cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

በብእሲ

እንኳን ወደ በብእሲ የቴሌግራም ቻናል መጣችሁ። በቻናላችን ግጥም 📕አዳዲስ መፅሀፍት 🤗የታዋቂ ሰዎች ታሪክ 😌 ስዕሎች 📖አጫጭር ወጎች 🤗ጭውውት ና ትረካዎች ወደናንተ ይደርሳሉ። አብራችሁን ለመስራት እንዲሁም ማስታወቂያ እንድንሰራላችሁ የምትፈልጉ በራችን ክፍት ነው። 👇 @BebesiEthiopia

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
254
Suscriptores
Sin datos24 horas
-17 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

አንድ ቪዲዮ እያየሁኝ ነበረ 👇🏾 እዚህ ቪዲዮ ላይ ቃለ መጠይቅ የሚቀርብለት ሰው ከተወሰኑ አመታቶች በፊት ከትልቅ ድልድል ላይ በመውደቅ ራሱን ለማጥፋት ሲሞክር በሰዎች ርብርብ የተረፈ ሰው ነው "ራስህን ለማጥፋት ስትሄድ ምን እያሰብክ ነበር ከቤትህ የወጣኸው?" ሰውዬው ይመልሳል 👇🏾 “በወቅቱ እጅክ ከፍቶኝ ነበር: ከጎኔ ሰው አልነበረም: ኑሮም ከብዶኝ ነበር:: ከዚያም ከቤት ወጥቼ ራሴን እስከማጠፋበት ድረስ ባለው መንገድ ላይ ሰላም የሚለኝ ሰው: ፊቱ ላይ ፈገግታ የሚያሳየኝ ሰው: እንዴት ነህ የሚለኝ አንድ ሰው ካገኘሁኝ ራሴን አላጠፋም ብዬ ነበር" "እና ምን ሆነ ታዲያ?" "አንድም ሰላም የሚለኝ ሰው አልነበረም: አንድም ጥሩ ፊት ያሳየኝ ሰው አልነበረም" 👇🏾 ሰላም በሉ! ፈገግታን ስጡ ሰው ምን ውስጥ እያለፈ እንደሆነ አናውቅምና !🙌🏼❤️
Mostrar todo...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
Photo unavailableShow in Telegram
ጥያቄ፡- ዶ/ር ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋር ከ2 አመት በኻላ በድጋሚ ማውራት ጀምረናል፡፡ እናም ይቅርታ ተደራርገን አብረን እንድንሆን ጠየቀኝ እኔ ግን በፊት ካደረገው ነገር አንፃር ከልቡ መሆኑን ስለ ተጠራጠርኩኝ ጊዜ እንዲሰጠኝ ጠይቄዋለው እሱም የፈለኩትን ጊዜ ወስጄ እንድወስን ተስማምቷል። እኔ ግን እንዴት ብዬ እና ምን ተጠቅሜ ከልቡ እንደተፀፀተ እና በድጋሚ ታማኝነቱን እንደማያጓድል ማረጋገጥ እንዳለብኝ አላውቅም። ወይስ ግንኙነቱን ማደሱ ስህተት ነው? መልስ፡- አንድ የፍቅር ግንኑነት ከተበላሸ በኋላ እንደገና ለመመለስ የመፈለግ ሁኔታ የተለመደ ሲሆን ውሳኔውም ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ውሳኔውን በማመዛዘን ሂደት ላይ ተጽእኖ የሚያመጡ ነገሮችን በሚገባ ማመዛዘን አስፈላጊ ነው፡፡ 1. እንደገና ወደፍቅር ግንኙነቱ ለመመለስ ያለሽ ፈቃደኝነት፡- በሁኔታዎች ተገድደሽ ሳይሆን ግንኙነቱን ከልብሽ የመፈለግሽ ሁኔታ፡፡ 2. ለመለያየት ያበቃችሁ የስህተት አይነት፡- ስህተቶቹ ቀላል አለመግባባቶች የመሆናቸውና በተቃራኒው ለመለወጥ ጊዜ የሚፈጁ ጥልቅ የባህሪ ችግሮች የመሆናቸውን ሁኔታ የመለየቱ ጉዳይ፡፡ 3. ወደቀደመው ግንኙነት ለመመለስ ጥያቄውን ያቀረበው ሰው ማን መሆኑና ለምን መመለስ እንደፈለገ፡- አንቺ ካቀረብሽው ለምን? እሱ ካቀረበውስ ለምን? 4. ስህተታችሁ መታረሙ የመመዘኑ ጉዳይ፡- አንቺም ሆንሽ እሱ ለመለያየት ያበቃችሁን ስህተቶች ማረማችሁ የሚረጋገጥበት መመዘኛዎች የማስቀመጣችሁ ጉዳይለ፡ 5. ለዚህ ሂደት በቂ ጊዜ በመስጠት በሚገባ የመግባባታችሁ ጉዳይ፡፡ በመጀመሪያ እነዚህን ሂደቶች ለጠቅላላ እውቀትና በጉዳዩ ለመብሰል መጠቀምሽን እርግጠኛ ሁኚ፡፡ ከዚም በኋላ ስህተቱ መታረሙን የምታረጋግጪባቸውን ነጥቦች አስቀምጪ፡፡ ያንን ለማስቀመጥ ቀላሉ መንገድ ስህተቱ መሰራቱን ያመለከቱሽን ንግግሮች ወይም ተግባሮ ደግመው አለመሰራታቸውንና ያንን ለማረጋገጥ የሚኖርን ግልጽነት መመልከት ነው፡፡ ፍቅረኞች በእውነተኛ ይቅር መባባል ካደረጉትና ትክክለኛውን ሂደት ከተከተሉ ሁል ጊዜ ግንኙነትን ማደስ የሚመከር ነው፡፡  https://m.youtube.com/user/naeleyob623 @fikermahi
Mostrar todo...
Dr. Eyob Mamo

