በመቃብር ይቀብሩት ዘንድ አያሰናብቱም። በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በእነርሱ ሞት ደስ ይላቸዋል እርስበርሳቸውም በደስታ እጅ መንሻ ይሰጣጣሉ እሊህ ሁለቱ ነቢያት በምድር በሚኖሩ ሰዎች መከራ አጽንተውባቸዋልና ይላሉ። ➯ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሕይወት መንፈስ መጥታ ታድርባቸዋለች ተነሥተውም በእግራቸው ይቆማሉ በሚያዩዋቸው ላይም ጽኑ ፍርሀት ይሆናል። ➯ከወደ ሰማይ ቃል መጥቶ ወደዚህ ውጡ ይላቸዋል ከዚህ በኋላ ጠላቶቻቸው እያዩአቸው በደመና ያርጋሉ። በዚያችም ሰዓት ጽኑ መነዋወጥ ይሆናል የዚያችም አገር ዐሥረኛ እጅዋ ይጠፋል በዚያም መነዋወጥ ሰባት ሽህ ሰዎች ይሞታሉ የቀሩት ግን ደንግጠው የሰማይ አምላክን ፈጽመው ያመሰግናሉ። @kidstsilas comment : @ye24lig
Mostrar todo...
👍 4
#ዝክረ_ቅዱሳን_ህዳር_30/፴ (ስንክሳር)
እንኳን #ለንጉሥ_አፄ_ገብረ_መስቀል ለዕረፍቱ መታሰቢያ፣ ለሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_አባት_አካክዮስ ለዕረፍቱ፣ #ለቅዱሳን_ቆዝሞስና_ድምያኖስ ቤተ ክርስቲያናቸው ለከበረችበት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"
#አፄ_ገብረ_መስቀል_ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
➯ህዳር ሠላሳ በዚህች ቀን ጻድቁ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ዕረፍቱ ነው። ➯ዐፄ ካሌብ የናግራንን ሰማዕታት ደም ተበቅሎ በድል ከተመለሰ በኋላ በአቡነ ጰንጠሌዎን እጅ መንኩሶ ገዳም ከገባ በኋላ ልጁ ገብረ መስቀል ነገሠ፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል በእውነትና በቅንነት ከነገሠ በኋላ አመራሩ ከአህጉሪቷ ጽንፍ እስከ ጽንፍ ደረሰ፡፡ በዘመኑም ሁሉ መንግሥቱን የሚቃወም አልተነሣም፤ እርሱም ቤተ ክርስቲያንን ከመሥራት በቀር ወደ ጦርነት የሄደበት ጊዜ የለም፡፡ መንግሥቱንም ይባርክለት ዘንድ ሠራዊቱን ይዞ ወደ አባታችን ወደ አቡነ አረጋዊ ዘንድ ደብረ ዳሞ ሄደና በፊቱ ሰግዶ ‹‹አባቴ ሆይ! እኔን ባሪያህን፣ መንግሥቴንና ሕዝቤን ሠራዊቴንም ሁሉ ባርክ›› እያለ አጥብቆ ማለደው፡፡ አባታችን አረጋዊም "የአባቶችህን የዳዊትንና የሰሎሞንን መንግሥት የባረከ፣ የአባትህን የካሌብንም መንግሥት የባረከ እግዚአብሔር የአንተንም መንግሥት ይባርክ…" ብለው ባረኩት፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ዐፀ ገብረ መስቀል አቡነ አረጋዊን የት ቦታ ላይ ቤተክርስቲያን እንደሚሠራ ጠይቋቸው ካሳዩት በኋላ ሲሠራ ሁለት ዓመት የፈጀበት ግሩም ቤተክርስቲያን ሠራላቸውና 12 የወርቅና የብር መስቀሎችን ጨምሮ ብዙ ንዋያተ ቅድሳቶችንና ሥጦታዎችን ሰጣቸው፡፡ ጳጳስም አስመጥቶ አስባረካትና ከማኅበረ በኩር ያመጣውን በወርቅ በብር የተለበጠች የእመቤታችንን ታቦት በውስጧ አስገባ፡፡ ጳጳሱና ንጉሡ ዐፄ ገብረ መስቀልም አቡነ አረጋዊን "ቀድሰህ አቁርበን" ብለውት ይቀድስ ዘንድ በገባ ጊዜ መላእክት ሙቀት ያልተለየው ኅብስትና ወይኑን በጽዋ ለቅዳሴው የሚያስፈልገውንም ሁሉ ከሰማይ አወረዱለትና ቀድሶ ሲያበቃ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡ ➯ከዚህም በኋላ ንጉሡ ዐፄ ገብረ መስቀል ከተራራው ጫፍ በሚወርድበት ጊዜ አባታችንን "ይህን የተራራውን መውጫ መሰላል ላፍርሰው ወይስ ልተወው?" አለው፡፡ አባታችንም "ለልጅ ልጅ መታሰቢያ እንዲሆን ይህን ድንቅ ሥራ እያየ በፍጥረቱ ሁሉ አንደበት እግዚአብሔር ይመሰገን ዘንድ የደረጃውን መሰላል አፍርሰው፣ ነገር ግን ስለዘንዶው ጅራት ፋንታ ገመድ አብጅ" አለው፡፡ ንጉሡም እንደታዘዘው የደረጃውን መሰላል አፈረሰውና ወደ ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፡፡ ጻድቁ ንጉሥ በዐፄ ገብረ መስቀል ካበረከተልን ትልቅ ውለታው ውስጥ አንዱ ዛሬ በዩኔስኮ የተመዘገበውን የመስቀል በዓልን በአደባባይ እንዲከበር ያደረገ መሆኑ ነው፡፡ በዘመኑም ካህናቱ ሕዝቡ ሁሉ አደይ አበባ ይዘው ወደ አደባባይ በመውጣት በያሬዳዊ ዝማሬ የመስቀልን በዓል ያከብሩ ነበር፡፡ ➯የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብርሃኗ የሆነ ነገር ግን እርሷ እንደሚገባው መጠን ያላከበረችው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በዚህ ጻድቅ ንጉሥ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት የነበረ ነው፡፡ አብረውም ብዙ ታሪኮችን ፈጽመዋል፡፡ ገዳማትን ላይ በመዟዟር ቅዱስ ያሬድ ዜማን ሲያስተምር ንጉሡ ደግሞ የቤተ ክርስቲያንን ይዞታ ያስፋፉና ቋሚ መተዳደሪያ ይሰጡ ገዳማቱን ያጠናክሩ ነበር፡፡ አቡነ አረጋዊ ደግሞ አብረው ምኩስናን ያስፋፉ ነበር፡፡ ሦስቱም ይህን ተግባራዊ እንዳደረጉ ለማሳያ ይሆን ይሆን ዘንድ ቅዱስ ያሬድ 3 ዓመት ዝማሬ መዋሥዕት ያስተማረባትንና ዛሬም ድረስ ማስመስከሪያ የሆነችውን እጅግ ጥንታዊቷን ዙር አባ ጽርዓ አርያም አቡነ አረጋዊ ገዳምን እንደምሳሌ ማየት እንችላለን፡፡ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ያሬድ በዘንዶ ታዝለው ዓምባው ላይ ከወጡ በኋላ ለንጉሡ ለዐፄ ገብረ መስቀል ደግሞ ተራራውን ባርከው ከፍለው መንገድ አበጅተውላቸው ወደ ዓምባው ወጥተው ሦስቱም በዚያ በጋራ ኖረው ብዙ መንፈሳዊ ሥራን ሠርተዋል፡፡ ➯ጻድቁ ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ከተስዓቱ ቅዱሳን ጋር ሆኖ ብዙ መንፈሳዊ ሥራን ሠርቷል፡፡ ሌላው በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ከነበሩት ቅዱሳት አንስት ውስጥ እናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዋነኛዋ ናት፡፡ ይኽችውም ቅድስት ከልጅነቷ ጀምራ በምግባር በሃይማኖት፣ በተጋድሎ በትሩፋት ያጌጠች ናትና ንጉሠ ነገሥቱ ዐፄ ገብረ መስቀል በሁለመናዋ የተመሰገነች መሆኗንና ዝናዋን ስለሰማ "በጸሎትሽ አስቢኝ" በማለት ከአገልጋዮቹ ውስጥ እርሷን እንዲያገለግሏት 174 አገልጋዮችን ልኮላታል፡፡ ለነገሥታት ሚስቶች የሚደረገውን በሐርና በወርቅ የተሠሩ ልብሶችና ጫማ ልኮላታል፡፡ ዐፄ ገብረ መስቀል በጽድቅ ሕይወት እየተመላለሱ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የዋሉት ውለታ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ገርዓልታ አካባቢ ከዱጉም ሥላሴ በእግር የ2 ሰዓት መንገድ ርቀት ላይ የቅዱስ ዐፄ ገብረ መስቀል አስደናቂ ፍልፍል ቤተ መቅደስ ይገኛል፡፡ @kidstsilas comment : @ye24lig
Mostrar todo...