Share your videos with friends, family, and the world

የፈጣሪ እዝነት ግሩም ነው!! . ይህን ለመፃፍ እጄን ሳነሳ አይኔ በእንባ ተሞላ፣ግን ከተማርኩት እና ብርታት ካገኘሁት የህይወት ክፍል ትንሽ ላካፍላችሁ፣ባለማወቅ ውስጥ ሁነን ከምንጠፋ ትንሽም ቢሆን ድክመታችንን አውቀን ወደ ጥንካሬ እንቀይረው፥ . . የሰው ልግስና ሁኔታን አስልቶ ነውና ይቋረጣል።የፈጣሪ ግሩምነት ግን በሁኔታ፣ ጊዜ እና ጥቅም የተመረኮዘ አይደለም።"በጠየቅነው ልክ የማይመለስ፣ በመለስነው ልክ ያልተጠየቅነው ነገር ብዙ ነው" ስንቱን ሰርቼ፣ ስንቱን አጥፍቼ ይቅር ብሎኝ ይሆን፥ . አንዳንዴ እጄን ዘርግቼ መጠየቅ አፍራለሁ፥ ብዙ የማይገቡኝ ነገሮችን በመስጠት ውስጥ ያኖረኝ ፈጣሪን፡ለድክመቴ ብቻ መሸሸጊያ ሳደርገው፣ ዳግም ቀና ብዬ መራመድ ስጀምር ፡መሸሼን ሳስብ ያመኛል፥ . ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው...ብዙ ሰው መሆን አይጠበቅባችሁም ፈጣሪ ዘንድ ዋጋ እንዲኖራችሁ፣ የፈለጋችሁትን ጠይቃችሁ ለማግኘት፣ ወድቃችሁ መሸሸጊያ ለመፈለግ፣ ከምንም በላይ ደግሞ አጥፍታችሁ ምህረት ለማግኘት፥ . ለመልካም ነገር እንኳን በቂ ላልሆነ እድሜ ክፉ አንስራበት...እስከዛሬ ስንት ቀን ተጨምሮልን ይሆን? ቀን ዕድሜ ነውና ስንኖር የማይገፋን ፈጣሪን ላለማስቆጣት እንኑር!!! @fikermahi
Mostrar todo...
መፍትሄ ለማይሰጥህ ሰው ችግርህን አታጋራ ችግርህን ላገኘኸው ሰው ሁሉ የመንገር ልማድናጥማት  ካለብህ ያንን ጥማት ለጊዜው ከማርካት ውጪ ከሁኔታው ምን ጥቅም እንደምታገኝና እንዲያውም ሊጎዳህ እንደሚችል ላስታውስህ፡፡ ችግርህን ምንም መፍትሄ ለማይሰጥህ ሰው የመናገር ጥማቱ ግን ረክቶ ስለማይረካ እንደገና ችግርህን የምታወራበት መስክ ፍለጋ መዞርህና መጦዝህ አይቀርም፡፡ ችግርህን ባገኘህበት ስፍራ የመናገር ሌላው መዘዝ ለሰሚዎቹ የግል አመለካከት ራስህን የማጋለጥና የሰዎች ፍልስፍና ማራገፊያ የመሆን ችግር ነው - አንዳንዴ ደግሞ የወሬኛ ሰው ሰለባ ትሆናለህ፡፡ ለሰዎች ችግርህን ስትነግር እነዚያ ሰዎች ከሁለቱ አቅም ቢያንስ አንዱ ሊኖራቸው ይገባል፡ 1ኛ) ችግርህን ከሰሙ በኋላ ያንን ችግር የማቃለልና መፍትሄ የመስጠት አቅም፤ 2ኛ) ችግርህን ከሰሙ በኋላ ምንም እንኳን የማቃለል አቅም ባይኖቸውም አንተን ከነሸክምህና ከነሚስጥርህ የመሸከም አቅም ሊኖራቸው ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ሁለት መመዘኛዎች ያለመጠቀም ምርጫ ከተከተልክ በየስፍራው ችግርህን ከማዝረክርክ ልማድህ የሚመጣውንም ሌላ ችግር ለመቀበል ዝግጁ መሆን የግድ ነው፡፡ ትምህርቶቼን በ YouTube የመከታተል ምርጫ አላችሁ:: Subscribe፡- https://m.youtube.com/user/naeleyob623 @fikermahi
Mostrar todo...
Dr. Eyob Mamo