👍 4
#ዝክረ_ቅዱሳን_ህዳር_26/፳፮ (ስንክሳር)
እንኳን #ለአቡነ_ኢየሱስ_ሞዓ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ፣ ለፃድቁ አባታችን #ለአቡነ_ሀብተ_ማርያም ለእረፍታቸው መታሰቢያ፣ #ለሀገረ_ናግራን_ሰማዕታትና ለአባታቸውም #ለቅዱስ_ኂሩት ለመታሰቢያቸው ቀን፣ #ለቅዱስ_ቢላርያኖስ_ሚስቱ_ኪልቅያና_እኅቱ_ታቱስብያ በሰማዕትነት ላረፉበት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።
"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"
#ቅዱስ_አቡነ_ኢየሱስ_ሞዓ_ዘሐይቅ
➯ህዳር ሃያ ስድስት በዚህች ዕለት አቡነ ኢየሱስ ሞዓ ዘሐይቅ እረፍታቸው ነው። በጐንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ዳህና ሚካኤል በተባለው ቦታ ከአባታቸው ከዘክርስቶስና ከእናታቸው ከእግዚእ ክብራ በ1210 ዓ.ም ነው ተወለዱ። ዕድሜያቸው 3ዐ ዓመት እስከሚደርስ ከቤተሰቦቻቸው ትምህርተ ሃይማኖትንና ግብረ ገብን ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በ124ዐ ዓ.ም ይኼንን ዓለም በመተው ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ገቡ። በደብረ ዳሞ ገዳም መነኰሳቱን እየረዱ፣ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን እያጠኑ፣ ትምህርተ ቅዱሳት መጻሕፍትን እየገለበጡ ለሰባት ዓመታት ከቆዩ በኋላ የደብረ ዳሞ 3ኛ አበ ምኔት ከሆኑት ከአባ ዮሐኒ ምንኩስናን ተቀበሉ (1247 ዓ.ም)። ➯አንድ ቀን ሌሊት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደርሳቸው መጥቶ (ገድልህና ትሩፋትህ በዓለም ሕዝብ ሁሉ ትተህ የስምህ መክበርያ ወደሆነው ሐይቅ ወደ ተባለው ሥፍራ ሂድ) አላቸው። አባታችን "ቦታውን እንዴት ዐውቀዋለሁ" በማለት ቢጠይቁት "ተነሥ። ጉዞህን ጀምር ቦታውን እኔ አሳይሃለሁ" አላቸው። አባ ኢየሱስ ሞዓ በመልአኩ እንደታዘዙት ከበአታቸው ተነሥተው ተከተሉት። የብዙ ወራት መንገድ የሆነው ጐዳናም በስድስት ሰዓት አለቀላቸው። ➯በዚያን ወቅት ከሐይቅ ገዳም በስተ ሰሜን ወደነበረው ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ደረሱ። ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከመግባታቸውም በፊት ለ6 ወራት ያህል በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል። ያገለግሉበት በነበረው ቤተ ክርስቲያን ቀን ቀን ሕዝቡን ሲያስተምሩ በመዋል ሲመሽ ወደ ሐይቁ በመግባት ሲጸልዩ ያድሩ ነበር። በሐይቅ እስጢፋኖስና በዙርያው ለነበሩ አበውም ማታ ማታ አንድ ብርሃን ወደ ሐይቁ ሲገባ ጠዋት ጠዋትም ሲወጣ ይታያቸው እንደነበር ዛሬ በገዳማቸው የሚገኘው ገድለ ኢየሱስ ሞዓ ያስረዳል። ➯በመጨረሻም በገዳሙ አባቶች ልመናና በልዑል እግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ ሐይቅ ገዳም ገብተው አበምኔት ሆኑ። ሐይቅ እስጢፋኖስ ማለት ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ሲሆን የመሰረቱት ካልዕ ሰላማ የተባሉ ግብጻዊ ጻድቅ ናቸው፤ ገዳሙን ከሰሩ በኃላ የማንን ታቦት እናስገባ ብለው ሲያስቡ ቶራ የምትባል እንስሳ ጭነት ተጭና ከመካከላቸው ተገኘች፤ ጭነቱን አውርደው ቢያዩት በሐር ጨርቅ የተጠቀለለ ሁለት ታቦት አገኙ አንዱ የእስጢፋኖስ አንዱ የጊዮርጊስ " ይህንን ታቦት በእየሩሳሌም የሚኖሩ የተሰወሩ ቅዱሳን ከእግዚያብሔር ታዘው የላኩት ነው" የሚል ጽሑፍም አገኙ ይላል። ይህ ከሆነ ከ 400 ዘመን በኃላ ነው አባ እየሱስ ሞኣ ወደዚህ ቦታ የመጡት ለ 52 ዓመት ቀን ቀን መንፈሳዊ ስራቸውን ይሰራሉ ሌሊት ሌሊት ሐይቁ ውስጥ ቆመው ሲጸልዩ ያድራሉ። ➯አባ ኢየሱስ ሞዓ በሐይቅ እስጢፋኖስ በአበምኔትነት በቆዩባቸው 45 ዓመታት ከየገዳማቱ ቅዱሳን መጻሕፍትን በመገልበጥና በማስገልበጥ ብሎም በማሰባሰብ የመጀመርያው ዘመናዊ የቤተ ክርስቲያን ቤተ መጻሕፍት በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም እንዲቋቋም አድርገዋል። በዚሁ ገዳም ውስጥም የመጀመርያውን የቤተ ክርስቲያን ቋሚ ትምህርት ቤት በማቋቋም 8ዐዐ መነኮሳትን በትምህርተ ሃይማኖት አሠልጥነው በንቡረ ዕድነት ማዕረግ በመላ ሀገሪቱ እንዲሠማሩ አድርገዋቸዋል። ➯ከተማሪዎቻቸውም መካከል አቡነ ተክለ ሃይማኖት (ዘደብረ ሊባኖስ)፣ አባ ተክለሃይማኖት ያመነኮሱ አባት ናቸው። አባ ኂሩተ አምላክ (ዘጣና ሐይቅ)፣ አባ ጊዮርጊስ (ዘጋሥጫ)፣ አባ ዘኢየሱስ፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን (ዘደብረ ዳሬት) ጥቂቶች ናቸው። አፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት ያነፁት እርሳቸው ናቸው። ➯እንደዚህ ነው የመነኮሳት አባት እንጦንስ ነው እንጦንስ መቃርስን ወለደ መቃርስ ጳኩሚስን ጳኩሚስ አቡነ አረጋዊን አቡነ አረጋዊ አባ ዮሐኒን አባ ዮሐኒ የሐይቁን አባ እየሱስ ሞአን ወለዱ አባ ኢየሱስ ሞዓ ደግሞ ተክለሃይማኖትን ወለዱ። ➯በዮዲት ጉዲት ተጐድታ የነበረችው ሀገራችን ዳግም የወንጌሉ ብርሃን እንዲበራባት ሊቃውንት እንዲይነጥፉባት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት እንዳይቆነጻጸሉ፣ መነኮሳት አባቶች ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወርደው ገዳማትን እንዲያስፋፉ ያደረጉት አባ ኢየሱስ ሞዓ ናቸው። በተለይም የሐይቅ እስጢፋኖስ ያፈራቸው 8ዐዐ ሊቃውንት በመላዋ ሀገሪቱ በመሠማራታቸው ዛሬ የምናያቸውን አብዛኞቹን ገዳማትና ቅዱሳት መጻሕፍት አቆይተውናል። ➯አባታችን አባ ኢየሱስ ሞዓ ለ45 ዓመታት ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከቆዩ በኋላ ኅዳር 26/1292 ዓ.ም በዕለተ እሑድ በ82 ዓመታቸው ዐረፉ። በዚያች ዕለትም በቦታው የታየው ብርሃን ሀገሪቱን መልቷት እንደነበረ ገድላቸው ይመሠክራል። @kidstsilas comment : @ye24lig
Mostrar todo...
👍 4
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.