Share your videos with friends, family, and the world

01:28
Video unavailableShow in Telegram
2.31 MB
Photo unavailableShow in Telegram
Mostrar todo...
“ዛሬ እጥበቱ ካለፈኝ እሞታለሁ" ጠና ያሉ ሰውዬ ናቸው - በግምት 54 አመት ገደማ "ልጄ እባክህን እርዳኝ: የኩላሊት እጥበት አለብኝ" አሉኝ ስልክ ላይ ነበርኩኝ: አንገቴን ጎንበስ አድርጌ "ፈጣሪ ይርዳዎች" ብዬ ወደ ስልኬ ተመለስኩኝ "እባክህን ልጄ ዛሬ እጥበቱ ካለፈኝ እሞታለሁ" ሲሉኝ የማወራው ስልኬን ዘጋሁኝ 👇🏾 ሰውዬው በተለያዩ የውጭ ድርጅቶች ውስጥ ለ17 አመታቶች በተለያዩ ሀላፊነቶች ሰርተዋል - ከ7 አመት በፊት ግን የስኳር ህመም ተጠቂ ሆኑ: ኩላሊቶቻቸው ስራ መስራት አቆሙ: የመተንፈሻ ችግር ገጠማቸው ቤታቸውን እስከ መሸጥ ድረስ ገንዘባቸውን አንጠፍጥፈው ተጠቀሙት ኩላሊቶቻቸው በየሳምንቱ ይታጠባሉ በስኳር ህመም የተነሳ የሚበሉት ውስን ምግቦችን ነው የመተንፈሻ መሳርያ ይጠቀማሉ 👇🏾 ኩላሊቶቼ በየሳምንቱ የማይታጠብ: ያገኘሁትን ምግብ ሳላማርጥ የምበላ: አየሩን እንደፈለግኩኝ የምምግ እኔም አማርራሉሁኝ ኩላሊትህ በየሳምንቱ የማይታጠብ: እንደፈለግክ እየበላህ: አየር ያለምንም ከልካይ እየሳብክ ታማርራለህ 👇🏾 በነጻ የተሰጠን ይበልጣል !!❤️🙌🏼 ©Enmare1988 @fikermahi
Mostrar todo...
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.